Friday, February 19, 2016

...መቼ ተነሱና የወዳደቁት..." ጂጂ


ግልጽ ደብዳቤ ለመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

(ያሬድ ሹመቴ

ይድረስ / ክንደያ /ህይወት

ለጤናዎ እንደምን አሉ?

ክቡርነትዎ በአካል ተያይተን አናውቅም። ከስምዎ እና ከስራ ድርሻዋ ውጪ ስለርስዎ ምንም የማውቀው ነገር የለኝም። ነገር ግን ወቀሳ ለማቅረብ ይህንን ደብዳቤ ስጽፍልዎ እርስዎን ባለማወቄ ምክንያት ስህተት ሰርቼ ከአቅምዎ እና ጥሩነትዎ ውጪ የሆነ አስቀያሚ ነገር ከጽሁፌ ቢወጣ በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ።
እርስዎ በሚያስተዳድሩት የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ስለሚገኘው አንድ ታሪካዊ ቦታ ላስተዋውቅዎ ነው። እርስዎ አጥሩን ለማሳጠር የወጣውን ወጪ እና የጊቢውን ስፋት በካሬ ሜትር ማወቅዎን እንጂ ውስጡ ስላለው እንቁ ታሪክ እንደማያውቁ እጠራጠራለሁ። ስለዚህም በእርግጠኝነትና በድፍረት ታሪኩን ላስተዋውቅዎ ወድጃለሁ። ምክንያቱ ደግሞ ታላቁን ታሪክ የሚያውቁ ቢሆን ኖሮ የቦታውን አያያዝ ያሳምሩት ነበርና ነው።
እንዳየሱስ በተለያዩ የታሪክ ፀሀፊያን ዘንድ ከዓድዋ ድል ጋር ስሙ በደማቅ ሁኔታ የሚነሳው መቀሌ የእንዳየሱስ ምሽግ ነው።
ወራሪው የጣልያን መንግስት 1888. ለአመታት ሲቋምጥባት የኖረችውን ኢትዮጵያ በወረረበት ወቅት ሰሜናዊውን ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛቱ ውስጥ እያደረገ ወደታች በመግፋት እስከ አሸንጌ ሀይቅ ድረስ ግዛቱን አሰፋ። ይህንንም ወረራ በመመከት ህዝባቸው አንድ ሆኖ እንዲሰለፍ ከፍተኛ ተጋድሎ ሲያደርጉ በነበሩት ብልሁ መሪ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ አማካኝነት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከሁሉም አቅጣጫ በጀግኖች የጦር አበጋዞቹ እየተመራ ጉዞውን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ አደረገ።
በዚህ ጊዜ ታዲያ ይህንን ታላቅ ሀይል ወራሪው የጣሊያን መንግስት ለመመከት ይቻለው ዘንድ ከመቀሌ 80 .. ርቀት ላይ በሚገኘው የአምባ አላጌ ተራራ ላይ መሽጎ የሰራዊቱን መንገድ ዘጋ። በራስ መኮንን የሚመራው ቀዳሚ ጦር ቦታውን ለማስለቀቅ ከፍተኛ የሆነ የድርድር ስራ ቢከውንም በማጆር ቶሴሊ የሚመራው የጣሊያን ሀይል ቦታውን "አለቅም!" በማለት አሻፈረኝ አለ።
በኢትዮጵያ ወገን ከነበሩ የጦር መሪዎች መሀል ፊታውራሪ ገበየሁ እና ቀኝ አዝማች ታፈሰ ከመሪዎቻቸው ፍቃድ ሳያገኙ ጦርነቱን በንዴት አስጀመሩ። በተጀመረው ድንገተኛ ውጊያ የጣሊያን ጦር ፍርክስክሱ ሲወጣ የጦሩ መሪም ማጆር ቶዜሊ በቦታው ላይ ህይወቱን አጥቷል።

ጦርነቱ ያለፍቃድ የተጀመረ ቢሆንም ድል ለኢትዮጵያዊያኑ ጀግኖች አያቶቻችን ሆነ። በውጊያው የተረፈው የጠላት ጦር እግሬ አውጪኝ ብሎ በመፈርጠጥ የመቀሌው እንዳየሱስ ምሽግ ውስጥ ሰፈረ።
ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ገና መንገድ ላይ የነበሩ በመሆኑ መቀሌ እንዳየሱስ የደረሱት ራስ መኮንን ጦርነቱን ያለንጉሱ ፍቃድ ላለማስጀመር ፔትሮ ፊልተር በተባለ ሰው አማካኝነት እየተደራደሩ ምሽጉን በርቀት ይጠብቁ ጀመር።
የጣሊያን መንግስትም በአንድ በኩል የሚታረቅ በመምሰል እየተደራደረ በሌላ በኩል ደግሞ መሰበር የማይችል ጠንካራ ምሽግ ገነባ። በዚህ ጊዜ ንጉሰ ነገስቱ ደርሰው ምሽጉን ሲያስተውሉ ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ሆኖ አገኙት። ይህንንም ግንብ ለማስፈረስ በራስ አሉላ ድጋፍ ሰጪነት የራስ መኮንን ጦር ግዳጅ ተጣለበት።
በዚህ ቦታ ላይ በተጀመረው ውጊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵታውያን ጀግኖች እንደ ቅጠል ረገፉ። ጣልያንን ከግንቡ መሀል ነጥሎ ለማውጣት የተከፈለው እልህ አስጨራሽ ትግል በስኬት ሊጠናቀቅ አልቻለም። የራስ መኮንን ቁጭት እራሳቸውም ጭምር እሳት ውስጥ እስከ መማገድ ስሜት ውስጥ ቢያስገባቸውም በራስ አሉላ ተቆጪነት ሊተርፉ መቻላቸው በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።
ይህ ሁሉ የደም ዋጋ የተከፈለበት የመቀሌው እንዳየሱስ ምሽግ በእቴጌ ጣይቱ ሀሳብ አመንጪነት(ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት በኦቶ-ባዮግራፊ መጻህፋቸው ሀሳቡ /ፃድቅ የተባለ የራስ መኮንን ፀሀፊ ያመነጨው መሆኑን እና ከእቴጌ ጣይቱ ሀሳብ ጋር መግጠሙን ይገልፃሉ) "ጣልያን ውሀ እየቀዳ የሚጠቀምበትን የምንጭ ውሀ ተቆጣጥሮ በመያዝ ከምሽጉ በግድ እናውጣው" የሚል ምክር ተመከረ።
በዚህም አማካኝነት በሶስት አዛዦች የሚመራ 900 ወታደር ውሀውን እየተታኮሰ 15 ቀናት ያህል ጣሊያን ድርሽ እንዳይልበት ጠበቀ። በመድፍ ተኳሽነታቸው ስመጥር የሆኑን ሊቀ መኳስ (የኋላው ራስ) አባተ ቧያለው እና በጅሮንድ(የኋላው ደጃዝማች) ባልቻ ሳፎ ከእቴጌ ጣይቱ በአዛዥ ዛማኔል በደረሳቸው መልዕክት ምንጩን እንቅልፍ አጥተው ሲያስጠብቁ ውለው አደሩ።
በሌላ በኩል ደግሞ በጠንካራው ምሽግ ዙሪያ የተረፈረፉትን አትዮጵያውያን ለመቅበር የተኩስ አቁም ድርድር ከጣሊያን ጋር ቢደረግም "በምትኩ ውሀውን ካለቀቃችሁ አናስቀብርም" በማለታቸው ምሽጉ ዙሪያ የወደቁ በሺዋች የሚቆጥርሩ አትዮጵያውያ ሬሳ እንደተነባበረ በስብሶ ቀረ።
የሆነ ሆኖ ጣሊያን ከአቅሙ በላይ በሆነው የውሀ ጥም ሳቢያ ምሽጉን ለመልቀቅ ተገደደ። በራስ መኮንን ዋስትና ከምሽጉ ወጥቶ ወደ አዲግራት ተሰናበተ። በዚህ ምክንያት መሬታችንን እያስለቀቁ አንድ ቦታ ላይ እንዲጠራቀሙ እና በአንድ ጊዜ ጦርነት እንዲገጥሙ በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ መሪነት የተደረጉት ጣልያኖች የካቲት 23 ቀን 6 ሰዓታት በፈጀ ውጊያ ሙሉ ለሙሉ ተደመሰሱ። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብቸኛ የሚያደርጋትን ነፃነቷን ለአለም አወጀች። ሌሎች ቅኝ የተገዙ የአፍሪካ ሀገራትም ኢትዮጵያን ተምሳሌት በማድረግ ከባርነት ቀንበር ወጡ።
ይህ ሁሉ ታሪክ ሲሰራ በመቀሌ እንዳየሱስ የረገፉ አያቶቻችን እዚያው በሞቱበት ቦታ ላይ አስክሬናቸው ተከምሮ አፈር ለበሰ። ቦታው እራሱ ቤተ ክርስቲያን በመሆኑ አፈር ብቻ በማልበስ ለጀግኖቹ አሸኛኘትት ተደረገላቸው።

ክቡርነትዎ
ይህን መሰለ ታሪክ የተፈፀምውበትን ቦታ ለማየት ጉዞ ዓድዋ ባዘጋጀው ከአዲስ አበባ ዓድዋ የሚዘልቅ የእግር ጉዞ አማካኝነት ላለፉት ሶስት አመታት መቀሌ እንዳየሱን ምሽግን ጎብኝቻለሁ። በሶስቱም አመታት የዩኒቨርሲቲውን ግቢ አልፈን ለመግባት ባለመከልከላችን ከልብ እናመሰግንዎታለን። በመጀመሪያው አመት ላይ የገረመን ነገር ቦታው ጊቢው ውስጥ ባሉ መምህራን ተማሪዎች እና አስተዳደር ምንነቱ አለመታወቁ ነበር።
የዛሬ አመት ደግሞ ሌላ አስደንጋጭ ነገር ለማየት ተገደድን። ይህም፥ 40ኛውን የትግል አመታት ለማክበር በዚህ ከፍታ ቦታ ላይ ከመቀሌ ከተማ የትኛውን ቦታ መታየት የሚችል 40 ቁጥር እና የቀድሞውን መሪ አቶ መለስ ምስል የያዘ ግዙፍ ምልክት እዚህ ቦታ ላይ ተተከለ። ምንም እንኳን ይህን ምስል ለመትከል መቀሌ የሚገኘው ወሳኝ ቦታ ከሁሉም አቅጣጫ ሊታይ የሚችል ተራራማ መሬት "እንዳየሱስ" ቢሆንም መተከሉ የቦታውን ታሪክ የሚበርዝ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ጥፋል ሊባል የሚችለው ይህንን ግዙፍ ምስል በቦታው ላይ ለማስቀመጥ እላይ ድረስ ተሽከርካሪ ማስወጣት የሚችል መንገድ ለመጥረግ በግሬደር መታረሱ ነው።
የዛሬ አመት እኛ እዚያ በደረስንበት ወቅት ከቦታው መታረስ በተጨማሪ በየቦታው የሰው አፅም ወድቆ በማየታችን ሁላችንም አምርረን አለቀስን። ጭፈራ ብዙ በነበረበት ሰዓት ሰሚ ማግኘት የማይቻል ቢሆንም በወቅቱ ለነበሩ የመንግስት ታላላቅ ሰዎች ሁኔታውን አሳወቅን። ታሪኩን ጠንቅቀው የማያውቁት ያካባቢው ሰዋች በየቦታው የወዳደቁትን ክቡሩን የሰው አጽም ምንነት ስጠይቅ፥ እርግጠኛ ባለመሆን "ደርግ የረሸናቸው ይሆናሉ" ከሚል በቀር የተቀራረበ መልስ ሊሰጠኝ የሚችል ሰው አልነበረም።
ይህንን እስካሁን በማንኛውም መንገድ ለህዝባችን ሳልገልጽ የቆየሁት በዚህ አመት ለውጥ ሊኖር ይችላል የሚል እምነት ይዤ ጉዳዩም የተለየ መልክ እንዳይይዝ በማሰብ ነበር። ነገር ግን ዘንድሮም ቢሆን እዚሁ ቦታ ላይ ተመልሰን ብንመጣም በየጥጋጥጉ በርካታ የሰው አጽም ወድቆ ተመለከትን። ከአንድ አመት በላይም አጽሞቹን በክብር አሰባስቦ ለማሳረፍ የተደረገ ነገር ባለመኖሩ አዘንን። የታላላቆቹ አባቶቻችን ገድል ሳይነገር ቀርቶ ጭራሽ የተከበረው አጽማቸው በየሜዳው ተጣለ።

ክቡርነትዎ
የትምህርት ተቋማት ይህን መሰል ታሪካዊ ቅርሶች፥ የምርምር ማዕከላት በማድረግ እንደማይጠቀሙባቸው ለማወቅ ትምህርት ቤቶቻችን የሚታወጡዋቸውን ተማሪዎች ሞራል ማየት በቂ ነው። ሀገሩን የሚወድ ታሪኩን የሚጠብቅ ትውልድ እየጠፋ ሳንቲም አባራሪ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑ በዩኒቨርሲቲው አጥር ግቢ ውስጥ የተከሰተውን ይህንን ታላቅ የታሪክ ኪሳራ ማየት በቂ ነው።
መማር ማለት ምን ማለት ነው?

መማር ማለት ይህ ከሆነ ከትምህርት በላይ የሀገራችን ጠላት የለም። በተማሩ ሰዋች ላይ የዚህ አይነት ችግር በጥልቀት የሚስተዋለው የሚማሩት ነገር ምንነት ነው ብዬ በግሌ አምናለሁ። "ሀገር ማለት ሰው ነው...ሀገር መሬትን አያጠቃልልም" ለሚለው መንግስታችን፥ "ሀገር ማለት ሰው ነው" ለሚለው መርሁ ተቃርኖ የሚያሳይ ኪሳራ ነው። "ሀገር ማለት ሰው ብቻ አይደለም!" ያሉ አያቶቻችን፥ እዚህ ቦታ ላይ ለሀገር ዳር ድንበር ሲሉ ዋጋ ከፈሉ" እነሱ ግን ሰዎች ናቸው። "ሀገር ማለት ሰው ነው" የሚለው የዘመናችን "እሳቤ" ግን ለመሬታችን የሞቱትን ሰዎች አስክሬን በየቦታው ይበትናል። ሀገር ማለት ሰው ከሆነ፥ ሰዋች ሞተውም ሰዎች ናቸው እንጂ ወደ ሌላ ፍጥረት አይቀየሩም።

በግሌም የማምነው፥ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው የርስዎ ተቋም የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ነው። በቅጥር ጊቢው የሚገኘውን ታሪካዊ ቅርስ አያውቀውምና። ትምህርት ቤቱን የእውቀት መካን ለማድረግ ለታሪካችን ክብር ይሰጥ። እግዚአብሔር ፈቅዶ በአመቱ ስንገናኝ፥ የአያቶቻችን አጽም በክብር አርፎ፥ ቦታው ባማረ ሁኔታ ተይዞ ለጎብኚ ምቹ ሆኖ እንደሚጠብቀን ተስፋ አለኝ።
አክባሪዎ ያሬድ ሹመቴ

ተፃፈ በመቀሌ ከተማ የካቲት 11 2008 ..
።።።
ለክቡራን አንባቢዎች

አንብበው ከጨረሱ ለታሪካችን ክብር ይሰጥ ዘንድ መልዕክቱን ሼር በማድረግ ያዳርሱ።

ፈጣሪ ውለታዎን ይክፈል።

ክብር ለሀገር ነፃነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ለከፈሉ የዓድዋ ሰማዕታት!


37 comments:

 1. ክብር ለሀገር ነፃነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ለከፈሉ የዓድዋ ሰማዕታት!

  ReplyDelete
 2. በጣም ጥሩ ነው ወንድም ያሬድ ወንድም ወንድሙን ገድሎ ማስታወሻ ይደረግለታል። ነገር ግን ለሃገሩ ሲል ለሞተ ጀግና
  ኣስታዋሽ የለም።

  ReplyDelete
 3. ክብር ለሀገር ነፃነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ለከፈሉ የዓድዋ ሰማዕታት!

  ReplyDelete
 4. አዉቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነቃም

  ReplyDelete
 5. very pity to hear...

  ReplyDelete
 6. Dr. Kndeya and TPLF leaders are followers of Illuminati, the religion of Satan followers,and are the enemies if Blessed Ethiopia. The president rapes youngsters of the university students and he is the top corrupt. The TPLF officials are committing Genocide in Welqait, Tegede, Telemet, Oromia, Somali. Afar, Tenben...in every corner of Ethiopia....and they act much more than Graziani. According to them, Ethiopia is a country of less than 100 years and doesn't have reliable history. MAY GOD ACT TO VANISH THIS EVER ENEMIES THROUGH HIS GRACE, AMEN. HEY, LET'S UNITE TO SAVE OUR BELOVED NATION...MAY GOD BLESS ETHIOPIA! Kibr leabatochahcin yihun.

  ReplyDelete
 7. ይህን የሚገርም ጉድ ስላካፈልከን እናመሰግንሀለን። ይገርማል ዘመናችን እንደዚህ መሆኑ። እነኚህ ዘመነኞች ያላስተዋሉት የቀደመ ታሪክን እያጠፉ የራስን ስራ ማግዘፍ። የሚያደርጉት ሁሉም ነገ በነርሱ እንዲደረግባቸው እያስተማሩ እንደሆነ ማስተዋል እርቋቸዋል። እግዚአብሔር በየቤታችን ታሪክ ተረካቢ ትውልድ እንድናፈራ ፈቃዱ ይሁን።

  ReplyDelete
 8. Please read the shocking phenomena happened in Tigray, in hear of Mekele how our heroes fathers who sacrificed and fallen heroes for. Sack of their country's sovereignty and freedom our people and the freedom that we are exercising today
  Shame on ዶ/ር ክንደያ ገ/ህይወት
  You are one of the top intellectual that our country has, but you are blinded with tribal and ethics politics and fail to understand your own history within your compound in the heart of Mekele University where we all hope the country's most educated young people will come out for better future of our people and our country Ethiopia but instead you erected the the tyranny, dictator, selfish Meles Zenawi who sold his country's in history of the whole natations' history on the planet, betrays his own people and washed his hands with innocents' blood
  Dr,take bit of your own time, what is education or the meaning being educated after all ? If someone lik you never says or pass the truth on to the next generations denied your own history?
  If someone educated like you had a short sighted thinking capacity and worst than illiterate? Spread lies in stead of the truth? You erect the statute Meles who was a lier, Nazi fascist who buterchered his own people blindly, destroyed and uprooted his believe, a pagan leader whose visions was to distroy the culture, the faith, the history of his own country Ethiopia. A man who preached hate, cruelty and enemty among peace loving people.
  Meles was a demon who eats his mother's womb or flesh while within his mother's womb.
  Dr, you blindly tried to build the dead man's dead story on the living memory of our fathers? Shame on you, you betrayed your own history, which the whole world written with a golden pen.
  Dr, hope the darkest blanket of tribal hate which totally eradicate your being human and intellectuality, would be back one day, and you may find being Ethiopian would be much more than what dirty games that you are playing today.
  Hope you will understand that being an Ethiopian would be much more important than self confined ,isolated to one particular ethic "wayane the incurable cancer cell"

  Please,
  Read how much the cancer cell of being TPLF or Being wayane infected the our intellectual even to the top educated person we trust most, are still on the dark side of history

  ReplyDelete

 9. ኦሪት ዘዳግም
  19፥14
  አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር በምትወርሳት ርስትህ የቀደሙ ሰዎች የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል።

  ReplyDelete
 10. አይ መቀሌ…
  በመጀመሪያ መቀሌ ይህን የሚከተለውን ነገር ስትሰማ ዝም አለች፡፡ ኢትዮጵያ በአስረኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ሙስሊም ወንድሞቻችንን ስትቀበል የነበረው ንጉስ አክሱማዊው ንጉስ አርማህ ሳይሆን አልነጃሽ የሚባል ሙስሊም ንጉስ ነው፤ ሲባል ዝም አለች፡፡ ራሳቸው ሙስሊሞቹ የሰሩት ፊልም እንኳን ያ ንጉስ ክርስትያን እንደነበረ አንዳች የሚያክል መስቀሉን አንገቱ ላይ በጠንካራ ወፍራም ማተብ ተሸክሞ ያስመለክተናል፤ ይህን ሰምታ ብዙ ሲደረግ እያየች ዝም እንዳለች አለች፡፡ “አክሱም ጎረቤቴ እንጅ እኔ አይደለችም፤ የአክሱም ጉዳይ ለኔ ምኔ ነው?” ብላ ይሆን፡፡
  ቀጥሎ ደግሞ ለአድዋ ድል መንደርደሪያ የሆነውን የራሷን ታሪክ በአፈር ሲያለብሱት እያየች እየሰማች ዝም አለች፡፡ ለመሆኑ መቀሌ ሰው የላትም? ልጅ የላትም? ወጣት የላትም? ጨርሶ በሆዳምነት (የእህል ድህነትን በማጥፋት ዘመቻ) እና በዘረኝነት ጠፍቶ አለቀ? ጥቂቶች እንደሚኖሩ ከፈጣሪ ጋር ተስፋ እናደርጋለን፡፡

  ReplyDelete
 11. መማር ማለት ይህ ከሆነ ከትምህርት በላይ የሀገራችን ጠላት የለም ያሬድ ሹመቴ ጠፍተህ ነበር እንኳን ደህና መጣህ እንዲህ ልክ ልካቸው ንገራቸው ለትውል ፀር ሁሉ

  ReplyDelete
 12. This is nothing. we will hear more worst news in the future. Saint Ethiopia, what can i do for u?

  ReplyDelete
 13. አይ መቀሌ…
  በመጀመሪያ መቀሌ ይህን የሚከተለውን ነገር ስትሰማ ዝም አለች፡፡ ኢትዮጵያ በአስረኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ሙስሊም ወንድሞቻችንን ስትቀበል የነበረው ንጉስ አክሱማዊው ንጉስ አርማህ ሳይሆን አልነጃሽ የሚባል ሙስሊም ንጉስ ነው፤ ሲባል ዝም አለች፡፡ ራሳቸው ሙስሊሞቹ የሰሩት ፊልም እንኳን ያ ንጉስ ክርስትያን እንደነበረ አንዳች የሚያክል መስቀሉን አንገቱ ላይ በጠንካራ ወፍራም ማተብ ተሸክሞ ያስመለክተናል፤ ይህን ሰምታ ብዙ ሲደረግ እያየች ዝም እንዳለች አለች፡፡ “አክሱም ጎረቤቴ እንጅ እኔ አይደለችም፤ የአክሱም ጉዳይ ለኔ ምኔ ነው?” ብላ ይሆን፡፡
  ቀጥሎ ደግሞ ለአድዋ ድል መንደርደሪያ የሆነውን የራሷን ታሪክ በአፈር ሲያለብሱት እያየች እየሰማች ዝም አለች፡፡ ለመሆኑ መቀሌ ሰው የላትም? ልጅ የላትም? ወጣት የላትም? ጨርሶ በሆዳምነት (የእህል ድህነትን በማጥፋት ዘመቻ) እና በዘረኝነት ጠፍቶ አለቀ? ጥቂቶች እንደሚኖሩ ከፈጣሪ ጋር ተስፋ እናደርጋለን፡፡

  ReplyDelete
 14. ዳንኤል ግን ምን ለማለት ፈልገህ ነው አንዱን ጦማር በደንብ ሳንወያይበት በሌላ አንገብጋቢ ባልሆነ ጦማር ተክተህ ትኩሳቱን የምታበርደው?

  ReplyDelete
 15. ክብር ለሀገር ነፃነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ለከፈሉ የዓድዋ ሰማዕታት

  ReplyDelete
 16. አይ መቀሌ…
  በመጀመሪያ መቀሌ ይህን የሚከተለውን ነገር ስትሰማ ዝም አለች፡፡ ኢትዮጵያ በአስረኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ሙስሊም ወንድሞቻችንን ስትቀበል የነበረው ንጉስ አክሱማዊው ንጉስ አርማህ ሳይሆን አልነጃሽ የሚባል ሙስሊም ንጉስ ነው፤ ሲባል ዝም አለች፡፡ ራሳቸው ሙስሊሞቹ የሰሩት ፊልም እንኳን ያ ንጉስ ክርስትያን እንደነበረ አንዳች የሚያክል መስቀሉን አንገቱ ላይ በጠንካራ ወፍራም ማተብ ተሸክሞ ያስመለክተናል፤ ይህን ሰምታ ብዙ ሲደረግ እያየች ዝም እንዳለች አለች፡፡ “አክሱም ጎረቤቴ እንጅ እኔ አይደለችም፤ የአክሱም ጉዳይ ለኔ ምኔ ነው?” ብላ ይሆን፡፡
  ቀጥሎ ደግሞ ለአድዋ ድል መንደርደሪያ የሆነውን የራሷን ታሪክ በአፈር ሲያለብሱት እያየች እየሰማች ዝም አለች፡፡ ለመሆኑ መቀሌ ሰው የላትም? ልጅ የላትም? ወጣት የላትም? ጨርሶ በሆዳምነት (የእህል ድህነትን በማጥፋት ዘመቻ) እና በዘረኝነት ጠፍቶ አለቀ? ጥቂቶች እንደሚኖሩ ከፈጣሪ ጋር ተስፋ እናደርጋለን፡፡
  አይ መቀሌ…
  በመጀመሪያ መቀሌ ይህን የሚከተለውን ነገር ስትሰማ ዝም አለች፡፡ ኢትዮጵያ በአስረኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ሙስሊም ወንድሞቻችንን ስትቀበል የነበረው ንጉስ አክሱማዊው ንጉስ አርማህ ሳይሆን አልነጃሽ የሚባል ሙስሊም ንጉስ ነው፤ ሲባል ዝም አለች፡፡ ራሳቸው ሙስሊሞቹ የሰሩት ፊልም እንኳን ያ ንጉስ ክርስትያን እንደነበረ አንዳች የሚያክል መስቀሉን አንገቱ ላይ በጠንካራ ወፍራም ማተብ ተሸክሞ ያስመለክተናል፤ ይህን ሰምታ ብዙ ሲደረግ እያየች ዝም እንዳለች አለች፡፡ “አክሱም ጎረቤቴ እንጅ እኔ አይደለችም፤ የአክሱም ጉዳይ ለኔ ምኔ ነው?” ብላ ይሆን፡፡
  ቀጥሎ ደግሞ ለአድዋ ድል መንደርደሪያ የሆነውን የራሷን ታሪክ በአፈር ሲያለብሱት እያየች እየሰማች ዝም አለች፡፡ ለመሆኑ መቀሌ ሰው የላትም? ልጅ የላትም? ወጣት የላትም? ጨርሶ በሆዳምነት (የእህል ድህነትን በማጥፋት ዘመቻ) እና በዘረኝነት ጠፍቶ አለቀ? ጥቂቶች እንደሚኖሩ ከፈጣሪ ጋር ተስፋ እናደርጋለን፡፡

  ReplyDelete
 17. ዳንኤል ግን ምን ለማለት ፈልገህ ነው አንዱን ጥሩ ጦማር በደንብ ሳንወያይበት ሌላ ብዙም አንገብጋቢ ያልሆነ ጦማር በአናቱ ከልሰህ ትኩስነቱን የምታበርደው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. የቀደመው ጦማር ስለሆድ ነበር?

   Delete
 18. We know your hidden objective: you are raised against PM Meles Zenawi.

  ReplyDelete
 19. ዲ/ን ዳንኤል ስለጽሑፎችህ በሙሉ እናመሠግናለን፡፡ እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና ይስጥህ፤ የአገልግሎት ዘመንህን ያስፋልህ፡፡
  ዲ/ን የባሻ ወልዴ ችሎት አውጫጭኝ የሚባለው ጊዜው መች ነበረ? እባክህ አመተ ምህረቱን እንድትነግረኝ ነበር፡፡ ወደፊትም ታሪኩን ብታስቃኘን እወዳለሁ፡፡

  ReplyDelete
 20. መማር ማለት ይህ ከሆነ ከትምህርት በላይ የሀገራችን ጠላት የለም።
  ትምህርት ተቋማት የታሪካችን ማወቂያ እንጂ መጥፊያ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ይደረግ።
  ክብር ለሀገር ነፃነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ለከፈሉ የዓድዋ ሰማዕታት!

  ReplyDelete
 21. ክብር ለሀገር ነፃነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ለከፈሉ የዓድዋ ሰማዕታት!

  ReplyDelete
 22. በጣም ጥሩ ነው ወንድም ያሬድ ወንድም ወንድሙን ገድሎ ማስታወሻ ይደረግለታል። ነገር ግን ለሀገሩ ሲል የሞተ ጀግና ኣስታዋሽ ይጣ?

  ReplyDelete
 23. የአያቶቹ ልጅMarch 3, 2016 at 12:55 PM

  በጣም ጥሩ ነው ወንድም ያሬድ ወንድም ወንድሙን ገድሎ ማስታወሻ ይደረግለታል። ነገር ግን ለሀገሩ ሲል የሞተ ጀግና ኣስታዋሽ ይጣ?

  ReplyDelete
 24. ክብርና ሞገስ ለወደቁት ታላላቅ የኢትዮጵያ ልጆች ይሁን አሜን !!!

  ReplyDelete
 25. ato yared shumete bizegeym tyakeh mlash yagegn ymslegnal balfew samnet sheger fm baweraw zenalay yesemaetate atsm bekbr ediyarefe tedergual

  ReplyDelete
 26. አገር ማለት
  አገር በታሪክ በቋንቋ በሀይማኖት በልምድ በተስፋ በደስታና በመክራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት
  የዓለም ክፍል ነው። አገር ማለት አያት ቅድም አያት የተወለዱበት አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየተከላከሉ
  ለሕዝብና ለመንግስት የሚጥቅም ሥራ ሠርትው እድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻችውን ተክተው የተቀበሩበት ጉድጓድ ነው።
  በመወለድ እትብት በመሞት አካል ከአፈሩ ጋራ ስለ ሚዋሐዱ የአገሩ አፈር ሕዝብ በላዩ የሚኖርበት ማለት ነው።
  እግዚአብሔር ከምድርዋ ፍሬ ሕይወት እንዲገኝባት በማድረጉ አገር እየጠባች የምታሳድግ ፍቅርዋ በአጥንት በሥጋ
  ገብቶ የማይደመሰስ የሆንች እናት ማለት ነው። ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን በማየት
  ስለ ማደግ አባቶች በሕህወትና በሞት የሥሩበት ደግ ሥራ በአእምሮ ታትሞ ስለ ቀረ በአገር እስካሉ ሲታይ በስድት ሲሆኑ
  ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው። አገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሀብት በመሆኑ ድህነትና ጥቃት
  በመጣ ቁጥር እስከሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድም አያትና ከአባቶች በጥብቅ የተሰጠ ያደራ ገንዘብ ነው። አገር!
  ከታሪክና ምሳሌ (3 ኛ ምጽሐፍ)

  ReplyDelete
 27. Abatochachin yeserullnn melkam neger maseb tegebi new enesuko legna melkamun ke kifuw leytew new yakoyuln silezih yenesun sira zemen teshagari madreg yitebekibnal

  ReplyDelete
 28. ye abatochin tarikna sira zemen teshagari madreg yitebekbnal.

  ReplyDelete
 29. Kibr le semaetat thanks Danii✍✍✍

  ReplyDelete
 30. ክብርና ሞገስ ለወደቁት ታላላቅ የኢትዮጵያ ልጆች ይሁን አሜን !!!
  Reply

  ReplyDelete
 31. it is so sad to hear this, I hope they will read it. I will share this to all my friend and family.

  ReplyDelete
 32. So you have to put what the reaction was!
  Proud to Dr. Kindeya and Yared

  ReplyDelete
 33. Major Tosseli be Ras Alula tor endetegedele eyawekik mn dar dar tlaleh yetekeberk tsehafi? Yezan jegna Ethiopia sm lalemetkes new? Lielam neger mechemer echl neber ezi tsihuf wusr sletetekesu sewoch gin btewew yshalal.Just for this reason only, I will not take your article seriously.

  ReplyDelete