Friday, May 4, 2018

ዳጋ እስጢፋኖስ - የመነነው ገዳምበ13ኛው መክዘ መግቢያ(እንደ ገዳሙ ታሪክ በ1268 ዓ.ም) የሐይቅ እስጢፋኖስ የአቡነ ኢየሱስ ሞአ ደቀ መዝሙርና የዐፄ ይኩኖ አምላክ(1263-1277 ዓ.ም.) ወንድም በነበሩት በአቡነ ኂሩተ አምላክ የተመሠረተው ዳጋ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም እስካሁን ድረስ በታሪክ ጥንታዊ፣ በእምነት ኦርቶዶክሳዊ፣ በአነዋወር ገዳማዊ፣ በሕይወት ተባሕቷዊ ሆኖ እንደቀጠለ ነው፡፡
አቡነ ኂሩተ አምላክ ገዳሙን በሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስም የቆረቆሩት የሐይቅ እስጢፋኖስን ለማሰብ ይመስላል፡፡ ጥንታውያን የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ከሚታወቁበት መለያ አንዱ ብዙ ጊዜ የሚጠሩት በሰማዕታት (ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ ቅዱስ ቂርቆስ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ በአርባዕቱ እንስሳ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ ወደ ዳጋ ሲመጡ በእመቤታችን ስም የተሠራች ቤተ ክርስቲያን ማግኘታቸውን የገዳሙ ታሪክ ይናገራል፡፡ አካባቢከአኩስም ዘመን ጀምሮ ክርስትና የተስፋፋበት በመሆኑ ይህ የሚደንቅ አይደለም፡፡ የእመቤታችንን ታቦት ወደ ደቅ ደሴት በመውሰድ የቅዱስ እስጢፋኖስ ታቦት የገባው በዐፄ ዓምደ ጽዮን ዘመን መሆኑ ይነገራል፡፡
ገዳሙ ከጣና ሐይቅ በስተ ምሥራቅ በጣና ማዕከላዊ ሥፍራ ላይ ከደቅ ደሴት አጠገብ ይገኛል፡፡ የደሴቱ ስፋት ሦስት ኪሎ ሜትር ያህላል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ከተራራው ጫፍ ላይ ሲገኝ የመነኮሳቱ መኖሪያ በዙሪያው ከትሟል፡፡ የመናንያኑ መቁነን ›መኩሬታ› የሚባል ሲሆን ከዳጉሳ እህል የሚዘጋጅ ዳቦ የመሰለ ምግብ ነው፡፡ የሚበላው ውሎ ነው፡፡ ያውም ወደ ሁለት ሰዓት የሚፈጅ ጸሎት ከተደረገ በኋላ፡፡ 

ዐፄ ዘርአ ያዕቆብ(1426-1460 ዓ.ም.)፣ ዐፄ ሱስንዮስ(1600-1625 ዓ.ም.)ና ዐፄ ፋሲለደስ(1625-1600 ዓ.ም.) ለገዳሙ ቤተ ክርስቲያን ሠርተዋል፡፡ የነበረውን ጠግነዋል፡፡ ዳጋ እስጢፋኖስ በጣና ውስጥ የመጀመሪያው ገዳም ነው፡፡ ዐፄ ይስሐቅ(1406-1421 ዓ.ም.) ለጎሜ እና ዘጎር የተባሉትን ርስቶች ለገዳሙ ሰጥተው ነበር፡፡ በዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ዘመን የገዳሙ መምህር የነበሩት አቡነ ይስሐቅ አባ ፍሬ ጽዮን የተባሉትን ሰዓሊ በመንበር ላይ የሚቀመጥ ሥዕል እንዲስሉ አድርገዋቸው ነበር፡፡ በወቅቱም ብዙ የግድግዳ ሥዕሎች ተሥለው ነበር፡፡ በመካከለኛው ዘመን አጋማሽ ዳጋ እስጢፋኖስ የነገሥታቱ የመቀበሪያ ገዳም ሆኖ ነበር፡፡ የዐፄ ዳዊት(1374-1406 ዓ.ም.)፣ የዐፄ ዘርአ ያዕቆብ፣ የዐፄ ፋሲል፣ የዐፄ ሱስንዮስ፣ ዐጽሞች ዛሬም በገዳሙ ይገኛሉ፡፡ ዐፄ ናዖድ(1488-1500 ዓ.ም.) የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን ዐፅም ከደብረ ነጎድጓድ አውጥተው ነው ወደ ዳጋ የወሰዱት፡፡ በ16ኛው መክዘ ገዳሙ የነገሥታቱና የንጉሣውያን ቤተሰቦች መቃብር ነበር፡፡
በ1556 አና በ1567 ዓም መካከል ባለው ዘመን የገዳሙ አበ ምኔት አባ ገብረ ክርስቶስ ከከንቲባ ገብረ ሚካኤል ባገኙት ድጋፍ ቤተ ክርስቲያኑን አንደገና አሳንጸውት ነበር፡፡ በገዳሙ የሚገኙ ሁለት የሸራ ሥዕሎች በዚህ ዘመን የተጠገኑ ሳይሆን እንደማይቀሩ ይገመታል፡፡ ዐፄ ሰርጸ ድንግል(1555-1589 ዓ.ም.) ከአዳሎች ጋር ለነበረበት ጦርነት ገዳሙን በጸሎት እንዲረዱት ጠይቆ ነበር፡፡ ሲመለስም ለገዳሙ በደቅ ደሴት ጉልት ሰጥቷል፡፡ አያሌ የከበሩ ዕቃዎችንም አበርክቷል፡፡ ድል አድርጎ የማረካቸውም ዕቃዎች በገዳሙ አኑሯቸዋል፡፡ ዐፄ ዘድንግል(1596-1597 ዓ.ም.) ያደገው በኋላም የተቀበረው በዳጋ ደሴት ነው፡፡ 

ዐፄ ፋሲለደስ(1625-1660ዓ.ም.) ለዳጋና ለክብራን በ1659 ዓም አካባቢ ደርደራ የተባለውን ጉልት ሰጥቶ ነበር፡፡ ዐፄ ዮሐንስም(1660-1674 ዓ.ም.) ይህንን ጉልት በ1670 አካባቢ አጽንተውታል፡፡ ዐፄ ፋሲል ከዚህም በላይ ቤተ ክርስቲያኑን ከ1654-56 ዓም ባለው ዘመን እንደገና ሠርቶ አጠናቅቆት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ቤተ ክርስቲያን በ1707 ዓ.ም ተቃጠለ፡፡ ንጉሡም ዘቢድ የተባለውን ጉልት ለካህናቱ ሰጠ፡፡ በዚህም የተነሣ መጀመሪያ በአዞዞ የተቀበረው ዐፄ ፋሲለደስ በኋላ ዐጽሙ ወደ ዳጋ ተዛውሯል፡፡
ዐፄ ኢያሱ አድያም ሰገድ(1674-1698 ዓ.ም) ከ1674 ዓም ጀምሮ ዳጋን በተደጋጋሚ ይጎበኝ ነበር፡፡ በ1676 ዓም. አባ አርኩን የተኩት አበምኔት መምህር አስካል ለንጉሡ በጣም ቅርብ ነበሩ፡፡ እቴጌ ብርሃን ሞገሳ ናርጋ ሥላሴን ባሠሩ ጊዜ የዳጋ እስጢፋኖስ የነበረውን ጉልት ለናርጋ በመስጠታቸው ችግር ተፈጥሮ ነበረ፡፡
ዐፄ ተክለ ጊዮርጊስ በሐምሌ በ1774 ዓም ዳጋ የመማጸኛ ቦታ እንዲሆን ዐውጀው ነበር፡፡
ዳጋ እስጢፋኖስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሦስት ነገር ይታወቃል፡፡ የመጀመሪያው ገዳማዊው ሕይወት ነው፡፡ ከዓለም የራቀ እውነተኛ ገዳም ነው፡፡ ዙሪያውን በባሕር የታጠረና ከአእዋፍ ድምጽና ከሐይቁ የማዕበል ድምጽ በቀር ምንም አይሰማበትም፡፡ ሥራ፣ ትምህርትና ጸሎት አንድ ሆነው የተገመዱበት ገዳም ነው ዳጋ፤ በገዳሙ ከሚገኙት በላይ በአውሮፓ አብያተ መጻሕፍት ተበትነው የሚገኙት መጻሕፍቱ የገዳማውያኑን ዕውቀትና ትጋት ይመሰክራሉ፡፡ ገዳማውያኑ ከጠዋትና ከማታው ጸሎት በሚተርፈው ጊዜ አትክልት ይተክላሉ፣ ፍራፍሬ ያመርታሉ፤ ከዚያም አልፈው ዳጋን የተሳለመ ቱሪስት ሳይገዛው የማይወጣውን ቢለብሱት የሚሞቅ፣ ቢያለብሱት የሚያስመርቅ ጋቢ ይሠራሉ፡፡ ያ ጋቢ በጸሎትና በተባረኩ እጆች የሚሠራ ነውና በረከቱም የማይጠገብ ነው፡፡
ዳጋ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ከግራኝና ከደርቡሽ ተርፎ ከተቀመጠባቸው ገዳማት አንዱ ነው፡፡ በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን(1600-1625 ዓ.ም.) በገዳሙ የድጓ መጽሐፍ ላይ የተጻፈው የመጽሐፍ ዝርዝር የዳጋን የዕውቀት ማዕከልነት ያመለክታል፡፡

ኆልቈ መጻሕፍት ዘዳጋ
  

1.    ኦሪት -1
2.   ግብረ ሕማማት -1
3.   ዕዝራ -2
4.   ኢሳይያስ - 2 ዳንኤል - 2
5.   ነገሥት - 1
6.   መቃብያን - 1
7.   ምሳሌያተ ሰሎሞን - 1
8.   ሄኖክ - 1
9.   ሲራክ - 1
10.  ሕዝቅኤል - 1
11.   ጦቢት - 1
12.  ኤርምያስ - 1
13.  ደቂቀ ነቢያት - 1
14.  መልከ ጼዴቅ - 1
15.  ኢዮብ - 1
16. ኩፋሌ - 1
17.  ዳዊት - 2
18.  ሳቤላ - 1
19. ወንጌል -3
20. ጳውሎስ ዘምስለ ትርጓሜ -1
21.  ግብረ ሐዋርያ - 1
22. ግጻዌ - 2
23. ጸሎተ ቁርባን - 1
24. ሲኖዶስ -3
25. ቀሌምንጦ - 1
26.ዲድስቅልያ - 1
27. ኪዳን - 3
28. ፍካሬ ኢየሱስ - 1
29.ምእዳን - 1
30. ተአምር - 2
31.  ስንክሳር - 2
32. ገድለ ሰማዕታት - 3
33. መጽሐፈ ዶርሆ - 1
34. መጽሐፈ ልደቱ - 1
35. መጽሐፈ በአታ ወቁስቋም - 2
36.መጽሐፈ ፍልሰታ - 2
37. አርአያ ማርያም - 1
38. ላሐ ማርያም - 1
39.ድርሳነ ሚካኤል - 1
40. ድርሳነ ገብርኤል - 1
41.  ድርሳነ አርባዕቱ እንስሳ ወካህናተ ሰማይ - 1
42. ድርሳነ ሩፋኤል ወአፍኒን - 1
43. መዝሙር - 3
44. ዝማሬ… ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን - 1
45. ገድለ ሐዋርያት - 2
46.ምዕላድ (መጽሐፈ) – 1
47. ርቱዓነ ሃይማኖት - 1
48. መጽሐፈ ምስጢር - 1
49.መቃቢስ - 1
50. አፈወርቅ - 1
51.  መጽሐፈ ዜና አበው - 2
52. ሥርዓተ ምንኩስና - 1
53. እንጦንዮስ - 1
54. ኪሮስ - 1
55. ገብረ ክርስቶስ (ገድለ) – 1
56.ገድለ አቢብ - 1
57. ገድለ … - 1
58. ዜና እስጢፋኖስ - 1
59.ገድለ እስጢፋኖስ - 1
60.(ገድለ) ጊዮርጊስ - 1
61. ገድለ ፋሲለደስ -1
62.ገድለ አበ ከረዙን - 1
63.ገድለ አባ ኖብ - 1
64.ገድለ ዮስጦስ - 1
65.ገድለ ቴዎድሮስ - 1
66.   ገድለ አባ በኪሞስ - 1
67.ገድለ አባ ነብዩድ - 1
68.ማርቆስ ዘቶርመቅ - 1
69.   ገድለ አባ ብሶይ
70. ገድለ ሄሮዳ - 1
71.  ሳቤላ - 1
72. ዮሐንስ መጥምቅ - 1
73. ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ - 1
74. ስሞኒ ወአሮን - 1
75. ገድለ አባ ገሪማ - 1
76.ገድለ አባ ጰንጠሌዎን - 1
77. ገድለ…. -1
78. ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት - 1
79.ገድለ አባ ተክለ ሐዋርያት - 1
80. ገድለ አባ በጸሎተ ሚካኤል - 1
81.  ድርሳነ ሰንበት - 1
82. እግዚአብሔር ነግሠ - 1
፻(ወ)፳ወ፯ ዝየ ኆልቈሙ ቦ እለ ባሕቲቶሙ ወቦ እለ በአኅብሮ ዘተጽሕፉ  መጻሕፍት ዘደብረ ዳጋ
(ከዚህ በኋላ እነዚህን ይጨምራል)
83. ጉባኤ ነቢያት -1
84.  ረድእ ወመምህር - 1
85. መጽሐፈ ኅዳር - 1
86.ማር ይስሐቅ - 1
87. መጽሐፈ ብርሃን - 1
88. ዮሐንስ ከማ - 1
89.መጽሐፈ ጥምቀት - 1
90.ገድለ ኢየሱስ ሞአ - 1
91. ቅዳሴ - 1
92.ገድለ አባ ጰንጠሌዎን

በአድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን በዳጋው ወንጌል ላይ በተመዘገበ ሌላ የቆጠራ ዝርዝር ደግሞ ቀጥለው ያሉት ተዘርዝረዋል፡፡
1.    ገድለ አባ ኢየሱስ ሞአ -1
2.   ተአምረ ቅዱስ ጊዮርጊስ - 1
3.   ገድለ ቅዱስ ቴዎድሮስ - 1
4.   ገድለ ማር ዮሐንስ -1
5.   ገድለ አባ ኖብ ወአርከሌዲስ- 1
6.   መጽሐፈ ዶርሆ - 1
7.   መጽሐፈ ቄድር - 1
8.   ፍካሬ ኢየሱስ - 1
9.   ድርሳነ ሚካኤልና ገብርኤል - 1
10.  መጽሐፈ ጥምቀት - 1
11.   ግጻዌ - 1
12.  መጽሐፈ ፍትሐት - 1
13.  ድጓ -2
14.  ዝማሬ -2
15.  የያሬድ እግዚአብሔር ነግሠ -1
16. መጽሐፈ ሰንበት - 1
17.  ቅዳሴ -3
18.  ታሪክ -1
19. መጽሐፈ ምግባር -1
20. መጽሐፈ ሐዊ- 1
21.  ርቱዓ ሃይማኖት -1
22. ክብረ ነገሥት - 1
23. ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ -1
24. መጽሐፈ በርለዓም -1
25. አርባዕቱ ወንጌል 4
26.ጳውሎስ - 2
27. ግብረ ሐዋርያት - 1
28. ቀለምሲስ - 1
29.ሐዋርያ -1
30. ሲኖዶስ - 2
31.  ዲድስቅልያ -1
32. ቀሌምንጦስ -1
33. ፈውስ መንፈሳዊ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን - 1
34. ሃይማኖተ አበው -2
35. ድርሳነ ቄርሎስ -1
36.አፈወርቅ -1
37. ረድአ እንጦንስ -1
38. ማር ይስሐቅ - 1
39.አረጋዊ መንፈሳዊ -1
40. አረጋዊ ዜና አበው - 1
41.  ፊልክስዩስ -1
42. ፍትሐ ነገሥት -2
43. ስንክሳር -2
44. ተአምረ እግዝእትነ ማርያም -2
45. ተአምረ ኢየሱስ -1
46.ትርጓሜ ጳውሎስ -1
47. ገድለ ሐዋርያት -3
48. ገድለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ -1
49.ገድለ ሰማዕታት -2
50. መጽሐፈ ኅዳር -1
51.  መጽሐፈ ኪዳንና ሰርጊስ -1
52. መቃቢስ - 1
53. ፈረጅ -2
54. ዜና አይሁድ - 1
55. ግብረ ሕማማት - 1
56.መጽሐፈ ነቢዩድ - 1
57. ዜና አበው - 2
58. ረድእ ወመምህር - 1
59.አክሲማሮስ - 2
60.ድርሳነ ሩፋኤል -1
61. ጉባኤ መልክእ - 1
62.ገድለ ጻድቃን - 1
63.ገድለ ወለቱ - 1
64.ሰንጠረዥ - 1
65.ላሐ ማርያም - 1
66.  መጽሐፈ ምንኩስና - 1
67.ገድለ ቂርቆስ - 1
68.ገድለ ያሳይ - 1
69.  ድርሳነ ኢየሱስ - 1
ወኩሎሙ ድሙር ኆልቆ መጻሕፍት ፻ወ፴
ኆቆ መጻሕፍት
70. ኦሪት - 2
71.  ዕዝራ፣ ኢዮብ - 1
72. ጉባኤ ነቢያት - 1
73. ኢሳይያስ -1
74. ዳንኤል - 1
75. ኤርምያስ፣ ዳንኤል - 1
76.ነገሥት -1
77. ጦቢትና መጽሐፈ ኪዳን - 1
78. ሲራክ - 1
79.ኩፋሌ -1
80. ደቂቀ ነቢያትና ሰሎሞን -1
81.  ሕዝቅኤልና ዕዝራ - 1
82. መቃብያን - 1
83. ዳዊት -1
84. ሄኖክና ድርሳነ ገብርኤል -1
85. ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስና ገድለ አፍቅረነ እግዚእ -1
86.ገድለ ተክለ ሃይማኖትና ገደለ ተክለ ሐዋርያት -1
87. ገድለ አባ ሳሙኤል -1
88. ገድለ አባ ከረዙንና አባ ጌርዳ
89.ገድለ አብርሃም
90.ገድለ አባ ገሪማና ገድለ እስጢፋኖስ -1
91. ድርሳነ ማርያም -1
92.ገድለ አቡናፍርና መልከ ጼዴቅ - 1
93.መጽሐፈ ፍልሰታ - 1
94.ገድለ ቴዎድሮስ ገድለ ኪሮስ -1
95.ገድለ አባ በግዑ ገድለ መብዐ ጽዮን - 1
96. ገድለ አርሲማ ገድለ በርበራ - 1
97.ገድለ አባ ጰንጠሌዎን - 1
98.መጽሐፈ ምስጢር- 1
99.  ገድለ አባ በጸሎተ ሚካኤል -1
100.  ገድለ ላሊበላ - 1
101.መጽሐፈ ምዕላድ - 1
102.   መጽሐፈ ብርሃን -1
103.   ገድለ ጳውሊና መጽሐፈ እንጦንስ -1
104. ገድለ ኪሮስ - 1
105.  ገድለ ፋሲለደስ - 1
106. ድርሳነ ማርያምና በኪሞስ - 1
107.  ርቱዓ ሃይማኖት - 1
108.  የሐፄ እግዚአብሔር ነግሠ ከነ ተአምሩ - 1
109.  እግዚአብሔር ነግሠ የአርኬ - 1
110.ገድለ ገብረ ክርስቶስና ገድለ አቢብ - 1
111. ገድለ እስጢፋኖስና ገድለ ገላውዴዎስ - 1

ይቀጥላል፡፡


5 comments:

 1. ketayun begugut entebikalen

  ReplyDelete
 2. kalehiwet yasemalin memihrachin
  edime tena abizito fetary yistih

  ReplyDelete
 3. wondemachen abatachen memekiachen edeme yistelen

  ReplyDelete
 4. msrhailu34@gmail.comJune 25, 2018 at 3:46 PM

  kale hiywet yamesmalen

  ReplyDelete