Wednesday, February 1, 2017

የቹንቾን ሐውልታችን


የቃኘው ሻለቃ መሥዋዕትነት መታሰቢያ ሐውልት

ዛሬ ከሴኡል ከተማ 75 ኪሎ ሜትር ርቀን ቹንቾን(Chuncheon) ወደምትባል የኮርያ ከተማ እንጓዛለን፡፡ በታሪክ ላይ በእግራችን ለመራመድ፡፡ በበረዶ በተሸፈኑት የኮርያ ተራሮች መካከል እያለፍን በኮርያ የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት ጸጥ ባለው ጎዳና ላይ እንበራለን፡፡ ዛፎቹ ቅጠሎቻቸውን ሸኝተው ግንዶች ብቻቸውን የብርዱን ወቅት ሊጋፈጡት ቆርጠዋል፡፡ መሬቱ ነጭ ሥጋጃ ለብሷል፡፡ ደግነቱ ጎዳናው እንደ ካናዳና አሜሪካ በረዶ አልለበሰም፡፡ 


ወደ ቹንቾን ደርሰን ካንግወን (Kangwon) ወደተባለው አደባባይ አመራን፡፡ እዚያ ለኮርያ ነጻነት ሲሉ መሥዋዕትነት ለከፈሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች የቆመ የመታሰቢያ ሐውልት አለ፡፡ ሐውልቱ በማርች 25 ቀን 1968 ተጀምሮ በሜይ 7 ቀን 1968  እኤአ የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት (2018) ሃምሳ ዓመት ይሞላዋል፡፡ ሐዉልቱን በሜይ 19 ቀን 1968  ዓም የመረቁት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ናቸው፡፡ ታሪኩን በአማርኛና በኮርያ ቋንቋ የመዘገቡ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች በዙሪያው ይገኛሉ፡፡ ከሐውልቱ አጠገብ ከ49 ዓመት በፊት ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ የተከሏት ዛፍ የሐውልቱን ቁመት በሚፎካከር ቁመት አድጋለች፡፡
ሐውልቱን ጎብኝታችሁ መንገዱን ስትሻገሩ በሚያዝያ 1999 ዓም ለኢትዮጵያውያን ጀግኖች መታሰቢያ የተገነባው ‹የጦርነት መታሰቢያ ሙዝየም› ይገኛል፡፡ ሙዝየሙ አዲስ አበባና ቹንቾን እኅትማማች ከተሞች ሆነው የተፈራረሙበትን የ1996 ዓም ስምምነት ተከትሎ የተገነባ ነው፡፡ በሙዝየሙ ውስጥ በኮርያ ጦርነት የተሳተፉ የቃኘው ሻለቃ አባላትን ገድል የሚዘክሩ ፎቶዎችና ወታደራዊ ቁሳቁሶች ሞልተዋል፡፡
ዐፄ ኃይለ ሥላሴ የተከሏት ዛፍ
ከሙዝየሙ አጠገብ በ1968 እኤአ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሐዉልቱን ሲመርቁት አብሮ የተከፈተ ‹የኢትዮጵያ ቤት› የተሰኘ ካፍቴሪያ ይገኛል፡፡ ይህንን ቤት የመረቁት ንጉሠ ነገሥቱ መሆናቸውን በቤቱ ውስጥ የሚገኙት ፎቶዎችና መዛግብት ይናገራሉ፡፡ በኢትዮጵያ ባሕላዊ ዕቃዎች የተጌጠው ይህ ቤት የኢትዮጵያን ቡና አፍልቶ በመሸጥ ይታወቃል፡፡ ያውም ከነጀበናና ረከቦቱ፡፡ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች የነበራቸውን ተጋድሎ፣ ያደረጉትን አስተዋጽዖና የንጉሠ ነገሥቱን ጉብኝት የሚያሳዩ ፎቶዎች ግድግዳውን ሞልተውታል፡፡ 

 
ሙዝየሙ ከውጭ ሲታይ
የቃኘው ሻለቃ ጀግኖች በኮርያ ጦርነት ተሳትፈው አኩሪ ገድል ለመፈጸም የኮርያን ምድር የረገጡት ሜይ 6 ቀን 1951 እኤአ ነው፡፡ ከአራት ዓመት በኋላ እኤአ በ2021 ዓም 70 ዓመት ይሆናቸዋል፡፡ በኮርያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤት ከሚገኙ የኮርያ ዘማቾች ጋር በመሆን አንድ ዐቢይ ኮሚቴ አቋቁመው ሰባኛውን ዓመት በሁለቱም ሀገሮች ለማክበርና አሁን ላለው ትውልድ የታሪክ ውርርስ ለማድረግ ቢነሣሡ ጊዜውን በበቂ ሁኔታ ለመጠቀም የሚቻል ይመስለኛል፡፡      
የኢትዮጵያ ቤት ባለቤት ቡና ሲያፈላ

8 comments:

 1. Why don't you write about Anole Monument which was built by lies and hatred of woyane and OLF.

  this generation was miguided by false history and propaganda of Woyane and OLF, ...WHY DON'T TELL THE TRUE HISTORY BEHIND OUR CONTROVERSIES.
  EVERYONE OF YOU RUN AROUND THE ISSUES, IGNORE THEM MANY TIMES, AND CONSOLE ONLY WHEN PEOPLE LOST THEIR LIVES. THIS IS NOT SPRITUAL.

  ENGIDA KALMETA HULU SET ZINAB KALMETA HULU BET YIBALAL....AND THE TIME HAS EXPOSED YOU. PEOPLE IN THIRSTY FOR TRUE HISTORY...BUT OU IGNORED THE UPROAR AND REMAINED SILENT...ONLY GONG HERE AND THERE TO MAKE YOUR LIVING. THIS IS NOT ORTHODOX. THIS IS NOT THE SON OF ABUNE PETROS.
  ORTHODOX HAS BEEN TARGETED AS ENEMY....BUT YOU REMAINED SILENT....YOU ARE ENGAGED IN SELECTING WORDS INSTEAD OF FACING IT.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear anonymous muhaze tebebe diakon daniel kibret Egziabher yeseten abatacen memheracrn new ante kalgebah lemen yetayehen ante atsefewem lemen yehn yan altsafem beleh kemetecete esuma yetayewen tsafe astemare sente eamanine melkamune menged mera kemetecete yerasehen sera. Melkam lebonane yadelen.

   Delete
  2. my friend i think you didn't read his previous articles "ሦስቱ የሕዝብ ማስጠንቀቂያዎች", "የሦስት ደብዳቤዎች አዙሪት" and so on regarding the gaps of the government. all the time he is the hero person. Pls do not dare to react like this or expecting him to fight with TPLF ????

   Delete
  3. do not expect to fight behalf of u ,u should also do u part even though dani is doing all his best he wrote so many issue about the present political situation of the country I do not know what are u looking for u mean he must be in person so that we should know he is the real fighter ! u talking nonsense ANONYMOUS

   Delete
 2. ዋጋ በከፈሉባት ሀገር እነርሱን የሚያስታውስና ታሪካቸውን በየትውልዱ ሊቀርጽ የሚችል ክብራቸውንና ደረጃቸውን የጠበቀ መታሰቢያ አላገኙም፡፡ ምናልባትም የሚያዝነው መንፈሳቸው ይሆን ሀገሪቱን በየዘመናቱ አዙሪት ላይ የሚጥላት?

  ReplyDelete
 3. Another great read from the one and the only D/N Danny.Thank you brother.

  ReplyDelete
 4. እባክህ ዲ/ን ወንድም ወንድሙን ገድሎ ሚፎክርብት ቀን
  ስለ ግንቦት 20 ብትጽፍ እና እዉነቱን ብታወጣ.....

  ReplyDelete