Wednesday, June 1, 2016

የበጎ ሰው ሽልማት አራተኛው መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረለሀገርና ለሕዝብ አርአያነት ያለው ታላቅ ተግባር ያከናወኑ ሰዎችን በየዓመቱ ዕውቅና የሚሰጠው የበጎ ሰው ሽልማት አራተኛው መርሐ ግብር ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2008 ዓም በይፋ ተጀምሯል፡፡

የ2008 ዓ.ም ‹‹የበጎ ሰው ሽልማት›› ዘርፎች
 1.   መምህርነት 
 2.  ቅርስ እና ባሕል
 3.   ሳይንስ
 4.  መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣ
 5. ንግድና ሥራ ፈጠራ
 6. ማኅበራዊ ጥናት
 7.  ስፖርት
 8. የበጎ አድራጎት ሥራ
 9. ኪነ ጥበብ - ( በድርሰት ዘርፍ ብቻ
 10. ሚድያ እና ጋዜጠኝነት
የ2008 ዓ.ም ‹‹የበጎ ሰው ሽልማት›› የጥቆማ መስፈርቶች

ጠቅላላ መስፈርቶች
የሚጠቆሙ እጩ በጎ ሰዎች፡-
በየተሰማሩበት ዘርፍ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ መልካም የሚሠሩ፣ ሀገራዊ ተልዕኳቸውን በብቃትና በልዩ ልዕልና የሚወጡ፣ የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ለውጥ አምጭ ተግባር የፈጸሙና የሚፈጽሙ፤ በብዙ ሰዎች የማይደፈርን ተግባር በተነሣሽነት የከወኑ፣ ለድጋፍ ፈላጊ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ትኩረት በመስጠት ሀገራዊ ኃላፊነት ወስደው የሠሩ፣ የሀገሪቱ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባሕል፣ እንዲጠበቅ የሀገሪቱ ሥልጣኔ ከፍ ከፍ እንዲል የሠሩና የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

የሚጠቆሙ እጩ በጎ ሰዎች፡-
ሥራቸው ሀገራዊ ፋይዳ እና ለሌሎች አርአያነት ያለው መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተጠቋሚ በጎ ሰዎች ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሥነ ምግባር ደረጃ ያሟሉ እና አብዛኛው የማኅበረሰብ ክፍል ሊያግባቡ የሚችሉ ሊሆኑ ይገባል፡፡
ከአንደኛው እስከ ሦስተኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብራት የመጨረሻ አምስት እጩዎች ውስጥ ገብተው የነበሩ ‹በጎ ሰዎች› ሊጠቆሙ አይገባም፡፡


 ዝርዝር መስፈርቶች
1.  መምህርነት
በመምህርነት ሙያ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ፣ ተማሪዎችን በዕውቀት ብቻ ሳይሆን በሥነ ምግባርም ለሀገር የሚበጁ አድርገው የሚያሳድጉ፣ ከሌሎች መምህራን በተለየ መልኩ ትምህርትን ለተማሪዎች በሚገባ መልኩ ለማቅረብ የጣሩ፣ በመምህርነት ሙያ ውስጥ አዳዲስ ጥበቦችን ያመጡ፣ መምህርነት በኅብረተሰቡ ዘንድ በመልካም ሰብእና እንዲሳል ያደረጉና በማድረግ ላይ ያሉ በየትኛውም ደረጃ ያሉ መምህራን፡፡

2.  ቅርስ እና ባሕል
ሀገራዊ ዕውቀቶችን በማስተማር፣ ቅርሶችንና ባህልን በማስጠበቅና በመከባከብና በማስተዋወቅ ለውጥ አምጭ ተግባር ያከናወኑ፣ የሀገርን ባሕልና ቅርስ በማጥናትና በልዩ ልዩ ዘዴዎች በመግለጥ እንዲሁም ለቅርስና ባሕል አጥኚና ተንከባካቢ አካላት ልዩ ልዩ ድጋፎችን በማድረግ ሀገራችን ስሟና ክብሯ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅ ያደረጉና የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን፡፡

3. ሳይንስ
በሳይንሱ መስክ ጥናትና ምርምር በማድረግ ችግር ፈቺ የሆኑ አዳዳሲ እውቀቶችን ለሀገር ያበረከቱ፣ ሳይንሳዊ እውቀት በሀገር እንዲስፋፋ ማኅበራትን በማቋቋም፣ ትምህርትና ሥልጠና በመስጠት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማበርከት፣ በሙያ ዘርፉ ከተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ልቆ የሚታይ ተግባር ያከናወኑ፡፡

4. መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት
በሕግ አውጪ፣ ተርጓሚና አስፈጻሚ ተሹመው ወይም ተመድበው የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ያሻሻሉ፣ ዜጎች በጎነታቸውን የሚመሰክሩላቸው፣ የመንግሥት ሹመት ሥልጣን ሳይሆን ኃላፊነት መሆኑን በተግባር ያሳዩ፣ አስቸጋሪ በሆኑ የሥራ አካባቢዎች ተሰማርተው አመርቂ ውጤት ያስመዘገቡ፣ ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ መንግሥታዊ አሠራሮችን ያስተዋወቁ፣ ኢትዮጵያውያን፡፡

5. ንግድና ሥራ ፈጠራ
ለሀገር ጠቃሚ አዳዲስ የንግድ አሠራርን ለሀገር ያስተዋወቁ፣ ነባሩን የንግድ ሥራ በተለየ መልኩ በማከናወን ውጤት ያመጡ፣ በተሰማሩበት የሥራ መስክ ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል የፈጠሩ ሌሎችም የእነሱን መንገድ እንዲከተሉ በማበረታታት ትርጉም ያለው ሥራ የሰሩ፣ ለአገር ጠቃሚ የሆኑ  አዳዲስ የንግድ ሥራዎችን በሀገር ያላመዱ፣ የንግድ ሥራቸውን በሚያከናውኑበት አካባቢ ለሚኖሩ ዜጎች ጠቃሚ ተግባራትን ያከናወኑ ኢትዮጵያውያን፡፡
6. ማኅበራዊ ጥናት
በማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ የተደበቁ አገራዊ እውቀቶችን ያስተዋወቁ፣ ለሀገር ሰላም ለሕዝቦች መቀራረብና መደጋገፍ ለውጥ አምጭ አስተዋጽዖ ያላቸው ጥናቶችን ያከናወኑ፣ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ችግር ፈቺ ጥናቶችን ያከናወኑ ጥናት የሚያደርጉ አካላትን የሚደግፉ፣ ማኅበራዊ ጥናት እንደ ባሕል እንዲዳብር ተቋማትን በመመስት ትምህርትና ሥልጠና በመስጠት አስተዋጽዖ ያበረከቱ ኢትዮጵያውያን፡፡ 
7. ስፖርት
በፌዴሬሽን አመራርነት ስፖርተኝነት አሰልጣኝነት የቴክኒክ ባለሙያነት እና በሌሎች የስፖርት ዘርፍ ተግባራት ላይ የተሰማሩ የተበላሹ የፌዴሬሽን አሰራሮች እንዲሻሻሉ ያላሰለሰ ጥረት ያደረጉ፣ ስፖርት እንደ ባሕል በኅብረተሰቡ ዘንድ እንዲዳብር መልካም ተግባራትን ያከናወኑ፣ የአገራችንን ስፖርት በገንዘባቸውና በዕውቀታቸው የሚደግፉ፣ የጨዋ ደጋፊነት ባሕል በየስታዲየሞቹ እንዲጎለምስ የሚሠሩ፣ በአጠቃላይ በሁሉም የስፖርት ዘርፍ ሀገራችን በዓለም መድረክ ከፍ ብላ እንድትታይ የደከሙ  ኢትዮጵያውያን፣

8. የበጎ አድራጎት ሥራዎች
በበጎ አድራጎትና ሰብአዊ ተግባራት ተሠማርተው የሰው ልጅን ሕይወት የለወጡ፣ የበጎ አድራጎት ሥራ ሌሎች የሚረዱበት እንጂ የራስ ኑሮ የሚደጎምበት አለመሆኑን በተግባር የገለጹ፣ ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባሕል እንዲያዳብሩ የሰሩ ኢትዮጵያውያን፡፡
9. ኪነ ጥበብ - ድርሰት(በዚህ ዓመት ከኪነ ጥበብ ዘርፍ የተመረጠው የድርሰት ዘርፍ ነው)
የድርሰት ጥበብ እንዲዳብር በጎ የሠሩ ደራስያን፣ አሳታሚዎች፣ ሀያሲዎች፣ መጻሕፍት አዟሪዎች፣ ኢትዮጵያውያን፡፡

10.       ሚድያ እና ጋዜጠኝነት
በኅትመት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ በብሮድካስትና ሌሎች ሚዲያ ዘርፎች ተሰማርተው ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ እውቀቶችን በማስፋፋት የሰሩ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ተቋማት፡፡

የ2008 ዓ.ም ‹‹የበጎ ሰው ሽልማት›› የጥቆማ ቀናት
 
የእጩ በጎ ሰዎች ጥቆማ ከግንቦት 24 ጠዋት 12፡00 እስከ ሰኔ 24 ማታ 12፡00 ድረስ ይከናወናል፡፡
 
የ2008 ዓ.ም ‹‹የበጎ ሰው ሽልማት›› የጥቆማ መንገዶች
በስልክ 0915 445555
በግንባር ለም ሆቴል ማትያስ ሕንጻ ቢሮ ቁ.408
                በፖስታ  150035 አዲስ አበባ
 በብሎግ www.daneilkibret.com
                በኢሜይል begosew2008@gmail.com
በቫይበር 0915 445555
በጎ ሠሪዎችን በማክበርና በመሸለም ሌሎች በጎ ሠሪዎችን እናፍራ!!

8 comments:

 1. Hi dani why don't u write about maiber kidusan exbision it has been open 3 day's ago.

  ReplyDelete
 2. http://video.ethsat.com/?p=24539
  Rahel yemitibal ethiopian tegogiwochin yemitireda yebego adiragot teshelami bitihon

  ReplyDelete
 3. I was expecting u with yr family in the 5 th Exihibition that u were fighting to make it happen.
  But......

  ReplyDelete
 4. To start with I would like to thank you for your service both for your country and the Church.
  Regarding ‹‹የበጎ ሰው ሽልማት››, I have always asked myself why the categories listed above doesn't include Politicians instead of መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣ , because this way it includes both people having a an administrative role as well as those politicians trying so hard and scarifying their life for the greater good,for their people. Let me ask you a simple questions. If I am about to present a nominee and came up with a name Dr. Merera Gudina, in which category should I present him? you might say መምህርነት but the Doctor's influence through politics is much greater than than he being an educator,although I am sure he would still be a great candidate for that category too!
  So, you Dn. Daniel and Co. should come up with a relevant Category and Include Dr. Merera Gudina, formerly professor of AAU, greatest politician, a true tolerance preacher and public speaker as your nominee and candidate for this years ‹‹የበጎ ሰው ሽልማት››

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hi Teddy , I love your idea but you have to see our country democracy. This program just start, it has only a few years so if Daniel pick some people form government opposition party, the current government immediately stop the program. If you remember last year, because of government Daniel change the meeting place at last time. In addition that after Daniel starts this program the Ethiopian government start the same program with different name. I gave you the above example how it is difficult to practice democracy in Ethiopia. They want to control everything with government. We have to pray for them because they don’t know they will die tomorrow.

   Delete
  2. Hi "Anonymous", lol .... I understand your concerns and fear but, this is a matter of public recognition and people who deserve to be recognized shouldn't be excluded in fear of making the so called government angry! it is about the credibility of the Campaign. After all, Ethiopia is the one nominating and giving the recognition. I say it is time to challenge any obstacle if any!Another simple question is , will the government go bad if Dr. Merera Gudina is nominated for the ‹‹መምህርነት›› Category? if so, what is the point to all of this since it will technically be the government picking and giving ‹‹ሽልማት›› !
   Well, sooner or later, we will see what is gonna happen!

   Delete
 5. Why don't you write instead of telling him to write your interest. He is doing a great job, because of him MK got permission to reopen. Everybody know the exhibition has been open so what is the different if he write or not. Shame on you.

  ReplyDelete
 6. I am sorry u got it all wrong i did't ask my interest I was rifering for those Who are abrode including me, he may tell us ditel information, as he always that is it.

  ReplyDelete