ሰሞኑን በአዲስ አበባ አንድ ትልቅ
የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የአዲስ አበባ ደረጃ አንድ ሌቦች ስብሰባ አድርገው ነበር፡፡ የስብሰባው መሪ ቃል ‹የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ
ሌቦች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?› የሚል ነው፡፡ ስብሰባው እንደተጀመረ አንደኛው የታወቀ ሌባ እጁን አወጣና ‹መፈክሩ ላይ የተጠቀስንበት
ስም ትክክል አይደለም፡፡ ገጽታችንን የሚያበላሽ ነው› ሲል አስተያየት ሰጠ፡፡ ጭብጨባ አዳራሹን ሞላው፡፡
‹ታድያ ምን ይሁን፤ መቼም ሌባ
መሆናችን ርግጥ ነው› አሉ ሰብሳቢው፡፡
‹ጠየም አድርጉት፤ እንደ ባለጌ
ጥፊ ድርግም አይደረግም› አሉ ሌላ አስተያየት ሰጭ፡፡
‹እኮ ምን እንባል› አሉ ሰብሳቢው፡፡
‹ሌሎቹ ሠርቶ አደር፣ አርብቶ አደር፣
ወቶ አደር፣አርሶ አደር ከተባሉ እኛም ‹ነጥቆ አደር› ነው መባል ያለብን›
ይኼው ጸደቀ፡፡
‹የሕዝቡ ምሬት ጨምሯል፡፡ ሕዝቡ
በሌቦች መማረሩን በተደጋጋሚ እየገለጠ ነው፡፡ አንድ ቀን መሣሪያ ቢያጣ እንኳን አካፋና ዶማ ይዞ መነሣቱ አይቀርም፡፡
ከተንተከተከ
እሳቱ ጨምሮ
ክዳኑን ይገፋል
የፈላበት ሽሮ
ሲባል አልሰማችሁም፡፡ ያን ጊዜ
ደግሞ ለሁላችን መግቢያ ቀዳዳው ጠባብ ነው የሚሆነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛው ራሳችን መፍትሔ ማምጣት አለብን› አሉ ሰብሳቢው፡፡
ሰብሳቢው የተገረሙ ይመስላሉ፡፤
አገጫቸው በእጃቸው ይዘው ‹እኔም የእናንተን ያህል ባይሆንም መቼም በዚሁ ስም ተጠርቼበታለሁ፡፡ አሁን የዘረዘርከው ግን ምንድን
ነው?› አሉት፡፡
ሰውዬው ዕውቀት በመጠየቁ ወንበሩ
ላይ ተገላብጦ ተቀመጠና፣ ጉሮሮውን ጠራርጎ ‹መቼም ዕውቀት ማካፈል ደስ ይለኛል፡፡ ኩሩ ሌባ ማለት ከሚሊዮን በታች የማይነካ፤ ዝም
ብሎ በመቶውም በሺውም የማይልከሰከስ ነው፡፡ ልክስክስ ሌባ ደግሞ የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ ጨዋ ሌባ ማለት ደግሞ ሲሰርቅ በሕጉ መሠረት
የሚሰርቅ ማለት ነው፡፡ ሰነድ አዘጋጅቶ፣ ጨረታ አጫርቶ፣ ማስታወቂያ አሠርቶ፣ ቃለ ጉባኤ አያይዞ፤ ዕቃ ገቢ አድርጎ የሚሰርቅ ማለት
ነው፡፡ ባለጌ ሌባ ደግሞ የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ ኢንቨስተር ሌባ ገንዘብ የሚቦጭቀው ከትላልቅ ኢንቨስትመንቶች ብቻ ነው፡፡ መጉመድ
እንጂ መጉረስ የማያውቅ ቆፍጣና፡፡ መጉረድ እንጂ መቁረጥ ያልለመደ ጀግና፤ መቦጨቅ እንጂ መንጨት የማያውቅ ሆደ ሰፊ ማለት ነው፡፡
ሸቃጭ ሌባ ግን ከገቢውም፣ ከወጭውም፣ ከሱቁም፣ ከኅብረት ሱቁም የሚቀነጣጥብ ቀነጣጣቢ ነው፡፡ ነጥቆ ሂያጅና ነጥቆ ገንቢ ስለሚባሉት
የሌባ ዓይነቶች በደንብ መግለጥ አለብኝ፡፡ ‹ነጥቆ ሂያጅ ሌባ› ማለት ካገኘ በኋላ እዚህ ሀገር የማይቀመጥ ሌባ ነው፡፡ ይኼ ዓይነቱ
ሌባ ለሀገሪቱ ዕድገት ዕንቅፋት ነው፡፡ የሀገርን ገቢ ወደ ባዕድ ሀገር የሚያሸሽ ከሐዲ ሌባ ነው፡፡ የሀገር ፍቅር ስሜት ፈጽሞ የሌለው ሌባ ነው፡፡ እዚሁ ነጥቆ እዚሁ መብላት ሲገባው
ሀገሩን ከድቶ ወጥቶ የሚበላ፡፡ እኛ ‹ወጥቶ በል ሌባ› ብለነዋል፡፡ ‹ነጥቆ ገንቢ ሌባ› ግን አገር ወዳድ ሌባ ነው፡፡ እዚሁ ነጥቆ
እዚሁ ፎቁንም፣ ፋብሪካውንም፣ ሆቴሉንም፣ እርሻውንም ይገነባል፡፡ ለሀገሩም አጥብቆ ያስባል፡፡ እዚሁ ነጥቆ እዚሁ የሚሊዮን ብሩን
መኪና ያሽቃብጠዋል፤ እዚሁ የመቶ ሺ ብር ውስኪ ያወርዳል፡፡
ነጥቆ ገንቢ ሌባ ደግ ሰው ነው፡፡
ሃይማኖተኛ ከሆነ ከነጠቀው ገንዘብ ወይ ለቸርች ወይ ለገዳም ይሰጣል፡፡ ነዳያን ያበላል፡፡ ድኻ ይረዳል፡፡ ሃይማኖተኛ ካልሆነ ደግሞ
ለወጣት ማኅበራት ይለግሳል፤ ለቀበሌ ቲሸርት ያሠራል፤ በዓል ስፖንሰር ያደርጋል፤ እንዲህ ያለው ነጥቆ ገንቢ ሌባ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡
ግን ምን ያደርጋል የሀገራችን ሕግና የኢንቨስትመንት ዐዋጁ በቂ ማበረታቻ ለዚህ ሀገር ወዳድ ሌባ አይሰጥም፡፡
በመጨረሻ የማብራራላችሁ ‹ገፋፊ
ሌባና ለካፊ ሌባ› ስለሚባሉት ነው፡፡ ገፋፊ ሌባ ማለት ሥጋ ሲበላ አጥንት የማያስቀር፤ እንጀራ ሲበላ ሞሰብ የማይተርፈው፤ ሻይ
ሲወስድ ከነ ብርጭቆው፤ የደራሲውን ድርሰት ወስዶ የደራሲው ስም የሚያጠፋ፤ ሚስቱን መንጠቁ ሳያንሰው ባሏን የሚገል፤ በመሬትህ ላይ
ባለ ዘጠኝ ፎቅ ሊሠራ አንተን በዘጠነኛው የኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ የሚወረውርህ፣ ሃምሳ ዓመት የኖርክበትን ቤት ወስዶ ከከተማው ሃምሳ
ኪሎ ሜትር አውጥቶ የሚጥልህ ማለት ነው፡፡ ለካፊዎቹ ሌቦች ዝም ብለው ነው፡፡ እዚህም እዚያም ለኮፍ ለኮፍ ነው የሚያደርጉት፡፡›
ሰውዬው ማብራሪያውን ሲጨርስ አድናቂዎቹ
እየሳቁ አጨበጨቡ፡፡ ሰው የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል ይባል የለ፡፡
‹ታድያ አሁን መፍትሔው ምንድን
ነው› አሉ ሰብሳቢው ነገሩ ውስብስብ ብሎባቸው፡፡ አንዱ እጁን አወጣ፡፡
‹ለችግሩ መባባስ ዋነኞቹ ተጠያቂዎች
ከመሐልና ከታች ያሉት ሌቦች ናቸው፡፡ አሁን እኔ ኩሩ ሌባ ነኝ፡፡ ልስረቅ አልስረቅ ሰፊው ሕዝብ አያውቅም፡፡ እይውልዎት፣ መንደር
መንገድ ላይ ያለችውን ዛፍ የሚቆርጠውን እንጂ ደን ውስጥ ያለውን ዛፍ የሚቆርጠውን ማንም አያየውም፡፡ አሁን ለኛ ችግር የሆኑብን
የመንደር ዛፍ ቆራጮች ናቸው፡፡ ለካፊ ሌቦች ከስኳሩም፣ ከጨውም፣ ከድንቹም፣ ከሸማቾቹም ይቀነጣጥቡና ሕዝቡን ያነሣሡታል፡፡ ሕዝቡኮ
ስኳሩ ወደ ሸማቾች ከገባ በኋላ አለቀ ሲሉት እንጂ መጀመሪያውኑ ወደ ሸማቾች ባልመጣው ስኳር ላይ አይበሳጭም፡፡ ሃምሳ ኩንታሉን
ወስደን ሃምሳውን ኩንታል ሩብ ሩብ ኪሎ ብናከፋፍለው ‹ተመስገን› ብሎ ነው ወደ ቤቱ የሚሄደው፡፡ ሥራው ግልጽነት ያለው እንዲመስል
ደግሞ የመጣውን ሃምሳ ኩንታል ከሴቶች፣ ከወጣቶችና ከአዛውንት የተመረጡ ኮሚቴዎችን አሰልፎ እኩል እንዲያካፍሉ ማድረግ ነው፡፡
›
‹ልክ ነው፡፡› አለ አንዱ ሰርቆ
አደር ኢንቨስተር ‹ሰው መብራት ተቆራረጠብን አለ እንጂ የመብራቱን ኬብል እነማን ናቸው ከውጭ የሚያስገቡት ብሎ ጠየቀ? ዱቄቱ ወደ
ሸማቾች በብዛት አልመጣም አለ እንጂ ዱቄቱን እነ እገሌ ብቻ ለምን ከውጭ ያስመጣሉ? ብሎ ጠየቀ፤ አልጠየቀም፡፡ ኮንደሚኒየም በትክክል
አልደረሰኝም አለ እንጂ እነ እገሌ የከተማ ቦታ በካሬ 300 ሺብር የሚጫረቱት ብሩን ከየት ቢያመጡት ነው ብሎ ጠየቀ፤ አልጠየቀም፡፡
‹እገሌና እገሌ የተባሉ ዋና አከፋፋዮች ለምን አስወደዱብን፣ ለምን አሳነሱን› አለ እንጂ ‹ግን እነርሱ የውጭ ምንዛሬ ከየት እያገኙ
ነው ዕቃውን ከውጭ የሚያመጡት?› ብሎ መች ጠየቀ፤ ስለዚህ ችግሩ እታች ያሉት አቀባባይ ሌቦች አሠራሩን ስላላወቁበት ነው ማለት
ነው፡፡ አያችሁ ሕዝቡ የዋሕ ነው፡፡ በጥፍርህ ስትቧጭረው ‹ጥፍሩን ቁረጡልኝ› ነው የሚለው፡፡ ሰውዬውኮ የቧጨረው ጥፍር ስላለው
አይደለም፡፡ በጥፍሩ እንዲቧጭር የሚያዝ ጭንቅላት ስላለው ነው፡፡ ሕዝቡ ‹ጥፍሩን አስቆርጦ› ወደ ቤቱ ይገባል፡፡ ለተወሰነ ጊዜ
ቧጫሪው ዝም ይላል፡፡ ቆይቶ ግን ጥፍሩ ሲያድግ መቧጨሩን ይቀጥላል፡፡ መጀመሪያ ጥፍሩን ያሳደገው፤ ተቧጨር ብሎ መብት የሰጠው ማን
ሆነና፡፡ አሁንም ያስቸገሩን ራሶቹ አይደሉም፡፡ ጥፍሮቹ ናቸው፡፡› እንደ ድጓ አድራሽ በሊቃውንት ፊት ዕውቀቱን ያስመሰከረ መስሎት
ትከሻውን ሰበቀ፡፡
ሰብሳቢው ግራ እየገባቸውም ቢሆን
‹ሐሳቡን እንጠቅልለው፤ የመቋጫ ሐሳብ አምጡ› አሉ፡፡
ሁለት ሰዎች ተረዳድተው ያዘጋጁትን
የአቋም መግለጫ ይዘው ወጡ፡፡ እነርሱ የአቋም መግለጫውን ሲያቀርቡ ተሰብሳቢዎቹ ወረቀትና ስክርቢቶ አዘጋጁ፡፡
አንደኛ፡- ኅብረተሰቡ ስርቆትን
እንዲጠየፍ ስለ ስርቆት በመገናኛ ብዙኃን ትምህርት ይሰጥ(ይኼ ሲነበብ አንድ አምስቱ በቲቪና ሬዲዮ የሚቀርበውን ማስታወቂያ ለመሥራት
እንዴት ከባለ ሥልጣናቱ ጋር እንደሚሠሩ ተንሾካሾኩ፤ አንድ ሁለቱ ደግሞ በእነርሱ ሬዲዮ ጣቢያ ይህን ፕሮግራም ለመሥራት የስፖንሰር
ገንዘብ ሲቦጭቁ ታያቸው)
ሁለተኛ፡- በየቀበሌውና በየደረጃው
ሕዝቡ ሌቦችን እንዲያጋልጥ ይደረግና ርምጃ ይወሰድ(የተወሰኑት ተሰብሳቢዎች ለቀበሌ ስብሰባዎች ሞንታርቦ፣ ውኃና ኮፍያ ያለ ጨረታ
ለማቅረብ ተጠቃቀሱ)
ሦስተኛ፡- ሌብነትን የተመለከተ
ዜማ በታዋቂ አርቲስቶች እንዲዘጋጅ ይደረግ (አርት ነክቶናል የሚሉ ነጥቆ አደር አርቲስቶች የሚዘጋጀውን የፀረ ስርቆት ቅስቀሳ ከእነርሱ
እንዳይወጣ ዘየዱ)
አራተኛ፡- ስለ ስርቆት አስከፊነት
የሚያስተምር ቢል ቦርድ በመላ ሀገሪቱ ይተከል (የማስታወቂያ ድርጅት ያላቸው ተሰብሳቢዎች ይቺ ፕሮጀክት ከኛ አታልፍም ብለው ማሉ)
አምስተኛ፡- የፀረ ስርቆት ቀን
በየዓመቱ ይከበር፡፡ (ቲሸርትና ኮፍያ፣ መድረክና መስተንግዶ የሚያቀርቡ ተሰብሳቢዎች ዓመታዊ ገቢ ተገኘ ብለው ጮቤ ረገጡ፡፡)
ተሰብሳቢዎቹ ሰወጡ የአዳራሹ ዘበኛ
በኀዘን ለጓደኛቸው ‹በሬ ሞተና ፍትሐት ሲፈታ ከበሮው ድምጹ እንዳይሰማ ‹ትሽ፣ ትሽ፣ ትሽ› ይል ጀመር፡፡ ከዚያ በፊት ‹እድም፣
እድም፣ እድም› ሲል ይሰሙት የነበሩት ጽናጽንና መቋሚያ ‹ምነው ዛሬ ያለወትሮህ ድምጽ እንዳይሰማ ‹ትሽ፣ ትሽ፣ ትሽ› ትል ጀመር›
ብለው ቢጠይቁት ‹የሞተው በሬ፤ የሚመታው የበሬ ቆዳ ሆኖብኝኮ ነው፡፡ እንዴት ከበሬ ቆዳ ተሠርቼ በሬ ሞተ ብዬ ከበሮ ልምታ› አላቸው
ይባላል ብለው ተረቱ፡፡
ግሩም እይታ ነው። እስኪ ለሌቦቻችን አስተዋይ ልቦና ይስጣቸዉ!!!
ReplyDeletenice view !
ReplyDeleteJust I sey waaaw god bless you
ReplyDeleteይህን ነው መነጋገር … በጣም ይገልጸናል፡፡
ReplyDelete“ድል ለሰርቶ አደሩ!”
ድል ለሰርቶ አደሩ! ለሠፊው ሕዝብ!
ነግቶ ልፋቱን ብቻ ለሚያስብ!
ሲሰራ እንጅ ሲከስብ፣
‘ኪራይ’ ለማይሰበስብ!
ከፈጣሪው ጋር ሲያወራ፣
ማስታወቂያ ለማይሰራ፡፡
ከእውነት ጋር ተጋብቶ በፅኑዕ ቃል ውል፣
ሲደክም ብቻ ለሚውል፡፡
ድል ለሰርቶ አደሩ! ለሠፊው ሕዝብ!
ነግቶ ልፋቱን ብቻ ለሚያስብ!
“ገደል ለሠርቆ አደሮች!”
ገደል ለሠርቆ አደሮች! ለሰርቆ አደሩ!
ያልተጠሩበትን ድንኳን ሲሰብሩ፣ እንዲሰበሩ!
ገደል ለነጥቶ አደፎች፣ ለነጥቶ አደፉ፣
ከስድ ቤት ተነስተው የሰው አጥር ለሚገፉ፣
በደልን ላልተጠየፉ፣
በእዉር ድምብስ ጉዟቸው ደህነኛውን መንገደኛ ከሚያነቅፉ፣
ራሳቸውን ችለው እንዲደፉ ፣
ገደል ለነጥቶ አደፉ፡፡
daniye werk betam temechitognal likachewun negerkilgn!
ReplyDeleteሰሚ የለም እንጂ ሰሚማ ቢኖር ኖሮ ...
ReplyDeleteሌብነት ዋልታና ማገር ሆኖ ያዋቀራት አገር አንደ ትሮይ በአንድ ሌሊት ብትጠፋ ጥሩ ነበር፤ በጥፋቷ ላይ በፍጥነት ለመገንባት ያስችላልና፡፡ ኢትዮጵያ የተያዘችው እየገዘገዘ በሚያጠፋ ደዌ ነው፡፡ ምናልባት በሚቀጥሉት 2ዐ ዓመታት የቀድሞ ዩጎዝላቪያ (ያውም ትንሽ ኀሊና ካለ)፣ ወይም የአሁኗ ባድማ ሶማሊያ ከመሆን የምታመልጥ አይመስልም፡፡ እድሜ ለሰርቆ አደሮች ከ90 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ለተሻለ የማኀበረሰብ እድገትና ልዕልና ከማብቃት ይልቅ የላሸቀ ሞራል ሰለባ አደረገ፡፡
ReplyDeleteሰርቆ አደሮች ሆይ፣
በቤተ መንግሥት ያላችሁ "ኩሩዎች"፣
በቤተ ክህነት ያላችሁ “ብሩካን”
በቤተ መስጅድ ያላችሁ “ኢማሞች”
በቤተ እውቀት ያላችሁ “ምሁራን/ልሂቃን”
የመካከለኛ እርከን አመራር “ዘዋርያን”
የበታች እርከን አከናዋኝ “ተጋዳላይ”
የሰርቆ አደር ማምረቻ “ሊጎች” ሆይ፤ ሁላችሁም በያላችሁበት ደስ ይበላችሁ፡፡ ኢትዮጵያ ለ 1ዐዐዐ ዘመን የናንተ ሆናለችና ሐሴት አድርጉ፡፡
በመስኩ ጨፌ በልማቱ ሜዳ፣ በኢንቨስትመንቱ ፏፏቴ፣ በሕዳሴው ግድብ ምንጭ ተጠራሩ፣ ተፈቃቀሩ፡፡ ውድሽና ውዴ፣ ለዛሬ ካለሆነ እኔ አንቺን መውደዴ ተባባሉ፡፡ በሰሎሞን ማኃልይ ተነጠቁ እስከ ሰማይ፡፡
የሚሰርቁ ብጹዓን ናቸው፤
“መንግሥተ ሰማያት” (ኢትዮጵያ) የእነርሱ ብቻ ናትና
ተሰፋዬ
የማይነጥፍ ምንጭ አዕምሮ የሰጠህ አምላክ ይመስገን።ረዥም ዕድሜ እንዲሰጥህ ተመኘሁ
ReplyDeleteየመልካም አስተዳደር ተሰብሳቢዎች ምን ትላላቸሁ?
ReplyDeleteዳኒ፣
ReplyDeleteታዲያ አንተን ከየትኛው የሌባ ምድብ እንመድብህ?
Please Guess
Deleteሰው የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል
Deleteሰው የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል
DeleteGOD BLESS YOU
ReplyDeleteየሞተው በሬ የሚመታው የበሬ ቆዳ
ReplyDeleteያስቃል እኮ ወለል ብሎ ታየህ ኣምላክ ልቦነናህ ያብራው ሙሐዘ ጥበባት!
ReplyDeleteፈሪዎቹ ፀሃፊዎች እነኚህን ሌባ ተሰብሳቢዎች የልማት አርበኛ እያሉ ሲገልጿቸዉ ፤ ጎመን በጤና የሚሉት ፀሃፊዎች ዝምታን ይመርጣሉ:: ጎበዞቹ እንዲህ አይነት አንገብጋቢ ፅሁፍ በመፃፍ ህዝብን ያነቃሉ:: እጅግ በጣም ተቆርቋሪ የሆኑት ሰምና ወርቁን ለይተዉ እና ባለቤት ሰጥተዉ ይፅፉታል:: ለምሳሌ የዚህ አይነቱን መልእክት ፕሮፌሰር መስፍን ቢሆኑ ያስተላለፉት እና ሰብሳቢዎቹ በረከት ስምኦን እና ስብሃት ነጋ ቢሆኑ የፕ/ር መልእክት ሊሆን የሚችለዉ:- “ የሌቦቹን ስብሰባ የመሩት በረከት ስምኦን እና ስብሃት ነጋ ናቸዉ :: እንግዲህ እነዚህ ሁለት ደናቁርት ስብሰባዉን ሲመሩ ….. “
ReplyDeleteWow nice view Dn Dani.yihn ewket yeseteh Egziabher yimesgen.
ReplyDeleteእኛ ሀገር ሌብነት መብት አርገው ለሚያስቡ ቆንጆ መልክት
ReplyDeleteአንዱ እኔ እንዳልሆን..........
ReplyDeleteEndet ke bere koda teserche bere mote biye kebero lemta...!!!
ReplyDeleteAmazing literature danie
ReplyDeleteThe tyrants can't read,hear the peopel voice,but they only can tell,until the peopel power tell them.Thank you Dani!The canning man!!!!!
ReplyDeleteThe tyrants can't read,hear the peopel voice,but they only can tell,until the peopel power tell them.Thank you Dani!The canning man!!!!!
ReplyDeleteLebochachins min tilalachu?
ReplyDeleteለሌቦች አስተዋይ ልቦና ይስጣቸዉ!
ReplyDeletearif view.
ReplyDeleteBetam tekikile thank ub
ReplyDeleteከተንተከተከ እሳቱ ጨምሮ
ReplyDeleteክዳኑን ይገፋል የፈላበት ሽሮ
ወታደር የሚለውን ቃል ምንጩን ዛሬ ገና አገኝሁት።
ReplyDeleteአመሰግናለሁ!
ሙሃዘ ጥበባት ዲያ ዳኒ ከመይ አሎካ ?
ReplyDeleteአምላክ ናይ አገልግሎት ዘመንካን ህይወትካን ይባርክን ይቀድስን !!!
አነ ሐደ ካብ ተከታታሊ ብሎግካ + ኩሉ ስብከትካን ጽሑፋትካን ኢየ ። ውዳሴ ከንቱ ከይኮነካ እምበር "ተረፈ አበው" ኢለ ዝጽውዓካ : ቀጽሎ በርትዕ አይዞ !
አምላከ ቅዱሳን ምሳካ ይኩን ።
ሎሚ ግን ካብ April 22 ዝኮነ ጽሑፍ አይጸሐፍካን!
1ይ, ናይ ሰላም ዲካ ጠፊእካ ? ሰላም ክትህሉ ልባዊ ትምኒተይ ኢዩ ።
2ይ, አብ ዝሐጸረ ግዜ መሃሪ ዝኮነ ጽሑፋትካ ሒዝካ ብመንገዲ ብሎግካ ኣሎኩ ሰላም ኢየ ኢልካ አብ ዝሐጸረ ግዜ ክትመጸና ብናፍቆት ንጽበየካ።
Sorry አማርና የንብብን ይዛረብን ኢየ ጽሕፈት ግን ብዙሕ ዘይመልክ ኢየ ብትግርና ጽሒፈልካ።
አምላከ ቅዱሳን ምስ ኩልና ይኩን ። አሜን !
thank you dani
ReplyDeleteአሁን በሀገራችን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣም አስተማሪ ፅሁፍ ነው።
ReplyDeleteዳኒ እንዲሁ እዳለህ ክብርህ ሳይቀንስ ረዥም እድሜ እንድትኖር ነው የምመኝልህ።
በፀሎትህ አስበኝ!!!
it is very nice persuading for EPRDF politics.
ReplyDelete