Thursday, February 15, 2018

ከማስታገሻው ወደ መፈወሻው

የሚፈቱትን ለመቀበል የወጣው ሕዝብ
መንግሥት መረራ ጉዲናን፣ እስክንድር ነጋን፣ አንዱዓለም አራጌን፣ በቀለ ገርባንና ሌሎችንም የፖለቲካ እስረኞችን መፍታቱ አንድ ርምጃ ወደፊት ነው፡፡ ቢያንስ ያንዣበበውን የሥጋት ደመና ይገፈዋል፡፡ የሀገሪቱንም ዜና ከ‹ታሠሩ› ወደ ‹ተፈቱ› ይቀይረዋል፡፡ የተስፋ ብልጭታም በሕዝቡ ላይ ይጭራል፡፡ ከታሠሩት ጋር አብሮ ለታሠረውም ወገን ትልቅ እፎይታ ነው፡፡ አብሮ ግን ሁለት ነገሮች ተያይዘውና ቀጥለው መምጣት አለባቸው፡፡

1.      መፈታት ያለባቸውን ወገኖች ጨርሶ መፍታት፡- የክስ ዐንቀጻቸው ምንም ይበል ምን በሕዝቡ ዘንድ በፖለቲካዊ ሐሳባቸውና ሥራቸው የታሠሩ መሆናቸው የሚታመንባቸው ብዙ ዜጎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ የሚታወቁ በመሆናቸው በየማኅበራዊ ሚዲያው ስማቸው ይነሣል፤ ሌሎቹ ደግሞ የሚጮኽላቸውም ሆነ የሚሰለፍላቸው የሌላቸው ናቸው፡፡ መንግሥት ሁለቱንም በመፍታቱ ያተርፋል እንጂ አይከስርም፡፡ አሁን እንደምናየው በሕዝቡ ላይ ሥጋት አንዣቧል፡፡ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንኳን ሳይቀር ፍርሐት እየነገሠ መሆኑን በቀላሉ ለማየት ይቻላል፡፡ መንገድ ሊዘጋ ነው፣ ነዳጅ ሊጠፋ ነው፣ እህል ሊወደድ ነው፣ ችግር ሊፈጠር ነው፣ የሚለው ወሬ ጉዳቱ ከኢኮኖሚው በላይ ነው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ለመላክ ሦስት ጊዜ ማሰብ እየጀመሩ ነው፡፡ እነዚህን ውጥረቶች ለማርገብ አንዱ መፍትሔ የታሠረውን የሕዝቡን ስሜት መፍታት ነው፡፡ ለዚህ አንዱ ርምጃ አሁን በተጀመረው መንገድ ሌሎችንም መፍታት ነው፡፡ 

ለምሳሌ የዋልድባ መነኮሳትን እንመልከት፡፡ የዋልድባን ጉዳይ ሙስሊም ከክርስቲያኑ ያውቀዋል፡፡ የተመሠረተባቸው ክስ ምንም ይሁን ምንም ከገዳሙ መሬትና ከስኳር ፋብሪካው ጋር የተያያዘው ጉዳይ ግን በሕዝቡ ልብ ውስጥ ቁርጥ ያለ መልስ ሳያገኝ እንደተንጠለጠለ ነው፡፡ እነዚህን አባቶች በየጊዜው ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት በማመላለስ፣ ልብሳችሁን አውልቁ አታውልቁ በመነታረክ፣ እየሰማናቸው ያሉትን አሳዛኝ ድርጊቶች በእነርሱ ላይ በማከናወን መንግሥት ፖለቲካዊም፣ኢኮኖሚያዊም፣ ሃይማኖታዊም ትርፍ አያገኝም፡፡ ጉዳያቸው የ35ሺ አድባራት፣ የ400ሺ ካህናት፣ የ1100 ገዳማት ጉዳይ ሆኗል፡፡ በየሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚያገለግሉ የ15 ሚሊዮን ወጣቶች ጉዳይ ሆኗል፡፡ ከዚያም አልፎ የመላ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ሆኗል፡፡ በዚህች ሀገር ጉዞ ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የማይነኩት የማኅበረሰብ ክፍል የለም፡፡ 98 በመቶ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖት ዋና ጉዳያችን ነው ማለታቸውን ጥናቶቹ እየነገሩን ነውና፡፡ ፍቱ፤ እነዚህን አባቶች ፍቱ፤ የሚጮህላቸው ቤተ ክህነት ባይኖራቸውም ፍቱ፣ ለሀገሪቱ ደኅንነት ስትሉ ፍቱ፤ የአቡነ ዘበሰማያት ጦር ሲወጋ እንጂ ሲወረወር እንደማይታይ በቅርቡ ከዋልድባ ጋር በተያያዘው ታሪካችን አይተናልና ፍቱ፤ ምናልባትም ይህ ሁሉ ድብልቅልቅ የእነርሱ ኀዘን ውጤት ይሆናልና ፍቱ፤
2.     ቀጥሎስ? ቀጣይ የፖለቲካ ሥራዎችን ለሀገርና ለወገን በሚጠቅም፣ ማንንም በማያገል፣ ያለፉ ችግሮችን በሚፈታ፣ ሌሎች ችግሮችን በማያስከትልና ተአማኒና ግልጽ በሆነ መንገድ ማከናወን ነው ከባዱ ሥራ፡፡ እያሠሩ መፍታት ለችግሩ ማስታገሻ እንጂ መፍትሔ አይሆንም፡፡ የሕዝቡ እንቅስቃሴ አሁን ባለው መንገድ ከቀጠለም ወደ አንድ፣ ሁሉን አስማሚና አሳታፊ ወደሚሆን ግብ መድረሱ ያጠራጥራል፡፡ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ሆነው ለሁሉም የማይጠቅም ነገር ከመከሠቱ በፊት መሥራት ያለብንን ነገር መሥራት ያለብን አሁን ነው፡፡ ‹ማንም ሊሠራባት የማይችል ሌሊት ትመጣለች› እንደተባለው እንዳይሆን፡፡ እንደ ሠፈር ልጅ ብሽሽቅ፣ እንደ ጎረምሳ ትንቅንቅ፣ እንደ እንደ ጅል እየሠሩ ማፍረስ፣ እንደ እብድ ያለ ውጤት መገሥገሥ አያዋጣም፡፡ ኢሕአዴግ ሁልጊዜ እንደሚተርከው የናዳው ምሳሌ እየተተገበረ ነው፡፡ ናዳው እየወረደ ነው፡፡ ወሳኙ ከናዳው ለማምለጥ መሮጥ አይደለም፡፡ የሚሮጠው ሰው ናዳውን በሚቀድም ፍጥነት ካልሮጠ መሮጡ ብቻዉን አያድነውም፡፡ ናዳው ይደርስበታልና፡፡ የሚያዋጣው ከናዳው ፍጥነት በፈጠነ ፍጥነት ለመሮጥ መቻል ነው፡፡
ከማስታገሻው ወደ መፈወሻው እንሂድ፡፡ ሀገሪቱ ታማለች፡፡ የሚያስፈልጋት ፍቱን መድኃኒት እንጂ ማስታገሻ (pain killer) አይደለም፡፡ ነገሩ ካለቀ በኋላ መድኃኒቱን ብናመጣው አይጠቅመንም፡፡
አንጀቴ ተቆርጦ ከሆዴ ከወጣ
እንግዲህ ሐኪሙ ምን ሊቀጥል መጣ
ይሆናል ነገሩ፡፡

32 comments:

 1. ፍቱ፤ እነዚህን አባቶች ፍቱ፤ የሚጮህላቸው ቤተ ክህነት ባይኖራቸውም ፍቱ፣ ለሀገሪቱ ደኅንነት ስትሉ ፍቱ፤ የአቡነ ዘበሰማያት ጦር ሲወጋ እንጂ ሲወረወር እንደማይታይ በቅርቡ ከዋልድባ ጋር በተያያዘው ታሪካችን አይተናልና ፍቱ፤ ምናልባትም ይህ ሁሉ ድብልቅልቅ የእነርሱ ኀዘን ውጤት ይሆናልና ፍቱ፤

  አንጀቴ ተቆርጦ ከሆዴ ከወጣ
  እንግዲህ ሐኪሙ ምን ሊቀጥል መጣ
  ይሆናል ነገሩ፡፡

  ReplyDelete
 2. እውነት ነው መነኮሳት አባቶቻችን ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጣላቸው ባይኖርም የሰላም ሰልፍ ማሰለፍ ይችላሉና ይፈቱልን... የሁላችንም ጥያቄ ነው አባቶቻችን ያለአበሳቸው ከገቡበት መከራ ይውጡ ... ይብቃቸውና የሀገራችን መከራ እንዲያበቃ ወደ ፈጣሪያቸው ይማልዱልን

  ReplyDelete
 3. የቅዱስ ዻውሎስና ሲላስ አምላክ አባቶቻችን መነኮሳትን ይፍታልን

  ReplyDelete
 4. ልክ ነው፤ ይፈቱልን!የዋልድባ መነኮሳትም ይፈቱልን!

  ReplyDelete
 5. ልክ ብለዋል መምህር፤ የአቡነ ዘበሰማያትን ጦር የተወጉት እነ መለስ እና አባ ጳውሎስ ከሚወዷት ዓለም አሰናበታቸው፤ እንዲሁም በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍላተ ሀገር ነውጥ እንዲነሣ አድርጎ ለቀጪዎቻቸው ዕረፍት ነሳቸው። ስለዚህ ወይ የዋልድባ መናኞችን በመፍታት የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ግንባታ በማቋረጥ ለራሳችሁ ሰላም አግኙ አልያም ሰላማችሁን አጥታችሁ ከማይገፋው ጋር እየተጋፋችሁ በሥጋዊ ሥልጣንና በጦር መሣሪያችሁ እየተመካችሁ እንደተተራመሳችሁ ቆዩ፤ ምርጫው የእናንተ የፖለቲካ ሰዎች ፣ የአባቶቻችሁ ቀጪና ገዳዮች ነው። ልቡና ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 6. you are correct ዲ/ን ዳንኤል

  ReplyDelete
 7. ፍቱ፤ እነዚህን አባቶች ፍቱ፤ የሚጮህላቸው ቤተ ክህነት ባይኖራቸውም ፍቱ፣ ለሀገሪቱ ደኅንነት ስትሉ ፍቱ፤ የአቡነ ዘበሰማያት ጦር ሲወጋ እንጂ ሲወረወር እንደማይታይ በቅርቡ ከዋልድባ ጋር በተያያዘው ታሪካችን አይተናልና ፍቱ፤ ምናልባትም ይህ ሁሉ ድብልቅልቅ የእነርሱ ኀዘን ውጤት ይሆናልና ፍቱ፤

  ReplyDelete
 8. ፍቱ፤ እነዚህን አባቶች ፍቱ፤ የሚጮህላቸው ቤተ ክህነት ባይኖራቸውም ፍቱ፣ ለሀገሪቱ ደኅንነት ስትሉ ፍቱ፤ የአቡነ ዘበሰማያት ጦር ሲወጋ እንጂ ሲወረወር እንደማይታይ በቅርቡ ከዋልድባ ጋር በተያያዘው ታሪካችን አይተናልና ፍቱ፤ ምናልባትም ይህ ሁሉ ድብልቅልቅ የእነርሱ ኀዘን ውጤት ይሆናልና ፍቱ፤

  ReplyDelete
 9. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 16, 2018 at 10:54 PM

  ሰሞኑን በተለየዩ ማህበራዊ መገናኛዎችና ገጾች የዋልድባ አባቶች ይፈቱ የሚሉ መልዕክቶች በመጠኑም ቢሆን እየታዩ ነው። ልጆች አባቶቻቸውን ማስታወሳቸውና ስለ እነርሱ ድምጻቸውን ማሰማታቸው ተገቢ ነው። እኔ ግን የተለዩ ዕይታዎች አሉኝ።

  1. እኒህ አባቶች በመታሰራቸው በብዙ ተጠቅመው እና በቅተውስ ከሆነ ማን ያውቃል? ይህ ከሆነ ደግሞ መፈታቱን የሚፈልጉት አይመስለኝምና እስኪ በቅርብ ያላችሁ ሄዳችሁ ጠይቋቸው።፡ታዲያ ብቃት ላይ መድረሳቸውን ይነግሩናል ብላችሁ አትጠብቁ፤ መፈታት ይፈልጉ እንደሆነ ብቻ መጠየቁ ይበቃል።
  2. ይህ ሁሉ ንቅናቄና የተወሰኑ እስረኞች መፈታት የእነርሱ ፀሎት ውጤት እንደሆነስ ማን ያውቃል? ከእግዚአብሔር በስተቀር።
  3. በእስር ቤትስ ዝም ብለው የሚቀመጡ ይመስላችኋል? ትምህርተ ሃይማኖትን አስተምርው ስንቱን እስረኛ አጥምቀው ወደ ክርስትና መልሰው ይሆን? ስንቱንስ ለንስሀ አብቅተው ይሆን?

  ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል የሚቻልህ ከሆነ እና የታሰሩትን የዋልድባ አባቶች መጎብኘት የሚቻል ከሆነ እባክህ አነጋግራቸውና ያሉበትን ሁኔታ አሳውቀን። ሌሎችም የዚህ ገጽ ታዳሚዎች እንዲሁ። ከላይ ካነሳኋቸው ጥያቄዎች የአንዱም መልስ አዎንታዊ ከሆነ እንደ እኔ፣ እንደ እኔ በዚያው ቆይተው አገልግሎታቸውን ቢቀጥሉ ይበጃል እላለሁ። መነኮሳት መሆናቸውን አትርሱ፤ ከዚህ ዓለም አይደሉም። እግዚአብሔር አምላክ እስር ቤቱን ገዳም አድርጎላቸው ከሆነስ? በእምነት የማይቻል የለም፤ እኔ አምናለሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሠይፈ ገብርኤልFebruary 21, 2018 at 11:42 PM

   ከላይ ያቀረብኳቸውን መላ ምቶችን በጥቂቱ ሊደግፍ የሚችል ጉዳይ ሪፖርተር አስነብቦናል:: https://www.ethiopianreporter.com/article/7582
   "...አባ ገብረየሱስ ኪዳነ ማርያምና አባ ገብረ ሥላሴ ወልደ ሃይማኖት የተባሉት ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት አቤቱታ፣ በማረሚያ ቤቱ የተሰፋ ዩኒፎርም ‹‹አንለብስም›› በማለታቸው ሲታሰሩ ከለበሱት ልብስ ሌላ መቀየሪያ ልብስ እንዳይገባላቸው በመከልከላቸው፣ ፍርድ ቤቱ መፍትሔ እንዲሰጣቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡..."

   "እኛም እንደተፈቱት እስረኞች ልንፈታ ይገባል" የሚል ጥያቄ አለማቅረባቸው አስደምሞኛል::

   እግዚአብሔር አምላክ አባቶቻችንን በቸርነቱ ይጎብኝልን!

   Delete
 10. እነዚህን አባቶች ፍቱ፤ የሚጮህላቸው ቤተ ክህነት ባይኖራቸውም ፍቱ፣ ለሀገሪቱ ደኅንነት ስትሉ ፍቱ፤ የአቡነ ዘበሰማያት ጦር ሲወጋ እንጂ ሲወረወር እንደማይታይ በቅርቡ ከዋልድባ ጋር በተያያዘው ታሪካችን አይተናልና ፍቱ፤ ምናልባትም ይህ ሁሉ ድብልቅልቅ የእነርሱ ኀዘን ውጤት ይሆናልና ፍቱ፤

  ReplyDelete
 11. Wooooooooooooooooooow excellent view Dani

  ReplyDelete
 12. መነኮሳት አባቶቻችን ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጣላቸው ባይኖርም የሰላም ሰልፍ ማሰለፍ ይችላሉና ይፈቱልን... የሁላችንም ጥያቄ ነው

  ReplyDelete
 13. dykone danale melkame bilhale menewe slamawe selfe yemiyaderge yelacheme alesa yaweme lemederaweyane yayedele lemetershawe yegebagne seme elete elete bitekersetiane yetaserutene asfetalene tele yelene ngregene egziabwehare serawne yeme serabetena yesewe gize yelayayalena ahuneme yetaserutene asfetalene belne eylekesenenew

  ReplyDelete
 14. dykone danale melkame bilhale menewe slamawe selfe yemiyaderge yelacheme alesa yaweme lemederaweyane yayedele lemetershawe yegebagne seme elete elete bitekersetiane yetaserutene asfetalene tele yelene ngregene egziabwehare serawne yeme serabetena yesewe gize yelayayalena ahuneme yetaserutene asfetalene belne eylekesenenew

  ReplyDelete
 15. dykone danale melkame bilhale menewe slamawe selfe yemiyaderge yelacheme alesa yaweme lemederaweyane yayedele lemetershawe yegebagne seme elete elete bitekersetiane yetaserutene asfetalene tele yelene ngregene egziabwehare serawne yeme serabetena yesewe gize yelayayalena ahuneme yetaserutene asfetalene belne eylekesenenew

  ReplyDelete
 16. እነዚህን አባቶች ፍቱ፤ የሚጮህላቸው ቤተ ክህነት ባይኖራቸውም ፍቱ፣ ለሀገሪቱ ደኅንነት ስትሉ ፍቱ፤ የአቡነ ዘበሰማያት ጦር ሲወጋ እንጂ ሲወረወር እንደማይታይ በቅርቡ ከዋልድባ ጋር በተያያዘው ታሪካችን አይተናልና ፍቱ፤ ምናልባትም ይህ ሁሉ ድብልቅልቅ የእነርሱ ኀዘን ውጤት ይሆናልና ፍቱ፤

  ReplyDelete
 17. ከማስታገሻው ወደ መፈወሻው እንሂድ፡፡ ሀገሪቱ ታማለች፡፡ የሚያስፈልጋት ፍቱን መድኃኒት እንጂ ማስታገሻ (pain killer) አይደለም፡፡ ነገሩ ካለቀ በኋላ መድኃኒቱን ብናመጣው አይጠቅመንም፡፡

  ReplyDelete
 18. ከማስታገሻው ወደ መፈወሻው እንሂድ፡፡ ሀገሪቱ ታማለች፡፡ የሚያስፈልጋት ፍቱን መድኃኒት እንጂ ማስታገሻ (pain killer) አይደለም፡፡ ነገሩ ካለቀ በኋላ መድኃኒቱን ብናመጣው አይጠቅመንም፡፡
  አንጀቴ ተቆርጦ ከሆዴ ከወጣ
  እንግዲህ ሐኪሙ ምን ሊቀጥል መጣ
  ይሆናል ነገሩ፡፡

  ReplyDelete
 19. እነዚህን አባቶች ፍቱ፤ የሚጮህላቸው ቤተ ክህነት ባይኖራቸውም ፍቱ፣ ለሀገሪቱ ደኅንነት ስትሉ ፍቱ፤ የአቡነ ዘበሰማያት ጦር ሲወጋ እንጂ ሲወረወር እንደማይታይ በቅርቡ ከዋልድባ ጋር በተያያዘው ታሪካችን አይተናልና ፍቱ፤ ምናልባትም ይህ ሁሉ ድብልቅልቅ የእነርሱ ኀዘን ውጤት ይሆናልና ፍቱ፤

  ReplyDelete
 20. Dn Daniel, thank you for bringing us the truth. I don’t live in Ethiopia and I was looking for a good balanced voice to get information from home and I see you have that voice. I will continue to pray for our country Ethiopia and the monks imprisoned. Please continue to write because there is many of us who are cautious to listen to any side as it seems to be filled with hate at the moment. That is not the Ethiopia I know and love. ETHIOPIA LE ZELALEM TENUR.

  ReplyDelete
 21. IT IS A DIRECTLY FORWARDED AND A GREAT MESSAGE. HOWEVER, IN MY LIMITED UNDERSTANDING, THEY ARE LACKEY RESULTED FROM THE REWARD THEY WILL GET FROM THE HEAVEN.AS WE SEE, THE REWARD THE POLITICIAN GET COMPARATIVELY FROM THE HERMITS OF WALDIBA IT WILL BE INFERIOR.

  ReplyDelete
 22. እነዚህን አባቶች ፍቱ፤ የሚጮህላቸው ቤተ ክህነት ባይኖራቸውም ፍቱ፣ ለሀገሪቱ ደኅንነት ስትሉ ፍቱ፤ የአቡነ ዘበሰማያት ጦር ሲወጋ እንጂ ሲወረወር እንደማይታይ በቅርቡ ከዋልድባ ጋር በተያያዘው ታሪካችን አይተናልና ፍቱ፤ ምናልባትም ይህ ሁሉ ድብልቅልቅ የእነርሱ ኀዘን ውጤት ይሆናልና ፍቱ፤

  ReplyDelete
 23. እድሜና ጤና ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት

  ReplyDelete