Wednesday, September 19, 2018
Wednesday, September 12, 2018
‹ግቡ የአጥቂው፣ ድሉ የቡድኑ ነው›
ሰውዬው አንበሳ ሊያድን ጫካ ይገባል፡፡
እየተሽሎከለከ ዛፍ ለዛፍ ሲያነጣጥር፣ የአንበሳውንም ዱካ እያዳመጠ ሲከተል፣ ቆየና አንድ የአንበሳ ደቦል በቀስቱ አነጣጥሮ ጣለ፡፡
ገና ደስታውን ሳያጣጥም የሰውነት ክፍሎቹ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፡፡ እጁ አንበሳውን አነጣጥሮ የጣለው እርሱ መሆኑን በማስረዳት የተለየ
ክብር ሊሰጠው እንደሚገባ ተናገረ፡፡ ይህንን የሰማው እግሩም ‹መጀመሪያውኑ ማን ተሸክሞህ መጥተህ ነው ወጋሁት፣ መታሁት የምትለው›
ብሎ ክብሩ የእርሱ መሆኑን ገለጠ፡፡ ነገሩን የታዘበው ዓይንም ‹በምን ዓይተህ ነው ያነጣጠርከው› አለና ክብሩ የእርሱ መሆኑን በኩራት
ደሰኮረ፡፡ ጆሮም የአንበሳውን ዱካ እኔ በጽሞና ባልከተል የት ታገኙት ነበር? ሲል ቀዳሚው ባለ ድል እርሱ መሆኑን ደነፋ፡፡ አፍና
ሆድም ‹ባልተበላ ምግብ በባዶ ሆድ እንኳን ማደን መታደን አይቻልም› ሲሉ ተከራከሩ፡፡
እንዲህ የሰውነት ክፍሎች ሁሉ እየተነሡ
‹ተኳሹ፣ መራዡ፣ አነጣጣሪው፣ እኔ ነኝ› እያሉ ሲከራከሩ ሰውዬው ወደ ግዳዩ ሳይሄድ ዘገየ፡፡ በዚህ መካከል ዓይን ቀና ቢል አንበሳው
ሲሞት ያሰማውን ድምጽ የሰሙ ሌሎች አንበሶች ዙሪያቸውን ከበዋቸዋል፡፡ ዓይን በድንጋጤ ሲፈጥ ያስተዋለው እጅም ለሌሎች አካላት መከባባቸውን
ጠቆመ፡፡ ይህን የተመለከተው እግር እሮጣለሁ ብሎ ሲያስብ እንኳን መሮጫ መሹለኪያ ቀዳዳ አላገኘም፡፡ ቅድም እኔ ነኝ እኔ ነኝ እሉ
ሲፎክሩ የነበሩት ሁሉ ለየብቻ ሮጠው ማምለጥ አልተቻላቸውም፡፡ አንበሶቹ ግን የግዳይ ቀለበታቸውን እያጠበቡ እያጠበቡ ተጠጉ፡፡ ፍጻሜውም
መበላት ሆነ፡፡
Thursday, September 6, 2018
የማይሰለቹት አባት፤ ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ
ንግግራቸው ምንጊዜም ፈዋሽ ነው፡፡
የትኛውም ቦታ ላይ ሆነው ቢሰሙት ለራስ የተላከ ደብዳቤ ይመስላል፡፡ ሃይማኖታቸውን ከንግግራቸው ማወቅ ከባድ ነው፡፡በቅርብ ለሚያውቋቸው
ወይም ልብሳቸውን ለተመለከተ ካልሆነ በቀር፡፡ የሚናገሩት ሁሉንም እምነት የሚመለከት ነውና፡፡ የሁለቱን ሲኖዶሶች ዕርቅ ምክንያት
በማድረግ በተዘጋጀው የሚሊኒየም አዳራሽ ጉባኤ ላይ ያስተላለፉትን መልእክት ሊቃነ ጳጳሳቱ ከልባቸው ካዳመጡት ‹ሲታረቁ ከሆድ፣ ሲታጠቡ
ከክንድ› የሚያደርግ ነው፡፡
እሑድ ዕለት የበጎ ሰው ሽልማት
ፕሮግራም ላይ ለክቡር አቶ ለማ መገርሳ ሽልማቱን ያበረከቱት እርሳቸው ነበሩ፡፡ ቢሮክራሲ የሚባል ነገር የማያውቃቸው፤ ነገርን በጉዳዩ
ልክ ብቻ የሚመዝኑ¶ የተጠሩበትን ጉዳይ እንጂ የጠራቸውን ሰው ማንነት ከቁም ነገር የማይቆጥሩ፣ የአለቃ ሳይሆን የአባት ጠባይ ያላቸው
ናቸው፡- ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ፡፡
Monday, September 3, 2018
Subscribe to:
Posts (Atom)