አንድን ሕዝብ ወይም ማኅበረሰብ
በተመለከተ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚደረጉ አሉታዊ የገጽታ ግንባታዎች ውጤታቸው ከሚታሰበውም የከፋ ነው፡፡ በዓለም ላይ አደጋ
ላይ የወደቁ ማኅበረሰቦችን ታሪክ ስንመለከት ከሁለት ወገን የመጡ አካላት የቆሰቆሱት እሳት ያስከተለውን ረመጥ እናይባቸዋለን፡፡
አንደኛው እነርሱን ከሚወደው ወገን ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከሚጠላቸው ወገን ነው፡፡
የተጠቂው ወገን ነኝ የሚለው አካል
ያልተሰጠውን ውክልና እየወሰደ የሚፈጽማቸው ተግባራትና የሚያቀርባቸው ሐሳቦች በተቃራኒ ሆነው ነገሩን ለሚቆሰቁሱት ቢላዋ ያቀብላል፡፡
በጣት የሚቆጠሩ ልዩ ተጠቃሚዎች ሚሊዮኖችን ወክለው ለመታየት ይጥራሉ፡፡ እፍኝ የማይሞሉ አቀንቃኞች የማኅበረሰቡ አፈ ጉባኤ አድርገው
ራሳቸውን እየሾሙ የሚናገሯቸው ንግግሮች የዚያ ማኅበረሰብ አቋም መስለው እንዲታዩ ይተጋሉ፡፡
በአንድ ማኅበረሰብ ስም ጥቅም የሚያገኙ
አካላት በየዘመናቱ ይፈጠራሉ፡፡ በክርስትናና በእስልምና ስም በተፈጸሙ ወረራዎች፣ ዝርፊያዎች፣ ቅኝ ግዛቶች፣ ጦርነቶችና ጭቆናዎች
ተጠቃሚዎቹ አማንያኑ አይደሉም፡፡ ተጠቃሚዎቹ በእምነቱና በአማንያኑ ስም የሚነግዱት አካላት ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት እምነቱንም
ሆነ አማንያኑን የሚፈልጓቸው ለሁለት ነገር ነው፡፡ ለምክንያትነትና ለከለላነት፡፡ መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንደሚባለው ግለሰባዊ
ስግብግብነትና የሥልጣን ጥመኝነት ላስከተለው ክፉ ተግባር የተቀደሰው ሃይማኖት ምክንያት እንዲሆን ይፈለጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ
ዘራፊዎቹና ገዳዮቹ እንዳይነኩ እምነቱን ለሽፋንነት ይፈልጉታል፡፡ እነርሱን መንካት እምነቱን መንካት ተደርጎ እንዲወሰድ፡፡ በዘር
ከለላ ተከልለው የሚበዘብዙና የሚጨቁኑ ሰዎችም ይሄው ነው መንገዳቸው፡፡
በአንድ ማኅበረሰብ ስም የሚነግዱት
አካላት በሌላው ማኅበረሰብ ዘንድ የሚፈጥሩት የተበላሸ ሥዕልም አለ፡፡ የእነርሱ መጠቀምና ክብር፣ ሥልጣን ማግኘትና መግዛት የማኅበረሰቡ
ተደርጎ እንዲወሰድ ያደርጉታል፡፡ በተለይ ደግሞ ግልጽነትና ጠያቂነት ባልዳበረበት ማኅበረሰብ ውስጥ እገሌ እና እገሊት፣ ይሄና ያ፣
እንዲህና እንዲያ ሁሉንም የሚገልጡ ማሳያዎች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ ይህ ደግሞ ለጅምላ ፍረጃ ያጋልጣል፡፡ አበበ ተጠቀመ ማለት አበበ
የተገኘበት ማኅበረሰብም ተጠቀመ ማለት ነው ተብሎ ይወሰዳል፡፡ አበበም እንደዚያ እንዲሆንለት ይፈልጋል፡፡
ከዚህ ባሻገር ደግሞ ዐውቀውና ሳያውቁት ሌላውን ማኅበረሰብ የማጥላላት፣ የማናናቅና
የመፈረጅ ዘመቻ የሚያደርጉም አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ግለሰብን ከማኅበረሰብ መለየት ያቃታቸው ናቸው፡፡ አንድ በሬ ከወጋቸው በሬዎችን
ሁሉ የሚጠሉና ሊያርዱ የሚነሡ ናቸው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ሆኖ ምንጊዜም የሚጠቀሰው በአይሁድ ማኅበረሰብ ላይ የደረሰው ነው፡፡ ምንም
እንኳን ክርስቶስን የተቃወሙት፣ ያስፈረዱበትና የሰቀሉት ከአይሁድ ወገን የተገኙ ባለ ሥልጣናትና ጥቅመኞች ቢሆኑም፣ የመጀመሪያዎቹ
ሐዋርያትና ክርስቲያኖችም ከአይሁድ ወገን የተገኙ ነበሩ፡፡ በተደጋጋሚ በየዘመናቱ የተገለጠው ግን ስለ ሰቃዮቹ አይሁድ እንጂ ስለ
ክርስቲያኖቹ አይሁድ አልነበረም፡፡ በጅምላ ‹አይሁድ ይህንን አደረጉ› እየተባለ የተነገረው ነገር ከ40 ሚሊዮን በላይ አይሁድ ያለቁበትን
ጥፋት በየዘመናቱ አምጥቷል፡፡
በዘመነ ክርስቶስ ከአንድ ሚሊዮን
በላይ አይሁድ እንደነበሩ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን ይናገራል፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን በክርስቶስ መከራና ሞት የተሳተፉት ከአምስት ሺ
አይበልጡም፡፡ መከራው ግን ለሁሉም ተረፈ፡፡
በየማኅበራዊ ሚዲያው፣ በየቀልዶቻችንና
በየዘፈኖቻችን የምናስተላልፈው አንድን ወገን የማስጠላትና የማክፋፋት ዘመቻ ማጣፊያው የሚያጥር ነው፡፡ በልጆቻችን አእምሮ ውስጥ
የሚቀመጡት እነርሱ ናቸው፡፡ ልጆቻችን ስለዚያኛው ማኅበረሰብ የሚኖራቸውን አመለካከት የሚቀርጹት በነዚህ ጽሑፎች፣ ቀልዶችና ዘፈኖች
ነው፡፡ በሀገራችን አንድን ማኅበረሰብ የሚያጥላሉ ዘፈኖች ቦታ እንዲያገኙ ተደርገዋል፡፡፡ አንድን ማኅበረሰብ ለይተው የሚያጠቁ የፕሮፓጋንዳ
ቃላት ተፈጥረዋል፤ አንድን ማኅበረሰብ ለይተው የሚያሸማቅቁ መግለጫዎች በባለሥልጣናት ደረጃ ተሰጥተዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ከሌሎቹ ጋር
እየተደመሩ የተጠቂነት ስሜት የሚሰማው፣ራሱን ወደመከላከል የሚገባ፣ሕልውናው አደጋ ላይ መድረሱን ያመነ ማኅበረሰብ ፈጥረዋል፡፡ እንዲህ
ያለው ማኅበረሰብ ሲፈጠር ደግሞ ከድልድይ ይልቅ ግንብ እየገነባ ከሌላው ጋር መራራቅንና መከለልን ይመርጣል፡፡
በአውሮፓ ከ16ኛው መክዘ በኋላ
ለተስፋፋው የፀረ ሴማዊነት ስሜት የታላቁ ጸሐፌ ተውኔት የሼክስፒር ‹የቬነሱ ነጋዴ› ቴአትር አስተዋጽዖ ማድረጉ ይነገራል፡፡ የቬነሱ
ነጋዴ ዋና ገጸ ባሕርይ ሻይሎክ የተባለ ገብጋባ ይሁዲ ነው፡፡ ሻይሎክ የዕብራይስጥ ስም አይደለም፡፡ ነገር ግን ‹ሳላን› ከተሰኘውና
የሴም የልጅ ልጅ፣ የዔቦር አባት ከሆነው ሰው ስም የተቀዳ መሆኑ ይታመናል፡፡ የሻይሎክ ገብጋባነትና ጭካኔ ለከት የለውም፡፡ ከእርሱ
ገንዘብ የተበደረው ክርስቲያኑ አንቶኒዮ መክፈል ቢያቅተው መያዣው ከአንቶኒዮ ሰውነት የሚቆረጥ አንድ ሙዳ ሥጋ ነው፡፡ አንቶኒዮ
ብድሩን መክፈል አቃተው፡፡ ሻይሎክም ሙዳ ሥጋውን ከአንቶኒዮ ሰውነት ቆርጦ ለመውሰድ ተነሣ፡፡
ሼክስፒር ይህንን ድራማ የጻፈበት
የኤልሳቤጥ ዘመን(Elizabethan Era – 1558-1605) የሚባለው ጊዜ እንግሊዞች በፀረ ሴማዊነት የተለከፉበት ዘመን ነበር፡፡
ከ1290 ጀምረው ከእንግሊዝ የተባረሩት አይሁድ ወደ እንግሊዝ ለመግባት አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ የድራማው መቼት በሆነው ቬነስ
ደግሞ አይሁድ ይጠላሉ፤ ለጥቃት የሚያጋልጥ የተለየ የመለያ ልብስ እንዲለብሱ ይገደዳሉ፡፡ በሼክስፒር ዘመን የነበሩ ድርሰቶች፣ ቀልዶች፣
ሥዕሎችና ድራማዎች አይሁድን ገብጋቦች፣ ክፉዎችና አጭበርባሪዎች አድርገው የሚስሉ ነበሩ፡፡ የሼክስፒርን ድርሰቶች ያጠኑ ሊቃውንትም
‹የቬነሱ ነጋዴ› ቴአትር ‹የቬነሱ ይሁዲ› እየተባለ ይጠራ እንደነበር ይገልጣሉ፡፡ ይህም ክሪስቶፈር ማርሎዊ ከደረሰው ‹የማልታው
ይሁዲ› ቴአትር ጋር ያመሳስለዋል፡፡ በ‹የማልታው ይሁዲ› ቴአትር ውስጥ የሚገኘው ይሁዲው ባራባስ እንደ ሻይሎክ ክፉ ነው፡፡ የቬነሱ
ነጋዴ የሚያልቀው ሻይሎክ ወደ ክርስትና ሲመለስ ነው፡፡
ይህ በሼክስፒር ድርስት ውስጥ የተሳለው
ይሁዲ ገጸ ባሕርይ አይሁድ ቀድሞ ከተሳሉበት ገጽታ ጋር ተደምሮ በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚታዩበትን መነጽር አበላሸው፡፡ ስለ እነርሱ
ክፉ መናገር፣ መጻፍና መቀለድ የተፈቀደ መሰለ፡፡ ለእነርሱ የሚከራከርም ጠፋ፡፡ በኋላ ዘመን በአይሁድ ላይ የተፈጸሙ ጥፋቶችን ያመጡት
እነዚህን የመሰሉ ድርሰቶች፣ ቀልዶችና ዘፈኖች ነበሩ፡፡
ዛሬም እኛ ኢትዮጵያውያን ከሁለቱም
ወገን ልንርቅ ይገባናል፡፡ የሌላችሁን የማኅበረሰብ ውክልና ለሥልጣናችሁ፣ ጥቅማችሁና ለክብራችሁ ስትሉ የምታቀነቅኑ ተቆጠቡ፡፡ ማንም
አልወከላችሁም፡፡ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤትም ይህንን አያረጋግጥላችሁም፡፡ ሕዝቡ ያላለውን በሕዝብ ስም አትናገሩ፡፡ እናንተ
ስትጠግቡ ሕዝቡ እንደጠገበ አታስመስሉት፤ እናንተ ሲያማችሁም ሕዝቡ እንደታመመ አታስቃስቱት፡፡ እናንተ ስትራቡ ሕዝብ የተራበ አድርጋችሁ
አትሳሉት፤ ዕዳችሁን ብቻችሁን ውሰዱ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ስለ አንድ ሕዝብ
በጅምላ የሚነገሩ የጥላቻ ንግግሮች፣ ቀልዶች፣ ጽሑፎች፣ ዘፈኖች፣ ግለሰቦችን ጠቅመው ሕዝብን ይጎዳሉ፡፡ ይበልጥ ደግሞ በልጆቻችን
አእምሮ ውስጥ ተቀርጸው እንደ ጊዜ ጠባቂ ቦንብ ይቀመጣሉ፡፡ ለሕዝብ ሲባል ግለሰቦችን መተው እንጂ ለግለሰቦች ሲባል ሕዝብን ማጥፋት
ሕጋዊም ሞራላዊም አይደለም፡፡
"ለሕዝብ ሲባል ግለሰቦችን መተው እንጂ ለግለሰቦች ሲባል ሕዝብን ማጥፋት ሕጋዊም ሞራላዊም አይደለም፡፡"
ReplyDeletewell said
ReplyDeleteለሕዝብ ሲባል ግለሰቦችን መተው እንጂ ለግለሰቦች ሲባል ሕዝብን ማጥፋት ሕጋዊም ሞራላዊም አይደለም፡፡
ReplyDeletelhizeb sebale glasabochen mtew eng lglasabch sebale hezben matfat hegawe maralem aydela!!!
Deleteጤና ይስጥልኝ ዲያቆን ዳንኤል ስለ በጎ ሰዉ ሽልማት አንዳንድ እየወጡ ስላሉ መረጃዎች ለመጠየቅ ነበረ፡፡ በተለይ ከጋዜጠኝነት ምርጫ ጋር በቃሉ አላምረዉ የተባለ ይዘጋል የተባለዉ የENN ጋዜጠኛ ተመርጫለሁ እያለ እያስወራ ነዉ በፌስቡክ ገጹም ላንተ ምስጋና አቅርቧልና እዉነት የሽልማት ድርጅቱ በዚህ ደረጃ ወርዶ ገና ሁለትና ሶስት አመት እንኳን ያላገለገሉ ምንም አይነት ማህበረሰባዊ ጠቀሜታ ያላበረከቱ በተለይም በአዕምሮም በልምድም ያልበሰሉ እንደበቃሉ አይነቶችን እንጭጭና ግልብ ግለሰቦችን ወደ መምረጥ ደረጃ ወርዶ ከሆነ ጥያቄ ያስነሳልና ግልጽ ብታደርገዉ፡፡
ReplyDeleteastesasebh betam nw emimechegn. ketlbet berta.
ReplyDeleteGood writing.
ReplyDeleteእንደዚህ አይነት ሃሳብ ያለው ሠው ትልቅ የሞራል እና ስነምግባር የጎደለው አካል ነው ዳግም ሊደግም አይገባም፡፡
ReplyDeletewhat nice perspective Dear and Beloved this the only way for us to overcome current crisis may God Bless you!!!!
ReplyDeleteእውነት ብለሃል መምህር፤ ግለሰብ እና ህዝብን መለየት ተገቢ ነው!!!
ReplyDelete"እናንተ ስትጠግቡ ሕዝቡ እንደጠገበ አታስመስሉት፤ እናንተ ሲያማችሁም ሕዝቡ እንደታመመ አታስቃስቱት፡፡ እናንተ ስትራቡ ሕዝብ የተራበ አድርጋችሁ አትሳሉት፤ ዕዳችሁን ብቻችሁን ውሰዱ" Daniel Kibret . Thank you very much for your incredible Post .I hope you Impacted millions of people in Ethiopia.
ReplyDeleteIf I were an able man to express my feeling I would have wrote it like this!
ReplyDeleteMany thanks Dn Daniel
የተለያዩ የማናዉቃቸዉ የማያዉቁን ሰዎችን ፤ የእግር ኳስ ክለቦችን እየደገፍን በሌሎች መሸነፍና ማዘን እና መበሳጨት እየተደሰትን እየተዝናናን እየተማርን አደግን የተማርነዉን በምናዉቃቸዉ ሰዎች ላይ ብንተገብር ምኑ ላይ ነዉ ጥፋታችን? ያልለመድነዉን በአንዴ ተዉ የምትለን?
ReplyDeleteየተለያዩ የማናዉቃቸዉ የማያዉቁን ሰዎችን ፤ የእግር ኳስ ክለቦችን እየደገፍን በሌሎች መሸነፍና ማዘን እና መበሳጨት እየተደሰትን እየተዝናናን እየተማርን አደግን የተማርነዉን በምናዉቃቸዉ ሰዎች ላይ ብንተገብር ምኑ ላይ ነዉ ጥፋታችን? ያልለመድነዉን በአንዴ ተዉ የምትለን?
ReplyDeleteፈጣሪ ማስተዋልን ይስጠን!! ሕዝብ በሕዝብ ላይ ጥላቻ እንዲያሳድር የሚሰሩ ማስተዋል የተሳናቸውን ወደ ልቦናቸው ይመልስልን!! ሕዝብ ታላቅ ሕዝብ እውነት ፈራጅ፣ ሕዝብ ተጋሽ ነው!! ሁላችንም በመጥፎ ሥራችን የወጣንበትን ማኅበረሰብ እናሰድባለን!! እውነቱ ግን በፅሁፍሕ የቀረበው ነው!! የራሱን አካባቢ፣ ሕዝብ እና ብሔር ሊያስመገን የሚችል መልካም ሥራ ሲሰራ ማመስገን ይገባል፡፡ ነገር ግን በግለሰብ ጥፋት ሕዝብ አጥፊ መደረጉ ተገቢነት የለውም!! ኢትዮጵያውያን በአንድ ቤታችን በፍቅር እንጂ እርስ በርስ በመጠላላት እንዳልመጣን ይህ ዘመን ይናገረዋል፡፡
ReplyDeleteሰሚ፡እንጂ፡ምን፡ሰማሁ፡ምንድን፡ነው፡የተረዳሁት፡ ወይም፡የተማርኩት፡ብሎ፡የሚያገናዝብ፡ኢትዮጽያዊ፡ቢፈጠር፡ኖሮ፡ይሄ፡የዳኔሌ፡መልእክት፡ብቻውን፡ኢትዮጽያን፡እንደሙሴ፡ከዚህ፡ማጥ፡ያሻግናራት፡ነበር።
ReplyDeleteOhhh this is great. ሰው ማለት ሰው የጠፋለት ሰው የሚሆን ነው፡፡
ReplyDeleteሰው ሰው ነኝ ብሎ ካመነ ደግሞ
ለሱ እንዲሆንለት የሚፈልገውን ለሌሎችም ያድርግ
በሱ ላይ እንዲደረግበት የማይፈልገዉን በሌሎች ላይ አያድርግ
i need the PDF of your posts how can i gate ?
ReplyDeleteአእምሮ ውስጥ ተቀርጸው እንደ ጊዜ ጠባቂ ቦንብ ይቀመጣሉ
ReplyDeleteስለ አንድ ሕዝብ በጅምላ የሚነገሩ የጥላቻ ንግግሮች፣ ቀልዶች፣ ጽሑፎች፣ ዘፈኖች፣ ግለሰቦችን ጠቅመው ሕዝብን ይጎዳሉ፡፡ ይበልጥ ደግሞ በልጆቻችን አእምሮ ውስጥ ተቀርጸው እንደ ጊዜ ጠባቂ ቦንብ ይቀመጣሉ፡፡ ለሕዝብ ሲባል ግለሰቦችን መተው እንጂ ለግለሰቦች ሲባል ሕዝብን ማጥፋት ሕጋዊም ሞራላዊም አይደለም፡፡
ReplyDeleteREALLY THISE
ReplyDeleteእናንተ ስትጠግቡ ሕዝቡ እንደጠገበ አታስመስሉት፤ እናንተ ሲያማችሁም ሕዝቡ እንደታመመ አታስቃስቱት፡፡ እናንተ ስትራቡ ሕዝብ የተራበ አድርጋችሁ አትሳሉት፤ ዕዳችሁን ብቻችሁን ውሰዱ፡፡
ReplyDeletethank you D. Daniel. the larger population in such contexts, which are used to camouflage the sinister interests of the few, is sadly doubly disadvantaged. first, they did not benefit from a system as much as they are portrayed and secondly, other people (ethnic groups) have developed hatred for them. it is such a bad situation to be in and one has to empathize to really understand their conditions. the feeling of constant fear and vulnerability is unavoidable. and who wants to live like that???
ReplyDeleteለሕዝብ ሲባል ግለሰቦችን መተው እንጂ ለግለሰቦች ሲባል ሕዝብን ማጥፋት ሕጋዊም ሞራላዊም አይደለም፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስህ ዲያቆን ዳንኤል፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስህ ዲያቆን ዳንኤል፡፡
ReplyDeleteIt's helpful.
ReplyDeleteI thank you my brother
ReplyDeleteዳቆን ዳንኤል ክብረት እግዛብሔር ይጠብቅ ሁሌም ነገሮችን አጤነህ በሚገባን መንገድ ነው የምታስተምረን፡፡
ReplyDelete‹‹ስለ አንድ ሕዝብ በጅምላ የሚነገሩ የጥላቻ ንግግሮች፣ ቀልዶች፣ ጽሑፎች፣ ዘፈኖች፣ ግለሰቦችን ጠቅመው ሕዝብን ይጎዳሉ፡፡ ይበልጥ ደግሞ በልጆቻችን አእምሮ ውስጥ ተቀርጸው እንደ ጊዜ ጠባቂ ቦንብ ይቀመጣሉ፡፡ ለሕዝብ ሲባል ግለሰቦችን መተው እንጂ ለግለሰቦች ሲባል ሕዝብን ማጥፋት ሕጋዊም ሞራላዊም አይደለም፡፡ ››
ወ/ሮ ተዘራ ደሳለኝ
ዳቆን ዳንኤል ክብረት እግዛብሔር ይጠብቅ ሁሌም ነገሮችን አጤነህ በሚገባን መንገድ ነው የምታስተምረን፡፡
ReplyDelete‹‹ስለ አንድ ሕዝብ በጅምላ የሚነገሩ የጥላቻ ንግግሮች፣ ቀልዶች፣ ጽሑፎች፣ ዘፈኖች፣ ግለሰቦችን ጠቅመው ሕዝብን ይጎዳሉ፡፡ ይበልጥ ደግሞ በልጆቻችን አእምሮ ውስጥ ተቀርጸው እንደ ጊዜ ጠባቂ ቦንብ ይቀመጣሉ፡፡ ለሕዝብ ሲባል ግለሰቦችን መተው እንጂ ለግለሰቦች ሲባል ሕዝብን ማጥፋት ሕጋዊም ሞራላዊም አይደለም፡፡ ››
ወ/ሮ ተዘራ ደሳለኝ
እውነት ነው ክርስቶስ እኛን ለማስተማር አይደል የሐዋሪያት እግር ዝቅ ብሎ ያጠበው እኛም ለህዝብ ስንል አንዳንድ ጅቦችን መርሳት አለብን ምክንያቱም ህዝብ ክብር ነውና፡፡
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል ካንተ ብዙ እንማራለን የምትናገረው እጅግ የሚገርም ንግግር ከማር የሚጣፍጥ አንዳች መዓዛ አለው ይህን የተቸርከው ከቸሩ መድሐኒአለም ስለሆነ ባንተ ላይ አምላኬን ድምፅ እሰማለሁ ጌታ እግዚያብሔር ጤናህን ይስጥህ ፤ በርታ እድሜ ማቱሳላን በረከት የአብርሃምን፣ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥህ እኔ በጣም ደካማ ነኝ ትንሽ ፈተና ሲመጣ መቋቋም ያቅተኛል በርግጥ አሁን ያለሁበት ሰዎች የሰሩብኝ ፈተና ለኔና ለቤተሰቤ መበተን ምክንያት ቢሆንም ትዳሬ ከመፍረስ ልጆቼን ከመበታተን እንዲያድነኝ በተሰጠህ ፀጋ በፀሎት አስበኝ በእመቤታችን በቅድስተ ቅዱሳን በንጽሂተ ንፁሃን በድንግል ማሪያም አደራ አደራ እላለሁ፡፡
ReplyDeletekalehiwet yasemalin wud memirachin mekariyachin
ReplyDelete"ለሕዝብ ሲባል ግለሰቦችን መተው እንጂ ለግሐሰቦች ሲባል ሕዝብን ማጥፋት ሕጋዊም ሞራላዊም አይደለም ::"
ReplyDeleteለምጣዱ ሲባል አይጢቱን ተዋት!!!
ReplyDeleteክብር ላንተ ይሁን እንደምን ውለህ አደርክ መቼም ገና ሳታውቀኝ አትበለኝ እና እኔ የ4 ልጆች እናት እንዲሁም አራት ልጆች ምንም እንኳን የባለቤቴ እና የኔ የስጋ ዘመድ ቢሆኑም ቤተሰባቸው ከኔ አቅም እጅግ ያነሰ እና በተለይ አባት የሞተባቸውን ልጆች አስተምሬ ሁለቱን እያስተማርኩ አንዱን ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ከአንድ ወር በፊት ያስመረቅሁ የአንድ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ ይህን ያክል እራሴን ካስተዋወቅሁ በኋላ በእኔ ላይ ወረዳ እና ክ/ከተማ ያደረሱብኝን በደል ልገልጽልህ ምን እንደማደርግ እንድትመክረኝ ወይም ከተቻለ ወደ መፍትሄ የምሄድበትን እንድትጠቁመኝ ትዳሬም ከሚፈታ ልጆቼን እና እነዚህን ለቁም ነገር አበቃለሁ ብሎ ያስጠጋኋቸውን ልጆች ከምበትን በሃያሉ እግዚያብሔር ስም በእመቤታችን በቅድስተ ቅዱሳን ስም እማፀንሃለሁ ስልክ 0911784160 ወ/ሮ ፋንታዬ አዘነ እባላለሁ፡፡
ReplyDeletethis is the only solution to overcome our country current situation by forgiving individuals for the society.
ReplyDelete