Thursday, July 21, 2016

የሰሎሞን ፍርድ

ሦስት ነጋዴዎች ድንገት አንድ ቀን በንጉሥ ሰሎሞን የዘውድ ችሎት ተገኙ፡፡ ሦስቱም ለብዙ ዘመን አብረው ለመነገድ ተማምለው፣ ግመል ጭነው፣ ገንዘብ ቋጥረው፣ ስንቅ አንጠልጥለው፣ ሀገር ጥለው የሄዱ ናቸው፡፡
‹ንጉሥ ሆይ› አለ አንዱ በዙፋኑ ፊት እጅ ነሥቶ፡፡ ‹እኛ አብረን ለመነገድ ተስማምተን መንገድ የጀመርን ጓደኛሞች ነን› አለ፡፡
ሁለተኛውም ነጋዴ ተቀብሎ ‹ቃላችንንም አክብረን ለንግድ ሩቅ ሀገር ስንጓዝ ድንገት የሰንበት በዓል ደረሰብን› ሲል ቀጠለ፡፡
ሦስተኛውም ነጋዴ ‹ሰንበትን አክብረን ለመዋል ስለፈለግንም ድንኳን ከተከልንበት ቦታ ራቅ አድርገን ጉድጓድ ቆፍረን ገንዘባችንን በከረጢት ቀበርነው፡፡ ከመካከላችን ማናችንም ገንዘቡን ተደብቀን ላንወስድ መሐላ ፈጽመን ነበር፡፡ በማግሥቱ ግን ወደ ጉደጓዱ ሄደን ስንቆፍረው ገንዘባችንን አጣነው› አለና አስረዳ፡፡ የመጀመሪያው ነጋዴም አንገቱን ከነቀነቀ በኋላ ‹ንጉሥ ሆይ ጉድጓዱን ስንቆፍርም ሆነ ገንዘቡን ስንደብቅ ሌላ ሰው ያየን የለም፡፡ ከሰረቅነው እኛው ነን፡፡ ነገር ግን ማናችን እንደሰረቅን ልንተማመን አልቻልንም› አለ፡፡

ንጉሥ ሰሎሞን በልቡ ‹መስረቅ የቻለ ሰው መዋሸትና መሐላን ማፍረስ አያቅተውም› ብሎ አሰበና  ነገሩን ቀለል አድርጎ ‹ነገ ተመልሳችሁ ስትመጡ ማን እንደሰቀረው እነግራችኋለሁ› ሲል አሰናበታቸው፡፡
በማግሥቱ ሦስቱ ጓደኛሞች መጡ፡፡ ችሎቱም ተጀመረ፡፡
ንጉሥ ሰሎሞን ‹የእናንተን ጉዳይ ከመመልከቴ በፊት ሦስታችሁም ጠቢባን መሆናችሁን ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ በመሆኑም በሚከተለው ታሪክ ላይ ያላችሁን አስተያየት እንድትሰጡ እፈልጋለሁ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- አንዲት ሴትና አንድ ወንድ ከልጅነታቸው ጀምሮ አብረው እየተማሩና እየተጫወቱ አደጉ፡፡ ወደፊት ትልቅ ሰው ሲሆኑ ተጋብተው አብረው ለመኖር ቃል ተግባቡ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የኑሮ መሥመር አለያያቸውና በተለያዩ ቦታዎች መኖርና መሥራት ጀመሩ፡፡ በዚህ መካከልም ሴቷ ቃል ኪዳንዋን ረሳችውና ሌላ ባል አገባች፡፡ ጋብቻው በተፈጸመበት ቀን ማታ የገባቺው ቃል ኪዳን ትዝ አላት፡፡ ደነገጠች፡፡ ነገሩን ለባልዋ ነገረቺው፡፡ ባልዋም ለቃል ኪዳን ትልቅ ቦታ የነበረው ሰው ነበርና ‹በይ ተነሺ ቃል የገባሺለትን ሰው እንፈልገው፤ ስናገኘውም ቃል ኪዳኑን ማፍረሳችንን ነግረነው፣ የገንዘብ ካሣም ከፍለነው ይቅርታ ያድርግልን፡፡ ያለበለዚያ ትዳራችን ይበላሻል› አላት፡፡
ሁለቱ አዲስ ተጋቢዎች ልጁ ይገኝበታል ወደሚባለው ቦታ ሩቅ መንገድ ተጉዘው አገኙት፡፡ የሆኑትንም ነገር ሁሉ ገለጡለት፡፡ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው፣ ገንዘቡን እንዲቀበላቸው ለመኑት፡፡ ልጁ ቀና ሰው ስለነበር ይቅርታ አደረገላቸው፡፡ ‹ያልሠራሁበትን ገንዘብ አልቀበልም› ብሎ ገንዘቡን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ እነርሱም አመስግነውት ተመለሱ፡፡ ሲመለሱ በመንገድ ላይ አንድ ዘራፊ አጋጠማቸውና የያዙትን ገንዘብ ነጠቃቸው፡፡ ልጂቱም ገንዘቡ በምን ምክንያት እንደተያዘ ታሪኩን እያለቀሰች ለዘራፊው ነገረቺውና እንዲመልስላቸው ለመነቺው፡፡ ዘራፊውም በታሪኩ ተደንቆ የወሰደውን ገንዘብ መለሰላቸው፡፡
ንጉሥ ሰሎሞን ይህን ታሪክ ከተረከ በኋላ ‹ከባልየው፣ ከሚስቱ፣ ከቀድሞ ወዳጇና ከዘራፊው የትኛው ሰው የበለጠ ምስጋና ይገባዋል ብላችሁ ታስባላችሁ?› ሲል ጠየቃቸው፡፡
የመጀመሪያው ነጋዴም ‹ለእኔ የበለጠ ምስጋና የሚገባት ሴቲቱ ናት፡፡ ቃል ኪዳንዋን አስታውሳ ይቅርታ ለመጠየቅ መነሣቷ ያስመሰግናታል› ሲል ሐሳቡን ሰጠ፡፡
ሁለተኛው ነጋዴም ‹ለእኔ ግን የበለጠ ምስጋና የሚገባው ባልዋ ነው፡፡ ምክንያቱም ሚስቱ ቃል ኪዳንዋን ማፍረሷን ስትነግረው ቃልዋን ተቀብሎ፣ ቤት ንብረቱን ትቶ፣ ገንዘቡን ይዞ ወደ እጮኛዋ ዘንድ መሄዱና ይቅርታ መጠየቁ ያስመሰግነዋል› ሲል አስተያየቱን ሰጠ፡፡
ሦስተኛውም ነጋዴ ‹ባልና ሚስቱ ያደረጉት ነገር የሚገርምና የሚያስመሰግን ነው፤ ነገር ግን የቀድሞ እጮኛዋ ሞኝ ሰው ነው፤ ገንዘቡን መቀበል ነበረበት› ሲል ሐሳቡን ለገሰ፡፡
ንጉሥ ሰሎሞንም ሐሳባቸውን ከሰማ በኋላ ሦስተኛውን ነጋዴ ‹ገንዘቡን የሰረቅከው አንተ ነህ› አለው፡፡ ሰውዬውም ደነገጠና ወደ ንጉሡ ተመለከተ፡፡ ንጉሥ ሰሎሞንም ‹ያልደከመበትን ገንዘብ የሚመኝ አእምሮ ባይኖርህ ኖሮ ያንን ልጅ ሞኝ አትለውም ነበር፡፡ አስተሳሰቡ ከሌለ ድርጊቱ አይመጣም፡፡ አንተ ውስጥ ተጣምሞ የበቀለ ነገር አለ፡፡ ሁለቱ ጓደኞችህ ታማኝነትን ዋጋ ሰጥተውታል፤ አንተ ግን ለታማኝነት ዋጋ አልሰጠኸውም፡፡ ስለዚህ ካንተ በቀር ይህን ሊያደርግ የሚችል ሰው የለም፡፡
የአንተን አእምሮ ሳየው የተሠራበትን ነገር አየሁት፡፡ አእምሮ ሲሰጠን ተሠርቶ አልተሰጠንም፡፡ እንዲሠራ ተሰጠን እንጂ፡፡ ሰው በርስቱ ላይ እንዴት ያለ ቤት እንደሚሠራ መወሰንና ቤቱን መገንባት የእርሱ ድርሻ ነው፡፡ የሚጠቀመው ዕቃ የሚገነባበትም መንገድ የቤቱን ጥንካሬ ይወስነዋል፡፡ አእምሮም እንዲሁ ነው፡፡ በሕግ፣ በምግባር፣ በትምህርት፣ በጥበብ፣ የተገነባ አእምሮ ያንተን ዓይነት አስተሳሰብ አይኖረውም፡፡ አሁን የሰጠኽው ሐሳብ ያሳለፍከውን ሕይወት፣ የተዘራብህን ዘርና የተሠራህበትን ነገር አሳይቶኛል፡፡ ወላጆችህን አየኋቸው፤ ጓደኞችህን አየኋቸው፣ መምህሮችህን አየኋቸው፡፡ እነዚህ ሁሉም ወይም ከእነዚህ አንዱ የዘራብህ ዘር ትክክል አይደለም፡፡ ምናልባትም ይህ ዘር ባንተ ላይ መዘራቱን አታውቀው ይሆናል፡፡ ግን ተዘርቶብሃል፡፡
‹አንድ ታሪክ ልንገራችሁ› አላቸው ጠቢቡ ሰሎሞን፡፡ እንዲቀመጡ ተፈቀደላቸው፡፡ ሁሉም ሌባውን ያወቀበት መንገድ አስደንቋቸዋል፡፡ ምንጣፍ ላይ ቁጭ አሉ፡፡
አንድ ቀን አንድ ልጅ እኔ ዘንድ ለፍርድ ቀረበ፡፡ የመጣው አባቱን ገድሎ ነው፡፡ ረበናቱ ሁሉ ‹አባቱን የገደለ ፈጽሞ ይሙት ይላልና ይገደል› ብለው ወሰኑበት፡፡ እኔ ግን ይህንን ነገር ያደረገበትን ምክንያት ለመረዳት ስለፈለግኩ ጠየቅኩት፡፡ ነገሩም እንዲህ ነበር፡፡ አንድ አባት ልጁን ሁል ጊዜ አንድ ነገር ያስተምረዋል፡፡ ጓደኞቼ መቱኝ ሲለው ‹በላቸው› ይለዋል፡፡ ፍየሉ ወጋኝ ሲለው ‹በለው› ይለዋል፡፡ ዕንቅፋት መታኝ ሲለው ‹በለው› ይለዋል፡፡ የአባቱ መፍትሔ ሁልጊዜ ‹በለው› ብቻ ነበር፡፡ ልጁ በዚህ ትምህርት ነበር ያደገው፡፡ አደገ፡፡ ጎለመሰ፡፡ ፈረጠመ፡፡ ያገኘውን ሁሉ እየደበደበ፡፡
አንድ ቀን የአባቱን በጎች ወስዶ አባቱ ሳይፈቅድለት ሸጠና መጣ፡፡ አባቱ ለምን እንደሸጠ ሲጠይቀው ‹ገንዘብ ያስፈልገኛል› አለው፡፡ አባቱ ተናደደና በበጎች መጠበቂያ ጅራፍ መታው፡፡ ያን ጊዜ ልጁ ድንጋይ አንሥቶ እንደ ቃየል አባቱን አናቱን መትቶ ገደለው፡፡ ልጁን ለምን አባቱን እንደገደለ ስጠይቀው ‹አባቴ ያስቸገረኝን ሰው ሁሉ እንድመታ አስተምሮኛል፡፡ አባቴም ስላስቸገረኝ መታሁት፡፡ ለመሆኑ ከመምታት በቀር ምን ማድረግ እችል ነበር?› ሲል ጠየቀኝ፡፡ ይህ ልጅ ሌላ ነገር አልተማረምና ያደረገው የተማረውን ነው፡፡ ሰው የትምህርቱ ውጤት ነውና› አለው፡፡ ሰውዬውም በነገሩ ተገርሞ ገንዘቡን መለሰ ይለናል ሚድራሽ የተባለው የአይሁድ የትውፊት መጽሐፍ፡፡
ይህንን ታሪክ ሳነብ ዛሬ በልጆቻችን ኅሊና እየገነባን ያለነው የዘረኛነትና የጠባብነት፣ የጽንፈኛነትና የአምባገነንነት ጡብ ይታወሰኛል፡፡ እያንዳንዳችን ለሌላው ብለን የምናስታጥቃቸው ነገር አፈሙዙ ወደራሳችን ሊዞረን እንደሚችል ያሰብንበት አልመሰለኝም፡፡ የተጣመመ ሐሳብ እያሰጠን፣ የተጣመመ ትውልድ አፍርተን የተስተካከለች ሀገር አንደመመኘታችን ያለ ሞኝነት ከወዴት ይገኛል?

17 comments:

 1. ሰው የዘራዉን ያጭዳል፤ በሀገራችን የዛሬ 42 ዓመት የተዘራው የዘረኝነት መርዝ የክፋት ፍሬን አፍርቶ የሚሊዮን ወገኖቻችንን ሕይወት ቀጥፏል፣ሚሊዮኖችንም አፈናቅሏል፡፡ ታዲያ ጊዜው በሰፈሩት ቁና መቀበል ያለ ነውና እነዚያ አረሙን የዘሩት ክፉ ዘሪዎች በሰፊው የሚያጭዱበት(የሚታጨዱበት) ጊዜ በጣም ቀርቧል፤ በጥቂቱም ቢሆን ማጨድ ጀምረዋል፡፡

  ReplyDelete
 2. እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ያብዛልህ ወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል
  "....በልጆቻችን ኅሊና እየገነባን ያለነው የዘረኛነትና የጠባብነት፣ የጽንፈኛነትና የአምባገነንነት ጡብ ይታወሰኛል፡፡ እያንዳንዳችን ለሌላው ብለን የምናስታጥቃቸው ነገር አፈሙዙ ወደራሳችን ሊዞረን እንደሚችል ያሰብንበት አልመሰለኝም፡፡ የተጣመመ ሐሳብ እያሰጠን፣ የተጣመመ ትውልድ አፍርተን የተስተካከለች ሀገር አንደመመኘታችን ያለ ሞኝነት ከወዴት ይገኛል? " ይህ በሀገር ላይ ብቻ ሳይሆን በትንሹ የሀገር መሰረትና ምሳሌ በሆነው በቤታችን እና በቤተሰባችን ልንጠነቀቅለት የሚገባ ነገር ነው።

  ReplyDelete
 3. በሕግ፣ በምግባር፣ በትምህርት፣ በጥበብ፣ የተገነባ አእምሮ

  ReplyDelete
 4. አቶ ዳንኤል በእውነት ብዙ ትደክማለህ፣ ትጽፋለህ፣ ሲሻህም ምሁር ልሁን ትላለህ፣ ግን ውስጥህ ካልተለወጠ ምንም ብትደክም ጥሩ ፍሬ ማፍራት አትችልም።ምክንያቱም ራሱን ያለወጠ ሰው፣በብልጣብልጥነት ጥቂት መሰሎቹን ሊያታልል ይችል ይሆን እንጂ ዘላቂ የሆነ ትርጉም ያለው ለውጥ ሊያመጣ አይችልም።"የዘረኝነትና የጠባብነት፣ የጽንፈኛነትና የአምባገነንነት ጡብ ይታወሰኛል።"ይላል አቶ ዳንኤል በእውነት ግን የአምባገነንነትና የትምክህተኝነት ልዩነት ሳይገባህ ቀርቶ ነውን? ወይስ በተለመደው የብልጣብልጥነት ውርስ መቀጠል ፈልገህ ነው?ለማንኛውም ድከም ብሎህ ነው እንጂ ትምክህተኝነት እኮ ማንኛውንም ነገድ አይወክልም፣ትምክህተኝነት በማንኛውም ነገድ የሚከሰት ክፉ በሽታ ስለሆነ ነው በኢትዮጵያ የሚወገዘው። እናም ራስህን አታታል፣ ሌላውን እንዲለወጥ ከመምከርህ በፊት ውስጥህ መለወጥ ይቅደም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. His name is Diakon daniel kibret.you made a mistake from the beigning.

   Delete
  2. And you are a changed man? You are too chicken to even post your name, hiding behind "anonymous". What a joke! At least Dn Daniel is offering something, what do you offer, a big NOTHING!

   Delete
  3. Yegermehal menem enkuan negative comment betaskemet, he still allow your garbage message to be pop up on the comment page.

   Delete
 5. ወዳጄ ሆይ ለብልህ አንዲት ቃል ብቻ ይላሉ... ለሚያስተውል ትርጉሙ ግልጽ ሊሆንለት ይችላል። ነገር ግን አሁን ላለውና ኅሊናው በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተበርዞ ለደነዘዘበት ትውልድ ምሳሌውም ሆነ ተረቱ ላይገባው ወይም ቢገባውም ላይወቅሰው ይችላል። ስለዚህ የተሻለ የሚመስለኝ እገሌ እንዲህ አደረገ፥ እከሊት እንዲህ ሆነች፥ እንዲህ አገኙ፤ ስለዚህ እናንተም እንደዚህ እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ ወይም እንደዚያ ለመሆን ተጣጣሩ ... እየተባለ ቢነገር ምናልባት ይሻል ይሆን ብዬ አስባለሁ።
  ቢቻል ክፉ አድራጊዎቹ በስም በአድራሻ በምስል እየተቀረጹ ቢጋለጡ ለሌላውም ማስጠንቀቂያና ማስተማሪያ ይሆን ነበር። ፈረንጁ በሚቀደው ፈር ጭፍን መጋለብ ስለሆነ የያዝነው መጨረሻው ክፉና ደግ እንኳ መለየት ያቅተንና መመለሻው ከባድ ዳገት ይሆንብናል።
  በግልጽ ከመናገርና ከመጻፍ ይልቅ በተረትና ምሳሌ እንዲሁም በቅኔ መነጋገሩ ከባለሥልጣኖች ቁጣና በቀል ሊያተርፍ እንዲችል ይገባኛል። ችግሩ ግን ትውልዱ አልገባው ካለ ምን ዋጋ ይኖረዋል። ጨርሶ ከደነዘዘና ልቡናው ከተሰውረ በኋላ በቀጥታም ቢነግሩት ወይ ያሾፍብሃል አሊያም ይስቅብሃል፥ ባለሥልጣን ቢጤ ከሆነ ደግሞ ፈረንጆቹ አሁን እንደሚያደርጉት ፖሊስ ይጠራና አብደሃል ብሎ አማኑኤል "ሆስፒታል" ያሳስርሃል።
  ፈረንጅ መሠሪ የዲያብሎስ አሽከር
  ከሰው ወገን ተፈጥሮ ነበር
  ግን ፍላጎቱ ሊሆን የዝንጀሮ ዘር
  ምድርን አተራምሶ በጦርነት ሽብር
  ሊኖር ይናፍቃል በማርስ ጁፒተር
  ነፍሱ አይማርም በሰማይ በምድር
  አንድ ቀን ይፈርዳል ቢዘገይም እግዜር።

  ReplyDelete
 6. "የአባቱ መፍትሔ ሁልጊዜ ‹በለው› ብቻ ነበር፡፡ ልጁ በዚህ ትምህርት ነበር ያደገው፡፡ አደገ፡፡ ጎለመሰ፡፡ ፈረጠመ፡፡ ያገኘውን ሁሉ እየደበደበ፡፡" ይኸዉ ነዉ እንግድህ አሁን እየገጠመን ያለዉ።
  ግሩም እይታ ነዉ በእዉነት።

  ReplyDelete
 7. Thanks Dani you are democratic when you posting z above comment.may be
  He is one of z merchant.

  ReplyDelete
 8. ዲ/ን ዳኒ እኔ የሚገርመኝ መጣርህንና መልፋትህን አምነው ሊሳደቡም ይቃጣቸዋል፡፡ አምላክ ልቦና ይስጠን!!! ዳኒ አንተን የሚመስሉ ብዙ ዳንዔሎችን አምላክ ያብዛልን፡፡

  ReplyDelete
 9. እኔ መቼም የአንተን ጽሑፍ ባገኘሁት የተጣበበ ጊዜ ሁሉ ከማንበብ ወደ ኋላ አልልም፡፡ ሃይማኖታዊ አስተምህሮህ ፥ ድንቅ ነው፤ የማኀበረሰባዊ አስተዋጽኦህ ፥ ወደር የለውም (በጡመራ ገጽህ፣ በመጽሐፍ፣ በበጎ ሰው ሽልማት ድርጅትህ፣ በተጋባዥነት በምታደርጋቸው ዲስኩሮች)፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን አንተም ሰው ነህና ፥ ከጥቃቅን ደካማ ጎንህ ጋር ነው፡፡ በግሌ፥ ሁሌም ለአኔ የሚሆን በርካታ ነገር ከአንተ ጡመራ ገጽ አገኛለሁ፡፡ ለዚህም ምሥጋና አቀርባለሁ፡፡

  ይህ ጽሑፍ ግን፥ በዚህ ጊዜ የቀረበበት ውስጠ ምክንያት (motive)ግልጽ አልሆነልኝም፡፡ ገዢዎችንን ለመገሰጽ ብለህ ከሆነ ግን በጣም በጣጣጣምምምምምምምምምም የዘገየ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች የአክሱም ባንክን የዘረፉት ከዛሬ 4ዐ ዓመት በፊት ነው፣ በለው በሚለው ፍልስፍናቸው ወልቃይት ጠገዴን አጭደው የረመረሙበት ስልት የተጀመረው ከ4ዐ ዓመት በፊት ነው፣ በሽህዎች ዓመታት በብልሃት እየተገነባች የዛሬ ቅርጿን የያዘችውን ኢትዮትጵያን፥ በአስደናቂና ግሩም ሁኔታ አራቁተው፣አጎሳቁለው አጽሟን የቀረች፣ የአንድ ሐሙስ ዕድሜ ያላት፣ ጣረሞት የያዛት አገር ያደረጉዋት በ25 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ታሪክ ገልብጠው መጻፍ ብቻ ሳይሆን ታሪክ መቀማት የጀመሩትም ዛሬ አይደለም፡፡ ሜጀር ጀነራል ሙሉጌታ ቡሊ ተግባረ እድ ት/ቤትን ሓየሎም አርአያ ብለው ፥ ይቺም ታሪክ ሆና በአንድ የጦር አካዳሚና የሞያ ት/ቤት ሳይቀር ቀንተው ታሪክ መስረቅ የጀመሩት ከ2ዐ ዓመታት በፊት ነው፡፡ መሬት ዘርፎ ፥ የኛ ነው ማለት የጀመሩት ፥ የሚመጻደቁበት ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ፥ እነርሱም ለኢትዮጵያ ምንና ማን እንደሆኑ ሳይታወቅ ከ25ዓመታት በፊት ነው፡፡ አባ መርቆሬዎስን አሳድደው ፥ አባ ጳውሎስን በአንብሮተ ሣንጃ፣ አባ ማቲያስን በትራንስፎርሜሽን ሥጋጃ (ልማታዊ አባት) ያ ቆሙትን እነዚህን “መሪዎቻችን” ለመምከር ታስቦ ከሆነ በእውነት በቀረ የሚያሰኝ ነው፣ በእኔ እይታ፡፡

  ሰላም

  ReplyDelete
 10. Wedaje: I remembered your article when I read this story
  http://www.aljazeera.com/indepth/features/2015/06/magazine-documenting-america-white-nationalists-150609095548558.html

  ReplyDelete
 11. ዱባ እንደመሪው ነው ይሏችኀል ይሔ ትውልድና ወላጆቹ ፌዴራሊስቶቹ ናቸው፡፡ እናመሰግናለን መምህር ወመራሔ ፅድቅ!!!

  ReplyDelete
 12. አንዳንዴ እንዲህ ነው አለ ያገሬ ሰው ፣ገዥዎቻችን እማ መናገረ ብትፈልግ ኖሮ ሰዓቱ አሁን አደለም ማንን መናገር እንደፈለክ ግልጽ ነው፣አንጠራጠርም ድፍርሱ እየጠራ ነው ዝም ብላችሁ ሙቱ ዝም ብላችሁ ተገዙ ዝም ብላችሁ ተኙ ከሆነ አናደርገውም አንተም ሳይመሽብህ ወደ መረጥከው ተጠጋ እኛም ሳይመሽብን የምናደርገውን አውቀናለና

  ReplyDelete
 13. really I appreciate you.thank you many, and long live.

  ReplyDelete