Tuesday, May 31, 2016

‹እኛና መንፈስ ቅዱስ› ማለት ሊቀር ነውን?

ቅዱስ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን እንደራሴ ሹመት በተመለከተ ለመወያት የያዘው አጀንዳ የመንግሥት ተወካይ ባለበት እንዲታይ መወሰኑን ዛሬ ጠዋት ሰማን፡፡ ከብጹዐን ጳጳሳት በቀር ካህናትና ቆሞሳት እንኳን የማይገቡበት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አማኝ ይሁን ኢአማኒ፣ ሙስሊም ይሁን ክርስቲያን የማይታወቅ የመንግሥት ተወካይ እንዲገኝበት መጋበዙ የደረስንበትን የውርደት ደረጃ የሚያሳየን ነው፡፡
በአንድ በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ወሳኝ አካል መሆኑን ስናስበው፤ በሌላ በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሚደረገው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ነው፤ ውሳኔውም በሐዋርያት ሥራ እንደተገለጠው ‹እኛና መንፈስ ቅዱስ› የሚባልበት ነው(የሐዋ. 15፣29) የሚለውን ስናየው ‹የመንግሥት ተወካይ ይኑርልን› የሚለውን ውሳኔ ኢሃይማኖታዊ ነው ያሰኘዋል፡፡ ለአንድ የሲኖዶስ ጉባኤ የመንፈስ ቅዱስ መገኘት አልበቃው ብሎ ነው የመንግሥትን ተወካይ የሚጋብዘው? ‹ሱባኤ ይዘን፣ ጸሎት አድርገን፤ አንድ ገዳም ወርደን፣ ከእግዚአብሔር ጋር መክረን› አይደለም ይሉን አባቶቻችን፡፡ ‹የመንግሥትን ተወካይ ጋብዘን› ነው ያሉን፡፡ እንዲያውም ቀኖናው የሊቀ ጳጳሳቱ(ፓትርያርኩ) ጉዳይ ሲታይ ‹በመቀመጫቸው መካከል አንድ ወንበር አስቀምጠው፣ ቅዱስ ወንጌሉን በዚያ ላይ አኑረው፣ ሊቀ ጳጳሳቱ በፊታቸው ተቀምጦ፣ አንድነት ተነሥተው በሩን ዘግተው ይጸልዩ፤ የተሰበሰቡበትንም ጉዳይ በሥውር(በኅቡእ) ይመርምሩ› ነው የሚለው(ፍ.ነ. ዐ.168)፡፡ እንዴት ተደርጎ ነው የመንግሥት ተወካይ ባለበት የሚታየው? አግዚአብሔር ያየናል የሚለው ጠፍቶ ታዛቢ ቢያስፈልግ እንኳን የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ለታዛቢነት አይበቁም? ቅዱስ ጳውሎስ ‹በወንድሞች መካከል ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን?› (1ኛቆሮ. 6፣5) ያለው ለዚህ ጊዜ አይሆነንም?

በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ የመንግሥት ተወካይ እንዲገኝ መጋበዙ በአንድ በኩል የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና የሚነካ በሌላ በኩልም ሕገ መንግሥቱን የሚጥስ፤ በመጨረሻም ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚያፈርስ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያለ ማንም ጣልቃ ገብነትና ታዛቢነት የራስዋን ጉዳዮች በራስዋ ሕግጋት፣ ቀኖናና ሥርዓት መሠረት የመወሰን መብት አላት፡፡ አባቶቻችን ከንጉሥ ሐርቤ ዘመን ጀምረው ከግብጽ ሲኖዶስ ጋር ሲሟገቱ የኖሩት ይህን ሉዐላዊነት ለቤተ ክርስቲያናቸው ለማስገኘት ነው፡፡ ጳጳሳትን ለማግኘት የግብጽ ሡልጣኖች መለማመጥ፣ የግብጽንም ፓትርያርኮች መለመን ሰልችቷቸው፡፡ ከግብጽ ቀድማ ክርስትናና የተቀበለች ሀገር፣ የራስዋን ጉዳይ ለመወሰን አለመቻሏ አስደናቂ ስለሆነባቸው፡፡ ከቤተ ክርስቲያንዋ ታላቅነትና ከሀገሪቱ ክብር ጋር ስላልተመጣጠነላቸው፡፡
ዛሬ ያ ሁሉ ተረስቶ መንግሥትን በገዛ ፈቃዳቸው ‹አንተ በመካከላችን ካልተገኘህ አንሰበሰብም› የሚሉ አባቶች መጡ፡፡ ቀደምት አበው ‹አንተ ከኛ ጋር ሁን› የሚሉት ፈጣሪያቸው ነበር፡፡ ዘመን ተቀየረ፡፡ በቀደመው ጊዜ ‹መንግሥት ለምን በጉዳያችን ውስጥ ይገባል?› ነበር ክርክሩ፡፡ ‹አሁን መንግሥት ከሌለ ይህንን አጀንዳ አናይም› የሚባልበት ዘመን ላይ ደረስን፡፡ የፓትርያርክ እንደራሴ ጉዳይ የሃይማኖት ጉዳይ ነው፡፡ እንደራሴውም የሚፈጽመው ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን ነው፡፡ የሥልጣን ክልሉም በቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን ክልል ነው፡፡ ታድያ ለምንድን ነው መንግሥት ያስፈለገው? ይህንን ጥያቄ ፓትርያርኩ ጠይቀውት ይሆናል፡፡ እንደመከራከሪያ ቢያቀርቡት አይገርምም፤ ቢያሳዝንም፡፡ የምልዐተ ጉባኤው መቀበል ግን ሕመም ነው፡፡
መንግሥትስ ቢሆን ምን ብሎ ነው ተወካይ የሚልከው? ምናልባት ‹ጠሩኝ፣ ሄድኩ› ካላለ በቀር፡፡ ሕገ መንግሥታችን መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ በግልጽ እየደነገገ እንዴት አድርጎ ነው በቀኖናዊ ስብሰባ ላይ የሚገኘው? ውሳኔውንስ ከየትኞቹ የቀኖና መጻሕፍት ጋር ሊያገናዝብ ነው? በጉባኤው የሚኖረውስ ሚና ምን ሊሆን ነው? ምን ዓይነት ወኪልስ ነው የሚወክለው? በየትኛው ሥልጣንና ሕግ ነው የሚገኘው? የዚህ ዓይነቱ አሠራርስ መጨረሻው ምን ይሆናል? በጉባኤው ላይ የሚተላለፈው ውሳኔ የማን ውሳኔ ነው? ‹የእኛና መንፈስ ቅዱስ› ወይስ ‹የእኛና የመንግሥት›? መንግሥትም ጉዳዩን ሊያስብበት ይገባል፤ ‹ሲጠሩት አቤት› ሳይሆን ‹ሲጠሩት ለምን?› መሆን አለበት፡፡
የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ኤጲስ ቆጶስ በዚህ ዓለም መኳንንት ርዳታ አንዳይቆም ያዝዛል፡፡ በእምነቱና በእግዚአብሔር ቃል ብቻ እንዲጸና፡፡ (ፍትሐ ነገሥት፣ 176፤ረስጠብ 21) በዲድስቅልያም ላይ ‹ከቤተ ክርስቲያን ሹሞች በቀር ሕዝባዊ አይፍረድ› ይላል (ዐንቀጽ 71)፡፡ ታድያ በምን ሕግ ነው የመንግሥት ተወካይ ባለበት የቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤውን የሚያደርገው?
ዛሬ እንደዋዛ የሚከፈተው በር ነገ እንዝጋህ ቢሉት አስቸጋሪ ነው፡፡ አንድ አባት የመንግሥት ተወካይ ይገኝልኝ ባለ ቁጥር የሚፈቀድ ከሆነ፤ ነገ ደግሞ ወንድሜ ባለበት፤ እናቴ ባለችበት፤ ሐኪሜ ባለበት፣ ፖሊስ በተገኘበት ይሄ አጀንዳ ይታይ የሚል ነገር መስማታችን አይቀሬ ነው፡፡ ጋባዡም፤ ተጋባዡም ቆመው ሊያስቡበት ይገባል፡፡ መቼም እንደዘንድሮ የእንጦንስና ጳውሊ ራእይ በተግባር የታየበት ዘመን የለም፡፡

51 comments:

 1. yemigerm new min eyetesera enidehone ayitawokim malet new?

  ReplyDelete
 2. ይህ አስደናቂ መልእክት በታሪክ የሜቀመጥ ነው ። እኔህ አባት ባይገባቸው ነው። ጾሎት ለመጸለያ ፣መጽሐፍ ለማንበብ፣ብሎም ያላስተዋሉትን የሜያስተውል መነፀር ቤታከል ይበጃቸው ነበር። ማስተዋሉን ይስጥልን ።

  ReplyDelete
 3. Be egna ena menifeskidus egna ena mengisit siteka. Mengisit be hawariat gubae sitera ...begeta metamen ersun mefrat yet hede.kibir lehawariawit betekiristian(eotc)

  ReplyDelete
 4. በመንፈስ ቅዱስ እንደተመረጠ የሚያምን መንፈስ ቅዱስ በርሱ አድሮ ሥራ እንደሚሠራ ያዉቃል፡፡ በምድራዊ ኃይል የተመረጠ፤ በምድራዊ ኃይል የሚተማመን የተሰጠዉ ምድራዊ ተልዕኮ እንዳይሰናከል ምድራዊዉን ኃይል ተማክሮ ቢሰራ አይደንቅም፡፡ ለኛ ለምዕመናን ግን ቸርነቱ እንዲበዛልን፡ እረኞቻችን እንደበተኑን ጌታም ለተኩላዎቹ አሳልፎ አንዳይሰጠን ጸሎት፡ የሚጸልዩልን ቅዱሳን ያስፈልጉናል፡፡

  ReplyDelete
 5. የከሸፈ ትውልድ ማለት ታዳ ይህ አደለምን!!ሁሉን አሜን ብሎ የሚቀበል!!

  ReplyDelete
 6. እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ

  ReplyDelete
 7. Abune Mathias got this position because of government without God help, so he doesn’t know God or Ethiopian Orthodox Church’s rule and regulation. He knows very well if the current government loses the power, he will lose his position. He works hard to destroy our church and unity.

  ReplyDelete
 8. You said it before ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት. We don’t expect chicken from snake egg. Abune Mathias is big snake, he work hard to bring 666 in our church.

  ReplyDelete
 9. Egziabher Le abatochachin Libona Yistilin!!!

  ReplyDelete
 10. Hi Daniel thank you so much. It is bad time for all us. I live in USA when I go church all the priest teach us or tell us against the bible. They don’t care about human being, they work day and time to get money. It is time to pray each other not criticize. They don’t know what are they doing or said.

  ReplyDelete
 11. Egziabher Hoya Ethiopian asbat.

  ReplyDelete
 12. Egziabher Hoya Ethiopian asbat.

  ReplyDelete
 13. እግዚአብሄር አምላክ ሆይ እባክህ ለአባቶቻችን ቤተ ክርስቲያንን የሚመሩበት ጥበብን ስጥልን። መንግስትንም አስታግስልን።ግን ወንድሞቸ እና እህቶቸ አይዟችሁ እግዚአብሄር ቀን አለው በፀሎት ትጉ።

  ReplyDelete
 14. እግዚኦ የሚያሰኝ ነው። ፈጣሪ በኪነ ጥበቡ ይህን አፍራሽ አደፍራሽ ሃሳብ አርቆ በጎውንና የተቀደሰውን መንፈስ ያስፍንልን።

  ReplyDelete
 15. መቼም እንደዘንድሮ የእንጦንስና ጳውሊ ራእይ በተግባር የታየበት ዘመን የለም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ድሮ “መነኮሰ ሞተ” ነበር አሁን ግን “መነኮሰ በላ” ሆኗል፡፡

   Delete
 16. ለአንድ የሲኖዶስ ጉባኤ የመንፈስ ቅዱስ መገኘት አልበቃው ብሎ ነው የመንግሥትን ተወካይ የሚጋብዘው?በእውነት ከዚህ በላይ የሚያሳዝን ነገር ምን ሊኖር ይችላል?ቤተ ክርስቲያን ስንዱ እመቤት ናት የሚጎድላት ነገር የለም፤ ተብሎ በተሰበከበት አንደበት ወረቀት ላይ በቀረው ዲሞክራሲ ወንበር ላይ ፊጥ ካሉ ባለስልጥናት ድጋፍ ፈለገች ቢባል ማን ያምናል?

  ReplyDelete
  Replies
  1. በጣም ነው ያዘንኩት ግን ሁሌ አዝነን ብቻ ዝም ማለት እስከመቼ?? አሁን ሁሉን ሰማን ምን ማድረግ አነብን ወደ ሚነው ነው መጋዝ ያለብን፡፡ ምን ማድረግ አነብን?? እውነት ነው እግዚአብሔር ህኒና ይስጣቸው ማለት አንድ ነገር ነው፡፡ ግን ይህን ሳንክድ ህሊና የሚሰጥበት መንገድ እኛ ከሆንስ፤ለምን ሰላማዊ ሰልፍ አንወጣም?? ማን ይከለክለናል?? ለነገሩ ወያኔው እያለ እንዴት አንከልከል? አባቶች እኮ ኤሊን ከሆኑ ስንት ዘመናቸው፤እኛ ደግሞ ሁሌም ዝም በእነርሱ ሓጥያት ህዝቡ እኮ ቅድስናን አጣ፡፡ እባክህ ዲያቆን ዳንኤል የሆነ መንገድማ መኖር አለበት ጽሑፍ ከመጻፍ ያለፈ፡፡ ማን ይሆን ሙሴ?? ሙሴ ናፈቀኝ፤ኢያሱም፤እነ ሳሙኤል የት ናችሁ?? ቅዱስ ጊዮርጊስ እባክህ ፈረስህን ይዘህ ተነስ ተነስ ተነስ፡፡

   Delete
 17. አረ ቆም ብለን እናሰብ

  ReplyDelete
 18. ጋባዡም፤ ተጋባዡም ቆመው ሊያስቡበት ይገባል፡፡ መቼም እንደዘንድሮ የእንጦንስና ጳውሊ ራእይ በተግባር የታየበት ዘመን የለም፡፡

  ReplyDelete
 19. በጉባኤው ላይ የሚተላለፈው ውሳኔ የማን ውሳኔ ነው? ‹የእኛና መንፈስ ቅዱስ› ወይስ ‹የእኛና የመንግሥት›? መንግሥትም ጉዳዩን ሊያስብበት ይገባል፤ ‹ሲጠሩት አቤት› ሳይሆን ‹ሲጠሩት ለምን?› መሆን አለበት፡፡

  ReplyDelete
 20. አይ ዲ/ን ዳኒዬ፣ ታዲያ መንግሥት ያስቀመጠው ሰው ማንን እንዲጠራ ትጠብቃለህ? ፓትርያሪኩ እኮ በእግዚአብሔር ተሸመው ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ይግባበት ይሉ ነበር፣ ለሾሙአቸው ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሕግ ይገዙ ነበር፤ እሺ አባቶቼ፣ ወንድሞቼ፣ እንደ ቃላችሁ ይሉ ነበር፡፡ እርሳቸው ግን የሾማቸውን ስለሚያውቁት፣ ኃይል አለኝ፣ ኃይል እጠቀማለሁ፣ እምቢ ብለው ቤተ ክርስቲያኒቱን ሊያፈርሷት ሲነሱ ሌሎች አባቶች ምን ያድርጉ? እግዚአብሔር ሊሰራበት ያዘጋጀው ሰው አልሰራ ሲል እኮ በማንኛውም ፍጥረቱ ላይ አድሮ መሥራት ያውቅበታል፡፡ ከነቢዩ በልዓም ይልቅ የተቀመጠባት አህያ መልአኩን እንዳየች ታውቀው የለ? ሕጉ እማ ከተጣሰ እኮ ቆየ፣ አሁን በየትም ብሎ በየት እግዚአብሔር ይምረን እንደሆነ እርሱን መጠባበቅ ነው እንጂ፣ በሕጉ፣ በልዕልናው፣ በደንቡ ወዘተ ማለት የምንችልበት ደረጃ ላይ አይደለንም፡፡ አምላከ ቅዱሳን አቤቱ አይኖቻችን ዘወትር ወዳንተ ናቸውና ቸል አትበለን፤ አሜን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውነት ነው። የጥፋት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ይሆናል የተባለው እኮ ኣንድ ባንድ እየተፈጽመ ነው። ጥፋትም ከቤታችን። ኢትዮጵያችንም በብዙ ነገር ተከባለች። እርሱ የምህረት ኣምላክ ያስበን እንጂ እኮ ያለው ነገር እጅግ የሚያሳስብ የሚያስጨንቅ ነው። ከበላይ ሆነው የሚያስጨንቁን መብዛታቸው በእኛም መሃል የሚያስቀጣን ነገር በመብዛቱ ነው። እንግዲ እሱ እግዚአሔር ይማረን።

   Delete
  2. እውነት ነው። የጥፋት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ይሆናል የተባለው እኮ ኣንድ ባንድ እየተፈጽመ ነው። ጥፋትም ከቤታችን። ኢትዮጵያችንም በብዙ ነገር ተከባለች። እርሱ የምህረት ኣምላክ ያስበን እንጂ እኮ ያለው ነገር እጅግ የሚያሳስብ የሚያስጨንቅ ነው። ከበላይ ሆነው የሚያስጨንቁን መብዛታቸው በእኛም መሃል የሚያስቀጣን ነገር በመብዛቱ ነው። እንግዲ እሱ እግዚአሔር ይማረን።

   Delete
 21. Bewunt zemenachin eyekefa new man endemitamen enkua eyekebede new kelay bemerint yalu abatochachin menfes kidusn sayteru mengistn yemigabzu kehone betam kebad new yemenfeskidus sayhon Yemengist kadrewoch wusane betekrstiyann yemimerabet zemen yasaznal kidusan hawariyat beneberubet menber lay endih yalu abatoch metekatachewu bewunet yeseyitan sira liko endemitay begltse yetayebt yesinodos gubae egziabher libon yisten yistln yemnadergewun endnawuk.....kale hiwot yasemaln

  ReplyDelete
 22. የዝቅጠት መጨረሻ
  ቅዱስ ሲኖዶስ በስጋዊ ሀሳብ እንጂ
  በመንፈስ ቅዱስ አለመመራት…በእውነት ያማል፡፡

  ReplyDelete
 23. What if the Patriarch has refused to accept the solution "እኛና መንፈስ ቅዱስ" and the Sinod members wisely planned to show the government how the Patriarch is behaving against the Churche's rules and regulations, then the Sinod to decide the Patriarch to resign? I am feeling this.

  ReplyDelete
 24. የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ከተበላሸ እኮ ቆየ፡፡ የተወገዘ እና ተሐድሶ የሆነ ሰው ፓትርያሪክ ሆኖ ሢሾም፡፡ "የአሊሚኒቲ" ተከታይ የሆኑት እኒህ "ፓትርያሪክ" ገና ብዙ ጥፋት ያመጣሉ፡፡ በራሳቸው የማይተማመኑ የጥፋት ልጅ ናቸው፣ አባት ሊባሉ አይገባቸውም፡፡ ዘመዶቻቸውን፣ ተሐድሶዎችንና የወንድሞቻቸውን ደም ሲያፈሱ የነበሩትን የቀድሞ ተጋዳዮችን የክህነት ማዕረግ ቀርቶ ክህነት በሚሰጥበት ደጅ አልፈው የማያውቁ ግለሰቦች ዘር ተቆጥሮ በማይገባቸው የቤተ ክርስቲያን የሥልጣን ማዕረግ ላይ ተቀምጠው ፈላጭ ቆራጭ ሆነው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከሕዝብና ከቤተ ክርስቲያኒቱ በማን አለብኝነት እየዘረፉ ሀብታሞች ሆነዋል፡፡ ምን ያድርጉ ሰው እና ሀገር የሚያድን ወንድ ሲያጡ፡፡ ለምሳሌ የቀድሞው የትግርኛ ቋንቋ የቴሌቭዥን ፕሮግራም አቅራቢ የነበረው አቶ የማነ ዘመንፈስቅዱስ ሳይገባው የአባ ማትያስ ጎሳ ተወላጅ ስለሆነ ብቻ በሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅነት ተቀምጦ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ሀብትና ገንዘብ ዘርፎ ምንሕጋዊ እርምጃ ተወሰደበት? ምንም፡፡ ዱሮስ "አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ" አይደል የሚባለዉ? ለጊዜው ከቦታው ላይ ዘወር አድርገው አስቀምጠውታል፡፡ከዚህ የዘለለ ምን እርምጃ ተወሰደ? የቀድሞው ታጋይ ሟቹ አባ ጳውሎስም ቢሆኑ የክፋት እና የጥፋት ልጅ ተላላኪ ሆነው ነበር ሲሰሩ የኖሩት፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካን አገር ነዋሪ በነበሩበት ጊዜ ከትግራይ ተወላጆች እና ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ ከሚፈልጉ ሀገሮች እንደ ግብፅ እና ሱዳን ከመሳሰሉት ገንዘብ በማሰባሰብ ሕወሀትን በደንብ አድርገው ሲረዱ ነበር፡፡ ለዚህም ታላቅ ውለታ ሕወሀት በለስ ሲቀናው ወንበር ላይ አስቀመጣቸው፡፡ ቢዮንሴ የምትባለው ዘፋኝ ኢትዮጵያ በመጣችበት ወቅትም ቢሆን ካሕናቱን በማስገደድ ልብሰ ተክሕኖ አስለብሰው ታቦት እና ንዋየ ቅዱሳት በማስወጣት አጅበዋታል፡፡ ከዚህ በላይ ውርደት እና መናቅ አለ? ለዚያውም ዘፋኝ እና የ"አሊሚኒቲ/ሰይጣኒዝም አማኝ ለሆነች ግለሰብ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም ቢሆን ስሙን ተሸከመ እንጂ ጥርስ የሌለው አንበሳ ከሆነ ፳፭ ዓመታትን አስቆጠረ፡፡ እንዲያውም የትግራይ ተወላጆች ፓርላማ ቢሉት ይሻላል፡፡ መንፈሳዊነቱን ለቋል፡፡ውሳኔ ተወሰነም አልተወሰነ ምን እርባና አለው፣ በአባ ማትያስ አምባገነናዊ ውሳኔ ይሻራል፡፡ አሁን ደግሞ ብለው ብለው በንቀትና ድፍረት እምነቱ የማወቅ ቅድስና የሌለው የመንግሥት ተወካይ ጋበዙልን፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትስ እስከ መቼ ፈርተው ሊኖሩ ነው? ሲመነኩሱ ሁሉን ንቀው እስከ ሞት ለእግዚአብሔር ታምነው አይደለምን? ወይንስ የሕወሀትን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኑ? እንደዚህ ከሆኑ ወደ ለየለት የሕወሀት ፓርላማ ይቀላቀሉ ፣ምስጋና ይግባውና በመንፈስ ቅዱስ ስም ከማጭበርበር ይጠንቀቁ፡፡ አንዱ የጥፋት ልጅ ጎግ ማንጎግ የሆነው ሽማግሌው ስብኀት ነጋ የኦርቶዶክስን አከርካሪውን ሰብረነዋል ብሎ የለም እንዴ? መቼ ይሆን እግዚአብሔር ከስብራታችን ደሚፈውሰን? ቸር ያሰማን!

  ReplyDelete
 25. Hailemariam BezabihJune 2, 2016 at 2:23 AM

  ፓትርያርኩ መነኩሴ መሆናቸውን እረስተው ጭልጥ ባለ ዓለማዊ አሰራር ተጠልፈው የወደቁ ይመስለኛል

  ReplyDelete
 26. በጣም የሚያሳዝን እና የሚያስለቅስ ነው::
  ለፖለቲካው ቢያቅተን ቤተክርስትያናችንን ግን አሳልፈን መስጠት እንደሌለብን ይሰማኛል::
  ለዚህ ግንባር ቀደም ማን ይሁን?
  አዎን “ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፏል እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት” ተብለን ሳንበተን አስቸኳይ ምላሽ የሚያሻው የሁላችንም ጥያቄ ነው::
  እኔ ማህበራችን ማህበረ ቅዱሳን ሰፊውን ድርሻ ተረካቢ መሆን አለበት ባይ ነኝ::
  thank you diaqon dani

  ReplyDelete
 27. ርኩስ ፥ ቅዱስ በሆነበት፤ አገርና ዘመን የሚጠበቀው ነው እየሆነ ያለው። የሚገርመው ተቃራኒው ቢሆን ነበር። የማይገርመው፥ የሚገርምበት አገር፥ ኢትዮጵያ።

  ተስፋዬ

  ReplyDelete
 28. ውድ ወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምታወጣቸው ጦማሮች ዕውቀት አዘል መንፈሳዊ እና ዓለማዊ ልሳኖችን የያዙና ትምህርት ሰጪዎች ናቸው።ሆኖም ትራክተር ኖሮህ የጓሮ አትክልት እንደሚያርስ ገበሬ ሆንክብኝ።ምነው ዲያቆን እንደዚህ የሰላና በጥናት ላይ የተደገፉ ጽሁፎችን ማቅረብ እየቻልክ ፤ብዕርህን ለምን የጓሮ አትክልት ትቆፍርበታለህ።ውጣና ማሳው ላይ በትራክተርህ ለጉጅሌው እጅህን አሳየው፤አሳየው፤በሕዝብ ትከበርበታለህ፥በተለይም ውሸቱን ውሸት፣ዕውነቱን ደግሞ ዕውነት ብለህ አቀናጅተህ ስትጦምር።አለበለዚያ አንተ የተረጎምከው ይሄ ጦማር የተባለ የጓሮ አትክልት ነው፤አልሰሜ ካላሰኘህ።መረጃውንም እያንዳንዱን እንድታይ አያይዤልሃለውና ተመልከተው፤እትዬ ሸዋዬን ሰላም በልልኝ፤ግጥም ትወዳለህና በእርሷ ልሰናበትህ።

  የማቴዎስ ወንጌል ፳፬፥፲፭
  እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል::
  [-[-[-[-[- ባንዳ ላይ ይትፉና። ]-]-]-]-]-]
  ድንጋይ ያቀበሉ ስንሞት ትናንትና:-

  እስኪ ዛሬ ያሳዩን ባንዳ ላይ ይትፉና::

  ቀረ'ኮ ይሉኝታ ቀረ'ኮ መደበቅ፤

  በጉጅሌ ጉያ ሕዝብ ላይ መሳለቅ።

  ሕሊናቸው ትናንት የተጨማለቀ፤

  ምን እንዳደረጉን ሕዝቡ እያወቀ፤

  ዛሬም እነሱን አይተው የሚጨማለቁ፤

  የሕዝብ እንዲሆኑ እውነቱን እንዲያውቁ፤

  ድንጋይ ያቀበሉ ስንሞት ትናንትና፤

  እስኪ ዛሬ ያሳዩን፤

  ባንዳ ላይ ይትፉና።

  እሰዬና አሰፋ ያ ታምራት ላይኔ፤

  በዚያ ግድያቸው ሳይገቡ ኩነኔ፤

  ይቅርታን ነፍገው ሕዝብን እንደናቁ፤

  ስናውቃቸው እኛ ወዴት ተደበቁ?????

  ኃይሌ ገብረ-ሥላሴስ ለወቸገል መለስ፤

  ያውም ባደባባይ የሕዝብን ሥም በማርከስ፤

  የኢትዮጵያን ንብረት እንደግሉ የሰጠው፤

  ሙታን ሊፋረዱት ቀን ነው የሚጠብቀው።

  ግና ያ ሕዝብን የካደ ይቅር ትናንትና፤

  እስኪ ዛሬ ያሳየን

  ባንዳ ላይ ይትፋና።

  ReplyDelete
 29. ኢትዮጵያውያንን ለመግደልና ለመፍጀት ለፋሽቱ የኢጣሊያን ፋሽስት ወራሪ ጦር የመርዝ ጭስ የሚተፋ ጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያን በ"መስቀል" ባርከዉ የላኩትን የካቶሊክ ቫቲካን "ቤተ ክርስቲያን" አባ ማትያስ ሄደው "አኛና እናንተ አንድ ነን አብረንም እንሰራለን" ብለው የ"ቅዱስነታቸውን" የቡራኬ ድምፅ በቫቲካን ማሰማታቸው ይታወቃል፡፡ ይህ የጀግኖች አባቶቻችንን የሰማዕትነትን ተጋድሎ መካድ እና ለጠላት መንበርከክ ነው፡፡ ቫቲካን ለፈፀመችው ወንጀል አንድም ቀን እስከ አሁን ድረስ ይቅርታ ኢትዮጵያን ጠይቃ አታውቅም፡፡ እኒህ ሰው አባ ሜትያስ ኢትዮጵያዊነታቸውን በአሜሪካዊ ዜግነት ስለቀየሩ፣ ምን አልባትም እኔም ምዕራባዊ ነኝ ማለታቸው ይሆን? ኢትዮጵያ ሆይ "እልል በይ" አሜሪካዊ ፓትርያሪክ ሕወሀት አምጥቶልሻል!!! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን መቼ ነው ከነ አርዮስ እና ንስጥሮስ ጋር አንድ ሆና የምታውቀው? እኒህ ሰው የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ በዓለም መድረክ ሳይማሩ ነው እንዴ እንደ ዘመዶቻቸው ሥልጣን ላይ የወጡት? እባካችሁ በቅርብ ያላችሁ በመኝታ ሰዓታቸው(bed time) አንብቡላቸው ለኝህ "ቅዱስ ካቶሊክ ፓትርያሪክ፡፡" ዲ|ን ዳንኤልስ ምን ትላለህ? ዜግነቱን የቀየረ "ፓትርያሪክ ቢሆን ችግር የለውም" ማለትህን ከቃለ ምልልስ ላይ አይቻለሁ፤ እንዲያውም የግብፆችን እና ሌሎችንም ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ ቅዱሳንን በመረጃነት እየጠቀስህ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ጳጳሳት መስፈርቱን የሚያሟላ ጠፍቶ ነውን? ወይንስ መንፈስ ቅዱስ ያለው በስደት ካሉ ዜግነታቸውን ከቀየሪ "ተጋዳላዮች" ጋር ነው? " ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል" እንዲሉ ጉዳዪ ፖለቲካዊ እና ጎሳዊ ሆነ እንጂ፡፡ ቸር ያሰማን፡፡

  ReplyDelete
 30. ወንድሜ ዳንኤል ጽሑፍህን አነበብኩት ጥሩ ምልከታ ነው። ሊሆን የሚገባው ነው እየሆነ ያለው። ሰው የዘራውን ያንኑ ራሱን ያጭዳል አይደል የሚለን መጽሐፍ ቅዱስ። ይህን አባባል በሌላ የአገላለጽ ዘዴ እንደዚህ ልንገልፀው እንችላለን።  የመጠን ወይም
   የጥራት ልዩነት የሚጠበቅ ቢሆንም እንኳ  ስንዴ ዘርቶ እንክርዳድ ፤ እንክርዳድ ዘርቶም  ስንዴ ማጨድ አይጠበቅም። የዘሩ ባለቤት ባህሪ ዓላማ እና ፍላጎትም የዘሩን ዐይነትና ፤ ድህረ መከር የሚያስገኘውን ውጤት ይወስናል። ገበሬው ወይን ቢተክል፣ ስንዴ ቢዘራ    ከተለመደው የምግብና የመጠጥ ፍጆታነቱ አልፎ ሥጋ አምላክ ፣ ደመ አምላክ እስከመሆን ለላቀ የቤተ መቅደስ  አገልግሎት ሊውል ይችላል። በሌላ በኩል ገበሬው አደንዛዥ እጽ አብቃይ ፣ ትንባሆ ተካይ ቢሆን ውጤቱ የጤና ፣ የገንዘብና የሕይወት ኪሳራ እንደሚሆን ግልጽ ነው።
  ጥያቄው ፓትራኩን ማን ተከላቸው? ለምን ዓላማስ ተተከሉ? ለየትኛው ዓላማ እየሰሩ ነው? የሚለው ነው። ሲጀመር በርሳቸው ምርጫና ሹመት ላይ መንፈስ ቅዱስ መቸ ድርሻ  ነበረው? እንኳን ለራሷ ለዓለም የምትተርፍ ቤተ ክርስቲያን ፆም አውጃ ፣ ሱባዔ ገብታ አሁን የገጠመንን ችግር የሚፈታልን ፣ በእፍረት የተዘለሰ አንገታችን እንድናቀና የሚያደርገን ፣ ወደ ፊት የሚገጥሙን ችግሮች በመንፈሳዊ ጥበብ ፣ በአምላክ እርዳታ ወንድሞቹ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳትን  እና መላውን የቤተ ክርስቲያኒቱን አቅም  አስተባብሮ የሚፈታ  መሪ እንዲሰጠን  መቸ ጠየቅን።  ከአዲስ አበባ ኢየሩሳሌም በተደረጉ የስልክ ምክክሮች ወይም ከአዲስ አበባ ቴላቢብ ለዚሁ ጉዳይ በተጓዙ የሥርዓቱ ካድረዎች አቅራቢነት፣ በቤተመንግስት ወይም የህዋት ኢህአድግ ቢሮ በተፈጸመ ውሳኔ  እንደተመረጡ መቼ ጠፋን? ዓለማውም ቤተ ክርስቲያኒቱ ህገ መንግስታዊ መብቶቿን ፣ ቁሳዊ፣ ሰብዓዊና የገንዘብ አቅሟን ተጠቅማ  ሐዋሪያዊ ጉዞዋን እንድትቀጥል አልነበረም ። በእንቅስቃሴ ነጻነቷ ላይ እርሳቸውን ልጓም አድርጎ  ያሻቸውን ለማድረግ ነበር እንጅ።  ለዚህ ነው ካለ በቂ ዝግጅት( መንፈሳዊ)  ባልተለመደ ሁኔታ አምስት እጩ አቅርበን ። በምን መመዘኛ እንደተገኙ ራሳቸው ጭምር ባልገባቸው  የምዕመናን የሊቃነ ጳጳሳት እና የካህናት ጉባዔ እንደ ቀበሌ ምርጫ በድምጽ የመረጥነው ። ምርጫው የመንፈስ ቅዱስ ቢሆን ኖሮማ እጨዎቹን ሲኖዶሱ ማቅረብ ፣ ውሳኔውን ደግሞ በዕጣ መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ ማድረግ ይቻል ነበር።
  ስለዚህ ሲዘራ የተበተነውን ፍሬ ነው ዛሬ ሲበቅል ማየት የጀመርነው። ሲያፈራ ደግሞ የባሰ ነገር መከተሉ አይቀርም።  ፓትርያርኩም ሆነ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉዳዪን ወደ መንግስት መውሰዳቸው ተሸናፊነታቸው ነው የሚያሳየው። ሲጀመር  ፓትርያርኩ ከተለመደው አሰራር ከመንፈስ ቅዱስ ጉባዔ ውጭ  በህጋዊ አሰራር በእግዚአብሔር ፈቃድ ሊቀመጡበት የሚችሉትን ወንበር ከካድሬ  ጋር መክረው፣ በድርጅት አስወስነው ፣በመንግስት አጸድቀው ከመቀበል በማስመሰያ የምርጫ መርሐ ግብር ከመቀበል ያለፈ ምን መሸነፍ አለ?  እንዴያውም ቃሉን አሳነስኩት መሰል መሞት ብለው ይሻላል። ሊቃነ ጳጳሳቱም ቢሆኑ የመንግስት እና የድርጅት ሰዎች የነርሱን እና የመንፈስ ቅዱስን ሚና ቀምተው  ፣ የሲኖዶሱን ልዕልና ንቀው ውሳኔ ሰጥተው  ለካሜራ የይስሙላ ምርጫ እንዲመርጡ ሲገፏቸው  ተቀብለው ከማስፈጸም የበለጠ መሸነፍ የት አለ?  እነሱ ከመሞት መሰንበት ብለው ይሆናል ለእኔ ግን  የሞቱት ያኔ  ነው። ስለዚህ  ፓትርያርኩ ትናንት የሾማቸውን መንግስት አርዳታ ቢሹ  ወይም ሊቃነ ጳጳሳቱ ትናንት የተሸነፉለትን መንግስት ቢማጸኑ ምን ይገርማል። ሰው ለተሸነፈለት ለርሱ ባርያ ነው እንደሚባለው ።ለዩነቱ ፓትርያርኩ አጋር ፈልገው ሊቃነ ጳጳሳቱ ደግሞ ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቆመው ማውረድ ቢቸግራቸው በምርጫ እጦት መሔዳቸው ነው።  እዚህ አሳፋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው እንኳ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ፣የጸሎትን ጥቅም ፣ የተተከለውን አሰራር ማየት አለመቻላቸው
  ግን ይገርማል።  ቤተ ክርስቲያንን ይዘዋት እየወደቁ፣ ማፈሪያ ሆነው እያሳፈሩን እንደሆነ ቢያውቁ መልካም ነበር ።

  ReplyDelete
 31. abetu egziabher hoy egnan kezih kealemawi fetena ante awutan. egziabher hoy egnan atrsan yih hulu afnchachin sir sifetsem min enlalen. abetu ante yemetfo tazabiwoch atadirgen........amen.

  ReplyDelete
 32. ዛሬ እንደዋዛ የሚከፈተው በር ነገ እንዝጋህ ቢሉት አስቸጋሪ ነው፡፡ egziabher dani ena mehabere kidusanin yaberta betechemari yebatochachin tselot ayleyen ::

  ReplyDelete
 33. ይሄ እንዴት ይገርመናል?? ዛሬ ነዉ መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ መግባት የጀመረዉ? ሿሚዉም ሻሪዉም ማን ሆነና ነዉ!! ህገ መንግቱ ተፃፈ እንጂ ይቅርታ ተገለበጠ እንጂ ስራ ላይ ዉሎ ያዉቃል?? ምናልባት አሁን በገሀድ የመንግስት አካል በሚል ሽፋን ጠባቂ ወታደር አስፈልጏቸዉ ይሆናል::

  ReplyDelete
 34. እውነት ነው መንግስሥት መግባት የለበትም። ነገር ግን ከጅምሩም የማቅ ጳጳሳቱ ይህንን የሲኖዶስ ጉባዔ በጥብጠው አጀንዳውን ወደራሳቸው ለመውስድ ያደረጉት ድራማ ነው። ሃሳባቸው በአብዛኛው ቢከሽፍም መንግሥት ይግባልን ብለው ድምጽ ሰተው ያስጠሩት ራሳቸው የማቅ ቢጽ ሀሳውያን ጳጳሳት ናቸው። ምንም እንኩዋን የመንግስት ጣልቃ ገብነትን ባይደገፍም ውጤቱ እንደ አላውያን መፈንቅለ ፓትርያርክን ያስቀረ፣ ህጋችሁን ተከተሉ የሚል መልካም መንፈስ ያለበት ነበር። የኤጲስ ቆጶሳቱንም ምርጫ እነዚህ የቤተ ክርስትያን ጠላት የሆኑ የማቅ ሎሌዌች ለመበጥበት ለብዙ ወራት ሲጠነስሱ የነበር ሲሆን ከተሳካላቸው ሽብር ፈጥረው የራሳቸውን ቢጽ ሃሳውያን ጳጳሳት ያሾማሉ። ለቤተክርስትያኑ የሚጠቅሙትንም ስም ሰተው ምርጫውን ያስተጒጉላሉ።

  ReplyDelete
 35. ወንድም እህቶቼ እኔ ስለዚህ ጉዳይ ጠለቅ ያለ ዕውቀቱ የለኝም ግን አንድ ነገር ልናስብ ልናምንም ይገባል 1ኛ ቸሩ እግዚአብሔር ሀገርን ያለአንድ ቅዱስ እንደማይተዋት እመኑ 2ኛ እንዲህ አይነት ቦታ ላይ የሚቀመጡ አባቶች የማን ፈቃድ ነው ያስቀመጣቸው ቦታው ላይስ እንዲቀመጡ ማን ሾማቸው ነው 3ኛ ደግሞ ኢትዮጲያ ጳጳሳት ከግብፅ ይላክላት በነበረ ጊዜ ሙስሊሞችን ጳጳሳት ናቸው ብለው ይልኩ እንደነበር የምናውቀው ታሪክ ነው ያኔም እንኳ ቤተክርስቲያን ነበረች ማንም ምንም ሊፈጥር አልቻለም በየዘመናቱ ብዙ መከራዎችን አሳልፋለች ሁሉም አለፉ እርሷ ግንየሐይማኖቷ ራስና ፈፃሚ የድንግል ልጅ ክርስቶስ ነውና አሁንም ከነክብሯ አለች ከዚህ የባሰ ቢከሰት ልንደነቅ አይገባም ይህ የመናፍቃን ተሐድሶ ሴራ ነው በፊት ከታች ባሉ ምዕመናኖቿ ነበር ትግላቸው ሁሉም ሀይማኖቱን እያወቀ ሲመጣ የማያዋጣ ሆኖ ተገኘ አሁን ደግሞ ከላይ ገቡ ይህም ግን ይከሽፋል ግን ጠባሳ ጥሎባት እንዳያልፍ እኛ ምን እናድርግ የሚለው ላይ ማተኮሩ ሳይጠቅመን አይቀርም ለምን ቢሉ የሐይማኖት ዕወቀት የሌላቸው ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ዕወቀት የሌላቸው ሐይማኖተኞች ተጋብተዋልና ልጅ ሳይወልዱ ወይም ሳይባዙ ሁላችንም ድንግልን ይዘን በጥበብ በእርጋታ ሀሳባቸውን ማፍረስና ማጥፋት የሚኖርብን ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ አንደኛው እቅዳቸው ሳይፈፅሙት አልቀረም ቅጥረኛ ያልሆነ መምህር በአውደምህረት ሊሰብክ አይገባም የሚል ነው ይህም ሀገረስብከቱ ለየአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ እንደተላለፍ አድርጓል ትንሹን ችግር ትልቁን ጥቅም ሊያሳጣን አይገባም አንድና ሁለት መምህር ለማስቆም ተብሎ ሀያና ሰላሳ መምህር መከልከል ምን የሚሉት እንደሆነ አልገባኝም ይህ ደግሞ በውስጡ ትልቅ ሴራ ያለው ነው የቤተክርስቲያናችንን ድምፅ ዘግተው እነሱ ሊፈነጩባት ነውና ጠንቅቀን ልንመለከተው ይገባል፡፡

  አመሠግናለሁ
  ቸር እንሰንብት

  ReplyDelete
 36. ኦ እግዚኦ ኢታርየነ ሙስናሃ ለቤተክርስቲያንነ!

  ReplyDelete
 37. እርሱ ላመንነው ለእያንዳንዳችን እረኛ እንደሆነ የቤቱም እረኛ መሆኑ እያስታወስን፤ ለብፁአን አባቶች የሚገባ ምንም ነገር ካለ ለባለቤቱ ብንተወው የሚሻል ይመስለኛል፤ እንደ አማኞች ፀሎታችንን ብናጸና፣እንባችን ብንረጭና ማድረግ የሚገባንን ነገር ብናደርግ(ያቅማችን በስርአቱ መሰረት) ተመራጭ ነው።በቤተክርስቲያኒቱ ስም ግን አወንታዊ ያልሆኑ የፖለቲካ አጀንዳችንን ማስፈጸምያ፣ ኢ-ክርስቲያናዊ የሆኑ ማንንም የማያንጹ ግለ ሂሶቻችን መርጪያ ባናደርገው፤ይህ ፔጅም በጎ ነገሮች ይምናገኝበት ብለን የምንጠብቀውም በመሆኑ ያልጠነከሩ ክርስቲያኖች ማሰናክያ ባናደርገው ፤ በቀረው እርሱ ንጉሳችን ንፋሱ ና ባህሩ ገስፆ ጸጥ ያሰኘው ዘንድ ይቻለዋል ቢዚህም የታመነ አምላክ ነው። (ማቴ 8:26)

  ReplyDelete
 38. GOD BLESS ETHIOPIA!!!!DREAR CHRISTIANS DO NOT WORRY RATHER PRAY ALWAYS ABOUT OUR CHURCH,GOD IS ALWAYS WITH ETHIOPIA!!!!IF THEY TORCH US WE BECOME MORE STRONG AND STRONG.OUR ALMIGHTY GOD PLEASE SEE THE PRAY OF OUR FOREFATHERS WHO LIVE IN MONASTERIES....

  ReplyDelete
 39. 25 እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።
  15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥
  40 በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤

  41 ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች።

  42 ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
  35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።
  13 እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
  የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24

  ReplyDelete
 40. መቼም እንደዘንድሮ የእንጦንስና ጳውሊ ራእይ በተግባር የታየበት ዘመን የለም፡፡ kale hiwot yasemh

  ReplyDelete
 41. መቼም እንደዘንድሮ የእንጦንስና ጳውሊ ራእይ በተግባር የታየበት ዘመን የለም፡፡

  ReplyDelete
 42. በመንፈስ ቅዱስ እንደተመረጠ የሚያምን መንፈስ ቅዱስ በርሱ አድሮ ሥራ እንደሚሠራ ያዉቃል፡፡ በምድራዊ ኃይል የተመረጠ፤ በምድራዊ ኃይል የሚተማመን የተሰጠዉ ምድራዊ ተልዕኮ እንዳይሰናከል ምድራዊዉን ኃይል ተማክሮ ቢሰራ አይደንቅም፡፡ ለኛ ለምዕመናን ግን ቸርነቱ እንዲበዛልን፡ እረኞቻችን እንደበተኑን ጌታም ለተኩላዎቹ አሳልፎ አንዳይሰጠን ጸሎት፡ የሚጸልዩልን ቅዱሳን ያስፈልጉናል፡፡

  ReplyDelete
 43. Yegna wetet enessun ameta- if only God was happy with what each one of us do this wouldn't happen. We have ( our sin ) has a part on this present. Let us change and this will change...

  ReplyDelete
 44. ምን ይደንቃል ከካድሪ ከዚህ የተለየ ለምን ትጠብቃላቹ የወያኔ ካድሬዎች የተሰበሰቡበት ሴኖዶስ ቅዱስ ብሎ መጥራት አይገባም

  ReplyDelete
 45. ምን ይደንቃል ከካድሪ ከዚህ የተለየ ለምን ትጠብቃላቹ የወያኔ ካድሬዎች የተሰበሰቡበት ሴኖዶስ ቅዱስ ብሎ መጥራት አይገባም

  ReplyDelete