Sunday, December 10, 2017

ራእየ ዮሐንስ (ክልስ እትም)


የራእየ ዮሐንስን የማብራሪያ መጽሐፍ ስትጠይቁኝ ለነበራችሁ፡፡ ከዚህ በፊት የታተመው መጽሐፍ ሁለት ችግሮች ነበሩበት፡፡ የፊደሉ መድቀቅና በወቅቱ ከግሪክ ቋንቋ ውጭ ባለመተርጎማቸው ሊካተቱ ያልቻሉ ቀደምት አበው ትርጓሜያት፡፡ ለብዙ ዓመታት ከገበያ ጠፍቶ የከረመውም እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ጊዜ በመውሰዱ ነው፡፡ አሁን አዳዲስ መረጃዎችንና ቀደምት አበው የሰጧቸውን ማብራሪያዎች በመጨመር ክልስ እትም (revised edition)በመታተም ላይ ነው፡፡ የገጹ ብዛት ከ600 በላይ ሲሆን የፊደሉ መጠንም ባለ 12 ፎንት ተደርጓል፡፡ የመጽሐፉ ስፋትም በአራቱ ኃያላን መጽሐፍ መጠን ሆኗል፡፡ በተለይም የፍጥሞ ደሴት የቅዱስ ዮሐንስ ገዳም ሊቃውንት ከቀድሞ ጀምሮ የነበሩ አበው በሰጧቸው ትርጓሜዎች ላይ ተመሥርተው ያዘጋጁት ባለ 4 ቅጽ ትርጓሜ ተካትቶበታል፡፡ የተወሰኑ ቅጅዎችን በጠንካራ ሽፋን (Hard cover) እያዘጋጀን ነው፡፡
በታኅሣሥ መጨረሻ ገበያ ላይ ይውላል፡፡

1 comment:

  1. እግዚአብሔር ይባርክህ …..ግን ለመሆኑ አቡነ ሺኖዳ ካሳተሙት ሐተታ ራእየ ዮሐንስ ከሚለው መፅሐፍ ብዙ የሚለይ ሀሳብ አካተህበታል ወይስ….. የእሳቸው መጽሐፍ ስላለኝ መግዛት ካለብኝ ለመወሰን ነው፡፡

    ReplyDelete