Monday, February 12, 2018

የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ (ክፍል ስድስት እና የመጨረሻው)

በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ ይህንን ይጫኑ
የጌታቸው ኃይሌ መከራከሪያ
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ዘርአ ያእቆብን በተመለከተ በቅርቡ ሁለት ጽሑፎችን አውጥተዋል፡፡ የመጀመሪያው በ2006 ዓ.ም. ባሳተሙት ‹ሐተታ ዘዘርአ ያእቆብ› በሚለው መጽሐፋቸው መግቢያ ላይ የሰጡት ትንታኔ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በ2017 ባወጡት Ethiopian Studies in Honor of Amha Asfaw በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ያቀረቡት ጥናት ነው፡፡
ጌታቸው ኃይሌ ዘርአ ያእቆብ በካቶሊክ ሚስዮናውያን ተጽዕኖ ውስጥ የወደቀ፣ ፍልስፍናውንም በአብዛኛው ከእነርሱ የወሰደ ኢትዮጵያዊ ዳዊት ደጋሚ ደብተራ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ለዚህ ድምዳሜ መድረሻ ያነሷቸው ነጥቦች አሉ፡፡ አንድ በአንድ እንያቸው፡፡
1.      ኡርቢኖ የሐተታ ደራሲ ከሆነ ለምን በግእዝ ይጽፈዋል? ምክንያቱም የጻፈው ለኢትዮጵያውያን ነው እንዳንል ሁለቱንም ቅጅዎች ወደ ፈረንሳይ ልኳቸዋል፡፡ በሐተታዎቹ ውስጥ ያሉት ሐሳቦች ደግሞ ለአውሮፓውያን አዲስ አይደሉም፡፡
2.     የቅጅ ቁጥር 234 በኡርቢኖ የእርማት ሥራ ተሠርቶበታል፡፡ ኡርቢኖ የራሱን ሥራ ለምን ያርመዋል?
3.     ሐተታ ኢትዮጵያዊውን መዝሙረ ዳዊት በሚገባ በሚያውቅ ሰው የተዘጋጀ ነው፡፡ ‹በዳዊት ደጋሚ ደብተራ›፤ መዝሙረ ዳዊት የዕለት የጸሎት መጽሐፉ ካልሆነ በዚህ መጠን አይጠቅሰውም፡፡ ይህ ደግሞ ዳዊትን በቃላቸው የሚይዙት የኢትዮጵያውያን ልማድ ነው፡፡
4.     ወለተ ጴጥሮስን እንዴት በበጎ ያነሳታል?
5.     ኡርቢኖ ሊያርመው የተነሣው የዘመን አቆጣጠር
6.     ‹ፋሲለደስ› እና ‹ወልደ ፋሲለደስ› በሚሉት ስሞች ላይ የሠራው ስሕተት
7.     ሌሎች ዝርዝር ማስረጃዎች
ኡርቢኖ ጽሑፎቹን ደጋግሞ የማረም ጠባይ እንዳለው በቅርጣግና ሌሊቶች የትርጉም ሥራው ላይ ታይቷል፡፡ ከማርች 1852 ጀምሮ የኢትዮጵያን ሊቃውንት ሊያስደስት የሚችል ቅጅ ለማውጣት የተለያዩ ቅጅዎችን አዘጋጅቷል፡፡ ኡርቢኖ አንዱን ቅጅ (215) የላከው ኢትዮጵያ ሆኖ ሲሆን ሌላኛውን (234) የላከው ግን ካይሮ ሆኖ ነው፡፡ ለምን? ኡርቢኖ ካይሮ የገባው ከኢትዮጵያ ተባርሮ ነው፡፡ አንደኛውን ቅጅ ለዲ. አባዲ የላከው ከዲ. አባዲ ገንዘብ ለማግኘትና የዕውቀቱን ልክ ለማሳየት ነው፡፡ ለዚህም ደብዳቤው ይነግረናል፡፡ ሌሎቹን ቅጅዎች ያዘጋጃቸው ግን ለኢትዮጵያውያን አገልግሎት ነበር፡፡ እንዳጋጣሚ ግን ከሀገር ሲባረር ይዞት ሄደ፡፡ በዚያውም ካይሮ ላይ የመመለስ ሐሳቡ የማይሳካ ሲመስለው ለዲ. አባዲ ላከለት፡፡ የዚህ ዓላማም ገንዘብ ማግኘት እንደሚሆን መገመት ይቻላል፡፡ ሁለቱም ወደ አውሮፓ የተላኩት በተለያየ ዓላማ ነው፡፡ የመጀመሪያው ለዲ. አባዲ አዳዲስ መዛግብት የማግኘት ፍላጎቱን ለማርካት፤ ሁለተኛው ደግሞ ካይሮ ላይ ተስፋ ሲቆርጥ የላካቸው ናቸው፡፡
‹ዘርአ ያእቆብ› ከዳዊት በላይ እንደማያውቅ ቀደም ብለን አይተናል፡፡ ይህ ግን ዘርአ ያእቆብ ተማርኩ ካለው የመጻሕፍት ትምህርትና ‹ባልንጀሮቼ በዕውቀቴ የተነሣ ቀኑብኝ› ከሚለው ገለጣው ጋር የሚጣረስ ነው፡፡ ዘርአ ያእቆብ ለምን በዚህ መጠን መዋሸት ፈለገ? ደግሞስ ያንን ያህል ‹የሚፈላሰፍ› ሰው እንዴት በዕውቀት ይህንን ያህል ደከመ? በውሸትስ ይህንን ያህል በረታ? እንፍራንዝስ ቁጭ ብሎ ምንድን ነው ሲያስተምር የነበረው? የማያውቀውን መጽሐፍ ነው ሲያስተምር የነበረው? እንደ እኔ ግምት እነዚያን የዳዊት መዝሙራት ያስገቡለት አብረውት የሠሩት ደባትር ናቸው፡፡ እርሱም በኋላ ጥቅሶቹን በኅዳግ ጨምሮባቸዋል፡፡

ሐተታ ዘርአ ያእቆብ ውስጥ ወለተ ጴጥሮስ የተባለች ሴት ታሪክ አለ፡፡ ወለተ ጴጥሮስ የሀብቱ የመጀመሪያ ልጅ የወልደ ሚካኤል ሚስት ናት፡፡ ዘርአ ያእቆብ በደግነቷ ያነሣታል፡፡ ሁለተኛ ስሟ ፋንታዬ መሆኑን ይገልጣል፡፡ አንዱ የዓለም አንዱ የክርስትና ስም መሆኑ ነው፡፡ ‹ኡርቢኖ የሐተታ ደራሲ ቢሆን ኖሮ ወለተ ጴጥሮስን በበጎ አያነሣትም ነበር፡፡ ምክንያቱም ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ የካቶሊክ ሚስዮናውያንን በመቃወም የተጋደለች ቅድስት ናትና› የሚል ነው የጌታቸው ኃይሌ አንዱ መከራከሪያ፡፡ ሐተታ ላይ ወለተ ጴጥሮስ የተሰኘችው ገጸ ባሕርይ ምንም እንኳን በበጎ የተሳለች ብትሆንም ‹ምንኩስናን እየተቸ ጋብቻን የሚያደንቀው› ዘርአ ያእቆብ ግን ወለተ ጴጥሮስን በምትታወቅበት ተጋድሎዋ ሳይሆን በጋብቻዋ እንድትታወቅ ነው የሳላት፡፡ ይህ ወለተ ጴጥሮስን ማክበር አይደለም፡፡ እንዲያውም ኡርቢኖ(ዘርአ ያእቆብ) የተጠቀማቸውን ስሞች እንድንገምት የሚያደርገን ጥቆማ አለው፡፡ ኡርቢኖ ለድርሰቱ የተጠቀማቸው ስሞች በአካባቢው ወይም በታሪክ አጋጣሚ የሚያውቃቸውን ስሞች ነው ማለት ነው፡፡ ወለተ ጴጥሮስን የተጠቀመው በታሪክ ስለሚያውቃት ነው፡፡
‹ወልዱ ፋሲለደስ› እና ‹ወልደ ፋሲለደስ›፡- በቁጥር 234 ላይ ‹ወነግሠ ወልዱ ፋሲለደስ› ሲል በቁጥር 215 ላይ ግን ‹ወነግሠ ወልደ ፋሲለደስ› ይላል፡፡ ይህም በፋሲል ዘመን የተጻፈውን መጽሐፍ የኋላው ሰው ሲያርም የተፈጠረ ነው › ይላሉ ፕሮፌሰር ጌታቸው፡፡ ቁጥር 215 ኡርቢኖ አሻሽሎ ሊያወጣው የተዘጋጀ ቅጅ መሆኑን ቀድም ብለን አይተናል፡፡ የቤተ ልሔሙ ደብተራ ነው ታሪኩን ስለሚያቀው ‹ወነግሠ ወልዱ ፋሲለደስ - ልጁ ፋሲለደስም ነገሠ› ያለው፡፤ ኡርቢኖ አርሞ ሲመልሰው ግን ‹ወልደ ፋሲለደስ› አለው፡፡ በቁጥር 215 ይህን ያገኘነውም ለዚህ ነው፡፡ በማኅደረ ማርያም የተጻፈው(መስከረም 7 ቀን 1778 ዓም.) የደጃዝማች ኃይሉ ታሪከ ነገሥት ‹ወነግሠ ወልዱ ፋሲለደስ› ነው የሚለው፡፡  አንደኛው ቅጅም በፈረንሳይ በቁጥር 143 ተመዝግቦ የሚገኝ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊው  ደብተራ አስተካክሎ የገለበጠውን ነው ኡርቢኖ ሲያርም ‹ወልደ ፋሲለደስ› ያለው፡፡
በሐተታ ዘርአ ያእቆብ ቅጅ ቁ. 215 ላይ ‹አመ ፲፩ ለጥቅምት በዕለተ ሰኑይ  እም ልደተ ክርስቶስ ፲፻ወ፮፻ወ፴ወ፩› የሚል አለ፡፡ ዳ. ኡርቢኖ የቀዳው ነው ተብሎ በሚታመነው በቅጅ ቁ. 234 ላይ ጥቅምት 10 ቀን ይላል፡፡ መጀመሪያ ሰኞን ወደ ማክሰኞ ሊለወጥ እንዳሰበ እርማቱ ያሳያል፤ በኋላ ሰኞን በቦታው መልሶ ጥቅምት 11ን ጥቅምት 10 አድርጎታል፡፡ ለምን? ኡርቢኖ በነበረበት ዘመን ጥቅምት 11ና ሰኞ ሊገጣጠሙ አልቻሉም፡፡ ድርሰቱ በተጻፈበት በ1631 ግን ጥቅምት 11 ቀን ሰኞ ነበር የዋለው፡፡ ይህም ድርሰቱ የተጻፈው ከኡርቢኖ ዘመን በፊት 200 ዓመት ቀድሞ መሆኑን ያሳያል፡፡ ወርቄና ኡርቢኖም የተለያዩ መሆናቸውን ያመለክታል› ይላሉ ጌታቸው ኃይሌ፡፡
በዘርአ ያእቆብ ድርሰት ውስጥ ሰባት ቦታዎች ላይ ዘመናት ተገልጠዋል፡፡
ሀ. የተወለደበት 1592
ለ. ልጁን የወለደበት፡- ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 1631
ሐ. ከሦስት ዓመት በኋላ አቡነ እፎንስ ወደ ሀገሩ ሄደ (1626/7 ዓም)
መ. በ1635 ረሃብ ሆነ
ሠ. ከአንድ ዓመት በኋላ ሀብቱ ሞተ(ምናልባት በ1636)
ረ. ፋሲለደስ ሞቶ ዮሐንስ ሲነግሥ ወርቄ 68 ዓመት ሲሞላው ተጻፈ፡፡ (ዮሐንስ1ኛ የነገሠው በ1660) ነው፡፡
ዘርአ ያእቆብ ዘመንን የጻፈው በሦስት መንገድ ነው፡፡
1.    ቀንና ዓመቱን በመግለጥ
2.   ዓመቱን ብቻ በመግለጥ
3.   ዓመቱን ባለመግለጥ፡፡
ቀኑንና ዘመኑን የገለጠው አንድ ቦታ ብቻ ሲሆን ልጁ የተወለደበትን ቀን ሲጠቅስ ነው፡፡ በዘርአ ያእቆብ ሕይወት ውስጥ የልጁን ያህል ቦታ የሚኖራቸው ሦስት ክስተቶችን እናንሣ
1.      በጣም  የሚወደውና ያስጠጋው የእንፍራንዝ ሰው ሀብቱ የሞተበት
2.     በትምህርቱ የተማረከበት ካቶሊካዊው አልፎንዙ ሜንዴዝ የተባረረበትና
3.     ራሱ ዘርአ ያእቆብ ያረፈበት፡፡
ዘርአ ያእቆብ ሀብቱን በጣም እንደሚወደውና እንደሚተማመንበት በሐተታው ላይ አስፍሯል፡፡ የዚህን ሰው ዘመነ ዕረፍት ግን ‹ከአንድ ዓመት በኋላ ሀብቱ ሞተ› ብሎ ብቻ ያልፈዋል፡፡ ዘመኑን እንኳን አላሠፈረውም፡፡ አልፎንዞ ሜንዴዝ የሄደበትንም ዘመን ‹ከሦስት ዓመት በኋላ አቡነ እፎንስ ወደ ሀገሩ ሄደ› ይላል፡፡ ዘመኑን ለምንድን ነው በግልጥ መግለጽ ያልፈለገው? ሜንዴዝ የተባረረው በ1626 ዓም ነው፡፡ የዘርአ ያእቆብ አገላለጥ ግን ያምታታል፡፡ በርግጥ ሦስት ዓመት የሚለው ሱስንዮስ ከሞተበት ዘመን ቆጥሮ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን በመካከል ልጁ የተወለደበት ዘመን 1631 ስለተጠቀሰ ያምታታል፡፡ በዘመኑ የነበረ ሰው ከሆነ እንዴት በዝርዝር መግለጥ አልፈለገም?
ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ ወልደ ሕይወት የዘርአ ያእቆብ ደቀ መዝሙር ሆኖ ሳለ ‹ይህ ታላቅ ፈላስፋ› ያረፈበትን ቀንና ዘመን አለመግለጡ ነው፡፡ ዘርአ ያእቆብ የተወለደበትን ዘመን ጠቅሷል፡፡ እንደ ልጁ ወሩንና ቀኑን ባይነግረንም፡፡ ደቀ መዝሙሩ ወልደ ሕይወት ግን ያረፈበትን ዘመኑንም፣ ቀኑንም ዕለቱንም አይነግረንም፡፡ ዘመኑን የምናውቀው ከተወለደበት ዘመን ያረፈበትን እድሜ 68 ዓመት ጨምረን ነው፡፡
ኡርቢኖ(ዘርአ ያእቆብ) ትዳርና ልጅ መውለድን በጽኑ የሚከራከርለት ጉዳይ ነው፡፡ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናት አያገቡም፡፡ ኡርቢኖ ከዚህ አፈንግጦ ጎጆ ቀልሶ ጋይንት ውስጥ ይኖር ነበር፡፡ ትዳርና ልጅም ነበረው፡፡ ለዚህ ነው ከሁሉም ዘመናት ይልቅ ልጅ የወለደበትን ዘመን የጠቀሰው፡፡ እዚህ ላይ ዋናው ጥያቄ ለምን በኋላ ሊያርመው ፈለገ? የሚለው ነው፡፡ ለኡርቢኖ ታሪኩን የጻፉለት ደባትር ከቀድሞ የታሪክ መዝገብ የአንዱን የልደት ቀን እንዲስማማ አድርገው መርጠውለታል፡፡ የልጁን የትውልድ ቀን እርሱ ሳይሰጣቸው አይቀርም፤ ያንን ከባሕረ ሐሳቡ ጋር ያስማሙት ግን የቤተ ልሔምና ደብረ ታቦር አካባቢ ልውጥ ደባትር ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ የልጁን ልደት በዝርዝር ሊጽፈው መፈለጉም ከኡርቢኖ ሐሳብ ጋር የሚሄድ ነው፡፡ ጋብቻና ልጅ መውለድን አጥብቆ ይፈልግ ነበርና፡፡ ደባትሩ ባሕረ ሐሳቡን ስለሚያውቁት አልተሳሳቱም፡፡ እርሱ ግን የባሕረ ሐሳብ ዕውቀቱ ስለሌለው ሊያርመው ፈልጎ ነበር፡፡ ዛሬ በፓሪስ ቤተ መጻሕፍት የሚገኙትን ኡርቢኖ የሰበሰባቸውን መጻሕፍት ስናይ የባሕረ ሐሳብን ነገር የሚያስረዱ ነገሮችን አናገኝም፡፡ የሌሎችን ቀናት ግን ደባትሩ ከሚያውቋቸው መዛግብት እያመሳከሩ ሞልተዋቸዋል፡፡
በነገራችን ላይ ኡርቢኖ ድርሰቱን ካገኘበት ዘመን በኋላ በድርሰቱ ላይ የነበሩትን ለውጦች ስንመለከት ድርሰቱ ሲሻሻል እንደኖረ ያሳየናል፡፡ ሁለቱ ‹ቅጅዎች›(215 እና 234) ቅጅዎች ሳይሆኑ ዓይነቶች (Versions) ናቸው፡፡
1.  በመስከረም 1852 በኢትዮጵያ ያልተለመደ ዓይነት መጽሐፍ ማግኘቱን ለአንቶኒዮ ዲ. አባዲ ገለጠ፡፡ያገኘውም ከአንድ የዋድላ ደብተራ መሆኑንና ስሙንም ‹‹ሐተታ ያዕቆብ› ወይም ‹መጽሐፈ ያዕቆብ ልንለው እንችላለን፡› ሲል ገለጠ፡፡
2.     በየካቲት 1853 መጽሐፉ በእጁ መግባቱን ገለጠ፡፡ መጽሐፉንም ተርጉሞታል፡፡ ይህንንም እርሱ ራሱ በእጁ ገልብጦታል፡፡ ይህም ቅጅ ቁጥር 234
3.     ኡርቢኖ ሐተታ ዘርአ ያእቆብን በብራና ተጽፎ ማግኘቱን ይገልጣል፡፡ ይህም ቅጅ ቁጥር 215 ነው፡፡
ኡርቢኖ የላካቸው ሁለቱ ቅጅዎች አንዱ ከደብረ ታቦር (234) አንደኛው ደግሞ ከካይሮ(215) የተላኩ ናቸው፡፡ በቅጅዎቹ ላይ በሂደት ሁለት ዓይነት ሥራ እንደተሠራባቸው የእጅ ጽሑፎቹ ያሳያሉ፡፡ የመጀመሪያው የተሻለ ቅጅ ለማግኘት የተሠራው የማሻሻያ ሥራ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለፕሮፓጋንዳ ዓላማ እንዲውል የተሠራው ማሻሻያ ነው፡፡ ሁለቱን ተራ በተራ እንያቸው፡፡ በሐተታ ዘርአ ያእቆብ በክፍል 7 ሁለቱ ቅጅዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንመልከት፡፡ በዚህ ረገድ የምጠቅሰው አናይስ ወይን( Anaïs Wion) ያቀረበችውን ነው[1]፡፡
         234 ክፍል 7
     215 ክፍል 7
1.  ወሐለይኩ፡ወእቤ፡በይነ፡ምንት፡እግዚአብሔር፡የኀድግ፡ሰብአ፡ሐሳውያነ፡ያስሕትዎሙ፡ለሕዝቡ ዚአሁ[2] በስመ፡ ዚአሁ፡
ወሐለይኩ፡ወዕቤ፡በይነ፡ምንት፡እግዚአብሔር፡የኃድግ፡ሰብአ፡ሐሳውያነ፡ያስሕትዎሙ፡ለሕዝበ፡ዚአሁ
2. እግዚአብሔር፡ወሀቦሙ፡ለኵሉ፡ለለ፩፩ልቡና፡ከመ፡ያእምሩ፡ጽድቀ፡ወሐሰተ፡ወጸገዎሙ፡ኅርየተ፡በዘየኃርዩ፡ጽድቀ፡አው፡ሐሰተ፡በከመ፡ፈቀዱ፡ 
እግዚአብሔር፡ወሀቦሙ፡ለኵሉ፡ለለ፩፩ልቡና፡ከመ፡ያእምሩ፡ጽድቀ፡ወሐሰተ፡ወጸገዎሙ፡ኅርየተ፡በዘየኅርዩ፡ጽድቀ፡አው፡ሐሰተ፡በከመ፡ፈቀዱ፡፡
3. ወለእመ፡ንፈቅድ፡ጽድቀ፡ንሕሥሣ፡በልቡናነ፡ዘወሀበነ፡ፈጣሪ፡ከመ፡ቦቱ፡ንርአይ፡ጥበበዘኮነለነ፡መፍትወ፡ ውስተ፡ኵሉ፡ መፍቅዳተ፡ ፍጥረት
ወለእመ፡ንፈቅድ፡ጽድቀ፡ንሕሥሣ፡በልቡናነ፡ዘወሀበነ፡እግዚአብሔር፡ከመ፡ንርአይ፡ቦቱ፡ዘኮነ፡ለነ፡መፍትወ፡ውስተ፡ኵሉ መፍቅዳተ፡ፍጥረት፡፡
4. ወአኮ፡ዘንረክባ፡ለጽድቅ፡በትምህርተ፡ሰብእ፡ እስመ፡ኵሉ፡ሰብእ፡ሐሳዊ፡ውእቱ፡
ወለጽድቅሰ፡ኢንረክባ፡በትምህርታተ፡ሰብእ፡እስመ፡ኵሉ፡ሰብእ፡ሐሳዊ፡ውእቱ፡
5. ወለእመሰ፡ኢንፈቅዳ፡ለጽድቅ፡ኢይትኃጐል፡ በእንተ፡ዝንቱ፡ሥርዓተ፡ፈጣሪ፡ወኢሕግ፡ጠባይዓዊ፡ዘፍጥረት፡እንበለ፡ንሕነ፡ዘንትኃጐል፡ በስሕተትነ፡
ወለእመሰ፡ናበድራ፡ለሐሰት፡እምጽድቅ፡ኢይትኃጐል፡በእንተ፡ዝንቱ፡ሥርዓተ፡ፈጣሪ፡ወኢሕግ፡ጠባይዓዊ፡ዘተሠርዓ፡ለኵሉ፡ፍጥረት፡እንበለ፡ንሕነ፡ዘንትኃጐል፡በስሕተትነ፡
6. እግዚአብሔርሰ፡የዓቅብ፡ ዓለመ፡ በሥርዓቱ ዘሠርዓ፡ወዘሰብእ፡ኢይክሉ፡አማስኖቶ፡እስመ፡እለ፡የአምኑ፡ከመ፡መንኮስና፡ይኄይስ፡እምአውስቦ፡እሙንቱኒ፡ይሰሐቡ፡እምኃይለ፡ፍጥረት፡ ኀበ፡ አውስቦ
እግዚአብሔርሰ፡የዓቅብ፡ዓለመ፡በሥርዓቱ፡ዘሠርዓ፡ወዘሰብእ፡ኢይክሉ፡አማስኖቶ፡እስመ፡ሥርዓተ፡እግዚአብሔር፡ይጸንዕ፡እምሥርዓተ፡ሰብእ፡ወበእንተዝ፡እለ፡የአምኑ፡ከመ፡ምንኩስና፡ይኄይስ፡እምአውስቦ፡እሙንቱኒ፡ይስሐቡ፡እምጽንዑ፡ለሥርዓተ፡ፍጣሪ፡ኀበ፡አውስቦ፡፡
7. ወእለ፡የአምኑ፡ከመ፡ጾም፡ያጸድቅ፡ነፍሰ፡እሙንቱኒ፡ይበልዑ፡አመ፡ይእኅዞሙ፡ረሐብ፡ወእለ፡የአምኑ፡ከመ፡ዘየኀድግ፡ንዋዮ፡ይከውን፡ፍጹመ፡እሙንቱ፡እምበቍዔት፡ዘይትረከብ፡በንዋይ፡ይሰሐቡ፡ኀበ፡ኃሢሠ፡ንዋይ፡ወእምድኅረ፡ኀደግዎ፡የሐሥሥዎ፡ካዕበ፡በከመ፡ይገብሩ፡ብዙኃን፡እመነኮሳተ፡ብሔርነ
ወእለ፡የአምኑ፡ከመ፡ጾም፡ያጸድቅ፡ነፍሰ፡እሙንቱኒ፣ይበልዑ፡ከመይእኅዞሙ፡ረኀብ፡ወእለ፡የአምኑ፡ከመ፡ዘየኃድግ፡ንዋዮ፡ይከውን፡ፍጹመ፡እሙንቱ፡እምበቍዔት፡ዘይትረከብ፡በንዋይ፡ይሰሐቡ፡ኀበ፡ኀሢሠ፡ንዋይ፡ወእምድኅረ፡ኀደግዎ፡የሐሥሥዎ፡ካዕበ፡በከመ፡ይገብሩ፡ብዙኃን፡እመነኮሳተ፡ብሔርነ፡፡
8. ወከመዝ፡ኵሎሙ፡ሐሳውያን፡ይፈቅዱ፡ይንሥትዎ፡ለሥርዓተ፡ፍጥረት፡ወባሕቱ፡ኢይክሉ፡እንበለ፡ያርእዩ፡ሐሰቶሙ፡ድኩመ፡
ወከመዝ፡ኵሎሙ፡ሐሳውያን፡ይፈቅዱ፡ይንስትዎ፡ለሥርዓተ፡ፍጥረት፡ወባሕቱ፡ኢይክሉ፡እንበለ፡ያርእዩ፡ሐሰቶሙ፡ድኩመ፡፡
9. ፈጣሪሰ፡ይስሕቆሙ፡ወእግዚአብሔር፡ይሣለቅ፡ ላዕሌሆሙ።እስመ፡የአምር፡እግዚአብሔር፡ገቢረ፡ፍትሕ፡ወበግብረ፡እደዊሁ፡ተሠግረ፡ኃጥእ።
ፈጣሪሰ፡ይስሕቆሙ፡ወእግዚአ፡ፍጥረት፡ይሣለቅ፡ላዕሌሆሙ።እስመ፡የአምር፡እግዚአብሔር፡ገቢረ፡ፍትሕ፡ወበግብረ፡እደዊሁ፡ተሠግረ፡ ኃጥእ።
10. ወበእንተዝ፡መነኮስ፡ዘያነውር፡ሥርዓተ፡አውስቦ፡ይሠገር፡በዝሙት፡ወበካልእ፡አበሳ፡ሥጋሁ፡በእኩይ፡ ሕማም።
ወበእንተዝ፡መነኮስ፡ዘያነውር፡ሥርዓተ፡አውስቦ፡ይሠገር፡በዝሙት።ወበካልእ፡አበሳ፡ሥጋሁ፡በዘኢኮነ፡ፍጥረቱ፡ወበእኩይ፡ ሕማም።
11. ወእለ፡ይሜንኑ፡ንዋዮሙ፡ይከውኑ፡መድልዋነ፡በኀበ፡ነገሥት፡ወአብዕልት፡ከመ፡ይርከቡ፡ንዋየ።
ወእለ፡ይሜንኑ፡ንዋዮሙ፡ይከውኑ፡መድልዋነ፡በኀበ፡ነገሥት፡ወአብዕልት፡ከመ፡ይርከቡ፡ንዋየ። .
12.  ወእለ፡የኃድጉ፡አዝማዲሆሙ፡በእንተ፡እግዚአብሔር፡ብሂሎሙ፡የኃጥኡ፡ረዳኤ፡አመ፡ንዳቤሆሙ፡ወርስዖሙ፡ወይበጽሑ፡ኀበ፡ሐሜት፡ወፅርፈት፡ላዕለ፡እግዚአብሔር፡ወላዕለ፡ ሰብእ።
ወእለ፡የኀድጉ፡አዝማዲሆሙ፡በእንተ፡እግዚአብሔር፡ብሂሎሙ፡የኀጥኡ፡ረዳኤ፡አመ፡ንዳቤሆሙ፡ወርስዖሙ፡ወይበጽሑ፡ኀበ፡ሐሜት፡ወፅርፈት፡ላዕለ፡እግዚአብሔር፡ ወላዕለ፡ ሰብእ።
13.  ወከመዝ፡ኵሎሙ፡እለ፡ይነሥቱ፡ሥርዓተ፡ፈጣሪ፡ይሠገሩ፡በግብረ፡ እደዊሁ። 
ወከመዝ፡ኵሎሙ፡እለ፡ይነሥቱ፡ሥርዓተ፡ፈጣሪ፡ ይሠገሩ፡ በግብረ፡ እደዊሁ። .
14. ወዓዲ፡የኃድግ፡እግዚአብሔር፡ስሕተተ፡ወእከየ፡ማዕከለ፡ሰብእ፡እስመ፡ነፍሳቲነ፡ሀለዋ፡ውስተ፡ ዝንቱ፡ዓለም፡ከመ፡ውስተ፡ብሔረ፡ፈቲን፡በዘይትከሩ፡ቦቱ፡ኅሩያነ፡እግዚአብሔር፡በከመ፡ይ፡ጠቢብ፡ሰሎሞን፡እስመ፡እግዚአብሔር፡አምከሮሙ፡ለጻድቃን፡ወረከቦሙ፡ድልዋነ፡ሎቱ፡ከመ፡ወርቅ፡ዘይትፈተን፡በምንሐብ፡አምከሮሙ፡ወከመ፡ጽንሐሕ፡ውኩፍ፡ተወክፎሙ።
ወዓዲ፡የኀድግ፡እግዚአብሔር፡ስሕተተ፡ወእከየ፡ማዕከለ፡ሰብእ፡እስመ፡ነፍሳቲነ፡ሀለዋ፡ውስተ፡ዝንቱ፡ዓለም፡ከመ፡ውስተ፡ብሔረ፡ፈቲን፡በዘይትከሩ፡ቦቱ፡ኅሩያነ፡እግዚአብሔር፡በከመ፡ይ፡ጠቢብ፡ሰሎሞን፡እስመ፡እግዚአብሔር፡አምከሮሙ፡ለጻድቃን፡ወረከቦሙ፡ድልዋነ፡ሎቱ፡ከመ፡ወርቅ፡ዘይትፈተን፡በምንሐብ፡አምከሮሙ፡ወከመ፡ጽንሐሕ፡ ውኩፍ፡ተወክፎሙ፡
15.  ወእምድኅረ፡ሞትነሰ፡አመ፡ንገብእ፡ኀበ፡ፈጣሪነ፡ንሬኢ፡ከመ፡እግዚአብሔር፡ሠርዓ፡ኵሎ፡በጽድቅ፡ወበዓቢይ፡ጥበብ፡ወከመ፡ኵሎ፡ፍኖተ፡እግዚአብሔር፡ሣህል፡ወጽድቅ።
ወእምድኅረ፡ሞትነሰ፡አመ፡ንገብእ፡ኀበ፡ፈጣሪነ፡ንሬኢ፡ከመ፡እግዚአብሔር፡ሠርዓ፡ኵሎ፡በጽድቅ፡ወበዓቢይ፡ጥበብ፡ወኵሉ፡ፍኖቱ፡ጽድቅ፡ወርትዕ።
16. ወከመሰ፡ነፍስነ፡ተሐዩ፡እምድኅረ፡ሞትነ፡ይተዓወቅ፡እስመ፡በዝንቱ፡ዓለም፡ኢይትፌጸም፡ ፍትወትነ፡ወእለ፡ቦሙ፡ይፈቅዱ፡ይወስኩ፡ዓዲ፡ለዘቦሙ፡ወእመኒ፡አጥረየ፡ብእሲ፡ኵሎ፡ዘሀሎ፡ውስተ፡ዓለም፡ኢይጸግብ፡ወይፈቱ፡ዓዲ። 
ወከመሰ፡ነፍስነ፡ተሐዩ፡እምድኅረ፡ሞተ፡ሥጋነይትዓወቅ፡እስመ፡በዝንቱ፡ዓለም፡ኢይትፌጸም፡ፍትወትነ፡ወእለ፡አልቦሙ፡የኀሥሡ፡ወእለ፡ቦሙ፡ይፈቅዱ፡ይወስኩ፡ዓዲ፡ለዘቦሙ፡ወእመኒ፡አጥረየ፡ብእሲ፡ኵሎ፡ዘሀሎ፡ውስተ፡ዓለም፡ኢይጸግብ፡ወዓዲ፡ይፈቱ።
17.  ወዝንቱ፡ጠባይዓ፡ፍጥረትነ፡ያጤይቅ፡ይኤምር፡ከመ፡ኢተፈጠርነ፡ለንብረተ፡ዝ፡ዓለም፡ባሕቲቱ፡አላ፡ለዘይመጽእ፡ንብረት፡በዘነፍሳት፡እለ፡ፈጸማ፡ፈቃደ፡ፈጣሪሆን፡ይጸግባ፡ፍጹመ፡ወኢይፈትዋ፡እንከ፡ካልእ፡ነገረ
ወዝንቱ፡ጠባይዓ፡ፍጥረትነ፡ይኤምርከመ፡ኢተፈጠርነ፡ለንብረተ፡ዝዓለም፡ባሕቲቱ፡አላ፡ወለዘይመጽእ፡ንብረት፡ወበህየነፍሳት፡እለ፡ፈጸማ፡ፈቃደ፡ፈጣሪሆን፡ይጸግባ፡ፍጹመ፡ወኢይፈትዋ፡እንከ፡ካልእ፡ነገረ
18.   እስመ፡እንበለዝ፡ፍጥረተ፡ሰብእ፡እምኮነ፡ንቱገ፡ወእምኢረከበ፡ኵሎ፡ዘይትፈቀድ፡ሎቱ።
እንበለዝ፡ፍጥረተ፡ሰብእ፡እምኮነ፡ንቱገ፡ወእምኢረከበ፡ኵሎ፡ዘይትፈቀድ፡ሎቱ።
19. ወዓዲ፡ነፍስ፡ትክል፡ተሐሊ፡አምላከ፡ወትርአዮ፡ለአምላክ፡በሕሊናሃወትክል፡ተሐሊ፡ነቢረ፡ ለዓለም። 
ወዓዲ፡ነፍስነ፡ትክል፡ተሐሊ፡እግዚአብሔርሃ፡ወትርአዮ፡በሕሊናሃ፡፡ወዓዲ፡ትክል፡ተሐሊ፡ነቢረ፡ለዓለም።
20.  ወእግዚአብሔር፡ኢወሀባ፡በከንቱ፡ተሐሊ፡ዘንተ፡አለ፡በከመ፡ወሀባ፡ተሐሊ፡ወሀባሂ፡ ወትርከቦ።  
ወእግዚአብሔር፡ኢወሀባ፡በከንቱ፡ተሐሊ፡ዘንተ፡ዳዕሙበከመ፡ወሀባ፡ተሐሊ፡ወሀባሂ፡ ወትርከብ። 
21.  ወዓዲ፡በዝዓለም፡ኢይትፌጸም፡ኵሎ፡ጽድቅ፡ወሰብእ፡እኩያን፡ይጸግቡ፡እምሠናያተዝ፡ዓለም፡ወየዋሃን፡ይርሕቡ፡ቦእኩይ፡ዘይትፌሣሕ፡ወቦ፡ሠናይ፡ዘይቴክዝ፡
ወዓዲ፡በዝዓለም፡ኢይትፌጸም፡ኵሉ፡ጽድቅ፡ወሰብእ፡እኩያን፡ይጸግቡ፡እምሠናያተዝ፡ዓለም፡ወየዋሃን፡ይርኅቡ።ቦእኩይ፡ዘትፌሣሕ፡ወቦሠናይ፡ዘይቴክዝ፡ቦዓማፂ፡ዘይትፌጋዕ፡ወቦ፡ጻድቅ፡ ዘይበኪ።
22.   ወበእንተዝ፡ይትፈቀድ፡እምድኅረ፡ሞትነ፡ካልእ፡ንብረት፡ወካልእ፡ጽድቅ፡ፍጹም፡ዘይፈድዮ፡ለኵሉ፡በከመ፡ምግባሩ።ወየአስዮሙ፡ለእለ፡ፈጸሙ፡ፈቃደ፡ፈጣሪ፡ዘተከሥተ፡ሎሙ፡በልቡናሆሙ፡ወበሕገ፡ ፍጥረት፡
ወበእንተዝ፡ይትፈቅድ፡እምድኅረ፡ሞትነ፡ካልዕ፡ንብረት፡ወካልዕ፡ጽድቅ፡ፍጹም፡ዘይፈድዮ፡ለኵሉ፡በከመ፡ምግባሩ።ወየአሥዮሙ፡ለእለ፡ፈጸሙ፡ፈቃደ፡ፈጣሪ፡ዘተከሥተ፡ሎሙ፡በብርሃነ፡ልቡናሆሙ።ወለእለ፡ዓቀቡ፡ሕገ፡ጠባይዓዌ፡ ዘፍጥረቶሙ።
23.   ወሕገ፡ፍጥረትስ፡ጥይቅት፡ይእቲ፡እስመ፡ልቡናነ፡ይነግረነ፡ክሡተ፡ለእመ፡ነሐትታ።ወባሕቱ፡ሰብእ፡ኢይፈቀዱ፡ይሕትቱ፡ወያበድሩ፡ይእመኑ፡በቃለ፡ሰብእ፡እምይሕሥሡ፡ፈቃደ፡ፈጣሪ፡ በጽድቅ።
ወሕገ፡ፍጥረትስ፡ጥዩቅ፡ውእቱ፡እስመ፡ልቡናነ፡ይነግረነ፡ክሡተ፡ለእመ፡ነሐትታ።ወባሕቱ፡ሰብእ፡ኢፈቀዱ፡ይሕትቱ፡ወአብደሩ፡ይእመኑ፡በቃለ፡ሰብእ፡እምይኅሥሡ፡ፈቃደ፡ፈጣሪሆሙ፡በጽድቅ።

      ከክፍል ሰባት ጽሑፍ ውስጥ በቁጥር 1፣2፣3፣4፣5፣7፣12፣14፣16፣17፣18፣19፣20 የተጠቀሱት ለውጦች የተሻለ የሰዋስውን ለመጠቀም የተደረጉ ናቸው፡፡ በቁጥር 6፣10፣9፣15፣21 እና 22 የተጠቀሱት ደግሞ ነገሩን በተሻለ መንገድ ለመግለጥ የገቡ ናቸው፡፡
·         ለምሳሌ በቁጥር 6 ላይ ‹ሥርዓተ፡እግዚአብሔር፡ይጸንዕ፡እምሥርዓተ፡ሰብእ - የእግዚአብሔር ሥርዓት ከሰው ሥርዓት ይልቅ ይጸናልና› በሚል የቀረበው ጭማሪ የዘርአ ያእቆብን ሐሳብ የበለጠ የሚያብራራው ነው፡፡ ‹ሕገ ጋብቻ ከሕገ ምንኩስና ይበልጣል› የሚለው ከዘርአ ያእቆብ አንጓ መከራከሪያዎች አንዱ ነው፡፡ ለምን? የሚለውን ሲመልስ ነው ይህን የሚያነሣው፡፡ ይህ የገልባጭ ጉዳይ ሳይሆን ይሁነኝ ተብሎ የተሻሻለ ነው፡፡
·         በቁጥር 10 ላይ የተገለጠው ‹በዘኢኮነ፡ፍጥረቱ - ፍጥረቱ ባልሆነ› የሚለው ማሻሻያ አሁንም የዘርአ ያእቆብን ሐሳብ በሚገባ ለማብራራት የተጨመረ ነው፡፡ ሐሳቡም ‹ሕገ ጋብቻ ከሕገ ምንኩስና ይበልጣል› የሚለው ነው፡፡
·         ከዚህ ቀደም ብሎ በቁጥር 9 ላይ የተደረገውን ማሻሻያ ብንመለከተው ቀላል የሚመስል ነገር ግን ሐሳቡን በሚገባ ለመግለጥ የገባ ማሻሻያ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በ234 ላይ ‹ወእግዚአብሔር ይሣለቅ - እግዚአብሔር ይሣለቅባቸዋል› የሚለውን በ215 ላይ ‹ወእግዚአ፡ፍጥረት፡ይሣለቅ - የፍጥረት ጌታ ይሣለቅባቸዋል› ወደሚለው ተለውጧል፡፡ እዚህ ላይ ፍጥረት የሚለው ማሻሻያ የተደረገው ‹ሕገ ምንኩስና ከሕገ ፍጥረት የወጣ ነው› ከሚለው ቀደም ብለን ካየነው የዘርአ ያእቆብ መከራከሪያ ጋር የሚሄድ ነው፡፡ ‹እግዚአብሔር› ከማለት ይልቅ ‹እግዚአ ፍጥረት› የሚለው የተፈለገው ‹ምንኩስና ከሕገ ፍጥረት የወጣ ስለሆነ የፍጥረቱ ጌታ በዚህ ይሣለቅባቸዋል› ለማለት ነው፡፡
·         በቁጥር 21 የተገለጠው ‹ቦዓማፂ፡ዘይትፌጋዕ፡ወቦ፡ጻድቅ፡ ዘይበኪ - ተድላ የሚያደርግ ዐማፂ አለ፤ የሚያለቅስ ጻድቅም አለ› የሚለው ጭማሪም ‹ጽድቅ በዚህ ዓለም አይፈጸምም› የሚለውን ቀደም ብሎ ያነሣውን ሐሳብ የበለጠ የሚያብራራ ነው፡፡
·         በቁጥር 22 የሚገኘው ‹ለእለ፡ፈጸሙ፡ፈቃደ፡ፈጣሪ፡ዘተከሥተ፡ሎሙ፡በብርሃነ፡ልቡናሆሙ።ወለእለ፡ዓቀቡ፡ሕገ፡ጠባይዓዌ፡ ዘፍጥረቶሙ› የሚለው የቁጥር 215 ጭማሪ ሁለት ነጥቦችን ለማስረገጥ የገባ ነው፡፡ የመጀመሪያው ‹ብርሃነ ልቡና› የሚለውን ሐሳብ ለመጨመር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ‹በፍጥረታቸው ያለውን ጠባይአዊ ሕግ ለጠበቁ› የሚለውንና ሕገ ምንኩስና ከሕገ ፍጥረት ውጭ ነው የሚለው ለመከራከር ያመጣውን ሐሳብ ለማጽናት ነው፡፡
እነዚህን ነገሮች ስንመለከት 215 የተዘጋጀው የተሻሻለ ቅጅን ለማዘጋጀት ሲባል መሆኑን ማየት እንችላለን፡፡ የተጻፈው በቤተልሔም አካባቢ በነበረው የቁም ጽሕፈት ቤት ነውና፡፡ ከሌላ ካላገኘነው ቅጅ ተሻሽሎ የተዘጋጀ ነው፡፡ ቁም ጸሐፊዎቹ ደባትር ይጽፋሉ ኡርቢኖ እያሻሻለ ይመልሳል ማለት ነው፡፡
ሁለተኛው ማሻሻያ ደግሞ ሐተታው የበለጠ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን እንዲመለከት የተደረገው ማሻሻያ ነው፡፡ በምሳሌ እንየው፡፡  በዚህ ጉዳይ ላይ የምጠቅሰው የጌታቸው ኃይሌን ማስረጃ ነው[3]፡፡
                                       
234
215
1
እም ድኅረ አእመርኩ ከመ ሃይማኖት ዘማ አው ሐሳዊት ይእቲ እቴክዝ በእንቲአሃ-ሃይማኖት ዘማ ወይም ሐሰተኛ መሆንዋን ካወቅኩ በኋላ ስለ እርሷ እተክዝ ነበር (14b)
እም ድኅረ አእመርኩ ከመ ሃይማኖትየ ዘማ አው ሐሳዊት ይእቲ እቴክዝ በእንቲአሃ - ሃይማኖቴ ዘማ ወይም ሐሳዊት መሆንዋን ካወቅኩ በኋላ ስለ እርሷ እተክዝ ነበር፡፡ (14a)
2
ወበዝንቱ ዘመንሰ ሰብእ አፍለሱ ፍቅረ ወንጌል ኀበ ጽልዕ -በዚህም ዘመን ሰዎች የወንጌልን ፍቅር አጠፉ(14b)
ወበዝንቱ ዘመንሰ ሰብአ ብሔርነ አፍለሱ ፍቅረ ወንጌል ኀበ ጽልዕ - በዚህስ ዘመን የሀገራችን ሰዎች የወንጌልን ፍቅር አጠፉ(14b)
ከቁጥር 234 ይልቅ ቁጥር 215 ባለቤቱን አጥብቦታል፡፡ የመጀመሪያው ስለ ሃይማኖትና ስለ ሰዎች በጠቅላላው ሲገልጥ ሁለተኛው(215) ግን ኢትዮጵያውያንን (የሀገራችን ሰዎች) የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን(ሃይማኖቴ) እንዲመለከት ተደርጓል፡፡
እነዚህን ምሳሌዎች ስንመለከት ሐተታ ዘርአ ያእቆብ ለተፈለገለት ዓላማ እንዲውል ሲሻሻልና ሲቀየር እንደኖረ ያመለክቱናል፡፡ በዚህ ሥራ ደግሞ ኡርቢኖና በዚሪያው የነበሩትና አባ ተክለ ሃይማኖት የገለጧቸው የቤተ ልሔም አካባቢ ደባትር አብረው ሠርተዋል፡፡
ማጠቃለያ
ከላይ በተከታታይ ያነሣኋቸውን መረጃዎች ሳገናኛቸው ዘርአ ያእቆብ የሚባል ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ነበር ብዬ ለመቀበል ይቸግረኛል፡፡ የሰጠን መረጃዎች እርስ በርሳቸው የተጣረሱ፤ ከሌሎች መረጃዎች ጋር የሚጋጩ፤ ወጥነት የማይታይባቸው፤ በውሸት የተሞሉ፣ ለኢትዮጵያ መልክዐ ምድር ባዕድ የሆኑ ልቦለዳዊነት የሚያጠቃቸው ናቸው፡፡ ፍልስፍናዎቹም የቀድሞ ካቶሊካውያን ፈላስፎች ተጽዕኖ ያየለበት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ድርሳኑም እየተቀያየረ የመጣና በሁለቱ ቅጅዎች መካከል ከገልባጭ ስሕተት የሚልቁ ልዩነቶችን እናገኛለን፡፡ የኡርቢኖና የዘርአ ያእቆብ ሕይወት የሚመሳሰል ነው፡፡ ከሁለቱ ቅጅዎች ውጭም ሌሎች ቅጅዎችን እስካሁን ድረስ አላገኘንም፤ ዘርአ ያእቆብንም በየትኞችም ሌሎች ድርሳናትም ሆኑ የቃል ታሪኮች ውስጥ ተጠቅሶ አናየውም፡፡ በኢትዮጵያውያን ሊቃውንትም አይታወቅም፡፡ ሚቶች(E. Mittwoch) ዘርአ ያእቆብን ያውቁት እንደሆነ የጠየቃቸው ካቶሊካዊው አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ (የአማርኛ መዝገበ ቃላቱ ደራሲ)የመለሱትን መልስ ስንመለከትም ጽሑፉን አንብበው አስተያየታቸውን ሰጡ እንጂ ከዚያ በፊት እንደሚያውቁት አልገለጡም፡፡   

1.      ‹ሐተታ ዘርአ ያእቆብ› የተሰኘውን ድርሳን ያዘጋጁት በቤተልሔምና በደብረ ታቦር አካባቢ የነበሩ ወደ ካቶሊክነት የተለወጡ ደባትርና ፈረንሳዊው ዳ. ኡርቢኖ በጋራ ሆነው ነው፡፡ ኡርቢኖ ለአንቶኒዮ ዲ. አባዲ የላከው እግዚአብሔር ነግሠ (BnF Eth Abb 211) እና ሐተታ ዘርአ ያእቆብ (BnF Eth Abb 215) ተመሳሳይ የአጻጻፍ የተከተሉ የቤተልሔሙ ደብተራ የደብተራ ገብረ ማርያም ሥራዎች ናቸው፡፡ ደብተራ አማርከኝና  ሊቀ ካህናት ጎሹም አብረውት ሲሠሩ እንደነበር በዘመኑ የነበሩት አባ ተክለ ሃይማኖት በማስታወሻቸው ገልጠውታል፡፡ ስቬን ሩቢንሰን ያሳተሙትን አክታ ኢትዮፒካ[4] ብንመለከትም ከአንቶኒዮ ዲ. አባዲና ከኡርቢኖ ጋር ሲሠሩ የነበሩ ደባትር የተጻጻፏቸውን ደብዳቤዎች እናገኛቸዋለን፡፡ 

2.     የ‹ሐተታ ዘርአ ያእቆብ› ዓላማው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ለመተቸት የተዘጋጀ የ17ኛው መክዘ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ ነው፡፡ ኡርቢኖ የነበረውን የግእዝ ዕውቀት የቅርጣግና ሌሊቶችን በመተርጎም፣ የግእዝ ሰዋሰው በማዘጋጀት(BnF Eth Abb 216)ና የግእዝ - ፈረንሳይኛ - አማርኛ መዝገበ ቃላትን(BnF Eth Abb 217) በማዘጋጀት አስመስክሯል፡፡ ኡርቢኖ ከካቶሊክ ሚሲዮናውያን የተለየ ሐሳብ የነበረው አፈንጋጭ ሚሲዮናዊ ነበር፡፡ ይህንንም በዘመኑ የነበሩት ሚሲዮናዊው አባ ተክለ ሃይማኖት በማስታወሻቸው ገልጠውታል፡፡ ኡርቢኖ ለዲ. አባዲ የጻፋቸው ደብዳቤዎች እንደሚያሳዩት ከካቶሊክ ሚስዮናውያን ይልቅ ከፕሮቴስታንት ሚስዮናውያን ጋር የተሻለ ግንኙነት ነበረው[5]፡፡ የእነርሱ ተጽዕኖም በአስተሳሰቡ ላይ ይታያል፡፡
3.     ‹ሐተታ ዘርአ ያእቆብ› ሲዘጋጅ የታሰበው የተሻለ ቅጅ አዘጋጅቶ ልክ እንደ ‹ቅርጣግና ሌሊቶች› ሁሉ ወደ ግእዝና አማርኛ ሥነ ጽሑፍ ለማስገባት ነው፡፡ ነገር ግን ኡርቢኖ ከሀገር በመውጣቱ ምክንያት ሳይሳካ ቀረ፡፡ ያሻሻለውን ቅጅ ካይሮ እያለ ወደ ፈረንሳይ ላከው፡፡
4.   በሆኑም ዘርአ ያእቆብ ዳ. ኡርቢኖና አብረውት የሠሩት ልውጥ ደባትር የፈጠሩት ልቦለዳዊ ገጸ ባሕርይ እንጂ በሕይወት የነበረ ፈላስፋ አይደለም፡፡ ጽሑፎቹም በዳ. ኡርቢኖና በልውጥ ደባትር ለፕሮፓጋንዳ ዓላማ የተዘጋጁ፣ በሐሰት መረጃዎች የተሞሉ ድርሳናት እንጂ ኢትዮጵያውያን ፍልስፍናዎች አይደሉም፡፡ በአሁኑ ጊዜም በዋናነት ለተመሳሳይ የፀረ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንና ፀረ ምንኩስና ፕሮፓጋንዳ ዓላማ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡
 (ወልደ ሕይወትንና ‹ፍልስፍናውን› የተመለከተውን ጉዳይ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ)     [1] Anaïs Wion, L'histoire d'un vrai faux traité philosophique (Ḥatatā Zar'a Yā'eqob et Ḥatatā Walda Ḥeywat). Épisode 2: Le temps de la démystification et la traversée du désert (de 1916 aux années 1950). November 2013.
[2] ዚአሁ፡- በመጽሐፉ ላይ ከላይና ከታች ሠረዝ አለዉ፡፡
[3] Getatchew Haile, Ethiopian Studies in Honour of Amha Asfaw, 2017
[4] Rubinson Sven. (Acta Æthiopica, vol. 1-3)
[5] ከእንግሊዙ ቆንስላ ፕላውዴን ጋር መልካም ግንኙነት እንደነበረው በደብዳቤው ያነሣል

18 comments:

 1. እግዚአብሔር ይባርክህ!!!

  ReplyDelete
 2. This well structured research and analysis on 'Zera Yakob'  throws what was 'believed' to be the 'philosophical' work of Urbino (who impersonated a person named Zera Yakob) in to the dust of history. Daniel brought historical, anthropological Orthodox Churche's tradition, chronological, philosophical...and other (including common sense) approaches to investigate what was beneath Zera Yakob's hateta and reveals the evil intent of Urbino. Such scholarly work is needed to weed-out heracies and made-up (manufactured) history that is being now 'referenced' by present day pseudo-historians, self-made ignorant politicians and heretics (you all know them) to challenge Ethiopia and Ethiopian's.

  Daniel's critical analysis will inspire others  to focus on other historical writings and sort the wheat from the chaff. Those  who wanted to create historical fallacy must learn that, what every they say and write unless truth is told, it will fall apart sooner or later.

  My little advise to Daniel - please publish all these six parts in a book. It can be a Chapter. This way it can reach many back home and can also be used for further research.

  God Bless you.

  Kidanemariam

  ReplyDelete
 3. Thank you very much Dn Daniel. This is a wonderfull work which shows a cautious, deep intellects. There are many poisons that western planted in our Church, Society and Country. This work, I believe, among others will definitely help weed out the toxic and clean our attitude.

  May God the Almighty give you the wisdom and light to continue to serve our Church.

  ReplyDelete
 4. It is also interesting to investigate why Father Claudio Summer (Professor), who is a Jesuits, is so much interested on the works of Zara Yakob (Urbino).I believe he continued from where Urbino left to push the propaganda and fallacy in this century and beyond. We are all glad their conspiracy is dead once and for all.

  ReplyDelete
 5. ቴዎድሮስ ፍቅሬFebruary 15, 2018 at 11:14 AM

  እጅግ በጣም ጥሩ ትንታኔ ነው። በጣም ኣሳማኝም ነው። ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ኣንተ የጠቀስከው ሀተታ ዘዘርዓ ያዕቆብ የሚለው መጽሓፋቸው ገፅ 6 ላይ Eugen Mittwochን ኦይገን ሚትቮኽ ብለው ነው የሚጽፉት ፤ ስለዚህ ኣንተም እንደሳቸው ብትጠቀመው ሳይሻል ኣይቀርም።

  ReplyDelete
 6. I read all the six sections of this research and I found your analysis well structured and evidence-based. Thank you!

  ReplyDelete
 7. ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  ==============

  ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  አልተገኘህምና…
  እንደ ጉም ባዶ ነህና ….
  የፈረንጅ ክፋት ነህና …
  የዳ ኡርቢኖ ቅርሻት ነህና …
  የዳ ኡርቢና ደሞዝ ነህና…

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣
  ቻው ያዕቆብ፣ ቻው ዘርዓ ያዕቆብ፣ ቻው ወርቄ፣ ቻው ዳ ኡርቢኖ፣
  ሰንብቷልና ያንተ ነገር ሳይበስል እንዲያው ተከድኖ፣
  አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ..
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ፈስ ቀረ ነውና፣
  እልሃለሁ በኢትዮጵያዊ ቃና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ የፈረንሳይና የጣልያን ሚስዮኑ፣
  የክህደት መልእክተኛው የሰይጣን መኮንኑ፣
  በስጋም በነፍስም ሚዛን ሚሽንህ ከሽፏልና በኢትዮጵያውያኑ፣
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣

  ጥር 16፣ 2010 ዓ.ም.
  መገናኛ፣ ከማቲያስ ህንጻ ብዙም ሳይርቅ፡፡

  ReplyDelete
 8. ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  ==============

  ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  አልተገኘህምና…
  እንደ ጉም ባዶ ነህና ….
  የፈረንጅ ክፋት ነህና …
  የዳ ኡርቢኖ ቅርሻት ነህና …
  የዳ ኡርቢና ደሞዝ ነህና…

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣
  ቻው ያዕቆብ፣ ቻው ዘርዓ ያዕቆብ፣ ቻው ወርቄ፣ ቻው ዳ ኡርቢኖ፣
  ሰንብቷልና ያንተ ነገር ሳይበስል እንዲያው ተከድኖ፣
  አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ..
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣
  እልሃለሁ በኢትዮጵያዊ ቃና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ የፈረንሳይና የጣልያን ሚስዮኑ፣
  የክህደት መልእክተኛው የሰይጣን መኮንኑ፣
  በስጋም በነፍስም ሚዛን ሚሽንህ ከሽፏልና በኢትዮጵያውያኑ፣
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣

  ጥር 16፣ 2010 ዓ.ም.
  መገናኛ፣ ከማቲያስ ህንጻ ብዙም ሳይርቅ፡፡

  ReplyDelete
 9. teru tentane new bewnetu gen zeryaqo ethiopiawi aydelm yemilew hasab tensh ahunem asamgn aydelem mekniyatum yezan gize yeh felsfena yemayonrbet mekniyat yelem urbino becha new way yewuchi zega becha new miflasef aynet melk alew dani tensh altewatelgnem ene degemo felsfnawn wesgewalew deme wust gebto sew men bil mesmat alchelem betelay esu mitelachewun neger menkusen ,bethwena,sele set lej,sel teftero,sele some,sele sega ,sel nese ,ena men teshalgn?????????????????????

  ReplyDelete
 10. ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  ==============

  ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  አልተገኘህምና…
  እንደ ጉም ባዶ ነህና ….
  የፈረንጅ ክፋት ነህና …
  የዳ ኡርቢኖ ቅርሻት ነህና …
  የዳ ኡርቢና ደሞዝ ነህና…

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣
  ቻው ያዕቆብ፣ ቻው ዘርዓ ያዕቆብ፣ ቻው ወርቄ፣ ቻው ዳ ኡርቢኖ፣
  ሰንብቷልና ያንተ ነገር ሳይበስል እንዲያው ተከድኖ፣
  አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ..
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣
  እልሃለሁ በኢትዮጵያዊ ቃና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ የፈረንሳይና የጣልያን ሚስዮኑ፣
  የክህደት መልእክተኛው የሰይጣን መኮንኑ፣
  በስጋም በነፍስም ሚዛን ሚሽንህ ከሽፏልና በኢትዮጵያውያኑ፣
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣

  ጥር 16፣ 2010 ዓ.ም.
  መገናኛ፣ አዲስ አበባ

  ReplyDelete
 11. ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  ==============

  ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  አልተገኘህምና…
  እንደ ጉም ባዶ ነህና ….
  የፈረንጅ ክፋት ነህና …
  የዳ ኡርቢኖ ቅርሻት ነህና …
  የዳ ኡርቢና ደሞዝ ነህና…

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣
  ቻው ያዕቆብ፣ ቻው ዘርዓ ያዕቆብ፣ ቻው ወርቄ፣ ቻው ዳ ኡርቢኖ፣
  ሰንብቷልና ያንተ ነገር ሳይበስል እንዲያው ተከድኖ፣
  አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ..
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣
  እልሃለሁ በኢትዮጵያዊ ቃና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ የፈረንሳይና የጣልያን ሚስዮኑ፣
  የክህደት መልእክተኛው የሰይጣን መኮንኑ፣
  በስጋም በነፍስም ሚዛን ሚሽንህ ከሽፏልና በኢትዮጵያውያኑ፣
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣

  ጥር 16፣ 2010 ዓ.ም.
  መገናኛ፣ ከማቲያስ ህንጻ ብዙም ሳይርቅ፡፡

  ReplyDelete
 12. ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  ==============

  ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  አልተገኘህምና…
  እንደ ጉም ባዶ ነህና ….
  የፈረንጅ ክፋት ነህና …
  የዳ ኡርቢኖ ቅርሻት ነህና …
  የዳ ኡርቢና ደሞዝ ነህና…

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣
  ቻው ያዕቆብ፣ ቻው ዘርዓ ያዕቆብ፣ ቻው ወርቄ፣ ቻው ዳ ኡርቢኖ፣
  ሰንብቷልና ያንተ ነገር ሳይበስል እንዲያው ተከድኖ፣
  አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ..
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣
  እልሃለሁ በኢትዮጵያዊ ቃና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ የፈረንሳይና የጣልያን ሚስዮኑ፣
  የክህደት መልእክተኛው የሰይጣን መኮንኑ፣
  በስጋም በነፍስም ሚዛን ሚሽንህ ከሽፏልና በኢትዮጵያውያኑ፣
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣

  ጥር 16፣ 2010 ዓ.ም.
  መገናኛ፣

  ReplyDelete
 13. thank you for revealing the truth well done

  ReplyDelete
 14. ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  ==============

  ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  አልተገኘህምና…
  እንደ ጉም ባዶ ነህና ….
  የፈረንጅ ክፋት ነህና …
  የዳ ኡርቢኖ ቅርሻት ነህና …
  የዳ ኡርቢና ደሞዝ ነህና…

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣
  ቻው ያዕቆብ፣ ቻው ዘርዓ ያዕቆብ፣ ቻው ወርቄ፣ ቻው ዳ ኡርቢኖ፣
  ሰንብቷልና ያንተ ነገር ሳይበስል እንዲያው ተከድኖ፣
  አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ..
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣
  እልሃለሁ በኢትዮጵያዊ ቃና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ የፈረንሳይና የጣልያን ሚስዮኑ፣
  የክህደት መልእክተኛው የሰይጣን መኮንኑ፣
  በስጋም በነፍስም ሚዛን ሚሽንህ ከሽፏልና በኢትዮጵያውያኑ፣
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣

  ጥር 16፣ 2010 ዓ.ም.
  መገናኛ፣

  ReplyDelete
 15. ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  ==============

  ቻው ዘርዓያዕቆብ…
  አልተገኘህምና…
  እንደ ጉም ባዶ ነህና ….
  የፈረንጅ ክፋት ነህና …
  የዳ ኡርቢኖ ቅርሻት ነህና …
  የዳ ኡርቢና ደሞዝ ነህና…

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣
  ቻው ያዕቆብ፣ ቻው ዘርዓ ያዕቆብ፣ ቻው ወርቄ፣ ቻው ዳ ኡርቢኖ፣
  ሰንብቷልና ያንተ ነገር ሳይበስል እንዲያው ተከድኖ፣
  አንድም ሁለትም አራትም ነህና፣
  ገመናም የሌለብህ ገመና ራስህ ነህና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ..
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣
  እልሃለሁ በኢትዮጵያዊ ቃና፣

  ቻው ዘርዓ ያዕቆብ የፈረንሳይና የጣልያን ሚስዮኑ፣
  የክህደት መልእክተኛው የሰይጣን መኮንኑ፣
  በስጋም በነፍስም ሚዛን ሚሽንህ ከሽፏልና በኢትዮጵያውያኑ፣
  ባገኝህም ላወግዝህ እንጅ ጥመኸኝ አታውቅምና፣
  ስላልተገኘህ ደስ ብሎኛል፣ ባቄላ ቀረ ቅሌት ቀረ ነውና፣

  ጥር 16፣ 2010 ዓ.ም.
  መገናኛ፣ አዲስ አበባ

  ReplyDelete