አሁን የዘነጋሁት አንድ የጎንደር
ቅኔ እንዲህ ይላል፡፡ ባለቅኔው አንድ ድግስ ላይ ይጠራሉ፡፡ ገበታም ላይ ይሰየማሉ፡፡ ጠጅ አሳላፊው ይመጣና በተሰነጠቀ የሸክላ
ዋንጫ ጠጅ ይቀዳላቸዋል፡፡ እያዘኑ ተቀብለው ጠጁን ቀመስ ያደርጉታል፡፡ ‹ከመ ወይን ጣዕሙ› የሚባልለት ዓይነት ነው፡፡ ጠጁንና
የቀረበበትን ዋንጫ አስተያይተው ‹ዋንጫው በጠጁ ከብሯል፣ ጠጁ ግን በዋንጫው ተዋርዷል፣ ዋንጫው ጠጁን ይዞ ይስቃል፣ ጠጁ ግን ዋንጫው
ውስጥ ገብቶ ያለቅሳል› የሚል ቅኔ ተቀኙ ይባላል፡፡ ያ ሰባራ ዋንጫ ያንን ለመሰለ ምርጥ ጠጅ መጠጫ መሆኑ የማያገኘው ክብርና ዕድል
ነው፡፡ እንደ ባሕሉ ቢሆን የተሰነጠቀ ዋንጫ የቅራሪ መጠጫ ከመሆን ያለፈ ክብር አልነበረውምና፡፡ ለጠጁ ግን በሰንጣቃ ዋንጫ መቅረቡ
ውርደት ነው፡፡ እንዲህ ያለው ጠጅ ሲሆን የወርቅ፣ ሲቀር ደግሞ የቀንድ ዋንጫ ይገባው ነበር፡፡
አንዳንድ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ
ክብር ጋር በማይመጥኑ ሰዎች እጅ ወድቀው ሳይ የእኒህ ጎንደሬ ቅኔ ትዝ ይለኛል፡፡ ለነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያን የምታህል የታሪክ ሀገር፣
የቅርስ ሀገር፣ የነጻነት ሀገር፣ የጥበብ ሀገር፣ የጀግኖች ሀገር፣ የልዩ ልዩ ባሕሎችና ወጎች ሀገር በእጃቸው መግባቷ በሥዕለት
የማያገኙት ክብራቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ናትና፡፡ ለኢትዮጵያ ግን በእነዚህ በማይመጥኗት ሰዎች እጅ መውደቋ ውርደቷ ነው፡፡
እነርሱ ሲስቁ፣ ኢትዮጵያ ታለቅሳለች፡፡
‹የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ጳጉሜ
5/6 እኩለ ሌሊት አይገባም› የሚለውን መስማት የማይፈልጉ ሰዎች ጊዜውና ሁኔታው ፈቅዶላቸው ጣፋጯ ጠጅ ኢትዮጵያ እንደ ሰባራው
ዋንጫ በእጃቸው ስለገባችላቸው ብቻ አሁንም ‹በከፍታው ዘመን› ሲያወርዷት አየናቸው፡፡ የእጅ ሰዓታቸው ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት እያለ፣
በሥልጣናቸው ከጠዋቱ 12 ሰዓት አደረጉት፡፡ ወይ አይረዱ ወይ አያስረዱ፤ ሰው እንዴት ከሁለቱም ይወጣል? ወይ እኩለ ሌሊት አዲስ
ዓመት ገብቷል ሲሉ መከራከሪያውን አምጥቶ ማስረዳት ነው፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ የሚቀርበውን መከራከሪያ መቀበል ነው፡፡ የኢትዮጵያ
ዕለት በእኩለ ሌሊት ይገባል ከተባለ፣ በእኩለ ሌሊት የሚገባው መስከረም 1 ቀን ብቻ ነውን? ለምን መስከረም ሁለትስ በእኩለ ሌሊት
አይገባም? ሞቅታ ዕውቀትና እውነትን እየሻረ እስከመቼ መጓዝ ይቻላል? ሀገር ከፍ የምትለው በጭፈራና በሆታ አይደለም፡፡ በእውነትና
በዕውቀት እንጂ፡፡ ችግሩ ግን አሁን ኢትዮጵያ በእጃቸው የገባችላቸው አንዳንድ ሰዎች እውነትም ዕውቀትም የማይፈልጉ መሆናቸው ነው፡፡
ዕውቀት ወደ እውነት፣ እውነትም ወደ ቆራጥነት ይመራልና፡፡ አውሮፕላኑን አብርር ተብሎ ሲሰጥህኮ በተፈቀደልህ ከፍታ፣ በተፈቀደልህ
ፍጥነት፣ በተፈቀደልህ ሕግ መሠረት፣ ወደተፈቀደልህ ቦታ፣ አብርር ማለት እንጂ መሪው እጅህ ስለገባ ብቻ ወደፈለግከው ቦታ በፈለግከው
መንገድ ይዘህ መሄድ አትችልም፡፡
ሌሊት እንጨፍር፣ ሌሊት ርችት እንተኩስ፣
ሌሊት እንጠጣ ማለት ይቻላል፡፡ የእነርሱ ጭፈራ፣ የእነርሱ አሥረሽ ምችውና ርችት እንዲያምር ስለተፈለገ ግን የኢትዮጵያ ታሪክና
ቅርስ መናድ የለበትም፡፡ የኢትዮጵያ ሚሊኒየም የተከበረበትን ዐሥረኛ ዓመት አከበርን እያልን በሚሊኒየሙ ጊዜ ስናወድሰው የነበረውን
ቅርስ ማበላሸት አለብን? ‹ኢትዮጵያ የራሷ የዘመን አቆጣጠር ያላት ሀገር ናት› ስንል አልነበረም እንዴ ያኔ? ዛሬ በዐሥር ዓመቱ
ረስተነው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በእኩለ ሌሊት ለምን ዘመኑን አባትነው? መሠረቱን እያፈረሱስ ከፍታ እንዴት ይገኛል? መቀየርም
ካስፈለገ ለተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ፣ በምክንያት መቀየር የሚችለው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር በሥልጣኑ ይህን የኢትዮጵያ
ታሪክ ለምን አባሪ ተባባሪ ሆኖ ሊቀይር ፈለገ?
ዕውቀት ሥልጣን ይሰጣል፤ ሥልጣን
ግን ዕውቀት አይሰጥም፡፡ ጊዜ ሥልጣን ይሰጣል፣ ጊዜ ግን ዕውቀት አይሰጥም፡፡ ለዚህም ነው ጊዜ የሰጠው ቅል በድንጋይ ቤት አይሠራም፣
ድንጋይ ይሰብራል እንጂ የተባለው፡፡
በጣልያን ወረራ ጊዜ ጊዜ ሰጠን
ብለው እሙር እሙር ይሉ የነበሩትን ሰዎች
‹አርኩም ይሄድና
ሶልዲውም ያልቅና
ያስተዛዝበናል ይሄ ቀን ያልፍና›
ብሎ ነበር ሐበሻ፡፡ እንዲህ ዛሬ
መድረኩ በእግራችሁ፣ ማይክራፎኑ በእጃችሁ፣ ሚዲያው በፊርማችሁ ሥር ስለሆነ ብቻ የፈለጋችሁትን ታሪክ ሠርዛችሁ የፈለጋችሁትን ለምትጽፉ
‹አርቲስቶች›፣ ለምታስጽፉም ባለሥልጣናት
መድረክ ይፈርስና
ማይኩም ይጠፋና
ሥልጣኑም ያልቅና
ያስተዛዝበናል አግዳሚ ወንበር ላይ
እንገናኝና፤
እንላችኋለን፡፡
I like it
ReplyDeleteበቀንማ ለማብሰር እውቀት ይጠይቃል ታሪክን ማገላበጥ ይጠይቃል ቀንማ አገሪቱ በሩቅ አሳቢና ብሩህ አእምሮ ወደፊትም ወደኃላም መመልከት ይጠይቃል ይህ ሁሉ የመመልከቻና የመመርመሪያ አእምሮ ስለሌለ ይመስላል ጨለማን ተገን አድርጎ የሀገሪቱ ታሪክ ትውፊትና የቀን ቆጠራ
ReplyDeleteBe EBS binebebelen(be ETV fikad selemiasfeleg new lemanbeb) thank you
ReplyDeleteዳኒ እንኳን አደረሰህ እንዳንተ አይነት ሰዎች ቢበዙልን እንዲህ መቀለጃ አንሆንም ሰዎቻችን ላይ እንስራ!!!!!!! ይህ የሚያሳየው ያልተሰራ ብዙ የቤት ሥራ እንዳለን ነው፡፡ መልካም የሥራ ዘመን፡፡
ReplyDeleteዕውቀት ሥልጣን ይሰጣል፤ ሥልጣን ግን ዕውቀት አይሰጥም፡፡ ጊዜ ሥልጣን ይሰጣል፣ ጊዜ ግን ዕውቀት አይሰጥም፡፡ ለዚህም ነው ጊዜ የሰጠው ቅል በድንጋይ ቤት አይሠራም፣ ድንጋይ ይሰብራል እንጂ የተባለው...Great idea if they learn from they mistake
ReplyDelete<> ‹‹ ወይ አይረዱ ወይ አያስረዱ፤ ››
ReplyDeleteእድሜ ይስጥህ ወንድሜ !!!!!!!
TEMESGIN AMELAKIE EWENETIEN BEDEFERET EMENAGER MEKARIE SELASATAHEN.
ReplyDeleteመድረክ ይፈርስና
ReplyDeleteማይኩም ይጠፋና
ሥልጣኑም ያልቅና
ያስተዛዝበናል አግዳሚ ወንበር ላይ እንገናኝና፤
መሠረቱን እያፈረሱ ከፍታ እንዴት ይገኛል?
ReplyDeletewish you a long life !
ReplyDeleteEGZIABHER yistilgn dani ende libe new yetenagerkew hul gize man yihon yihen neger mige thanks Daniye
ReplyDeleteለኢትዮጵያ ግን በእነዚህ በማይመጥኗት ሰዎች እጅ መውደቋ ውርደቷ ነው፡፡ እነርሱ ሲስቁ፣ ኢትዮጵያ ታለቅሳለች፡፡
ReplyDeleteከሁሉ አስቀድሜ የተከበረ ስላምታየን እያቀረብሁ ከጉዳዩ ጋር ባይገናኝም አንድ በጣም የቸገረኝ ነገር ስላለ በእሱ ጉዳይ ሊያስተምር የሚችል ነገር እንድትጽፍልኝ ፈልጌ ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ አሁን አሁን በየገዳማቱና በየአድባራቱ ያሉ መነኮሳት እና አባቶች ወይም ካህናት ነን የሚሉ ሰዎች የሰዎችን ህይወት እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትን አደጋ ውስጥ እየጣሉት ይገኛል፡፡ ይህም ሲባለ የሁለት ፍቅረኛሞችን ህይዎት መንፈስ ቅዱስ እንደነገረኝ፣ በህልም እንዳየሁለሽ፣ እሱን አታገቢም፣ እሱ ባልሽ አይደለም ፊችው በማለት ስንቶች ሊጋቡ የነበሩ ጥንዶችን እና የስንቱን ቤተሰብ ትዳር መስርተው በመኖር ላይ ያሉትን ሳይቀር እያለያዩ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ዳንግላ አካባቢ የሚገኝ ገዳም ውስጥ ያሉ መነኩሴ አይሉት ጠንቃየ፣ መራዊ ዙሪያ ያለ አንድ ቤተክርስትያን ዉስጥ፣ ባህር ዳር ዙሪያ ያለ አቡነ ሃራ የሚባል ገዳም ዉስጥ ያሉ አባቶች በተለይም ሴት እህቶቻችንን ስህተት ዉስጥ እየከተታቸው ይገኛል፡፡አማኞችንም ፈተና ውስጥ ከትታል፡፡ እባክህ ሊያስተምረ የሚችል ነገር ጻፍ፡፡
ReplyDeleteYes ...you are right...we are losing many things however..we have a big hope..
ReplyDeleteልቡን ለነሳው ልብ ይስጥልን
ReplyDeleteእውቀት ለሌለው አድማጭ ጆሮና አንባቢ አይን ይስጥልን፡፡
የማታውቁ ለማወቅ ቅን ልቦና ይኑራችሁ
ዳኒ እግዚአብሔር አገልግሎትህን ይባርክልህ፡፡
ግዜክስ
You are wrong at this time please check how we start new days at the midnight, for example,fasting days start at the midnight.
ReplyDeleteየኢትዮጵያ ዕለት በእኩለ ሌሊት ይገባል ከተባለ፣ በእኩለ ሌሊት የሚገባው መስከረም 1 ቀን ብቻ ነውን? ለምን መስከረም ሁለትስ በእኩለ ሌሊት አይገባም? ሞቅታ ዕውቀትና እውነትን እየሻረ እስከመቼ መጓዝ ይቻላል?
ReplyDeleteእድሜና ጤና ይስጥህ፡፡
ReplyDeleteጊዜ ዕውቀት አይሰጥምን??
ReplyDeleteጥያቄህን ተረዳሁት ፣ ነገር ግን ከአገባቡ ለመረዳት የሚቻለው ወይም የሚያግባባው፣ ቁጭ ብሎ የኖረ አለ ዕውቀትc አጋጣሚ ፈቅዶለት ይሾማል። ቁጭ ብሎ በመኖሩ ግን/አለሥራ ምግባር ጥረት ትምሕርት/ ዐዋቂ ሊባል አይችልም።
DeleteYou didn't mention the time when the new year starts
ReplyDeleteewnet blehal Dn. Daniel, "lebeluat yasebuaten jegra yeluatal Doro" aydel yehagere sew yalew
ReplyDeleteመድረክ ይፈርስና
ReplyDeleteማይኩም ይጠፋና
ሥልጣኑም ያልቅና
ያስተዛዝበናል አግዳሚ ወንበር ላይ እንገናኝና፤
የአዲስ ዓመት መለወጫ ሰዓትን በተመለከተ ማኅበረ ቅዱሳን መስከረም 06/2010 ዓ.ም በድረ ገጹ ያወጣውና አንተ የጻፍኸው የተለያየ ስለመሰለኝ በሚያስማማ መንገድ ቢገለጽ መልካም ይመስለኛል፡፡ በድረ ገጹ ላይ ዲያቆን ኃይለ ኢየሱስ ቢያ እንደጻፈው በሁሉም ዘመናት አዲስ ዓመት የሚጀምረው ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ አይመስልም፤ ይለያያል፡፡ ጸሐፊው “የዘመናት አከፋፈል በአራቱ ወንጌላውያን እና ዘመን የሚለወጥበት ሰዓት” በሚል ርእስ የሚከተለውን አስፍሯል፡-
ReplyDelete• ማቴዎስ ዘመኑን ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ይፈጽማል፡፡
• ማርቆስ ዘመኑን ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ይፈጽማል፡፡
• ሉቃስ ዘመኑን ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት (በቀትር) ይፈጽማል፡፡
• ዮሐንስ ዘመኑን ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከቀትር በኋላ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ይፈጽማል፡፡
አንተ ደግሞ “‹የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ጳጉሜ[ን] 5/6 እኩለ ሌሊት አይገባም› የሚለውን መስማት የማይፈልጉ ሰዎች ጊዜውና ሁኔታው ፈቅዶላቸው ጣፋጯ ጠጅ ኢትዮጵያ እንደ ሰባራው ዋንጫ በእጃቸው ስለገባችላቸው ብቻ አሁንም ‹በከፍታው ዘመን› ሲያወርዷት አየናቸው፡፡ የእጅ ሰዓታቸው ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት እያለ፣ በሥልጣናቸው ከጠዋቱ 12 ሰዓት አደረጉት፡፡ ወይ አይረዱ ወይ አያስረዱ፤ ሰው እንዴት ከሁለቱም ይወጣል?” ትለናለህ፡፡
ለመሆኑ የትኛው ነው ትክክል?
Fetari yibarkih bergit enezihin sewoch tekerarbachihu bitinegageruna sitetoch tarimew tarik bewegu biketil mignote new Daniye.
ReplyDeleteጆሮ ካላቸዉ ጥሩ ምክር ነው።
ReplyDeleteGod bless you.
ReplyDeleteteru new
ReplyDeletelela menem yemleh yelem deyakon edmehen yarezemlen!!! egzyabher yetebkeh
ReplyDeletedaniel buzum comment alsetihim ..........ahun gin lingerih esketefekedelih wedefit hid. yesemah yisemal yalsemah yegun yagegnal.
ReplyDeletethis is just one aspect of the gradual loss of Ethiopian heritage that you have mentioned. it has been going on in different locations, forms, and occasions. it seems like a certain group is trying to remould the shape of this country; but with malicious intentions. we should all be careful and keep watch of our heritages and values because by the end of the day, if we lose those pillars, it will surely be difficult to define our identity.
ReplyDeleteእንዲህ ዛሬ መድረኩ በእግራችሁ፣ ማይክራፎኑ በእጃችሁ፣ ሚዲያው በፊርማችሁ ሥር ስለሆነ ብቻ የፈለጋችሁትን ታሪክ ሠርዛችሁ የፈለጋችሁትን ለምትጽፉ ‹አርቲስቶች›፣ ለምታስጽፉም ባለሥልጣናት
ReplyDeleteመድረክ ይፈርስና
ማይኩም ይጠፋና
ሥልጣኑም ያልቅና
ያስተዛዝበናል አግዳሚ ወንበር ላይ እንገናኝና፤
እንላችኋለን፡፡
መድረክ ይፈርስና
ReplyDeleteማይኩም ይጠፋና
ሥልጣኑም ያልቅና
ያስተዛዝበናል አግዳሚ ወንበር ላይ እንገናኝና፤
መድረክ ይፈርስና
ReplyDeleteማይኩም ይጠፋና
ሥልጣኑም ያልቅና
ያስተዛዝበናል አግዳሚ ወንበር ላይ እንገናኝና፤
መድረክ ይፈርስና
ReplyDeleteማይኩም ይጠፋና
ሥልጣኑም ያልቅና
ያስተዛዝበናል አግዳሚ ወንበር ላይ እንገናኝና፤
ዕውቀት ሥልጣን ይሰጣል፤ ሥልጣን ግን ዕውቀት አይሰጥም፡፡ ጊዜ ሥልጣን ይሰጣል፣ ጊዜ ግን ዕውቀት አይሰጥም፡፡ ለዚህም ነው ጊዜ የሰጠው ቅል በድንጋይ ቤት አይሠራም፣ ድንጋይ ይሰብራል እንጂ የተባለው። ዳን ዘመንህን አምላክ ይባርክልህ!
ReplyDeletedani ante yemtgerm temeramari neh
ReplyDeleteGreat
ReplyDelete