የኖርዌዩ አባ ቴዎድሮስ የሚተርኳት
አንዲት ገጠመኝ አለቻቸው፡፡ በአንድ ወቅት የቅኔ መምህር ሆነው አንድ ቦታ ይመደባሉ፡፡ በተመደቡበት ቦታ አንድ የታፈሩና የተከበሩ
አፈ ንቡረ እድ ነበሩ፡፡ ሰው ሁሉ ይፈራቸዋል፡፡ አባ ቴዎድሮስ የቅኔውም የመጽሐፉም ዕውቀት አለ፡፡ በዚህ ላይ ከሰው ጋር ተግባቢ
ናቸው፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ያኔ ወጣት ናቸው፡፡
አፈ ንቡረ እዱ በእኒህ ወጣት መምህር
መምጣት አልተስማሙም፡፡ ዐውቃለሁ ባይ ወጣት አድርገው ቆጠሯቸው፡፡ ይህንን ያወቁ ሌሎች ሰዎች ለአባ ቴዎድሮስ አንድ ነገር ሹክ
አሏቸው፡፡ ‹እኒህ ሊቅ ከባድ ሰው ናቸው፡፡ ፊት ለፊት አግኝተው እፍ ካሉብዎት ሽባ ሆነው ይቀራሉ› ይሏቸዋል፡፡ አባ ለሀገሩም
ለነገሩም እንግዳ ስለሆኑ ግራ ገባቸው፡፡ እንዴት ከእፍታው እንደሚያመልጡ ሆነ የዘወትሩ ሐሳባቸው፡፡ እንዲህ እያሰቡ ሰሞነ ጽጌ
ደረሰ፡፡ በሌሊቱ ማኅሌት አባ በአንድ መሥመር አፈ ንቡረ እዱ በአንድ መሥመር ለማስረገጥ ተሰለፉ፡፡ ደግሞ ይግረምዎ ብለው አባና
አፈ ንቡረ እዱ ፊት ለፊት ገጠሙ፡፡
አሁን በቀላሉ እፍ ማለት ይችላሉ፡፡
አባ ቴዎድሮስ አሰቡ አሰቡና መላውን አገኙት፡፡ በወረቡ ጊዜ አፈ ንቡረ እዱ እያሸበሸቡ ሸብረክ ብለው ፊት ለፊት ሲመጡ አባ ቴዎድሮስ
እያሸበሸቡ ከፍ ብለው ይሄዳሉ፡፡ አፈ ንቡረ እዱ ከፍ ብለው እያሸበሸቡ ሲመጡ ደግሞ አባ ቴዎድሮስ ሸብረክ ብለው ይሄዳሉ፡፡ አፈ
ንቡረ እዱ ጎንበስ ሲሉ አባ ቀና፣ አፈ ንቡረ እዱ ቀና ሲሉ አባ ጎንበስ እያሉ ማኅሌቱ አለቀ፡፡
በኋላ አፈ ንቡረ እዱ ይህንን ሰምተው
በሳቅ ፈርሰዋል፡፡ እርሳቸው እንደሚባሉት አልነበሩምና፡፡
ዛሬ ሀገራችን በዘረኛነት ወረርሽኝ
ስትታመስና የግርግርና የመገዳደል አውድማ ስትሆን ወሳኙ መፍትሔ የአባ ቴዎድሮስ መንገድ ነው፡፡ ተቃራኒዎቻችን በመጡበት መንገድ
አለመሄድ፡፡ ጎንበስ ሲሉ ቀና፣ ቀና ሲሉ ጎንበስ ማለት፡፡ ሸብረክ ሲሉ ከፍ፣ ከፍ ሲሉ ሸብረክ ማለት፡፡ ጠላቶቻችን በቀደዱት ቦይ
እየፈሰስንና እኛው ራሳችን የምንቃወመውን ነገር እያደረግን ችግሩን መፍታት አንችልም፡፡ የምንጠላውን ኃጢአት ደጋግመን መሥራት የለብንም፡፡
በዘረኛነት ሲመጡብን በኢትዮጵ ያዊነት፤ በጎጠኛነት ሲመጡብን በሰብአዊነት፤ በመግደል ሲመጡብን በማዳን፤ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሲመጡብን
በእውነት ምስክርነት፤ በጦርነት ሲመጡብን በሰላም፤ እያቃጠሉ ሲመጡ እየገነባን፤ እገሌ ይውጣ ብለው ሲመጡ እገሌ ይግባ እያልን፤
ከሚያልሙት በተቃራኒ፣ ከሚያቅዱት በተጻራሪ መሄድ ነው ያለብን፡፡
እንዳይደረግ የምንታገልለትን እኛው
ካደረግነው፤ እንዳይሆን የምንለፋለትን እኛው ከፈጸምነው፤ እንዳይመጣ የምንከላ ከለውን እኛው ካመጣነው፤ እንዳይከተል የምንደክምለትን
እኛው ከመራነው፤ የጠላቶቻችን ዓላማ አስፈጻሚዎች ሆነናል ማለት ነው፡፡
የአባ ቴዎድሮስ መንገድ - ኢትዮጵያ
እንድትበታተን ለሚሠሩት - አንድነትን፤ እንድታፍር ለሚሠሩት - ክብሯን፤ የጦር አውድማ እንድትሆን ለሚቆፍሩት - ሰላምን፤ እንድትሞት ለሚሠሩት - ትንሣኤዋን፤ እንድትዋረድ ለሚሠሩት - ልዕልናዋን
በማምጣት ከታሰበልን በተቃራኒው እንሂድ፡፡
Ewenete new gonbese bilo masalefee
ReplyDeleteEgziabher yirdan lehulum
ReplyDeleteኢትዮጵያ እንድትበታተን ለሚሠሩት - አንድነትን፤ እንድታፍር ለሚሠሩት - ክብሯን፤ የጦር አውድማ እንድትሆን ለሚቆፍሩት - ሰላምን፤ እንድትሞት ለሚሠሩት - ትንሣኤዋን፤ እንድትዋረድ ለሚሠሩት - ልዕልናዋን በማምጣት ከታሰበልን በተቃራኒው እንሂድ፡፡
ReplyDeleteኢትዮጵያ እንድትበታተን ለሚሠሩት - አንድነትን፤ እንድታፍር ለሚሠሩት - ክብሯን፤ የጦር አውድማ እንድትሆን ለሚቆፍሩት - ሰላምን፤ እንድትሞት ለሚሠሩት - ትንሣኤዋን፤ እንድትዋረድ ለሚሠሩት - ልዕልናዋን በማምጣት ከታሰበልን በተቃራኒው እንሂድ፡፡
ReplyDeletebm,n,mn
ReplyDeleteየምንጠላውን ኃጢአት ደጋግመን መሥራት የለብንም፡፡ በዘረኛነት ሲመጡብን በኢትዮጵ ያዊነት፤ በጎጠኛነት ሲመጡብን በሰብአዊነት፤ በመግደል ሲመጡብን በማዳን፤ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሲመጡብን በእውነት ምስክርነት፤ በጦርነት ሲመጡብን በሰላም፤ እያቃጠሉ ሲመጡ እየገነባን፤ እገሌ ይውጣ ብለው ሲመጡ እገሌ ይግባ እያልን፤ ከሚያልሙት በተቃራኒ፣ ከሚያቅዱት በተጻራሪ መሄድ ነው ያለብን፡፡
ReplyDeleteየዚህ ችግር ሰለባ በአብዛኛው ወጣቱ መሆኑ ቢያሳዝንም ከኃላ ሆኖ በል የሚለውና መጠቀሚያው የሚያደርገው የተማረና የበሰለ ተብሎ የሚታሰበው የገዛ ህብረተሰቡ አካል ሲሆን ደሞ ከማሳዘንም ያንገበግባል። ወጣቱ በአፍላ ስሜትና በግልፍተኝነት ዛሬ ላይ ባለማገናዘብ የሚፈፅመው ነገ ሀገሩን ሊያስከፍለው እንደሚችል ቆም ብሎ ቢያስብ እንዴት ጥሩ ነበር። የሆነ ቦታ ያነበብኩትን አባባል አስታወሰኝ። "War is where the young and stupid are tricked by the old and bitter into killing each other". እንዳንተ አይነት አዕምሮን የሚከፍት አስተማሪ በየቦታው የሚያስፈልገን ሰዐት አሁን ነው። እናመሰግናለን ዳንኤል።
ReplyDeleteArif new dn
ReplyDeleteyas d/n that is good for Ethiopia!
ReplyDeleteከታሰበልን በተቃራኒው እንሂድ
ReplyDeleteexcellent view. MAY GOD bless you and your family
ReplyDeletethis is the only truth way i can't able to say anything you are real true man of Ethiopia.
ReplyDeleteትክክል
ReplyDeleteewnet yewsten hasab migeltsibet amarigna atiche enji yihe hasab wiste nber..amesegnalew
ReplyDeleteየአባ ቴዎድሮስ መንገድ - ኢትዮጵያ እንድትበታተን ለሚሠሩት - አንድነትን፤ እንድታፍር ለሚሠሩት - ክብሯን፤ የጦር አውድማ እንድትሆን ለሚቆፍሩት - ሰላምን፤ እንድትሞት ለሚሠሩት - ትንሣኤዋን፤ እንድትዋረድ ለሚሠሩት - ልዕልናዋን በማምጣት ከታሰበልን በተቃራኒው እንሂድ፡፡
ReplyDeleteጥሩ ነው!
ReplyDeleteThat is a great perspective! Thank you, Dn. Daniel.
ReplyDeleteEwunet New
ReplyDelete