Saturday, May 26, 2018

ሰው ተዋርዶ ሰይጣን ክብር ያገኘበት ዘመን


የቤተ ክርስቲያናችን የገድላትና የተአምራት መጻሕፍት ሲጻፉ፣ የሰዎቹን ክብር በሚጠብቅ መንገድ ካልሆነ በቀር ችግር ደርሶባቸው ተአምር የተደረገላቸውን ሰዎች የተጸውዖ ስም አይገለጡም፣ ወይም የክርስትና ስማቸው ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ሰዎቹን በስማቸው መጥራት ቢያስፈልግ እንኳን ለዝርዝር ማንነታቸው በማይመች ስም ይገለጣሉ፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረግበት ዋናው ምክንያት የሰውን ልጅ ሰብአዊ ክብር(Human dignity) ለመጠበቅ ነው፡፡ እነርሱ ቢያልፉም እንኳን ልጅና ልጅ ልጅ ይኖራልና፡፡
እኅታችን ጌጤ ዋሚ ‹ሩጫን በሚከለክሉ በአጋንንት› ተያዘች ተብሎ የተለቀቀባትን ቪዲዮ ስመለከት በእምነት ስም የሚነግዱ ሰዎች የደረሱበትን ሞራላዊ ኪሣራ አየሁት፡፡ ከመጀመሪያው ሰይጣንን እየቀዱ ለገበያ ማዋል በየትኛውም የቅዱሳን ሕይወት ውስጥ የማናየው ነው፡፡ መቼም ሰይጣን እንደዚህ ዘመን በክብር መድረክ ያገኘበት ጊዜ የለም፡፡ ከዚህም አልፎ ልጅ፣ ቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ዓለም አቀፋዊ ተክለ ሰብእና ያላትን አትሌት በዚያ ዓይነት ክብርን በሚነካ ሁኔታ እያሰቃዩ በቪዲዮ ማሳየት ፈጽሞ የእግዚአብሔርን ክብር መግለጥ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰውነትን ማዋረድ እግዚአብሔርን ማዋረድ ነውና፡፡ አስፈላጊ ነው ካለች እርሷ ራሷ ትንገረን እንጂ ይህንን የመሰለ ቪዲዮ እንኳን ሌላው እርሷም ልታሳየን የተገባ አይደለም፡፡  

ሃይማኖት ታረደ ደሙን ውሻ ላሰው
ከንግዲህ ልብ ልብ አልተገናኘም ሰው
እንደተባለው ሆኖብን ነው እንጂ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የቅድስና ሕይወትስ በሰውነት ክብር ላይ የሚቀልድ አልነበረም፡፡ የአንድን ሰው ‹ፈዋሽነት› ለማሳየት የሌላን ሰው ዝና፣ ክብርና ሰብአዊ መብት መከስከስ በምንም መልኩ ጸጋ እግዚአብሔርን አያመለክትም፡፡ የወንድማቸውን ክብር ለመጠበቅ ያልፈጸሙትን ፈጸምን ብለው መከራ የተቀበሉት የነ አባ መቃርስ፣ የነ እንባ መሪና፣ የነ ሙሴ ጸሊም፣ ቤተ ክርስቲያን፤ ለራሳቸው ክብር ሲሉ የወገኖቻቸውን ክብር በሚደፈጥጡ ‹አጥማቂዎች› ሲቀለድባት ማየት ያማል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም የጳጳሳትን ዝውውር ከሚመለከት ይልቅ እንዲህ ያሉ ነገሮች ሕግና ሥርዓት እንዲኖራቸው ቢያደርግ መልካም ነበር፡፡ ማን ያጥምቅ? የተጠማቂዎች ሰብአዊ ክብር፣ የተጠማቂዎችን መረጃ የመጠቀም መብት፣ በአደባባይ ራቁትን መቆምና ራቁትን ፎቶ የመነሣት ጉዳይ፣ የምስክርነት አሰጣጥ ሥነ ምግባር፣ የሴቶችና የሕጻናት መብቶች፣ የአካል ጉዳተኞችና የአእምሮ ሕሙማን መብቶች፣ ወዘተ ሕግና ደንብ የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ ያ ካልሆነ ግን ገና ከዚህ የከፋም እናያለን፡፡

29 comments:

 1. ቃለ ህይወት ያሰማልን!ረጅም እድሜ እና ጤና ይስጥልን!

  ReplyDelete
 2. ዳኒ ወንድማችን ስለ ጥቆማው እግዚአብሔር ይስጥልን
  እናነባለን ። ደጃዝማች ወልደሰማያትም የተወሰነ ቢጽፋ?
  ላለው የአለቃ ገበረ ሀና ልጅ ቄሰ አንተነህ ገ/ሀና
  አዛውንት በህወት አሉ።
  ወላይታ አረካ ከተማ የዱቦ ማርያም መስራችና አሰተደደሪ
  ጠይቋቸወ

  ReplyDelete
 3. ትክክል!የአንዱን ዝና ለማናኘት ሰብአዊነት መጉደፍ የለበትም::
  ለመማርያ ከሆነም በተገቢዉ መንገድ ማድረግ ይገባል ዛሬ እንደትንሽ ምናየዉ ነገር ነገ ትልቅ ነገር ሳያስከትል በእንጭጭነቱ ፈር እንዲይዝ ሥልጣኑን ያላቸዉ ሰዎች ትኩረት ሰጥተዉ ሊያዩት ይገባል::

  ReplyDelete
 4. lga ewent blhale ymsema sew teff sytan bagerachen lay berate abatwechem bsletancew le tegwebt ytstachewen ader tweet bbetcrestenew sm ymenegedeweten masqem alchalewer egzabher amelak yabatochanne libona ymleselen !! twelidew eytblach new bhasatzaa nebe nenn bmelew hasateza nebewech hasatez atemakewech bhastez mmeher bthadesewech nen bayewech abaterw bmhertew yechen ydengle marya asrat ager endyesebat yzweter thalata new leg egzabher bsalemen bten tbekew yethiopian tensayen ysayane amen!!!
  ReplyDelete
 5. ልቦና ይስጥህ

  ReplyDelete
 6. ክፍ ነገር ባትፅፍ ደግ ነብር ክፉ ክፉ ፀሀፉ ትባላለህና።ይውልህ እንግዲ እነ አፍልሆ እነ የጠንቖይ ስጋ የበሉ እና ያጎነበሱ ሁሉ መምህር ግርማን እንዲሁም የእግዚአብሄርን ክብር ሲገለፅ አይወዱም።እና አፍልሆ ለተናጋሪነት ለተፈሪነት ይውላል የሩጫው ደግሞ ለጥንቓይ ይውላል ።ሰለዚህ ነው ልቦና ይስጥህ የምልህ።አልታደልክም እንጂ ምናምንቴ እና እንዳንተ አይነቱ ግብስብስ ከምትሸልም መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙን ብትሽልም ይሻልህ ነበር።ግን ግንባር ይፈልጋል።አልታደልክም ልክብርህ እና ለእንደበትህ የጠጣህው አፍልሆ ለበጎ ሰው እንዳታይ እና እንዳታከብር ቃል ብሎ በ4 ነጥብ አስማለህ።ፈውሱን ይላክልህ። በአስቸኳይ በአስቸኳይ በአስቸኳይ ለመምህር ግርማ እና ለምእመናኑ ይቅርታ ጠይቅታ ጠይቅ ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አዚም የጋረደብህ ነገር አለ፡፡መድኃኔ ዓለም ያንሳልህ ይግለጽልኅ፡፡ዳኒ ግን ምርጥ ልጅ

   Delete
  2. ዉይይይይይይይ አይይይይይይዞህ

   Delete
 7. meche yihonale kiduse sinodos lebatechiristina gudaye techenko yemiyawukewu! Danial

  ReplyDelete
 8. አላዋቂ አዋላጆች የተዋሕዶ ምሥጢር ያልገባችሁ አንሄድባትም ያላችሁ) ገብቷችሁም የሸሻችሁ
  በሕገ ወጥ አጥማቂያን መርዝ ልባችሁ ሳያመነታ
  ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ብትጠይቋት በእርጋታ
  ከሊቃውንት የዕውቀት መዝገብ ትሰጣለች በአንድምታ

  ReplyDelete
 9. https://www.youtube.com/watch?v=oCNDtwgN02k

  ReplyDelete
 10. https://www.youtube.com/watch?v=oCNDtwgN02k

  ReplyDelete
 11. ዲያቆን ጌጤ ዋሚ ክብሯ የተነካው አጋንንቱ በያዛት ጊዜ እንጂ ስትፈወስ በሚያሳየው Video መለቀቅ አይደለም። ከጌጤ ዋሚ በፊት እኮ ብዙ ታሚሚዎች እንዲሁ ሲፈወሱ የሚያሳይ ቪድዮ ተቀርፆ ተለቋል………ታዲያ ጌጤ ዋሚ ላይ እንዲህ የገነነበት ምክንያት ታዋቂ ስለሆነች ነው?! ተዋቂነቷ ስራዋ ነው እንጂ የሰውነት ክብሯን ከሌሎች የሚያበስለጥ አይደለም። እነዛም ቢሆን ሲፈወሱ በገሃድ መታየቱ አንደኛ ግልፅ የፈውስ ስነስርዓት እንዳለ አመላካች ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ለተፈዋሾቹም የእግዚአብሔር ስራ በእነርሱ ሲሰራ የሚያሳይ ምስክነታቸውን ማጠናከሪያቸው ነው ማለት ነው። ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለቅዱሳኑ አውርተሃል። ኢየሱስ ክርስቶስ እኮ ህዝብ በነቂስ በወጣበት አደባባይ ፈውሷል። ይህ የፈውስ ስራ እንዲደበቅ ቢፈልግ ኖሮ ታማሚዎቹን ወደ ድብቅ ስፍራ ወስዶ መፈወስ ይችል ነበር! ቅዱሥ ዮሐንስንም ተመልከተው! ከሚኖርበት የበረሃና የብትሕውትና ኑሮ ወጥቶ የጥምቀት ስራውን ባደባባይ ይሰራና ይፈውስ ነበረ………ታዲያ መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ላይ ምን የተለየ ነገር ታየ?! ስለቅዱሳኑ ትህትና ለመግለፅ ሞክረሃል። ቅዱሳኑ በመከራና በመገፋት ትሩፋታቸው ስለሚበዛ ያላጠፉትን ጥፋት እንዳጠፉ ሆነው ሳይገባቸው ቅጣትን ተቀብለዋል! እውነት ነው! ታዲያ ይሄ ከመምህር ግርማ የማጥመቅ ስራ ጋር ምን አገናኘው?! ዲያቆን ላንተ እንኳን እንዲህ አይነት ትንታኔ መስጠት ለቀባሪው ማርዳት ነው ሚሆነውና የፃፍከውን መለስ ብለህ ብታየው መልካም ነው! አመሰግናለሁ!

  ReplyDelete
 12. ዲያቆን ጌጤ ዋሚ ክብሯ የተነካው አጋንንቱ በያዛት ጊዜ እንጂ ስትፈወስ በሚያሳየው Video መለቀቅ አይደለም። ከጌጤ ዋሚ በፊት እኮ ብዙ ታሚሚዎች እንዲሁ ሲፈወሱ የሚያሳይ ቪድዮ ተቀርፆ ተለቋል………ታዲያ ጌጤ ዋሚ ላይ እንዲህ የገነነበት ምክንያት ታዋቂ ስለሆነች ነው?! ተዋቂነቷ ስራዋ ነው እንጂ የሰውነት ክብሯን ከሌሎች የሚያበስለጥ አይደለም። እነዛም ቢሆን ሲፈወሱ በገሃድ መታየቱ አንደኛ ግልፅ የፈውስ ስነስርዓት እንዳለ አመላካች ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ለተፈዋሾቹም የእግዚአብሔር ስራ በእነርሱ ሲሰራ የሚያሳይ ምስክነታቸውን ማጠናከሪያቸው ነው ማለት ነው። ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለቅዱሳኑ አውርተሃል። ኢየሱስ ክርስቶስ እኮ ህዝብ በነቂስ በወጣበት አደባባይ ፈውሷል። ይህ የፈውስ ስራ እንዲደበቅ ቢፈልግ ኖሮ ታማሚዎቹን ወደ ድብቅ ስፍራ ወስዶ መፈወስ ይችል ነበር! ቅዱሥ ዮሐንስንም ተመልከተው! ከሚኖርበት የበረሃና የብትሕውትና ኑሮ ወጥቶ የጥምቀት ስራውን ባደባባይ ይሰራና ይፈውስ ነበረ………ታዲያ መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ላይ ምን የተለየ ነገር ታየ?! ስለቅዱሳኑ ትህትና ለመግለፅ ሞክረሃል። ቅዱሳኑ በመከራና በመገፋት ትሩፋታቸው ስለሚበዛ ያላጠፉትን ጥፋት እንዳጠፉ ሆነው ሳይገባቸው ቅጣትን ተቀብለዋል! እውነት ነው! ታዲያ ይሄ ከመምህር ግርማ የማጥመቅ ስራ ጋር ምን አገናኘው?! ዲያቆን ላንተ እንኳን እንዲህ አይነት ትንታኔ መስጠት ለቀባሪው ማርዳት ነው ሚሆነውና የፃፍከውን መለስ ብለህ ብታየው መልካም ነው! አመሰግናለሁ!

  ReplyDelete
 13. እኝህ ሰውዬ ከቤተ ክ/ን መድረክ ተከልክለዋል፡፡ ከዚህ በኋላም ኦርቶዶክስ ቤተ ክ/ን የምትጠቀምባቸውን ቅዱሳን ስዕላትም ሆነ ስማቸውን እየተጠቀሙ የጥንቆላ ስራቸውን እንዳይሰሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ትኩረት ቢሰጠው ጥሩ ነው፡፡ መምህራኖችም በየመድረኩ ይህንን ሴራቸውን ለምዕመናን ማሳወቅ አለባቸው፡፡ ይህንን በምልክት የሚያምን ትውልድ ለመሳብና ዝናቸዉንም ለማሳያት የታዋቂ ሰዎችን ምስክርነትም እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ ወገኖቼ ልብ ያለው ልብ ይበል!

  ReplyDelete
 14. What is wrong with you Dn Daniel Kibret? I never expected such kind of commitment from you!
  Were you seriously written this or you let someone to publish this text.
  The reason I said this is I used to watch your sermons and read your texts for long time, honestly I changed my self and started my journey for good. However, since I started to watch Memhir Girma sermons and Aba Yohannes Tesfamariam sermons, I learned very important things, such as ways of stopping a Davel work on myself and my family.
  You Dn Daniel don't understand how human controlled by Davel in one way to another due to many factors, such as we were born from none spiritual family, because of juelious people we ware witchcarfted and due to our weakness and luck of praying we became a victim for bad spirits. You are not in this situation because you don't Understand the pain either God protect you or you come from blessed family which most of us not lucky enough to come from blessed family. You are not a victim for Davel doesn't mean everyone is clear. Since I watched this fathers sermons hope grow in my heart which was chained my life and my family life by Davel. I now have a hope And problem will be solved by the Power of God through Aba Yohannes as Father Girma is not serving. The reson I said this is I did all my best, I prayed and begged God a lot to solve my situation but my problem never solved(be aware it is not money problem). my problem never solved by ur sermon but my problem solution hope I got is from these fathers. Your sermons only showed me the journey to God. I don't understand how you thought and easy this for you while our life is distroyed. Please make corrections on this comment otherwise your teaching seems good at the start but blocking at the end. I really need an answer if you can either to my email or you can public.

  ReplyDelete
  Replies
  1. This comment has been removed by the author.

   Delete
  2. kedest.... i can understand how hard your life could be but don't ever give up on GOD and trust HIM that HE won't let you down. It is just to test your level of faith and patience. I think you misunderstood something... being born from christian family or not is not the point for salvation. the main point is to find the true GOD, to follow HIS commandments, to love one another and so on. I say this because in our church i could give you a couple of Great Saints whose family were non-Christians. Example Abraham, St. Pakumious the Egyptian, St. Ephiphany and many more. So, keep going with your fasting,prayer and bowing. GOD got ever solution for our problem and you will see it by yourself. D.Daniel's sermon are really helpful as you put it " shows the way to GOD" that is the aim of any sermon. and a believer has to be eager to that not for "miracles". Remember Saint Paul, he was a great apostle but he saw the devil beating him so hard and he prayed so many times to GOD to cure him but that wasn't GOD's will so he just accept GOD's will and reject his will. there are things that we should accept if that is GOD's will. on Matthew 26: 36-56 Our LORD JESUS said “My Father, if it be possible, let this cup pass from me; nevertheless, not as I will, but as you will.” you see there are things to let go if GOD's Will reject them. I am not worth of giving advice for anyone but it is just to say few points. I say on to you that even if your problem is so big just stick with GOD and don't follow people. Let the prayers of saints be with you and help you to be free from your problem. But if you would like to talk to Dn. Daniel his number is available on this web.

   Delete
 15. ትክክል ነገር ግን ዳኒ እስካሁን የት ነበርክ ወይስ የተከበረ ነው የምታከብረው?

  ReplyDelete
 16. Dn. Daniel wrote on September 27, 2015
  የዘመናችን አጥማቂ ነን ባዮች፡- የሐሳዊው መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች article (part 1-4 or 5) so this is not his first time to write about this issue

  ReplyDelete
 17. getachen eko yetenakut gar neber atmaki nen yemilut gen tawaki artist ena zena yalachewn sewoch eyefelegu lerasachew sem zena lemakabet mdrawi keber felega kentu sera endemiseru eko kale sebaki kale astemari videwon ayto becha mawek kelal new egziabhir kezih kefu zemen bechernetu yetebken kemalet wechi men yebalal. yekedemut abatoch tarikn man mawek yefelgal yemitay ena yemidases neger kalhone......kefu tewled melketen yeshal.....

  ReplyDelete
 18. For those of you commented to advice me, thank you for your posetive thinking. I understand your intention. it is to save me from danger but my situation is more complicated, which is why I need others prayer. Please remember me in ur prayer! I’ll come back with answer in September. May God be with our church orthodox tewahedo!

  ReplyDelete
 19. ሰውየው እኮ ሲጀመር እግዚአብሄርን አያውቅውም፡፡ ጊዜውን የሚያጠፋው ገንዘብን በማሳደድ ነው፡፡ ወሎ መጥቶ እኮ ክርስቲያኑ ወደ እርሱ አንሄድም ሲሉ ተሳድቦ ሙስሊሙ ይሻላል ያለ ወንበዴ እኮ ነው፡፡ የመቁጠሪያን እና የቅባ ቅዱስን ክብር ያረከሰ የሰይጣን መልክተኛ ነው

  ReplyDelete
 20. ሰውየው እኮ ሲጀመር እግዚአብሄርን አያውቅውም፡፡ ጊዜውን የሚያጠፋው ገንዘብን በማሳደድ ነው፡፡ ወሎ መጥቶ እኮ ክርስቲያኑ ወደ እርሱ አንሄድም ሲሉ ተሳድቦ ሙስሊሙ ይሻላል ያለ ወንበዴ እኮ ነው፡፡ የመቁጠሪያን እና የቅባ ቅዱስን ክብር ያረከሰ የሰይጣን መልክተኛ ነው

  ReplyDelete
 21. Dear all,
  Here I am back after I promised to come back with an answer to the above comments. I staid in Wenkishet Monastry bahir Dar for 2 weeks. I met Aba Yohannes and got blessed as well as Aba Zwengel from Adomba Tigray. Thanks to God Dn Danel Kibret is not the only person God servant in our Orthodox Church. According to the above text against our fathers, I could have been ended up suffering by enemy davel, but God is great! Or lord created ways for us to survive. We speak what we have seen according to the bible. By the time I met Aba Yohanes Tesfamariam placed his cross on my back, I felt something came out and felt happiness and freedom. I didn’t get this chance by praying and by following Dn Daniel’s sermons. This is what our faiths power by the grace of God. My massage to Dn Daniel kibret is by trying to block our fathers grace, it is impossible to stop God’s work. I know many of your followers loose this chance, but any one with clear heart will still get the chance. I don’t know what will your answer to these father got permission to serve including memhir Girma. You tried to be against these fathers, but you fail to stop them. I think it is your time to go and see this fathers work or if you think you have the power of holly spirit more than them, it is your time to go and stop them or if you are unable to do this it is ur time to stop being aginest this fathers. May God open your heart and those of your followers blinded by ur comments.

  ReplyDelete
 22. ክቡር አፋርን ህዝብ ቢጎበኙ እና ምልከታዎን ለህዝብ ቢያቀርቡ እንዲሁም በአፋር ክልል አሳይታ ወረዳ የንጉስ እያሱ ተራራ የሚባል አለ ምን ያህል እውነት ነው ቢገልጹልኝ፡፡ ከፈለጉኝ yisfaz@gmail.com

  ReplyDelete