Monday, February 1, 2016

የደጃች ውቤ ልቅሶ

ዐፄ ቴዎድሮስ በበጌምድር ማንም ለሞተ ዘመዱ እንዳያለቅስ የሚል ዐዋጅ ዐውጀው ‹ሰው ሁሉ ዕንባውን ያጠጣ ነበር፡፡› በዚህ መካከል ደጃች ውቤ ሞቱና ለእቴጌ ጥሩ ወርቅ ወደ መቅደላ መርዶ ተላከ፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስም ሕዝቡን ‹ለደጃች ውቤ አልቅሱልኝ› ብለው አዘዙ፡፡ ሰውም ሁሉ ዘመዱ ሲሞት የቀረበት ልቅሶ ያን ጊዜ ወጣለት፡፡ ይህንን ያየች የበጌምድር አልቃሽ
የኔታ ደጅ አዝማች ሁልጊዜ ደግነት
ዛሬ እንኳን ለድኻው ዕንባ አስተረፉለት
ብላ ገጠመች ይባላል፡፡
ያን ቀን በበጌምድር ወጥቶ የማያውቅ ሰው አደባባይ ወጥቶ፣ ተለቅሶ የማያልቅ ልቅሶ ተለቀሰ ይባላል፡፡ ከወጣው በጌምድሬ መካከል ደጃች ውቤን የሚያውቃቸው፣ ለደጃች ውቤም ያለቀሰላቸው ጥቂት ነው አሉ፡፡ አብዛኛው ሰው ያለቀሰው ከዚህ በፊት ለሞተውና ተከልክሎ ሳያለቅስለት ለቀረው ዘመዱ ነበር፡፡ በየማርገጃው የወረደው ሙሾ ደጃች ውቤን ከሚያስታውስ ይልቅ ቴዎድሮስን የሚወቅሰው ይበዛ ነበር አሉ፡፡ በዚህ የተነሣ የደጃች ውቤ ልቅሶ በድምቀቱ ተወዳዳሪ አጥቶ ይኖራል፡፡
ምክንያትና ሰበብ ይለያያሉ፡፡ ምክንያት የአንድ ነገር መነሻ ሥር መሠረቱ፣ ቫይረሱና ጀርሙ፣ መንሥኤውና መብቀያው ነው፡፡ ሰበብ ግን ያ በአንዳች ምክንያት ሲበቅል፣ሲያድግ፣ ሲጎነቁል፣ ሲከካ፣ ሲቦካ የኖረ ጉዳይ የሚገለጥበት ምቹ አጋጣሚ ነው፡፡ ‹እንኳን እናቱ ሞታ እንዲያውም አልቅስ አልቅስ ሲለው› የኖረ ሰው ‹ዋይ› ብሎ የሚወጣለት ቀን፡፡ የበጌምድርን ሰው በነቂስ ወጥቶ እንዲያለቅስ ያደረገው ምክንያት የደጃች ውቤ መሞት አልነበረም፡፡ የቴዎድሮስ አስተዳደራዊ በደል እንጂ፡፡


 ዐፄ ቴዎድሮስ ሞጣ ሄደው ሬሳ በሬሳ አድርገውት ሲመጡ
ሞጣ ቀራንዮ ምነው አይታረስ
በሬሳ ላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረስ
ተብሎ ተለቅሷል፡፡ ንጉሥ ግን አልሰሙም፡፡ ሸዋ ወርደው የሰውን እጅ እየቆረጡ ገደል ሲከቱትም
ዐፄ ቴዎድሮስ እጅግ ተዋረዱ
የሸዋን ሰው ሁሉ እጅ ነሥተው ሄዱ ተባለ፡፡ ንጉሥ ግን አልሰሙም፡፡
ጎጃም አገው ምድር ሄደው የደጃች ጓሉን ሠራዊት ገጥመው ድል ካደረጉ በኋላ የተማረከውን ስምንት ሺ ሠራዊት እንደ ከብት አሳርደው ባደሩ ጊዜ
አንጥረኛው ብዙ ከንጉሡ ቤት
ባል አልቦ አደረጉት ይኼን ሁሉ ሴት
ተብሎ ተለቀሰ፡፡ ንጉሥ ግን አልሰሙም፡፡
ከጣና ምጽርሐ ደሴት ተነሥተው የደንቢያንና የበጌምድርን ሰው በየቤቱ እያስገቡ እሳት ባነደዱት ጊዜ፤ የበጌምድር አልቃሽ
እግዜርና ንጉሥ ተጣልተው ቁመው
ቅዱስ ሚካኤልን ዳኛ አስቀምጠው
እግዜር በግራ ነው ንጉሡ በቀኝ
በል ፍጅና ስጠኝ ሲሉ ሰማሁኝ፤ ብላ አለቀሰች ፡፡ ንጉሥ ግን አልሰሙም፡፡
የጎጃምም አልቃሽ ሜጫን በዘረፉት ጊዜ
ልብሴንም ገፈፈው ለበሰው እርዘኛ
በሬዬንም ነዳው አረደው ነፍጠኛ
እህሌንም ዘረፈው በላው ቀለበኛ
ንጉሥ የቀረዎ ጥቂት አማርኛ
ምነው ሆድ አይዘርፉ አርፌ እንድተኛ፡፡ አለች አሉ፡፡ ንጉሥ ግን አልሰሙም፡፡
ይህ ሁሉ ብሶት በሕዝቡ ውስጥ ታምቆ ይኖር ነበር፡፡ ብሶቱም እንደ ሙዳየ ምጽዋት በየቀኑ እየተጠራቀመ፣ እንደ ፍግ እሳት ውስጡን እየፋመ፣ እያብተከተከው ኖሯል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲህ እንደዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ፣ ጋዜጣ፣ ሬዲዮ፣ ፌስ ቡክና ሚዲያ ከመምጣቱ በፊት የብሶቱ ማውጫ፣ የሐሳቡም መግለጫ የልቅሶ ላይ ሙሾ ነበር፡፡ ቴዎድሮስ ይባስ ብለው የከለከሉት እርሱን ነው፡፡ ማንም ልቅሶ እንዳይቆም፣ ማንም ሙሾ እንዳያወርድ አወጁ፡፡ ‹የሚያስቆጣ ነገር ነግሮ አትቆጣ ይለኛል› እንደሚባለው፡፡
ሰውን ከብሶቱ በላይ ሁለት ነገር ይጎዳዋል፡፡ ብሶት ሰሚና ብሶት ማሰማት ሲከለከል፡፡ ሰው ዘመድ ሲሞትበት እንኳ ምን ዘመዱን ከሞት ባይመልሰው ‹አልቅሼ ይውጣልኝ› ይላል፡፡ በትግርኛ ‹ካስለቀሰኝ ይልቅ አታልቅስ ያለኝ ያመኛል› የሚል አባባል አለ፡፡ ሰው አልተናገረም ማለት የሚናገረው ነገር የለውም ማለት አይደለም፡፡ ሰው አላመጸም ማለት የሚያሳምጽ ነገር አልገጠመውም ማለት አይደለም፡፡ ሰው አልተቃወመም ማለት የሚቃወመው ነገር የለም ማለት አይደለም፡፡ ሰው ዝም ሲል ተስማምቷል ማለት አይደለም፡፡ እንደ ደጃች ውቤ ልቅሶ ሰበብ እየጠበቀ ይሆናል እንጂ፡፡
የደጃች ውቤ ሞት የልቅሶው ሰበብ ነበር እንጂ ምክንያት አልነበረም፡፡
በጣልያን ጊዜ ለጣልያን የገባ ባንዳ አራዳ ወርዶ የአራዳን ሴተኛ አዳሪዎች እንደ ጌቶቹ እንደ ጣልያኖች በጥፊና በካልቾ ሲማታ ያዩት የአራዳ ሴቶች
በጥፊም ተማታ
በካልቾም ተማታ
እንገናኛለን የዘመመ ለታ፡፡
ብለው ገጠሙበት አሉ፡፡ አልቀረም፡፡ የጣልያን ዘመን ዘምሞ፣ ዐርበኞችና እንግሊዝ ወደ አዲስ አበባ ሲገሠግሡ ያ ባንዳ መግቢያ አጣ፡፡ የተመካባቸው ጌቶቹም ዘመኑ ለእነርሱም ዘምሞባቸው ነበርና ሊያስጥሉት አልቻሉም፡፡ ወድቀህ ተነሣ የሚለው አጥቶ እሪ በከንቱ ላይ ተገደለ አሉ፡፡
ሰበቦችን ማስተንፈስ ቀላል ነው፡፡ የበጌምድር ሰውም ደጃች ውቤን አመስግኖ የሆዱን ሁሉ አልቅሶ ወጣለት፡፡ ግን ብሶቱ እንጂ ችግሩ አልወጣለትም፡፡ ደጃች ውቤ የልቅሶው ሰበብ እንጂ ምክንያት አልነበሩምና፡፡ የልቅሶው ምክንያት ሳይፈታ፤ የቴዎድሮስም ጭካኔ ከተስፋ መቁረጥ ጋር እየባሰ መጥቶ የመቅደላው ጦርነት እያዘገመ ደረሰ፡፡ የአራዳ ሴቶች ‹የዘመመ ለታ› እንዳሉት የቴዎድሮስ ዘመን ዘመመ፡፡ ሕዝቡ የእርሳቸውን ርዳታ ሳይሆን እርሳቸው የሕዝብ ርዳታ የሚፈልጉበት ዘመን መጣ፡፡ በጀግንነታቸው ካደነቃቸው፤ የንግሥና ዘር የለህም እየተባሉ እንኳን ካነገሣቸው፣ ዛሬም ድረስ ከማይረሳቸው ሕዝብ ጋር ተጣልተው ብቻቸውን ከጥቂት ባለሟሎቻቸው ጋር መቅደላ ላይ ቀሩ፡፡
ከሕዝቡ ጋር ያጣላቸውን፣ ያላግባባቸውንና ቀስ በቀስም ከሕዝብ ልብ እያወጣ ያመጣቸውን የችግሩን ምክንያት ሳይፈቱት፣ ራሱ ችግሩ ተብትቦ መቅደላ ላይ ጣላቸው፡፡ የንግሥናቸው ዘመን በጨመረ ቁጥር ችግሩን ለመፍታት የነበራቸውን እድል እያጡት፣ ችግሩን ከመፍታትም ይልቅም ችግሩን ሕዝቡ እንዳይናገር ወደማድረግ እየገቡ፤ የሚያስለቅሰውን ምክንያት ከማጥፋት ይልቅ እንዳያለቅስ እያወጁ፤ በትልቅ ጉዳይ ወደ ዙፋን የመጡት ቴዎድሮስ በትንሽ ጉዳይ ተሰናበቱ፡፡
ባለፉት ሰሞናት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ያየናቸው የሕዝብ ተቃውሞዎች መተንተን ያለባቸው ሰበብ ናቸው ወይስ ምክንያት? በሚለው መሆን አለበት፡፡ የማስተር ፕላኑ ጉዳይ ሰበብ ነው ወይስ ምክንያት? ሳይፈቱ ለኖሩ ችግሮች የመገለጫ ሰበብ ሆናቸው ወይስ ጥያቄው ፕላኑ ነው? ‹የአማራና ቅማንት› ጉዳይ ያንን ያህል ያወዛገበውና ደም እስከማፋሰስ የደረሰው የመሬቱ ጥያቄ የችግሩ መገለጫ ሰበብ ነው ወይስ በራሱ ምክንያት ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች የበሽታው ምልክቶች ናቸው ወይስ ራሱ በሽታው ነው፡፡ ያየነው ትኩሳቱን ነው ወይስ ጀርምና ቫይረሱን? ይኼን የመለስን ለት ነው ከመቅደላ የምንተርፈው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ይህን መሰል አጋጣሚዎች የኖረ ችግር፣ ያልተመለሰ ጥያቄ፣ የተበላሸ አሠራር ወይም የተነፈገ ፍትሕ  የመግለጫ አጋጣሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
መልካም አስተዳደር ከስብሰባ ይልቅ ቁርጠኝነት፣ ሥርዓት(ሲስተም)፣ ሳይንሳዊ አካኼድ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድን ይጠይቃል፡፡ አሁን በየመድረኩ የሚነሡት ችግሮቹ አይደሉም፣ የችግሮቹ መገለጫዎች ናቸው፡፡ ነገሩ እንደ ደጃች ውቤ ልቅሶ ላልተለቀሰለት፣ ለማልቀስም ዕድል ለታጣለት ነገር ማልቀሻ ነው የሆነው፡፡ የሆኑ ሰዎችን ከቢሮ ማባረር እንደ ደጃች ውቤ ልቅሶ ማስተንፈሻ እንጂ መፍቻ አይሆንም፡፡ 
ችግሩን ከመሠረቱ አጥንቶ እንዳያዳግም አድርጎ ከመፍታት ይልቅ በስብሰባ ብዛት ለመፍታት መሞከር አሁንም እንደ ደጃች ውቤ ልቅሶ ነው የሚሆነው፡፡ በደጃች ውቤ ልቅሶ የከረመውን ሟች የበላውን እርም እያስታወሰ ብሶቱን ተነፈሰበት እንጂ ሕዝቡ ችግሩን አልፈታበትም፡፡ የሚያይና የሚሰማ ቢኖር ኖሮ ግን የሕዝቡን የምሬት መጠን የደጃች ውቤ ልቅሶ ያሳይ ነበር፡፡ ቴዎድሮስ የደጃች ውቤን ልቅሶ የፈቀዱት ለሕዝቡ ብለው ሳይሆን ለእቴጌይቱ ብለው ነበር፤ ሕዝቡ ለራሱ ብሶት ማስተንፈሻ አደረገው እንጂ፡፡ አሁንም ሰበቡን ትተን ምክንያቱን እንፍታ፡፡ አለማልቀስ አንድም የልቅሶውን አለመፈቀድ፣ አለበለዚያም የልቅሶው መዳፈን እንጂ የሚያስለቅስ ነገር አለመኖርን አያሳይምና፡፡ ተለቀሰ ማለትም የሚያስለቅሰው ነገር ተፈታ ማለት አይደለም፡፡ ሙሾ ወረደ ማለት እንጂ፡፡ ከሰበቡ ወደ ምክንያቱ፡፡    

61 comments:

 1. You are expecting something from wild animal. Our leaders are wild animal, they don’t have any knowledge to do something better. They grown up by killing human being so they don’t care about other people.

  ReplyDelete
 2. Sew alitenagerem malet yeminagerew neger yelem malet ayidelem

  ReplyDelete
 3. Killing,juming,jailing,harassing and so forth are the behavior of dictaters. Now a days the TPLF regime is doing the same thing on our people.

  ReplyDelete
 4. Killing,juming,jailing,harassing and so forth are the behavior of dictaters. Now a days the TPLF regime is doing the same thing on our people.

  ReplyDelete
 5. ተለቀሰ ማለትም የሚያስለቅሰው ነገር ተፈታ ማለት አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 6. አለማልቀስ አንድም የልቅሶውን አለመፈቀድ፣ አለበለዚያም የልቅሶው መዳፈን እንጂ የሚያስለቅስ ነገር አለመኖርን አያሳይምና፡፡ ተለቀሰ ማለትም የሚያስለቅሰው ነገር ተፈታ ማለት አይደለም፡፡ ሙሾ ወረደ ማለት እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 7. ...አሁንም ሰበቡን ትተን ምክንያቱን እንፍታ፡፡ አለማልቀስ አንድም የልቅሶውን አለመፈቀድ፣ አለበለዚያም የልቅሶው መዳፈን እንጂ የሚያስለቅስ ነገር አለመኖርን አያሳይምና፡፡....
  what an insight!!!, thanks Deakon Dani,
  May they get wisdom to contemplate their very wrong deeds.
  ...A...

  ReplyDelete
 8. God bless you Daniyee! you are rock.No word were found to explain my happiness. Thank you Boss.

  ReplyDelete
 9. ጥሩ ምክር ነው ቀጥልበት

  ReplyDelete
 10. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
  Replies
  1. You guy:
   I couldn't judge who is right and who isn't, but my very instinct told me, the way you respond is absolutely non-ethical; and wish you blessed spirit.

   Delete
  2. Hi, Daniel you should remove this comment. I know someone from the current government use this word to separate Amhara and Oromo but it is strong word to read. My son always follow your blog and he asked me why Daniel post this comment?

   Delete
  3. Shame on you Daniel, it is not democracy posting this kind of idea. Anybody can write whatever believes but you have to choose to post on your blog. This kind comment is not teaching us anything. I am very glad my family are not the Anonymos person February 3, 2016.

   Delete
  4. በጣም ታሳዝናለህ እኛ እኮ እንደ አንተ አናስብም መይሳው ኢትዮጵያዊ እንጂ እንደ አንተ ጠባብ አስተሳሰብ ያለው አይደለም እባክህ በአንተ የተነሳ ብዙዎቹ እኛ አንገት ደፍተናል እንደ አንተ ያሉ ጎንደሬዎች ናቸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ያራራቁን ።ዳኒ ጥሩ አድርገሃል የሰውዬውን ኮሜንት እንዳለ በማስቀመጥህ (ፍራንክፈርት)

   Delete
  5. Three words should not be posted here...

   Delete
  6. balege dedeb mehaym edate aynetun tede adenkewalehu yalkew erasu biyagegnh angethne korto neber yemitlh kalgeah bedenb degmeh abb dedebit!!!!!!!!!

   Delete
  7. faras ante dedeb kalgebah lemn degmeh atanebm

   Delete
  8. Dani please remove this. I love your democracy but it is too much for our culture. As you know that some children read your blog so what do you think about this comment. Please remove it. thank you.

   Delete
  9. ኧረ.... ወንድም ጥሩ አይደለም እንዴት እንዲህ አይነት አስተያየት በሚዲያ ይጻፋል? እኔም እንደ ጎንደሬነቴ የተወሰነ ነገር ተሰምቶኝ ነበር ነገር ግን ታሪክ ታሪክ ነው። በጎ በጎውን ብቻ ስንሰማ ስለኖርን ድክመት መስማት አይዋጥልንም። የዚህን ጽሁፍ ዋናውን ጭብጥ ማስተዋሉ የተሻለ ይመስለኛል ። በተረፈ ወዳጄ በተለይ ጸያፍ የሆነ ስድብና ዘለፋ የኛ መገለጫ አይደለምና ለወደፊቱም ቢሆን ከዚህ አይነት አጻጻፍ በመቆጠብ ትልቅ ሰው ለመሆን ሞክር።

   Delete
  10. Yalehin hasab be tiru amarigna mastelalef tichilaleh baltegera afih yechinkilatihin badonet atagalit wendime

   Delete
  11. እግዚአብሔር ይገስፅህ እንጅ ሌላ ምን ይባላል። ስልጣኑ ቢኖረኝ ኖሮ ይህን ተሳዳቢ አንደበትህን እስከ እለት ምጻት ድረስ ዲዳ እንዲሆን አድረገው ነበር።

   Delete
  12. አፍህን ስትከፍት ጭንቅላትህ ባዶ መሆኑን አሳየህ

   Delete
 11. ወንድም ዳኒ የሰበቡንና ምክኒያቱን አለመረዳት አሁን እየታየ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግርና የፍትህ እጦትን አስከትሏል፡፡ የመፍትሄው ባለቤቶች ይህንን ጽሁፍ ስለማይረዱት በመጽሃፍ መለክ ከነ ቃላት መፍቻው ጋር አሳትመህ ለገጸ በረከት አብቃው

  ReplyDelete
 12. Just like Jemokenyata & Achinoacebe of the Nigerian writer....The amazing analysis. Thanks Dn Dani

  ReplyDelete
 13. ይህ አጀንዳ ጥልቅ ነው፤ከብሔረተኝነት ጋርም ተያይዞ ሥልጣን ላይ ያለው ብሔር የተሰጠውን ጊዜ ተጠቅሞ የሁሉንም ብሔርና ዜጎች መብት ከማክበር ይልቅ የመረጠው የአፈናውን መንገድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ወደፊት ለሚነሳው የትግራይ ትውልድ ዕዳ የሚተው አካሄድ ነው፡፡ ለብዙ ዘመናት ሥልጣን ላይ የነበሩት የአማራው ነገሥታት ሠሩ በተባለው ስህተት ዛሬ የአማራ ብሔር የሆነ ሁሉ እንዲጠላና ከሌሎች ክልሎች እንዲፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡ በተመሳሳይ /እኔ የምፈራው/ እነዚህ ጥቂት የትግራይ ባለሥልጣናት በሌሎች ብሔሮች ላይ እያደረሱ ያለው በደል ተጠራቅሞ ለመላው የትግራይ ህዝብ እንዳይደርስ ነው፤ይህን ለማስቆም የራሳቸው ሰዎች ነቅተው መንቀሳቀስና ገዢውን መደብ ተዓቀብ ሊሉት ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 14. What about the Ethiopian Orthodox Church? Abune Mathias(Abune Abay Tsegaye) is converted to "TEHADSO?" I have no trust on him from the beginning. His words of speech are like his TPLF brothers.Really, Really, Really! Is he representative of EOC? I expecting two assumptions: 1/His mind may not be OK(mental sickness and retardation) 2/ He might be the activists of " TEHADSO menafik." Trust me, you will see his future doing.He is the other hand of Abay Tsegaye too.He is not religious leader, rather he is the missionary of TPLF bandits.

  ReplyDelete
 15. አለማልቀስ አንድም የልቅሶውን አለመፈቀድ፣ አለበለዚያም የልቅሶው መዳፈን እንጂ የሚያስለቅስ ነገር አለመኖርን አያሳይምና፡፡ ተለቀሰ ማለትም የሚያስለቅሰው ነገር ተፈታ ማለት አይደለም፡፡ ሙሾ ወረደ ማለት እንጂ፡፡ ከሰበቡ ወደ ምክንያቱ፡፡ አለማልቀስ አንድም የልቅሶውን አለመፈቀድ፣ አለበለዚያም የልቅሶው መዳፈን እንጂ የሚያስለቅስ ነገር አለመኖርን አያሳይምና፡፡ ተለቀሰ ማለትም የሚያስለቅሰው ነገር ተፈታ ማለት አይደለም፡፡ ሙሾ ወረደ ማለት እንጂ፡፡ ከሰበቡ ወደ ምክንያቱ፡፡

  ReplyDelete
 16. Dani we have been looking different opposition from universities&from different personal opinions.However,most political personnel's promoted to d/t levels do not have ears to listen those who promoted them.Lets pray!!!

  ReplyDelete
 17. Dani you are trying to raise a big issues&prediction too.However,our political leaders have no ears to listen those who promoted them.lets pray!!!

  ReplyDelete
 18. God bless you Dani. Please let's do what we can do for better Ethiopia.
  God Bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 19. From this video( https://www.youtube.com/watch?v=gTh-ePtC2Lc):
  A story about Journalist Reyot Alemu, from the very instance she was caught in the name of "terrorist", until she got freed, I leanrt what the current regime is working and for what it is standing.

  And thanks Deakon Daniel Kibret for composing and posting this thorough article, which exactly discloses the current situation, in other-way round.


  You could watch Journalist Reyot Alemus's jail story from the following link:

  https://www.youtube.com/watch?v=gTh-ePtC2Lc

  ReplyDelete
 20. አንተንም ደግሞ አሸባሪ እንዳይሉህ። የሚፈልጉት እነርሱ የሚሉትን ብቻ እንድናደርግ እና እንድናዳምጥ ስለሆነ።

  ReplyDelete
 21. ሰላም ዳኒ እይታህ ሁሌም የሚደነቅ ነው ይህ አይነቱ ውጥረት ከኢትዮጵያ ውስጥ ይልቅ ከኢትዮጵያ ውጪ ባለነው ሰዎች ላይ የከፋ ይሆናል እየሆነም ነው አሁንስ ዳኒ በጣም ፈራሁ እጅግ በጣም ፈጣሪ ብቻ ይታደገን ።(እስኩ ድግሙ) ከጀርመን

  ReplyDelete
 22. Dikon Daniel tarik yaskemetewn new yetesafew. lemen kesen megaber wochi yohene neger tenegareleh. yehe manenetehn new yemeglesew.

  ReplyDelete
 23. ንባቡ እንቆቅልሽ የሆነበት እንደዚህ ለስድብ ይሮጣል የገባው ደግሞ መፍትሄውን እግዚአብሄር እስኪያመጣው ድረስ በፀሎት ይታጋል ወዳጄ

  ReplyDelete
 24. Dear Dn Daniel,

  some of the comments like the one posted on Feb 3 at 3:00 does not qualify to be posted. Please check the comments first before letting them go. I understand it takes time to check every comment thoroughly. But something should be done!

  ReplyDelete
 25. አሁንም ሰበቡን ትተን ምክንያቱን እንፍታ፡፡ አለማልቀስ አንድም የልቅሶውን አለመፈቀድ፣ አለበለዚያም የልቅሶው መዳፈን እንጂ የሚያስለቅስ ነገር አለመኖርን አያሳይምና፡፡ ተለቀሰ ማለትም የሚያስለቅሰው ነገር ተፈታ ማለት አይደለም፡፡ ሙሾ ወረደ ማለት እንጂ፡፡ ከሰበቡ ወደ ምክንያቱ፡፡ ተባረክ ወንድሜ፡፡

  ReplyDelete
 26. You write the rumours not facts about Atse Teodros...this is dividing us in to pieces.
  You mixed honey with poison & let us to eat it.The good news is majority of Ethiopians know who you are & with whom you are working with.
  SORRY! !!

  ReplyDelete
 27. መልካም አስተዳደር ከስብሰባ ይልቅ ቁርጠኝነት፣ ሥርዓት(ሲስተም)፣ ሳይንሳዊ አካኼድ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድን ይጠይቃል፡፡ አሁን በየመድረኩ የሚነሡት ችግሮቹ አይደሉም፣ የችግሮቹ መገለጫዎች ናቸው፡፡ ነገሩ እንደ ደጃች ውቤ ልቅሶ ላልተለቀሰለት፣ ለማልቀስም ዕድል ለታጣለት ነገር ማልቀሻ ነው የሆነው፡፡ የሆኑ ሰዎችን ከቢሮ ማባረር እንደ ደጃች ውቤ ልቅሶ ማስተንፈሻ እንጂ መፍቻ አይሆንም፡፡

  ReplyDelete
 28. Teaching new tricks to an old dog...
  Is there a word for compromise in amarigna or tigrigna? If there is, how come i never heard it?
  ችግራችን በጣም ሥር ሰደድ እና ውስብስብ ሆኗል። መፍትሔ ከመሻት ይልቅ መደብደብና መግደል ቀላሉ ዘዴ ተብሎ ታስቦ ይሆን? ከተንኮል ከቂም ከክፋትና ከክህደት ይልቅ ቅንነት ይቅርታ እና እምነት ቢኖሩ ኖሮ መፍትሔ ከላይ ከባለቤቱ ባገኘን ነበር! ሰው የዘራውን ያጭዳል።

  ReplyDelete
 29. መልካም አስተዳደር ከስብሰባ ይልቅ ቁርጠኝነት፣ ሥርዓት(ሲስተም)፣ ሳይንሳዊ አካኼድ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድን ይጠይቃል፡፡አለማልቀስ አንድም የልቅሶውን አለመፈቀድ፣ አለበለዚያም የልቅሶው መዳፈን እንጂ የሚያስለቅስ ነገር አለመኖርን አያሳይም፡፡

  ReplyDelete
 30. You said it all Thanks you. የሚሰማ ጅሮ ካለ

  ReplyDelete
 31. የቴዎድሮስ የጥፋት መንስኤ ከዚህ ዘመን የጥፋት መንስኤ ጋር ይነጻጸራል?
  የማይገናኝ ነገር አገናኙ አቶ ዳንኤል፡፡ የቴዎድሮስ ዓላማ ካልገባዎ እንደገና ያንብቡ፡፡ ምናልባት ንባብ ሲበዛ ተምታቶብዎ እንዳይሆን፡፡ ረጋ ብሎ በጽሞና ማሰብም ከግብስብስ ንባብ በብዙ ሊበልጥ ይችላል፡፡ ያው የታሰበ አይደል የሚጻፈው? በታየና በተሰማው መሰረት፡፡ የቴዎድሮስ የአንድነት እሴት በእንዲህ አይነት ውሃ የማይቋጥሩ ጽሁፎች መቼም መቼም አይጠፋም፡፡ ቴዎድሮስ ሰው አይደለም፤አያጠፋም ልንል አንችልም፡፡ የጥፋቱ ሁሉ መነሻ ግን እንዳሁን ሆድ አምላኩ መሪዎች፣ አርቲስቶች፣ ደራሲዎች፣ ጦማሪዎች፣ አይነት አይደለም፡፡ የእርሱ ጥፋት መነሻ “አንድ እንሁን”፤ “ብዙ ከመዘመር በንጹህ ልቡና ጥቂት ዘምረን ብዙ እንስራ”፤ “ሌብነት ይቅር”፤ ”ህግ ይምራን”፤ወዘተ የሚል ነበር፡፡ እሱ በነበረበት በዛ ትምህርት የሚባል ነገር ብርቅ በነበረበት ዘመን ግን ይህ ዓላማ ተፈጻሚነቱ ኢምንት የሆነ ሰፊ ዓላማ ነበር፤ በከፊል ግን ተሳክቷል፡፡ በመንፈስም በአካልም ጠንካራ በሆነው መንፈሱ ሞቶ ተሟሙቶ ወደስልጣን በመውጣት ኢትዮጵያ የምትባልን ሀገር ከጠፋች ከ200 ዓመት በኋላ እንደገና አግኝቶልናል፤ ክብር ለንጉስ ቴዎድሮስ ለክቡር ነፍሱ ይድረሰው፡፡ (ቴዎድሮስን ህዝቡ እንዳነገሰው ጠቅሰሃል፤ ቴዎድሮስን ያነገሰው ግን ቴዎድሮስ ነው እንጅ ህዝቡ አይደለም፤ ምርጫ እኮ አልነበረም፣ በጠንካራ እምነት (ኃይማኖት) በደደረ ብቃቱ ነው የነገሰው፡፡ እንደ እስራኤሉ ቅዱስ ንጉስ ዳዊት ልትለው ትችላለህ፤ ብታምንም ባታምንም፡፡ ዳዊት የበግ እረኛ ነበረ፣ ቴዎድሮስ ምናልባት የፍየል እረኛ ነበር፤ ፈጣሪ ግን እስከ ንጉስነት አደረሳቸው፤ ትንሽነታቸውን ሳይሆን ትልቅ ልባቸውን አይቶ፤ የጠፋችውን ኢትዮጵያን ፈልጎ አግኝቶ ያቋቋማት እና የመራት ቴዎድሮስ ያልጠፋችውን እስራኤልን ከሳውል ቀጥሎ ከመራው ንጉስ ዳዊት በምን ያንሳል? ይበልጣል ብላችሁ ምን ታመጣላችሁ፤ ይበልጣል፡፡) ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቴዎድሮስ ቀጥሎ ንጉስ ዮሃንስ የቴዎድሮስን ዓላማ ቀጠለው፤ ለንጉስ የሃንስም እንዲሁ ክብር ይድረሰው፡፡ ከሱ ቀጥሎ የቴዎድሮስ የመንፈስ ልጁ የሆነው ምኒልክ ኢትዮጵያን ከአባቱ በበለጠ መልኩ አስፋፍቶ በአንድነቷ አጠንክሮ፣ በትምህርትም በስልጣኔም ለማራመድ ደክሟል፤ ክብር ለንጉስ ምኒልክ፡፡ ይባስ ብሎ ንጉስ ኃይለ ሥላሴ ከሀገሩ አልፎ ከታላቅ ክብርና ግርማ ጋር አፍሪካን አንድ አደረገ፤ አላደረገምን? ቴዎድሮስ ይችን ኢትዮጵያን ከጠፋችበት ፈልጎ ባያገኛት ኖሮ፣ ዮሀንስና ምኒልክ የተገኘችውን ኢትዮጵያን እንዳትጠፋ ባይፋለሙ ኖሮ፣ ይሄኔ እያንዳንዳችን በየጎጃማችን፣ በየጎንደራችን፣ በየወሎአችን፣ በየትግራያችን በየሐረር ግንባችን፣ በየጅማችን፣ በየሲዳማችን እንኳን ተወሽቀን ከነማንነታችን እንቆይ ይመስልሃል? በፍጹም፤ በማንም ባእድ ተወረን ባገራችን ባእድ ሆነን ማንነታችን ተገፎ ክብረ ቢስ ሆነን እንቀር ነበር፡፡ ክብር ከ”ነጥፋታቸውም” ቢሆን ማንነታችንን ላቆዩልን ታላላቅ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፡፡
  የቴዎድሮስ የጥፋት መንስኤ ከዚህ ዘመን የጥፋት መንስኤ ጋር ይነጻጸራል? ለማነጻጸር ማሰብ በራሱ ያሳፍራል፡፡ በትምህርት እና በመረጃ በእጅጉ እየበሰለ ያለው የዚህ ዘመን ሰው “ከልዩነታችን ይልቅ ለአንድነታችን አጽንኦት እንስጥ” ሲል፣ ከትምህርት ብቃት ይልቅ በፖለቲካ ጥገኝነት ወደላይ የተንጠላጠሉት አብዛኛዎቹ መሪዎቹ ግን “የለም ከአንድነታችን ይልቅ ለልዩነታችን ነው አጽንኦት መስጠት ነው ያለብን” ይላሉ፡፡ በዚህ መሃል የሚፈጠረውን የተቃውሞና የግጭት አይነት አስቡት፡፡ የቴዎድሮስ ዘመን ግን የዚህ ግልባጭ ነው፡፡ እንዲያውም የዋህ ከሆነ መልካም ባህሉ በስተቀር የዚያን ጊዜው ህዝብ ሀገር ክብር አንድነት ወዘተ ስለሚባሉ ትላልቅ ጽንሰ ሃሳቦች የሚያስብበት ጊዜም እድልም አልነበረውም፡፡ የዚያን ጊዜ የነበረው ህዝብ የሚለው ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወዘተ ነው፡፡ በዚህ መሃል ሀገር፣ ክብር፣ ትምህርት የሚል መሪ ምን ሊገጥመው እንደሚችል አስቡት፣ እንደውም አታስቡት፤ ይቅር፡፡ የቴዎድሮስ የጥፋት መንስኤ ከዚህ ዘመን የጥፋት መንስኤ ጋር ይነጻጸራል? ቴዎድሮስን የሚቃዎም ኢትዮጵያን የሚቃዎም ነው፡፡ ኢትዮጵያን የሚቃዎም ኃይማኖት የሌለው ነው፤ እንዴት? በእስልምናም በክርስትናም (በኦርቶዶክስ፣ ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ፣) ቅዱሳን መጻህፍት ስሟ በበጎ የተነሳላት ስለሆነ፡፡
  የቴዎድሮስ ጥፋት በስልጣን ጥም ላይ የተመሰረተ አልነበረም፡፡ እንደዛ ቢሆን በራሱም ላይ ጥፋት ለመፈጸም የሚያስችል የሞራል ብቃት አይኖረውም ነበር፡፡ ቴዎድሮስ በዘመኑ የንጉስ ህግ መሰረት ጥፋተኞች ላይ መፈጸም የነበረበትን ቅጣት በቆራጥነት ፈጽሟል፡፡ ንጹሃን የተቀጭዎች ቤተ ዘመድ በበኩላቸው በቅጣቱ ምክንያት ማዘንና የፈለጋቸውን ማለታቸውም ተገቢ ነው፡፡ ቴዎድሮስ እንደዚህ ዘመን ሰው ሆዳም ቢሆን ኖሮ ከእንግሊዞች ጋር ተባብሮ አገሩን መሸጥ ይችል ነበር፡፡ እሱ ግን እንደዛ አላደረገም፡፡ ክርስቶስን እንጅ ሆዱን ስለማያመልክ በሌሎች ላይ የጨከነች እጁን በራሱም ላይ አስጨከናት፡፡ ክብር ለማይዎድ ትውልድ፣ በህይዎት ከመኖር የሚበልጥ በመሞት የሚገኝ ልዕልና እንዳለ መስረዳት እጅግ ከባድ ነው፡፡ ታሪክ እንደፈለጉ “በሚታይበት” በዚህ ዘመን አንተም በበኩልህ የደጃች ውቤን የልቅሶ መንስኤ ከዚህ ዘመን የተቃውሞ መንስኤ ጋር አመሳስለህ ስላየኸው ገርሞኛል፡፡ ወደ ዝርዝሩ መግባት ሳያስፈልግ ይህ እይታ የተንሸዋረረ እይታ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡ በሌላ የተስተካከለ እይታ እንደምንገናኝ ግን ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለንም፤ ቅንጣት፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear sir,
   What I see in your comment is that what daniel compares is right. You are saying that what happened in Meysaw is the reciprocal of what is happening today. In my opinion the best way to compare will happen when the the points happened on a reciprocal way.
   If your argument comes, why daniel did not explain the reciprocal event... you will be judged. The team of the piece in my perspective is not comparing, instead commenting what is going on based on history.

   Delete
  2. Betam betam yemiasdesit mels setachihulegn bezihm ameseginachihoalehu bewunetu D.Danel bezi melk endet endayew enem germognal. Lemangnawum sewu nehina yemeselehin yemetsaf mebt aleh gin tariken letarik temeramariwoch bintewow woy demo be ewuket bintsefew. Muhranum bithonu zm atbelum be ewunet le Ethiopia tarik mitkorekoru kehone giziew ahun yimeslegnal 1 Hunachihu mitkomubet giziew ahun new. Egziabher Ethiopian yibark.

   Delete
  3. Ygermal! Huletum tikikil nachew. D/n, Daniel yalewm, Comment Adragiw yalew tikikil new yehone yetederege. Gin yayubet menetsir new yeteleyayew. D/n Daniel ye Atse Tewodros wondinet, ager wodadinet, hymanotegninet teftot aydelem, lemalet yefelegew lehzb joro alset ale new. Slezih minale hulachinm bego begown binasb? D/n yetsafew ahun slalew joro daba libes new. comment adragiw degmo Atse Tewodrosn yamogesku meslot ahun yalewun wuneta madafen new, Atse Tewodros 1 yaderguatin ager stibeten zim blo mayetn mefked ymeslegnal enji yetenegna sew comment aymelegnm. slezih endiaw endet blen, bemin kuankua new lingbaba yemnchilew? Bicha gin ye Ethiopia amlak kin libona ysten.

   Delete
  4. @Desalegn W.February 8, 2016 at 9:45 AM
   ነገሮችን በአንድ አቅጣጫ ብቻ ማየት እንዲህ ካለ ስህተት ላይ ይጥላል፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቢሆን አሁን አንተ ያልከውን ታሪክ ያውቃል። አጼ ቴዎድሮስንም ያከብራቸዋል፤ ይወዳቸዋልም። ከላይ እንደገለጽከው ደግሞ እርሳቸው መልአክ አይደሉም፤ አይሳሳቱም አይባልም፤ ስለዚህ ይህ ስህተት ምንድን ነው? ብለን ከስህተቱ መማማር አለብን እንጂ በጭፍን አካሄድ እና በስሜታዊነት የሚገኝ አንድም ጥቅም ወይም ትምህርት የለም። ጭፍን ወዳጅነት ከመጣ ግን፣ ለምሳሌ ይህ መንግሥትም ለልማት እየታገለ ነው ብለህ ልትነሳ ትችላለህ፣ ስህተቱ ሊነቀፍበት አይገባም ብትል ግን ግልጽ የሆነ ጭፍንነት ውስጥ ስላለህ ራስህን ብትመለከት እና ብታስተካክል ጥሩ ነው፤ እላለሁ።
   @Mulugeta MekonnenFebruary 9, 2016 at 6:24 PM
   ታሪክን ጨፍልቀህ እያየህ አጼ ቴዎድሮስ ምንም ክፉ ነገር እንዳልፈጸሙ አድርገህ፤ የራስህን የታሪክ እውቀት መመልከት ሲገባህ አንት ልትገምተው በማትችለው ሁኔታ ታሪክን ያጠናን ሰው እንዲህ ማቃለልህ ችግር እንዳለብህ ያሳያል፤ ስለዚህ ታሪክን መለስ ብሎ ማንበብ እና ብዙ መጻሕፍትን መመርመር እንዳለብህ ያሳያል።

   Delete
 32. Bemigeba tazibehal D. Dani...long life

  ReplyDelete
 33. Dani you wrote the right one!!!.....Our historians have been written only the positive side of our kings like Tewodros the second.I read about Tewodros who let the people be number one by avoiding their two hands.His cruelty was real.Do Some readers PLease do not hesitate from truth!!!

  ReplyDelete
 34. ዐፄ ቴዎድሮስ ደብረ ታቦር ላይ ቆመው እያሉ አንድ ገበሬ ሰክሮ በአጠገባቸው ያልፋል፡፡ ያም ገበሬ ወደ ንጉሡ ጠጋ ይልና «በቅሎው ይሸጣል» ይላቸዋል፡፡ የዐፄ ቴዎድሮስ ጋሻ ጃግሬዎች እነ ገብርዬ ሰይፍ መዝዘው «እንዴት ንጉሡን በድፍረት ይናገራል፤ እንበለው» አሏቸው፡፡ ንጉሡም ትእግሥት አድርገው «ተውት፣ ይሂድ፡፡ ነገር ግን የሚገባበትን ቤት ተከታትላችሁ ተመልከቱት አሏቸውና ተከታትለው ተመለከቱት፡፡

  በማግሥቱ ያንን ሰው ንጉሡ አስጠሩት፡፡ እየፈራ እየተንቀጠቀጠ መጣ፡፡ «ትናንትና እነዚህ ሁሉ ሰዎች ባሉበት በቅሎዬን ለመግዛት ጠይቀህ ነበርና እንድንስማማ ነው ያስጠራሁህ» አሉት፡፡ ሰውዬው ግን ማመን አልቻለም፡፡ የንጉሥ በቅሎ፣ ያውም ታጠቅ የተባለውን የዐፄ ቴዎድሮስን በቅሎ ለመግዛት የምጠይቅ እኔ ማነኝ ብሎ ደነገጠ፡፡ «የለም ንጉሥ ሆይ እኔ ብቻዬን ሆኜ እንዲህ ያለውን ሃሳብ አላስበውም፡፡ ይህንን ጥያቄ ያቀረብነው ከጓደኞቼ ጋር አብረን ሆነን ነውና ከእነርሱ ጋር ተማክሬ መልስ ልስጥ» ብሎ ጠየቀ፡፡

  ንጉሡም «ትናንትና ስናይህ ብቻህን ነበርክ፡፡ ሌላ ጓደኛ አልነበረህም፡፡ ከየት አምጥተህ ነው የምትማከረው?» ሲሉ ገርሟቸው ጠየቁት፡፡ ያም ገበሬ «ንጉሥ ሆይ አላዩዋቸውም እንጂ አብረውኝ እነ ብቅል፣ ጌሾ፣ እነ ደረቆት፣ እነ ጠጅ፣ እነ ጠላ፣ እነ አረቄ ነበሩ፡፡ እነርሱ በሌሉበት ይህንን ነገር ብቻዬን አልናገረውም» ብሎ አሳቃቸው፡፡ ንጉሡም በአነጋገሩ ተገርመው ምሕረት አደረጉለት ይባላል፡፡ ለዚህ ነው ለምጣዱ ሲባል አይጧን ማሳለፍ የሚጠቅመው፡፡ ያንን ድፍረት የደፈረው ገበሬው ብቻውን አይደለም፡፡ እነ አረቄ፣ ጠላ፣እና እነ ጠጅ ናቸው፡፡ ስለዚህም አይጧን ከምጣዱ ለይቶ መምታቱ መልካም ነው፡፡ was written by him. tirum ye sera ale mexifom yesera ale. be gizewu hulum mexifom tiru sertowal....so ibakachu be tarik mewokakes titen wodefit inasib. please please le hagerachign andi honen be andinet inunuri....demo andi neger bewketu indalewu, sil lelawu abati sinawora sil rasachin abat masebi alebin. demo sina wor tarikin awukeni anbiben mehon alebet zim bilen andi page anbiben amet mawurat ayidelem, plus tirum hone mexifo yemiyawku sewoch siyaworu madamex ye astewyi bahari nw...please inasib

  ReplyDelete
 35. እንደ እኔ የዲ/ን ዳኒኤልን ሃሳብና ኣፃፃፍ ስልቱን ካለመረዳት ካልሆነ በስተቀር ኣፄ ቴዎድሮስን ማሳነስ ፈልጎ ኣይመስለኝም። ክብራቸውን ለቅድስቲቱ ሃገር ኣንድነት ያደረጉትን ኣስተዋፅኦ በሚገባ ያውቃል...ይፅፋልም። የኣፄ ቴዎድሮስ …ክፍተት ሁሉ ኢትዮጱያዊ ያውቃል ... ግን ጥንካሬኣቸው ይበልጣል... ዲ/ን ዳኒኤልም ይህንን ያውቃል.. ተረድቶኣልም።
  በኦሮምያ፣በጎጃም፣በበጌምድር ያደረጉትን እያለ ያሰቀመጠው በኣሁኑ ግዜ በየክልሉ ኣንዳንድ ኣካባቢዎች ያሉትን ጥያቄዎችንና ችግሮች መነሻ እንድናጠናና መረዳት እንድንችል በማሰብ እንጂ የኣፄ ቴድሮስን ክፍተት ለማጉላት ኣይደለም።
  ከዛም በኣንዴ መግፋት የሙሁር ኣስተሳሰብ ኣይደለም።...ዲ/ን ዳኒኤል በእንደዚህ ዓይነት በኣንድ ኣቅጣጫ የሚያዩ ወገኖች የሚሰማው ቢሆን ንሮ ኣጥማቂዎች ነን ባዮችን ኣስመልክቶ ሲፅፍ … ጋሻ ኣጃግሬዎቻቸውንና ራሳቸውን ሲንጫጩ በፈራ ኣልያም በጎመጎመ ነበር። ግን እውነት ስለያዘ ቀጠለበት።
  ኣሁን እናስተውል፤ የፀሃፊው/ዳኒ/ዓላማው ምንድር ነው?...ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲነሳ ገዢው መንግስትና ሹሟሙንቶቹ ምንድር ነው ምንጩ ብለው ማደመጥ ማየት እንደ ኣለባቸው፤ ህዝቡም ችምር ሃሳብ እንዲሰጥ ማሳሰብነው። ይህ ፅሁፍ ኣፄ ቴዎድሮስን መቃወም ኣይደለም! ጎንደሬ ነኝ፣ ጎጃሜ ነኝ፣ ከፋኝ የሚያስብል ኣይደለም። ኣፄ ቴዎድሮስ ለኢትዮጰያዊ ሁሉ በተለይ በዛ ዘመን ኣንድነቱ ለተቀበለ እኩል ናቸው። ልብ ላለው ዛኔ ላልተቀበለም ወገን ሁሉ ኣንድናቸው….ባንዳና….ነጭ ገዢ ኣይወዱም፣መለያየትን ኣይወዱም ነበርና ነው።
  .. ደግሞም እንዲያውም ዳኒን ትክክለኛ ታሪክ ፀሃፊ እንበለው እንጂ ።የምንወደውን ሰው ለምሳሌ ኣፄ ቴዎድሮስን ማለቴ ነው ክፍተት በፍቅር፣በቁጭት ወይኔ ይህችን ነገር ክፍተት ነበረችው ምነው ባስተካከላትና የቴድሮስን ኣካሄድና ኣመራር በተስተካከለና ኣንድ ግማሽ ክፍለዘመን መርቶ፤ የሚገባውን ሌላ ንጉስ/መሪ/ሰው በነፍጥ ሳይሆን በማሰብ በመተሳሰብ በቶሾመና ሶፓስቶባልና ዓይነት ብዙ ስራዎችን በተፈፀሙ፤ በቀጠለ ቴድሮስ ሆይ ለ200 ሞቶና ከዚያ በላይ ዓመታት ተበታትና ኣጥተናት የነበረችውን ኣገራችንን ኣዳንህልን፤ ግን ደግሞ እዚህ ላይ ክፍተት ነበረህ፤ ምነው የቅኔንና የኣቡሻህር የሃዲሳቱንና የቁርዓኑን እንዲሁም ብለሆች በለኣገሮች/ገበሬዎችህን/ ሊቃውንትንም ባማከርክ” ማለት ኣይገባም ወይ ….ኣንጥበብ።
  የዳኒኤል ሃሳብ እንደዛ ነው. ምነው ይህ ክፍተትም ባየሀው ነው?.. የኣጼ ቴድሮስን ጠንካራ ያጠናሀውን ኣጥነተህም ፃፍልን ብንለው----- እኛ ታች ሁነን ከምንምቧረቀው በበለጠ ኣስፍቶ ኣምልቶ ይመሰክራል ። የኣሁኑ ግን ስንቱን ስራ የሰሩትን ኣፄ ቴዎድሮስን እንዴት ህዝቡን ብዙ ውለታ እያዋሉለት እየሰሩለት እየሰራላቸው ትንሹ ነገር ላይ ኣል ነቁም? እንዴት የብሶቱን መግለጫ የነበረውን ልቅሶውንና የልቅሶውን ግጥም/ሙሾ ውን/ ኣላጣጣሙትም ኣልሰሙትም፤ የኣሁኑ መሪዎችስ ለምንድር ከታሪክ የማይማሩት ነው።
  ዲ/ን ዳንኤል ኣፄ ቴዎድሮስ ላይ ሃሳብ የመስጠት መብትም ኣለው፤ ግን ዓላማው ንጉሱን መተቸት ኣይደለም ብያለሁ። የችግር መንስኤን በሚገባ መሪዎቻችንና እኛም ህዝቦቻቸው እንዲያጠኑ/እንድናጠናም ጭምር ታሪክ ጠቅሶ ኣስረዳን እንጂ። በድጋሚ ከታሪክ እንማር ነው መልእክቱ።
  ደግሞ እዚህ ብሎግ ላይ የምንሳተፍ ሰዎች ቢያንስ ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከ10 እንበለው የተማርን ነን። ታድያ ለምንድር ነው ቶሎ ምንጮኸው? ምን ማለትህ ነው ኣብራራው? ብለን ጠይቀን በበለጠ መማርና መመራመር በኣሁኑ መንግስት ላይም ሃሳብ መስጠት ኣይሻለንም ወይ? እኔ ኣሁን ላይ በኮምት ሲጪዎች ላይ ያየኋቸው ሁሉን ኮሜንቱንም የዲ/ንንም ኣንብቤኣለሁ ኣስቤበተም ኣለሁ…… የተወሰኑ ጥቂት ግን ጠማማ ኣስተሳሰቦች ያለን ወንድሞችና እህቶች ግን ዲ/ን ዳኒኤልን በሃይማኖት ወይም በብሔር ተጣልተነው ኣልያም በፖለቲካ ኣመለካከት ስላልደገፈን ካልሆነ በስተቀር በኣሁኑ ፅሁፉ ብቻም ኣይመስለኝም።
  የዲ/ን ዳኒኤል ኣስተሳሰብ ሁሉን ኢትዮጰያዊና የኢትዮጰ ወዳጅ ያማከለ ነው፤ ክርስትያኑ ሲያሞግስ እስላሙ ኣልጣለም፣ ሲሸልምም ኣብሮ ሸለመ እንጂ፤ሲመክርም እምነትና ጎሳ ዘርን ቋንቋ ኣይለይም። በተራጋጋ ለሚያስብና ለሚመራመር እንደፃፈው ነገሮችን ደጋግሞ እንደ የቀንድ ከብቶች የሚያመነዥክ/ኣላምጦ ለሚውጥ/ ሰው ዳ/ን ዳኒኤልን ገና ከርእስ ኣመራረጡ እና ከመግብያ ሀሳቡ ላይ በሁለት ኣንቀፆችን ይረዳዋል።
  ፅሁፎቹንና ስብከቶቹን ትምህርቶቹና ዋናውም መጣጥፎቹ ብሎጎቹ ላይ ሳነብና ስሰማ የማያዳላ ብሄርና ቋንቋ የማይለይ ኣስተሳሰብ ኣለው ። ኣሁንም ካልደጋገምኩት በስተቀር “
  ኣፄ ቴዎድሮስን ኣላሳነሰም፤ባህልንም ኣልነካም፤ዓላማውም ግልፅ ነው ምነው መንስኤዎችንና ምክንያቶችን ብንረዳ ብንለይ ነው፤ ከዛ እንማር ነው ያለው ። ቻው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
  ………………………………………………. ዲያቆን ዳኒኤል ክብረት በርታልን!……ከጓደኞችህ……..ወንድም እህቶችህ ከመምህራንም ጭምር መመካከር ኣትተው……. ስራ ዎችህ ግን ደስ ይላሉ!

  ReplyDelete
 36. Your comment will be visible after approval. Good!

  ReplyDelete
 37. yehinen taric sitetsef nigusu gizatun lemasfafat yemigebawen ermega mewsed endemigebaw lemen zenegahe? ante yeweyane buchla ader bay hodam mehon alebe mekenyatum lib kalehe esti sle gimela chefchafiw weyane tseafe?

  ReplyDelete