Thursday, March 17, 2016

በዓሉ ግርማ- ሕይወቱና ሥራዎቹበእንዳለ ጌታ ከበደ
የካቲት 2008 ዓም
ዋጋ፡- 120 ብር
 
እንዳለ ጌታ ከበደ በዓሉ ግርማን እንደ ጌታ ነፍስ ዘርቶ እንደደአልዓዛር ከሞት አስነሥቶታል፡፡ ከትውልድ ቀየው ጀምሮ ‹እስከ መቃብሩ› ደረስ እየተከተለ፡፡ መዛግብቱን ያገላብጣል፣ እናውቃለን የሚሉትን ይጠይቃል፣ ያውቃሉ ብሎ የገመታቸውን ያናግራል፤ ሄዶበታል፣ ውሎበታል፣ ገብቶበታል፣ ወጥቶበታል የተባለው ቦታ ድረስ እየገባ ‹ማጀት በጎረሰው፣ ደጃፍ በመለሰው› ያገኘውን ያህል ይነግረናል፡፡
ሰው የሚያውቀውን ሲጽፍ፣ የሚጽፈውንም ሲያውቅ እንዴት የሚያጠግብ እንጀራ እንደሚጋግር በእንዳለ ጌታ መጽሐፍ ልኬቱን እናገኘዋለን፡፡ ከሱጴ እስከ ደርግ እሥር ቤት፣ ከአዲስ አበባ እስከ አሜሪካ፣ ከአሠሪ እስከ አሣሪ፣ ከወዳጅ እስከ አሳዳጅ ድረስ መረጃ ፍለጋ የኳተነው ‹ለሞተው› በዓሉ ነፍስ ሊዘራ እንጂ ለሌላ ነገር ነው ብሎ ለማመን እጅግ ጅል መሆንን ይጠይቃል፡፡ 

መጽሐፉ በቀብር ላይ እንደሚነበብ የሕይወት ታሪክ ሙቀት አልባ አይደለም፡፡ ድርቀት የተለየው፣ወዝ የተዋሐደው እንጂ፡፡ እንደ አንድ የሀገራችን ታሪክ ጠገብ ሽማግሌ ሆኖ ያወጋናል፡፡ ቃለ መጠይቅ ያደረገላቸውን ሰዎች እንደ አጃቢ ገጸ ባሕርይ ያስመስላቸዋል፡፡ በዓሉን ደግሞ እንደ ዋናው ገጸ ባሕርይ፡፡ ‹ተናደደ፣ ጠረጲዛ መታ፣ ፊቱን ጥቁር አደረገ፣ ሳቀ፣ ፈገግ አለ፣ ሮጠ፣ ተሹሎከሎከ› እያለ አብሮ የነበረ ያህል ነው የሚነግረን፡፡
በዓሉ በድርሰት ሥራዎቹ ሰዎችን ሲስል ፍጹማን አያደርጋቸውም፡፡  እንደ ሁላችንም እንከን ያላቸው፤ የበዓሉ ሰዎች አንድም እንከናቸውን አሸንፈው፣ አንድም እንከናቸውን ይዘው ኑሮን ድል ለማድረግና ታሪክ ለመሥራት የሚተጉ ናቸው፡፡ የበዓሉ ሰዎች የሠፈራችን ሰዎች የሚመስሉን ለዚህ ነው፡፡ የበዓሉ ሰዎች ጀንበርና ጥላ ያላቸው ናቸው፡፡
እንዳለ በዓሉን ሲጽፈው እርሱ ስለ ራሱ ቢጽፍ ኖሮ በሚጽፍበት መንገድ ነው፡፡ ጀንበርና ጥላ አድርጎ፡፡ በዓሉ ጎበዝ ደራሲ፣ ትኁት፣ ትጉ ሠራተኛ፣ ከሰው ጋር ተግባቢ፣ ዐዋቂ፣ ቆራጥና ጀግና ነው፡፡ ነገር ግን ደግሞ ሰው ነው፡፡ ጥላ ነበረው፡፡ እንከን ነበረው፡፡ ድካም ነበረው፡፡ ስሕተት ነበረው፡፡ ውሱንነት ነበረው፡፡ ከሻማው ሥር እንዳለው ጨለማ ያለ ነበረው፡፡ እንዳለ ይህንንም እንድናይ ያደርገናል፡፡
በቀብር ላይ እንደምናነበው ታሪክ ‹ትጉ፣ቅን፣ሰው ወዳጅ፣ ታታሪ፣ ታማኝ፣ እግዜርን የሚፈሩ ነበሩ› ብeሎ አይደመድምም፡፡ በዓሉ ሰው ነበረ፡፡ ሰው ሆኖ ሠርቶ ሰው ሆኖ ነው የሞተው ይለናል፡፡ እንድናደንቀው ብቻ ሳይሆን እንድንበሳጭበት፣ እንድንወደው ብቻ ሳይሆን ‹ለምን ይህን ያደርጋል› እንድንለው፣ እንድናከብረው ብቻ ሳይሆን እንድንተቸው፣ ‹እንኳን አደረገ› እንድንል ብቻ ሳይሆን ‹ምን ነካው› እንድንል አድርጎ ነው የሳለው፡፡
በዓሉና እንዳለ ልብ ለልብ ተናበዋል፡፡ ይል ነበር በሚባለው የጎጃም ልቅሶ ላይ  ስለ ወዳጃቸው አሣምረው እየገጠሙ የዋሉ አንድ ሰው ነበሩ አሉ፡፡ በዚህ በጎንጅ ጽላሎ፡፡ ሁኔታውን የታዘበች አልቃሽ
እርሳቸው እርሳቸው እርስዎም እርስዎ
እንዴው የወዳጅ ልብ ምን አሰረቀዎ
ብላቸዋለች አሉ፡፡ የወዳጅዎን ልብ ሰርቀው ቢወስዱት እንጂ እንዲህ አድርገው የልቡን እንዴት ዐወቁት ማለቷ ነው፡፡ የቅጅ መብትን ባልፈራ ለእንዳለ እለው ነበር፡፡
በዓሉን የሚወድ፣ የሚያደንቅና ስለ በዓሉ ማወቅ የሚፈልግ ሰው አሁን የእንዳለን መጽሐፍ ከማንበብ የተሻለ አማራጭ የለውም፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ በዓሉ ብቻ ሳይሆን እንዳለም ተጽፏል፡፡ ሲወጣና ሲወርድ፣ ተሥፋ ሲያደርግና ሲቆርጥ፣ ሲያገኝና ሲያጣ፣ ሲያዝንና ሲደሰት፣ እናየዋለን፡፡
ተራራ ቁልቁለት ወጥቼ ወርጄ
ስሙ የማይታወቅ ሩቅ ሀገር ሄጄ
እንዳለቺው የከበደ ሚካኤል የአይጥ ግልገል የተደበቀውን ለመግለጥ ‹ስሙ የማይታወቅ ሩቅ ሀገር› ድረስ ሲተጋ እናየዋለን፡፡ እኛም አብረነው እየተጓዝን ‹እንዘ ሥውር እምኔነ፣ ይእዜሰ ክሡተ ኮነ› እንላለን፡፡
የእንዳለ አጻጻፍ የታላላቆቻችን ታሪኮች እንዲህ በፍቅርና በትጋት ተሠርተው፣ ሰው ሰው ሸተው፣ በደረቅ እንጀራ ሳይሆን በአዋዜ ቢቀርቡ እንደ ወግ ተደምጠው፣ እንደ ፊልምም እንደሚታዩ ማንጸሪያ ነው፡፡ የእንዳለ መጽሐፍ በዓሉን አግኝቶ ከማነጋገር ቀጥሎ ስለ በዓሉ ሊነግረን የሚችል ሁለተኛው መዝገብ ይመስለኛል፡፡ ምናልባትም ደግሞ ከራሱም ከበዓሉም በላይ፡፡
እናም
በድግሱ የተደሰተ የቆሎ ተማሪ የወረበውን ማኅሌተ ገንቦ እንወርብለታለን፡፡
ዝ ጠላ ከመ ወይን ጣዕሙ
እስኩ ድግሙ ድግሙ፣ እስኩ ድግሙ፤

18 comments:

 1. በቀብር ላይ እንደምናነበው ታሪክ ‹ትጉ፣ቅን፣ሰው ወዳጅ፣ ታታሪ፣ ታማኝ፣ እግዜርን የሚፈሩ ነበሩ› ብeሎ አይደመድምም፡፡ በዓሉ ሰው ነበረ፡፡ ሰው ሆኖ ሠርቶ ሰው ሆኖ ነው የሞተው ይለናል፡፡ እንድናደንቀው ብቻ ሳይሆን እንድንበሳጭበት፣ እንድንወደው ብቻ ሳይሆን ‹ለምን ይህን ያደርጋል› እንድንለው፣ እንድናከብረው ብቻ ሳይሆን እንድንተቸው፣ ‹እንኳን አደረገ› እንድንል ብቻ ሳይሆን ‹ምን ነካው› እንድንል አድርጎ ነው የሳለው፡፡

  ReplyDelete
 2. ምነው እንደዛ አሞካሽተህ ስታበቃ
  በአይጥ ግልገል መመሰልህ በመጨረሻዋ ደቂቃ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ye ayit gilgel yalew esun sayihon, kebede Michael gitim wust yalechiw ye'ayit gilgel new yalew

   Delete
 3. Derasiyan hizbn ke meriwoch yemiyagenagnu dildiy nachew sintoch bier chebtew taglew alfewal

  ReplyDelete
 4. ወንድሜ በቅንነት ካላየኽዉ የተኛዉንም እንሰሳ ቢጠቀም ስድብ መሆኑ አይቀርም:: አህያም ቢል ስድብ ነዉ ፤ ፈረስ ስድብ ነዉ ፤ ሽኮኮ ስድብ ነዉ፤ ግመል ስድብ ነዉ ፤ በግ ስድብ ነዉ ፤ ተኩላም ስድብ ነዉ፤ ዝንጀሮ ስድብ ነዉ ፤ ጦጣም ስድብ ነዉ፤ ጅብ ስድብ ነዉ:: አይጥ ስድብ ነዉ :: አካሏን ከፍ አድርጎ ዉሻ ቢላትም ከስድብነት አያመልጥም:: ለኔ የታየኝ ጥረቱ እንጂ ስድቡ አይደለም:: ዉብ የሆነዉን ተፈጥሮ ለስድብ የሚጠቀመዉን ባህል መዋጋት እንጂ እንሰሳቱ ስድብ ናቸዉ ብሎ መዉሰድ አላዋቂነት ይመስለኛል:: ዳኒ ግን የንባብ አፒታይቴን ስለከፈትክልኝ አመሰግናለሁ::

  ReplyDelete
 5. የእንዳለ መጽሐፍ በዓሉን አግኝቶ ከማነጋገር ቀጥሎ ስለ በዓሉ ሊነግረን የሚችል ሁለተኛው መዝገብ ይመስለኛል፡፡

  የእንዳለ ጌታ ከበደ መጽሐፍ በዓሉን አግኝቶ ከማነጋገር ቀጥሎ ሊነግረን የሚችል ነው ብለህናል እንግዲህ አንብበን እናየዋለን፡

  ReplyDelete
 6. ግንኮ የመፀሀፉን ርዕስ አልጠቆምከንም ሙሐዘ ጥበባት? በነካ እጅህ " ያንን! እንዳለጌታ ስለ በዓሉ የፃፈውን መፀሀፍ ፈልጉና ላኩልኝ!" ከማለት አውጣንማ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. የመጽሐፉን ፎቶ አታየውምን? ‹በዓሉ ግርማ፣ ሕይወቱና ሥራዎቹ› ይላልኮ

   Delete
 7. My bad! Please don't publish my question. Found out the title of the book on your post title :(

  ReplyDelete
 8. እንዳለ ጌታ ከበደ በዓሉ ግርማን እንደ ጌታ ነፍስ ዘርቶ እንደደአልዓዛር ከሞት አስነሥቶታል
  Better if the above statement was articulated by "Nigist Elleneye and the true cross".

  ReplyDelete
 9. I knew some about the prominent author and legend Balu Girma by our usual behavior from hear says and also reading his well known book "Oromayee". I will try to get the present published book to know more about him and share the facts to my and next generation how much he and other legends have contributed to our country as much as I can as a story teller of the present epoch .

  ReplyDelete
 10. ዳኒ አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Metshaf Megzat Alwedm Manbebe Gen Ewdalhu Metshafun Ymanebebet ken Enafekalehu!!!!

   Delete