Tuesday, September 20, 2016

ሦስቱ የሕዝብ ማስጠንቀቂያዎች

ሕዝብ ለመሪው በሦስት ደረጃ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡ የመጀመሪያው ‹አርም› የሚል ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ሕዝቡ ሦስት ነገሮችን አምኗል ማለት ነው፡፡ አንድም መሪው በጎ ኅሊና አለው፤ ለማረም የሚችል ዐቅም አለው፤ ችግሩ የተፈጠረው ከአሠራሩ ላይ ነው ብሏል፡፡ አንድም ደግሞ ሕዝቡ መሪው እንደማንኛውም ፍጡር ተሳሳተ እንጂ ራሱ ስሕተት አይደለም፡፡ ስለዚህ ሊያርም ይችላል ብሎ አምኗል፡፡ በመጨረሻም ሕዝብ መሪውን ይወዳል፣ ስሕተቱን ግን ይጠላል ማለት ነው፡፡
 
እዚህ ላይ የደረሰ መሪ የታደለ የሚሆነው ስሕተቶቹን ነቅሶ ‹ሳይርቅ በቅርቡ፣ ሳይደርቅ በርጥቡ› ለማረም ከቻለ ነው፡፡ የሚሳሳት ፈጣሪ እንደሌለ ሁሉ የማይሳሳት መሪ የለም፡፡  መሪዎችን ታላቅና ታናሽ የሚያደርጋቸው ስሕተታቸውን ለማመንና አምነውም ለማረም ያላቸው ዐቅምና ቁርጠኛነት ነው፡፡ መሪ የሕዝቡን ጥቆማ ሰምቶ፣ የሕዝቡንም ልብ አድምጦ ችግሩን በጊዜ ካረመ ስሕተቱ ከሥራ የመጣ እንጂ ከመሪው ጠባይ የመነጨ አይደለም ብሎ ሕዝብ በመሪው እንዲተማመን ያደርገዋል፡፡ ‹ከሰው ስሕተት፣ ከብረት ዝገት አይጠፋም› ብሎ ያልፈዋል፡፡ ሕዝብ የነገረውን ስሕተት ከማረም ይልቅ ‹እኔ ደኅና ነኝ ችግሩ ከአፈጻጸሜ የመጣ ነው› እያለ ችላ ካለው ሕዝብ ወደ ሁለተኛው ደረጃ ይሻገራል፡፡ ጃን ሜዳ ሠፍሮ እያደመ ራስ ተፈሪን ወደ ዙፋን ያመጣው መሐል ሠፋሪ ጦር (ሠራዊቱ) ነበር፡፡ በኋላም አርሙ ቢላቸው አላርም ሲሉ በ1953 መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው ይኼው ሠራዊት ነው፡፡    
 
ሁለተኛው የሕዝብ ማስጠንቀቂያ ‹ታረም› የሚል ነው፡፡ ሕዝብ  መሪውን ‹ታረም› ካለ ሁለት ነገሮችን አስቧል፡፡ ‹መሪው ልክ ነበር ነገር ግን  እንደማንኛውም ፍጡር ተሳስቷል› የሚለው ሐሳቡን ቀይሯል፡፡ ‹መሪው ስሕተቱን ሊያርም ይችላል› ከሚለው ወጥቷል፡፡ ይህንን ዕድል ላይመለስበት አልፎ መሪው ስሕተት የሚሠራ ሳይሆን ስሑት (የተሳሳተ) መሪ ነው፡፡ ስሕተቱ ከሥራ ሂደት ሳይሆን ከአመራሩ፣ ከአስተሳሰቡና ከአካሄዱ የመጣ ነው፡፡ ተግባሩ እንዲስተካከል መሪው መስተካከል አለበት ብሎ ሕዝቡ አምኗል ማለት ነው፡፡ ከኩርንችት በለስ፣ ከአጋምም ወይን ሊለቀም አይችልም፡፡ ውኃው እንዲስተካከል ምንጩ መስተካከል አለበት ብሎ ሕዝብ ማሰብ ጀምሯል፡፡ እንደዚያም ቢሆን ግን መሪው ራሱን ሊያረም የሚችል መሪ ነው ብሎ አምኗል፡፡
 
በዚህ እከን ላይ የደረሰ መሪ ራሱን ፈትሾ፣ መርምሮና አንጥሮ እንደ ወይን ግንድ እየገረዘ ሸለፈቱን መጣል አለበት፡፡ ሌላውን ሰውነት ለማዳን ሲባል ሕመምተኛው የሰውነት አካል እንደሚቆረጠው ሁሉ ሀገርን ለማዳን ሲባል የሚቆረጡ አሠራሮች፣ አስተሳሰቦች፣ አካሄዶች፣ መሪዎች፣ ፖሊሲዎችና መርሖች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ‹ታረም› የተባለ መሪ እነዚህን አርሞ እንደ እባብ ሳይሆን እንደ ንሥር ታድሶ ከመጣ፤ ጥፋቱ ከአፈጻጸሜ የመጣ ነው፣ ሕዝቡ ስላልገባው ነው፣ ስላልተማረ ነው፣ ስላልሠለጠነ ነው፣ እያለ የመሥዋዕት በግ ፍለጋ ካልኳተነ፤ ‹ችግሩ እኔ  ነኝ፤ መፍትሔውም የእኔ መለወጥ ነው› ብሎ ካመነ፤ አምኖም ከሠራ፤ ሠርቶም ከተለወጠ፡፡ ሕዝቡ፡-
‹አሁን ወጣች ጀንበር
ተሸሽጋ ነበር› ብሎ ይቀበለዋል፡፡
ይህንን ሁሉ ትቶ መሪው በሕዝቡ ትዕግሥት ላይ ከቀለደ፤ ሕዝብም ለትዕግሥቱ ምላሹ ካለፈው የባሰ፣ ከተስፋው ያነሰ ሲሆንበት፤ ሕዝብ አመለካከቱን ይቀይራል፡፡ አርም፣ ታረም ማለት ዋጋ አልባ መሆኑን ይረዳል፡፡ ሊያርም ሊታረም የሚችል መሪና አመራር የለም ብሎ ያምናል፡፡ ችግሩ መሠረታዊ ነው ብሎ ይረዳል፡፡ በዚህ ጊዜ ሦስተኛውንና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያውን ይሰጣል፡፡ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴን ሆ ብሎ ወደ ሥልጣን ያመጣው ወታደር፣ ስሕተቶቻቸውን ማረም ሲያቅታቸው በ1953 መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው ወታደር፤ በ1966 ደግሞ ሥልጣናቸውን አሳጣቸው፡፡ የ1953ቱ መፈንቅለ መንግሥት ‹ታረም› የሚል መልእክት እንዳለው ንጉሡ ቢረዱ ኖሮ የ66ቱን ነገር ያስቀሩት ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ‹ታረም› የሚለውን አልረዳ ሲሉ ‹ተወገድ› የሚለው የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ መጣ፡፡ 
 
ደርግም እንዲህ ነበር፡፡ በ66 አብዮቱ ሲፈነዳ፣ መሬት ላራሹ ሲታወጅ የሕዝብ ድጋፍ ነበረው፡፡ ቆይቶ ስሕተት ሲያበዛ ‹አርም› የሚለው መልእክት ከያቅጣጫው መጣ፡፡ ሰልፎች፣ ወረቀቶች፣ ተቃውሞዎች መጡ፡፡ ከማረም ይልቅ ‹መረምረም› ስለመረጠ የመጀመሪያውን ዕድል አሳለፈው፡፡ ከውስጥና ከውጭ ጠብመንጃ አንሥተው ግራ ቀኝ የወጠሩት ኃይሎች ‹ታረም› ቢሉትም መታረም ትቶ ማውደምን መረጠ፡፡ የ1981 ዓም መፈንቅለ መንግሥት ‹ተወገድ› የሚለውን መለከት ነፋ፡፡ ደርግ የሚተርፍ መስሎት ለፋ፡፡ ግን ተወገድ ከተባለ በኋላ መትረፍ በተአምር ብቻ ነበርና ሊተርፍ አልቻለም፡፡
 
ይህ ‹ተወገድ› የሚለው ሦስተኛው  ማስጠንቀቂያ የመጨረሻው የሕዝብ ጥያቄ ነው፡፡ መሪው ታምሞ አይደለም፡፡ ራሱ በሽታ ነው፡፡ ተቸግሮ አይደለም፡፡ ራሱ ችግር ነው፡፡ ደክሞ አይደለም፡፡ ራሱ ደካም ነው፡፡ ተፈትኖ አይደለም፤ ራሱ ፈተና ነው ብሎ አምኗል፡፡ ስለዚህም መፍትሔው መወገድ ብቻ ነው ብሎ ይቆርጧል፡፡ ቆርጦም ይሠራል፡፡ ሕዝብ እዚህ ደረጃ ከደረሰ በኋላ መመለስ ብዙ ጊዜ ከባድ ነው፡፡ ማረምንም መታረምንም ከሚቀበልበት እርከን አልፏልና ቀሪው ዕድል የሚሆነው በሰላም መሰናበት ነው፡፡
 
የአንድ መሪ ብስለት በሁለት ደረጃ ይለካል፡፡ የመጀመሪያው ሲቻል በፊተኛው፣ ሳይቻል በቀጣዩ ደረጃ ላይ መንቃት፣ ነቅቶም  ተገቢውን ማድረግ፡፡ ያም ዘመን ካለፈና ጀንበር ካዘቀዘቀች ደግሞ ራሱንም ሀገሩንም ሳያጠፋ መልካም የወንድ በር ማዘጋጀት ነው፡፡
ዘቦ እዝን ሰሚዐ ለይስማዕ፡፡  
21 comments:

 1. ጊዜው የደረሰ ልዕለ ሃሳብ ይፈጠፍጣል እንጂ አይጋፈጡትም፡፡

  አይደለም እንዴ? ዋሸሁ እንዴ? እንዳለ ዘፋኝ፡፡

  ReplyDelete
 2. እውነተኛ መንግስት ቢኖር ነበር ነገርግን እውነተኛ ገዢ ስለሆኑ አያምኑበትም።

  ReplyDelete
 3. መፍትሔው መወገድ ብቻ ነው

  ReplyDelete
 4. Rgzabher Zerehen ende ashewa yabzaw Dn. Daniel Eewentenena ewketen Yegeletselehe Cheru Egzeabehere yemesgen.please at least in this last minute the people who are in power as a citizen for your citizen leave your sit(chair)to the next one in peace you are not going to be a looser.i pray so hard who ever comes next is who is going to listen his creator's voice. God bless Ethiopia and save our nation for ever.

  ReplyDelete
 5. Well said!!! I don't think our government gets it though.

  ReplyDelete
 6. ‹ተወገድ› የመጨረሻው የሕዝብ ጥያቄ ነው፡፡ መሪው ታምሞ አይደለም፡፡ ራሱ በሽታ ነው፡፡ ተቸግሮ አይደለም፡፡ ራሱ ችግር ነው፡፡ ደክሞ አይደለም፡፡ ራሱ ደካም ነው፡፡ ተፈትኖ አይደለም፤ ራሱ ፈተና ነው ብሎ አምኗል፡፡ ስለዚህም መፍትሔው መወገድ ብቻ ነው::

  ReplyDelete
 7. እንበለ እዝን አኮ ----------

  ReplyDelete
 8. it is wonderfull and smart idea.many peoples in majority of countries followed(did)those steps.So we have to carefull on the current situations.

  ReplyDelete
 9. የዚህ መንግሥት expiry date ካለፈ ቆየ።
  ተወገድ የተባለው ገና፣ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ና እኩልነትን አሣቦ፣ በቀልን በሕዝቡ ልብ የዘራ ጊዜ ነው። በኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት አስፈላጊነቱ የማያጠራጥር የማያነጋግር ቢሆንም፣ አሸባሪው ሕወሓት "እኩልነት" ያወጀበት ጊዜና መንገድ ከሃገር አሸባሪ እንጂ ከሃገር መሪ የሚጠበቅ አልነበረም።

  ተወገድ የተባለው ገና ፌዴራሊዝምን በጂኦግራፊ/መልክዐ ምድራዊ/ ሣይሆን በዘርና በቋንቋ መሰረትነት ሲያቀናጅ ነው። አይ ብስለት ማጣት!

  ተወገድ የተባለው ያለ ሕዝብ ሬፈረንደም ኤርትራን ገንጥሎ አስተዳድራለው የሚለውን የኢትዮጵያን ግዛት የባሕር በር ሲያሳጣው ነው። ስላቅ!

  አልቦ ዕዝን ለዝንቱ ቀታሊ እስመ ሰየጦ ሰሚዐ ዕዝኑ ወፍትሐ ሕሊናሁ ለዕቡይ ልብ ወእድ ዘይክዕው ደመ ዜጋሁ

  ReplyDelete
 10. Out of those three steps in which one we are at now?

  ReplyDelete
 11. But, the third one doesn't seem a warning.

  ReplyDelete
 12. But, the third one doesn't seem a warning.

  ReplyDelete
 13. ‹ተወገድ› የመጨረሻው የሕዝብ ጥያቄ ነው፡፡ መሪው ታምሞ አይደለም፡፡ ራሱ በሽታ ነው፡፡ ተቸግሮ አይደለም፡፡ ራሱ ችግር ነው፡፡ ደክሞ አይደለም፡፡ ራሱ ደካም ነው፡፡ ተፈትኖ አይደለም፤ ራሱ ፈተና ነው ብሎ አምኗል፡፡ ስለዚህም መፍትሔው መወገድ ብቻ ነው::

  ReplyDelete
 14. ‹ተወገድ› የመጨረሻው የሕዝብ ጥያቄ ነው፡፡ መሪው ታምሞ አይደለም፡፡ ራሱ በሽታ ነው፡፡ ተቸግሮ አይደለም፡፡ ራሱ ችግር ነው፡፡ ደክሞ አይደለም፡፡ ራሱ ደካም ነው፡፡ ተፈትኖ አይደለም፤ ራሱ ፈተና ነው ብሎ አምኗል፡፡ ስለዚህም መፍትሔው መወገድ ብቻ ነው::

  ReplyDelete
 15. This really shows our country's current scenario.

  ReplyDelete
 16. I think our current government should ask and find in which steps is its leadership. I think they are not in between tarem and teweged. But they are pushing the people to fight them. They have to correct themselves by avoiding ethnic politics. I am so tired of this ethnicity. We need the government to avoid ethnic based administration. BERELE KENEKA AYHONEM EKA>>>>>>>>>>>>

  ReplyDelete
 17. ዘቦ እዝን ሰሚዐ ለይስማዕ፡፡

  ReplyDelete
 18. Dn Daniel, Kale Hiwot Yasemalen. Cheru Medhani Alem Hagerachinen Ethiopia Ketifat Lejochuan Kelekite Ena Kesedete Becherenetu Yitadegilen. Abet Egziyo new yetinibitu mefetsemiya endanehone. Ebakachihun Ye Ethiopian Tifatuane Yewodedachihu Hule Ethiopia Hager Egziaabehere natena Atitefame Ebakachihune Kehizibu ena Kehageritu lagne Ejachihun Ansu. Hulu Alafi new ena Ye Ethiopia Geziwochu Ebakachihu Bemechereshawu seate enkun bekane belu Ye hizibuan dimets semu. ETHIOPIA EJOCHUAN WODE EGZIABEHER TIZEREGALECH.

  ReplyDelete
 19. Good read Daniyee!! Thank you tho.

  ReplyDelete
 20. መንግሥት ይወገድ ከማለታችን በፊት የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ብንመረምር አይሻልም? የሀገራቱ ጉዞ ከደርግ ጀምሮ ከድጥ ወደ ማጥ እየሆነ እያየን ለመንግሥት ለውጥ ባንቸኩልስ? በተለይ ደግሞ ለቤ/ክ ፈተናው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ ወደፊትም ይብሳል እንጂ የተሻለ ነገር አይጠበቅም ምክንያቱም ከኃጢኣት ብዛት የተነሳ የብዙ ሰው ፍቅር ቀዝቅዞ በጎሳ ተለያይተን እየተጠፋፋን ነው፤በዘር የመለያየት ጉዳይ በዓለም ላይ ተንሰራፍቶ ይኸው እኛንም እያተራመሰን ይገኛል፤ይህ ትንቢት ስለሆነ የግድ መፈጸሙ የማይቀር ነው፤ ትናንት በዓለ መስቀል በአዲግራት በደማቅ ሁኔታ የተክበረ ሲሆን በሌሎቹም ቦታዎች ተከብVል፤ በ2008 የተከሰተው ግድያና እስራት በዚህ ዘመን እንዳይደገም የመስቀሉ ጌታ በቃችሁ ይበለን፡፡ እኔን የገረመኝ ግን በመስቀል እናምናለን እያልን ወንድሞቻችንን ስናጠፋ ምን ያህል የዘር ጉዳይ በቤክ ጭምር ውስጥ እንደገባ ማየታችን ነው፤ይህ በሞሶሎኒ ወረራ ጊዜ የሮም ነዋሪዎች ድጋፍ መስጠትን ያስታውሰናል፡፡ እንደ ክርስቲያን ሳስብ ግን ሁላችንም ወንድማማች ነን፡፡ በአንድ ወቅት በ4 ኪሎ በዓታ ለማርያም ቤ/ክ ውስጥ የሚያገለግሉት ካህናት ተጣልተው ሲቀድሱ የእመቤታችን ስዕል ከዓይንዋ ዕንባ ፈስሶ ስዕሉ የተሳለበት ክርታስ ተጨማዶ አይቻለሁ፡፡ አሁንም ቢያንስ በሃይማኖት አንድ የሆንን መጣላት የለብንም፣ ሲቀጥል ደግሞ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ የሚለውን የቅ/ጳውሎስ ማሳሰቢያ ተግባራዊ እናድርግ፡፡ እርግጥ ነው በትንቢተ ዳንኤል እንደተጻፈው ልዑል እግዚአብሔር የዓለምን መንግስት ለወደደው ወገን ይሰጣል፤በዚህም መሠረት አሁን በሀገራችን ተራው ደርሶአቸው እየመሩ ያሉት ብሔረ ትግራይ ናቸው፣ እነርሱን መቃወም ስልጣንን የሰጣቸው እ/ርን መቃወም ይሆን? ግን ደግሞ የእነዚህ ሰዎች ድረጊት ቁጭ ብሎ የእ/ርን ጊዜ የሚያስጠብቅ ነው ሊባል ይችላል?ለምሳሌ በልማት ስም የተፈናቀሉት በአ/አ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሞ አርሶ አደሮችና የአ/አ ነዋሪዎች፣የንግዱና ሁሉም የኢኮኖሚ አውታሮች በአንድ ብሔር መያዙ፣በኢንቨስትመንት ስም እየገቡ ያሉት ባህላቸውና አመጋገባቸው ከእኛ ጋር የማይሄድ (ውሻ የሚበሉ) የውጭ ዜጎችን ማስገባት ወዘተ. ሲታይ እነዚህ ገዢ መደቦች ምንጫቸው ክርስቲያን ቢሆንም ግብራቸው የአሕዘብ እና ከልክ ያለፈ ራስ ወዳድ በመሆናቸው የህዝቡ መነሳት ተገቢ ነው ያሰኛል፡፡ ሰው በተማረና በሰለጠነ ቁጥር ራስ ወዳድ፣ዓለምን ወዳጅና ፈሪሀ እ/ርን የሚያጣ ከሆነ የምዕራባውያን /አስኮላ/ ትምህርት በቀረብን ያሰኛል፣ድሮ አባቶቻችን ሰላም ለኪ ብለው የሚያጡት ነገር አልነበረም፣ በፍቅር ኖረው ጠላትን አሸንፈው ለእኛ አስረከቡን፣በጣሊያን ጊዜ አርበኛ የነበሩ እንድ ታላቅ አባት ጣሊያን 11 ጥይት ተኩሶባቸው ምንም ሳይሆኑ እርሳሱ በደረታቸው ላይ ቀር~ል፤ ያ ሁሉ የጣሊያን ኃይል የወጣው በእምነትና በእ/ር ረዳትነት ነበር፤ አሁን ተማርን፣ሰለጠንን አልን ግን አልተማሩም ከተባሉት አነስን፣እምነት ቢኖረን መሣሪያ ምንም አይደለም፤ ሌላው ዋነኛ ነገር የኢየኃድግ መንግሥት ስልጣን ቢለቅ ማን ይመጣል ቢባል የባሰ ጽንፈኛ ቢሆንስ? ቢያንስ አሁን እግዚአብሔርን ማምለክ በነጻነት እያመለክን ነው፡፡ ትርጉም ባለው መልኩ ተደራጅቶ መዋጋት የትግራይ ልጆች በመጡበት መንገድ ዋጋ ከፍሎ ጨካኝ ሆኖ የብዙ ሰው ነፍስ አጥፍቶ ከንቱና ሀላፊ የዓለምን ሥልጣን ለመያዝ መሞከር በመንፈሳዊ ዕይታ ጤናማ አይመስለኝም፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ልዩ ባህሪይ ለእንስሳት ነፍስ ጭምር የሚያስብ መሆኑና የሰው ደም የሚሰቀጥጠው መሆኑ ነው፣ ይህ ሆኖ ነው እንጂ የኦሮሞና አማራ ሕዝብ እንደተነሳው የትኛውም የኢየኃድግ ሠራዊት ሊመልሰው አይችልም ነበር፤ይህንን ተገንዝቦ አመራሩ የታሰሩትን እንዲፈታና ለከንቱ ሥልጣን ብሎ ለብዙ ሺ ዓመት በፍቅር የኖረውን ህዝብ ባያባላ ጥሩ ነው፤ ህዝቡም ደግሞ አላስፈላጊ መስዋዕትነትን ከመክፈል እንዲቆጠብና ‘አትሩጥ አንጋጥ’ የሚለውን ብሂል አስቦ ሁሉን ቻይ ወደሆነው ፈጣሪ እንዲጸልይ ለሞቱት ወንድሞቻችን እ/ር ዕረፈተ ነፍስ እንዲሰጥልን በመለመን በትዕግስት ይቺን ቀን እንዲያልፍ እላለሁ፡፡ ‘ኦ ሕዝብየ ባ ቤተከ ወእጹ ሆኅተከ ወተኃባእ ኅዳጠ ምዕረ እስከ የኃልፍ መዓቱ ለእግዚአብሔር’ ይላል ኢሳይያስ፡፡

  ከዚሁ ጋር አያይዤ ቀሲስ በላይ ስለኦሮሞ ባህልና ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አስመልክቶ በኦሮሚያ ቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ገለጻ የእሬቻ በዓል ከሃይማኖት ጋር አይገናኝም ብለዋል፤ይሁን እንጂ ይህ ሃሳባቸው በቅድሚያ ውድቅ የተደረገው በዋቄፈታ እምነት ተከታዮች ነው፤ የኛስ ቤ/ክ ምን ትላለች?ቅ/ሲኖዶስ ምን እየሠራ ነው? አንድ ቄስ ወይም ጳጳስ እንዲህ ማለት ይችላል?ይህ ከዶግማ ጋር የሚገናኝ ጉዳይ በሲኖዶስ እንጂ በአንድ ቄስ ሊወሰን ይችላል?

  ReplyDelete
 21. የድረ ገፅ ጽሁፎችህንም ሆነ የፃፍካቸውን መጽሐፎች መጣም በመደነቅና በመገረም አነባቸዋለሁ ለጓደኞቼም ማለፍ የሌለበት ዕውቀት ሥለሆነ እጋብዛቸዋለሁ፡፡ እና በዚሁ ግፋበት፡፡ ከቻልክ ሥለቅባትና ተዋህዶ አምነት ሠፋ ያለ ማብራሪያ ብትፅፍ፤ ምክንያቱም በተዋህዶ ሥም ቤተክርሥቲያን በሌሎች አማኞች ተከባለጭና፡፡

  ReplyDelete