Monday, August 15, 2016

ሕመም አንድም ለትምህርት አንድም ለሞት

ጥንታውያን የአብነት ሊቃውንት ‹ሕመም አንድም ለትምህርት አንድም ለሞት ነው› ይላሉ፡፡ መታመሙን ላወቀ፣ መድኃኒቱን ለፈለገ፣ መድኃኒቱንም በትክክል ለወሰደ፣ ወስዶም ለዳነ ሰው ሕመም ለትምህርት ይሆነዋል፡፡ ሦስት ነገር ይማርበታልና፡፡ አንድም ዳግመኛ እንዳይዘው ጥንቃቄን፣ አንድም ቢይዘው ሊትርፍ የሚችልበትን መፍትሔን፣ አንድም ደግሞ ለሌላው የሚመክረው ልምድን ያተርፋል፡፡ ያለበለዚያ ግን የሕመም መጨረሻው ሞት ነውና ላንዱ ትምህርት የሆነው በሽታ ሌላውን ይገድለዋል፡፡
አሁን ታመናል፡፡ ሕዝቡ የሚያነሣው ጥያቄ፣ መንግሥት የሚሰጠው ምላሽ፣ የሃይማኖት ‹አባቶች› የሚያወጡት መግለጫ፣ ማኅበራዊ ሚዲያው ከግራ ከቀኝ የሚያናፍሰው ነገር፣ ደጋፊና ተቃዋሚው ከወዲህ ወዲያ የሚሠናዘረው ዱላ ሕመም ላይ መሆናችንን የሚገልጥ ነው፡፡ አሁን የሚያስፈልገን መታመሙን የሚያምን፣ መድኃኒቱን የሚፈልግና መድኃኒቱንም በተገቢው ሁኔታ የሚወስድ መንግሥትና ሕዝብ ነው፡፡
መጀመሪያ መተማመን የሚያስፈልገው ‹ችግር አለ ወይ?› የሚለው ላይ ነው፡፡ አዎን ችግር አለ፡፡ እየሆኑ ያሉት ነገሮች የሚነግሩን ችግር መኖሩን ነው፡፡ ችግሩ እነ እንትና ያነሣሡት፣ የቀሰቀሱት፣ ያደራጁት ምናምን ማለታችን ችግር መኖሩን አያስቀረውም፡፡ በሀገራችን ‹የጥያቄ ክፉ የለውም፤ የመልስ እንጂ›  ይባላል፡፡ የጥቂቶች ወይም የብዙዎች፣ የእነ አንቶኔ ወይም የነ እንትና መሆኑ ጥያቄውን አይለውጠውም፡፡ ለውጥ የሚያመጣው ለጥያቄው ተገቢውን መልስ መስጠቱ ነው፡፡ ‹በቅርቡ ያልመለሰ እረኛ በሩቁ ሲባዝን ይውላል› እንደሚባለው በየጊዜው ተገቢ መልስ ሳይሰጣቸው፣ ወይም ደግሞ ይዋሉ ይደሩ እየተባሉ፤ ያለበለዚያም የተፈቱ የመሰሉ ነገሮች እንደገና እያመረቀዙ መሆናቸው እየታየ ነው፡፡ በሽታው ምንድን ነው? ይኼ የምር የሆነ ውይይትና መግባባት የሚጠይቅ ነው፡፡ ለፖለቲካ ፍጆታ ወይም ለፕሮፓጋንዳ ወይም ለጊዜያዊ ድል ወይም የመሥዋዕት በግ ፍለጋ ወይም ለዶክመንተሪ ፊልም ወይም ደግሞ ለቁጣ ማብረጃ ከሚሆን ወይይት፣ መግለጫና ንግግር ያለፈ ሁሉን ዐቀፍ፣ ለመፍትሔ ብቻ የቆመና በእውነት የሚደረግን ውይይት የሚጠይቅ፡፡ አንድ ዓይነት ሰዎች ተሰብስበው አንድ ዓይነት ንግግር የሚናገሩበት ሳይሆን ልዩ ልዩ ፍላጎቶችን፣ ወገኖችን፣ አቋሞችንና የመፍትሔ ሐሳቦችን የሚወክሉ ወገኖች ለአንዲት ሀገር ሲባል ሁሉን ዐቀፍ፣ ግን የምር የሆነ፣ ምናልባትም አንዳንዶቻችንን ሊመረን የሚችል መድኀኒት የሚፈልጉበት ውይይት ነው፡፡  በተለመደው መንገድ መጓዛችንን ትተን አዲስ መድኃኒት በአዲስ መንገድ እንፈልግ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ እየተጓዘ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ ሞኝ ብቻ ነውና፡፡
ከያቅጣጫው የሚሰጡ መግለጫዎች ሆድ ለባሰው ማጭድ የሚያውሱ፣ ከሚያረጋጉ ይልቅ የሚያናድዱ፣ ከሚያስታግሡ ይልቅ የሚያባብሱ፣ ከሚመክሩ ይልቅ የሚያነዝሩ ናቸው፡፡ ራሳቸው ችግር ናቸው እንጂ ችግር የሚፈቱ አይደሉም፡፡ ሌላው ቀርቶ የሃይማኖት አባቶች እንኳን የሚናገሩት ነገር ሃይማኖት ሃይማኖት የሚል አይደለም፡፡
አሁን የሚታየው የመሥዋዕት በግ ፍለጋ ነው፡፡ ማዶ ያሉትን አካላት የችግሩ መነሻና መድረሻ ማድረጉ መፍትሔ አያመጣም፡፡ እንዲያውም ጥያቄ ይፈጥራል፡፡ እዚህ አብረውት ከሚኖሩት የመንግሥት አካላት ይልቅ ማዶ ያሉትን ለምን ሰማ? እነዚያስ እዚህ ገብተው ሕዝብ እስኪቀሰቅሱ ድረስ እንዴት ዐቅም አገኙ? ሰው ውጭ ውጭ የሚያየው ቤቱ ምን ሲሆንበት ነው? መልሶ መላልሶ ችግሩ እዚሁ ነው የሚሆነው፡፡ የሚያዋጣው ወደገደለው መግባት ነው፡፡ ወደ ችግሩ፡፡
ቀጥሎ የሚነሣው ድግሞ ‹መድኃኒቱስ ምንድን ነው?› የሚለው ነው፡፡ ሁሉንም ወገኖች የሚወክለውና ለሀገሪቱ ሁነኛ መድኃኒት ለመፈለግ የሚደረገው የምር ውይይት ነው መድኃኒቱን ሊያመጣው የሚችለው፡፡ ከአንድ አቅጣጫ የሚመጣ መድኃኒት የሚያድንበት ጊዜ አብቅቷል፡፡ አሁን ሁሉን አግባብቶ ሁሉንም ሊያድን የሚችል መድኃኒት የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ በዚህ ሂደት የሚፈራም የሚናቅም መኖር የለበትም፡፡ የሚገለል የሚጣልም መኖር የለበትም፡፡ መድኃኒት አንዳንድ ጊዜ የሚያስፈልግ እንጂ የሚፈለግ ላይሆን ይችላል፡፡ የሚያድን እንጂ የሚወደድ ላይሆን ይችላል፡፡ መድኃኒት ፍለጋው ይህንን ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡ በዚህ ሂደት ልናድናት ቆርጠን መነሣት ያለብን ኢትዮጵያን ነው፡፡ ሥርዓቶች፣ ፖሊሲዎች፣ አደረጃጀቶች፣ አወቃቀሮች፣ ሊቀየሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ ከጠላትነት ወደ ተነጋጋሪነት፣ ከአጥር ወደ ድልድይ፣ ከተጻራሪነት ወደ ተደጋጋፊነት መምጣት ያስፈልግ ይሆናል፡፡
በተበታተነ ሁኔታ በየአካባቢው የሚነዱትን እሳቶች ለማጥፋት ከመሯሯጥ ይልቅ ልብን ሰብሰብ አድርጎ የማያዳግም መፍትሔ መስጠቱ ነው የሚሻለው፡፡ በተለይም መንግሥት ይህ ይጠበቅበታል፡፡ እየሮጡ መስማት እየሮጡ መርሳትን ያመጣልና ቆም ብሎ ሰምቶ ቆም ብሎ መፍትሔ መስጠት ነው ብልሃቱ፡፡ 
ኮሶ ሲያሽር እየመረረ ነው፡፡ ወይ ሁላችን አናሸንፋለን፤ አለያም ሁላችንም እንሸነፋለን፡፡ ወይ ሁላችንም ለሕመሙ ትክክለኛውን መድኃኒት አግኝተን ተምረን እንድናለን፤ አለያም መድኃኒቱን አጥተን ሞተን እናርፋለን፡፡ ምርጫው ሁለት ነው፡፡ ሕመም አንድም ለትምህርት አንድም ለሞት ነውና፡፡
‹ሕመምተኛ ሲሻለው የዳነ ይመስለዋል፤ ሕመምተኛ ሲያቃዠው የሞተ ይመስለዋል› ይባላል፡፡ አንድ ነገር በትክክል መነሻው ሳይታወቅ፣ ችግሩም ሳይፈታ፣ በራሱ ጊዜ ጋብ አለ ማለት ሕመሙ ዳነ ማለት አይደለም፡፡ ብርድ እንዳገኘ የጉንፋን ቫይረስ ሁኔታው ሲመቻችለት እንደገና ይነሣል፡፡ ሕመምተኛው ሲሻለው የዳነ እየመሰለን ከምንተወው በሚገባ ሕመሙን መርምረን ተገቢውን መድኃኒት መስጠቱ የተሻለ ነው፡፡ ዛሬ የተነሡት ነገሮች ጋብ ቢሉ እንኳን ባንድ በኩል ጥለውት የሚያልፉት ጠባሳ፣ በሌላ በኩል በትክክል ባለመፈታታቸው ምክንያት በባሰ ሁኔታ ዳግም መነሣታቸው አይቀሬ ነው፡፡ እንደምናየው ከሆነ በሀገሪቱ የሚከሰቱ ለውጦች የሰውን አስተሳሰብ፣ አነዋወር፣ መስተጋብርና አሰላለፍ እየለወጡት ነው፡፡ ዛሬ እንደትናንቱ የሆነ የለም፡፡ ነገም እንደዛሬ የሚሆን አይገኝም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ‹በሽተኛ ሲያቃዠው የሞተ ይመስለዋል› እንደተባለው ሀገሪቱ ያለቀላት የሚመስላቸው ወገኖች የሀገሪቱን ታሪክ የማያውቁ ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ የባሰ ችግርና መከራ፣ ከዚህ የባሰ ውጥንቅጥና ፈተና አሳልፋ የምትኖር ሀገር ናት፡፡ አሳልፋ የማታልፍ ሀገር ናት፡፡ በየዘመኑ ከሕመማቸው መማር ያልቻሉ መንግሥታትና ኃይላት አልፈዋል፡፡ ኢትዮጵያ ግን አሁንም አለች፡፡
ሕመሙን ከማባባስ፣ በሕመሙ ለማትረፍም ከመሮጥ፣ ሕመሙን በትክክል አክመን ከሕመሙ እኛው ተምረን እንውጣ፡፡ ካልሆነ ግን ሞተን ለሌሎች የታሪክ መማሪያ እንሆናለን፡፡      

22 comments:

 1. Diakon Daniel Egziaber yibarkeh lib yalew leb yibel

  ReplyDelete
 2. ሕመሙን ከማባባስ፣ በሕመሙ ለማትረፍም ከመሮጥ፣ ሕመሙን በትክክል አክመን ከሕመሙ እኛው ተምረን እንውጣ፡፡

  ReplyDelete
 3. እግዜር ይባርክህ:: ልቤ ያለዉን ነዉ የፃፍኸዉ::

  ReplyDelete
 4. ኢትዮጵያውያን በሙሉ ብዙ ከማውራት ወደሰማዩ አምላክ እጃችንን መዘርጋት የኢትዮጵያ መፍትሄ ከፈጣሪ ነው እና ባለስልጣናቱንም የጋረደባቸውን ያለማስተዋልና ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱን ትተው በትህትና ተሸንፎ ህዝብን አንድ የማድረግ ጥብብን ያድላቸው ፡፡የሁላችንንም መጨረሻ የኢትዮጵያ አምላክ ያሳምርልን፡፡

  ReplyDelete
 5. Nothing to be added. May The Almighty God make all involved to think this way & save our nation & people.

  ReplyDelete
 6. ወንድም ዳንኤል፤

  ቤንዚን በማርከፍከፍ ቃጠሎውን ያጠፋ እየመሰለው ለሚያባብሰው፤ ትኩሳቱ ጋብ ያለ ሲመስለው በድንፋታ አዋራውን ለሚያጨሰው፤ እሳቱ ተመልሶ ሲቀጣጠል ልምምጥ አይሉት ልመና፣ ይቅርታ አይሉት ተጠያቂነት በመግለጫ ጋጋታ ለሚልፈሰፈሰው መንግሥት ተብዬ ጥሩ ምክር ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ በጫጫታው መካከል እኩይ ተግባር ለመፈጸም ለሚርመጠመጡትም፤ ግርግርም ለሌባ ያመቻል በሚለው ብሂል ኢትዮጵያን እነርሱ በሚፈልጉት ቁመትና ወርድ ለመስፋት ለሚራወጡትም፤ የረዥሙን የኢትዮጵያን የመከራ ዘመን ትርክት ጠቅሰህ መናገርህም በጣም ተገቢ ነው፡፡
  በሊደርሺፕ አስተምህሮ አዎ-አሉ የሚባል ውሳኔ ሰጪነት አለ፡፡ በእንግሊዝኛው consequential decision making የሚሉት ነው፡፡ በዚህ ስትራቴጂካዊ አመራር ሰጪነት ቦታ ላይ የተቀመጠ ሰው የጠለቀ እውቀት፣ልምድና ኃላፊነትን በማጣመር የበሰለ መሪ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ የዚህ ምክንያቱም እርሱ የሚሰጠው ውሣኔ ውጤቱ አዎንታዊም ይሁን አሉታዊ የሚገለጠው በረዥም ዓመታት ውስጥ ነውና፡፡ ምናልባትም ሃያና ሠላሳ ዓመታት ከዚያም በላይ ይጠይቅ ይሆናል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የአንድን ከባቢ (environment) መሠረታዊ ይዘት ሊቀይር የሚችል ውሳኔ አሰጣጥ ምንያህል ጥንቃቄ እንደሚጠይቅ አገራችን ኢትዮጵያ የገባችበት ቅርቃር ከበቂ በላይ ምስክር ነው፡፡
  ሕወሃት ደርግን ለመጣል ከታገለው በላይ ራሱን ሲያሞኝበት የመጣውን ታላቅ ሪፐብሊክ የመተግበር ደካማ አስተሳሰብ ከነባራዊው እውነታ ጋር አመሳክሮ እርማት ሳያደርግ፤ ራስን ነጥሎ መውጣት እንደማይቻል ብቻ ተገንዝቦ የቀጠለበት መንገድ የት እንዳደረሰን እያየነው ነው፡፡ ውስጥ ውስጡን ሲብላላ፣ ሲፈላ የቆየው እሳተ ገሞራ በጥቂቱ በየቦታው እየተነፈሰ መታየቱ ይመጣ ዘንድ ያለው የከፍተኛው ፍንዳታ መገለጫ እንጂ መጨረሻው አለመሆኑ ሊሠመርበት ይገባል፡፡
  የባለ ራእዩ መሪ ስትራቴጂካዊ መሪነት ብቃት ርቃኑን የቀረበት፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የመንግሥቱን አመራር ከሚዘውሩት ስብስቦች በላቀ ደረጃ፤ ዘላቂውን ማሰብ የሚችሉና፣ እያደረጉትም የኖሩ ሕዝቦች መሆኑን በግልጽ ያስመሰከሩበት የቅርብ ታሪክ ቢኖር ያለፉት ሦስት ሳምንታት ናቸው፡፡ በሕዝቦቹ ስነ ልቡና ውስጥ ቅቡልነትን ያላተረፈ፣ ለሕዝቦች ብልጽግናና መስተጋብር ነጽሮተ አመራር የሌለው ቡድን እንኳን መጻኢውን አሁን የተሸነቆረውንም ቀዳዳ ተቀባይነት ባለው መንገድ ለመድፈን የሚችል አይደለም፡፡
  በቆረጡት ጨንገር ቢመቱ
  በቆጠሩት ምስክር ቢረቱ
  አሁን የማን ይሆን ጠፋቱ?
  የሚለውን ብሂል እንዳስታውስ ያደረገኝ የአቶ ጌታቸው ረዳ “የጭድና የእሳት” ገለጻ ነው፡፡ ሌ. ጀኔራል ጻድቃን ችግሩ ሥርዓታዊ ነው (systemic) ብለው በጥቅል ያስቀመጡትን አቶ ጌታቸው በዝርዝር አቀረቡት፡፡ የመንግሥት የአመራር ማጠንጠኛ ምሕዋሩ ከፋፍለህ ግዛ፣ በታሪክ ጠባሳ መናቆሩን አብዛ መሆኑን በግልጽ አስረድተውናል፡፡ ይህን አስተሳሰብ ከሚያራምድ አመራር ለሕመማችን ፍቱን መድኃኒት ይገኛል ብሎ መጠበቅ ይቻላል? ተገቢነቱስ? እንጃ ብቻ…

  ተስፋዬ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዳኒ ተባረክ!

   እዛው እንጅ ዘመኑ የሚጠይቀውን አይደሉም !
   የሃገሬ ልጆች በመጀመሪያ ሰሞኑን የደረሰብንን ሃዘን አንድ ቀን እግዚአብሔር በጊዜውና በቃሉ እንደሚመልስልን አልጠራጠርም፡፡ የወላጆቻችንንም አንጀት እግዚአብሄር ያፅናልን፡፡ ከዚህ በኋላ ለምናደርገው ነገር ሁሉ በማስተዋል ብንቀሳቀስ መልካም ነው፡፡ እኔ የሰሞኑን ድርጊት በምመለከትበት ወቅት ከዚህ በፊት ለመንግስት ያለኝን አመለካከት ወደተለየ አቅጣጫ ወስዶብኛል፡፡ በነገራችን ላይ ፖለቲከኛ አይደለሁም፡፡ የምመለከታቸው ነገሮች ግን ለምን እስከዛሬ ድረስ ሲነገሩ የነበሩና የተሳሳቱ ናቸው ብየ የማስባቸውን ለማንበብ ሞከርኩ፡፡ ለንባቤ መነሻ የነበረው ሃሳብ "አንድ ቡድን ሃሳቡ ምንም ይሁን ምን መሳሪያ ይዞ እንኳን ሰልፍ ሲወጣ ጥይት አይተኮስበትም ሌላው ደግሞ ባዶ እጁን ሲወጣ ይተኮስበታል ይሞታል፡፡"በዚያ ላይ በቴሌቪዥን ህጋዊ ስድብ ማለት እንችላለን ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሳይቀሩ "ትምክህተኞች" "ጠባቦች" ምናምን እያሉ አሁን እሳቸውን አቅፎ የያዛቸው ቡድን የሚሳደበውን ለዚያውም እንደገፅታ ግንባታ አድረገው በመውሰድ ለውጭ ዲያስፖራ ተብየዎች እየደገሙልን ስመለከት፡፡ ሳምንት ሳይሞላው ደግሞ ህገ ወጥ ሰልፍ በሚል በጥይት ህዝቡን ሲያስቆሉት፡፡ እነዚህ ሰዎች መነሻቸው ለዲሞክራሲና ለነፃነት ሳይሆን ለበቀልና ሃገሪቷን ለማፈራረስ እንደሆነ እየገባኝ መጣ፡፡ ወደ ኋላ ዘወር ብየ በ1968 ዓ.ም የፃፉትን ማንፌስቶ ለማንበብ ሞከርኩ፡፡ በዚህ አጋጣሚ እናንተም ብታነቡት እና ባለፉት 25 አመታት እየተጋጓዝን የመጣንበትን መንገድና አሁን በሃገራችን ውስጥ እየሆነ ያለውን ለመገምገም ያስችላል ብየ አስባለሁ፡፡ በርግጥ እውነቱን ለመናገር የተፃፈበት አማርኛ የዚያን ጊዜ የፖለቲካና ባህል ተከትሎ ስለሆነ አንዳንዶቹን ሃሳቦች በትክክል ለመረዳት ከብደውኛል፡፡ለምን ወደ 1968 ተመለስክ የተሻሻለውንና ልክ እንደ ኢትዮጵያዊ እያሰቡ የመጡበትን አታነበውም ? ካላችሁኝ መልሴ ፡ በልጅነት አዕምሮየ ቢሆንም ሲወሩ የሰማኋቸው እና አሁን እየተራመዱ ያሉ ሃሳቦችን ስመለከት እነዚህ መሪዎቻችን እዚው እንደሆኑ ተረዳሁና የመጀመሪያ ሃሳባቸውን አነበብኩት፡፡ ወገን እውነትም አዲሲቷ ኢትዮጵያ፡ ዲሞክራሲ፡ እኩልነት፡ ህዳሴ ወዘተ የሚሏቸው ሃሳቦች ማደናገሪያ ናቸው፡፡ የሚገርመው መሪዎቻችን አሁንም እንደዚያዉ እንደ 1968 ማንፌስቶዎቻቸው ናቸው ፡፡ በነገራችን ላይ ለአማራዉ ወንድሜ የሚሰማኝን ያክል ለኦሮሞው ወንድሜም ይሰማኛል፡፡ለትግሬው ወንድሜ የሚሰማኝን ለኮንሶው ወንድሜም እንደዚያው፡፡ ነገር ግን አሁን እንደምንረዳው ግን ትግሬው ወንድሜ ለሌሎች ወንድሞቹ ምንም ስሜት እንደሌለው እረዳለሁ፡፡ ምክንያቱም ምንም እንኳን የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረን ጭቆናን ከትገሬ በልጨ እንደማላውቀው እርገጠኛ ነኝ፡፡ ስለዚህ እኔ እሱን ብሆን ግን በምገልፅበት መንገድ የወንድሞቻችንን ደም መፍሰስ አወግዝ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ሰብአዊነት ብቻ ሳይሆን ነግ በኔም ነው፡፡ ለምን ? ጊዜ ፈራጅ ፡ ጊዜ ዳኛ፡ ጊዜ አዋራጅ፡ ጊዜ አክባሪ፡ ጊዜ አዳኝ ፡ ጊዜ ገዳይ ፡ ጊዜ ሁሉንም ስለሆነ፡፡ የጊዜ ባለቤት እግዚአብሄር ግን ሁሉንም በጊዜው ያደርጋል ፡፡ በቀልን አናስብም ለደም አፍሳሾቻችን እንኳን ቢሆን እርሱ በመልካም ነገር ይመልስልን እንጅ በኛ ሊሆን የማንፈልገውን በእነርሱ አይሁንባቸው፡፡
   ለማንኛውም መፍትሄው
   • የመንግስት ባለስልጣናትም ባለ ጊዜ ናችሁ እና በቀልን አናስብ ፤ ቆም ብለን እናስብ፡፡ ዛሬ ታግላችሁ ያመጣችሁት ዲሞክራሲም በሉት ፤ልማትም በሉት ፤ ከፈለጋችሁም ሙስናም ዘረኝነትም በሉት፤እንደፈለጋችሁ መሳደብም በሉት፤ መጨቆንም በሉት፤ ሁሉም የዚህ አለም ከንቱ ስራዎች ናቸውና አስቡበት፡፡ልብ በሉ ዛሬ ከናንተ ባለጊዜዎቹ ጋር የሚያሸረግዱት ምዕራባውያን ለዜጊቻቸው ገና ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ያስባሉ፡፡ እናም እናንተን መጠቀሚያ ያደርጓችኋል፡፡
   • ህዝብም የምናደርገውን ነገር ሁሉ በጥበብና በማስተዋል እንጅ በስሜት ባይሆን ለዚህም እናንብ ፤ ስልታዊ እንሁን ፤ እንተማመን ፤በተቻለን መጠን አንድ እንሁን፤ ምክንያታዊ እንሁን፡ካመንንበት ላመንንበት እንሙት ፤ በማይረባ ነገር ወንድማችንን አንክሰስ፤ እራሳችንን እንይ፤ ነግ በኔ እንበል፤ ሌሎችን አንጠብቅ፤የመረጃ ሰው እንሁን፤ ህገወጥ ሰዎችን ላለው ህግ እናቅርብ ፤ ህጉ ጥርስ አላባ ከሆነ እንሞግተው፤ አሻፈረኝ ካለ በሌላ ላይ ሳይሆን በተዋናይዎቹ ላይ እርምጃ እንውሰድ፤
   • የፖለቲካ ፓርቲዎችም ፃፉ፡ አስተምሩ፡ ልክ ከነሱ የተሻለ ማንፌስቶ ይኑራችሁ፡ህዝብን መነገጃ አታድርጉ ፡ የአሰራር ግድፈቶችን በግልፅ ተቹ፡ ለሰራችሁት ጥሩ ነገር ታሰሩ ፡ ሞትም ቢሆን ሙቱ ስራችሁ ከመቃብር በላይ ይሆናል፡እኛም እንደዚሁ እናድርግ ፡ እንጅ እንደክረምት አግባ ነፍሳት ምርጫ ሲመጣ ብቻ አትውጡ፡ ተመልከቱ ለምርጫ የተመዘገባችሁት ከ70 በላይ፡ ችግሮች ሲኖሩ ከህዝቡ ጎን የቆማችሁት ከ5 የማትበልጡ ይህ ታዲያ ምንድን ነው ወይም አልችልም ካላችሁ ቀድሞውንም አለመመዝገብ፡ ይህ እርምን እንደመብላት ነውና፡
   • ምሁራን ፃፉ ፤ተቹ ፤ ህዝባችሁን አስተምሩ ፤ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለማረም ተሽቀዳደሙ፤ ለመሰላችሁ ነገር አቋም ያዙ፤ እስኪ አስቡት እንደ አሸን ከፈሉት ዩኒቨርሲቲዎቻችን የታሪክና የፖለቲካ መልካም ሀሳብ ሳይሆን ሰፈርተኝነት፤ ፍርሃት፤አስመሳይነት፤መሰኝነት የመሳሰሉ ዲያብሎሳዊ ሃሰቦች እንጅ መልካም አይወጣም፤ የተማረና ያልተማረ ልዩነቱ እስኪጠፋብን ድረስ ዘቅጠናል፤ አስቡት ትናንት ባልተማሩት መሪዎቻችን የተንፀባረቁ ለዛሬ ክፋታችን የሆኑ በጊዜው ተችታችሁ ቢሆን ኖሩ ትውልዱ ገደል አይገባም ነበር...ለማንኛውም እግዚአብሄር ይርዳን፡፡
   • ዲያስፖራዎቻችንም እባካችሁ ገንዘብና በተስተካከለ አካባቢ መኖር የሌሎችን ችግሮች አለመረዳት መሆን የለበትም፤ እኛም ዘራችን የተመዘዘበት ስለሆነ ለህዝባችን እናስብ፤ ምናልባትም ዛሬ ለተፈጠሩብን አረመኔ መሪዎችም እናንተ የምትኖሩባቸው መንግስታት ናቸው ፤ ምናልባትም የናንተ ቤተሰቦችም ጭምር፤ ጭቆናን ከማንም በላይ ለናንተ የሚያስተምር የለምና የተቻላችሁን አድርጉ
   • ለሃይማኖት መሪዎች ፤ አባቶች ከማለት ይልቅ መሪዎች ብያችኋለሁ ምክንያቱም ልክ እንደኛ እነደምዕመናኖች አስመሳዮች ፤ አድር ባዮች፤ ሰፈርተኞች ፤ ፈሪዎች ፤ልጆቻችሁን የማትኮተኩቱ፡ ሙሰኞች ሆናችኋል፡፡ በእርግጥ ይህን ሁሉ ያመጣው ሃጢአታችን እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ቢሆንም አስተምሩ ፤ ለጥሩ ነገር እንጅ እራሳችሁን ላልተገባ ነገር አሳልፋችሁ አትስጡ፡፡ አካሄዳችሁ ከትዕቢተኞችና ውሸታሞች ጋር አይሁን ፤ ምከሯቸው እንጅ ሁሉንም አትቀበሏቸዉ ፤ ፀልዩ ቤት ለቤት አስተምሩ፤ የቆሻሻ መጣያቸው አትሁኑ

   አመላክ ይርዳን !

   Delete
 7. ዳኒ ሁሌም እንደምትለው ነው ያልከው
  ነገር ግን በዚህ ስዓት የሚገዛው መንግስት ህውሓት/ወያኔ ብዙ መናገርያ አለው ( ሚዲያ ማለቴ ነው ) የሚገርመው ግን የህዝቡን ብሶት የሚሰማበት አንድ ሚዲያ የለውም በእውኑ በኢትዮጵያ ካሉት ብሄር ብሄረሰቦች ውስጥ ሰፊውን ቁጥር የሚዙት ማለትም ኦሮሞና አምሃራ ባብዛኛው ዞኖችና ወረዳወች እስከ ቀበሌ ድረስ ያነሱት ተቃውሞ እቃቃ ጨዋታ ነውን? አይመስለኝም መንግስት ወይ እራሱን ያሰተካክል አልያ ጀሮውን ያብዛ የዚህ 70 % የሚሆነው ህዝብ ብሶት ምን ይሆን ብሎ ‘’አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ’’ ይላል ሲተረትር አምሀራ ለአብነት ባህርዳር ላይ 100,000 በላይ ህዝብ ሲወጣ እነንትና ቀስቅሰውት ነው ወለጋ ፤ጎንደር፤ ባሌ፤ አምቦ በጥቅሉ በሁለቱ ክልሎች ድፍን ህዝብ ሲወጣ የአሸባረወች ነውን አር ተው ተው መንግሰት ይህን ስማ ምነው አይኤስ አይኤስ 30 ሰው አረደ ብለን እየየ አላልንም? ምነው በአጋዚ ከ600 በላይ በኦሮም ከ100 በላይ ህዝብ በአምሀራ በደረታቸው ‘እኛው በኛው’ ክፉ ሞት ሲሞቱ መንግሰት ምነው ዝም አለ? ገዳዩ እርሱ ስለሆነ ነው ሌላ አይደለም ‘’ሟቹ የናቴ ልጅ ገዳዩ ወንድሜ እሰከመቸ ድረስ ይመለሳል ደሜ’’ ነው የሚባለው ይተወቃል ‘ለሰው የሰው ስጋ እርሙ ነው’ ወያኔ ግን እርሙን በልቷል ህዝቡን በህዝቡ አሰፈጅቷል ተውኝ በቃቃቃቃቃ…….’እኔ አውቃለሁ ዝም በሉ’ ይላል
  እግዚብሔር ሆይ የህዝብ መንግስት ስጠን !!!

  ReplyDelete
 8. betekekelegnaw Seat Astemari yehonu gudayoch betam yemiyaberetun selehonu Dani Ketlebet bertaln

  ReplyDelete
 9. dane amlak yetbkhe hulam astmari nehe memare kale

  ReplyDelete
 10. ወይ ዳኒ ማንን ሰው ብለው ቆጥረው ነው የሚያወያዩን ማንን ፈርተው ፤ ሰውየው ነው አሉ ሚስት አግብቶ ሰዎች ያገኙትና ሚስትህ አረገዘች ቢሉት ማንን ወንድ ብላ ብሎ መለሰ አሉ፡፡ መንግስት ማንን ብሎ ነው የሚያወያየው የሃይማኖት አባቶችን እንዳንል የመንግስት ቀኝ እጅ ሆነው የመንግስትን ፍላጎት ደጋግመው እያመነዥኩ ነው የሃገር ሽማግሌ እንዳንል ለዕውነት ቆሞ የሚያረጋጋ አባት ጠፍቷል፤ሁሉም ፈርቷል እኛም ክርስቲያን ነን የምንለው ፀሎት ከማድረግ ወሬ ማውራትን መርጠናል አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አንድ የሚያግባባ አቋም የለውም ፤እኔ ካልተነካሁ ምን አገባኝ የሚል አቋም ያላቸው ሰዎች ቀላል አይደሉም፡፡ የቸገረ ነገር ነው የገጠመን ፤ ነገሩን ችላ ከማለት ይልቅ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ በደል የሁላችን በደል እንደሆነ ማሰብ መጀመር አለብን፡፡ አለበለዚያ የጋቭሮቮች ታሪክ ይደርስብናል፡፡ቡልጋሪያ ውስጥ የሚኖሩ ታወቂ ስግብግቦች አሉ እና የሆነ ቀን ላይ ቀበሌው ላይ እንግዳ ይመጣና ለፕሮግራሙ የሚሆን ባህላዊ መጠጥ(በእኛ ሀገር ጠላ) እንዲያመጡ ይታዘዛሉ ፤እነርሱ ግን እያንዳንዳቸው ለራሳቸው እንደዚህ ብለው አሰቡ “ከዚህ ሁሉ ሰው ውስጥ እኔ ብቻ ውሃ ይዤ ብሄድ መጠጡን አያበላሸውም ስለዚህ ውሃ ይዤ ልሂድ” ሁሉም ስግብግብ ስለሆኑ ይሄንን ሃሳብ አሰቡ እናም ለእንግዳ ባህላዊ መጠጥ ማቅረብ ቀርቶ ውሃ አመጡ ፕሮግራማቸውም ተበላሸ በእንግዳቸው ፊት ተሸማቀቁ ምክንያቱም በማህረሰብ ውስጥ የአንድ ሰው አስተዋፆ ምን ያህል ጉልህ እንደሆነ ማሰብ ባለመቻላቸው ነው፡፡ስለዚህ ውሃ ማምጣቱን ማሰብ ትተን ጠላውን ለማምጣት መፈለግ አለብን ፤ለውሃው ጊዜ አለውና፡፡ሌላው የገረመኝ ከአማራውና ከኦሮሞው ውጪ ይሄ ጉዳይ በዕውነት ትግሬዎችን አይመለከትም ፣ደቡቦችን አይመለከትም ፣ሌሎችንስ አይመለከትም? በተለይ በዚህ ወቅት ከትግራይ ህዝብ ብዙ ነገሮችን እንጠብቅ ነበር አብዛኞቹ ግን ነገሩን የብሄር ጦርነት አደረጉት ያሳዝናል!!! እስራኤልን ከግብፅ ባርነት ያወጣ እግዚአብሄር ቀንን ያመጣል ይህችም ቀን ታልፋለች ታሪክም ይፈርዳል፡፡ የሰላም አምላክ መድኃኒዓለም ምህረትን ያምጣ!!!

  ReplyDelete
 11. Dear ato Daniel ,why do you clearly write the current situation of political case in Ethiopia,but why don't you write the difference of people & party in Ethiopia?look iam the one person from tigray people ,there is a lot of problem in tigray people in relation to good governance like other ethiopian brothers. but my question is do you think that the Tigray people have better living condition better than others?this is 100% plus mistake ,there is a parallel level serious problem,luck of good governance ,monopolistic leadership,luck of freedom,.....in tigray people.this all now the amhara people,this all now the oromo people.but why did they stand against the innocent Tigray people.why they all trying to kill this people?why?why? And you have to write about how to make peace,instead of ......


  ReplyDelete
 12. ዲ/ን ዳንኤል፡ እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ ልከው ሁሉ እውነት ነው፡፡ ከምንም በላይ ሀገር ይቀድማል፡፡ ቢመረንም ቢጥመንም ትልቁ ሥራ መድኃኒት ፍለጋው ስለሆነ የሁሉም አስተሳሰብና ሀሳብ ወደ መድኃኒት ፍለጋው ቢሆን መልካም ነው፡፡ እንደ ሀገር ትልቁ ያለመታደላችን መገለጫ ከስህተቶቻችን እኳን ለመማር ያለን ዝግጁነት እጅግ አናሳና የቀጨጨ መሆኑ በጣም ያሳዝናል፡፡ ነፍሳት ስለምን ጠፉ;፡፡ ወንድምህ አቤል ወዴት ነው; ብሎ የሚጠይቅ አምላክ አለ፡፡ መልስ ለመስጠት የምንችልበት ሞራል አለን;
  ከምንም በላይ መሪዎችም ተመሪዎችም ሁላችንም ወደ መድኃኒት ፈለጋ ብናተኩር፡፡ ያበርታህ፡፡ አእ

  ReplyDelete
 13. ይህን ጽሁፍ ሳነብ“ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን ጠቅላይ ሚኒስትር መሰሎቹን ከያሉበት አፈላልጎ የምክር ቤት አባላት ማድረግ ቢቻል ሀገራችን የት በደረሰች አልኩ ዳሩ ምን ዋጋ ጡንቻ እንጅ ጭንቅላት የማይነግስባት ሀገር !ያ ባይሆን ኖሮ ማንነቴ ይከበርልኝ፣ ድንበሬን አትንኩብኝ፤ የሚልን ትውልድ ጭንቅላታቸው ተኮላሽቶ በጡንቻቸው የሚያስቡ “ፀጥታ አስከባሪ” ተብዮዎችን ልኮ ከማስጨረስ ይልቅ፤ በታሪክና በፖሊቲካው ዘርፍ ፒ.ኤች.ዲ እና ማስትሬት ካላቸው ሀገር በቀል ምሁራን ጋር አገናኝቶ ማወያየት፤ የተበላሸውንም እንደሚገባ ማስተካከል ምንኛ በተሻለ።

  ReplyDelete
 14. I read this article as much as I can and understand that we are the creator of the problem and as the same time we are the solution maker though we are now divided in to several uncountable sects of religious, political, tribal and so on small parts . These are very tiny problems when we compare them from the original citizenship obligations and duties we need to fulfill . We as a nation feared the present dictators the last 25 years and it is time now to confront them . I think we have finished our patience and their vague home work to fight each other to show that we are loyal to their political agenda . We are no more minorities to them . Here comes time which opens our eyes and shows us that they are not our freedom fighters from their origin rather brutal dictators who want to profit from our losses . That is why the major tribes now showing a united straggle and try to create common agenda on how to continue our common survival as a nation from the historic wound which we participated with out knowing the dictators who were the messengers of foreign enemies and devil itself . After this moment, which all the individual citizens will pay results the better outcome of our future by building our institutions and values in a modern way based on our fore fathers and fathers found it . Then we can have a better way of governance who can listen to its people and the people will have better governance which can listen them. Let God give us wisdom to all .

  ReplyDelete
 15. ‘’ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር ------ ትማራለች ይባላል’’
  አዎ አንዳንዴ ብቻ አይደለም ሁሌም እኛነታችንን እረስተን ስለሌላው የምናዎራ የምንናገር ከሆነ እራሳችንን እረስተን ያን የምናዎራለትን ሰው (አካል) ከመምሰልም አልፈን ልንሆንው ወይንም ከዚያ ልንበልጥ እንችላለን ፡፡ ምክንያቱም ለራሳችን ጊዜ ሰጥተን አናቅም እራሳችንን ሁነን አቅም ሁሉንም ጊዜአችንን የሰጠነው ለዚያ ሰው ነው ፡፡ ባስልጣኖቻችንም የሆኑት እንደዚያ ነው ፡፡ ኢትዮጵያን ከገዳዩ ከጨቋኙ ከአረመኔው ደርግ ነጻ አውጥተናታል !!!!! በማለት የደርግን አረመኔ ተግባሮች እና ክፋት ለ25 አምት አስተማሩ እንደት ብለው እንዳሸነፉም ነገሩን ዛሬም ዲረስ የደርግን ሀጢያት ዘመሩልን ነገር ግን እነሱ ከቆሙበት ሳይሆን ህዝቡ ከቆመበት በኩል ሲታዩ ደርግን ከመምሰል አልፈው በእጂጉ ከደርግ በሁሉም ነገር ልቀው ተገኙ ፡፡ታዲያ ያኔ እነሱ ደርግን ለመጣል ሲነሱ መንገድ ያሳየ ስንቅ ያቀበለ ሲቆስሉ ያስታመመ ህዝብ ግማሹን በአሸባሪነት ግማሹን በአክራሪነት --------------- በመበጣጠስ በማሳደድ በማሰርና በመግደል ጥሬ ላበደር ጠጠር መለሰለት እንደተባለው ሆነና አረፈ ታዲያ ይህ ይነስ ደርግስ ከዚህ በላይ አደረገን አላደረገም ፡፡ አሁንም ደርግን ይኮንናሉ የድርግ እርዝራዦች የፈጠሩት ነው በማለት ይከሳሉ በደል ከበድል ያወዳድራሉ ፡፡

  ተው የሚል ጠፋ

  ReplyDelete
 16. መልካም ነው፥ መድኃኒቱ መደማመጥና መነጋገር ነውና ለሁላችንም ለመወያየት ቻይ የሆነ ልቦናን ይስጠን::

  ReplyDelete
 17. ye zemenachin toliqu na asteway leHagerachin Adinet bego astesaseb genbi hasab aqirabi, yemiyanits mixuq atayay balebet, Diaqon Daniel Kibret rejim idme Amlak Yisxih. (Tesfa Lidet)

  ReplyDelete
 18. በጣም ትልቅ ትምህርት ሰጪ ጽሑፍ ነው ዲ/ን ዳንኤል እናመሰግናለን
  ከታች ኮሜንት የሰጡትን አንብቢያለሁ ደስ ብሎኛል እናንተንም አመሰግናለሁ

  ReplyDelete