Wednesday, May 24, 2017

የመርሕ ጥያቄ


ሰሞኑን ዶክተር አባ ኃይለ ማርያም ኦርቶዶክሳውያን ካልሆኑ አካላት ጋር ያከናወኑትን ‹የጠበልና እምነት› ጉዳይ በተመለከተ አያሌ ጥያቄዎች ሲነሡ ነበር፡፡ ነገሩን ከየምንጮቹ ብሰማቸውም በቅዱስ ጳውሎስ ዘመን የነበረው የቂሣርያው ገዥ ፊስጦስ ‹ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም፣ ለተከሰሰበትም መልስ ይሰጥ ዘንድ ፈንታ ሳያገኝ ማንንም ቢሆን አሳልፎ መስጥ የሮማውያን ሥርዓት አይደለም› (የሓዋ.25፣16) ብሎ የተናገረውን መሠረት በማድረግ አባ ኃይለ ማርያም ለጉዳዩ የሚሰጡትን መልስና ማብራሪያ ጠብቄ ነበር፡፡ መልስና ማብራሪያውንም ሰጡ፡፡
አባ የድርጊቱን መከናወን አምነው የክንውኑን ዓይነት ከተወራው የተለየ መሆኑን አብራሩልን፡፡
መልሳቸውን ስናጠቃልለው፡-
1.      መርሐ ግብሩ ‹ውኃ ለሁሉም› በሚል መርሕ እንደተዘጋጀ
2.     ፓትርያርኩና ሊቃነ ጳጳሳት እንደተገኙበት
3.     ተበጥብጦ ከመጣው ውኃና እምነት ጠቅሰው በተሳታፊዎቹ ግንባር ላይ ምልክት አንዳደረጉ
4.     ሰውዬው ጣቱን አስጠጋ እንጂ አንዳልቀባቸው
መርሐ ግብሩ ‹ውኃ ለሁሉም በፍትሐዊነት እንዲዳረስ› ከሆነ እንዴት ነው እምነትና ውኃ በመበጥበጥ ውኃ ለሁሉም ሊዳረስ የሚችለው፡፡ ‹ውኃ ለሁሉም› የሚለው ጉዳይ የዐውደ ጥናት፣ የምክክርና ምናልባትም የጸሎት ርእስ ሊሆን ይችላል እንጂ እምነትን በውኃ በጥብጦ በመቀባት ‹ውኃ ለሁሉም› እንዴት ለማዳረስ  ይቻላል? እምነት በውኃ በጥብጦ መቀባት ለፈውስ ያገለግላል እንጂ እንዴት ከውኃ ፍትሐዊ አጠቃቀም ጋር ተገናኘ? ደግሞስ እኛ ከሌሎች እምነቶች ጋር አንድነታችንን ማምጣት ያለብን በክርስቶስ እንጂ እምነት በውኃ በመበጥበጥ ነው እንዴ?  

አባ ኃይለ ማርያም በሰውዬው (የሌላ አምነት መሪ መሆኑ ከፎቶውና ከመረጃው ይታወቃል) ግንባር ላይ ሲቀቡት ምን እንዲያደርግ አስበው ነው? እንዲፈወስ የቀረበ በሽተኛ ነው? ለበረከት የመጣ ደጅ ጠኚ ነው? እንዴትስ ነው የተበጠበጠው እምነት ከ‹ ውኃ ለሁሉም› አስተሳሰብ ጋር የሚሄደው?
ሌላው አስገራሚ ነገር ደግሞ ‹ሰውዬው ጣቱን አስጠጋ እንጂ አልቀባኝም› ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹ ሁሉ የሚያሳዩት ግን ሲቀባዎት ነው፡፡ ደግሞስ ሰውዬው ለመቀባት ካላሰበ እጁን ለምን ወደ እርስዎ ያስጠጋል? ሊባርክዎ ነው? አስቀድማችሁ የተስማማችሁበት ሥነ ሥርዓት ይህንን የማይፈቅድ ከሆነስ እንዴት እጁን ወደ እርስዎ አስጠጋ? ‹እጁን አስጠግቶ ነበር› ካሉን ደግሞ ከተበጠበጠው እምነት እንደ እርስዎ ጠቅሶ ነበር ማለትዎ ነው? ለመሆኑ ኦርቶዶክሳዊ ክህነት የሌለው ሰው ከእምነት ጠቅሶ ሌላውን ሰው መቀባት፣ ያውም ቆሞሱን ይችላልን?
ሥነ ሥርዓቱ ሲከናወን ፓትርያርኩና ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደነበሩ አባም ነግረውናል፣ ፎቶውም አሳይቶናል፡፡ ምን ወስነው? ምን ሊያደርጉ ሄዱ? ውኃ ለሁሉ እንዲዳረስ ሊጸልዩ ወይስ ውኃ ለሁሉ እንዲዳረስ እምነት በውኃ ሊበጠብጡ? ለመሆኑ ይህንን እንዲያደርጉ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይፈቅድላቸዋል? ወይስ ሥልጣን ከቀኖና ስለሚበልጥ?

አባን ለዚህ ሁሉ ነገር የዳረጋቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ መርሕ እየተጣሰ ስለመጣ ነው፡፡ ሁለት መሠረታዊ ጥያቄዎችን እናንሳ፡-
ቤተ ክርስቲያናችን ኢኩሜኒካል ግንኙነትን የምትመራበት ፖሊሲና ደንብ አላት?
ቤተ ክርስቲያናችን ኢኩሜኒካል ግንኙነቶችን የምታከናውንበት ተቋምስ አላት?
የሁለቱም መልስ የላትም የሚል ነው፡፡ በሌሎች እኅት አብያተ ክርስቲያናት የኢኩሜኒካል ግንኙነትን የተመለከተ ፖሊሲና ደንብ ሲኖዶሱ ያጸድቃል፡፡ ከነማን ጋር ምን ዓይነት ውይይት ይደረጋል፣ ምን ዓይነት ውይይቶች በምን ደረጃ (በሊቃውንት፣ በጳጳሳት) ይደረጋሉ፣ ስምምነቶች እንዴት ይጸድቃሉ፣ የጸደቁት እንዴት ለሕዝብ ይገለጣሉ፣ የጸደቁትን እንዴት መተግበርና መከታተል ይቻላል፣ ስምምነት እስኪደረስ ድረስ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ምን ዓይነት ግንኙነቶች ይኖሩናል? በምን በምን እንተባበራለን? በየደረጃው ያሉ አካላት (ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምእመናን) ያላቸው ድርሻ ምንድን ነው፣ የሚሉትን የሚወስን የፖሊሲ መዝገብ አላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ግን ይህ ፖሊሲ የላትም፡፡ ፖሊሲውንም መሠረት አድርጋ የምትመራበትን ሕግ አላጸደቀችም፡፡ ስብሰባ ስትጠራ መሄድ ብቻ ነው፡፡
በሌላ በኩልም የኢኩሜኒካል ግንኙነትን የሚያካሂድ፣ ባለሞያዎችን የሚሰባስብ፣ መረጃዎችን የሚመዘግብ፣ በዓለም ላይ የሚደረጉ የኢኩሜኒካል ግንኙነቶችን የሚከታተል፣ ግንኙነቶቹን በፖሊሲውና በደንቡ መሠረት የሚመራ፣ ስሕተቶች ሲፈጠሩም የሚያርም ተቋምም የለም፡፡ ያለው የውጭ ግንኙነት መምሪያ ነው፡፡ እርሱ ደግሞ ብዙ ጊዜ እንግሊዝኛ ይችላሉ ተብሎ ስለሚታሰብ አሜሪካ በኖሩ ሰዎች የሚመራ ነው፡፡ የኢኩሜኒካል ግንኙነት ግን የአሜሪካን እንግሊዝኛ በመቻል ብቻ የሚሠራ አልነበረም፡፡ የውጭ ግንኙነት መምሪያው ወደ ውጭ ለሚሄዱ ሰዎች ሂደቶቻቸውን መከታተል፣ ከውጭ አጥቢያዎች ጋር ‹መገናኘት› የሚላኩ ሰዎችን መላክ እንጂ ራሱ እንኳን የሚመራበት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ያለው አይመስልም፡፡

ይህ በሆነበት ሁኔታ አባ ኃይለ ማርያም ያንን ነገር ቢያደርጉት የሚገርም አይደለም፡፡  ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ በዕለቱ የነበሩት ፓትርያርኩና ሊቃነ ጳጳሳቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን መርሕ እየጣሱ ያዘዟቸውን ነው የተገበሩት፡፡ እርሳቸው ቢሆኑም ግን  ፖሊሲና ሕግ በሌለበት ይህንን ተግባር ከሚያከናውኑ ‹ዱክትርናቸውን› ተጠቅመው ፖሊሲውና ሕጉ እንዲዘጋጅ ቢያደርጉ ኖሮ ይመሰገኑ ነበር፡፡ ነገ ጳጳስ የሚሆኑትን አባት ማንም እየተነሣ እጁን ወደ ግንባራቸው አይልክም ነበር፡፡ በሃይማት መሥመር የበላይ ያመጣውን ሁሉ በእምነት መመርመር ያስፈልጋል፡፡ የበላይ አዞኝ ነው ብሎ ቀኖና መጣስና እምነት ማፋለስ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ በጉባኤ ኬልቄዶን የክህደቱን ውሳኔ አልቀበልም ያለው ዲዮስቆሮስ በሮም ቤተ መንግሥት ተጠርቶ ‹ለምን አትቀበልም? ልዮንኮ አለቃህ ነው› ሲባል ‹ልክ ነው ልዮን አለቃዬ ነው፡፡ ነገር ግን ከእምነቱ ሲወጣ አልቀበለውም፡፡ ሳጥናኤልም ለቅዱስ ሚካኤል አለቃው ነበር፤ ከእምነቱ ሲወጣ ግን አልተቀበለውም› ያለውን እዚህ ላይ ማስታወሱ መልካም ነው፡፡ አሁንም ቤተ ክርስቲያናችን ኢኩሜኒዝምን የተመለከተ ፖሊሲና መመሪያ ካላወጣች፣ ጠንካራ ተቋምም ካልመሠረተች ነገ ከዚህ የባሰ ነገር ማየታችን አይቀርም፡፡ ከዚህ ተግባር የተማርነው ግን የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ በነቃ ኅሊና መከታተል እንዳለብን ነው፡፡ ያሳወቁንን እያመሰገንን፣ ያላወቅነው እንዲገልጥልን እንለምናለን፡፡    

30 comments:

 1. በቃ እሄዉ ነዉ ወንድሜ ዳኒ? ታናናሾች ሲያጠፉ ሊወገዙ ትልቅ የሚመስሉት ግን ሁሌም እንዳጠፉ ሊኖሩ ነዉ? ብቻ ቆይ!!!

  ReplyDelete
 2. Thanks to Zemedku and his friends. I dont know what they are doing in the church? But God have a power to do any thing. Please God help this church and its real believers. I do not know why they did not do it out side the church. For sure they do have a mission.

  ReplyDelete
 3. የሚገርመዉ የቤተክርስቲያን ሥርዓት የሚፈቅደው እንዲህ ለሰዎች አሥተማሪ ያልሆኑ መግባራትን በማዳመጥ ማስተካከል ነዉ። ነገርግነ እንኳን እነደዚህ በቅርቡ የተሰማ ጉዳይ እነ ቸክሌነ ከጋምቤላ እየታሠበ ።። የቤተ ክርስቲያን አምላክ ይፈረዳል ......

  ReplyDelete
 4. Zim Sitl germogn neber... Min ayinet zemen lay deresin

  ReplyDelete
 5. ከዚህ ተግባር የተማርነው ግን የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ በነቃ ኅሊና መከታተል እንዳለብን ነው፡፡ Thanky Dn Dani for your info.

  ReplyDelete
 6. እኔን ግን ከሁሉም ከሁሉም ያስቆጨኝ ይህን ስብሰባ መቅደስ ውስጥ ማድረጋቸው ነው፡፡ ያላመኑ ሰዎች ሲጀመር መቅደሳችን ውስጥ ምን ይሠራሉ፡፡ መቼም መቅደስ ለመግባት እነዚህ ሰዎች የእኛን ቀኖና ጠብቀው ነው ለማለት ይከብደኛል፡፡ ስብሰባው ወይ የተለያዩ አጥቢያዎች በሚገኙ የስብከተ ወንጌል አዳራሾች ወይ ደግሞ ቤተ ክህነት አልያም አንዱ ሆቴል ማድረግ አይቻልም ነበር? ግራ የገባው ነገር!?

  ReplyDelete
 7. የሃይማኖት አንድነት ታወጀ ማለት ነዉ? ያሁኑ ይባስ!

  ReplyDelete
 8. You are right Dn Daniel. The designing of policy and the establishment of an institution for such a purpose is indeed a vital recommendation.

  ReplyDelete
 9. እውነት የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ ከነጫማቸው ቤተመቅደስ ውስጥ ገብተው ይህን ሁሉ ነገር እንዲያደርጉ በሩን የከፈትነው እኛ ነን፡፡ እግዚአብሔር የተነሳ ቀን ሁላችንም ከፍርድ አናመልጥም ከእግዚአብርሔር ይልቅ ለሰው እየታዘዝን ስለሆነ ካህኑ ዔሊ ልጆቹን ባለመገሰጹ የእግዚአብሔርን ቅጣት እንደተቀበ

  ReplyDelete
 10. Thanks Dn Daniel. It is a good short article, as always. It is the 21st century and our EOT Church is still crawling on these matters when she should be on the forefront, ie being the oldest church. Maybe it is time to deal with this at the local church level, since nothing will be done at the top. What do you think?

  ReplyDelete
 11. ከዚህ ተግባር የተማርነው ግን የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ በነቃ ኅሊና መከታተል እንዳለብን ነው፡፡ ያሳወቁንን እያመሰገንን፣ ያላወቅነው እንዲገልጥልን እንለምናለን፡፡ thank you Bro...

  ReplyDelete
 12. Egzio Meharene Kirstos Ye Dingil Maryam Lig !!!!!!

  ReplyDelete
 13. Thank you Dn Dani.
  This is truly sad. It shows how the so called church leaders don't even care about EOTC canon. Slippery slop ... what is next?
  May God protect His church and true followers

  YeAwarew

  ReplyDelete
 14. unbelivable thing we here.thank you dn daniel.

  ReplyDelete
 15. Can someone pls write in English what and who is being crucified

  ReplyDelete
 16. እውነት ነው ከእንቅልፋችን መንቃት አለብን ከማንኛውም ግዜ በላይ ማድረድ የሚያስፈልገውን ሁሉ ማድረግ መቻል አለብን ከእግዚአብሔር ጋር

  ReplyDelete
 17. እውነት ነው ከእንቅልፋችን መንቃት አለብን ከማንኛውም ግዜ በላይ ማድረድ የሚያስፈልገውን ሁሉ ማድረግ መቻል አለብን ከእግዚአብሔር ጋር

  ReplyDelete
 18. እውነት ነው ከእንቅልፋችን መንቃት አለብን ከማንኛውም ግዜ በላይ ማድረድ የሚያስፈልገውን ሁሉ ማድረግ መቻል አለብን ከእግዚአብሔር ጋር

  ReplyDelete
 19. ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል! የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይጠብቅህ፡፡ ለሁላችንም የምታውቀውን ባገኘኸው አጋጣሚ ስለምታካፍለን፡፡ ይህ ጉዳይ ግን ከአንድ አስተያየት ሰጪ እንደተፃፈልህ ስብሰባውን ሌላ ቦታ ቢያደርጉት ይሻላቸው ነበር፡፡ ሆኖም ሰዎቹ……….፡፡ ግን እግዚአብሔር ስለቤቱ ክብር ይፈርዳል፡፡ ቢዘገይም የሚቀድመው የለምና፡፡

  ReplyDelete
 20. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 21. thank you dani. the main mistake is that of our church!

  ReplyDelete
 22. በእንደዚህ ዓይነት ጉባኤያት ቤተ ክርስቲናችን የምትወክላቸው ሰዎች አስተምህሮዋን የጠነቀቁ የነቁ የበቁ ፣ ባለቤቶች ሊቃውንት ካልሆኑ፤ ምንደኞችማ የስብሰባ አበል እና ሽርሽር እንዳይቀርባቸው አዎን አዎን ብለው አጨብጭበው ፈርመው ተፈራርመው መምጣታችው የማይቀር ነው። እዚሁ አፍንጫችን ስር እንዲህ ካደረጉ ውጭ ሄደው ሲሰበሰቡማ እንዴት ይሆን? አሁንም እንደተባለው እንደዚህ ዓይነት ስብሰባዎችን በነቃ ኅሊና መከታተል አለብን፣በቤተ ክርስቲናችን ስም ምን እንደሚፈርሙ ምን እንደሚፈራርሙ . . . ፠

  ReplyDelete
 23. ዲያቆን፤ እኔ ለአንተ ትልቅ ክብር እና አድናቆት አለኝ፡፡ አንተ ጎበዝ ጸሀፊ ነህ፤ ጎበዝ ተናጋሪ ነህ፤ ትመስለኝም ነበር፡፡ ግን በጣም ዘቀጥክብኝ፤ ቢያንስ ሰውዬ ብለህ ያለፍከው ሰው ማን መሆኑን ሳታውቅ ቀርተህ አይመስለኝም የካቶሊክ ቄስ ብለህ ማለፍ ትችል ነበር፡፡ አንዳንዴ ስንጽፍ ስናስተምር እኛም ልንኖረው እንደሚገባን አንርሳ፡፡ አንተ ከአንተ ወገን ስላልሆነ ብቻ የምታውቀውን ማዕረግ ነሳኸው፡፡ እኔ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነኝ፡፡ አንተን ግን ሰውዬው ብዬህ አላውቅም፤ አውቅሃለሁና፡፡ ግን ደግሞ ስላንተ የነበረኝ ግምት በዚህች ተራ በምትመስል እና በተከታዮችህ ተቀባይነትን ለማስፋት ብለህ በተጠቀምከው ቋንቋ አነስክብኝ፡፡ አንተን የሚከተሉ ኦርቶዶክሳዊያን ብቻ አይደሉም፡፡ ብዙ ሰው ወዶ አስተማሪ የሆኑ ጽሁፎችህን ይከታተላሉ፡፡ እኔ የኦርቶዶክሱ ቄስ የካቶሊኩን ካህን በቅባት ግንባራቸውን ቢቀቡ ምንም አይመስለኝም፡፡ ከሀይማኖት በላይ አንድነት፤ ሰውን በሰውነቱ ብቻ ማክበር ይበቃ ነበር፡፡ እግዚአብሄር ለኦርቶዶክስ ወፍራም፣ ለካቶሊክ ቀጭ፣ ለሙስሊም እሳት፣ ለጴንጤው አሲድ አያዘንብም፡፡ ለሁሉም የበረከቱ ዝናብ በእኩል ያዘንባል፡፡ አንተ ማስተማር ያለብህ ስለ እግዚአብሄር ፍቅር እንጂ ስለ ኦርቶዶክሳዊነት ብቻ ከሆነ ጠላት ባንሆንም እንኳን ጠላትህን ውደድ ያለውን አምላክ ትተሃል፡፡ ለ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መልካሙ እመኛለሁ፡፡ የዘመኑ ሰው ያመዛዝናል፤ በቀቀን አይደለም የሰማውን እንደ ወረደ የሚቀበልና የሚደግም፡፡ ይጠይቃል፤ መልስ ካጣ አደጋ ይሆናል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሥልጣንና ጊዜን ወይም ሀብትን ተመክቶ የሰዉ ርስትን የሚደፍር ሰዉዮ እንጂ ቄስ እንዴት ይባላል፡፤ እናንተ ካቶሊኮች ዘንድ እኮ ወንድ ለወንድ ለመጋባትም ችግር የለዉም፡፡ እኛ ግን በቀኖና የቆምን ስለሆነ ችግር አለዉ፡፡ ችግር አለዉ ካልን ደግሞ ተቀብላችሁ ማክበር ነበረባችሁ

   Delete
  2. ከማይገባውና ክማይመጥነው ቦታ የሚገኝን ሰው ሰውዬ ማለት ክብርን መቀነስና አንተ እንዳልከው ድጋፍ ማፈላለግ ሳይሆን ሰወውነተቱነን አከክበብረሮ ማንነቱን እንዲረዳ ማገዝ ነው ወዳጄ... እናንተ ግን ምነው እንደዚህ አጉራ ዘለል ሆናቸችሁ ከእንደዚህ ዓይነት ቦታ መገኘትንና የፈጸማችሁትን የመቀባባት ስርዓትስ ከወዴት አገኛችሁት ... ውስጥ ወይራ ሆናችሁብኝ እግዚአብሔር ሚስጥራችሁን ከገለባ ያቅልለው....

   Delete
 24. ይህ የምንሰማወም ሆነ የምናየው ነገር የሚያስረዳው መጥተን መጥተን ወይንም ልዋስና “ወርደን ወርደን” የደረስንበት አዘቅት ምልክት ነው፡፡እንግዲህ ምህረትም የሚያስፈልገን ምህረትንም የምንናፍቀው ለዚህ ነው፡ ሠው ሲጠፋ... እንደሚባለው ፡፡ሀገር ምህረት ስታገኝ ነው ህዝብ ምህረት የሚያገኘው፡፡ ሀገር ደግሞ በሶስት ምክንያቶ ምህረትን ታገኛለች፡፤ እነሱም
  1. ህዘቡ አመጸኛ በኃጢያት ያደፈ የማይሰማ ማን አለብኝ የሚል ሲሆን፤ የኃይማኖት መሪዎቹ ገንዘብ ወዳድ መናፍቅ ዝንጉና ፌዘኞች ሲሆኑ ህዝቡን ከጥፋት የሚመልስ የኃየማኖት መሪዎቹን የሚገስጽ ከእግዚአብሔር ምህረትን የሚለምን ከሚመጣው መከራና ስቃይ የሚጠብቅ መሪ የሀገር ሽማግሌ ሲገኝ ወይ እግዚአብሔር ሲያስነሳ፤ እንደ ሙሴ
  2. ለሚያስተዳድረው ህዝብ “ማቅ ለብሶ አመድ ነስንሶ እንደኦሪቱ” ዘመን ሳይሆን በትጋት የሚጸልይ ምህረትን ከአምላኩ የሚለምንና የሚያሰጥ የሚናገረውን የሚያስብ የሚያስበውን የሚናገርና የሚያደርግ መሪ ሲገኝ፤ እንደ ዳዊት
  3. ህዝቡን የሚገስጽ ከኃጢያት የሚመልስ አስተዳዳሪዎችን ወደ መንገድ የሚመልስ የኃይማኖት መሪ ሲገኝ ወይ እግዚአብሔር ሲያስነሳ ነው ምህረት የሚገኘው፤ እንደእነ ዮሐንስ፤ አቤሜሌክ ሌሎችም ያሉ፤
  አሁን ሀገራችን እንደነዚህ ያሉ የስብዐና አንጓዎች የሏትም ከሶስቱ ስብዕናዎች አንዱንም ያጣችበት ዘመን ላይ መድረሳችን ነው የሚያሰጋውም የሚያስጨንቀውም፡፡ ምልክት የሌለን ህዘቦች ሆነናል ለዚህም ነው መጪው የሚያስጨንቀው የሚያሳዝነው የሚያስከፋው፡፡ እግዚአብሔር ምህረቱን ያምጣ!

  ReplyDelete
 25. ... ነገ ከዚህ የባሰ ነገር ማየታችን አይቀርም፡፡ ከዚህ ተግባር የተማርነው ግን የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ በነቃ ኅሊና መከታተል እንዳለብን ነው፡፡ ያሳወቁንን እያመሰገንን፣ ያላወቅነው እንዲገልጥልን እንለምናለን፡፡

  ReplyDelete
 26. what we have seen currently on our church must have to stimulate all of us. please don't give everything to priests only. we also part of the church, so we have to attentively follow our church.

  ReplyDelete
 27. what we have seen currently on our church must have to stimulate all of us. please don't give everything to priests only. we also part of the church, so we have to attentively follow our church.

  ReplyDelete
 28. አበከችሁ አባቶቻችን ባለቤቱ ያቃለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውምና ለማይገባ ሰው ቢያንስ ክብራችሁንና ግንባራችሁን እንኳ አታስነኩ

  ReplyDelete