ይገርምሃል ወንድሜ በሕይወትህ ድል
አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም፡፡ አታየውም ቸልሲን መከራውን
ሲቀበል፡፡ አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎችኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል፡፡
ለሚወጣ ሰው ግን መውረድ የጥላውን ያህል ቅርብ ነው፡፡ ‹እኖራለሁ ብለህ ሥራ እሞታለሁ ብለህ ኑር› ሲባል አልሰማህም? መውረድን
የረሳ ባለ ሥልጣን፣ ሕመምን የረሳ ጤነኛ፣ ድህነትን የረሳ ሀብታም፣ ሞትን የረሳ ነዋሪ፣ ድቀትን የረሳ ጻድቅ፣ ውርደትን የረሳ
ክቡር፣ ወደረሳው ነገር ለመጓዝ እንዴት ይፈጥናል መሰለህ? ድቅድቁ ጨለማ ያለው ከሻማው ሥር ነው፡፡
እነ እገሌ ካሉ፣ እነ እገሌ ቦታውን
ከያዙ፣ እነ እገሌ እዚያ ላይ ከወጡ፣ በቃ አይሳካልኝም አትበል፡፡ ሌስተርን ያየ እንዲህ አይልም፡፡ ለወትሮው የእንግሊዝ እግር
ኳስ ማንቸስተር ዮናይትድና ማንቸስተር ሲቲ፣ አርሴናልና ቼልሲ በእግራቸው ርግጥ፣ በእጃቸው ጭብጥ አድርገው የሚዘውሩት ይመስል ነበር፡፡
መቼም ዋንጫውን ከእነዚህ ከአራቱ አንዱ እንጂ ሌላው ይቀምሰዋል ተብሎ አይታሰብም ነበር፡፡ ‹ሙሴ በሩቁ ከነዓንን አያት እንጂ አልወረሳትም›
እንደሚባለው ሌሎቹ ቡድኖች ዋንጫውን በሩቁ ከማየት አልፈው ይወርሱታል ብሎ ማን ያስብ ነበር፡፡
ወዳጄ በዚህ ዓለም ላይ የማይነጠቅ
የተጨበጠ፣ የማይንሸራተት የተረገጠ የለም፡፡ nothing for granted ይሉ የለም ስታድየሙን ሞልተው የሚጨፍሩት እንግሊዞች፡፡
የጨበጥክበት እጅህ፣ የረገጥክበት እግርህ አንድ ቀን ይዝላል፡፡ የትናንት አይበገሬነትህ፣ የትናንት ጀግንነትህ፣ የትናንት ክብርህ፣
የትናንት አሸናፊነትህ፣ የትናንት ተፈሪነትህ በዛሬ ጥረት ካልታገዘ ታሪክና ቅርስ እንጂ ድልና ውጤት አይኖርህም፡፡ አታያቸውም እንዴ
እነ ማንቸስተር ዩናይትድና እነ ማንቸስተር ሲቲ ከአራቱ ውስጥ ለመግባት መከራቸው ሲያዩ? አታያቸውም እንዴ እነ አርሴናል ከቀበሮ
አምልጦ ዛፍ ላይ እንደወጣ ዶሮ ካሁን አሁን ከአራቱ ወረድን እያሉ ሲጨነቁ? አላየኸውም እንዴ ስንት ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የኖረው
አስቶንቪላ ተሰናብቶ ከሊጉ ሲወርድ፡፡
ዓለም እንደዚህ ናት፡፡ ድል በታሪክ
ቢሆን ኖሮ ከሊቨርፑል በላይ ማን ዋንጫ ይወስድ ነበር፡፡ ምን እዚያ ወሰደህ፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን የአፍሪካን ዋንጫ የጠነሰስን፣
የአፍሪካን እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንስ የመሠረትን አልነበርንምን? ከብዙዎቹ ቀድመን ኳስ ተጫውተን፣ ከብዙዎቹ ቀድመን ዋንጫ አልበላንምን?
ከብዙዎቹስ በፊት የአፍሪካን የእግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አልመራንምን? ዛሬ ግን የት ነን? ትዝታ ሆነናል፡፡ ዋንጫ እንደ መንግሥተ
ሰማያት፣ ድልም እንደ ሰማይ ርቆናል፡፡
ሊቃውንቱ ‹ድል ማለት ጥረትና ዕድል
የሚገናኙባት አጋጣሚ ናት› ይላሉ፡፡ አንተ ትታገላለህ፣ ትጥራለህ፣ ትለፋለህ፣ ትደክማለህ፣ ትወጣለህ፣ ትወርዳለህ፤ እንዲህ ባለማቋረጥ
ስትታገል አንድ ቀን የአንተ የጥረትህ መንገድ ከዕድል መንገድ ጋር ይገናኝና ታቋርጠዋለህ፡፡ ያኔ አይወድቅም የተባለው ወድቆ፣ አይሸነፍም
የተባለው ተሸንፎ፣ አይነቀነቅም የተባለው ተነቅንቆ፣ አይፈርስም የተባለው ፈርሶ፣ አይነካም የተባለው ተነክቶ ቦታውን ሲለቅ ታየዋለህ፡፡
አንተ ካልጣርክና ካልታገልክ፣ ካልሠራህና
ካልሞከርክ ግን በዕድል ብቻ የሚሆን ነገር የለም፡፡ ዛሬ አላሸነፍክም? ተስፋ አትቁረጥ ቢያንስ የማሸነፍ ሞራልና የማሸነፍ ተስፋ
አለህና፡፡ የሚሸነፍ ትግል የለም፡፡ የሚሸነፍ ሰው እንጂ፡፡ ትግል ትግልን ይወልዳል፣ ጥረት ጥረትን ይተካል፣ ሙከራ ሙከራን ያመጣል፡፡
ዛሬ አንድ አካፋ አፈር ከተራራው ላይ ስታነሣ ተራራውን አልናድከው ይሆናል፡፡ በርግጠኝነት ግን የተራራውን መልክ ቀይረህዋል፡፡
በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎች፣ ወይም አንተ ራስህ እንኳን የተራራው መልክ መቀየሩን ላታውቀው ትችላለህ፡፡ ተራራው ራሱ ግን ያውቀዋል፡፡
የመሬት መሸርሸር የሚባለው ግማሽ ተራራ ተሸርሽሮ አይደለምኮ፡፡ ውኃ እያሳሳቀ አፈሩን በየጊዜው ሲወስደው ነው፡፡
ምናልባትም ምንም አታመጣም ብለው
ሰዎች ይነግሩህ ይሆናል፡፡ ሌስተርን ተመልከቱ በላቸው፡፡ ሌስተር የት ነበረ፡፡ አምና ቼልሲ ዋንጫውን ሲወስድ፣ ማንቸስተር ሲቲ
ሁለተኛ ሆኖ ሲጨርስ አርሴናልና ማንቸስተር ዩናይትድ ሦስትና አራተኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ፣ ሌስተር የት ነበር? እስከ ሰባት፣ እስከ
ዐሥር ደረጃ ብትፈልገው ታገኘዋለህን? ፈጽሞ፡፡ ሌስተር ከወራጅ ቀጠናው
በአራት ደረጃ ርቆ፣ ከወራጁ ከሁልሲቲ በ7 ነጥብ ብቻ በልጦ 14ኛ ደረጃ ላይ ነበረልህ፡፡
ዘመን መሰላል ነው፡፡ የወጣው ሲወርድ፣
የወረደው ሲወጣ ይገናኙበታል፡፡ በአንድ ዓመት ልዩነት የቸልሲን ቦታ ሌስተር፣ የሌስተርንም ቦታ ቼልሲ ይዞ አየነው፡፡ እንዳያርግ
ስንፈራው የነበረው ቼልሲ እንዳይወርድ ተሳቀቅንለት፡፡ ‹የናቁት ይውርሳል› እንደተባለው አራቱን ኃያላን ገፍቶ ሌስተር መጣና እንደ
ሽሮ ቅቤ በአናት ተቀመጠ፡፡ ‹ይሞታል ያሉት ተርፎ፣ ይቀብራል ያሉት ሞተ› ሲባል አልሰማህም?
እናም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ግፋ፣
ጣር፣ ታገል፣ ሥራ፣ ሞክር፣ ድፈር፤ ድል ይጠራቀማል፡፡ አንድ ቀን ከላይ ያየሃቸው ኃያላን እንደ ቼልሲ ደክመው፣ እንደ አርሴናል
አርጅተው፣ እንደ ማንቸስተር ዩናይትድ ቀልብ ርቋቸው፣ እንደ ሲቲ ነገር ዓለሙ ዞሮባቸው ታገኛቸዋለህ፡፡ ያኔ እንደሌስተር ገፋ ገፋ
አድርገህ ከላይ ቁጢጥ ነው፡፡ ሰውን መናቅ እንጂ በሰው መናቅ አይጎዳም፡፡ ሰውን መናቅ ትዕቢትን ወልዶ ስንፍናን ያመጣል፡፡ በሰው
መናቅ ግን እልህን ወልዶ ትግልን ይፈጥራል፡፡ እናም አሸናፊነትህ የሚወሰነው ሰዎች ባንተ ላይ ባላቸው አመለካከት አይደለም፤ አንተ
በሌሎች ላይ ባለህ አመለካከት እንጂ፡፡ እንዴት ያዩኛል? ብለህ አትጨነቅ፡፡ እንዴት አያቸዋለሁ? ብለህ ግን አስብ፡፡ እያሸነፍክ
ስትመጣ የማያዩህ ሁሉ ያኔ ያዩሃል፣ የጠሉህ ያኔ ይወዱሃል፣ የናቁህ ያኔ ያደንቁሃል፡፡ የበለጠ ወደ ማይክራፎኑ በተጠጋህ ቁጥር
የበለጠ ድምጽህ ይሰማል፡፡
እንዲያውም ሲንቁህ መልካም ነው፡፡
ጫና አይበዛብህም፤ ጠላት አይበዛብህም፤ ተገዳዳሪ አይበዛብህም፤ ጉልበትህን ለሥራህና ለዓላማህ ብቻ እንድታውለው ጊዜ ታገኛለህ፡፡
ሰዎች ዓይናቸውን ቼልሲ ላይ ያርጉልህ፣ ማንቸስተር ላይ ይጣሉልህ፣ ሲቲ ላይ ያኑሩልህ፣ አርሴናል ላይ ያትኩሩልህ፡፡ አንተ ዝም
ብለህ ሥራና እንደ ሌስተር እየገፋህ ና፡፡ መንደርህ ትንሽ ናት? ስምህን የሚያውቀው የለም? ገንዘብህ ጥቂት ነው? የተሰጠህ ግምት
አነስተኛ ነው? ባንተ የሚተማመኑ የሉም ወይም ጥቂት ናቸው? እነዚህ ሁሉ ካልለወጡህ ልትለውጣቸው ትችላለህ፡፡
እንደ ንሥር ታድሰህ፣ እንደ እባብ
አፈር ልሰህ፣ እንደ ከራድዮን ራስህን ለውጠህ እስካልመጣህ ድረስ እንደ ቼልሲ ትናንት ዋንጫ በልተህ ዛሬ መውረድህ የማይቀር ነው፡፡
ወደላይ ከሚሄድ ሰው ይልቅ እላይ ያለ ሰው ለታቹ ቅርብ ነው፡፡ ጊዜ ይለወጣል፣ ሐሳብ ይለወጣል፣ ወዳጅ ይለወጣል፣ አሠራር ይለወጣል፣
እሴቶች ይለወጣሉ፡፡ አንተም ትናንት የሠራኸውን ብቻ እየዘፈንክ፣ የትናንቱንም ታሪክ ብቻ እየተረክህ፣ ‹ትናንት እንዲህ ያደረግኩት
እኔ ነኝ› ብለህ እየፎከርክ መኖር አደገኛው አኗኗር ነው፡፡ ‹ሆ› ብለው ያወጡህ ‹ውይ› ብለው እንዳያወርዱህ፣ ‹ጀግና› ብለው
የሰቀሉህ፣ ‹ፈሪ› ብለው እንዳይጥሉህ፤ ‹ጉሮ ወሸባዬ› የዘፈኑልህ፣ ‹ዋይ ዋይ የት ትሄዳለህ› እንዳይሉህ፣ ‹ያለ አንተ› ያሉህ
‹ካንተ በቀር› እንዳይሉህ፡፡ የኮሩብህ እንዳያፍሩብህ፣ ‹እዩኝ እዩኝ› ብለህ ‹ደብቁኝ ደብቁኝ› እንዳትል ከፈለግክ መንገዱ አንድ
ብቻ ነው፡፡ የትናንቱን ለታሪክ ተወውና ለዛሬው የሚያስፈልግህንና የሚገባህን ሥራ ሥራ፡፡ ከታሪክ ተማር እንጂ ታሪክ ላይ አትተኛ፡፡
አታይም እዚህ ሀገር እንኳን የሊቨርፑል
ዘመን አልፏል፡፡ ዛሬ በሃምሳዎቹና በስድሳዎቹ ውስጥ ያሉ የኳስ አፍቃሪዎች በዘመናቸው የሊቨርፑል ደጋፊዎች ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን የእነርሱ
ልጆች እንኳን ሊቨርፑልን አይደግፉም፡፡ ያማ ቀርቶ ሌላ ዘፈን መጥቶ፡፡ ዘመን ተቀይሮ፤ ደጋፊም ተደጋፊም ተቀይሮ፡፡ አዲስ ጀግና
መጥቶ፣ አዲስ ተከታይ አፍርቶ፡፡ ያም ዘመን አለፈ፡፡ የነማንቸስተርና የነአርሴናልም ዘመን መጣ፡፡ እርሱም ሊያልፍ ነው መሰል፣
ደግሞ የነ ሌስተርና የነ ቶተንሐም ዘመን መጣ፡፡
‹በቃ ጨርሻለሁ› ወይም ‹በቃ ተጨርሻለሁ›
አትበል፡፡ ‹አለቀ›ም ‹አለቀልኝ›ም አትበል፡፡ ካንተ በፊት ሌሎች ነበሩ፡፡ ካንተም በኋላ ሌሎች ይመጣሉ፡፡ ‹ታግለን ጨርሰናል›
ያሉ እንደ ቼልሲ ቦታ እየለቀቁ፣ ‹ገና ይቀረናል› የሚሉ ታጋዮች እንደ ሌስተር ቦታውን እየተረከቡ ይሄዳሉ፡፡ ሕይወት ሌስተርና
ቼልሲ ናት፡፡
Thank you so much I am working hard to be ሌስተር. Please help me by praying . God bless you and your family.
ReplyDeleteWe love you Dani ! Leicester city is a definition of hard work and self believe.If God will, they will celebrate this coming Sunday with our Fasika.Thank you Boss.
ReplyDeleteRespect
Also,You can add more about the the leader who can take you on the top if you are lucky enough to have good leader. Ranieri is the man made this History and he deserve every penny and praise.Thank you Danny
ReplyDeleteእያሸነፍክ ስትመጣ የማያዩህ ሁሉ ያኔ ያዩሃል፣ የጠሉህ ያኔ ይወዱሃል፣ የናቁህ ያኔ ያደንቁሃል፡፡
ReplyDeletethank you.god bless you.
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል፡ እግዚአብሔር ይስጥልን፤ ልብ ለሚለው በእውነትም ቆም ብለን ማሰብ አለብን ውጣ ውረድ በበዛባት በዚህች ምድር ለምንኖር ሰዎች ታላቅ ምክር አለው፡፡ እውነትም ህይወት እንዲህ ናት፣ በቤት፣በመ/ቤት፣ በት/ቤት፣ በሰፈር፣ በከተማ፣በገጠር በሁሉም ቦታ ያነሳሃቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ መቋጫው ማሰሪያ ልጡ ግን እንዳልከው እኛ መግፋት፣ መጣር፣ መታገል፣ መሥራት፣ መሞክር፣ መድፈር…ይጠበቅብናል፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ አክባሪህ ታናሽ ወንድምህ፡፡
ReplyDeleteወይኔ ዳኔ በምሳሌ እያዋዛክ ታስተምረናለህ በርታ እግዛብሔር ካንተ ጋር ይሁን መልካም ፋሲካ
ReplyDeleteWow great view bro.....
ReplyDeleteWow great view bro.....
ReplyDeleteበጊዜ መልካም ነገር ማድረግን ስላስተማርከኝ አመሰግናለሁ መልካም መካሪ ነህ እግዛብሔር ይጠብቅህ
ReplyDeleteBetam telik kezemenu gar mihed eyta new...amesegnalew...!!!
ReplyDeleteIt is true, i agree with your statment
ReplyDeleteCongratulation!!! Your prediction comes true.
ReplyDeleteI agree, this is a good lesson for our life. Thanks Dani
ReplyDeleteAbo Dani yimechih ! Man yehinin yastewulal bileh new ? Mastewalun yabzalih ! Melkam fasika !
ReplyDeletearif new
ReplyDeletetiru melikt yalew ymesilagnal tnx
ReplyDeleteNothing for granted...thanks
ReplyDeleteLet look into the secret if the article. JERRO YALEW YISMA.
ReplyDeleteTIRU EYITA!
ReplyDeleteባለፈው ያንተ ፁሁፍ ላይ ኮሜንት ሳነብ ዲ.ን ዳንኤል ያንተን ፁሁፍ አንብቤ እንድጨርስ እ/ር ዕድሜ ና ጤና ይስጠኝ የሚል ኮሜንት አንብቤ ነበር. እኔም ለራሴ ይህን ተመኘው እ/ር ምሥጢሩን ይግለፅልኝ.የሌስተር ና የቼልሲ ጉዳይ ተጨማሪ ምን መሰለህ ቅድስት ሥላሴዎች የጆዜ ሞሪኒሆን ዕውቀት ወሰዱበት ለክላውዲዮ ሪያኔሪ(የሌስተር) አሰልጣኝ የእነሞሪኒሆን ያህል ዕውቀት ያልነበርውን ሰው ዕውቀት ሰጡት. እናም በትንሽ ገንዘብ ሌስተርን ሻምፒዎን እፕደርገው ታዲያ ይህ የቅድስት ሥላሴዎች ስራ አይደለምን? ነው. ይህን ያልኩበት ምክንያት ፍኖተ አእምሮ የሚለውን የልዑል ራስ ካሳ ሀይሉን መፅሐፍ ካነበብኩ በኃላ ነው።
ReplyDeleteRely thank you very much, Happy Easter D/n Daniel!
ReplyDeleteenamesegnalen
ReplyDelete...ወደ ላይ ከሚሄድ ሰው ይልቅ እላይ ያለ ሰው ለታቹ ቅርብ ነው። ...
ReplyDelete...ወደ ላይ ከሚሄድ ሰው ይልቅ እላይ ያለ ሰው ለታቹ ቅርብ ነው። ...
ReplyDeleteእውነት ነው በዱሮ በሬ ያረሰ የለም ትልቁ ቁም ነገር ሆኖ መገኘት ነው፡፡
ReplyDeleteእ/ር ይባርክህ