Thursday, March 22, 2018

የጣና ቂርቆስ መጻሕፍት በሦስት ዘመናት

ጥንታውያን ጳጳሳት፣ ሊቃውንት፣ ካህናትና ምእመናን፤ ነገሥታት መኳንንት፣ ወይዛዝርት ባላባቶች መጻሕፍትን እያስጻፉ ለየገዳማቱና አድባራቱ ይሰጡ ነበር፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በእሳት፣ በጦርነት፣ በዝርፊያና በስጦታ ያለቁት አልቀው የቀሩት ቀርተዋል፡፡ አንዳንድ ገዳማት የነበሯቸው መጻሕፍት ዝርዝር በብራና መጻሕፍት ላይ ይመዘግባሉ፡፡ እነዚህን መዛግብት ዛሬ ስናነባቸው ስንት መጻሕፍት እንደጠፉ ይነግሩናል፡፡ በሌላው ሀገር የተወሰዱትስ ምንም በስደት ቢኖሩ ሕልውናቸው አልጠፋም፡፡ ሕልውናቸው የጠፉት መጻሕፍት ናቸው የሚያስቆጩት፡፡ ከትናንት ብንዘገይ ከነገ እንድንቀድም የቀደሙትን የሥነ ጽሑፍ ሀብቶቻችንን መቃኘት፣ ማጥናትና መጠበቅ አለብን፡፡ ሀገር የምትቆመው በዕውቀትና በእውነት ነውና፡፡ ዕውቀትን ያለ እውነት፣ እውነትንም ያለ ዕውቀት ማሰብ አይቻልም፡፡ 

ቀጥሎ የቀረበው ዝርዝር ዛሬ በፈረንሳይ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ በቁጥር 68 ተመዝግቦ ከተቀመጠውና ይሄ ዝርዝር ከተጻፈበት ከመጽሐፈ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ የተገኘ ነው(fol.107b)፡፡ በመጀመሪያው ሰንጠረዥ(1) የተቀመጠው በብርሃን ሰገድ ኢያሱ ጊዜ ከ1723-1747 ዓ.ም. ባለው ዘመን መካከል መምህር ወልደ ኢየሱስ የገዳሙ መምህር እያሉ በተደረገው ቆጠራ የተመዘገበው ነው፡፡ በሁለተኛው ሠንጠረዥ (2) ያለው ደግሞ በዐፄ ኢዮአስ ዘመነ መንግሥት 1747-1761 ዓ.ም. ባለው ዘመን መምህር ዘፈረ ሥላሴ የገዳሙ መምህር እያሉ የተደረገ ቆጠራ ነው፡፡ በሦስኛው ሠንጠረዥ (3) የጣና ቂርቆስ መጻሕፍት በ1965/66 በማይክሮ ፊልም ሲነሡ የተገኙ መጻሕፍት የተጻፉበት ዘመናቸው የተገለጠበት ሲሆን አራተኛው ሠንጠረዥ(4) ደግሞ በዚህ ዘመን ማይክሮ ፊልም ሲነሣ ያልተገኙት መጻሕፍት የ ‹የ› ምልክት ሲደረግባቸው የተገኙት ደግሞ የ‹አ› ምልክት ተደርጎባቸዋል፡፡ በብራናው ላይ ዝርዝራቸው ሳይገኝ በኋላ የተጨመሩትም በዚሁ በቁጥር 4 ሠንጠረዥ መጨረሻ ላይ ተቀምጠዋል፡፡


የመጽሐፉ ስም
1) ብዛት
በብርሃን ሰገድ ኢያሱ ዘመን
2)ብዛት በዐፄ ኢዮአስ ዘመን
3)በማይክሮ ፊልም ሲነሣ የዘመኑ ግምት
4)ማይክሮ ፊልም በተነሣ ጊዜ የተገኙ
1.  
ሐዊ
1
1
16ኛው መክዘ
2.      
ኦሪት ምስለ መጽሐፈ ሰሎሞን
3
3
ይሄ ወይም ሌላው  መጽሐፈ ሰሎሞን በ16ኛው መክዘ የተጻፈ ነው፡፡
3.      
ጉባኤ ነቢያት
1
1
13ኛው መክዘ
4.      
ነገሥት ምስለ መጽሐፈ ሰሎሞን ወኢዮብ ወኢሳይያስ
1
1

5.      
ነገሥት ምስለ መጽሐፈ ሰሎሞን ወኢዮብ ወኢሳይያስ (የተገዛ)
X
1

6.      
ሲኖዶስ
3
2 X
አንዱ የ9ኛው መክዘ ነው አንደኛው ደግሞ የ15ኛው መክዘ
7.      
ዲድስቅልያ
2
2

8.      
ቀሌምንጦስ
2
2
ሁለቱም የ14ኛው መክዘ ናቸው
9.      
ገድለ ሐዋርያት
1
1
18ኛው መክዘ
10.     
ገድለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
1
1
17ኛው መክዘ
11.      
ስንክሳር
2
2
አንደኛው የ16ኛው መክዘ፣ ሌላው የ17ኛው መክዘ ናቸው
12.     
ሃይማኖተ አበው
2
2
1ኛው የ16ኛው መክዘ ሌላው 18ኛው መክዘ
13.     
ድርሳነ ቄርሎስ
2
2
18ኛው መክዘ
14.     
ዮሐንስ አፈወርቅ
1
1

15.     
አረጋዊ መንፈሳዊ ከፊልክስዩስ ጋራ
1
1

16.    
ማር ይስሐቅ ከፊልክስዩስ ጋራ
1
1

17.     
አረጋዊ መንፈሳዊ ለብቻው
1
1
17ኛው መክዘ
18.     
ዜና አበው
2
2
18ኛው መክዘ
19.    
ወንጌል
3
3
ሦስቱም የ17ኛው መክዘ ናቸው
20.    
ጳውሎስ
2
2
ሁለቱም የ18ኛው መክዘ ናቸው
21.     
ተአምረ ማርያም
4
4
18ኛው መክዘ
22.    
ዜና አይሁድ(መምህር ወልደ ኢየሱስ የሰጡት ሥዕል ያለበት)
1
1

23.    
ዜና አይሁድ ምስለ በድራን
1
1

24.    
ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ
1
1

25.    
ግብረ ሕማማት
2
2
አንደኛው የ17ኛው መክዘ፣ ሌላው የ18ኛው መክዘ ናቸው
26.   
ፈረጅ
1
1

27.    
ገድለ ሰማዕት
3
3
አንዱ 14ኛው መክዘ፣ ሁለቱ 16ኛው መክዘ ናቸው
28.    
ገድለ ፊቅጦር
1
1
14ኛው መክዘ
29.   
ርቱዓ ሃይማኖት
2
2
የ10ኛው መክዘ እና የ15ኛው መክዘ
30.    
ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ምስለ ድርሳነ ሩፋኤል
1
1
15ኛው መክዘ
31.     
ገድለ ዮልዮስ
1
1

32.    
ገድለ ተክለ ሃይማኖት
2
2
አንዱ የ15ኛው መክዘ ነው
33.    
ገድለ ማማስ
1
1

34.    
ድርሳነ አብርሃም
1
1

35.    
ገድለ ኪሮስ
1
1
18ኛው መክዘ
36.   
መጽሐፈ ኅዳር
1
X

37.    
መጽሐፈ ብርሃን
1
1

38.    
ክብረ ነገሥት
2
1X
አንዱ 18ኛው መክዘ ነው
39.   
ፍትሐ ነገሥት
1
1
18ኛው መክዘ
40.    
መጽሐፈ ኪዳን
1
1
18ኛው መክዘ
41.     
መጽሐፈ ጥምቀት
1
1

42.    
ቅዳሴ
3
3

43.    
የፍትሐት መጽሐፍ
3
3

44.    
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
1
1
17ኛው መክዘ
45.    
ጉባኤ መልክእ
3
3
18ኛው መክዘ
46.   
ነገረ ማርያም
1
1
17ኛው መክዘ
47.    
ላሃ ማርያም
1
1

48.    
ድጓ
3
3
አንደኛው የ15ኛው መክዘ ሌላው የ17ኛው መክዘ ነው
49.   
ምዕራፍ ከዝማሬ ጋር
1
1
17ኛው መክዘ
50.    
መዋሥዕት ከዝማሬና ምዕራፍ ጋር(ወልደ ሩፋኤል የሰጠው)
1
1

51.     
እግዚአብሔር ነግሠ
1 X
2
አንዱ የ17ኛው ሌላው የ18ኛው መክዘ ናቸው
52.    
አርኬ
2
2
18ኛው መክዘ
53.    
ሰዓታት
1 X
2
18ኛው መክዘ
54.    
ገድለ ቂርቆስ
3
3
18ኛው መክዘ
55.    
ገድለ ገብረ ክርስቶስ
1
1
14ኛው መክዘ
56.   
ገድለ ኤዎስጣቴዎስ
3
2 X
አንደኛው የ19ኛው መክዘ ነው
57.    
ድርሳነ ሚካኤል
1
1
16ኛው መክዘ
58.    
ዜና እስክንድር ከአክሲማሮስ ጋር
1
1

59.   
ሳዊሮስ ዘእስሙናይ
1
1

60.   
መጽሐፈ ዶርሆ
1
1

61.    
ገድለ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት
1
1

62.   
መጽሐፈ ነቢያት
1
1

63.   
ድርሳነ መድኃኔ ዓለም ከገድለ አቡነ አቢብ ጋር(አባ ገብረ ማርያም የሰጡት)
1
1

64.   
ያልተመለከተ ድጓ ሙዛ ጋራ
2
2
6ኛው መክዘ
65.   
ድርሳነ ማርያም የዓመቱ
1
1

66.   
ድርሳነ ኪዳነ ምሕረት
1
1

67.   
ሔርማ
1
1
16ኛው መክዘ
68.   
ድርሳነ ፍልሰታ
1
1

69.   
ድርሳነ በዓላት የዓመት
1
X

70.    
ዜና ነቢያት የሚነግር
1
X

71.     
መጽሐፈ ግጻዌ
2
2
ሁለቱም የ17ኛው መክዘ ናቸው
72.    
መልክአ ሐዋርያት
1
1

73.    
መጽሐፈ ምንኩስና (አፈ መምህር ወልደ ሳሙኤል የሰጡት)
2
2

74.    
ተአምረ ኢየሱስ (ሥዕል ያለበት እንደ ሁለተኛው ዝርዝር ይህንንም አፈ መምህር ወልደ ኢየሱስ ናቸው የሰጡት)
1
1
17ኛው መክዘ
75.    
መጽሐፈ ነቢያት (ጌታዬ ወልደ ሐና የሰጡት)
X
1

76.   
ገድለ ጊዮርጊስ (እንደ ሁለተኛው ዝርዝር ይህንንም የሰጡት መምህሬ ሕንጻ ክርስቶስ ናቸው)
1
1

77.    
ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (መምህሬ ሕንጻ ክርስቶስ የሰጡት)
1
1

78.    
ሐዲሳት ትርጓሜ
X
4

79.   
ትርጓሜ ጳውሎስ
X
1

80.    
ቅዳሴ
X
1

81.     
ገድለ ተክለ ሃይማኖት
X
1

82.    
ድምር
114
117


83.    
ገድለ ፋሲለደስ18ኛው መክዘ
84.    
ገድለ አባ ኖብ16ኛው መክዘ
85.    
ገድለ አቦሊ14ኛው መክዘ
86.   
ሲላዳስ16ኛው መክዘ
87.    
ውዳሴ አምላክ19ኛው መክዘ
88.    
ዳዊት18ኛው መክዘ
89.   
ድርሳነ ዑራኤል19ኛው መክዘ
90.   
መድብል19ኛው መክዘ
91.    
ገድለ አባዲር16ኛው መክዘ
92.   
አርጋኖን18ኛው መክዘ
93.   
የመድብል ትርጓሜ17ኛው መክዘ
94.   
ተአምረ ኢየሱስ19ኛው መክዘ
95.   
ድርሳነ ጽዮን18ኛው መክዘ

አንዳንድ ነገሮች ስለ ዝርዝሩ

·         ዝርዝሩ በገዳሙ በየዘመኑ መጻሕፍንና ሌሎች ንብረቶችን የመቁጠር ልምድ እንደነበር ያመለክተናል፡፡ ከመጻሕፍቱ ዝርዝር ጋር በገዳሙ የነበሩ ሌሎች ንዋያትም ዝርዝር ተቀምጧል፡፡
·         በሁለቱ ዘመናት መካከል የጎደለም የተጨመረም አለ፡፡ ‹ነገሥት ምስለ መጽሐፈ ሰሎሞን ወኢዮብ ወኢሳይያስ› አዲስ ተገዝቶ ተጨምሯል፡፡ እግዚአብሔር ነግሠም አንድ ተጨምሮበታል፡፡ መጽሐፈ ነቢያትን ጌታዬ ወልደ ሐና ሰጥተው በሁለተኛው ዝርዝር ውስጥ ተካቷል፡፡ አራት የሐዲሳት ትርጓሜ፣ አንድ የጳውሎስ ትርጓሜ፣ አንድ ቅዳሴና አንድ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ተጨምረዋል፡፡ ሲኖዶስ ደግሞ 3 የነበረው ሁለት ሆኗል፡፡ መጽሐፈ ኅዳር በሁለተኛው ዝርዝር ውስጥ የለም፡፡ ክብረ ነገሥት በኋለኛው ዝርዝር አንዱ የለም፡፡ ገድለ ኤዎስጣቴዎስም ከሦስት ወደ 2 ወርዷል፡፡ ድርሳነ በዓላት የዓመት በኋለኛው ዝርዝር ውስጥ አልተገኘም፡፡ ዜና ነቢያትን የሚነግረው መጽሐፍም እንዲሁ፡፡
·         ጉባኤ ነቢያት፣ ዜና አይሁድ ምስለ በድራን፣ ፈረጅ፣ ገድለ ዮልዮስ፣ ገድለ ማማስ፣ ድርሳነ አብርሃም፣ መጽሐፈ ኅዳር፣ ያልተመለከተ ድጓ ሙዛ ጋራ፣ ድርሳነ ማርያም የዓመቱ፣ ድርሳነ ኪዳነ ምሕረት፣ ድርሳነ ፍልሰታ፣ ድርሳነ በዓላት የዓመት፣ ዜና ነቢያት የሚነግር፣ መልክአ ሐዋርያት፣ መጽሐፈ ምንኩስና፣ የተሰኙት መጻሕፍት ማብራሪያ ይፈልጋሉ፡፡
                          I.    ጉባኤ ነቢያትን አላገኙሁትም፡፡ ምናልባት ግን የነቢያትን መልክእ የያዘ መጽሐፍ ሊሆን ይችላል፡፡
                         II.    ዜና አይሁድ፡- የታወቀው የዮሴፍ ወልደ ኮርዮን መጽሐፍ ነው
                       III.    በድራን፡- በድራን የሚባል አርመናዊ ስለ ጽድቅ ሥራና እምነት የጻፈው  ክታብ ነው፡፡ በፈረንሳይ ቤተ መጻሕፍት አንቶኒዮ ዲ. አባዲ ከሰበሰባቸው መጻሕፍት አንዱ ‹መጽሐፈ ምስጢራተ ባሕርያተ ነገር እም ቃለ ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ ወግዑዘ ዚአሁ በድራን ወልደ ሲማኦን ዘአርማንያ በልቡና መንፈስ ቅዱስ ጽዱቀ ቃል› ይላል፡፡(Abaddie 77, fol37v)
                       IV.    ፈረጅ፡- ስለዚህ መጽሐፍ እስካሁን ፍንጭ አላገኙሁም፡፡
                         V.    ገድለ ዮልዮስ፡- እስካሁን ገድሉን ለማግኘት አልተቻለም፡፡
                       VI.    ገድለ ማማስ፡- ማማስ በ13ኛው መክዘ በአኩስም አጠገብ በጉሎ ማከዳ የነበሩ መነኮስ ናቸው፡፡ አባ በጸሎተ ሚካኤል ከአምሐራ ተሰደው ወደ ትግራይ በሄዱ ጊዜ ከሌሎች መነኮሳት ጋር አግኝተዋቸዋል፡፡ ያረፉትም እዚያው ነው፡፡ 
                      VII.    ድርሳነ አብርሃም፡- አበ ብዙኃን አብርሃም በግእዝ የተጻፈ ገድል እንዳለው ይታወቃል፡፡ ድርሳነ አብርሃም ወሳራበግብጽ የተሰነው ድርሳን በቅዱስ ኤፍሬም የተጻፈ ሲሆን ከ15ኛው መክዘ ቀደም ብሎ ወደ ግእዝ ተተርጉሟል፡፡ በኢትዮጵያ የማይክሮ ፊልም ቤተ መጻሕፍት ውስጥ በቁጥር 1496የ14ኛው/15ኛው መክዘ ቅጅ ይገኛል፡፡
                     VIII.    መጽሐፈ ኅዳር፡- በኅዳር ወር ውስጥ የሚታሰቡ ሰማዕታትንና ጻድቃንን ታሪክ የያዘ፤ በኅዳር ወር እንዲነበቡ በሊቃውንት የተዘጋጁ ድርሳናትን ያሰባሰበ መጽሐፍ ነው፡፡ እኔ ያየሁት በመካከለኛው ዘመን (14ኛወ/15ኛው) የተጻፈውንና በፓሪስ የሚገኘውን ቅጅ ነው፡፡ በውስጡ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተአምራት ከኅዳር 7 ጀምሮ ይጽፋል፡፡
                        IX.    ያልተመለከተ ድጓ (ሙዛ ጋራ)፣ በጣና ቂርቆስ ውስጥ ሁለት ያልተመለከተ ድጓ ይገኛል፡፡ የገዳሙ ትውፊት እንደሚገልጠው ይህንን ድጓ በእጁ የጻፈው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡
                         X.    ድርሳነ ማርያም የዓመቱ፡- ድርሳነ ማርያም ብዙ ዓይነት ነው፡፡ የመጀመሪያው አቡነ ሰላማ መተርጉም በ14ኛው መክዘ ከዓረብኛ ወደ ግእዝ ያስተረጎሙት መጽሐፍ ነው፡፡ ‹ድርሳን በእንተ ዕበየ ወክብራ ለእግዝእትነ ማርያም - ስለ እመቤታችን ማርያም የክብሯን ታላቅነት የሚናገር ድርሳን› ይላል ሲጀምር፡፡ ሌላው ደግሞ በእስክንድያው ፓትርያርክ በአቡነ ቴዎፍለስ የተዘጋጀውና ወደ ግእዝ የተተረጎመው ነው፡፡ ‹ድርሳን በእንተ እግዝእትነ ማርያም በእንተ ቤተ ዘኀደረት ምስለ ፍቁር ወልዳ በደብረ ቁስቋም - በደብረ ቁስቋም ከተወደደው ልጇ ጋር ስላደረችበት ቤት የሚናገር የእመቤታችን ማርያም ድርሳን› ይላል፡፡
                        XI.    ድርሳነ ኪዳነ ምሕረት፣ ስለ ኪዳነ ምሕረት ከተዘጋጁት ድርሳናት አንዱ ነው፡፡ እመቤታችን ከልጇ ጋር ስለኖረችው ዘመንና በመጨረሻም ስለ ተቀበለችው ቃል ኪዳን በሰፊው ያትታል፡፡
                      XII.    ድርሳነ ፍልሰታ፡-  የእመቤታችንን ዕረፍትና ትንሣኤ የሚናገር ድርሳን ነው፡፡
                     XIII.    ድርሳነ በዓላት የዓመት፡- ይህን መጽሐፍ በሚገባ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ በዓመት የሚከበሩትን በዓላት የሚገልጥ መጽሐፍ ሳይሆን አይቀርም፡፡
                     XIV.    ዜና ነቢያት፡- ይህ መጽሐፍ የነቢያትን ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡  
                      XV.    መልክአ ሐዋርያት፡- የሐዋርያትን መልክእ ሰብስቦ የያዘ ነው፡፤ እኔ ያየሁት ከኤርትራ የተገኘውን ቅጅ ነው፡፡  
                     XVI.    መጽሐፈ ምንኩስና፡- በቤተ ክርስቲያን ከምንኩስና ጋር የተያያዙ አያሌ መጻሕፍት አሉ፡፡ ከምናውቃቸው ከሦስቱ መጻሕፍተ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ፣ አረጋዊ መንፈሳዊና ፊልክስዩስ) በተጨማሪ፡፡ ገነተ መነኮሳት፣ ሕንጻ መነኮሳት፣ነገረ መነኮሳት፣ ዜና አበው ክቡራን፣ ገድለ አበው ቅዱሳን፣ ቀኖና መነኮሳት፣ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ መጽሐፍ ምንኩስና የትኛውን መግለጡ እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ወይም በዚህ ስም የሚጠራ ሌላ መጽሐፍ ይኖራል፡፡
·         በአንድ በጣና ቂርቆስ ይህንን ያህል መጻሕፍት ከነበሩ በየገዳማቱ የነበሩትን መገመት ይቻላል፡፡

ያላገኘናቸው መጻሕፍት የት ሄዱ?

አንድም ተቃጥለዋል፤ አንድም ጠፍተዋል፤ እንድም ወደ ሌላ ገዳም ወይም ደብር ተዛውረዋል፤ ወይም ከሀገር ወጥተዋል፡፡

4 comments:

 1. ይህን ስላስነበብከን እግዚአብሔር ያክብርልን። አሁንም ቁጥራቸው ዳጎስ ያሉ ጥንታውያን መጽሃፍት online እየተቸበቸቡ እንዲሁም የትም እየወደቁ ይገኛሉ። "ከትናንት ብንዘገይ ከነገ እንቀድም!"

  ReplyDelete
 2. ''ያላገኘናቸው መጻሕፍት የት ሄዱ?

  አንድም ተቃጥለዋል፤ አንድም ጠፍተዋል፤ እንድም ወደ ሌላ ገዳም ወይም ደብር ተዛውረዋል፤ ወይም ከሀገር ወጥተዋል፡፡'' በጣም ነው እማመሰግን እንዳነብ ህሊናየ ይነቃቃል

  ReplyDelete
 3. ቃለ ህይወት ያሰማልን ………ስለ ድርሳነ ማርያም ይዘት ከተቻለ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ብትሰጠን መልካም ነው፡፡

  ReplyDelete