Monday, March 14, 2016

ጆሮና ቀንድአንድ ጥጃ የሚያሳድግ ሰው ነበር፡፡ ጥጃውን ሲፈልግ ጆሮውን ይጎትተዋል፣ ሲፈልግ በዱላ ይዠልጠዋል፣ ሲፈልግ ጨው እያላሰ ይስበዋል፣ ሲፈልግ ደግሞ በገመድ አሥሮ ያስከትለዋል፡፡ በዚህ መንገድ ሄዶ ጥጃው አደገና  ወይፈን ሆኖ ቀንድ አበቀለ፡፡ የጥጃውም ባለቤት እንደለመደው በዱላ ሊመታው፣ ጆሮውን ሊጎትተው፣ በዱላም ሊዠልጠው ተነሣ፡፡ ያን ጊዜ ጥጃው አፍንጫውን ወደ መሬት አስነክቶ አኩረፈረፈና እንደ ስፔን በሬ ተወርውሮ በቀንዱ ወጋው፡፡ ሰውየውም ወገቡን ይዞ እየተጎተተ ቤቱ ደረሰ፡፡

ታሞ ሊጠይቁት የሄዱ ጎረቤቱ የሆነው ነገር ሰሙናወዳጄ የጆሮና የቀንድን ዘመን እንዴት መለየት አቃተህ?አሉት፡፡የጆሮና የቀንድ ዘመን ምንድን ነው?አላቸው ወገቡን አሥሮ እየተገላበጠ፡፡ በመጀመሪያ የበቀለን ጆሮ በኋላ የመጣ ቀንድ በለጠውሲባል አልሰማህም፡፡ ጥጃው መጀመሪያ ጆሮ ብቻ ስለነበረው ያልከውን ሁሉ ይሰማህ፣ ይታዘዝህ ነበር፤ ብትመታው ይችላል፣ ብትጎትተው ይከተላል፣ ብታሥረው ይታሠራል፡፡ ጆሮ ብቻ ስለነበረው መስማት ብቻ ነበር የሚችለው፡፡ በኋላ ግን ቀንድ አበቀለ፡፡ ቀንድ ካበቀለ በኋላ እንደ ድሮው እጎትተዋለሁ ብትል አይሆንም፡፡ አሁን ከተስማማው ይቀበልሃል፤ ካልተስማማው ግን መዋጋት ይጀምራል፡፡ አሁን አንተ ያደረግከውን ማድረግ የሚቻለው በጆሮ ዘመን ነው፡፡ በቀንድ ዘመን እንደዚህ ማድረግ ሞኝነት ነው፡፡


 

ሁሉም ነገር የጆሮና የቀንድ ዘመን አለው፡፡ በሀገራችን አንድ መንግሥት ሲተከል ሕዝቡ የጆሮ ዘመን ይሰጠዋል፡፡ ዝም ይላል፣ ይሰማል፣ ይቀበላል፤ አልጋው እንዲረጋ፣ ዙፋኑ እንደዲጸና ይተጋል፤ ከትናንት ዛሬ፣ ከዛሬም ነገ ይሻላል ብሎ በተስፋ ይጠብቃል፡፡ ባያምንም ይቀበላል፤ ባይስማማም ይተባበራል፤ ባይግባባም አብሮ ይሠራል፡፡ ይሄ የጆሮ ዘመን ነው፡፡ ብልህ መሪ ከጆሮ ዘመን በኋላ የቀንድ ዘመን እንደሚመጣ ያውቃል፡፡ ስለዚህም ሥርዓት ሠርቶ፣ ሕግ አጽንቶ፣ አገር አልምቶ፣ ሕዝብን አስማምቶ ይጠብቃል፡፡ በጆሮመን ያልሠራውን ሥራ በቀንድ ዘመን እሠራለሁ ቢል የሚያምነው የለም፡፡ እንደ ቀድሞው ዝም ብሎ የሚሰማ፣ አሜን ብሎ የሚቀበል፣ እሺ ብሎ የሚከተል፣ ጎንበስ ብሎ የሚጎተት አይገኝም፡፡ ለተስማማው ጆሮውን ላልተስማማው ቀንዱን ያቀርባል፡፡ ሥራውን በግድ ብተትሠራ እንኳን ትግሉ ብዙ ነው፡፡ ሕዝብ ቀንድ ከማብቀሉ በፊት እንደ ቀንዱ ዘመን ማድረግ እንደማይቻለው ሁሉ፣ ቀንድ ካበቀለ በኋላም እንደ ጆሮው ዘመን ማድረግ አይቻልም፡፡ ራሱ ቀንድ አብቃዩም እንደ ድሮው ልሁን ቢል እሺ አይለውም፡፡ ያላወቁትን እንዳላወቁ፤ ያልሰሙትን እንዳልሰሙ፣ ያላዩትን እንዳላ፣ ያልደረሱበትን እንዳልደረሱ መሆን አይቻልም፡፡ ለውጥን ፈልገህው ብቻ አታመጣውም የቀንድ ዘመን ሲሆን ሳትፈልግም ትለወጣለህ፡፡  

አገር ብቻ ሳይሆን ድርጅት፣ ማኅበር፣ ፓርቲና ተቋምም ቀንድ ያበቅላሉ፡፡ በጆሮ ዘመን አባሉ ሁሉ ይሰማሃል፤ ትእዛዝ ከበላይ እግር ወደላይ ብሎ ያምናል፡፡ አንድ ቦታ የበሰለውን በልቶ፣ አንድ ቦታ የተጠመቀውን ጠጥቶ፣ የተባለውን ሁሉ ሰምቶ፣ ውደድ የተባለውን ወድዶ ጥላ የተባለውን ጠልቶ ይኖራል፡፡ በአንድ ዓላማ የተመመ፤ በአንድ አቋም የቆመ፤ አንድ ግብ የጨበጠ፤ በአንድ መመሥመር የሠለጠ የሚመስልበት የጆሮ ዘመን አለው፡፡ እንደ አህያ ጆሮ እንደ ጦር ጉሮሮ አንድ ሆኖ ተካክሎ የሚታይበት፡፡ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ የሚመስልበት ዘመን አለ፤ያኔ አባሉና አካሉ የተግባባና የተስማማ የመሰለው ተግባብቶና ተስማምቶ ብቻ አይደለም፡፡ ጊዜው የጆሮ ጊዜ ስለሆነ ነው እንጂ፡፡

የቀንዱ ዘመን ሲመጣ ጠያቂ፣ መርማሪ፣ ተከራካሪ፣ ሞጋች ተች፣ ይበዛል፡፡ በፊት የጣመው አሁን ይመረዋል፤ በፊት ያስደሰተው አሁን ያስከፋዋል፤ በፊት ዝም ያለው አሁን ያስጮኸዋል፣ በፊት የታገሠውን አሁን ይሰለቸዋል፡፡ በፊት የፈራውን አሁን ይደፍረዋል፡፡ በፊት የተወውን አሁን ያነሣዋል፡፡ቀኝ ኋላ ዙርስለተባለ ብቻ አይዞርም፡፡፡ አባል ስለሆነ ብቻ የድርጅቱን ነገር ሁሉ አይቀበልም፡፡ መለኮታውያን ናቸው ያላቸውን መሪዎቹን ሰው አድርጎ መመልከት ይጀምራል፡፡ ላመነው ነገር እንኳ ቢሆን ተጨማሪ ማስረጃ ይፈልጋል፡፡ የጥንቱን ትርክት ብትተርክ፣ የጥንቱን ዘፈን ብትዘፍን፣ የጥንቱን ፉከራ ብትፎክር እንደ ሞኝ ይቆጥርሃል፡:፡ ያ ሁሉ የጆሮ ዘመን ታሪክ ነውና፡፡ በዚህ ጊዜ ለምን እንደ ጥንቱ ጆሮውን ስንጎትተው አልተጎተልንም፣ ስንመታው ለምን አልሄደም፣ ስንስበው ለምን አልተሳበም፤ ስንቆነጥጠው ለምን አልተቆነጠጠም ብለው የሚያስቡ ዘመንን ማንበብ የማይችሉ ናቸው፡፡ አሁን የቀንድ ዘመን ነው፡፡ የጆሮ ጊዜ አልፏል፤ ማሳመን ማግባባት፣ ማስረዳት፣ ይፈልጋል፡፡ መስማት ብቻ ሳይሆን መሰማትም ይሻል፡፡

እርጅና በየዘመኑ ነው፡፡ ልጅነት በዘመኑ ያረጃል፤  ወጣትነትም በጊዜው ይጠወልጋል፤ ድርጅትና ማኅበር፤ ተቋምና ፓርቲ በዘመናቸው ያረጃሉ፡፡ ብልህ እንደ ንሥር ያድሳቸዋል፡፡ እንደ እባብ ቆዳ ለዘመኑ የሚመጥን ልብስ ያለብሳቸዋል፡፡ በጆሮ ዘመን የሠሩበትን በቀንድ ዘመን እንሠራበት አይሉም፡፡ እባብ ያድግና ቆዳው አላላውስ ሲለው ቆዳውን ገሽልጦ ጥሎ ለዕድገቱ የሚስማማ ቆዳ ይለብሳል፡፡ ድርጅትና ፓርቲም እንዲህ ካልሆኑ እርጅናው ሞትን ያመጣል፡፡ የጆሮ ዘመን ሲያረጅ ለቀንዱ ዘመን ተዘጋጅ፡፡

ቤተ እምነቶች በዘመናችን ያልተረዱት ቁም ነገር ይሄ ነው፡፡ አንተ ምእመን ነህ ዝም ብለህ ገንዘብህን ስጥ፣ የምንልህን ብቻ ተቀበል፣ ለምን? የት? መቼ? እንዴት? ብለህ አትጠይቅ፤ አባቶችህ ከአንተ በላይ ያውቃሉ፤ አገልጋዮቹ ከአንተ ይሻላሉ፤ አትከራከር፣ ቁጣ፣ መቅሰፍት፣ መዓት ይወርድብሃል፣ ስለተባለ ብቻ የሚቀበልበት የጆሮ ዘመን አልፏል፡፡ መስጠት ብቻ ሳይሆን የሰጠው ገንዘብ የት እንደዋለ ማወቅም ይፈልጋል፤ አባቶቹን ማክበር ብቻ ሳይሆን ክብራቸውን ሲጠብቁ ማየትም ይፈልጋል፤ የሚባለውን መስማት ብቻ ሳይሆን ለሚባለው ነገር ማስረጃም ይሻል፤ ይመዝናል፤ ያመዛዝናል፤ የጥንቱን ከዛሬው፣ ድርጊቱን ከሕጉ ያመሳክራል፤ በሕጋዊው ቤት ሕገ ወጥነት፣ በመንፈሳዊው ቤት ዓለማዊነት፣ በእግዚአብሔር ቤት ቄሣር፣ በጽድቁ ቤት ርኩሰት ሲሠለጥን እያየ ዝም የሚልበት የጆሮ ዘመን አልፏል፤ አሁን የቀንድ ጊዜ ነው፡፡

ተገለጠልኝ፣ ታየኝ፣ በራልኝ፣ ወረደልኝ፣ ፈለቀልኝ፣ ሰማይ ደርሼ መጣሁ፤ አሥር ሺ ሰይጣን አወጣሁ ስላልክ ብቻ የሚቀበልበት የጆሮ ዘመን አልፏል፡፡ ይመዝነዋል፣ ይፈትነዋል፤ ያነጥረዋል፣ ያበጥረዋል፡፡ ‹ኩሎ አመክሩ ወዘሠናየ ግበሩ› ነውና የተባለው፡፡ ከቻለ ይሞግትሃል፤ ካልቻለ ትቶህ ይሄዳል፡፡ ዝም ብለህ ተቀበል የሚባልበት የጆሮ ዘመን አሁን የለም፡፡ እንደ ጆሮው ዘመን ወደፈለግከው አዳራሽና ጸሎት ቤት፣ ወደፈለግከው የራእይና የተአምራት ቦታ አትጎትተውም፡፡ አሁን አልሄድም ብሎ ሊወጋህም ይችላል፡፡ በዚህ ዘመን በየቤተ እምነቱ በምእመናኑና በእምነት አለቆች መካከል የምናየው ውጊያ ይሄ ነው፡፡ ወደፈለግነው አቅጣጫ እንጎትታለን በሚሉ የጆሮ ዘመን አለቆችና ‹ቀንዴ ከፍ ከፍ አለ› በሚሉ ቀንድ ባበቀሉ ምእመናን መካከል፡፡

ድርጅትህን ስትመሠርተው ልጅ ስለነበር እንደፈለግክ ታደርገው ይሆናል፡፡ እየሰፋ፣ እያደገ፣ እየተለጠጠ፣ እየታወቀና እየሠለጠነ ሲሄድ ግን ከጆሮው ዘመን አልፎ የቀንዱ ዘመን ላይ ይደርሳል፡፡አንተ ድርጅቱን መምራት ብቻ ሳይሆን ድርጅቱም አንተን ሊወጋህም ይችላል፡፡ ብዙዎች በገዛ ድርጅታቸው ቀንድ ተወግተው ታሥረዋል፣ ከሥረዋል፣ ጠፍተዋል፣ በሽተኞች ሆነዋል፡፡ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል፤ ሙስና ውስጥ ተዘፍቀዋል፡፡ ብልህ ነጋዴ በጆሮው ዘመን ቀድሞ ያስባል፡፡ እንደ ጥንቱ እመራዋለሁ፣ አስተዳድረዋለሁ፣ እኔ እበቃዋለሁ፣ ለዚህ ደግሞ መቼ አንሳለሁ አይልም፡፡ የልጅነቱን ልብስ አሁን ልልበስ እንደማይለው ሁሉ የጥንቱን አሠራር አሁን ልከተል አይልም፡፡ ለቀንዱ ዘመን የሚመጥን አሠራር፣ ሥርዓት፣ አስተዳደር፣ ባለሞያ፣ ሕግ፣ አደረጃጀት፣ የደረጃ ምጣኔና አስተሳሰብን ይገነባል እንጂ፡፡

በሀገራችን ዘመን ተሻግሮ ከልጅ ልጅ የሚተርፍ ድርጅት ያጣነው፣ ባለቤቶቹ ድርጅቱን በጆሮው ዘመን አስተሳሰብ በቀንዱ ዘመን እንምራው ስለሚሉ ነው፡፡፡ ድርጅቱ አድጎ አድጎ ከዐቅማቸው በበላይ ይሆንና ያሳደገው አውሬ እንደሚበላው አዳኝ ያሳደጉት ድርጅት እነርሱንም ይበላቸዋል፡፡ ስንት ዘመን መርቼው፣ ድንጋይ ጥዬ መሥርቼው፣ ላቤን ጠብ አድርጌ እዚህ አድርሼው ማለቱ አይጠቅምም፡፡ ያ የጆሮ ዘመን ነውና፡፡


47 comments:

 1. Anjet Aris eko neh Dani!

  ReplyDelete
 2. Good word expression of all authority leaders!!!

  ReplyDelete
 3. be zemenachin ye astesaseb lewt yasfelgal yin yanebebe hulu rasun yetuga endale yimeremr betam astemari Tsuf new thanks Dani\\\\

  ReplyDelete
 4. የቀንዱ ዘመን ሲመጣ ጠያቂ፣ መርማሪ፣ ተከራካሪ፣ ሞጋች ተች፣ ይበዛል፡፡ በፊት የጣመው አሁን ይመረዋል፤ በፊት ያስደሰተው አሁን ያስከፋዋል፤ በፊት ዝም ያለው አሁን ያስጮኸዋል፣ በፊት የታገሠውን አሁን ይሰለቸዋል፡፡ በፊት የፈራውን አሁን ይደፍረዋል፡፡ በፊት የተወውን አሁን ያነሣዋል፡፡ ‹ቀኝ ኋላ ዙር› ስለተባለ ብቻ አይዞርም፡፡፡ አባል ስለሆነ ብቻ የድርጅቱን ነገር ሁሉ አይቀበልም፡፡ መለኮታውያን ናቸው ያላቸውን መሪዎቹን ሰው አድርጎ መመልከት ይጀምራል፡፡

  ReplyDelete
 5. To the point and spectacular, thanks Dn.Daniel.
  The following is not to inflate,to speak the fact,instead. I feel as you are prophet for this needy country, whose speech, should be given due consideration and contemplated by any one, any organization within the country.

  ReplyDelete
 6. ‹ኩሎ አመክሩ ወዘሠናየ ግበሩ›

  ReplyDelete
 7. እውነትን መናገር ዋጋ የሚያስከፍል ሰማዕትነት ነውና እግዚአብሔር አምላክ ዋጋህን ይክፈልህ ወንድማችን ዲን ዳንኤል ከብረት።
  እውነት ነው "በህጋዊው ቤት ህገወጥነት፤ በእግዚአብሔር ቤት ቄሣር፤ በጽድቁ ቤት እርኩሰት ሲሰለጥን ዝም የሚልበት የጆሮ ዘመን" የቀረበት ዘመኑስ የቀንድ ዘመን ነበር። ይሁን እንጂ የበሬው ባለቤቶች የቀንድ ዘመን መሆኑን ብቻ ሳይሆን የበሬው በጆሮው ዘመን በጅራፍ ቀንቶ፣ በቀንበር ተጠምዶ እየታዘዛቸው አርሰውበት እንዳገለገላቸው ውለታውንም የዘነጉ ናቸው። ዘመኑ የቀንድ ብቻ ሳይሆን ቀንዱንም ሲላቸው ቀንዱን ብለው(ሰብረው) በጆሮ ሊያስቀሩት፤ አሊያም ለአራጁ(ለቄሣር) ታልፎ የሚሰጥበት ዘመንም እንደሆነ ስለሚያውቅ፤ ትውልዱ ቀንድ እያለው ጆሮም ሲባል ቀንዱን እንዳያጣ አንድም ሞቱን ፈርቶ አሊያም መንፈሳዊነቱ ይዞት ያሚሉትን ተቀብሎ ጆሮም ተብዬ በቀንድ ዘመን ብኖር ይሻለኛል እንዲል አድርገውታል። እናም የጆሮው ዘመን አልፎ በቀንድ ዘመን ቢሆኑም በጭንቅላቱ ይዞት ይዞራል እንጂ ይህ ትውልድ በቀንዱ ስላልተዋጋቸው እንደ በሬው ባለቤት ሊማሩ አልቻሉም። አዳም በገነት ሳለም የእንስሳትና አራዊቱ ባላቸው ቀንድ አልተዋጉትም፤ በጥርሳቸው አልተናከሱትም፤ በመርዛቸው አልተናደፉትም፤ በክንዳቸው አልታገሉትም፤ በአፋቸው አልጮሁበትም፤ በኮቴያቸው አልተራገጡትም። ሁሉን ንዳ፣ ግዛ ቢባል ተገዢነቱን ረስቶ ህግ ቢተላለፍ ግን እነርሱም ለእርሱ እንዳልተገዙለት ሁሉ በእርሱ ላይ አምጸው ሊናከሱት፣ ሊበሉት፣ ሊዋጉት፣ ሊታገሉት፣ ሊናደፉት፣ ሊያሳድዱት ተነሳሱበት። ዛሬም የእምነት መሪዎቻችችን ለእግዚአብሔር መገዛትን ለቄሣር ቢሰጡት፤ ቄሣሩም ቤተ እምነቱን(ቤተ እግዚአብሔርን) እንደ ቤተ መንግሥት ልዘዝበት ቢል ግን በፍቅርም ሆነ በውድ የተገዙላቸው ተከታዮቻቸው ቀንዳቸውን አንስተው ዘመናቸው ዘመነ ቀንድ ይሆንባቸዋል ። እኛ ግን ለእግዚአብሔር ልንመች ሳያስፈልገን አይቀርም ቀንዳችን የሚዋጋና ከዘመነ ጆሮ አገዛዝ እንወጣ ዘንድ።

  ReplyDelete
 8. Be jero zemen tebel or wuhe tatibek endea medan ychalal bakih....zemenu yekend zemen new zim biye amiyen malet silekebedegn new ....please dont say that eminetik new yemiyadinih endatilegn mikiniatum.....

  ReplyDelete
 9. Yes I agree with you, this is the end of the world so we don't agree with our father. I don’t have the correct answer who is correct? This is my question for our church leader. Why we fast on Wednesday and Friday? For the all year. Is there any place in the Bible said fast on Wednesday and Friday for the all year? I asked many Preacher and priest they don’t have answer and they don’t know when, where and how started. Some of the preacher said that on Wednesday Israel people decided to kill Jesus Chris and on Friday, they killed him. I agree with them for on those days to fast to remember Jesus sacrifices but why we fast the all year without Bible order.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear anonymous March 14,2016 at 11:24
   You seem an elementary student. What you know and want is always 1+1=2, but there are lots of mathematical equation that give 2. Very simple once 4-2=2, 4/2=2...
   As an elementary student you said the reasons but as high school or university student instead of arguing you go back to elementary knowledge.
   If you love to christ goes to the depth of your reasons not only wednesday and Friday that you fast, you will fast for your whole life. Please try to dig much to know how to live for his true love being seen from his birth up to the cross. Try to make your self mature enough for the bible and its whole message. Literary reading can not make you mature on it, as knowing English can not make oneself a physicist, chemist, mathematician or any thing else. I can feel even what I am saying might be difficult for you to understand, as a word can not say every feeling of a human being. Any way ask and read lots of books.

   Delete
  2. You asked a question on the minds of many, and there's always answer for all questions, and I'm sorry your supposed sources did not give you enough answers.

   The reason the we EOTC members fast roughly 250 days out of the 365 days is because EOTC synod members decided to have 7 mandatory fastings and additional willful fasting times set by consulting with your ንስሐ አባት (the Wednesday. and Friday are part of the 7 fastings counted as one) here is a helpful link, spend 30mins to get answers.

   https://www.youtube.com/watch?v=IVD4oQ-h0iI

   The basis for all the 7 mandatory fastings are all major Holy reasons. What you have to understand is, our fathers set the fasting dates and seasons to help us grow our Christian life; just like a plant feeds on water, sunlight and nutrients to grow, our spirituality needs fasting to grow and help us become better Christians. I suggest you try one out of the 7 fastings, with the intent of getting blessings.

   Unfortunately, we are living in the dark days, where literally everything is being questioned and challenged, not with the intent to understand, but with the intent to make all important norms worthless. The devil also works day and night to push its idea of deceiving believers by throwing out ideas amid the life of believers, just like a heckler disturbs meetings, regardless of its point.
   I hope the blessing of the Holy TRINITY finds you in your effort to find answers to your questions.

   Delete
  3. Thank you Anonymous March 18, 2016 at 6:46 AM and Anonymous March 14, 2016 at 11:24 PM. This question was on my mind as well but I am always afraid to ask question because some people answer my question with wrong words like Anonymous March 17, 2016 at 12:18 PM. There is no wrong questions so the people they know the answer always they answer wrong way or they accuse the person instead of answering the question. We have to learn something from our brother Daniel Kibret. He always post the positive and negative feedback .

   Delete
  4. አሁን በዚህ ቁምነገር መሀል ስለ ሆድ ይጠየቃል!?

   Delete
 10. ዲ/ን እግዚአብሔር ያክብርህ ግሩም ጹፍ ነው። ድርጅት ስትል አንተም እንደ ቀላል የጀመርከው አሁን ግን እውቅ ስለሆነው የበጎ ሰው ሽልማት አስብበት

  ReplyDelete
 11. ዲ/ን እግዚአብሔር ያክብርህ ግሩም ጹፍ ነው። ድርጅት ስትል አንተም እንደ ቀላል የጀመርከው አሁን ግን እውቅ ስለሆነው የበጎ ሰው ሽልማት አስብበት

  ReplyDelete
 12. ‹‹ከቻለ ይሞግትሃል፤ ካልቻለ ትቶህ ይሄዳል፡፡›› ከአውሮፓውያን ቤተ እምነቶች የምንወስደው ትምህርት ነው፡፡

  ReplyDelete
 13. Tiru Milketa new Dani, Joro yalew yisma.

  ReplyDelete
 14. ዘመኑን የዋጀ እንደ ጆሮ ዘመን ያላፈጀ ጥልቅ እሳቤ!!!

  ReplyDelete
 15. ዘመኑን የዋጀ እንደ ጆሮ ዘመን ያላፈጀ ጥልቅ እሳቤ!!!

  ReplyDelete
 16. ዲያቆን ዳንኤል እያነበብኩት ውስጤ በዚህ የጾም ወቅት ቅቤ ጠጣ ፡ ብቻየን እንደ እብድ እስቃለሁ ምንም ማለት አልችልም የውስጤን አውጥተህ የጻፍከው ያህል ነው የተሰማኝ፡፡ እግዚአብሔር ለሁላችንም ልቦና ይስጠን፡፡ የሚያሳዝነው የሀይማኖት አባቶች በጆሮ ዘመን ኑሩ ማለታቸው ነው፡፡

  ReplyDelete
 17. Why u are silent abt death of Abune Natnael?

  ReplyDelete
 18. OOOOHHHH Dn. Dani min largih?
  Essay enkuan ye joro zemen alefe, lewt malet ye kend zemen siderse new!!!!!

  ReplyDelete
 19. That is true "Anjet Aris eko neh Dani!"

  ReplyDelete
 20. ክፉ ኣይንካህ፣ እመቤቴ በጧ በማታ ኣትለይህ።

  ReplyDelete
 21. ችግሩ እኮ የቀንድና የጀሮን ዘመን ኣያውቁትም።

  ReplyDelete
 22. The article suites best expressing the evil and ignorant mentality of the Woyane junta. HD bluffed in his parliamentary discourse the era of the Ears without considering the time we are now.

  ReplyDelete
 23. ምን ዋጋ አለው አንባቢ መሪ የለ።
  በ e-mail ቢላክላቸው ያነቡ ይሆን???

  ReplyDelete
 24. "ምን ዋጋ አለው አንባቢ መሪ የለ።
  በ e-mail ቢላክላቸው ያነቡ ይሆን???"

  ReplyDelete
 25. True,
  The Arab spring should have been a teaching moment, those people had lived the "years of ears" when they were fed 3 times a day, but the "years of horn" should have come and the leaders were not prepared.

  EPRDF should have learned from ethnic clashes of Rwanda, and Kosovo when they ehtnsized the country's politics. Now it's experiencing the "fruits" of ethnic federalism, the clash between Ethiopian nations and it denies the occurrence of clashes instead of finding lasting solution. This is the legacy of the so called "the great leader"

  There's still time for the EPRDF to switch gears before the dreaded "sub Saharan spring"

  ReplyDelete
 26. Thank you anyway.We all can write amazing and surprising ideas but we all cann't live in what we write.I may write what I have read or what I have thought but what I live and what I wrote two different lives at two different worlds.Hi guys let's write inwards rather than outwards.

  ReplyDelete
 27. Yemigerm tsihuf new! Tikus tikusun liawm benetsa. Egziabher Yistilin

  ReplyDelete
 28. Dn. Daniel K. thanks for the insightful article. I always enjoy reading your post and learn a lot from it.

  ReplyDelete
 29. የጆሮ ጊዜ አልፏል፤ ማሳመን ማግባባት፣ ማስረዳት፣ ይፈልጋል፡፡ መስማት ብቻ ሳይሆን መሰማትም ይሻል፡፡

  ReplyDelete
 30. Thanks Dn. Daniel K. I trust your blog is a good learning site for many Ethiopians!

  ReplyDelete
 31. D/n Dani, absolutely right as usual.

  ReplyDelete
 32. Ethiopiawi martin.....beteret ena misalea hager, haimanot...
  Bezian zemen endeat yekend gizea tayew bakih martin......
  Yemalawkew genet mignote mena aderekew emgermew demo betam new yemameseginik....
  yemin genet new genet bemidir new....
  Yemin hatiyat new sew rasu yemifetrew firacha new tsidikim endeza.....
  hatiyat, kuneniye, tsidk, genet , gahenem (hell) etc yemesaselut tarik ena yejero zemen eyatakesachu sayhon endihum asredun mikniatu zarea yekend zemen newuna.....no taboo or stupid word I ask only to those who have +ve mind and thought.

  ReplyDelete
 33. Sorry for the last generation who lived in the time of ear and always lived only by listening what was told by its bosses . This is the time of horn which the former ear not only listens but also asks why, who , what .when and how so that the mistakes of last and old generation could not repeat itself and live the same old way . Let all of us accept our shortcomings and try to modify our way of life spiritual, mentally , socially ,economically and politically so that the future be bright on earth and in heaven .

  ReplyDelete
 34. keep the good work Dn Dani. you are the best who share nuggets of wisdom for whom interested in learning

  ReplyDelete
 35. ላመነው ነገር እንኳ ቢሆንተጨማሪ ማስረጃ ይፈልጋል፡፡ የጥንቱን ትርክት ብትተርክ፣ የጥንቱን ዘፈን ብትዘፍን፣ የጥንቱን ፉከራ ብትፎክር እንደ ሞኝ ይቆጥርሃል፡:፡ ያ ሁሉ የጆሮ ዘመን ታሪክ ነውና፡፡ 

  ReplyDelete
 36. Antin bicha kifu ayinkabin Dn Daniel

  ReplyDelete
 37. The best writer in our age thanks dani

  ReplyDelete
 38. The best writer in our age so far I know thanks deacon dani

  ReplyDelete