‹ዜና ደብረ ሊባኖስ› የተሰኘውና በ1590 ዓም የተጻፈው መጽሐፍ በገዳሙ የተፈጸሙ አስደናቂ የቅዱሳን ታሪኮች ተመዝግበውበታል፡፡
ከእነዚህ አንዱ ‹ኢየሩሳሌም እንሂድ› የሚለው ታሪክ ነው፡፡ ታሪኩ የተፈጸመው በእጨጌ ዮሐንስ ከማ ዘመን [ከዐፄ ይስሐቅ
(1407-1423) እስከ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ(1426-1469 )የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የነበረ የደብረ ሊባኖስ 7ኛ አበ ምኔት] ነው፡፡
በደብር (በደብረ ሊባኖስ) ውስጥ ስሙ ፍሬ ቡሩክ የተባለ ሰው ነበረ፡፡ አንድ ቀንም ወደ አንደ አረጋዊ ዘንድ ደረሰ፡፡ ፊቱንም ሻክሮና ወይቦ አገኘው፡፡ ያም ወንድም አረጋዊውን ሥጋው እንደዚህ የመነመነበትን ምክንያት ጠየቀው፡፡ አረጋዊውም ‹በላየ ላይ ምንም ሕመም የለም፤ ነገር ግን አንድ ነገር ያስጨንቀኛል፡፡ የመጸዳጃ ቤት የለኝም፡፡ በዚህም ምክንያት የት እሄዳለሁ ብዬ ምግብ ከመብላት እከለከላለሁ› አለው፡፡ ያም ወንድም ሰምቶ ወደ ቤቱ ሄደና ሲመሽ የሚወደውን ወንድም ጠርቶ ‹ና ኢየሩሳሌም እንሂድ› አለው፡፡ እርሱም ‹አስቀድመን ጸሎት ሳናደርግ፣ ለመንገድም ስንቅን ሳናዘጋጅ እንዴት ድንገት እንሄዳለን› አለና መለሰለት፡፡ ያም ወንድም ‹እንዲህ አትበል፤ ነገር ግን የምነግርህን ስማ፡፡ እነሆ የመጸዳጃ ቤቱ ሞልቶበት በረሃብ የሚሞት አንድ አረጋዊ አለ፡፡ ና ለእርሱ የፍቅርን ሥራ እንሥራለት፡፡ የመጸዳጃ ቤቱንም እንጥረግለት፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ ያልኩህም ይህንን ነው› አለው፡፡
ያም ወንድም ‹እሺ ቃልህ ያማረ ነው› አለው፡፡ ትልቅ የጋን ስባሪ ይዘውም ሄዱ፡፡ ፍሬ ቡሩክም ልብሱን አውልቆ ወደ መጸዳጃ ቤቱ ገባ፡፡ ሲገባም እስከ አንገቱ ድረስ ተዋጠ፡፡ ነገር ግን ጨክኖ ቆሻሻውን እያወጣ ለወንድሙ ይሰጠው እርሱም በፍንቺት በኩል ጥሎ ሲመለስ ይፈስ ነበር፡፡ ይህንን ሌላ ሰው ሠርቶት የማያውቀውን ግብራቸውን እስኪነጋ ድረስ ሠርተው ፈጸሙ፡፡ ቦታውንም አጠቡት፤ አጸዱትም፡፡ ሰውነታቸውንም ይታጠቡ ዘንድ ወደ አጋት ወንዝ ሄዱ፡፡ ታጥበውም ወደ ቤታቸው ተመለሱና በዚያ ተቀመጡ፡፡ ማንም ሰው ሥራቸውን እንዳያውቅባቸው፡፡ ነገር ግን ሽታው እስከ ሰባት ቀን ድረስ ቆየ፡፡ በዚህም የተነሣ የአደስ ቅጠል አጤሱበት፡፡ ሰውነታቸውም በዕጣንም ያታጠኑ ነበር፡፡ ሽታውም እስኪጠፋ ብዙ ጊዜ ፈጀ፡፡ ይህም ነገር በደብረ ሊባኖስ ሆነ፡፡
ኢየሩሳሌም መሄድ ማለት ይኼ ነው፡፡ የሰውን ጭንቀት መጋራት፣ የሰውን ችግር መፍታት፤ ከባቴ አበሳ መሆን፡፡ ጾም፣ ጸሎት፣
ስግደት፣ትምህርት፣ የጽድቅ መሥሪያ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ወደ ጽድቅ ጎዳና የማይወስዱት ሰው አውሮፕላኑ በአየር ላይ
ቆመበት ተሣፋሪ ነው፡፡ በየአካባቢያችን የሰው ችግር የሚታያቸው፣ አይተውም ለመፍታት የሚነሡ፤ ፈትተውም ዘምሩልን የማይሉ ክርስቲያኖች
ቢበዙ ኖሮ እነዚህ ሁሉ ችግሮች እየተቆለሉ ባላጎበጡን ነበር፡፡
ኑ ኢየሩሳሌም እንሂድ፤ የወንድሞቻችንን ችግር እንፍታ፡፡ ኑ ኢየሩሳሌም እንሂድ፤ የወገኖቻችንን ጭንቀት እንጋራ፡፡ ኑ
ኢየሩሳሌም እንሂድ፣ መናገር ለማይችሉት አንደበት እንሁን፤ ኑ ኢየሩሳሌም እንሂድ፤ ያፈሩትን ሃፍረት እናስወግድ፤ ኑ ኢየሩሳሌም
እንሂድ፤ የሰዎችን ገደል እንሙላ፣ ኑ ኢየሩሳሌም እንሂድ፤ የሰዎችን ተራራ እናፍልስ፡፡ ኑ ኢየሩሳሌም እንሂድ የሰለሉትን እጆች
እናጽና፤ ኑ ኢየሩሳሌም እንሂድ፣ የዛሉትን ክንዶች እናበርታ፡፡ ኢየሩሳሌም እዚሁ በሠፈራችን ናት፡፡
ኑ ኢየሩሳሌም እንሂድ
እግዚአብሔር ይስጥልን
ReplyDeleteእምነት እንዲህ በምግባር ሲከወን እጅግ ደስ ይላል። የሚደንቀው ደግሞ በዚያን ዘመን የመፀዳጃ ጉድጓድ መኖሩ ነው። በዚህኛ ዘመን ይኸው የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ስለ መፀዳጃ ቤት አጠቃቀምና ሽፋን ወሬ ያደነቁሩናል። በአባቶቻችን ዕውቀት እና ተመክሮን ብንጠቀምበት፥ የምዕተ ዓመቱ ግብ እኛን ባልተመለከተን ነበር።
ReplyDeletedani des yemil timihirt new tebarek!!!
ReplyDeleteplease deacon danel sile ephis koposat ameraert bemimeleket tolo sefi sihf bitisf tekami new.mesfertu,mesfrtu mindinew?
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይስጥህ
Deletea nice view
ReplyDeleteytkedese hasab new dani
ReplyDeleteድንቅ ነው፣አያልቅበት ዳንኤል። መልካም ሥራ እንጂ የሚያጸድቅ መች ኢየሩሳሌም መሄድ ብቻውን። መሄዱንማ ኢአማኒውም ቱሪስት ሁሉ ያደርገዋል።
ReplyDeleteዳንኤል፣ እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜ ይስጥህ።
God Bless You!
ReplyDeleteወንድማችን መምህራችን ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የድንግል ማርያም ልጅ ከነቤተሰብህ ይጠብቅህ።
ReplyDeleteእጅግ በጣም እንወድሃለን የማቱሳላን እድሜ ከሙሉ ጤንነትና ሰላም ጋር ቸሩ መድሐኒዓለም ይስጥህ!
Amen,Amen. Yistilin,ignam mistirun yigletsilin
DeleteThanks Dani your point of view is amazing,it is a good lesson.faith with out kindness is nothing,God gives you a super mind for the purpose of teach us a wonderful lesson. God be with you and your family forever.love you so much.
ReplyDelete"በየአካባቢያችን የሰው ችግር የሚታያቸው፣ አይተውም ለመፍታት የሚነሡ፤ ፈትተውም ዘምሩልን የማይሉ ክርስቲያኖች ቢበዙ ኖሮ እነዚህ ሁሉ ችግሮች እየተቆለሉ ባላጎበጡን ነበር::"
ReplyDeleteእጅግ ድንቅ ነው፣ ቸሩ መድሐኒዓለም ረጅም ዕድሜና ጤንነት ይስጥህ!
ሰላም ዲ/ን ዳኒ :: ምነዉ ብሎግህን ብታሻሽለዉ :: ማለቴ ለምሳሌ ቢያነቧቸዉ ይጠቅማሉ የምትላቸዉን ብሎጎች ጨመር ብታደርግ :: ለነፃ አስተሳሰብ ማደግ ካለህ ብርቱ ትግል አንፃር የዘረዘርካቸዉ በቂ አይደሉም:: መልካሙን ሁሉ ከነቤተሰብህ እመኝልሃለሁ
ReplyDeleteGod bless you.
ReplyDeleteጥሩ ምክር።"ከገባን"
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይባርክህ ዳኒ
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይባርክህ ዳኒ
ReplyDeleteክብሩ ይስፋ ለድንግል ልጅ ለመድኃኔዓለም! አኗኗራችንን በኢየሩሳሌም እንድናደርግ የፃፍክልን መልካም ነው፡፡ ልብ ያለው ልብ ያድርግ ነውና! ከልብ እናመሰግናለን መምሕራችን!!
ReplyDeleteክብሩ ይስፋ ለድንግል ልጅ ለመድኃኔዓለም! አኗኗራችንን በኢየሩሳሌም እንድናደርግ የፃፍክልን መልካም ነው፡፡ ልብ ያለው ልብ ያድርግ ነውና! ከልብ እናመሰግናለን መምሕራችን!!
ReplyDeleteታላቁ መምህር ክቡር ዳያቆን ዳንኤል ክብረት በመጀመሪያ ደረጃ ይህን የረቀቀ የዕውቀት ጥበብ ልዑል እግዚአብሄር ላንት ችሮህ ለኛ እስተማሪ እንድትሆን ችሎታውንና ጊዜውን። ስለሰጠህ የተመሰገነ ይሁን እያልኩ። ከዚህ በፊት ከነበረኝ ዝም ብሎ እንባቢነት ጊዜው ደርሶ እድናቆቴን እንድገልጽ ብርታቱን ለቸረኝ ፈጣሪየ አመሰግናለሁ።
ReplyDeleteላንተም ፈጣሪ ዕድሜና ጤንነት ስጥቶህ የማያልቅ ዕውቀትህን እንድታካፍለን ብርታቱን ይስጥህ እያልኩ ለኔ የምትጽፋቸው አዝናኝ ታሪካዊና ባህላዊ ለነገሮች የምትሰጣቸው ምሳሌያዊ ትምህርቶችህ ከሰወች ጋር ለማደርገዉ መልካም ግንኙነት በር ከፋቾቸ ሲሆኑ የእውቀት እድማሴንም ሰፋ እንዳደርግና ነገሮችን በጥልቅ እንድመለከት ስለረዳኝ አመሰግናለሁ።
Amen Amen Amen kale heyeweten yasemalen
ReplyDelete