Wednesday, December 28, 2016

እየላሱ መሞት

click here for pdf 
በርለዓም ወየወሴፍ
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከምናገኛቸው የጥበብ መጻሕፍት አንዱ ‹በርለዓም ወየወሴፍ› የተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ 
በርለዓም ወየወሴፍ የተለያዩ ምሳሌዎችንና ተረቶችን የያዘ የሕንድ መጽሐፍ ነው፡፡ የተወሰደውም ከትውፊታዊው የጉተማ ቡድሐ የሕይወት ታሪክ ነው፡፡ ታሪኩ የፍቅር ታሪክ ነው፡፡ የዚህ መጽሐፍ ቅጅዎች በአይሁድ፣ በማኒያውያን[i]፣ በሙስሊሞች ዘንድና በክርስቲያኖች ዘንድ ይገኛሉ፡፡ 
ዋዳጎስ የተባለ እጅግ ባዕለ ጸጋ የሆነ ኃይለኛ የሕንድ ንጉሥ በሕንድ የሚገኙ ክርስቲያኖችን ጨፈጨፈ፡፡ አንድ ቀን ዋዳጎስ የወሴፍ የሚባል ወንድ ልጅ ወለደ፡፡ ኮከብ ቆጣሪዎችና ጠንቋዮች ስለ ልጁ ዕጣ ፈንታ ሲጠየቁ ልጁ ወደፊት ክርስቲያን እንደሚሆንና የክርስቶስን ሃይማኖትንም ከፍ ከፍ እንደሚያደርግ ይናገራሉ፡፡ ይህንን በመፍራት ንጉሡ ልጁን በአንድ ቤተ መንግሥት ውስጥ ወስኖ አስቀመጠው፡፡ ኀዘን፣ ድክመት፣ ሞት የሚባሉትን ነገሮች እንዳያውቅ እርሱንም ከደስታ የሚያወጣውን ነገር እንዳያጋጥመው አደረገው፡፡ 
እያደገ ሲሄድ ግን መስፍኑ ከዚያ ቤተ መንግሥት ውጭ ያለውን ዓለም ለማወቅ ፈለገ፡፡ ከቤተ መንግሥቱ ውጭም ኃዘን፣ በሽታ፣ ልቅሶ፣ ረኃብና ሞት መኖራቸውን ተረዳ፡፡ ታዋቂው መናኝ መምህር በርለዓምም መስፍኑን አገኘው፡፡ ስለ እግዚአብሔርና ስለ ክርስትናም አስተማረው፡፡ ይህንንም ያስተማረው የተለያዩ ታሪኮችንና አባባሎችን በመጠቀም ነበር፡፡ መስፍኑ የወሴፍ ዓለምን ለመካድ ከበርለዓም ጋር ያለውንም ግንኙነት አባቱ ሳይሰማ ለማቆም ፈለገ፡፡ አባቱ ነገሩን ከመስማቱ በፊትም በርለዓም ከእርሱ ተለየ፡፡ ንጉሡም ነገሩን ሲሰማ እጅግ ተበሳጨ፡፡ የወሴፍን ወደ ጥንት እምነቱ ለመመለስም የቻለውን ሁሉ አደረገ፡፡ የመንግሥቱን አንድ ሦስተኛ ለመስጠት ቃል እስከ መግባትም ደረሰ፡፡ የወሴፍ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ በመጨረሻም ንጉሡ ራሱ ስሕተቱ ገባው፡፡ አማካሪዎቹ ሁሉ ክርስቲያን ከሆኑ በኋላም ንጉሡም ክርስትናን ተቀበለ፡፡ 
አባቱ ከሞተ በኋላ የወሴፍ መንግሥቱን ተወ፡፡ እጅግ ለሚያምነው ተከታዩ ዙፋኑን በመስጠትም መምህሩ በርለዓምን ለመፈለግ ወደ በረሐ ሄደ፡፡ እዚያ በርለዓምን ሲያገኘውም ሁለቱም የምናኔ ሕይወታቸውን እስከ ዕለተ ሞታቸው ቀጠሉ፡፡
መጽሐፉን ያስተረጎመው ዐፄ ገላውዴዎስ ሲሆን የተረጎመው ደግሞ እጨጌ ዕንባቆም ነው፡፡ ትርጉሙም የተከናወነው በ1546 ዓ.ም. ነው፡፡ [ii]

አልቫሬዝ እንደሚለው ካህናቱ የበርለዓምንና የወሴፍን መጽሐፍ አምጥተው የበርለዓምን የመታሰቢያ ቀን እንዲነግራቸው ጠይቀውት እንደነበር ጽፏል[iii]፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ መጽሐፈ በርለዓም ወየወሴፍ የተጻፈበት ዘመን 1519 ዓ.ም. ቀደም ይላል ማለት ነው፡፡ ምናልባትም ዕንባቆም መጀመሪያ ተርጉሞት በኋላ ለዐፄ ገላውዴዎስ እንደገና ጽፎለት ይሆናል፡፡[iv]
 
በበርለዓም ወየወሴፍ ከምናገኛቸው ምሳሌያዊ ትምህርቶች መካከል ለዛሬ አንዱን እንጋበዝ፡፡

እየላሱ መሞት
አንድ ሰው ድንገት አውሬ ይመጣበታል፡፡ የአውሬው ጩኸትና ድንፋታ እግሬ አውጭኝ ብሎ እንዲሸሽ ያደርገዋል፡፡ ከአውሬው ሸሸሁ ብሎ ሲሮጥ ጥልቅ ወደሆነ ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል፡፡ ወደ ጉድጓዱ ጥልቅ እየተወረወረ እያለ በጉድጓዱ ግድግዳ ላይ የበቀለ ሁለት ቅርንጫፎች ያሉት ዛፍ ያገኝና ያንን በሁለት እጆቹ ይዞ ፋታ ያገኛል፡፡ እግሩም በዛፉ ሥሮች ላይ ያርፋል፡፡ ይህን ዕድል ሲያገኝ እስከ ጊዜው ድረስ ነፍሱ መትረፏን፡፡ ጥቂት በዚህ ሁኔታ ከቆየ ደግሞ ቀስ በቀስ ከዚህ ጉድጓድ ሊወጣ እንደሚችል ማሰላሰል ጀመረ፡፡ ከሞት መትረፉንም ርግጠኛ ሆነ፡፡
የዛፉን ቅርንጫፎች እንደያዘ፣ እግሩንም በግንዱ ላይ እንዳስደገፈ አንገቱን ዝቅ አድርጎ ሊወድቅበት የነበረው ጉድጓድ ተመለከተው፡፡ በጉድጓዱ ሥር ዓይኑ አንደ እሳት የሚያበራ፣ ሰውነቱ አንደ ሰርዶ የተጠቀለለ፣ ራሱ እንደ ዱባ የሚንከባለል፣ አፉ እንደ ገደል የተከፈተ ዘንዶ ተመለከተ፡፡ በዚያ አጋጣሚ ነፍሱ ጥላው ልትሄድ ስትል ለጥቂት ነው የመለሳት፡፡ ከአንደኛው አውሬ አፍ አመለጥኩ ሲል ወደሌላው አውሬ አፍ እየተሸጋገረ መሆኑን ሲያስበው ልቡ እንደ እማሪት ያለ ማቋረጥ ይመታ ጀመር፡፡
ዓይኑን ከዘንዶው ነቅሎ ወደ ላይ ሲመልሰው እርሱ የተንጠለጠለበትን ቅርንጫፍ አንድ ነጭና አንድ ጥቁር አንበጣዎች ባለማቋረጥ እየበጠሱ ሲጥሉት ተመለከተ፡፡ ሁለቱም እጆቹ ስለያዙ ምን ያድርጋቸው፡፡ አንበጣዎቹ ለየትና ከበድ ያሉ ናቸው፡፡ ይበላሉ፣ ይበላሉ፣ ይበላሉ፣ አያቋርጡም፡፡ እርሱ ተማምኖ አጥብቆ የያዘውን ቅርንጫፍ እነርሱ በበሉት ቁጥር ግንዱ እየመነመነ ይሄዳል፡፡ ይህንን ሲያስብም የተንጠለጠለበት ሰው ተስፋም እየመነመነ ሄደ፡፡ ያ ቅርንጫፍ ተቆርጦ አጆቹ የሚይዙት አጥተው ቢወድቅ የዚያ እሳታማ ዘንዶ ራት እንደሚሆን ሲያስበው ዘገነነው፡፡
የእጆቹ ነገር እንዲህ መሆኑን ሲያይ ያለ የሌለ ጉልበቱን ሰብስቦ እግሩ ያረፈበትን ግንድ ተመለከተው፡፡ አራት እባቦች ከዛፉ ግንድ ስንጥቅ ውስጥ እየወጡ ነበር፡፡ የነዚያ እባቦች ቤት ያ የዛፉ ስንጥቅ ነው፡፡ እነዚያ አራት እባቦች ከዚያ ስንጥቅ ውስጥ ከወጡ እግሩ ወዳረፈበት ቦታ መምጣታቸው ነው፡፡ እንኳንስ አራቱንና አንዱንስ በምኑ ይከላከለዋል፡፡ አራቱ ከአራቱም አቅጣጫ ከመጡበት ደግሞ እግሩን የሚያሳርፍበት ቦታ ፈጽሞ አይኖረውም፡፡ ከላይ አንበጦቹ አጁ ያረፈበትን ይገዘግዛሉ፣ ከታች እባቦቹ ራሳቸው እንደ ባትሪ እየወዘወዙ ከስንጥቁ ይወጣሉ፡፡ ከጉደጓዱ ሥር ደግሞ እሳታማው ዘንዶ አፉን ከፍቶ ይጠባበቃል፡፡
ሰውዬው ተስፋ ወደ መቁረጥ ደረጃ ደርሶ የአንበጦቹን ፍጻሜ ለማየት ቀና ሲል አንዳች ጣፋጭ ነገር አፉ ውስጥ ጠብ አለ፡፡ በዛፉ ቅርንጫፍ ጫፍ ላይ ንቦች ከበው ማር እየሠሩ ነው፡፡ ያ የንች ማር ጠብ፣ ጠብ ይላል፡፡ ከነዚያ ተብታዎች አንዷ ናት ምላሱ ላይ የነጠበችው፡፡ እፎይ አለ ሰውዬው፡፡ የማሩን ወለላ አጣጥሞ፡፡ የማሩን ወለላ ሲያጣጥም ጅቡ ከጉድቃዱ አፍ ቆሞ አንደሚጠብቀው፤ ቅርንጫፉን አንበጦቹ እንደሚገዘግዙት፤ አራቱ እባቦች እግሩ ከረገጠበት ግንድ ስንጥቃት ውስጥ እንደሚወጡ፣ ከጉድጓዱ ሥርም አፉን የከፈተ ዘንዶ እንደተኛ፤ ልጡ የተራሰ፣ ጉድጓዱ የተማሰ መሆኑን ዘነጋው፡፡ ልቡ በማሩ ጣዕም ከጉደጓዱ ወጣች፡፡
በዙሪያው ያለውን እውነታ ዘነጋና በጠብታዋ ማር ጊዜያዊ ርካታና ደስታ ተዋጠ፡፡ በዙሪያው ያለው ሊውጠው የደረሰውን ችግር ትቶ ድንገት ባገኛት ደስታ ሰመጠ፡፡ አንደኛዋን ጠብታ አጣጥም ሌላኛዋን ለመቀበል አፉን እየከፈተ፣ ከገዛ ድርጊቱ ጋር ፍቅር ይዞት ጅቡንም፣ አንበጣውንም፣ እባቦቹንም፣ ዘንዶውንም ረሳቸው፡፡ እየመጣበት ካለው ጥፋት ይልቅ እየተንጠባጠበለት ወደለው ማር ዞረ፡፡
በርለዓም እንዲህ ይተረጉማል፡፡
ጅብ የተባለ ሞትና ጥፋት ነው፡፡ ሰው መጥፊያው ሲያባርረው፣ ሞትም ሲከተለው የሚያመልጥ መስሎት ይሸሻል፡፡ ሲሸሽ ባላሰበው የችግር ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል፡፡ መጋፈጥ እንጂ መሸሽ ማሸነፍን አያመጣም፡፡ ጉድጓዱ ሁሉም ዓይነት ችግር የተጠራቀመበት ነው፡፡ አንዱን ችግር በብልጠት አልፋለሁ ብለህ ከሸሸህ የባሰው ችግር ውስጥ ትወድቃለህ፡፡ አንዱን መፍታት ካቃተህ ችግሮች በማኅበር ይመጡብሃል፡፡ አንዱን ቸላ ካልከው ከመከራ መንጋ ጋር ትጋፈጣለህ፡፡ ሰውዬው የተንጠለጠለበት ባለሁለት ቅርንጫፍ ዛፍ የተሰጠን የእድሜ ዘመናችን ነው፡፡ ዘመን ስትሠራበት አንጂ ስትንጠለጠልበት መከራ ይጎትታል፡፡ ሁለቱን ቅርንጫፎች ነጭና ጥቁር አንበጦች ባለማቋረጥ ይገዘግዟቸው ነበር፡፡ እነዚህም ቀንና ሌሊት ናቸው፡፡ አንተ የተንጠለጠልክበት ጊዜ የሚባለውን ዛፍ ቀንና ሌሊት የተባሉ አንበጦች በየቀኑ እየገዘገዙ ያመናምኑታል፡፡ የያዝከው ይመስሃል እንጂ የያዝከው እስከጊዜው ብቻ ነው፡፡
አራቱ ከዛፉ ስንጥቃት ውስጥ በየተራ የሚወጡት እባቦች አራቱ የሰዎች ጠባዮች ናቸው፡፡ ነፋስ፣ እሳት፣ ውኃና አፈር፡፡ እነዚህ በየተራ ከጊዜ ውስጥ እየወጡ ልጅነትህን፣ ወጣትነትህን፣ ጉልምስናህንና እርጅናህን እየበሉ ይጨርሱታል፡፡ አራቱም በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ አራቱም የእድሜ ምዕራፎች በዘመንህ ውስጥ አሉ፡፡ እሳቱ ከውኃው ጋር፣ ነፋሱም ከአፈሩ ጋር ተሰጥቶሃል፡፡ በየዘመናቱ ካልሠራህባቸው ግን ከጉደጓዳቸው እየወጡ መምጣታቸው እንደሆነ አይቀርም፡፡
በጉደጓዱ መጨረሻ የነበረው ዘንዶ ሞት ወይም ጥፋት ነው፡፡ በስተመጨረሻ የሚጠብቀው ይህ ነው፡፡ የምንዘነጋውም ይህን ነው፡፡ ከታች ያንን የመሰለ ዘንዶ እየጠበቀው ሰውየው ድንገት ባገኛት የማር ጠብታ ነገር ዓለሙን ሁሉ ዘነጋው፡፡ ችግሮችህ ከበውህ፣ ዙሪያህንም እየገዘገዙህ፣ ወደ መጨረሻው ጥፋትም እየወሰዱህ፣ ጉድጓድ ውስጥ መውደቅህን አያወቅህ፤ ከእውነታው ጋር ስትጋፈጥ ድንገት እንደ ማር ጠብታዋ ያለች ጊዜያዊ ድል፣ ርካታና ፋታ ታገኛለህ፡፡ ያን ጊዜ ጅቡንም፣ አንበጣውንም፣ እባቡንም ዘንዶውን ትረሳዋለህ፡፡ ከእውነታው ጋር ከመጋፋጥ ይልቅ እውነታውን መርሳትን ትመርጣለህ፡፡ ጅቡም፣ አንበጣውም፣ እባቦቹም፣ ዘንዶው ባሉበት አሉ፡፡ ጅቡ እየጮኸ ነው፤ አንበጦቹም እየገዘገዙ ነው፣ እባቦቹ ከስንጥቃቱ እየወጡ ነው፤ ዘንዶው አፉን ከፍቶ ሊያጣጥምህ እየቋመጠ ነው፡፡ ሁሉም ነገር አልተቀየረም፡፡ የተቀየረው የአንተ ልቡና ብቻ ነው፡፡ እውነታውን ረሳኸው፡፡ የማሩን ጠብታ ስትልስ ከጉድጓድ የወጣህ መሰለህ፡፡ ሁሉም ነገር የተቀየረ፣ ሰላም የሆነና የተረጋጋ መሰለህ፤ ጉድጓዱን ሜዳ፣ ዘንዶው በግ፣ አንበጣውን ቢራቢሮ፣ እባቦቹን ርግቦች፣ ጅቡንም ፈረስ አድርገህ ቆጠርከው፡፡
እውነታውን መርሳት እውነታውን አይቀይረውም፡፡ አንተ የማሩን ጠብታ ስላጣጣምክ ጅቡም፣ አንበጦቹም፣ እባቦቹም ዘንዶው ሥራቸውን አያቆሙም፡፡ ምናልባት እየተራቡና እየተማረሩ ከመሞት የማር ወለላ እያጣጣሙ መሞት ይሻላል ካላልክ በስተቀር፡፡[i] ማኔ በ3ኛው መክዘ በኢራን የተነሣ የግኖስቲክ አራማጅ ነው፡፡ የማኒ ዋናው እምነት ምንታዌ ነው፡፡ ክፉና ደግ ነገሮች በተለያዩ ፈጣሪዎች የተፈጠሩ ናቸው የሚል፡፡
[ii] Encyclopedia Aethiopica, Vol. 1, P. 472-473
[iii] The Preseter John of the Indies, p. 312
[iv] ስለ ተርጓሚው ስለ እጨጌ ዕንባቆም ለማወቅ ‹ እጨጌ ዕንባቆም - ከየመን እስከ ደብረ ሊባኖስ› የሚለውን መጽሐፍ ያንብቡ፡፡

29 comments:

 1. በመጀመሪያ እንኳን ለመላኩ ዓመታዊ በዓል በሰለም አደረስህ/ን ወንድሜ በሰላም ነው ወይ የጠፋኸው? ዳኒ እግዚአብሔር ሰላምህን ያብዛልህ እመብርሃን ትከተልህ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 2. WOW Dani, MIn enilalen... Egziabher Yistih... It tells my story very clearly

  ReplyDelete
 3. Welcome back መጥፋትህ አሳስቦኝ ነበር

  ReplyDelete
 4. Thank You Dn.Daniel
  This days you disappeared
  what happened to you

  ReplyDelete
 5. D/n dani enkuan beselam metah bemetfateh betam kir belogn nebr beselam new? hullem tsufochehen selemiketatel sus honobign nebr anway ahunim enkuan beselam metahilen antem tsaf egnam enemaralen ...

  ReplyDelete
 6. Dear Dani,

  Enkuan bedigami lemetsaf abekah ebakih tsihufochih lene migib nachewina atitfa.

  egzihabher yebelete gulbetna tibebun yistih!

  ReplyDelete
 7. ዲያቆን ዳንኤል፡ አንተ በጣም ብልጥ ነህ፤ ብዙ ታውቃለህ፤ ግን እምነት ደግሞ የለህም፡
  ስለ ኦርቶዶክስ ታውቃለህ፤ ግን አታምንበትም።
  እምነት ስሌለህ ፈሪ ነህ፤ ስለዚህ እውነትን በፊት ለፊት መናገር ድፍረት የለህም።
  እነዚያ እንዳንተ ብዙ ሳይራቀቁ፤ በ40 እና በ80 ተጠምቀው ብቻ ኦርቶዶክስ ሆነው
  ያለፍርሃት እውነትን ተጋፍጠው በእስር የሚማቅቁት ብዕረኞች ክርስትናን ይበልጥ ይኖሩታል። ክርስትና ስለእውነት መሳደድ፤ መሰቃየት ስለሆነ።
  ፈሪ እምነት የለሽ ስለሆንክ ቅኔ አዘል ስብከት የምትሰብከው፤ አልተናገርክም ተብለህ እንዳትወቀስ ሲሆን፤ ይህች አካሄድህ ደግሞ ከገዳዩም ከሟቹም ጋር በሰላም ያኖርሃል።
  አንተ እና የዘመኑ ሰባኪያን ሁሉ፤ ክርስትናን መተዳደሪያችሁ አታምኑበትም።
  እውነትን ብትጋፈጡት እና ከዕምነት የምጣ ድፍረት ቢኖራችሁ ኖሮ፤ ዛሬ ቢያንስ ቦያንስ ህዝቡ ማወቅ የሚገባውን እያሳወቃችሁ፤ ለለውጥ ባስነሳችሁት ነበር፡
  ታሪክ ተቀይሮ ቤተክርስቲያን እና ምዕምኖቿ ተሳዳጅ በሆኑበት ዘመን፤ ታሪክን በማስተማር ብዙ ብዙ የማንቃት ሥራ በተሰራ ነበር።
  እውነትን የምታውቁት እናንተ ዝም ስትሉ፤ የዲያቢኢሎስ መልዕክተኞች ወያኔ እና የጃዋር ጀሌዎች በጠራራ ጸሀይ ሃሰትን ይዘው ህገሪቷን ለከፋ አደጋ እያጣደፏት ነው። እናንተ ደግሞለሰው ጆሮ የሚጥም ስብከት ብቻ እያስተላለፋችሁ። እንደ ፕሮተስታንቲስም
  ታምርን ከሰማይ እንዲጠብቅ፤ ከጸሎት በቀር ምንም አማራጭ እንደሌለ እየንገራችሁ፤ ለቀጣይ ጥፋት እና አጋዛዝ ታመቻቹታላችሁ።
  ዘመናችሁን ሙሉ ስለክርስትና አውርታችሁ ሳትኖሩበት በብልጠት ብቻ ዘመናችሁ ሲያልፍ በጣም ታሳዝናላችሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. why don't you do your part instead of waiting or telling someone to do it.

   Delete
  2. አጻጻፍህ/ሽ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም ምክንያቱም ኦርቶድክሳዊ የሆነዉን አስተምህሮ እየኮነንክ/ሽ ነው ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም የፀሎትን ሃይል እያቃለልክ/ሽ ነዉና።
   የመጨረሻዉ ዘመን ማመላከቻ የሆነውን ክስተት ያለፀሎት ሌላ መፍትሄ ሊኖረው አይችልም። ስለዚህ ፀሃፊዉ ወንድማችንን ዝም ብልህ ባትኮንነው ደስ ይለኛል።

   Delete
 8. ኀጢአትን ጠልተውና ንቀው በመጋፈጥ ንስሓ ሳይገቡበት ቢረሱት፤ ኀጢአትነቱን አያሳንሰውም ልማድ ሆኖ ያጠፋል እንጂ።

  በተመሳሳይ መልኩ አስተዳደራዊ በደልን እየፈጸሙ እርምትና ማስተካከያ በመውሰድ ፋንታ፤ አንዳልተፈጸመ ለማረሳሳት መሞከር፤ የበደሉን መራራነት አይቀንሰውም፣ ከታሪክ ማኅደርም አይፍቀውም፣ይልቁን፣ በተበዳዩ ልብ በቀልን በበዳዩ ሕይወትም የጊዜ ቦንብን ነው የሚቀብረው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምን ነው ወዳቻችን እራስዎ ስመዎን የሸሽጉ ፈሪ ሆነው ሳለ፣ ለምን ከእርሰዎ የሚሻለውን ይውቅሳሉ። ፈሪ ማለት እኮ ስሙን ሸሽጎ የሚሳደብ እንጂ እንደ ዳኒ ብሎግ ክፍቶ እውነቱን የሚናገር አይደለም። እስኪ እርሰዎ ምን ሰሩ? የትኛው ጋ ተጋፈጡ? እኛ ሙቱ እንላለን እንጂ ሞትን አንጋፈጥም። ዻኒ ቢታሰር እኮ የእኛ አንደበትም እኮ ነው አብሮ የሚታሰረው። እርሰዎ ብዙ መናገረወ፣ የጭንቅላተዎን ባዶነት ያሳብቅበዎታል እና ዝም ይበሉ፣ ያን ጊዜ ሁላችንም አለማወቀዎትን አናውቅም

   Delete
  2. ስመዎን የሸሸጉ Bሎገር፣ የቀደመውን አስተያየት ስንት ግዜ አንብበው ነው፣ ይኼን ተመጻዳቂ አስተያየት የሰጡት?

   Delete
 9. tefah wendimachin
  dink new

  ReplyDelete
 10. EGZIABHER yistilen. It's good to hear from you again. EGZIABHER YIMESSGUEN.

  ReplyDelete
 11. እግዚአብሔር ሰላምህን ያብዛልህ እመብርሃን ትከተልህ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 12. በመጀመሪያ እንኳን ለአባታችን ተ/ሀይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰለም አደረስህ/ን ወንድሜ በሰላም ነው ወይ የጠፋኸው? ቃለ ሂዎት ያሰማልን

  ReplyDelete
 13. ቃለ ህይወት ያሰማልን ውድ መምሕራችን ...ለረጅም ሳምንታት በመጥፍትህ ይህ ጣፍጭ ምክርህ እና እይታህ ናፍቆኝ ነበር ተመስገን

  ReplyDelete
 14. Kalehiwot yasmalin batami astamari tshufi nawu!!! welcome back batami tafahi eko ba selam nawu Egizabher ragimi edima ka tena ga yistilini!!!

  ReplyDelete
 15. Dn Daniel Kale Hiwot Yasemalen, Enkuan bedehina temelesek.Cheru amelakachin Behagerachine be emiye Ethiopia ena lejochua lay eyehonebene yalewun y aseb ke zendo , keba kegintu yisewuren ye mare wolela yehonewun yemenfes tsega yafiselen

  ReplyDelete
 16. ቃለ ህይወት ያሰማልን ውድ መምሕራችን ...ለረጅም ሳምንታት በመጥፍትህ ይህ ጣፍጭ ምክርህ እና እይታህ ናፍቆኝ ነበር ተመስገን

  ReplyDelete
 17. enkuan dehna mexah dani bexam ameseginalew yemitsifachew negeroch astemarowoch silehonu qexilibet

  ReplyDelete
 18. melkam new d/n. negergn yehagerachn wd ena astemari tarikoch balubet yeruku metenten ena metereku belom mastemar tegegbi new beye almnim. miknyatu mejemerya yerasachn yhonewn atbken keyazn behala yegorebtachnin benawk turu new...

  ReplyDelete
 19. Dear Deacon Danial,It is best, for those on the verge of behavioral change and I need your advice for good will. Still many thanks.

  Remain nice and healthy.

  ReplyDelete