አንድ አገልጋይ በመንፈሳዊ ሕይወቱ
እየተጠቀመ መሆኑ የሚታወቀው የአገልግሎት ዘመኑ እየጨመረ ሲሄድ ትኅትናው እየጨመረ ከመጣ ነው፡፡ የአገልግሎት ብርታትና ጥንካሬ
በዕውቀት መጨመር ወይም በታዋቂነት ብዛት ብቻ አይለካም፡፡ ብዙ ቦታዎችን በማዳረስና ብዙ ነገሮችንም በመሥራት ብቻ አይመዘንም፡፡
ከኢየሩሳሌም ያልወጣው ቅዱስ ያዕቆብ ነው ከሐዋርያት መካከል የመጀመሪያውን አክሊል የተቀዳጀው(የሐዋ12)፡፡ ከፊት በመምጣት ወይም
ከኋላ በመነሣትም አይታወቅም፡፡ መጀመሪያ ከተጠሩት ወገን የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስና በመጨረሻ የተጠራው ቅዱስ ጳውሎስ በአንድ ቀን
ነው የሰማዕትነት አክሊል የተቀበሉት፡፡ ሊቁ አውግስጢኖስ ‹ኢየሱስ ክርስቶስ አልፋና ዖሜጋ ስለሆነ. ነው ይላል፡፡
የአገልጋይ ብቃት በዋናነት የሚለካው
በትኁት ሰብእና ነው፡፡ ይበልጥ ባገለገለ ቁጥር ይበልጥ ክርስቶስን ያውቃል፡፡ ይበልጥም ክርስቶስን ባወቀ ቁጥር ይበልጥ ራሱን ያውቃል፡፡
ይበልጥ ራሱን ባወቀ ቁጥርም ይበልጥ ድካሙን ይረዳል፤ ይበልጥ ድካሙን በተረዳ ቁጥርም ይበልጥ ትኁት ይሆናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን
የምትጠቀመው ራሳቸውን የሚያውቁ አገልጋዮችን በማፍራት እንጂ ብዙ ነገር የሚያውቁ አገልጋዮችን በማፍራት አይደለም፡፡ ዕውቀት የሚጠቅመው
ራስን በማወቅ ውስጥ ከተቀመጠ ነው፡፡ ያለበለዚያ ዕውቀት ያስታብያል(1ኛቆሮ. 8÷1)፡፡