ሀገር ሰላም እንድትሆን፤ ሰላም
ሆናም በብልጽግና ጎዳና እንድትራመድ ከታሰበ ሁለት ነገሮች የግድ ያስፈልጓታል፡፡ ሕዝብን የሚያዳምጥ መንግሥትና መንግሥትን የሚያዳምጥ
ሕዝብ፡፡ ማዳመጥ ከመስማት ይለያል፡፡ መስማት ጆሮ ለተፈጠረለት ሁሉ የሚቻል ነው፡፡ ይህን ጽሑፍ ስናነብ እንኳን ስንትና ስንት
ድምጾችን ፈልገንም ሳንፈልግም እንሰማለን፡፡ ማዳመጥ ግን ሦስት ነገሮችን ይፈልጋል፡፡ ይሁነኝ ብሎ መስማት፣ ሰምቶ ማስተዋል፣ አስተውሎም
መመለስ፡፡
ሕዝብን የሚያዳምጥ መንግሥት ስንልም
ይሁነኝ ብሎ ሕዝቡን የሚሰማ፣ ሰምቶ ሕዝቡ ምን እንዳለው የሚያስተውልና ከዚያም አስተውሎ መልስ የሚሰጥ መንግሥት ማለት ነው፡፡
ለሕዝብ የመናገር ነጻነት ብቻውን ምንም አያደርግለትም፡፡ የመደመጥ መብት ከሌለው በቀር፡፡ ሰሚ ከሌለ እንኳን ሕዝብ ፈጣሪ አይናገርም፡፡
ቢናገርም ጥቅም የለውም፡፡ ለዚህም ነው ሊቃውንቱ እንደሚነግሩን መላእክት እስኪፈጠሩ ድረስ ፈጣሪ ፍጥረታትን በአርምሞ ብቻ የፈጠረው፡፡
ለምን? ቢሉ ሰሚ ሳይኖር መናገር ምን ያደርጋል ብሎ፡፡ መላእክት ከተፈጠሩ በኋላ ግን ‹ብርሃን ይሁን› ብሎ ሲናገር እንሰማዋለን፡፡
አሁን ሰሚ ተገኝቷልና መናገር ዋጋ አለው፡፡
ሕዝብም መናገሩ ብቻ ጥቅም የለውም፡፡
የተናገረውን የሚያዳምጠው መንግሥት ያስፈልገዋል፡፡ ሕዝብ የሚያዳምጠው ሲያጣ ጩኸቱን የሚያዳምጠው አጥቶ ቤቱ እንደተዘረፈበት ውሻ
‹ነባህነ ነባህነ ከመ ዘኢነባህነ ኮነ
- ጩኸን ጩኸን እንዳልጮኽን ሆን› ብሎ አይቀመጥም፡፡ ራሱን በራሱ ማዳመጥ ይጀምራል፡፡
የልቤን መከፋት ሆዴ እያዳመጠ
ሊመረው ነው መሰል ነገር አላመጠ
የሚል የቆለኛ ፉከራ አለ፡፡
ሰውዬው
በልቡ መከፋቱን ለሰው ቢናገር ቢናገር የሚሰማው አጣ፡፡ እርሱ ሰሚ ሲያጣ ሆዱ ግን የልቡን መከፋት እየሰማ ይቃጠል ጀመር፡፡ በኋላም
ሆዱ እየቆረጠ ሲሄድ ጊዜ ነው ይህንን የፎከረው፡፡ ሕዝብ ራሱን ማዳመጥ ሲጀምር ‹ሊመረው ነው መሰል› የሚለው ፉከራ ላይ እየደረሰ
ነው ማለት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ የሚሆነውን ለመገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ ሕዝብን በርእዮተ ዓለም፣ በሐሳብና በአመለካከት አንድ ለማድረግ
እጅግ ጽኑ ትግል፣ እጅግ ብርቱ ጥረት፣ እጅግ ብዙ ልፋት ይጠይቃል፡፡ ሕዝብን በቀላሉ የሚያስተባብረው አንድ ነገር ነው፡፡ መጠቃት
ወይም መገፋት፡፡ ያን ጊዜ ወዲያ ማዶ ሆኖ አንዱ የተጣራውን ወዲህ ማዶ ሆኖ ሌላው ይሰማዋል፡፡
እዚያ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ተጣራ
እዚህ ማዶ ሆኖ ሌላ ሰው ወይ አለው
ጎበዝ ተነቃቃ ይህ ነገር ለኛ ነው
ማለት የሚችለው የሚዳምጥ መንግሥት
ካለ ብቻ ነው፡፡
መንግሥት ሕዝብን ይሁነኝ ብሎ ነው
ማዳመጥ አለበት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሕዝብ የተናገረው ላይደርሰው ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሕዝብ ያልተናገረውን ሊሰማ ይችላል፡፡
ሕዝብ የተናገረው ለመንግሥት ካልደረሰው ወይም ሕዝብ ያልተናገረውን
መንግሥት ከሰማ እወደድ ባዮች ለመንግሥት የሚያስፈልገውን ትተው መንግሥት የሚፈልገውን ብቻ ይነግሩታል ማለት ነው፡፡ ሕዝብ ብዛት
ብቻ አይደለም ያለው፡፡ ውጥንቅጥም ነው፡፡ በእምነት፣ በርእዮተ ዓለም፣ በመፍትሔ አቅጣጫ፣ በባህልና ቋንቋ፣ በዕውቀትና ሥልጣኔ፣
በዕድሜና ጾታ የተወነቀጠ ነው - ሕዝብ፡፡ ሕዝብን ማዳመጥ ማለት
እነዚህን ሁሉ በየመልካቸው ማዳመጥ ማለት ነው፡፡ ሕዝብ ውስጥ መንግሥትን የሚወዱና የሚደግፉ፣ መንግሥትን የሚጠሉና የሚቃወሙም አሉ፡፡
ሕዝብን ማዳመጥ ማለት እነዚህን በየመልካቸው ማዳመጥ ማለት ነው፡፡
ሕዝቡ ይህንን ሲል ምን ማለቱ ነው?
ለምን እንዲህ አለ? ምን ስለ ሠራሁ ወይም ምን ስላልሠራሁ ነው? የትኛውን ችግሬን ስፈታው የሕዝቡ ጥያቄ ይመለሳል? ብሎ ማስተዋል
ነው ሕዝብን መማዳመጥ ማለት፡፡ ሕዝቡ ስላልገባው ነው? ስላልተረዳ ነው? ስላልተማረ ነው? ስላልሠለጠነ ነው? እያሉ ጠያቂውን የችግሩ
መነሻ ማድረግ ሕዝብን ያለመስማት ዋናው መገለጫው ነው፡፡ ‹ደንበኛ ንጉሥ ነው› እያልን ‹ሕዝብ ንጉሥ ነው› የሚለውን እንዴት መቀበል
ያቅተናል? ‹ደንበኛ አይሳሳትም› እያልን ‹ሕዝብ አይሳሳትም› የሚለውን እንዴት ማመን ይሳነናል?
በደርግ ጊዜ አንድ የገጠር ሕዝብ
ያምጻል፡፡ መሬት ሲከፋፈል የመሬት ኮሚቴዎች በጉቦ አስቸገሩት
ከዛፍ ወደዛፍ ላይ ትዘላለች ጦጣ
መሬትን ያገኘ ኮሚቴን ያጠጣ
ብሎ ዘፈነ፡፡ የሰማው ግን አልነበረም፡፡
ትንሽ ቆይቶ የመንደር ምሥረታ ተባለና የኖረበትን ቀዬ ልቀቅ ተባለ፡፡
ቤቱን አፍርሱ አሉን የበላንበትን
ማፍረስስ አልጋውን ትኋን ያለበትን
ብሎ ዘፈነ፡፡ የሰማው ግን አልነበረም፡፡
ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ልጆችህ ይዝመቱ ተብሎ ወታደር ተመራበት፡፡
ልጅህን አምጣ ይላል የኛ ዘመናይ
እኔ ልጄን ስወልድ አዋልዶኛል ወይ
ብሎ ገጠመ፡፡ የሰማው ግን አልነበረም፡፡
በመጨረሻም ከእንግዲህ ደርግ ጠላታችን ነው፡፡ ለጠላታችን ለደርግ አንገዛም ብሎ ተማማለ፡፡ ነገሩ እየከረረ መሄዱን የሰሙ ካድሬዎች
ወረዱና ሕዝቡን ሰበሰቡት፡፡ ሲነግሩት ዋሉ፡፡ ሲሰማቸው ግን አልዋለም፡፡ ስብሰባው ሲያልቅ ‹ጠላቶቻችን ይውደሙ› ብሎ ካድሬው መፈከር
አሰማ፡፡ ሕዝቡም በአንድ ድምጽ እጁን አውጥቶ ‹ይውደሙ› አለ፡፡ ካድሬዎቹም ደስ ብሏቸው ስብሰባውን በመፈከር አሳርገው ሄዱ፡፡
ለአለቆቻቸው ሕዝቡን አሳምነው እንዳስፎከሩት ተናገሩ፡፡ ሕዝቡ ያለው ሌላ እነርሱ ያዳመጡት ሌላ፡፡
ሕዝብን ማዳመጥ ማለት ሕዝብ የሚለውን
ለማዳመጥ መቻል ነው፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅኔ ሕዝብ ነውና ሕዝቡን ለማዳመጥ ባለቅኔ መንግሥት ያስፈልገዋል፡፡
ሕዝብን የሚያዳምጥ መንግሥት ማዳመጡን
በሚሰጠው ምላሽ ነው የሚገልጠው፡፡ ምላሹ የሚወሰነው ለማዳመጥ በሰጠው ማስተዋል ነው፡፡ የመጣው ከዚህና ከዚያ፣ ከነ እንቶኔና ከነ
እንትና ነው ማለቱን ትቶ ሕዝብ ተናግሯል ብሎ የሚያምን ከሆነ፣ ያንንም ይዞ ከየዓይነቱ ሕዝብ ጋር የሚመክር ከሆነ፡፡ መክሮም መንግሥት
የሚፈልገውን ሳይሆን ሕዝቡ የጠየቀውን የሚመልስ ከሆነ፣ ያ መንግሥት ‹ሕዝብን የሚሰማ መንግሥት› ይባላል፡፡
ሕዝብን የሚሰማ መንግሥት መንግሥትን
የሚሰማ ሕዝብ መፍጠር ይችላል፡፡ ሕዝብ የሚያከብረውን፣ የሚወደውንና ይሰማኛል ብሎ የሚያምነውን መንግሥት ይሰማል፡፡ መደማመጥ የጋራ
ነው፡፡ ሕዝብ ፈጣሪው የሚለውን የሚሰማውኮ ፈጣሪዬ የምለውን ይሰማኛል ብሎ ስለሚያምን ነው፡፡ ፈጣሪ አይሰማኝም ካለማ ፈጣሪውን
መስማት ያቆማል፡፡ ማንም የማያዳምጠውን አያዳምጥም፡፡ ፈጣሪም ‹ኑ እንዋቀስ› ያለው የሚወቀስ ነገር ኖሮት ሳይሆን ሕዝቡን እንደሚያዳምጥ
ሲናገር ነው፡፡
ሕዝብ መንግሥት አያዳምጠኝም ብሎ
ተስፋ ሲቆርጥ ቀስ በቀስ መንግሥትን ማዳመጥ ያቆማል፡፡ መንግሥት የመናገሪያ መሣሪያ ስላለው ብቻ ይናገራል፡፤ ሕዝብም ጆሮ ስላለው
ብቻ ይሰማል፤ ግን አያዳምጥም፡፡ ነገሩን እውነት ነው ብሎ አይቀበለውም፡፡ ለእኔ ነው ብሎ ልብ አይለውም፡፡ አዳምጦም የሚፈለገውን
ምላሽ አይሰጠውም፡፡
አንተ ስትናገር ያልፋል በእኔ ላይ
እኔም ስናገርህ ያልፋል ባንተ ላይ
ከንግዲህ ሆነናል ወንዝና ድንጋይ
የተባለውኮ ያለምክንያት አይደለም፡፡
ወንዝ በድንጋይ ላይ ሲያልፍ ይጮኻል ግን ድንጋዩ አይሰማውም፡፡ ድንጋዩም ውኃው በላዩ ላይ ሲያርፍ ይጮኻል፤ ግን ወንዙ አይሰማውም፡፡
ሕዝብን የማያዳምጥ መንግሥትና እርሱ
የሚፈጥረው መንግሥትን የማያዳምጥ ሕዝብ እንዲህ ናቸው፡፡
Fetari yemiadamet mengest yamtalen kemalet lela men yebalal.
ReplyDeleteበአስደናቂው የዶ/ር መራራ ጉዲና ትንቢታዊ ንግግር ልጀምር፤ "አፍ እንጂ ጆሮ የሌለው መንግሥት" እንዴት ሊያዳምጥ ይችላል፡፡ ቅጥፈት እንጂ እውነት ተፈጥሮው ያልሆነ መንግሥት በእንደዚህ ያለ ምክር ሊቃና አይችልም፡፡ ያንተው፣ የድንጋይና የውሃ ነገር ማጠቃለያ ታላቅ ቃለ ኃይል ነው፡፡ 25 ዓመታት ሙሉ የድንጋይና የውሃ ነገር፡፡ እኔም ላዋጣ ይሆን፣ እብን ዲበ እብን ነቢሮ፡፡
ReplyDeleteተስፋዬ
ውድ ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ። የሚያስተውል ልቦና ቢሰጠን እግዚአብሄር በአንተ አማካኝነት እየመከረና እየገሰፀን ነበር። መሪ ተብየዎቹን የዘረኝነት አባዜ ስላናወዛቸው እያዩ እንዳላዩ እየሰሙ እንዳልሰሙ እንዲሆኑ ማስተዋልን ተነጥቀዋልና። ልክ እንደ ፈርኦን። በመጨረሻም ልክ እንደ ኤርትራ ባህር የኢትዮጵያ ህዝብ ጎርፍ ሆኖ ይጠራርጋቸዋል።
ReplyDeleteኢትዮጵያ መዝ.ዳዊት 68÷31 ተብሎ የተጻፈላት ሀገር ነገር ግን የእግዚአብሔርን ስራ የዋህነት፣ ትህትና፣ ወንድምን አለማበሳጨት፣ ባልንጀራን መውደድ፣ ከሰው ሁሉ ጋር መስማማትትና መፋቀር መስራት ለዘመናት ያልቻለች ሀገር፡፡
ReplyDeleteኢትዮጵያ “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” መዝ.ዳዊት 68÷31 ተብሎ የተጻፈላት ሀገር ነገር ግን የእግዚአብሔርን ስራ የዋህነት፣ ትህትና፣ ወንድምን አለማበሳጨት፣ ባልንጀራን መውደድ፣ ከሰው ሁሉ ጋር መስማማትና መፋቀር መስራት ለዘመናት ያልቻለች ሀገር፡፡
ReplyDeleteኢትዮጵያ “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” መዝ.ዳዊት 68÷31 ተብሎ የተጻፈላት ሀገር ነገር ግን የእግዚአብሔርን ስራ የዋህነት፣ ትህትና፣ ወንድምን አለማበሳጨት፣ ባልንጀራን መውደድ፣ ከሰው ሁሉ ጋር መስማማትና መፋቀር መስራት ለዘመናት ያልቻለች ሀገር፡፡
ReplyDeleteLet God give our government officials the hearts and minds, to see and understand the cry of their people; also God wipe the tears of all the Ethiopians who have been going through this misery. GOD bless our brother Daniel with his peace, health and long life.
ReplyDeleteጋዳፊ ሊጠፍ ሳምንት ቀርቶት ህዝቤ ይወደኛል ይል ነበር በአለም ታሪክ አንባ ግነኖች አንድም ግዜ በሰላም ወርደው ወይም ህዝብ ሰምተው አያቁም ምክንያቱም ህዝብ ምን ችግር እንዳለበት አያውቁትም ከሰው ተገናያተ አያቁም በካድሬ ያማረ ሪፖርት እያነበብ ነው ሲፈርዱ የሚኖሩት 21 አመት ቤተ መንግስት ስር ኖሬ በስትት እንኩአን አንድ ባለስልጣን ሳላይ ከሀገር ወጣሁ
ReplyDeleteGood read Danniye! peace be with you.
ReplyDeleteThanks
ይህ አውሬና አፋኝ፣ጎጠኛና ዘረኛ፣ውሸታምና ከፋፋይ፣ቂመኛና ገዳይ መንግሥት ተብዬ ቡድን ምንም ጥገናዊ ለውጥ አያስፈልገውም፤መፍትሔው ማስወገድ እና ማፈራረስ ብቻ ነው።ልጠግንህ ቢባልስ እንዴት ይሆናል? የሚሰፋበት ቆደ በስብሶና ከርፍቷል እኮ! በውሸት፣በዘረኝነት፣በአድልዎ፣በጥላቻ፣ በመከፋፈል፣በግድያ፣ በማሰር፣ዘር በማጥፋት፣በዘረፋ፣በሙሰኝነት፣በጥቂት ግለሰቦች ፍፁማዊ የበላይነት/Absolute power/ ላይ የተመሰረተን አንድን ከአንድ ሰፈር የተሰበን ቡድን ከዚህ በኋላ መንግሥት ሆኖ እንዲቀጥል መፈለግ ባርነትን አምኖ መቀበል ነው። የነፃነት ፋና በሩቁ እየታየን ስለሆነ፣ ይህን ዘረኛ የበሰበሰ ቡድን በተባበረ ክንዳችን ገፍተን እንጣለው!
ReplyDelete100% agreed!
DeleteJesus teaches us to what extent to forgive for those while they crucifie him on the cross...Daniel always preaches and teaches the right way why you people always turn the subject into hateful and tribal issue ...no body denies their is social political and economical problem but no body can fix those problems by poisonous propogandas like the one you comment.those politicians you demonizing are our brothers and sisters they are born and grow up in the country called Ethiopia and they are part our social psychological entity we are one people
Deleteትዕግስተኛ ሁን እባብ ሊነድፍህ እየመጣ ግን ትዕግስት ብለህ ብትቀመጥ እኔ የለሁበትም።
Deleteየኢትዮጵያ ሕዝብ የሚሰማው ፡ ኢትዮጵያዊ መንግስት ሲኖር ነው!
ReplyDeleteKalehiwot yasemalin !!
ReplyDeleteሕዝብን የሚሰማ መንግሥት መንግሥትን የሚሰማ ሕዝብ መፍጠር ይችላል፡፡ ሕዝብ የሚያከብረውን፣ የሚወደውንና ይሰማኛል ብሎ የሚያምነውን መንግሥት ይሰማል፡፡ መደማመጥ የጋራ ነው፡፡ ሕዝብ ፈጣሪው የሚለውን የሚሰማውኮ ፈጣሪዬ የምለውን ይሰማኛል ብሎ ስለሚያምን ነው፡፡ ፈጣሪ አይሰማኝም ካለማ ፈጣሪውን መስማት ያቆማል፡፡ ማንም የማያዳምጠውን አያዳምጥም፡፡ ፈጣሪም ‹ኑ እንዋቀስ› ያለው የሚወቀስ ነገር ኖሮት ሳይሆን ሕዝቡን እንደሚያዳምጥ ሲናገር ነው፡፡
ReplyDeleteወንድሜ አሁን ኢትዬዽያ የሚባል ነገር አያዋጣም። መጀመሪያ ወያኔ ባጠመደልን መንገድ ተጉዘን የብሔር ሕብረታችንን ማጠንከር የግድ ነዉ። ያለበለዚያ ወያኔ ባፈረሰዉ ኢትዬዽያዊነት አማራዉ ብቻዉን ቢጮህ ዉጤቱ ከሌለች ኢትዬዽያ ጋር አብሮ መጥፋት ነዉ። መጀመሪያ ብሔርተኝነት፡ ልክ እንደ ትግሬወች። ከዚያ በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት። ባሪያ ሁነን መፈቃቀድ የሚባል ነገር የለም፡ አርፎ መገዛት እንጅ። ለነፃነታችን እንሙት!!!
ReplyDeleteWe Christians promote hate. What you just said is suppose to be our life style. As Christians we spreed hate and the God we worship does not teach us to condemn. When we see a problem we are suppose to be a solution to the problem not be part of the problem. We all need to understand what is going on and who is behind all this to paralyze the country. What ever happens it affects all of us, so let us all be bold and spreed our faith. In this last days God is very near and he is giving us the chance to be like him. In Jesus name I love you my brothers and sisters.
ReplyDeleteHello Dn.Daniel! How are you doing? I would like express my personal feelings. You are starting to jam many public comments.You might be faced pressure from TPLF group.Anyways do what do.
ReplyDeleteእኔ ሁሌ አንድ ነገር ሲመጣብኝ ምን አጥፍቼ ይሆን ያለ ነገር እንዲህ አልሆንኩም ወይ እግዚአብሔርን አሳዝኜዋለሁ ወይ እግዚአብሔ4ር ሊያስተምረኝ የፈለገው ነገር አለ ብዬ እፈራለሁ። መጀመሪያ ሁሉም ሰው እንደዚህ ሊያስብ የሚገባው ይመስለኛል። በተለይ እግዚአብሔር ዝም ሲል ያስፈራል የኢትዮጵያን ነገር ሳስበው ሕዝቡ አራዊት በሞላው ጫካ ውስጥ ያለ እየመሰለኝ ነው ምክንያቱም የገዛ የአገሩ ወታደር ወይም ይሻለኝ ይሆናል ብሎ ያወጣው መንግሥት ቋንቋ እንደማይችል፣ እንደማያውቀውና እንደማይሠማ ሆኖ በጥይት ሲቆላው እና በዱላ ሲጨፈጭፈው መሥማት እንኳን እንደማይፈልግ ነው የምረዳው ሲጀመር ያልታዘዘ ወታደር አይተኩስም። እግዚአብሔር ብቻ ነው ታዳጊያችን እንደቸርነቱ ካልማረን እኛም ከዚህ የተሻልን እንሆናለን ብዬ ማሠቡ ይከብደኛል ኃጢያታችንን ይቅር ብሎ ፈርሀ እግዚአብሔር ያለው መንግሥት ይስጠን እንጂ መሠማማት ከቆመማ ቆየ እስኪ የትኝው ኢትዮጵያዊ ቤት ነው ሙሉ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የሚከፈተው? ሁሉም ጣብያውን የሚጠቀመው ለድራማ ነው በገጠመው ዲሽ በሃሳብ ውጭ አገር ነው ያለው ታድያ ለመንግሥት ቢሠማ ባይሠማ ጉዳዩ ነው???!!! አንዴ ተቆናጧል ይሄ መቼም ለኔ የእግዚአብሔርን ኃይል መካድ ነው አይተወንም ከእንቅልፉ እንደነቃ ሆኖ ይነሳል ያኔ ሁሉም ጣቱን ያያል። ብቻ በቸርነቱ ቀኑን ያሳጥርልን አሜን።
ReplyDeleteI am interested to know if Mr. Daniel Kebret is a politician or a follower of Christ? We need to spreed his love and live the life style. We need to talk and to walk as he did to teach us. Christianity is a life style. Jesus Christ died for us and we need to respect the blood of Jesus and we need to understand why he died for us all.
ReplyDeleteDn. Daniel is doing exactly what you mentioned!
Deletedani bzih yemekera zemen ewinetun yeminager agelgay hone siletayeh des bilognale hizibachin eyaleke zim linil anchilim hizibachin bgifegna tiyit eyaleke lyetignaew hizib new agelgay minhonew?? fetari ethiopian khizibocha gar yitebik!!
ReplyDeleteindeed its the right time to promote such important massage for our people specially who live in US,Eurpe,Australia I can say most of them are engaged on promoting hate,division,curse each other based on ethnicity.unfortunately most of them are failed in every perspective of life journey as an immigrant as well as an ethiopian. their is a saying in our country "ene komotku serdo ayibkel alech ahiya" having say this... on the government side you have expressed my comment more professionally .finally I beg you to enlighte and teach more on ethiopian diaspira's it seems to me they are equally stabbing and bleeding their country.
ReplyDeletetnx
ReplyDeleteWonderful message if listers are there!!! What surprising me is that why these leaders are purchasing enemies to their Tigry people???
ReplyDeleteegziabhere yadamiten
ReplyDeleteeziabhere yisman
ReplyDeleteAt anonymous@ 9:32 AM Aug31,2016. በመጀመሪያ ደረጃ ለእውነት ቁም የሰውንም ተሰጥኦና ክብር እወቅ፤እነዚህን ስታደርግ ነው መልዕክትህም ሚዛን የሚደፋው። ዲ/ን የሚለውን እና አቶ የሚለውን ለማን እንደሚሰጥ ተረዳ። ክህነት ከሰማይ እንጅ እንደ ስጦታ እቃ ከሱቅ የምንገዛው አይደለም፤ ወይንም በግልበጣ የሚገኝም አይደለም። አነጋገርህ ማን እንደሆንክ ያሳብቅብሃል፤ ሃይማኖትም ቢሆን ለእውነት መቆምን ያስተምራል እንጂ ከወንጀለኞች እና ከጨቋኞች ጋር እንድንቆም አያዝም። በሃይማኖት ሰበብ እውነትን ለመካድ ሞክረሃል። መፍትሄ ማስቀመጥና እውነትን መናገር ከቶ ቦለቲከኛ(politician) ሊያሰኝ አይችልም። ይቺን ምክርህን ሌላ ካድሬ ሳይቀድምን ለህወሓት ሬዲዮና ቴሌቪችዥን ጣቢያ " እውነትን¡" ሁል ጊዜ ለሚናገሩት ሂድና ምክራቸው።
ReplyDeleteአትግደል።
ReplyDeleteኦሪት ዘጸአት ም፳፥ቁ፲፫
ኢትዮጵያ “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” መዝ.ዳዊት 68÷31 ተብሎ የተጻፈላት ሀገር ነገር ግን የእግዚአብሔርን ስራ የዋህነት፣ ትህትና፣ ወንድምን አለማበሳጨት፣ ባልንጀራን መውደድ፣ ከሰው ሁሉ ጋር መስማማትና መፋቀር መስራት ለዘመናት ያልቻለች ሀገር፡፡
God bless you Dan! You are the only religious guy who can criticize this government in a genuine way though TPLF has no ears and mind: Eye of the eagle!!
ReplyDelete"ሕዝቡንም እረኛ እንደሌላቸው በጎች ሲቅበዘበዙ አይቶ አለቀሰላቸው።" ለእስራኤል ሕዝብና ለኢየሩሳሌም ከተማ አዝኖ ያለቀሰው ፈጣሪ አምላካችን መድኃኔዓለም ስለእናቱ ቅድስት ድንግል እመቤቴ ማርያም ብሎ ለሀገራችንና ወገኖቻችን አዝኖ፥ እራርቶ በርሱ ብቻ የሚመኩ፣ እርሱን የሚፈሩና የሚወዱ አስተዋይ መሪዎችን ይስጠን። አርባ ዓመት በላይ ተቆራኝቶ የሚያሰቃየን ጋኔን ያለጾምና ጸሎት ስለማይወጣ ዐቅም ያላችሁ ሁሉ በርቱ። እመቤታችን ደጓ እናት ኪዳነምሕረት ትርዳን።
ReplyDeleteዘላቂ መፍትሔ የሚገኝ ከወደላይ ብቻ ነው፤ በሰው መታመን በአለቆችም ተስፋ ማድረግ ከንቱ ነው።
አንብበውት ይሆን
ReplyDelete"አዉቆ የተደበቀ ቢጠሩት አቤት አይልም" ይላል ያገሬ ሰዉ: ሆን ብሎ መስማት ያማይፈልግ መንግስት ሊሰማ አዪችልም.....
ReplyDelete"ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ" ነው እኮ ነገሩ
መንግሥት የሚሠማ ሕዝብ በአሁን ሰዓት የለም፡፡ ለምን ቢሉ ኢሣትን የሚሠማ ሕዝብ ስላለ፡፡ እዚህ ያለውን እውነታ ሳይሆን የምንሰማው የርቀት አሉባልታ ወሬ ነው የምንሠማው፡፡ አቤቱ አምላክ ሆይ አንተ የሾምከውን መንግሥት እንዳያከብሩ የሠፈረባቸው አጋንንት በዚህ በአዲስ ዓመት በስምህ እንዲባረር እፀልያለሁ፡፡
ReplyDeleteፀሎቱ ግሩም ነው፡፡ ግን በማን ላይ የሠፈረው በሕዝቡ ወይስ በመሪዎቹ ላይ? ገለጥለጠ አድርገ/ጊዋ አስተያየት ሰጪ
Deleteገለጥለጥ ያለ መሠለኝ፡፡ "አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም" ነገርማ አትሁንብኝ፡፡ መንግሥትንማ የሾመው እግዚአብሔር ነው፡፡ ጥቂት ሕዝብ ግን የመበጥበጥ አባዜ ያለበት አርፌ አልገዛም ስላለ መፀለይ ያለበት ለጥቂቱ ሕዝብ ነው፡፡ መንግሥትን ሊያወርድም ሊሾመውም የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ እምነት ከሌለህ ግን ሀርድ ውስጥ ነህ፡፡ ቻው፡፡
Deleteሂትለርም ሞሶሎኒም ህወሓትም ንግሣቸው ከፈጣሪ ፈቃድ የወጣ አይደለም። ሁሉም ለምክንያት ይመጣል ይሄዳል። በዚህ መሰረት በህወሓት ላይ የሰፈረውን እንዲያርቅልን ነው መጸለይ።
Deleteበተሻለ ደግሞ፣ ራሱን ህወሓትን እንዲያርቅልን፣ ኢትዮጵያዊ መንግሥት፣ ብሔራዊ አንድነትን የታጠቀ፣ ፈጣሪውን የሚፈራ ባለ ህሊና መንግሥ እንዲያመጣ ነው መጸለይ።
PLEASE Ethiopia ppl let us pry pry pry... to give them just
ReplyDeletelittle mind
ጥበበኛ መሪን እግዚአብሄር ያድለን!
ReplyDeleteከዚህ በላይ ጥበበኛ መሪ ከየት ይምጣ፡፡ በኢትዮጵያ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ ብልህ መሪ አሁን ነው ኢትዮጵያ ያገኘችው፡፡ አራት ነጥብ
DeleteI always appreciate your view .
ReplyDeleteIn this week a lot of people's wrriting race,polotics,religous....
Please Dani can you write to face book to add in their mane as"like" to add "dislike" ?
አንተ የት ነህ?
ReplyDeleteውድ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት አንተ የት ነህ?
ምንስ እየሰራህ ነው? የዚች አገርንና ቤተ-ክርስቲያን ተመራማሪ እና መካሪ (በፅሁፎችህም በስብከትህም) አደለህምን? በአንተ አገላለፅ አገርህ ስትንገጫገጭ አንተ የት ነህ? ከፅሁፍ የዘለለ ተግባርህ የታለ?
ዲ/ን ዳንኤል አንተ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ያደረከውን ቃለምልልስ አነበብኩት እናም ይህን ልፅፍልህ ውስጤ አስገደደኝ፡፡ ጠንካራ የሐይማኖት መሪዎች ቢኖሩን ኖሮ እንዲህ አይነቱ ሥጋት ላይ አንወድቅም ነበር ባልከው እኔም እስማማለሁ የሐይማኖት አባቶች (ጳጳሳት፣ ቆሞሳት፣ካህናት፣ዲያቆናት፣ ሸህ …) ቢኖሩን ኑሮ ከዚህ ደረጃ ባልደረስን ብንደርስም መንፈሰ ጠንካሮች፣ ነገን የሚያዩ ልባሞች ሁነን ጥፋቱም በትንሽ መስዋትነት እንዲሆን ባደረግን ነበር፡፡ ከወንጌል ይልቅ ፖለቲካ ፤ ከሰው ሒወት ይልቅ ልማት፤ ከሰማያዊዩ ቤት ይልቅ ምድራዊውን የሚያስቀድሙ አባቶች እያሉን(ሁሉን ማለት ቢከብድም) ከዚህ የባሰ ደረጃ እንካን ብንደርስ የሚገርም አይደለም፡፡ አገር የቆመችው በካህን ፣በወቶአደር፣ እና በንጉስ ነው ይባላል እንዳልከው አሁን አንዱንም አጥተናል፡፡ ሕዝብ ብቻ ያላት አገር ሁናለች ህዝብ ደግሞ ልባም ልጆች ከሌሉት ፍፃሜው መጠፋፋትና መጥፋት ይሆናል፡፡
ከቃለ ምልልሱ መጨረሻ ላይ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ በማዋቀር በኩል የአገር ሽማግሌወች ሀላፊነት አለባቸው ፤ በዚህ ወቅት የአገር ሽማግሌወች ጥያቄ ያላቸውንም ሆነ መንግስትን ለማነጋገር ችግሩን ለመፍታት ፍጠኑ ማለት እፈልጋለሁ ፡፡ መንግስት ከሚሔድበትም ሆነ ህዝብ ከሚሔድበት አቅጣጫ ወጥታችሁ ሶስተኛ ና የተሻለ የመፍትሔ አቅጣጫ ይዛችሁ ቅረቡ የአገራችንን ችግርም ሳይባባስ ለማስተካከል ጣሩ እላለሁ፡፡
ብለሀል በጣም ጥሩ ምክርና ጥሪ ነው ልባም ሽማግሌወች ካሉን፡፡
ግን
"ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን?” እንዳለ ጥልቁ መፅሐፍ አንተ እና በዙሪያህ ያሉት አስተዋይ ሽማግሌ አትሆኑምን? ሽማግሌወቻችን የምትሸመግሉት መቸ ነው? የእኛን ጉዳይ እኛው መሸከም፤ የእኛን ትኩስ ድንች እኛው እጅ ላይ ማቆየት፤ የምንመክረውን መተግበር እንዴት ተሳነን?
ዲ/ን ዳንኤል አንተ እና ባንተ ዙሪያ ያሉት ሽማግሌ መሆን ፣ መፍትሔ ማንጣት መፍትሔው ቢከብድ እንካን ለተጠቂው መቆም በዳዩን ባደባባይ ቆሞ ተው ማለት አትችሉምን? አገራችሁን ለማዳን ጣታችሁን ወደ እራሳችሁ የምትቀስሩት ፣ ከፅሑፍ እና ከመድረክ ስብከት ላለፈ ለሚታይ እና ለሚዳሰስ ተግባር የምትነሱት መቼ ነው?
ባንተ ዙሪያ ትልቁ ማሕበር በወጣቱም በአዛውንቱም በሁሉም ልብ ውስጥ ያለው ማሕበረ ቅዱሳን የለምን? ፍሬስ አላፈራምን?
ከሁሉም ቤተ እምነት ያላችሁ ሰባኪያነ ወንጌል በአንድ ላይ ሁናችሁ ከተበዳይ ፣ ከተጠቂ ጎን በአንድነት የምትቆሙት መቸነው? በተለይ የኦርቶዶከስ ተዋህዶ ሰባኪያን ሰማዕትነትን አትሰብኩንምን? መቼ ነው እንደምታስተምሩን ሰማእታት ከተበዳይ ጎን የምትቆሙት?
በየአመቱ የበጎ ሰው ሽልማት የምትሸልማቸው በጎወችስ የት ገቡ? በጎነታቸው አገር ስትንገጫገጭ አይሰራም? ሽማግሌ በሚያስፈልግበት ወሳኝ ጊዜ በጎነታቸው መሸምገል አይችልም? ከተበዳይ ጎን አይቆምም?
አንተስ በግልህ ከብዙ ደግ ጳጳሳት፣ ቀሳውስት ፣መምሕራን፣ ምሑራን፣ የሌላ እምነት ተከታይ ወንድሞች እና እህቶች(እናትና አባቶች) ጋር አትገናኝምን? መቼ ነው አስተባብረህ ለአገር የምታስነሳቸው ለተበዳይ ይቆሙ ዘንድ የምታስተባብራቸው? መቼም ሕዝብ አስተባባሪ ይፈልጋልና፡፡
ከፅሁፍ እና ስብከት የምታልፈው መቼ ነው?
አገራችን ማንም ማየት በሚችለው ሁኔታ አደጋ ውስጥ ናት፡፡ ነገ ላለመፈራረሷ ዋስትና የለንም ተስፋ የምናደርጋችሁ እናንተ ስትገፋፉ ሽማግሌወቹ ሽማግሌ ቢኖር ኑሮ ስትሉ ማን ይችን አገር ይታደጋት? ዲ/ን ብዙ አስማምቶ መፃፍ አልችልም ግን ከፅሁፍ አልፈህ የተግባር ስራ የምትሰራበት ጊዜ አሁን ነው እላለሁ፡፡ በአካባቢህ(በአገር) ያሉትን ለእውነት ለአገራቸው የሚቆሙ ደግ ሰወችን ተመልከት ከነሱ ጋር ከመፍትሔ ጋር ብቅ በል ጊዜው አሁን ነው፡፡ ከዘገየህ ወይም ጀሮ ዳባ ልበስ ካልህ ታሪክ ነገ አንተንም ትወቅስሀለች፡፡
ቼር ወሬ ያሰማን!
Dear Daniel,
ReplyDeletethank you for this piece. it is timely and appropriate. I wish that God will give our leaders and the people the humility to listen to each other's views and act upon them. Government, by principle, is there to serve people. I think it is time for EPRDF to start listening rather than opting to violence and killings and I believe it is in every body's best interest if they put their guns aside and listen to what the people have to say. we all have to bear in mind that Ethiopia is our country; it is the country of its people. it does not specifically belong to some group and no body can have an eternal claim to it or to anything for that matter.
ጤና ይስጥልኝ ይህድንቅና ብልህ አባባል ነው። ግን ባሁኑ ሰአት በልጅነቱ ያላቃኑት ዛፍ ካደገ በውሀላ ላቃናው ብንል እንደማይሆን ሁሉ ህዝብም ጥርስ ነክሶአል መንግስትም ስንቅ ያለቀበት የበረሀ ተኅዥ ሆኖአል።
ReplyDeleteጤና ይስጥልኝ ይህ ጥሩ ምክር ነው ግን እንዳልከው ሰሚ አጣ እንጅ አሁን መንግስትና ህዝብ ከመሰማማት አልፈው ጥርስ መናከስ የደረሱ መሰለኝ መንግስትም ያገር ውስጥ ቅኝ ገዥ መስሎአል ህዝብም ግፍ በዛብኝ ተናቅኩ ብሎአል ከዛማ ምከረው ምከረው እምቢካለ መከራ ይምከረው ያለፍን ይመስለኝአል።
ReplyDeleteEnde ante yale asteway ena mekari sew bemenoru des bilenem semi ena asteway mengest balemenoru enaznalen.
ReplyDeleteGadafi was killed by NATO and us forces help its undeniable truth.
ReplyDelete