Tuesday, July 18, 2017

<እኔ ጵጵስና የተሾምኩበትን ቀን የማስታውሰው በኀዘንና በልቅሶ ነው>


ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ወደ ጵጵስናው የመጡት ብዙ ጫና ተደርጎባቸው ነበር፡፡ ከጵጵስናው ይልቅ በሶርያውያን ገዳም መኖርን ይመርጡ ነበር፡፡ ሺኖዳ የኮሌጅ ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ምኞታቸው እንደ አባ ገብረ ክርስቶስ በበረሓ መኖር ነበር፡፡ የወቅቱ ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ ግን ገዳሙን እንዲረዱ ወደ ሶርያውያን ገዳም ላኳቸው፡፡ በወቅቱ የነበሩት የገዳሙ አበው ሺኖዳ ለገዳሙ መሻሻል የሚሠሩትን ሥራ አልወደዱትም፡፡ የኢትዮጵያዊው የገብረ ክርስቶስ (አብዱል መሲሕ) ደቀ መዝሙር የነበሩት ሺኖዳ (በጥንቱ ስማቸው አባ እንጦንስ) ግን መከራውን ሁሉ ተቋቋሙት፡፡ በመጨረሻም አቡነ ቄርሎስ ገዳሙን እንዲያስተዳድሩ በጫና ሾሟቸው፡፡ በኃላፊነታቸው ላይ እያሉ ግን እርሳቸው ለገዳሙ መሻሻል የሚሠሩትን ሥራ ያልወደዱ መነኮሳት ተነሡባቸው፡፡ ለፓትርያርኩም ከሰሷቸው፡፡ ፓትርያርኩም አባ እንጦንስን ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ጠሯቸው፡፡ ሺኖዳም ከሳሾቻቸው ትክክል እርሳቸው ግን ስሕተት መሆናቸውን ገልጡ፡፡ ይህ ፈተና የመጣውም በእርሳቸው ድክመት እንጂ በከሰሷቸው አባቶች ምክንያት እንዳልሆነ ተናገሩ፡፡ ስለዚህም ከኃላፊነት እንዲነሡና ወደ በረሓ ገብተው በምናኔ እንዲኖሩ የፓትርያርኩን ፈቃድ ጠየቁ፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ ግን ውሳኔያቸውን በማግሥቱ እንደሚያሳውቋቸው ነግረው በመንበረ ፓትርያርኩ እንዲቆዩ አደረጉ፡፡
በማግሥቱ ሴፕቴምበር 30 ቀን 1962 ዓም አቡነ ቄርሎስ አቡነ እንጦንስን ለውሳኔው ጠሯቸው፡፡ አባ እንጦንስም ወደ በረሓው የሚመለሱበትን ቀን እየናፈቁ ጠበቁ፡፡ አቡነ ቄርሎስም እጃቸውን በአቡነ ሺኖዳ ላይ ጭነው ‹የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የነገረ መለኮትና የትምህርት ጉዳዮች ጳጳስ› አድርገው ሳያስቡት ሾሟቸው፡፡
ይህ በተፈጸመ ሰሞን የትምህርት ቤት ጓደኛቸውና የብዙ ጊዜ ወዳጃቸው ጀርመናዊው ፕሮቴስታንትና በካይሮ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የኮፕቲክ ጉዳዮች ፕሮፌሰር ዶክተር ሜናድረስ (Dr. Otto Meinardus) ‹እንኳን ደስ ያለዎት› የሚል የደስታ መግለጫ ደብዳቤ ላከላቸው፡፡ ብጹዕ አቡነ ሺኖዳም ደብዳቤውን በደስታ ከተቀበሉ በኋላ የሚከተለውን መልስ ላኩለት፡፡ 

‹ሰላምና ጸጋ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይሁንልህ፡፡ ስለ ላክህልኝ የደስታ መግለጫ መልእክት ምስጋናዬን አቀርብልሃለሁ፡፡ ወዳጅነትህንና ፍቅርህን መቼም አልዘነጋውም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን እንዲህ ላለው (ለጵጵስናው ሹመት) ጊዜ የኀዘን መግለጫ እንጂ የደስታ መግለጫ አይስማማውም፡፡ አንድ መነኩሴ ጸጥታ የነገሠበትን በረሓ ትቶ ውጥንቅጡ ወደ በዛ ከተማ ሲገባ እንዴት እንኳን ደስ ያለህ ይባላል? በክርስቶስ እግር ሥር መቀመጧን ትታ እኅቷ ማርታ ወደምትደክምበት የማድቤት ሥራ ስትመለስ ማርያምን ማነው እንኳን ደስ አለሽ የሚላት? ለእኔ ይህ አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ እኔ ጵጵስና የተሾምኩበትን ቀን የማስታውሰው በኀዘንና በልቅሶ ነው፡፡ እውነት ለመናገር የምናኔና የጸሎት ሕይወት ከማንኛውም መለኪያ በላይ ነው፡፡ ከኤጲስቆጶስነትም ሆነ ከጵጵስና ጋር የሚወዳደር አይደለም፡፡ ወዳጄ ሆይ እውነተኛው መቀባት (ለጵጵስና መቀባት ሳይሆን) ልብን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ መቅደስ አድርጎ መቀባት ነው፡፡ እርሱ በመጨረሻው ቀን የሚጠይቀን ማዕረጋችንን ሳይሆን ንጹሕ ልባችንን ነውና፡፡ ይህንን የምጽፍልህ በዋዲ - ኤል - ናትሩን፣ ባሕር - ኤል - ፋሬግ ከሚገኘው ከምወደው ዋሻዬ ውስጥ ውስጥ ሆኜ ነው፡፡ በዚህ ቦታ እስከ ጥምቀት በዓል ድረስ ለመቆየት አስባለሁ፡፡ ከዚያም ወዲያ ወደ ካይሮ እመለሳለሁ፡፡

ለተሾሙት ጳጳሳት በየአካባቢው የሚደረገውን ድግስ ስመለከት ይህ ትዝ አለኝ፡፡ 

Otto Friedrich August Meinardus, Two Thousand Years of Coptic Christianity,1999, p. 5

7 comments:

 1. dani lefa bilh new zre eko abatochachen be egrachew teguzew Yakoyuat batekrstian be V-8 Enkua ligobegnun Yiteyfunal eko.mechem Enzih sewoch Menekusa mohonachewn Eteratralhu.Abun Teklehaymanote Ke Haique Estifanose Asekama likbelu Debredamo mn Endgetemachew Tawuk Ylem???Patriariku Dessie metew eko HaiQue Estifanose Ymesel gedam Tetew Ye 4000 birr Hotel eko new Yadrut.

  ReplyDelete
 2. የቅዱስነታቸው የአቡነ ሽኖዳ ቡራኬ ትድርሰን፣ትክክል ብለዋል፣አሁን እኮ ጳጳስ ሆኑ ማለት ጡረታ ወጡ ማለት መሰለኝ።የንግሥ በዓል ሲመጣ ቡራኬ ከመስጠትና ከዲያቆንና ቄስ ራስ ላይ እጅን ከመጫን ውጭ የትኛው አገልግሎታቸው ነው?በዚያ ላይ ድግሱና የስጦታው መብዛት እኮ ለአንዳንዶች ለጉቦ ወጭ ላደረጉት ገንዘብ ማግኛ ገቢ ማሰባሰቢያ ይመስላል፣

  ReplyDelete
 3. ሀሳብህና ትጋትህን በጣም አደንቃለሁ በእግዚህአበሔር ቤት ደስታና ፈንጠዝያን ማየት ከጀመርን ቆየት ብለናል ከእግዚህአበሔር ጋር በድሎት መኖር እንዴት እንደሚቻል አይገባኝም መፅሐፍ ቅዱስ ያንንም ይህንንም በግልፅና በአንክሮ ይደነግገጋል እኛ ግን የተዘረዘሩልን የእግዚአሐብሔርን ሕጎች እየጣስን ለማይገባን በትጋት ለማንወጣው ስልጣን እግዚአሐብሔርን እያሳዘንን ነው፡፡ ውድ ዳኒ ፃፍ ሀሳብህን አስፍር በእግዚአሐብሔር የተሰጠህን መክሊት አውጣ እስተምረን፣ አሳስበን፣ ማይታየንን አሳይን እግዚአሐብሔር ዘመንህን ያባርክ፡፡

  ReplyDelete
 4. እግዚአብሔር ዕድሜና ጤናውን ያድልህ!!!

  ReplyDelete
 5. Dik Daniel Kibiret Thank you very much for your Inspirational Writing!!!
  እንደኔ መረዳት የገዳም ህይወት ለጾምና ለጸሎት መትጊያ፣ በተቀደሰ መለኮታዊ ኃይል መሞያ ማዕከል ነው፡፡ እንደኔ ጵጵስና ከዋሻ ኑሮ በተለየ በደስታ ምትክ የለቅሶ መግለጫ የሚያሻው ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፡፡
  1- ቅዱስ አምላከችን እየሱስ ክርስቶስ እንኳን በገዳም 40 ቀንና ሌሊት በፆምና በጸሎት ቆይቷል፤ ነገር ግን ሁሉንም ነገሩ ገዳም ውሥጥ ጀምሮ እነዲያበቃ ሲያደርግ አላየንም፤ይልቁንም በትውልድ ሁሉ ብፅት ለምትባል፣ ብፅት ቅድስት ድንግል ማርያም ሲታዘዝ፣ በየቦታው እየተዘዋወረ ሲያስተምር፣ሲፈወሰ፣ሽባን ሲተረትር፣በረከትን ፣ታምራትን ሲገልጥ ፣የአምላክ መመለኪያ ስፍራ ምን መምሰል እንዳለበት ሲያስተምር፣ሲሟገት፣ በጠላቶች ሲፈተን፣ በሠይጣን ሲፈተን-ሰይጣንን ሲያዋርድ፣አዋቂነን ባዮችን/ፈታኞችን እንዲመረምሩት ሲፈቅድ፣ እውነትን ቀና መንገድን ሲያሳይ ቅዱስ መጸፍ ያስነብብናል፡፡

  2- ሐዋሪያትም ለዓለም ብረሃን እንዲሆኑ፣ ወደ ዓለም እንዲሄዱ ፣ዓለምን ሁሉ እንዲያቀኑ ፣ የክርስቶስ እየሱስን ብረሃን ለዓለም ሁሉ እንዲገልፁ፤ወደ ዓለም ሁሉ እንዲወጡ እንጂ ከዓለም ተሸሽገው ወደ ዋሻ እንዲገቡ በዛም እንዲወሰኑ የሚል ቃል አልገጠመኝም፤ከተሳሳትኩ ልታረም?

  3- እርግጥነው በዓለም እየኖሩ የክርስቶስን ዳና መከተል፣ ለክርስቶስ ብረሃን መቅናት፣ ለክርስቶስ ሰማያዊ መንገድ ጠራጊነት መታተር፤ ትልቅ ዋጋን ያስከፍላል፡፡

  - ለጌታችንና መድሓኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአጥያተኞች መገፋት፣መዋረድ፣ መሰቃየት፣ ግርፋት፣መስቀል መሸከም፣ መሰቀል ፣መሞት በዓለም እየኖረ ሰማያዊ ሕይወትን ስለሰበከ፣ ቅድስናን በዓለም ለማስረፅ ስለደከመ ፣ ስለታገል እንጂ በገዳመ ቆረንጦስ ቢቆይ ለቄሳርም ሆነ ለዘመኑ ካዕናት እመም ባልሆነ፣

  - እነቅዱስ ጳውሎስ በዓለም እየኖሩ ሰማያዊ ሕይወትን ባይሰብኩ፣ በገዳም ብቻ ተሸሸገው ቢኖሩ ኖሮ፤ ለመከራ፣ለመወገዝ፣ለመሳደድ፣ አንገታቸውን ለሰይፍ ለመስጠት ባልተገደዱ

  - እንቅዱስ ጴጥሮስ በዓለም እየኖሩ ሰማያዊ ሕይወትን ባይሰብኩ፣ በገዳም ብቻ ተሸሸገው ቢኖሩ ኖሮ፤
  ለመከራ፣ ለመወገዝ፣ለመሳደድ፣ ለመሰቀል ባልተገደዱ፤

  - እነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመጥቀስ የሚታክት መሰቃየት( መገረፍ፣በወፍጮ መፈጨት፣በመርዝ መመረዝ…) የተቀበሉት በዓለም ኖረው ክርስቶስን ስለሰበኩ እንጂማ ወደ ዋሻ ቢወርዱ ኖሮ ማን ይነካቸዋል፤እንደውም ለዓለም ፈተና፣ሙገሳ፣ድሎት እምቢ ባይሉ እኮ ቅዱስ ጊዮርጊስ ምንም መከራ ባላተቀበለ፤ ቢሸሽ ፣ቢርቅ በዋሻ ቢሸሸግ ንጉሱ ባላተጣላው፤ ከዚ ሁሉ መከረ በራቀ ነበር፡፡ ከንጉሰ ጋር ያለው ጸብ እኮ ብዙዎችን ክርስቲያን እያደረገ አማልክቶቻችንን እንዳይመለኩ አድርጉዋል፤ አማልክቶቻችንን ድንጋይ ብለ አዋርዶብናል የሚል ነው፡፡


  - በዓለም እየኖሩ ሰማያዊ ሕይወትን ከመስበክ በላይ፣ በዓለም እየኖሩ ለጸሎትና ጾም ከመትጋት በላይ ፣በዓለም እየኖሩ በዓለም መጥፎ ትሩፋቶች ላለመዝቀጥ ከመፈተን በላይ ፣ በዓለም እየኖሩ ፍጥረተ ክርስቶስ (ሰው) ሲገፋ አብረው ገልተገፉ፣ ሲታመም አብረው ካልታመሙ፣ሲራብ አብረው ካልተራቡ፣አጋር ሆነው ወደ ሕያው መንገድ አቅጣጫን ካላሳዩት እንዴት ከመከራ ሸሽቶ፣ከዓለም ግፊያና ፣ተንኮል ርቆ ስሊዚች ዓለም ሰው ምትጋት ይቸል ይሆን??
  ወደ ዓለም ሁሉ ውጡ …ለዓለም ብረሃን ሁንዋት እንጂ..የጋን ውሥጥ መብራት ሁኑ የሚል አላየውም፡፡መንፈሳዊ ኮሌጆች ለምን ይጠቅማሉ ታዲያ? በብረሃን፣በዕውቀት የታጨቀ ማንነትን ለመፍጠር አይደለምን? ወደዓለም የታጨቀውን ዕውቀትና ልምድ እንዲሻገር ድልድይ እንዲሆኑ የተዘጋጁ እንጂ በዋሻ እንዲቀሩ ከቶ እንዳልታቀደ አምናለው፡፡
  እርግጥ ነው በዓለም አያሌ ፈተናዎች ተጋርጠውብናል፡፡ ያንን ሁሉ ፈተና አልፎ ፣ የክርስቶስን ሰማያዊ መንገድ መከተል ብሉም ደቀመዝሙራትን ማፍራት ቀሊል የማይባል ታላቅ ሸክም ነው፡፡
  ሸክምን ያልፈሩ በዓለም እየኖሩ ሰማያዊ መንገድን ይከተላሉ፣ዳናቸውም የክርስቶስን ይምስላል፣ፍጻሚያቸውም ከነደቀመዝሙራቸው ወደለመለመው መስክ ወደ ረፍቱም ውሃ ይሆናል ፡፡
  በዓለም ፈተና አሸናፊ ሆኖ የድል አክሊል መቀዳጀት ፣የለመለመውን መስክን፣ የረፍቱን ውሃ መውረስ ከተግዳሮት፣ከአመኬላው ላይ ካለው ሩጫ በፊት የሚቻል ይሆን?
  ለኔ የገዳም ህይወት ለጾምና ለጸሎት መትጊያ፣ በተቀደሰ መለኮታዊ ኃይል መሞያ ማዕከል ነው፡፡ ነገር ግን የተሞላነውን ኃይል ወደ ኣለም መጥተን ካላደረስን ፣ጅማሪያችንም ፍጣምያችንም ገዳም አንዲሆን ከታቀደ ፡፡ያልተተኮሰ እምቅ ኃይል፣የልተዘራበት ለም መሬት፣ተቆፍሮ ያልወጣ የከርሰምድር ሀብት፣ወደ ወተት ወደ ስጋ ያልተለወጠ የቀንድ ከብት ሀብት እንደማለት ይሆናል፡፡
  ይሄ ማስፈራሪያ ከመሆን የዘለለ አንድምታ የለውም፡፡ያም ቢሆን ለራስ ብቻ የሚሆን እንጂ 30፣60፣100 ፍሬ ለማፍራት ያስቻለ አይሆንም፡፡
  ከተሳሳትኩ፣ ከጠመምኩ ልማር ፣ልቅና፡፡ እንወያይ፡፡

  ReplyDelete
 6. DN DANIYE LEGNA ENDET YALE TIMHIRT MESELEH!! ENATIE TILEGNALECH <> EGNA GIN ENITSELIYALEN YE AFININ ENA YEFINIHAS TARIK ENDIDEDEM!

  ReplyDelete
 7. ጥሩ ማስታወሻ ነው ሙኃዘ ጥበብ
  የሹመቱ በዓል አከባበር ብቻ ሳይሆን አሹዋሸሙም፣ አመራረጡም ልዩ ነው፡፡ የኛ ሀገር ድግስ እንኳን ደስ አለዎት ለማለት ሳይሆን ቤተ ክርስቲያናችን ጥሩ አባት አገኘችልን በማለት ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ ጥሩ ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete