Wednesday, September 19, 2018

የድኅረ ወሊድ ጭንቀት

የድኅረ ወሊድ ጭንቀት(postnatal depression) እናቶች ከወለዱ በኋላ የሚያጋጥማቸው፣ ከአንድ ወር እስከ አንድ ዓመት ሊዘልቅ የሚችል የጭንቀት ዓይነት ነው፡፡ ልጅ መውለድ የሚያስከትለውን አዲስ ሁኔታ፣ ጠባይ፣ የሰውነትና የስሜት ለውጥ ለማስተናገድ በሚደረገው እናታዊ ትግል ምክንያት በመጀመሪያዎቹ ቀናት የጠባይ ልውጠት(baby blues) ይከሠታል፡፡ ይህ ግን ለሁለትና ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነው፡፡ ነገሩ ከእነዚህ ቀናት በላይ ከዘለቀ ወደ ጭንቀት ያድጋል፡፡ እርሱም የድኅረ ወሊድ ጭንቀት(postnatal depression) ይባላል፡፡ በዚህ ዓይነት ጭንቀት ውስጥ የሚገኙ እናቶች ‹ሙዳቸው› ይጠፋል፤ የተሸናፊነት ስሜት ይሰማቸዋል፤ ተስፋ ቢስነት ይነግሥባቸዋል፤ ስለ ተወለደው ሕጻን አብዝተው ይጨነቃሉ፤ አንዳች የሆነ ነገር ልጃቸውን የሚነጥቃቸውና የሚገድልባቸው ወይም የሚያሳምምባቸው ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ፈልገው የሚያመጡት ጠባይ ሳይሆን ወሊድ የሚያመጣባቸው ክስተት ነው፡፡

የድኅረ ወሊድ ጭንቀት ቁጣን ያስከትላል፣ ያነጫንጫቸዋል፣ ተናጋሪ አንዳንዴም ጯሂ ያደርጋቸዋል፡፡ እጅግ የሚገርመው ደግሞ የሚቆጡትም፣ የሚነጫነጩትም፣ የሚናገሩትም፣ የሚጮኹትም በሚወዱትና በሚቀርባቸው ሰው ላይ ነው፡፡ ይህም  መውለድ ያመጣው የጠባይ ለውጥ እንጂ ውሳጣዊ የልቡና ለውጥ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ የሚነጫነጩበትን፣ የሚቆጡበትንና የሚጮኹበትን ብቻ ለተመለከተ ሰው ትዳሩ የፈረሰ፣ ቤተሰቡ የታመሰ ሊመስለው ይችላል፡፡ ግን በውስጣቸው ፍቅር አለ፡፡ ለዚህም ነው በሚቀርቡትና በሚወዱት ሰው ላይ ብቻ የሚያደርጉት፡፡

በዚህ የድኅረ ወሊድ ጭንቀት ውስጥ ያሉ እናቶች ከምንም ጊዜ በላይ ክብካቤ፣ ፍቅርና እገዛን ይፈልጋሉ፡፡ ከምንም ነገር በላይ የሚረዳቸው፣ የሚገነዘባቸው ሰው ይሻሉ፡፡ ባሎቻቸው፣ የቅርብ ቤተሰቦቻቸውና ጠያቂዎቻቸው ሳይረዷቸው ከቀሩ ጭንታቸው ይበልጥ ይጨምራል፡፡ ይህ ችግር የቤተሰባቸውን መረዳትና እገዛ ካገኘ በቶሎ የሚጠፋ መሆኑን የሚያውቁ ብልሆች ጊዜውን በትዕግሥት፣ በአርምሞ፣ በመቻልና በማሳለፍ ይሻገሩታል፡፡ የማይረዱ ቤተሰቦች ግን መልሰው ይጮኹባቸዋል፤ ይቆጧቸዋል፤ ያኮርፏቸዋል፤ ይርቋቸዋል፤ ከዚህም አልፎ ይፈርዱባቸዋል፡፡ በተለይም ወንዶች በዚህ ይታማሉ፡፡   

ኢትዮጵያ ለውጥንና ተስፋን ወልዳ አሁን የድኅረ ወሊድ ጭንቀት ላይ ናት፡፡ ስለዚህም በሕዝቡ ላይ ንጭንጭ፣ ተሥፋ መቁረጥ፣ ስሜታዊነትና ቁጣ ይታያል፡፡ ይህንን የሚገልጠው ደግሞ በሚያደንቀው፣ በሚወደውና በሚያከብረው ላይ ነው፡፡ ይህ ግን የሚያልፍ ጠባይ ነው፡፡ ልጁ እያደገ፣ እናቲቱም እየበረታች ስትሄድ ጭንቀቷ ወደ ደስታ፣ ንጭንጯም ወደ ሳቅና ጨዋታ ይቀየራል፡፡ ነገር ግን ይህን ወቅት በሚገባ የሚረዳ የቅርብ ቤተሰብ ያስፈልጋታል፡፡ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ የሕዝብ መሪዎች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ሹማምንትና የሐሳብ መሪዎች ይህንን የድኅረ ወሊድ ጭንቀት ጠባይ መረዳት፣ ለአንዲት ወላድ እናት ሊደረግ የሚገባውን ክብካቤ ማድረግ፣ በወሊድ ምክንያት የሚከሠቱ የጠባይ ለውጦችን ዐውቆ የተጠናና ተገቢ የሆነ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋቸዋል፡፡  

ሁሉም ተናዳጅ፣ ሁሉም፣ ተሥፋ ቆራጭ፣ ሁሉም ጯሂ፣ ሁሉም ተነጫናጭ፣ ሁሉም አፉ እንዳመጣለት ወርዋሪ፣ ሁሉም ልቡ ያጎሸውን ሁሉ ተናጋሪ ከሆነ የእናቲቱ ጭንቀት እየጨመረ፣ ጤንነቷ እየተቃወሰ፣ የልጁ ጤንነት እየተበላሸ፣ የቤተሰቡ ሰላም እየተናጋ፣ በመጨረሻም ለደስታና ለእልልታ የተወለደው ልጅ ለመከራና ለጭንቀት ይሆናል፡፡

እንረጋጋ፣ እናረጋጋ፤ ሀገር የድኅረ ወሊድ ጭንቀት(postnatal depression) ላይ ናት፡፡  

16 comments:

 1. ግሩም ምልከታ ነው፣ መምህር! ለወላዷ የቅርብ ሰዎች ለእኛም ማስተዋልና ትዕግሥት ይኖረን ዘንድ ይገባናል፡፡ እኛ ካልተረዳናትና ካላገዝናት የተወለደው ልጅ መታመም ወይም መሞት ብቻ ሳይሆን እናትዮዋም ወይ የዕድሜ ልክ ሕመም ወይ ደግሞ ያልታሰበ ሞት ሊያጋጥማት ይችላል፡፡ ልጁ በዚህ ሁኔታ ከሞተባት ደግሞ እርሷ ብትተርፍ እንኳ ወደፊትም አርግዛ የመውለድ ተስፋዋ በስጋት የተሞላ መሆኑ አይቀርም፡፡ እስኪ ለሁሉም ደግ ደጉን ያስመልክተን፤ አሜን!

  ReplyDelete
 2. Yenegestat Nigus kidus egziabher endih nefisn yemiyalemelm Yehiwot kal yasemah. Wud Dani hoy lante yalegnin fikir ena kibir min aynet kalat nachew yemigeltsut? LeAlem hizboch Yemibeka ewketina tibeb ante lay yaleke yimeslegnal. I wish all Ethiopians read this message!!! I wish dear Dr. Abiy read this b/c esu wedefit sihed egna degmo singotitew sew slehone yichenekal ena yihe dink message yaberetawal. benegerachin lay dani anten ke Dr. Abiy gon Mayet lenga Tesfana Selam new, besu wust anten anayihalen. Dingil Mariam kekifu hulu titebikih!!! kezih belay bil des yilegn neber kalatoch aterugn enji!

  ReplyDelete
 3. I think it does not give sense and not reflect the actual condition and situation well.

  ReplyDelete
 4. ዳኒ በጣም ትክክል ነዉ

  ReplyDelete
 5. እንደ ቃልህ ይደረግልን!

  ReplyDelete
 6. It is a wonderful metaphorical analysis. Thees things happened because we are in the era of freedom that we haven't dream to happen.
  Thanks Daniel.

  ReplyDelete
 7. የሰው ጥንካሬ የሚታየው በችግርና በመከራ ጊዜ ነው፡፡ ውሾቹም ይጮሃሉ ግመሎቹ መሄዳቸውን አያቆሙም፡፡ fantastic idea for those who read and have potential of understanding no words for you thanks.

  ReplyDelete
 8. Daniel you have a very good point, I wish every media owner and some so called " activist " read your blog, I believe, racism is widely spreading in our country. Even if racism is not as deep as it is in western countries, we all know that we Ethiopian have practiced racial politics for the last decades. And we know it is divisive as each party only talks on behalf of the racial group it represents. I believe, when all races are in a single party, no one person will try to be the champion of the party.... It is easy to be a a party hero, but it is difficult to be an Ethiopia hero.... our country is facing mainly economic problems now and it is important that our government and political parties come up with a Ethiopia agenda on how to unite the people and face these challenges rather than their political party agenda. On his speech Dr Abiy stated that, the most important asset for our country is not its natural resources but it’s our human resources. It is especially true for our country. I suggest we the people of Ethiopian need to stand and say NO to our difference , so we can easily pass this " postnatal depression." Race, religion, whether you were born north or south of that artificial line called “a border” our media spend an enormous amount of their time and resources on talking our differences rather than celebrating our similarities and bringing us together.

  Anteneh.

  ReplyDelete
 9. እንረጋጋ፣ እናረጋጋ፤ ሀገር የድኅረ ወሊድ ጭንቀት(postnatal depression) ላይ ናት፡፡

  ReplyDelete
 10. በረከት ስቃደስላሴ እባላለሁ። ላንተ ትልቅ አክብሮት አለኝ። ጽሁፎችህን ለብዙ አመትት ስከታተል እና ሳነብ ነበር። ሃሳቦችህንም በጣም እወድችዋለሁ። ነገር ግን ዛሬ አንድ አዲስ ነገር ልነርህ ስለምፈልግ ከታች ያለውን ኢሜል ተጠቅመህ መልእክት ላክልኝ።
  bekifikade@gmail.com
  አመሰግናለሁ።
  አክባሪህ በረከት ፍቃደስሴ

  ReplyDelete
 11. ወዳጄ ዲያቆን ዻነኤል :
  ይሄንን post partum depression የሚለውን ፅሁፍ ሳነበው በ2011 GC " ልርሳህ ብልስ ብርዱ እንዴት ያስረሳኛል" በሚል ርእስ በሁለት ተከታታይ ክፍሎች የፃፍከውን አስታወሰኝ። አንድ ቅን የነበረ የዋህ ሰው ምሽቱ በወለደች በ3 ወርዋ ጠባይዋ ተበላሸ ብሎ ጥሎዋት ሄዶዋል እዚ እኔ ያለሁበት አገር ። ምክንያቱ ደሞ ይሄን ፅሁፍ እንደ መይሃፍ ቅዱስ ዋቢ አርጎ ነው።መግባባት ያልቻለ መፋታት ይችላል ብሎ ይህን ፅሁፍ ዋቢ አርጎ። ምነው ይሄን ቀድመህ ፅፈሀው ቢሆን ኑሮ። ልጅቱ አሁን ድረስ ጤናም አትመስለኝ። ቤተክርስቲያንና የቤተክርስትያን ሰው ጠልታ ና ተጠይፋ ትኖራለች ይሀው። እንዳውም ባለፈው ጴንጤ ሆነች ሲሉ ነበር። ለመንጋው እያሰቡ መፃፍ ይሻላል። ሌላም ትዳሩ እስካሁን ፈተና ዉስጥ ያለ ወዳጅ አለኝ። ምሽቱ በየግዜው እየጣለችው እየሄደች። እርስዋን በቄስ በየግዜው ማስለመን ተጨማሪ ሲራው ሆነዋል። አሁን አሁን አሁንማ ልክ እዛ ፅሁፍ ላይ እንዳልከው "በቄስ ተሞከረ አልሆነም" እያለች ዙሩን አክራበታለች። እርሱ ደሞ ዲያቆን ሲለሆነና ልጆች ስላሉት ኑሮው ሁሌ በጭንቅ ነው። እንደው አንዳንዴ አግኝቼህ ይሄን ፅሁፍ ሚያስተባብል ነገር እንድትፅፍ እግርህ ላይ ወድቄ ብለምንህ ብዬ እመኛለሁ። ብዙ የዋሃን ነብሳት እንዳሉ ማሰብ ያስፈልጋል። ክፍዎችም አንዳንዴ ለክፋታቸውና ለሴሰኝነታቸው ቃለ እግዚኣብሄርን ማጣቀስ ይፈልጋሉ። እና ለመንጋው መጠንቀቅ ይገባል ወንድሜ

  ReplyDelete
 12. Good point...Kalehiwot yasemalen!

  ReplyDelete