Wednesday, August 17, 2016

የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ታወቁ
click her for pdf
ጋዜጣዊ መግለጫ
ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደውና ለሀገራቸውና ለወገናቸው ላቅ ያለ አገልግሎት የሰጡ ዜጎች የሚከብሩበት የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ በአቤል ሲኒማ አዳራሽ ይከናወናል፡፡ በዕለቱ የክብር እንግዶች፣ ተሸላሚዎች፣ ዕጩዎች፣ ታዋቂ ሰዎችና መገናኛ ብዙኃን  በሚገኙበት ሥነ ሥርዓቱ ይከናወናል፡፡
የበጎ ሰው ሽልማት ኮሚቴ ያለፉትን ሦስት ዝግጅቶች ሂደት ሲያከናውን እንደኖረው ለዚህ ክብር መብቃት አለባቸው የተባሉ ዜጎች በሕዝቡ የተጠቆሙ ሲሆን፤ በየዘርፉ ከተጠቆሙት ዜጎች መካከልም ሥራዎቻቸው ተመዝነው ሦስት ሦስት ዕጩዎች ተለይተዋል፡፡ በእነዚህ እጩዎች ላይ አምስት አምስት ዳኞች (በየዘርፉ) ደምጽ እየሰጡ ነው፡፡ የየዘርፉ ተሸላሚዎችም ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓም በሚካኼደው ሥነ ሥርዓት ይከበራሉ፡፡
መገናኛ ብዙኃንና ሌሎች የመገናኛ አካላት እጩዎችን በማስተዋወቅና በማክበር ለሀገራቸው በጎ የሚሠሩ ዜጎችን ለማብዛት የበኩላቸውን እንዲወጡ እየጠየቅን ዕጩዎቹን በየዘርፋቸው እንደሚከተለው እንገልጣለን፡፡ 1.    መምህርነት
·         ተ/ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው (በአዲስ አበባ ዩኚቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ መምህር)
·         ተ/ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የነበሩ)
·         መ/ር አውራሪስ ተገኝ (ምሥራቅ ጎጃም፣ ቢቡኝ ወረዳ የሚገኙ፤ በዘውዴ ልየው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር)
2.   ንግድና ሥራ ፈጠራ
·         አቶ ብዙአየሁ ታደለ (የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግስ ባለቤት)
·         አቶ ሳሙኤል ታፈሰ (የሰንሻይን ሪል እስቴት ባለቤት)
·         አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ (የኅብረት ኢንሹራንስ ኩባንያ መሥራች)
3.   ማኅበራዊ ጥናት
·         ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ (የግእዝ መዛግብትን በማጥናት የታወቁ ሊቅ)
·         ዶክተር አንዳርጋቸው ጥሩነህ (በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የታሪክ ምሁር)
·         ፕሮፌሰር ባየ ይማም (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልሳን ሊቅ)
4.   ሳይንስ
·         ሎሬት ዶክተር መላኩ ወረደ (በኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ላይ የሠሩ ሳይንቲስት)
·         ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ (በኢትዮጵያ ሥነ ምኅዳር  ላይ የሠሩ ሊቅ)
·         ዶክተር ወንዱ ዓለማየሁ (የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ እንዲቋቋም ታላቁን ሥራ ሠሩና፣ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ቤ ት ለቤት በመጓዝ የብዙዎችን ዓይን ያበሩ ሳይንቲስት)
5.   ቅርስና ባህል
·         የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ)
·         ኢንጅነር ታደለ ብጡል (የአኩስምን ሐውልት በማስመለስ፣ የኢትዮጵያን ቅርሶች በማስተዋወቅና የታላላቅ ሰዎችን ታሪክ በመመዝገብ የታወቁ ምሁር)
·         መ/ር ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር (የኢትዮጵያን ቃላዊ ቅርሶች የሚሰበስቡ ሊቅ)
6.   መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት
·         ኢንጅነር ዘውዴ ተክሉ (የአዲስ አበባን ከተማ ካስተዳደሩትና ለውጥ ካመጡት ከንቲባዎች አንዱ)
·         ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር (የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንን ለብዙ ዓመታት የመሩ የአካባቢ ሳይንስ ሊቅ)
·         ዳኛ ስንታየሁ ዘለቀ (በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የኮንስትራክሽን ችሎት የሚያገለግሉ ዳኛ)
7.   ስፖርት
·         አቶ ጌቱ በቀለ (በሰበታ አካባቢ ስፖርትን ለማሳደግ የሠሩ ሰው)
·         ጋቶች ፓኖ (ከጋምቤላ ክልል ለብሔራዊ ቡድን የተመረጠ የቡና ክለብ የእግር ኳስ ተጨዋች)
·         ዶክተር ይልማ በርታ (የአትሌቲክስ ስፖርት አሠልጣኝ)
8.   ኪነ ጥበብ (ድርሰት)
·         አቶ አስፋው ዳምጤ (የሥነ ጽሑፍ ሰው፣ ሐያሲና ደራሲ)
·         ወ/ሮ ፀሐይ መላኩ (ሴት የረዥም ልቦለድ ደራሲ)
·         አቶ አውግቸው ተረፈ (የአጫጭር ልቦለዶች ደራሲና ተርጓሚ)
9.   ሚዲያና ጋዜጠኛነት
·          መንሱር አብዱል ቀኒ (የስፖርት ጋዜጠኛ)
·         አቶ አጥናፍ ሰገድ ይልማ (በኢትዮጵያ የኅትመት ሚዲያ ላይ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ አንጋፋ ጋዜጠኛ)
·         አቶ ደረጀ ኃይሌ (በቃለ መጠይቅ ጥበቡ የሚታወቅ ጋዜጠኛ)
10.  በጎ አድራጎት
·         ዶክተር ቦጋለች ገብሬ (የከምባቲ መንቲ ገዚማ-ቶፔ ‹የከምባታ ሴቶች አንድ ላይ ተነሥተዋል› የተሰኘው ድርጅት መሥራችና በከማባታ ሴቶች ሕይወት ላይ ለውጥ ያመጡ ሴት)
·         ወ/ሮ ፀሐይ ሮቺሊ (የሰላም ሕጻናት ማሳደጊያ መንደር መሥራች)
·         ወ/ሮ ዘውዲቱ መሸሻ (ሕይወት የሕጻናትና ቤተሰብ መርጃ ድርጅት መሥራች)

8 comments:

 1. ኪነጥበብ ሽልማቱ ለዳንኤል ክብረት ይገባ ነበር

  ReplyDelete
 2. Dear Daniel

  Greeting and bless for you!

  I always admire you. you are special for this nation. But I have one question in relation to the selection criteria. Almost all of the above stated personalities are known in Ethiopia either due to media coverage or other reason. then how could you select/address those who do not promoted in media and have done good work for their locality. Please think on collecting information from different cities atleast from (hawassa,adama,Diredawa,bahrdar,mekele moyale,jinka.............)

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Tiruneh,
   Until Daniel replies,
   I don't think you are right in saying that the list includes only those who are known through the media. For example, I have never heard of መ/ር አውራሪስ ተገኝ and even some who are in the other categories.
   In any case,

   here is how it works. You can campaign for a nomination of people who you think deserve to be included. There is a process that is announced in the print and electronic media ahead of time. Perhaps there is also a website.

   Delete
 3. በእርግጥ እነዚህ ግለሰቦች ማስታወስና ማበረታታት ከፍተኛ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ በተፈጥሮ (ከኢትዮጵያዊነት) የተማርነውን በጎነት ለማዳበር ብዙ ስራ አልሰራንም ነበር፡፡ በጎነታችንና መተሳሰባችን ጥንካሬውን ይዞ እንዳይቀጥል የ21ኛው ክ/ዘመን እየተፈታተነው መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ይህ ዝግጅት የጎላ በጎነትን የሰሩ ግለሰቦችን ሲያበረታታ ሌሎችን ማስተማሩና ማነሳሳቱ አይቀርም፡፡ መልካም ጅምር ነው፡፡ ነገር ግን ለቀጣይ እጅግ ውጤታማ ከሆኑት ግለሰቦች ጎን ለጎን ለወጤት በጅምር ላይ ያሉትን ወጣቶችን ቢያካትት ጥሩ ነው እላለሁ፡፡ ዲ/ን ዳንኤልን ለዚህ ጅምር በጣም አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
 4. በእርግጥ እነዚህ ግለሰቦች ማስታወስና ማበረታታት ከፍተኛ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ በተፈጥሮ (ከኢትዮጵያዊነት) የተማርነውን በጎነት ለማዳበር ብዙ ስራ አልሰራንም ነበር፡፡ በጎነታችንና መተሳሰባችን ጥንካሬውን ይዞ እንዳይቀጥል የ21ኛው ክ/ዘመን እየተፈታተነው መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ይህ ዝግጅት የጎላ በጎነትን የሰሩ ግለሰቦችን ሲያበረታታ ሌሎችን ማስተማሩና ማነሳሳቱ አይቀርም፡፡ መልካም ጅምር ነው፡፡ ነገር ግን ለቀጣይ እጅግ ውጤታማ ከሆኑት ግለሰቦች ጎን ለጎን ለወጤት በጅምር ላይ ያሉትን ወጣቶችን ቢያካትት ጥሩ ነው እላለሁ፡፡ ዲ/ን ዳንኤልን ለዚህ ጅምር በጣም አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
 5. Sports potential candidates: Adane Girma, Salhadine said are missing

  ReplyDelete
 6. ለእኔ፤ የበጎ ሰው ሽልማት ከሚሸልማቸው ሰዎች ባለፈ፤ ኃሳቡ መጀመሩ በራሱ በጣም ጥሩ ነው፡እላለሁ፡፡ ለእኛ የበጎነት ምሳሌ የሚሆኑ ከውጭ አለም በላቀ ደረጃ ኢትዮጲያዊያን ናቸው፡፡ ምክንያቱ በጎ እንዳናደርግ ምክንያት ማግኘት ስለማንችል ነው፡፡ በጎ የሆኑ ኢትዮጲያን እንደሌሎቻችን ያሉት በተመሳሳይ ነባራዊ ሁኔታ ስለሆነ በጎ እንዳንሆን ምክንያት መጥቀስ ያቅተኛል፡፡ በጥቆማው ላይ በርካታ ሰዎች የምንሳተፍ ከሆነ ፍትሀዊ የሆነ፤ምርጫና ጥቆማ ማድረግ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ፍትሀዊ የሆነ የበጎ ሰው ተሸላሚን ማግኘት የምንችለው ጠቋሚዎቹ ናቸው እንጂ ዳኞች እና የበጎ ሰው ሽልማት ሃሳብ አመንጭዎች አይደሉም፡፡ ለእኔ አንዳድ እጩዎች ስማቸውን እንኳ ሰምቸው የማላውቃቸው ስላሉ ጥቆማው በሚዲያን ብቻ የሚታወቁ ሰዎችን ብቻ አይደለም ያካተተው፡፡

  ReplyDelete