Tuesday, April 26, 2016

ሥርዓተ ዕለተ ስቅለት ዘደብረ ሊባኖስከ500 ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕለተ ስቅለትን እንዴት ታከብር እንደነበር በመጠኑ ሊያሳዩን ከሚችሉ መዛግብት አንዱ ‹ዜና ደብረ ሊባኖስ› የተሰኘው መዝገብ ነው፡፡ ዜና ደብረ ሊባኖስ በ1586 ዓም የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ አምስት ነገሮችን ይዟል፡፡ የደብረ ሊባኖስን ታሪክ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት እስከ ዐፄ ሰርጸ ድንግል ዘመን፤ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ጥንታዊ ሥርዓተ ማኅበር፤ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ጥንታዊ ሥርዓተ ጸሎት፤ በመጽሐፈ መነኮሳት መልክ የተጻፈ የልዩ ልዩ መነኮሳት አስደናቂ መንፈሳዊ ሕይወት እና በዐፄ ሰርጸ ድንግል ዘመን የተፈጸሙ አንዳንድ ሀገራዊ ኩነቶች፡፡

እስካሁን በተደረገው ጥናት ዜና ደብረ ሊባኖስ ሦስት ቅጅዎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው በፓሪስ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት፣ በአንቶንዮ ዲአባዲ ስብስብ ውስጥ በቁጥር 108 ተመዝግቦ የሚገኘው፤ ሁለተኛው ከደብረ ጽጌ ማርያም የተገኘውና በማይክሮ ፊልም ተነሥቶ በEMML 7346 ተመዝግቦ የሚገኘው፤ ሦስተኛው ደግሞ በደቡብ ጎንደር ማኅደረ ማርያም ደብር የሚገኘው ቅጅ ነው፡፡ ከሦስቱም ቁልጭ ብሎ የሚነበበው የማኅደረ ማርያሙ ቅጅ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከምናገኛቸው ጉዳዮች አንዱ በቤተ ክርስቲያን በዓላት ስለሚደረጉ ጸሎቶችና የጸሎቱ ሥነ ሥርዓት አንዱ ነው፡፡ አንዳንድ ሥርዓቶች በዘመን ብዛት ተረስተዋል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ተጎርደዋል፡፡ የጥንቱን ከዛሬው ማስተያየትና የጎደለውን ለመሙላት፣ የተረሳውን ለማስታወስ፣ የተሳተውንም ለማቅናት መሞከር ብልህነት ነው፡፡ እስኪ ለምሳሌ ሥርዓተ ዕለተ ስቅለቱን እንየው፡፡ 


ደግሞም የዕለተ ስቅለት ሥርዓት (ወግ) ይህ ነው፡፡ (ጠዋት) በ3 ሰዓት ቤተ ክርስቲያንን በወርቀ ዘቦ ግምጃ ካስጌጡ ሥዕላትንም በየመስቀያቸው ካስቀመጡ በኋላ የመጻሕፍት ንባብ በየተራቸው ይሁን፡፡ የስቅለቱንም ሥዕል በመካከል ያኑሩት፡፡ ሦስት ማዕጠንቶችንም በፊቱ ይስቀሉ፡፡ ሁለት ዲያቆናትም አንዱ በቀኙ ሌላውም በግራው የሐር መነሳንስ ይዘው፣ የሐር ልብስም ለብሰው፣ ራሳቸውም ተሸፍኖ ይቁሙ፡፡ እስኪመሽና የስቅለቱ ሥዕል እስኪነሣ ድረስም እንዲሁ ይሁኑ፡፡
ወዳነሣነው ነገር እንመለስ፡፡
የመዓልቱን ቅኔ አድርሰውም በጌታችን ምሳሌ ይገረፉ ዘንድ ወደ ምሥራቅ ይሂዱ፡፡ ይህንንም ፈጽመው ወደ መዓልቱ ቅኔ ይመለሱ፡፡ ያመስግኑ፣ የመዝሙረ(ዳዊትንም) ቃል ሃምሳውን በሦስት ሰዓት፣ ሃምሳውን በስድስት ሰዓት፣ ሃምሳውን 9 ሰዓት ይድገሙ፤ በምሽትም ጊዜ የስቅለቱ ሥዕል ከተገነዘ በኋላ 150ውን ይድገሙ፡፡ መዝሙረ ዳዊትም በሰሙነ ሕማማት ጊዜ ይድረስ፡፡ አንደኛው በመንፈቀ ሌሊት፣ አንደኛው በነግህ፣ አንደኛው 3 ሰዓት፣ 6 ሰዓትና 9 ሰዓት ሃምሳ ሃምሳ በሰሙነ ሕማማቱ ሁሉ አምስቱ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ይድረስ፡፡ በአንድ ቀንም ሦስት ጊዜ (ሙሉው መዝሙረ ዳዊት) ይድረስ፡፡ ሰኞ ዕለትና ማክሰኞ ዕለትም እንዲሁ እስከ ዓርብ ድረስ ይደረግ፡፡ በዕለተ ዓርብ ግን አራት ጊዜ(ሙሉው መዝሙረ ዳዊት) ይድረስ፡፡ 3 ሰዓት፣ 3 ቃልግፍዖሙ እግዚኦ ወጽብዖሙ እግዚኦበዜማ ይበል፡፡ ሕዝቡም በግራና በቀኝ ሆነው እስኪፈጸም ድረስ እየሰገዱ ይቀበሉት፡፡ የስቅለቱንም ሥዕል ይግለጡት፡፡ መገለጡም ሰባት ጊዜ ይሁን፡፡ አንደኛውግፍዖሙሲባል፣ አንደኛው ወንጌል ሲነበብ፣ አንደኛውበመስቀልከ ንሰግድሲባል፣ አንደኛው በቀትር ወንጌል ሲነበብ፣ አንድ ጊዜምአምንስቲቲሲባል ነው፡፡ በመጨረሻ ሦስት ጊዜአምንስቲቲይበሉ፡፡
ከዚያም ተነሥተው መልክዐ ወልድንሰላም ለጸአተ ነፍስከእስከሚለው ድረስ ይቀኙ፡፡ ከግብረ ሕማማትም በኋላ መጻሕፍትን ማንበብ ይቀጥሉ፡፡ ዮሐንስ አፈወርቅና መጽሐፈ ምሥጢር፡፡ ነገረ ማርያምም ከሁለቱ መጻሕፍት ይቅደም፡፡ ዳግመኛም መጽሐፈ ዶርሆ፣ ርቱዐ ሃይማኖት፣ ተስፋ ክርስቲያንና መልእክተ አቃርዮስ ዘሀገረ ሮሐ ይነበቡ፡፡ 9 ሰዓት በንባበ ወንጌል ሰዓት ሥዕለ ስቅለቱን አንድ ጊዜ ይግለጡት፣ አንድ ጊዜ ደግሞ በምሽት ሁለት ዲያቆናት ሥዕለ ስቅለቱን ይሸከሙት፤ ቄሰ ገበዙምንሰግድ ለከ ክርስቶስ ምስለ አቡከ ሔር ሰማያዊይበል፡፡ የሚከተሉትም በንዑስ የእዝል ዜማኪርኤ ኤላይሶንእያሉ በአራት መዓዝን መቶ መቶ ጊዜ ስግደትን ከማብዛት ጋር ይቀበሉት፡፡ ቁጥሩም ሲመላ ሥዕለ ስቅለቱን ጎንበስ ያድርጉት፡፡ ያልብሱት፣ በስቅለት ሥዕል ላይም መጋረጃ ይጋርዱ፤ በራሳቸውም ተሸክመውትኪርኤ ኤላይሶንእያሉ ወደ ቤተ መቅደስ ይግቡ፡፡ እያንዳንዳቸውም በቀኝ ገብተው በግራ ይውጡ፡፡ መንበረ ታቦቱንም ሦስት ጊዜ ይዙሩት፡፡ ከዚያም በመንበሩ እግር ሥር በከርሰ ሐመሩ ሥዕለ ስቅለቱን ያስቀምጡት፡፡ ደም ባለበት በችንካሮቹ ሁሉ የከርቤ ዱቄት ይጨምሩበት ዘንድ ይግለጡት፡፡ ሲጨርሱም በልብስ ይሸፍኑት፤ መጋረጃውንም ይጋርዱት፡፡  
ከዚህ በኋላም ቄሱ ስላረፉት ወገኖች ይለምን፡፡ እርሱምብቋዕ እግዚኦነው፡፡ ወደ መዓልት ቅኔም ይውጡና መዝሙረ ዳዊትን ፈጽመው ያንብቡ፡፡ መጽሐፈ ሕማማትንም ያስከትሉ፡፡ ሲፈጸምም ካህኑተሰቅለ ወሐመይበል፡፡ ቀጥሎምንሴብሖይበል፡፡ አስከትሎምእግዚኦ ኢትጸመመኒየሚለውን ያንብብ፡፡ ሕዝቡምለይሁዳ ለወልዱ ላዕለ ውሉደ ውሉዱይበሉ፡፡ ከዚያ ደግሞብጹዕ ብእሲ እስከ ፍጻሜው ያንብብ፡፡ መብራቶችንም ሁሉ አጥፍተው ወደየቤታቸው ይሂዱ፡፡ በዚያ ሌሊትም መጽሐፈ አፈወርቅንና መጽሐፈ ምሥጢርን ያንብቡ፡፡ ደግሞም ዳዊትን ከወንጌልና ከጸዋትው ጋር እንደ ሰሙነ ሕማማት አድርገው ያንብቡ፡፡
በነጋም ጊዜ(ቅዳሜ) መኃልየ መኀልይን ያንብቡ፡፡ ቀጥለውምቅዱስ፣ ዘተወልደ፣ ወዘተጠምቀ፣ ወዘተንሠአይበሉ፡፡ መዝሙረ ያሬድንም ያስከትሉ፡፡ገብረ ሰላመከተባለ በኋላ አስቀድመው ከቤተ ክርስቲያን ይውጡና ዲያቆኑስግዱ ለእግዚአብሔርይበል፡፡  ከሁሉም የሚበልጠው የሊቃነ ጳጳሳትን ቡራኬ ያንብብ፡፡ ይህቺም ሥርዓት ዳግመኛ በርእሰ ዐውደ ዓመት እንዲሁ ትፈጸም፡፡ በፋሲካ ዋዜማ ዕለት ከሁሉ የሚበልጠው(ሊቅ) ራእየ ዮሐንስን በቀትር ጊዜ ያንብብ፡፡ የቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰዓት ሲደርስምአሌዕለከበሚለው ፋንታይትነሣእ እግዚአብሔርየሚለውን ይበል፡፡ሐዳፌ ነፍስየሚለውን ግን አይበል፡፡ ወደ ቤታቸውም አይሂዱ፣ ነገር ግን ወንጌላትንና መዝሙራትን፣ ጸሎታትንም ሁሉ እያነበቡ በቤተ ክርስቲያን ይደሩ እንጂ፡፡ አንደኛውም ወንጌለ ዮሐንስን በመንበሩ ላይ ያንብብ፤ ከዚያም ቄሱ ሥዕለ ስቅለቱን ከማንሣቱ በፊት ይጠን፡፡ ካህናቱም አፈወርቅንና መጽሐፈ ምሥጢርን ያንብቡ፡፡ ከዚያም ሙሉውን መዝሙረ ዳዊት ከወንጌልና ከጸዋትው ጋር ልክ እንደ ዕለታተ ሰሙነ ሕማማት አድርገው ያድርሱ፡፡ 
ያን ጊዜም ዲያቆኑ ከወንጌል በፊት ከመዝሙረ ዳዊትወተንሥአ እግዚአብሔርየሚለውን ይስበክ፡፡ ሦስት ወንጌላትንም ያንብቡ፡፡ አንደኛው ወንጌልም ለቁርባን ሰዓት ይቆይ፡፡ በዕለቱም መምህሩ ይቀድስ፡፡ እርሱም ካልቻለ በዕለተ ዓርብ ወንጌሉን ያደረሰው ይቀድስ፡፡ በትንሣኤ ምሽትም ካህናቱ በረከት ለመቀበል ተሰብስበው ‹ተስኢነነእንዲሉ ሥርዓት አለ፡፡ ይህም ከሌለ ደግሞእግዚአብሔር ነግሠአለ፡፡ ከፋሲካ ዋዜማ እስከ ግብር ፍጻሜ ድረስ ቡራኬ አለ፡፡ ይኼውምግብር ዘወሀብከኒ ዘውእቱ ጸጋ ዘአብየሚለው ነው፡፡ ከጾሙ እስከ ወርኃ ፋሲካ የሚሆነውንሥርዓተ ከኒሳ ተፈጸመ፡፡ ነገር ማብዛቱን ትተን በአጭሩ አቀረብነው፡፡

15 comments:

 1. ዳኒ ይሄ ሁሉ ስርዓት በፊት አይታወቅም ውይ? እኔ ይህንን ልልህ የቻልኩት ሰለ ኦርቶዶክስ የጠለቀ ዕውቀት የለኝም እንደውም አላቅም ማለቱ ይቀለኛል

  ReplyDelete
 2. Thank you Deakon Danial, Mamush, MN

  ReplyDelete
 3. kalhiwot yasmalin D/N Daniel!!!

  ReplyDelete
 4. ካወቅነው ያላወቅነው፤ ከሰጋንለት ይልቅ በእውቀት ማነስ ያልሰጋንለት በለጠ። ከጠበቅነው (ለትውልድ ካስተላለፍነው) ይልቅ ጥለነው የመጣነው በለጠ። ደብተራችን፣ ላፕቶፓቺን፣ በተ—መፅሃፍትና አእምሯቺን በምእራቡ ግሳንግስ ተጨናንቋል፤ በታላቅ ክብርም ተይዟል። የኛው ግን ያይጥ ሙሁር ያገላብጠዋል፣ የብል ቀለሜ ያመነዥከዋል፣ የዝናም ቸካይ ያጥበዋል። ወይ አለመታደል።

  ReplyDelete
 5. እግዚአብሔር ይስጥልን። ሥርዓቱን እንዳለ ማወቁ ጥሩ ነው፤ እንዳልከው የተወሰኑቱ አሁንም በየዓመቱ ሲደርሱ አያለሁ። በተለይ ከኢትዮጵያ ውጪ አገልጋይ ካህናት እንደልብ በማይገኙባቸው ክፍላተ ዓለም፤ሙሉ ሥርዓቱን ማከናወን ለአንድ ወይም ለሁለት ካህናት ይከብዳል፤ የዕውቀቱ ጉዳይ ደግሞ ሌላ ነገር ነው።

  በዚህ ጉዳይ የምዕመናን ድርሻ ውሱን ነው። ማከናወን እየቻሉ ሙሉ ሥርዓቱን የማያከናውኑ አገልጋይ ካህናት ግን ቢያስቡበት መልካም ነው። ዓመታዊ ሥርዓት ስለሆነ ምክንያት አያበዙበትም።

  ReplyDelete
 6. በእውነት እንዴት ልዩና ደስ የሚል ስርአት አለን ግን እያጣነው እየመጣን መሆኑ ብቻ በጣም ያሳዝናል። አሁንም እግዚአብሄር የቀድሞው የአባቶቻችንን ስርአት የሚመልሱ አባቶች እንዲሰጠን መልካም ፈቃዱ ይሁንልን አሜን!

  ReplyDelete
 7. በእውነት እንዴት ልዩና ደስ የሚል የቤተክርስትያን ስርአት አለን ግን እንደቀልድ እያጣነው መምጣታችን በጣም ያሳዝናል አሁንም እግዚአብሄር የቀድሞውን የአባቶቻችንን እምነት እና ስርአት የሚጠብቁ አባቶች እንዲሰጠን በርትተን መጸለይ አለብን

  ReplyDelete
 8. Ye zare 500zemen sew baregegn neber...!!!

  ReplyDelete
 9. አመሰግናለሁ ዲያቆን ዳንኤል: አምናና ዘንድሮ በሳህሊተምህረት ቤተክርስቲያን ይህ ስርዓት በተለይም የተወሰኑ ካህናት ጥቁር ልብሰ ተክኖ አድርገዉ ስቅለቱን ተሽክመዉ በአራቱም መዕዘን መቶ መቶ ጊዜ እግዞታ ሲያደርሱ ግር ብሎኝ ነበር። ለካ የነበረና የተዘነጋ ስርዓት ነው። ወይ ማወቅ ደጉ።
  ሰይፈሚካኤል

  ReplyDelete
 10. ዲያቆን, መምህራን በንግስ እና በትምህርት ጊዜ እጃችሁን ወደላይ አውጡ እያሉ ምርቃት አይሉት ጸሎት "ይህ እጅ የተባረከ ነው ይህ እጅ ..." በማለት ስው እጁ ዝሎ ሲያዩትም እጃችሁን ወደ ላይ አውጡ እንዳታወርዱት በማለት የመናፍቃንን ስርዓት ቤተክርስቲያን ላይ ሳይ በጣም አዘንኩ:: የሚገርመው ግን እንደወረርሽኝ በየቦታው ይህን ስሰማ እጃችን ወደ ላይ ወጥቶ ወጥቶ እንደ ባቢሎን ህዝብ እግዚአብሔርን ልውጋ እንዳይል ፈራሁ። አንተስ ምን ትለህ?

  ReplyDelete
 11. ዲያቆን, መምህራን በንግስ እና በትምህርት ጊዜ እጃችሁን ወደላይ አውጡ እያሉ ምርቃት አይሉት ጸሎት "ይህ እጅ የተባረከ ነው ይህ እጅ ..." በማለት ስው እጁ ዝሎ ሲያዩትም እጃችሁን ወደ ላይ አውጡ እንዳታወርዱት በማለት የመናፍቃንን ስርዓት ቤተክርስቲያን ላይ ሳይ በጣም አዘንኩ:: የሚገርመው ግን እንደወረርሽኝ በየቦታው ይህን ስሰማ እጃችን ወደ ላይ ወጥቶ ወጥቶ እንደ ባቢሎን ህዝብ እግዚአብሔርን ልውጋ እንዳይል ፈራሁ። አንተስ ምን ትለህ?

  ReplyDelete
 12. Dn Daniel cheru medhanialem kale hiwot yasemalen.Ye Ethiopia Orthodox Bet chirstiyan bale bizu tsega ena ye kirse balebe nech neger gin egna lejochu addisun bich enyenafeken kirese aleban tarki alba lenhon new. Abatochachine bich min yargu yegne yesega felagot eko michote ena zemenawiwun eyefelege ater zena yale merha giber ena sereat betchirstiya new yemnfelgeu. Ebakachihu Ezibe chirstiyan tebaberen Emnetachinen ena tefitachinen entebike, Yekidusan Amelak Yiradan

  ReplyDelete