Wednesday, March 30, 2016

‹ሀገር ማለት ሰው ነው›፤ እስኪ ሙት በለኝ!

click here for pdf


ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገርሙኝ ዘፈኖች አንዱ ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው ነው፡፡ እሥራኤላዊና ጂፕሲ ይህንን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን? እላለሁ፡፡ አይሁድ በመላው ዓለም ለ1900 ዓመታት ያህል ተበትነው ሲኖሩ በየአካባቢው ሰው ነበራቸው፤ያውም እንደ ብረት የጠነከረ ማበረሰብ፤ ሀገር ግን አልነበራቸውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ አይሁድ ሀገር ፍለጋ ከሺ ዓመታት በላይ መኳተን አልነበረባቸውም፡፡ በአውሮፓ የሚኖሩት ጂፕሲዎች የታወቀ ማኅበረሰብ አላቸው፡፡ ነገር ግን ሀገር የላቸውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ቢሆን ኖሮ ጂፕሲ የሚባል ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ጂፕሲ የሚባል ሀገርም ይኖር ነበር፡፡ ግን የለም፡፡
በአሜሪካ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ‹በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን› የምትባል ሀገር ግን የለቺም፡፡ 1.3 ሚሊዮን የሚደረሱ ግሪኮች በአሜሪካ ይኖራሉ፡፡ ‹የአሜሪካ ግሪኮች› የምትባል ሀገር ግን የለችም፡፡ ‹ግሪክ ሲሠራ አሜሪካ ይኖራል፣ ሲያረጅ ግሪክ ይጦራል› የተባለው ሀገር ሰው ብቻ ስላልሆነ ነው፡፡ 
ሰዎች ተሰብስበው ሀገር ሊመሠርቱ አይችሉም፡፡ በየሀገሩ የተሰበሰቡ ማኅበረሰቦች ‹ኮሙኒቲ› ይባላሉ እንጂ ሀገር አይባሉም፡፡ ሀገር ሀገር ለመሆንና ለመባል ከሰው በተጨማሪ የምትፈልገው ብዙ ነገር አላትና፡፡ ሀገርን ሀገር ለማስባል መሬትም ያስፈልጋል፤ መሬት ሳይኖርህ ሰው ስለሰበሰብክ ብቻ ሀገር ልትሆን አትችልም፡፡ ያውም የእኔ የምትለው፣ የምትሞትለትና የምትለፋለት ታሪካዊ መሬት ያስፈልግሃል፡፡ አይሁድ በ1930 አካባቢ በኡጋንዳ ኡዋሲን ጊሹ (Uasin Gishu County) በተባለ ቦታ እንዲሠፍሩና ሀገር እንዲኖራቸው ታስቦ ነበር፡፡ እንደ ቴዎዶር ኸርዝል ያሉ ታላላቅ የጽዮናዊነት መሪዎችም ለጊዜውም ቢሆን  ተስማምተውበት ነበር፡፡ ብዙኀኑ አይሁድ ግን ‹ሀገር ማለት የሆነ መሬት አይደለም፡፡ ታሪካዊ መሬት ነው› ብለው ተቃወሙት ሀገር ማለት የሆነ መሬት ብቻ ቢሆን ለአይሁድ ከዛሬዋ እሥራኤል ይልቅ በአየር ንብረትና በተፈጥሮ ማዕድን፣ ብሎም በአቀማመጥ ኡጋንዳ ትሻላቸው ነበር፡፡ 

ባድሜ ለምትባል ከጦርነቱ በፊት ብዙው ሕዝብ ሰምቷት ለማያውቅ መሬት የተደረገውን ጦርነት የረሳ ሰው ነው ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚል፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለባድሜ የተደረገው ጦርነት ለማን የተደረገ ነው ሊባል ነው፡፡ በሄግ ፍርድ ቤት የነበረው ክርክርስ የመሬት ክርክር እንጂ የሰው ክርክር ነበር እንዴ?
ሀገር ማለት ሰው ቢሆን ኖሮ ሰው ስለ ሀገሩ ሲያነሣ ወንዙን፣ ተራራውን፣ ሸለቆውን፣ ሜዳውን፣ ጫካውን እያነሣ ለምን ይዘፍን ነበር ፡፡
‹ያገሬ ተራራ ወንዛ ወንዙ ለምለም
እማማ ኢትዮጵያ ኑሪ ለዘላለም› ለምን ይል ነበረ፡፡
ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ይሄ የኔ ክልል፣ ጎጥና መንደር ነው የሚለው ክርክር ከየት ይመጣ ነበር? ሀገር ማለት ሰው ከሆነ የተለየና የታወቀ የሀገር ድንበርና ካርታ ለምን ያስፈልግ ነበረ? ሰውማ የትም ነው የሚኖረው፡፡ ካርታ አያሻውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለምን የአብዛኞቹ ሀገሮች ብሔራዊ መዝሙር ስለ መሬቱና ስለ ድንበሩ ያወራል? ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ለሰው ፓስፖርትና ቪዛ ለም ያስፈልገዋል? ሰው ያለበት ቦታ ሁሉ ሀገሬ ስለሆነ ለምን እንደፈለግኩ ወጥቼ አልገባም? አንድ ሰው ወደ አንድ ሀገር ገባ የሚባለው ወደ መሬቱ ሲገባ እንጂ የሀገሩን ሰው ሲያገኝ ነው እንዴ? ምናልባትም ከአንታርክቲካ በቀር ቪዛ መጠየቅ ያለበት ሀገር አልነበረም፡፡ እርሱ ሰው የለበትምና ‹ሀገር ማለት ሰው ነው› የሚለው አይመለከተውም፡፡ ሀገር ማለት ሰው ከሆነ በሰማይ የሚሄድ አውሮፕላን ‹የአየር ክልሌን ጣሰ› ብሎ መሟገት ምን የሚሉት ሞኝነት ነው? ሰውን አልጣሰ፣ የጣሰው አየር ነው፡፡
ደግሞም አገር ማለት መሬት ብቻ አይደለም፡፡ ያማ ቢሆን ኖሮ አንታርክቲካ ሀገር ይሆን ነበር፡፡ ያማ ቢሆን ኖሮ በዓለም ላይ የሚገኙ ወደ ሃምሳ የሚጠጉ ሰው አልባ ደሴቶች(nonecumene)‹ሀገር› ተብለው በተባበሩት መንግሥታት ይመዘገቡ ነበር፡፡ ሀገር ማለት መሬት ቢሆን ኖሮ መሬት ያለው ሁሉ ሀገር ይኖረው ነበር፡፡ የአሜሪካ ሕንዶች፣ የአውስትራልያ አቦርጅኖች፣ ከጥንት ጀምሮ የሚኖሩበት መሬት አላቸው፡፡ የራሳቸው የሆነ ሀገር ግን የላቸውም፡፡ ደቡብ ሱዳናውያን የራሳቸው የሆነ የሚኖሩበት መሬት ነበራቸው፤ ሀገር ለመሆን ግን መዋጋት ነበረባቸው፡፡ ደቡብ ሱዳኖችን ያን ሁሉ ዘመን ያዋጋቸው የመሬት ጥያቄ ሳይሆን የሀገርነት ጥያቄ ነው፡፡ የራሳቸው ፖለቲካዊ መሬት አግኝተው እንኳን ሀገር ለመሆን ገና እየተሠሩ ነው፡፡ ፍልስጤማውያን ይብዛም ይነስ የሚኖሩበት መሬት አላቸው፡፡ አገር ግን የላቸውም፡፡
አገር ከዚህ ሁሉ በላይ ነው፡፡ ሰው፣ ሰው የኖረበትና ታሪክ የሠራበት መሬት፣ ማኅበረሰብ ከማኅበረሰብ፣ ሰው ከሰው፣ ሰው ከማኅበረሰብ፣ ሰው ከመሬት፣ ሰው ከአራዊት፣ ሰው ከተፈጥሮ፣ ሰው ከወራሪ ጋር የነበረው ትግል፣ ውጊያና ወዳጅነት፤ የተረተው ተረት፣ ያወጋው ወግ፣ የፈጠረው አፈ ታሪክ፣ ያከማቸው ትዝታ፣ ሰው ለመሬቱ፣ ለወገኑና ለእምነቱ የከፈለው መሥዋዕትነት፤ የዘፈነው ዘፈን፣ ያቅራራው ቀረርቶ፣ የፎከረው ፉከራ፤ ያገኘው ድልና የተሸከመው ሽንፈት፤ ያደረሰው በደልና የደረሰበት በደል ይሄ ሁሉ ነው ሀገር፡፡
መገለጫው ቅርስ፣ መዋሐጃው ባህል፣ መታያው ልብስና መዋቢያው ጌጣጌጥ፣ መገናኛው ቋንቋ፣ መዝናኛው ጭፈራ፤ ማስተማሪያው ተረት፣ መክበሪያው ዓመት ባል፣ መጠበቢያው ምግብ፣ መቆዘሚያው እንጉርጉሮ፣ መተከዣው ልቅሶ፣ መተኪያው ልደት፣ ማሳረጊያው ቀብር፤ መገምገሚያው ምግባር፣ ማነወሪያው ነውር፤ መኩሪያ ጀግንነቱ፣ ማፈሪያ ገመናው፤ መደበቂያ ቤቱ፣ መመረሪያ ጫካው፤ ይሄ ሁሉ ነው ሀገር፡፡ ታሽቶ ተገርኝቶ ያመጣው አንድነት፣ ተጣልቶ ተባልቶ ያመጣው ልዩነት፣ እንደ ዘሐ ዘጊ የተጠላለፈው፣ እንደ እግር ሠንሠለት የተቆላለፈው፣ ሲፈተል፣ ሲገመድ፤ ሲባዘት፣ ሲዳውር፤ ሲከካ፣ ሲሰለቅ፤ ሲጣላ፣ ሲታረቅ፤  ሲያውቅና ሲማይም፤ ሲሠለጥንና ሲደኸይ፤ ሲሰፋና ሲጠብ፤ የኖረውና የኖረበት፣ የኖረለትም ነው ሀገር፡፡
ሀገር ትዝታ ነው፡፡ የትም ቦታ ስትሄድ ጠምዶ የሚያመጣህ፡፡ ምንም ሥጋ ብትቆርጥ ከብቱ ትዝ ይልሃል፤ ምንም ቢች ዳር ብትዝናና ወንዙ ትዝ ይልሃል፤ ምን በሽቱ ብትታጠን አፈሩ ይሸትሃል፤ ምን በሥጋጃ ላይ ብትሄድ ጉዝጓዙ ይመጣብሃል፡፡ በኮምፒውተር እየሠራህ ያቦካኸው ጭቃ ይናፍቅሃል፤ በጄት እየበረርክ አህያና በቅሎው ያምርሃል፤ ማንሐተን ተቀምጠህ ሰባተኛ፣ ሎንደን ተቀምጠህ ቂርቆስ፣ ኖርዌይ ሆነህ ጅግጅጋ፣ ካናዳ ሆነህ ሐረር ይወዘውዝሃል፡፡ ሀገር ማለት ትዝታ ነው፡፡
ሀገር ማለት ከምትገልጠው ብታስበው፣ ከምትኖርበት ብትሞትበት፤ ከምትስቅለት ብታለቅስለት የምትመርጥለት ነገር ነው፤ ሀገር ማለት ትተህው ብትሄድ ትቶህ የማይሄድ፣ በራቅከው ቁጥር ልብህ ውስጥ የሚቀር፣ ባወቅከው ቁጥር የምትንገበገብለት፤ በተረዳኸው ቁጥር የምትሳሳለት፣ አንተን እርሱ ውስጥ እንደምታገኘው ሁሉ እርሱንም አንተ ውስጥ የምታገኘው፤ የተሠራህበት ውሑድ፤ የተቀረጽክበት ማንነት ነው ሀገር፡፡
ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ዘመድ የሌለው ሰው ወደ ሀገሩ ለመምጣት ባልናፈቀ ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ዘመዶቹ ሁሉ ከእርሱ ጋር ውጭ የሚኖሩለት ሰው ‹ሀገሬን ሀገሬን› እያለ መከራ ባላየ ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ሰዎች በየዘመናቱ የበደሉት ሰው ሀገሬ በደለችኝ ባለ ነበር፡፡ ሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ሰው ስለ ሀገሩ ሲያስብ ተራራውና ወንዙ፣ አዕዋፉና አራዊቱ፣ ማሳውና ቀየው ለምን ትዝ ይለው ነበር፡፡ በሀገር ማለት ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ያሸነፈ አትሌት፣ ድል ያደረገ ኳስ ተጨዋች ባንዴራው ሲሰቀል ለምን ያለቅስ ነበር?
‹አዙረሀ አዙረህ ሀገሬ መልሰኝ
በሹም ታዘዘ አፈር አታልብሰኝ› ብሎ ለምን ያንጎራጉር ነበር፡፡ ዐጽሙ በአፈሩ እንዲያርፍ ለምን ይናዘዝ ነበር፡፡ ለምን ሙሾውን፣ የሠርግ ዘፈኑን፣ ወጉን ማዕረጉን ይፈልገው ነበር፡፡
ሀገር በአርምሞ እንጂ በንግግር፣ በተግባር እንጂ በዝርዝር ሊናገሩለት የማይቻል ነገር ነው፡፡ ውጥንቅጥ ሰበዞች የሰፉት ሞሰብ፣ዓይነተ ብዙ  ድርና ማጎች የሸመኑት ጋቢ፣ ልዩ ልዩ ቅመሞች የሠሩት ወጥ፣ ብዙ ገባሮች የፈጠሩት ዓባይ፣ ብዙ ትውልዶች የከመሩት ተራራ፣ ከአራቱ አቅጣጫ ተሰብስቦ በአንድ ወፍጮ የተፈጨ እህል፣ ከየአበባው ተቀስሞ በአንድ ቀፎ የተሠራ ማር፣  ከየእህሉ ወጥቶ በአንድ ማድጋ የተጠመቀ ጠላ፣ ከየ እንጨቱ ተለቅሞ በአንድ ጽንሐ የታጠነ ዕጣን ነው ሀገር፡፡
ሀገር ማለት ሰው ነው? እስኪ ሙት በለኝ

49 comments:

 1. Great Idea Daniel. Indeed Country means the Soil that made us who we are ...I agree. I love your blog and I also have a poetry blog check it please at http://gonder.blog.com/

  ReplyDelete
 2. ዳ/ዳኒ
  የዘመኑን ወፍ ዘራሽ አለቆችና አጫፋሪዎቻቸውን ግልብ አስተሳሰብ አሳፋሪነት ጎልቶ ያወጣ መጣጥፍ ነው፡፡ ስለግጽነትህ እግዚያብሔር ይባርክህ፡፡

  ReplyDelete
 3. adnkyalehu grum new ene mut alelem nurna bzu ey aytehm akaflen bay negn edme yisth diakon daniel

  ReplyDelete
 4. በትክክል ከተረዳነውማ ለኛ ለሰው ልጆች ሀገራችን ምድር ናት። በሞት እስክንለያት ድረስ። ይሄ በተለያየ ግጭት ምክንያት የሰው ልጆች አብረው ተከባብረው ምድርን አልምተው መኖር በተሳናቸው ጊዜ የተፈጠረው 'የካርታ ሀገር' ከሰው ልጅ ጋር ያለው ትስስር ፖለቲካዊ እንጂ ተፈጥሮአዊ አይደለም። የ አዳም ሀገሩ ምድር ናት። የአዳም ልጆችም እንዲሁ። ስለዚህ ሰው ሆነን መኖር እስከቻልን ድረስ ምድር ላይ በየትኛውም ስፍራ ብንቀመጥ ለኔ ከሀገራችን አልተሰደድንም እላለሁ። እናም ሀገር ማለት ሰው ነው፤ ሰው ሆኖ መኖር እስከቻለ ድረስ። ሰው መሆን መቻልስ ምን ማለት ነው ቢሉ:
  1)ጥሮ ግሮ፣ በላቡ የምድርን እሾህ አሜከላ አስወግዶ ምድርን አልምቶ የሚኖር
  2)ሌላ ሰው ለፍቶ ያመረተውን ወይም ያስገኘውን እርሱ ራሱ ካመረተው ወይም ካስገኘው ጋር በንግድ ተለዋውጦ እንጂ በሀይል ቀምቶ ለመኖር የማይፈቅድ
  3) በጋራ ለመኖር የሰው መብት መጋፋትን የማይፈቅድ
  ወዘተ ወዘተ ...

  ReplyDelete
  Replies
  1. Tiru new, gin ychalal? Ante rasih/rasish tadergewaleh? Endeza madreg yemichal bihon noro Iyasu le 12tu negede Israel rst balakefafele, bota balkelele neber.

   Delete
  2. It is the other way we shall see about country, however; a serious jock when we bring it real. IT seems like true but not. Nothing like MOTHERLAND unless we are going to be BANDA (one who is going betray his/her country). If you may not agree you would have your own reason differently.y).

   Delete
 5. ዳንኤል በጣም ጥሩ እይታ ነው ቀጥልበት

  ReplyDelete
 6. YEBIZU GIZIE HIMEMEN ZARIE DASESKEW. LONG LIVE DANI.

  ReplyDelete
 7. ሁለገብ መክሊትህን እንድትተገብር የፈቀደልህ አምላክ ይክበር ይመ ስገን ።

  ReplyDelete
 8. ሀገር ማለት ትተህው ብትሄድ ትቶህ የማይሄድ፣ በራቅከው ቁጥር ልብህ ውስጥ የሚቀር፣ ባወቅከው ቁጥር የምትንገበገብለት፤ በተረዳኸው ቁጥር የምትሳሳለት፣ አንተን እርሱ ውስጥ እንደምታገኘው ሁሉ እርሱንም አንተ ውስጥ የምታገኘው፤ የተሠራህበት ውሑድ፤ የተቀረጽክበት ማንነት ነው ሀገር፡፡

  ReplyDelete
 9. እድሜህን ያርዝምልን፡፡ልክ ብለሀል፡፡

  ግዜክስ

  ReplyDelete
 10. Girum tsihuf! Egziabher Hagerachin Ethiopiyanina Hizbochuan Yitebikilin! Ethiopia le Zelalem Tinur!

  ReplyDelete
 11. ትክክለኛ አገላለፅ ነው ሀገር ማለት ሰው ነው? እስኪ ሙት በለኝ ትልቅ እውቀት ነው ያገኘሁት እግዚአብሔር ይስጥልን ዲያቆን ዳንኤል

  ReplyDelete
 12. Beewnet betam des yemil tshuf new!!!eyitah betam liyu new!!!ketilbet!!!enwedihalen!!!

  ReplyDelete
 13. EGZIABHERE YEBATKEHE BETESEBOCHEHIN YETEBEKILIH

  ReplyDelete
 14. አገር በታሪክ በቋንቋ በሀይማኖት በልምድ በተስፋ በደስታና በመክራ ተሳስሮ የሚኖር
  አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው። አገር ማለት አያት ቅድም አያት
  የተወለዱበት አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየተከላከሉ ለሕዝብና ለመንግስት
  የሚጥቅም ሥራ ሠርትው እድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻችውን ተክተው የተቀበሩበት
  ጉድጓድ ነው። በመወለድ እትብት በመሞት አካል ከአፈሩ ጋራ ስለ ሚዋሐዱ የአገሩ አፈር
  ሕዝብ በላዩ የሚኖርበት ማለት ነው። እግዚአብሔር ከምድርዋ ፍሬ ሕይወት እንዲገኝባት
  በማድረጉ አገር እየጠባች የምታሳድግ ፍቅርዋ በአጥንት በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ
  የሆንች እናት ማለት ነው። ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን
  በማየት ስለ ማደግ አባቶች በሕህወትና በሞት የሥሩበት ደግ ሥራ በአእምሮ ታትሞ ስለ
  ቀረ በአገር እስካሉ ሲታይ በስድት ሲሆኑ ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው።
  አገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሀብት በመሆኑ ድህነትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስከ
  ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድም አያትና ከአባቶች በጥብቅ የተሰጠ ያደራ ገንዘብ
  ነው። አገር!
  ከታሪክና ምሳሌ (3 ኛ ምጽሐፍ)

  ReplyDelete
 15. Tnx 4 ur outlook!!! May some people say sth.on ur script. Leave them alone.keep it up!! Millions follow u!!!

  ReplyDelete
 16. they coined the term "Hager malet sew new" to make citizens not to think about their own land sold and arbitrated by government. It is their foolishness to think that Ethiopians are that ignorant to accept their non-sense and meaningless ideology. Take simple example of wolkait Tekede's case, if country means people the Amharic speaking farmers would have been able to teach their kids in Amharic. what a Cheep game ...

  ReplyDelete
 17. A wonderful comment I have never expressed
  ብዙ ትውልዶች የከመሩት ተራራ፣ ከአራቱ አቅጣጫ ተሰብስቦ በአንድ ወፍጮ የተፈጨ እህል፣ ከየአበባው ተቀስሞ በአንድ ቀፎ የተሠራ ማር፣ ከየእህሉ ወጥቶ በአንድ ማድጋ የተጠመቀ ጠላ፣ ከየ እንጨቱ ተለቅሞ በአንድ ጽንሐ የታጠነ ዕጣን ነው ሀገር፡፡

  ReplyDelete
 18. አዎ ሃገር ማለት በቃላት የማይገለጽ በተግባር የሚኖሩት፤የሚሞቱለት የማንነትና የህልዉና መገለጫ ነዉ፡፡ደስታም ሆነ ሃዘን የሚያምረዉ በሀገር ነዉ፡፡የእኔ የሚለዉ ሀገር የሌለዉ ሰዉ የዉሃ ላይ ኩበት ነዉ፡፡ሀገር የማንነት መገለጫ ባይሆን ኖሮ ለባድሜ መሬት ስንቱ ኢትጵያዊ እንደቅጠል ባልረገፈ ነበር፡፡ዛሬም ለሱዳን እንደ ዳቦ ተቆርሶ ሊሰጥ የተዘጋጀዉ መሬት እንደሳት ባላቃጠለዉ ነበር፡፡አዎ ሀገር እናትም፤አባትም ወገንም ጠላትም እርሃብም ደስታም ጥጋብም ….ሁሉንም ናት፡፡ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሄር ይባርክህ፡፡ሃገር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያልገባቸዉ በርካታ ከንቱዎች አሉና ይማሩበታል ብየ አስባለሁ፡፡

  ReplyDelete
 19. ይህ ጽሑፍ የተከተበው በሥጋዊ ዕይታ ነው ወይስ በመንፈሳዊ ዕይታ?
  ታዲያ ክርስቶስ መንግሥቴ በዚህች ምድር አይደለችም ለምን አለ?
  ሀገርን ሀገር የሚያሰኘው ዋናው ሰው ነው፡፡
  ምድርንም ሀገር የሚያሰኛት ሰው ነው፡፡
  ጌታም የሞተው ለሰው እንጂ ለምድር አይደለም፡፡
  እኔ ልሙት ተሳስተሃል፡፡

  ReplyDelete
 20. dani ene yehenen comment lemadereg akim selelelegne egiziabeher rejim zemen setoh hulem tsufochehen endaneb yerdan 10q dani

  ReplyDelete
 21. ሀገሬን ተውሁና ብሄድ እሰው ሀገር
  እንደምን ይመራል የምሰማው ነገር። ማን ነበር ያለው?

  ReplyDelete
 22. በእውነቱ እጅግ ጥልቅ ሃሳብ ነው ያጋራኽን። ከሁሉ የገረመኝ ግን የመለስን ደንቁርና የበለጠ አጉልቶ ያሳየኝ መሆኑ ነው።

  ተስፋዬ

  ReplyDelete
 23. አንጀት አርስ!!!

  ReplyDelete
 24. Really Interesting - Thank You!

  ReplyDelete
 25. እዮቤል ደጀንApril 2, 2016 at 6:08 PM

  ድምፅእ ማጉያ አገኘን ብላችሁ በተለያየ ሚዲያ ሀገር ማለት ለኔ ሰው ነው እያላቹ የምትለፍልፉ ከዚህ ፁሁፍ እንማር. እራሳቹ ተሳስታቹ ሰውን አታሳስቱ. ዲ.ን ዳንኤል. እግዚአብሔር ይመስገ.

  ReplyDelete
 26. ትክክል ነህ ዳኒ ኣገር ምድሪቱህዝቡም ኣንድላይ ያጣመረ ነው። የሕዝቡ እምነት ባህል ልማድስርዓት ወግ ታሪክ ኣንድነት እና እንዲሁም የተወለደበት ያደገበት የተጫወተበት ያንተ ምድር ተብሎ በወላጆቹ የተነገረው ልክ ኤርትራ የእኛ የኢትጱያን ስለነበረች ስትለየን አንደከፋን እንደዛ መሬትም ህዝብ ነው፡ መሬት ያለ ህዘብህ ብቻው ኣገር ኣይንም ህዝቡም ያለ ታሪኩና ባህሉ ያለስርዓቱና ባህሉና ቋንቋው ሀገር ኣይሆንም ያለ ምድር ደግሞ ያው ህዝብ ብቻ ሀገር ኣይሆንም ህዝብ+ ህዝቡ ከቅድሞ ኣያቶቹ ጀምሮ የነረበት ያደገበትም ምድር+ ፖለተካዊ ባህላዊ ስርዓታዊ ማነንቱ የሚገልጥበት የተከለለ ምድር/ደንበር/ ያለበት ሌላ ሰው እንዳያገፋው የተከለለ+ ሰንደቅ ዓላማ/መለያ/+ ባህሉ ስርዓቱ ወዘተ ......................... ብቻ ዳኒ እግዚኣብሔር ይባርክህ... ኣንዳንዶች ሐገር ማለት ሰው ነው ሲሉ ለሀገሬ ምን ሰራሁ ስንል ለህዝብ ምን ኣገዝኩ ከችግር ከድህነት እንዲወጣ እንዲመገብ እንዲኮራ ምን ኣደረግኩ የሚለውን ከመግለፅ ከሆነ ምናልባት ሀገር ግን ኣንተ ያልከው ሁሉ ልዩ መስህብ ያለው ማነነትህን ህዘብህን ምድርህን ሃይማኖትህን ወዘተ ነው ሀገር!

  ReplyDelete
 27. egziabher edme ena tena yestk dn dni

  ReplyDelete
 28. እኛ ሀገር አንዱ የተናገረውን እንደ ገደል ማሚቶ ከማስተጋባት በስተቀር ምን፣ ለምን፣ እንዴት ወዘተ ብሎ ማመዛዘን ከጠፋ እኮ ብዙ ዓመታት አለፉ፡፡ አንተ ከሚገርሙኝ ዘፈኖች አልክ፣ እኔ ደግሞ ኢቲቪን ከሚያዘጉኝ ነገሮች ዋናው ይሄ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ለፖለቲካ ትርፍ እነ --- ለማስደሰት ተባለ በቃ አሁንም እነርሱ እንዲደሰቱ መደስኮር ነው፡፡ የኪነጥበብ ሰው የት አለ? በደመሰፍስ እንጂ በማስተዋል የሚከይን እንደጠፋ ከዚህ የበለጠ ማሳያ እኮ የለም፡፡ ዲ/ን ዳኒኤል አንጀት በሚያርሰው ብእርህ አንጀቴን አራስከው፡፡ አምላከ ቅዱሳን እድሜና ጤና ይስጥህ፡፡

  ReplyDelete
 29. ሀገር በአርምሞ እንጂ በንግግር፣ በተግባር እንጂ በዝርዝር ሊናገሩለት የማይቻል ነገር ነው፡፡

  ReplyDelete
 30. ሀገር ማለት ብር ነዉ ፤ ዋናዉ ይዞ መገኘት ነዉ ፤ ካለህ ማንኛዉም ቦታ ሀገርህ ይሆናል የሚሉ በበዙበት :: በምንም ያተረጓጎም ሁኔታ ዉስጥ ተገኝቶ ስለ ሀገር ቢዘፈን ብዙ ዉርጅብኝ የሚያስፈልጋቸዉ አይመስለኝም:: የቆነፀሉትን ሳይሆን ያዛቡትን ያዝልን::

  ReplyDelete
 31. እዮቤል ደጀንApril 8, 2016 at 12:03 PM

  ሀገር ማለት ሰው ነው እያላችሁ በየሚዲያው የምትናገሩ ጋዜጠኞች እባካችሁ ተሳስታችሁ ሰውን አታሳስቱ.ከዚህ ፁሁፍ እንማር ዲ.ን ዳንኤል. እግዚአብሔር እስከ መጨርሻው ይጠብቅህ.

  ReplyDelete
 32. ወያኔዎች ነገረ ስራቸው ሁሉ ደስ የሚል አይደለም፡፡ሲበዛ ተንኮለኞች ሸፍጠኞች በቀለኞች ናቸው፡፡አማራና ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጠላታችን ነው ብለው ከበረሃ ጀምሮ ፖሊሲ መቅረፃቸው ይህንን በግልፅ ያሳያል፡፡አብዛኛውን የትግራይ ህዝብ በዚህ መርዘኛ አስተሳሰባቸው በርዘውታል፡፡ምግባራቸው ሁሉ ክርስቶስን የሰቀሉት አይሁድ ፈሪሳውያን አይነት ነው፡፡በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ የተባለውም ለዚህ አይደል፡፡ዛሬ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እየታመሰች ያለችው በነዚሁ ሰርገው በገቡ የፈሪሳውያን እርሾ የተነሳ ነው፡፡አንዱ ወዳጄ ዮዲት ጉዲት ከ 900 ዓመት በኋላ በመልኳን ቀይራ ተመልሳ መጣች ነበር ያለው፡፡ዮዲት ጉዲት ከዛሬ 900 ዓመት ገደማ የአይሁድ ሃይማኖትን በኢትዮጵያ የበላይ አድርጋ ለማስፋፋት ከሰሜኑ የተነሳች ንግስት ነበረች፡፡ዮዲት ጉዲት ብዙ ቤተ-ክርስቲያኖችን ያቃጠለች ክርስቲያኖችን የፈጀች ነበረች፡፡ከአፄ-ቴዎድሮስ በፊት የነበረውን ዘመነ-መሳፍንት የፈጠሩት እዚያው ትግራይ ክልል ውስጥ የነበሩ ግለሰቦች ነበሩ፡፡ዛሬም ይኸው በኢትዮጵያ ዘመነ-መሳፍንት ተመልሶ መጣ፡፡ወያኔዎችም የነዚሁ አይሁድ ፈሪሳውያን የጋኔን መንፈስ ስላደረባቸው መግደል ማጭበርበር መዝረፍ ሰውን ማፈናቀል ማደህየት ማሰደደድ በሰው ስቃይ መደሰት የተለመደ የቀን ተቀን ምግባራቸው ነው፡፡ፖለቲካቸው ሲበዛ በሸፍጥ የተሞላ የሆነው ለዚህ ነው፡፡ኢትዮጵያውያንን ሀገራቸውን ቀምተው እነሱ ባለገር ሆኑበት፡፡በመላው አለም የተበተኑት ክርስቶስን የሰቀሉት አይሁዶች ባህሪም ተመሳሳይ ነው፡፡አንድ ጊዜ ብቻ በዚያ ሀገር ውስጥ እንደምንም ብለው እግራቸውን ብቻ ይትከሉ፡፡ከዚያ በኋላ ኢኮኖሚውን ፖለቲካውን ባህሉን ሃይማኖቱን በመቀየር ቀስ በቀስ የዚያን ሀገር ህዝብ የራሳቸው ምርኮኛ አድርገው ሀገር አልባ ያደርጉታል፡፡ይህንን አላማቸውን ለማሳካት ደግሞ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አይሉም፡፡ያለበለዚያ ሀገር አልባ መሆናችን አይቀሬ ነው፡፡ኢትዮጵያዊ እንደ ጨው ዘር በመላው አለም እየተበተነ ነው፡፡ክርስቶስን የሰቀሉት አይሁድ ፈሪሳውያን ከተበተኑበት ወደ ሀገራቸው ተመልሰው እንደ ሀገር ሲቋቋሙ የተቀረው አለም ግን በጦርነት በርሃብ በችግር እየተሰቃየ ሀገር አልባ ሆኖ እንደ ጨው ዘር በመላው አለም በስደት እየተበተነ ነው፡፡ይህንን ምስጢር ፖለቲከኞቻችን ወይንም የሃይማኖት አባቶች ከቻሉ ያስረዱን፡፡
  እግዚአብሄር በቸርነቱ ኢትዮጵያውያን በጎችን ከፈሪሳዊ ተኩላዎች ይጠብቀን፡፡


  ReplyDelete
 33. In this case,Col Mingestu was absolutely right when he said he is much interested to the land than the Tigrian or Eritrian people. To me, man without land or land without man does not mean anything.

  ReplyDelete
 34. እጅግ ከባድ ሃሳብ ነው ያነሳኸው፡፡
  እውን ሀገር ማለት ምን ማለት ነው?
  ለእኔ ሀገር ማለት ህዝብ ማለት ነው፡፡
  ለእኔ ሀገር ማለት ወንዝ ተራራ መሬት ማለት አይደለም አለን መለስ ዜናዊ፡፡
  ከዚያም ጉደኛው መለስና ወያኔ ኢትዮጵያውያንን ሀገር አልባ አድርገው መሬቱን የባህር በሩን ታሪኩን ባህሉን ወዘተ ለባእድ ቸበቸቡት፡፡ምን ይህ ብቻ መለስ ከኢሳያስ ጋር ተመሳጥረው ለባድሜ መሬት ሲሉ ሊበቀሉት የፈለጉትን አማራ ከፊት አሰልፈው ከ70 ሺህ በላይ አስጨረሱት፡፡መለስና ወያኔ በሰው ፍቅር እንጂ በመሬት ፍቅር መቼ ይታሙና ነው፡፡አንድ ዌብ-ሳይት ላይ ታላቂቷ ኢትዮጵያ ቀስ በቀስ ወደ ታላቂቷ አዲስ አበባ እየተቀየረች ነው የሚል አነበብኩኝ፡፡እውነት ይመስላል፡፡ከእያንዳንዱ ሀብት ጀርባ ወንጀል አለ የሚባለው ለካ እውነት ነው፡፡ይህ አባባል ከምንጊዜም በላይ በዘመነ ወያኔ ግልፅ የሆነ አባባል ነው፡፡ዛሬ ግን ከእያንዳንዱ ወንጅል ጀርባም ሀብት አለ ለማለት ያስደፍራል፡፡ወያኔ በ17 ዓመት የነፃ-አውጪ ጦርነት ዘመኑ የሰው ህይወት ቸበቸበ ኤርትራን ቸበቸበ የባህር በራችንን ቸበቸበ መሬታችንን ቸበቸበ ታሪካችንን ቸበቸበ ቅርሳችንን ቸበቸበ ሃይማኖታችንን ቸበቸበ ኢትዮጵያውያን ሴቶቻችንን ለዘመናዊ ባርነት(ግርድና) አረብ ሀገር ቸበቸበ በጉዲፈቻ ሽፋን ህፃናትን ለውጪ ሀገራት ካኒባሊስቶችና ለፔዶፊሊያ ሳታኒስቶች ቸበቸበ በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያንን ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን እንደ ጉድ ቸበቸበ፡፡በዘመነ ወያኔ ምን ያልተቸበቸበ ነገር አለ፡፡ከዚያም ኢትዮጵያዊ ሀገር አልባ እንዲሆን ተደርጎ በስደት በድህነት በርሃብ በበሽታ በድንቁርና በአደንዛዥ-ዕፅ በጫት በግብረሰዶም በዝሙትና በአጠቃላይ በሞራል ውድቀት ትውልዱ ተኮላሽቶ ተስፋ ቢስ ሆኖ እንዲሰቃይ ተደረገ፡፡ሀገር የውክልና ቅኝ ግዛት ውስጥ ወደቀች፡፡ከዚያም የሀገርና የህዝብ ችብቸባው የውጪ እርዳታና ብድር ተጨምሮበት አዲስ አበባ ላይ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ መቀሌ ውስጥ ደግሞ ፎቅና ፋብሪካ ተገነባ፡፡ወያኔም ታላቂቷን ኢትዮጵያን በዘር ክልል ከፋፍሎና እርስ በርስ አናክሶ ሲያበቃና ወደ ታላቂቷ አዲስ አበባ ቀይሮ እንካችሁ አዲስቷን ኢትዮጵያን እዩልኝ አለን፡፡ገበያ ሲደራ የሚባለው ለካ እንደዚህ ነው፡፡ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ የቃብድ ብር እየተቀበሉ የሚጠፉ ነጋዴዎች በርክተዋል አሉ፡፡ወያኔም ኢትዮጵያን ቃብድ ተቀብሎባት ሸጧት እንዳይሄድ ቦሌ ላይ ጥበቃው ቢጠናከር ጥሩ ነው፡፡እንግዲህ የ11 በመቶው የኢኮኖሚ እድገት ውጤት ይህ ነው፡፡ከ20 ሚሊዬን ህዝብ በላይ በርሃብ እየተሰቃየ እንደ ቅጠል የሚረግፍባት የጉድ ሀገር፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም አዲስ አበባ ውስጥ ቤትና ቦታ ከመግዛት ይልቅ ገነት ወይንም መንግስተ-ሰማያት ውስጥ ቦታ መግዛት ይቀላል ነው የሚባለው፡፡ሀገርና ሰው እረከሰ መሬት ተወደደ፡፡ለካ ሀገር ሲረክስ ሰውም ይረክሳል ማለት ነው፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ አያት ቅድማያቶቹ መስዋእትነት የከፈሉበትን መሬትና ሀገር ተቀምቷል፡፡እድሜ ለወያኔዎች ሀገር የሚባለውን ትልቅ ፅንሰ-ሃሳብ አጥፍተውታል፡፡ዛሬ ሀገር ማለት መንገድ ፎቅ ባቡር መኪና ሸቀጣ-ሸቀጥ አርሰናል ማንቸስተር ወዘተ ሻል ካለ ደግሞ ሀገር ማለት ብሄር-ብሄረሰብ ወይንም ዲሞክራሲ ማለት ነው፡፡በዘመነ ወያኔ ለብዙሃኑ ሀገር ማለት ትርጉሙና ፋይዳው ከዚህ የዘለለ አይደለም፡፡ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን የሀገርንና የነፃነትን ትርጉምና ፋይዳ ላለፉት 25 ዓመታት ያክል ብዙም አያውቁትም ነበር፡፡ብኩርናውን ለምስር ወጥ እንደሸጠው ኤሳው እኛ ኢትዮጵያውያን ሀገርንና ነፃነትን ለሸቀጥና ለሌላም ሌላም የማይረባ ነገር ለውጠነዋል፡፡የሀገርና የነፃነት ትርጉምና ፋይዳው የሚገባን ስናጣው ብቻ ነው፡፡ምክንያቱም ጦርነትን ያላየ የሰላምን ዋጋ አያውቃትምና፡፡ስለዚህም ሀገራችንን እና ነፃነታችንን መልሰን ለማግኘት ውድ ዋጋ መክፈል አለብን፡፡በቀላሉ ሊገኝ አይችልም፡፡አያት ቅድመ-አያቶቻችን ለሀገርና ለነፃነት ሲሉ የከፈሉትን ውድ የህይወትና ሌላም መስዋእትነት ዋጋ አቃለነዋል፡፡ዛሬ ለእኛ ሀገር ማለት ከምንዝናናበት ሆቴልና ካፍቴርያ ወይንም ከምንነዳው አውቶሞቢል የተለየ ነገር አይደለም፡፡አሳፋሪ ዘመን ነው፡፡
  ይህ ትውልድ ሀገርና ነፃነት አይገባውም፡፡ደግሞም ሀገርና ነፃነትን ይገባኛል ካለ በውድ ዋጋ ይግዛት፡፡ዝም ብሎ በነፃ የሚሰጥ ነገር የለም፡፡ከውጪ የፈረንጅ እርዳታ ማግኘት እንደ መብት የሚቆጠርበት ዘመን፡፡ለምንድን ነው ከውጪ እርዳታ ማግኘትን እንደ መብት የቆጠርነው?ፈረንጆቹ የሚረዱንስ እውን ለምንድን ነው? እውን ለእኛ ብለው ነው? ነው ወይንስ የዘመኑ ኢትዮጵያዊ በርካሽና በነፃ የሚሰጥ ነገር ይወዳል ማለት ነው?ወያኔዎች ከውጪ ባገኙት እርዳታና ብድር አዲስ አበባ ላይ ፎቅ ገነቡበት መቀሌ ላይ ፋብሪካ ገነቡበት የቢሊዬን ዶላር ካምፓኒ ኢፈርትን ገነቡበት ሌላም-ሌላም ነገር አደረጉበት የተቀረው ኢትዮጵያዊ ግን ማንነቱን ክብሩን ሀገሩንና ነፃነቱን ተቀማ፡፡በዘመነ ወያኔ ያለው እድገት ከወጪ ቀሪ ሂሳቡ ሲወራረድ ይህንን ይመስላል፡፡ወያኔ የኢትዮጵያን ገበሬ በሴፍቲ ኔት እንደ ራሱ የውጪ እርዳታ ጥገኛና ለማኝ አደረገው፡፡ዛሬ የኢትዮጵያ ገበሬ በርሃብ እንዲያልቅ የተደረገው ሆነኝ ተብሎ ነው፡፡
  የኢትዮጵያ ገበሬ ሀገሩን የሚመግብ የሰብል እህል ሳይሆን ለወያኔዎች በሚመች መንገድ ጫት ቡና ወዘተ ብቻ የንግድ ምርት እንዲያመርት ተደረገ፡፡ግብርናው የተዋቀረው ለወያኔ ዝርፊያና አፈና በሚመች መንገድ ሆነ፡፡በአጠቃላይ ሀገርና ነፃነት የሚባለው ትልቅ ቁም-ነገር ቢዝነስ በሚባል ነገር እየተተካ የመጣ ይመስላል፡፡በእርግጥ ለተራ ቢዝነስ የሸጥነውን ሀገርና ነፃነት ምን ያህል ቢዝነስ ሰርተን መልሰን እንደምናገኘው አላውቅም፡፡እውን ሀገር ማለት ሰው ነው?ብሄር በሄረሰብ ማለት ነው? ዲሞክራሲ ማለት ነው?የፖለቲካ ፓርቲ ማለት ነው? ሃይማኖት ታሪክና ባህል ነው?እቁብ እድር ሰርግ ማህበር ሰንበቴ ተዝካር ለቅሶ?እናት አባት እህት ወንድም ባል ሚስት ልጅ ነው?አርሰናል ማንቸስተር ጊዮርጊስ ቡና ማለት ነው ?ወይንስ ግኡዝ የሆነ መሬት ወንዝ ተራራ ሸለቆ ፎቅ መንገድ መኪና ባቡር? ነው ወይንስ ነፍስ ወይንም መንፈስ ያለው ነገር ነው?በእውነት ሀገር ማለት ምን ማለት ነው?ምናልባት ሀገር የሚባለው ትርጉሙ በደንብ የሚገባን ስናጣው ይመስለኛል፡፡ስለዚህም ትርጉሙ እንዲገባን ከእጃችን ወጥቶ እንጣውና ትርጉሙ ሲገባን መልሰን ውድ ዋጋ ከፍለን እናግኘው፡፡ጨረስኩ፡፡

  ReplyDelete
 35. ሀገር
  በአርምሞ
  እንጂ
  በንግግር፣
  በተግባር
  እንጂ
  በዝርዝር
  ሊናገሩለት
  የማይቻል
  ነገር
  ነው፡፡
  ውጥንቅጥ
  ሰበዞች
  የሰፉት
  ሞሰብ፣
  ዓይነተ
  ብዙ
  ድርና
  ማጎች
  የሸመኑት
  ጋቢ፣
  ልዩ
  ልዩ
  ቅመሞች
  የሠሩት
  ወጥ፣
  ብዙ
  ገባሮች
  የፈጠሩት
  ዓባይ፣
  ብዙ
  ትውልዶች
  የከመሩ

  ተራራ፣
  ከአራቱ
  አቅጣጫ
  ተሰብስቦ
  በአንድ
  ወፍጮ
  የተፈጨ
  እህል፣
  ከየአበባው
  ተቀስሞ
  በአ
  ንድ
  ቀፎ
  የተሠራ
  ማር፣
  ከየእህሉ
  ወጥቶ
  በአንድ
  ማድጋ
  የተጠመቀ
  ጠላ፣
  ከየ
  እንጨቱ
  ተለቅሞ
  በአንድ
  ጽንሐ
  የታጠነ
  ዕጣን
  ነው
  ሀገር፡፡

  ReplyDelete
 36. መገለጫው ቅርስ፣ መዋሐጃው ባህል፣ መታያው ልብስና መዋቢያው ጌጣጌጥ፣ መገናኛው ቋንቋ፣ መዝናኛው ጭፈራ፤ ማስተማሪያው ተረት፣ መክበሪያው ዓመት ባል፣ መጠበቢያው ምግብ፣ መቆዘሚያው እንጉርጉሮ፣ መተከዣው ልቅሶ፣ መተኪያው ልደት፣ ማሳረጊያው ቀብር፤ መገምገሚያው ምግባር፣ ማነወሪያው ነውር፤ መኩሪያ ጀግንነቱ፣ ማፈሪያ ገመናው፤ መደበቂያ ቤቱ፣ መመረሪያ ጫካው፤ ይሄ "ሁሉ ነው ሀገር፡፡ ታሽቶ ተገርኝቶ ያመጣው አንድነት፣ ተጣልቶ ተባልቶ ያመጣው ልዩነት፣ እንደ ዘሐ ዘጊ የተጠላለፈው፣ እንደ እግር ሠንሠለት የተቆላለፈው፣ ሲፈተል፣ ሲገመድ፤ ሲባዘት፣ ሲዳውር፤ ሲከካ፣ ሲሰለቅ፤ ሲጣላ፣ ሲታረቅ፤ ሲያውቅና ሲማይም፤ ሲሠለጥንና ሲደኸይ፤ ሲሰፋና ሲጠብ፤ የኖረውና የኖረበት፣ የኖረለትም ነው ሀገር፡፡" እዉነት ብለሃል ዲ/ን

  ReplyDelete
 37. ዳንኤል ታሰረ ስትባል ነበር እውነት ነው ?

  ReplyDelete
 38. እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቅህ።

  ReplyDelete
 39. Thanks Dn Daniel K. stay blessed!!

  ReplyDelete
 40. It is only a saying to reinforce the need to respect human rights. It is not a denial on the need for a physically,Socially, Culturally ,historically and politically bounded entity ,a country.It is only a motto to remind dictators who kill their citizens and you are not being fair ridiculing those who struggle for democracy and respect for human right.Come on baby, show us where you really stand on these major issues of our time.Writing 100 books is disastrous,if it ignores more than half of our reality. People will judge your work,it is only a matter of time.No more hide and seek games!

  Also Ethiopians in America do not believe they know everything,remember your Sheger radio interview? Ethiopians in America have freedom to speak or right what they think.Got it?

  ReplyDelete
 41. Amesegenalew arif eyta new betam...!!!

  ReplyDelete
 42. ማለፊያ ነው በረታ

  ReplyDelete
 43. Ewenat dani betam enamesegenale betam egzhabeher yyesetelen kale heyeweten yasemalen

  ReplyDelete
 44. thank you many!!! it is very good view.

  ReplyDelete