Friday, August 17, 2018

የ 2010 ዓ.ም. የበጎ ሰው ሽልማት ዕጩዎች6ኛው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ነሐሴ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ይካኼዳል፡፡ በዚህ ዓመት ለሚካኼደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ዕጩዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1.በመምህርነት ዘርፍ
1.  መምህር ሥዩም ቦጋለ( በአዊ ዞን ታላላቅ ሥራዎችን የሠሩ መምህር)
2.  መምህር ስመኘው መብራቱ( በደቡብ ጎንደር ታች ጋይንት ልዩ ልዩ ሥራዎችን የሠሩ መምህር)
3.  መምህር ስለሺ ካሣዬ(በድሬዳዋና በሐረር ከተማ ታላላቅ ሥራዎችን የሠሩ መምህር)

2) ለኢትዮጵያ በጎ የሠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች
1.  ኢያን ካምፕቤል (Ian Campbell)(በጣልያን ወረራ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸሙ ግፎችን በማጥናትና በማሳተም ይታወቃሉ)
2.  ሬልዶፍ ኬ. ሞልቬር (Reidulf K. Molvaer)(የ Black Lions - መጽሐፍ ደራሲ)
3.  ሐጋይ ኡልሪክ (Hagai Ulrich)(ስለኢትዮጵያና መካከለኛው ምሥራቅ ግንኙነት ብዙ መጻሕፍት የጻፉ)

3) መንግሥታዊ የሥራ ሐላፊነትን በብቃት መወጣት
1.  ዶ/ር አበራ ዴሬሳ (የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩ)
2.  ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም
3.  ወ/ሮ ሙሉ ወርቅ ገብረ ሕይወት(የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሥራ አስኪያጅ የነበሩ)

4) በበጎ አድራጎት ዘርፍ
1. አቶ መኮንን ሙላት
       (መስማት የተሣናቸውን ከሠላሳ ዓመታት በላይ በመርዳት የሚታወቁ)
2. ሄርሜላ ወንድሙ
       (የጠብታ ውኃ /Drop of Water/ ድርጅት መሥራች)
3. ሲስተር (ሎሬት) ጥበበ ማኮ
       (የሕይወት የተቀናጀ የልማት ድርጅት /HIDO/ መሥራችና ዋና ሥራ   
       አስፈጻሚ)

5) በቅርስ እና ባህል ዘርፍ
1. የአዊ የፈረስ ማኅበር
       (ከሰባ ዓመታት በላይ የቆየ ባህላዊ የፈረስ ማኅበር)
2. አባ ገብረ መስቀል ተሰማ
       (ላስታ ውስጥ ውቅር አብያተ ክርስቲያትን የሠሩ)
     3.መላኩ በላይ (ፈንድቃ)
       (የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃና የሙዚቃ መሣሪያዎችን በማጥናትና
       በማሰባሰብ የታወቀ ባለሞያ)
6) በሳይንስ ዘርፍ
1. ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ
2. ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ
3.ዶክተር ሞሚና አሕመድ (በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያካኼዱ ሐኪም)

7) ንግድ እና ሥራ ፈጠራ
    1. ኃይሌ ገብረ ሥላሴ
    2. አቶ ወልደ ሔር ይዘንጋው
      (የግዮን ኢንዱስትሪያል ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ)
   3. አቶ ተቻለ ኃይሌ
      (የተቻለ ጋራዥ ወይም የተቻለ ብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ ድርጅት
      ባለቤት)
8) ሚዲያና ጋዜጠኛነት
    1. ጸጋዬ ታደሰ (ጸጋዬ ሮይተርስ)
    2. ጥበቡ በለጠ
    3. ነቢዩ ሲራክ
9) ኪነ ጥበብ (ዜማ)
    1. ቴዎድሮስ ካሣሁን
    2. አበበ ብርሃኔ
    3. አየለ ማሞ
           

7 comments:

 1. 1. ስለሁሉም ተሳታፊዎች ለእጩነት ያበቋቸውን ስራዎች አጠር ብሎ ቢቀመጥ ዋናው እነሱን አርአያ አድርጎ ሚነሳ ትውልድ መፍጠር ስለሆነ ስማቸው ብቻ የተቀመጡትን ለማለት ነው
  2. የዘንድሮው እንደባለፈው ጥቆማ ያላችሁ ጠቁሙ የሚል ዐይነት መልእክት አልሰማሁም ከኔ ከሆነ ይቅርታ ጠይቃለሁ ተዘሎ ከሆነ ደግሞ ቢታሰብበት
  3. ሽልማቱ ዓመታዊ ነውና መዚህ ዓመት የተሰሩ አሸላ ተግባራት ያሏቸው ላ ቢያመዝን
  4. መርሃግብሩ ላይ ስለመሳተፍ ምን አልተገለጸም ቢቻል ቢጠቆም

  ReplyDelete
 2. How can I register to participate on the event?

  ReplyDelete
 3. Gigiyen adera bemiketilewu kesikahunochu keteshelemutim echu kehonutim belay nech

  ReplyDelete
 4. Ayte Daniel Kibrom...... woyane mehonkin emayakew erasih bicha neh
  hahah....bante beit hulun, dofterun frofesseroon mehaymun hulu ataleh motehal.... Tifir neqay bego adragi shelamiwoch....dinqem bego adragi...aye jibo...yeqen jibo

  ReplyDelete
 5. ዳኒ በሃገራችን ማኅበራዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ውስጥ የምትሰራቸው ሥራዎች ሁሉ ለሁላችንም በተለይ ለኛ ለወጣቶች ዓርዓያ ናቸው፡፡ የዕውቀትና የጥበብ ባለቤት፣ የጸጋም ሁሉ ምንጭ እግዚአብሔር ዕደሜና ጤና ሰጥቶ ከዚህ በላይ እንድትሰራ ብዙዎችንም ልጆች እንድታፈራ ይርዳህ፡፡

  ReplyDelete
 6. how should we give nominees for the next year 'yebego sew shilmat'? is there any requirement and any platform for it?

  ReplyDelete
 7. ዲያቆን ዳንኤል ጆሲን ለምንድነው ብጎ ሰው ተሸላሚ ያልሆነው

  ReplyDelete