Monday, January 4, 2016

እውነት ስትሰቀል


(የዴንቨር መድኃኔዓለም ካህናትና ምእመናንን ባሰብኩ ጊዜ ይህንን ጻፍኩ)

ሰሞኑን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዴንቨር ከተማ ተገኝተው የዴንቨር መድኃኔዓለምን በተመለከተ ‹ከእናት ቤተ ክርስቲያን ወጥቷል› ብለው መናገራቸውን ስሰማ የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለምን በቅዱስ ያዕቆብ መንበር ሥር መሆን የለባትም /አለባተ በሚል ከ50 ዓመታት በፊት በፍርድ ቤት ክርክር ሲደረግ አንድ ሕንዳዊ አባት የሰጡት ምስክርነት ትዝ ያለኝ፡፡ 
 
በሕንድ ፍርድ ቤት የሕንድን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለማየት ከ50 ዓመታት በፊት ክርክር በተደረገ ጊዜ የሶርያውን መንበር የተቀበሉ ምእመናን ከባድ ፈተና ላይ ወድቀው ነበር፡፡ በአንድ በኩል በሶርያ መንበር የነበሩ አበው ለሕንድ ቤተ ክርስቲያን ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠታቸው ምእመናኑ ይማረራሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከመንበሩ መነጠሉ ጥንታዊውን መንገድና ሥርዓት አዛብቶ ለተኩላ ስለሚዳርግ ያስጨንቃቸዋል፡፡ 

በፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በተመለከተ የተጠየቁት አባ ያዕቆብ የተባሉ ሕንዳዊ መነኮስ ‹እኔ መንበረ ያዕቆብ ስል ስለ እምነቴና ስለ ሥርዓቴ እየተናገርኩ እንጂ በቦታው ዛሬ ስለተቀመጡት አባቶች አይደለም፡፡ እነርሱ እንደሰውነታቸው ይበረታሉ ወይም ይደክማሉ፤ ይሠራሉ ወይም ይሰንፋሉ፡፡ ያቺ የተቀደሰቺው የያዕቆብ መንበር ግን ምን ጊዜም ቅድስት ናት፡፡ እኔ ያቺን መንበር ሳስብ ለእምነታቸው የታገሉትን ቅዱሳን አበው፣ ለመንጎቻቸው የሞቱትን ሰማዕታት እረኞች፣ በአሕዛብ ተከብበው በየዘመናቱ የደረሰባቸውን መከራ አሳልፈው በእምነታቸው የጸኑትን ጠንካሮቹን አበው ነው የማስበው፡፡ መንበሪቱ ማንም ቢቀመጥባት የማትረክስ ናት፡፡ ወርቅ ላይ ምንም ዓይነት ጭቃ ቢቀመጥ የወርቁን ክብር አይቀንሰውም፡፡ እንዲያውም ወርቁ የጭቃውን ክብር ይጨምረዋል፡፡ ለእነዚያ አበው የተሰጠው ቃል ኪዳን እንዲሁ የሚጠፋ አይደለም፡፡ እኔ ከመንበረ ያዕቆብ አልለይም ስል ለዘመናት ከተከፈለው መሥዋዕትነት አልለይም፣ በሐዋርያዊት ትውፊት ከምትኖረው ቤተ ክርስቲያን አንድነት አልለይም፣ እነዚያ ብርቱዎች የታገሉለትን ዓላማ ለደካሞች ብዬ አላፈርስም ማለቴ ነው› ብለው ነበር ምስክርነታቸው የሰጡት፡፡ 
 
በዚህ ዘመን በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚገኙ አበውና ምእመናንም ተመሳሳይ ፈተና ነው የሚገጥማቸው፡፡ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር መሆን ማለት ድሎትና ምቾት አይደለም፡፡ የአባቶችን ጥበቃና እረኝነት ማግኘትም አይደለም፡፡ መከራ መቀበልና መሥዋዕትነት መክፈል እንጂ፡፡ ‹በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር መሆን› ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ያልገባው ኦርቶዶክሳዊ ፈተናው ከባድ ይሆንበታል፡፡ መንበሩን ከሰዎቹ፣ እምነቱን ከፖለቲከኞቹ፣ ሥርዓቱን ከዘረኞቹ መለየት ካልቻለ ፈተናውን አይቋቋመውም፡፡ ይሁዳን ብቻ የሚያይ ከሆነ ሐዋርያነትን ይጠላል፡፡
 
አባቶቻችን ‹እስክንድርያ እናታችን፣ ማርቆስ አባታችን› ብለው ለ1600 ዓመታት ሲኖሩ በመንበረ ማርቆስ የተቀመጡት አበው ሁሉም  አስደስተዋቸው፣ የእስክንድርያው ቤተ ክህነት ሥራ አርክቷቸው አልነበረም፡፡ ለመንጋው የማይራሩ፣ በሲሞናዊነት የዘቀጡ፣ ከግብጽ መሪዎች ጋር ተመሳጥረው እረኝነታቸውን ለፖለቲካ የሸጡ አበው ነበሩበት፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት 111 ጳጳሳት ሁሉ ደጋጎች፣ ሊቃውንት፣ ብርቱዎችና መንጋውን በትጋት የሚጠብቁ አልነበሩም፡፡ ሙስሊሞች ጳጳሳት ሆነው መጥተው ያውቃሉ፡፡ የግብጽ መሪዎችን ፈቃድ ለመፈጸም መስጊድ የሠሩ ግብጻውያን ጳጳሳት ነበሩ፡፡ ምንም ያልተማሩና ከምእመናኑ በዕውቀት ያነሱ ጳጳሳት ተልከው ያውቃሉ፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን አባቶቻችን መንበሩንና ርእሰ መንበሩን አክብረው ኖረዋል፡፡ ለምን?
 
አባቶቻችን ‹እስክንድርያ እናታችን› ሲሉ እስክንድርያ የምትወክለውን የአትናቴዎስና የቄርሎስ፣ የተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስና የዲዮስቆሮስ እምነት ማለታቸው ነው፡፡ እስክንድርያ ሲሉ ‹ወልድ ዋሕድ› የሚለውን የማይናወጽ ትምህርተ ሃይማኖት ማለታቸው ነው፡፡ እስክንድርያ ሲሉ በኒቂያ፣ በቁስጥንጥንያና በኤፌሶን የተወሰነውን የተዋሕዶ ትምህርተ ሃይማኖት ያገኙባትን መንበር ማለታቸው ነው፡፡ ለእነርሱ ‹ማርቆስ አባታችን› ማለት ከማርቆስ ጀምሮ ሳይቋረጥ የኖረውን ሐዋርያዊ የክህነት ቅብብል ያገኙበትን ቅዱስ መንበር ነው፡፡ መንበሩን ለማጽናት ከአረማውያን፣ ከአርዮሳውያን፣ ከንስጥሮሳውያን፣ ከልዮናውያንና ከሙስሊሞች ጋር የተደረገውን መሥዋዕትነት ነው፡፡ 
 
እነርሱ ታማኝ ሆነው የኖሩት ለዚህ ጽኑዕ እምነትና ሐሳብ ነው፡፡ ለዚህም ነው በዘመናት መካከል ዓላማው ያልገባቸው ሰዎች ሲነሡና በመንበሩ ላይ ሲቀመጡ፣ ኃላፊነታቸውን ትተው የንጉሥ ፈቃድ ፈጻሚዎች ሲሆኑ፤ መንጋውን ረስተው ለግል ጥቅማቸው ሲያደሉ የአባቶቻችን ሐሳብ ያልተቀየረው፡፡ 
 
ዛሬም ‹እናት ቤተ ክርስቲያን› ስንል አቡነ ጳውሎስ ወይም አቡነ ማትያስ ማለታችን አይደለም፡፡ እናት ቤተ ክርስቲያን ስል አቡነ ዳንኤል ወይም አቡነ አትናቴዎስ ማለታችን አይደለም፡፡ እናት ቤተ ክርስቲያን ስንል ንቡረ እድ እንትና ወይም ሥራ አስኪያጅ እንቶኔ ማለታችን አይደለም፡፡ እነዚህ ሁሉም በእርሷ ሥር ሆነው የሚሠሩ፡፡ አንዳንዶች የሚጠበቅባቸውን አንዳንዶችም የማይጠበቅባቸውን የሚያደርጉ ተላላኪዎቿ ናቸው፡፡ አንዳንዶች መጥተውላታል፣ አንዳንዶችም መጥተውባታል፡፡ አንዳንዶች ተነሥተውላታል፣ አንዳንዶችም ተነሥተውባታል፡፡ አንዳንዶች ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ ይጽፋሉ፤ አንዳንዶችም በሞት መጽሐፍ ይመዘገባሉ፡፡ እናት ቤተ ክርስቲያን ግን ከእነርሱ ብቻ ሳይሆን ከድምራቸውም በላይ ናት፡፡ እነርሱ ያልፋሉ፤ እርሷ ግን ሁሉን ታሳልፋለች፡፡ እነርሱ ይቀራሉ፤ እርሷ ግን ትሻገራለች፡፡ 
 
እናት ቤተ ክርስቲያን ስንል ዐርባ ሺ  አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን፣ 400 ሺ ካህናትን፣ 1100 ገዳማትን፣ ሃምሳ ሚሊዮን ምእመናንን፣ ከሦስት ሺ ዓመታት በላይ የዘለቀውን ታሪክ የጠበቀች ብሔራዊት ቤትን፣ እልፍ ቅዱሳንን ወደ መንግሥተ ሰማያት ያሻገረች ሰማያዊት መሰላልን፣ ከ200ሺ በላይ የሚደርሱ መጻሕፍትን ለትውልድ ያቆየች መዝገብ ቤትን ማለታችን ነው፡፡ ዮዲትን ያለፈቺውን፣ ግራኝን የተሻገረቺውን፣ ደርቡሽ አቃጥሎ፣ ጣልያን መዝብሮ ድል ሊያደርጋት ያልቻለቺውን ቤተ ክርስቲያን ማለታችን  ነው፡፡ መንበሯ ከርእሰ መንበሯ በላይ ነው፡፡ ሲኖዶሷም ከአባላቷ በላይ ነው፡፡ ለእኛ መንበሯ የታሪኳ፣ የቀኖናዋ፣ የትምህርተ ሃይማኖቷ፣ የቅርሷ፣ የባሕሏ፣ የስብከተ ወንጌሏ፣ የፈተናዋ፣ የምእመናኗ፣ የአጥቢያዎቿ፣ የአህጉረ ስብከቶቿ፣ የገዳማቷ፣ የመናንያኗ የአንድነታቸው መገለጫ (ትእምርተ አሐተኒ)፣ አንዲት ጉባኤ የመሆናቸው አይከን ማለታችን ነው፡፡ ይኼ ደግሞ ከባለ ሥልጣኖቿ ሁሉ በላይ ነው፡፡ እርሷ ‹መልዕልተ ኩሉ› ናትና፡፡
ባለ ሥልጣኖቿ የሚሠሩት ስሕተትና ጥፋት ያሳዝነናል፤ ግን ተሥፋ አያስቆርጠንም፣ ያስለቅሰናል፣ ግን ከመንገድ አያስቀረንም፡፡ ከጥፋታቸው እንጂ ከአንድነቷ አያስወጣንም፣ እንደ ሸረሪት ቤታችን ሲቃጠል ትተን የምንጠፋ ሞኞች አይደለንም፡፡ ልጆቿ ነንና መከራዋን አብረን እንሳተፋለን፤ እንደ ባዕድ ባወጣ ያውጣሽ አንላትም፡፡ ድግስ እንደተጠራ ሰው ሲስተካከል ጥሩን ብለን ትተን አንሄድም፤ እንዲስተካከል በኣት አጽንተን እንጋደላለን እንጂ፡፡  
 
የቤተ ክርስቲያን ልጅነትን ማንም እንኩ ብሎ የሚሰጠን፣ ወይም ማንም አትችሉም ብሎ የሚከለክለን አይደለም፡፡ በዐርባ በሰማንያ ያገኘነው፣ በእምነትና በምግባር ተግተን፣ በመዋቅርና በሥርዓት ኖረን ያጸናነው ጸጋችን ነው፡፡ እኛ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ስንል አባ ጊዮርጊስ እንዳስተማረን መስቀላዊቷን ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ከላይ ወደ ታች ከፓትርያርክ እስከ ምእመን፣ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ፡፡ ከግራ ወደቀኝ ከአሶሳ እስከ ቶጎ ጫሌ፣ ከዛላ አምበሳ እስከ ሞያሌ ያለቺውን ቤተ ክርስቲያን፡፡ ከላይ እስከ ታች - ከዐጸደ ነፍስ እስከ ዐጸደ ሥጋ፣ ከግራ ወደ ቀኝ - ከቶኪዮ እስከ ሎስ አንጀለስ፣ ከሜልበርን እስከ ጃማይካ ያለቺውን ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ከላይ እስከ ታች ከአርእስተ አበው እስከ ዓለም መጨረሻ የሚነሡ ክርስቲያኖች፤ ከግራ ወደ ቀኝ - ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ የተበተኑ የእግዚአብሔር ልጆች ያሉባትን ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ 
 
የምንኖረው በዚህች ቤተ ክርስቲያን ነው፤ የምንሠራው ለዚህች ቤተ ክርስቲያን ነው፤ የምንሞተውም በዚህች ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ የምንታመነውም ለዚህች ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ እንዳትገነጠል፣ እንዳትከፋፈል፣ የምንታገለው ይህቺን ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ እኛ ሲኖዶስ ስንል አባቶቻችን የራሳችን ጳጳሳት እንዲኖሩን ያደረጉትን ተጋድሎ እናስባለን፡፡ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ብለው፣ ክብራቸውንም ትተው የአንበሳ ደቦል፣ የዝሆን ግልገል፣ የወርቅ እንከብል ይዘው እስክንድርያ ድረስ ጳጳስ ለማምጣት የደከሙትን ድካም እናስባለን፡፡ አሁን ያሉት አባቶች ቢያቀሉትም ኢትዮጵያውያን ጳጳሳትን ለማግኘት፣ አዲስ አበባ ላይ መንበረ ፕትርክና ለመመሥረት ሺ ዓመታትን የፈጀ ተጋድሎ ተደርጓል፡፡ በአንድ በኩል የቤተ ክርስቲያንን አንድነት አስጠብቆ፣ በሌላ በኩል ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን እረኞች እንዲያገኙ እየታገሉ ያለፉትን አበው እናስባለን፡፡ 
 
ቀራንዮ ላይ ዮሐንስን መስሎ የመቆምን ያህል ከባድ ነገር የለም፡፡ ባልንጀሮቹ በሙሉ ሄደዋል፡፡ የሚወደው መምህሩ ራቁቱን ተሰቅሏል፡፡ ሽፍቶችና አልፎ ሂያጆች ይዘብቱበታል፡፡ ቀያፋና ሐና ድል አደረግን ብለዋል፡፡ ያንን ጌታ፣ ያንን ራቁቱን የተሰቀለ ጌታ፣ ተጠማሁ የሚለ ጌታ፣ ልብሶቹን ዕጣ የሚጣጣሉበትን ጌታ፣ በደም አበላ የተዋጠውን ጌታ - ጌታ ነው ብሎ እንደማመንና፣ ባመኑትም እንደመጽናት ያለ ምን ከባድ ነገር አለ? ጌታን ዓይን ሲያበራ፣ ጎባጣ ሲያቀና፣ ኅብስት ሲያበረክት፣ ሙት ሲያስነሣ፣ ማዕበል ጸጥ ሲያደርግ ማመን ቀላል ነው፡፡ ጌታን ተሰቅሎ ማመን ግን ከባድ ነው፡፡ ያ ቀን እውነት የተሰቀለችበት ቀን ነውና፡፡
ይህ ዘመን እውነት የተሰቀለችበት ዘመን ነው፡፡ በእናት ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ አንዳንድ አባቶችና አገልጋዮች ራሳቸው አንዲቷን ቤተ ክርስቲያን ሊያፈርሱ ሲሠሩ፤ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ከሚጋደሉት ይልቅ አፍራሾቹ የቤት ልጆች ሲሆኑ፣ ከአማኞቹ ይልቅ ከሐዲዎቹ፣ ከጽኑዐኑ ይልቅ መናፍቃኑ በር ሲከፈትላቸው፣ ከልጆቿ ይልቅ ጠላቶቿ ሲሾሙ ‹እናት ቤተ ክርስቲያን› ብሎ መጋደል በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ እንደተገኘው እንደ ዮሐንስ መሆን ነው፡፡ እውነት ስትሰቀል ከእውነት ጋር መቆም፡፡ 
 
ዕለተ ዓርብ ያልፋል፡፡ የቀያፋ ድንፋታ፣ የሐናም ኩራት ያከትማል፡፡ የተቀበረው እውነት ይነሣል፡፡ የሄሮድስና የጲላጦስ ማኅተም ይፈታል፡፡ የሸሹ ሐዋርያት ይመለሳሉ፤ የካደው ጴጥሮስ ንስሐ ገብቶ ይመጣል፡፡ የሸጠው ይሁዳም ተቀስፎ ይሞታል፡፡ ያን ጊዜ በመስቀሉ ግርጌ እውነት ስትሰቀል ከእውነት ጋር የቆመው ዮሐንስ ‹ሞትን ከማይቀምሱት ወገን› ይሆናል፡፡ የዓርብን ግርግር፣ የቅዳሜን ጸጥታ በትእግሥትና በጽናት የሚያልፍ ዮሐንስ ከተገኘ - አላውቅም ካለው ከጴጥሮስ ጋር ሆኖ ትንሣኤውን ለማየት ወደ መቃብሩ ይጠራል፡፡ 
 
እስከዚያ ግን እውነት ትሰቀላለች፤ ልጆቿም ራሳቸው ለማዳንና መከራውን ላለመቀበል ሲሉ ትተዋት ይሄዳሉ፡፡ እውነት ያለብነ ትተው ገንዘብ ያለበትን ይመርጣሉ፤ ምቾት ያለበትን ይፈልጋሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እንደ ዮሐንስ የሚጸና ብጹዕ ነው፡፡

87 comments:

 1. Well Said! Truly inspiring.

  ReplyDelete
 2. አቤት አምላኬ የኛ እዳ ብዛቱ ዳኒ በዚ ዘመን የሃዋርያት ልጅ የቤ/ክርስትያን ጋሻ የኛ የማንቂያ ደውል ነህ።
  ግማሹ ይግለሰብ ተከታይ ግማሹ ጥቅሙን አሳዳጅ ግማሹ በድፍረት ይችን ሃይማኖት ለማፍረስ ልጅዋ መስሎ ሲጥር እንዳንተ አይነቱን ሳይ አቤት ያምላክ ጥበቃ እላለው።
  ሰባኪ ነን ባዩ ብዛቱ ስህተትን እያዩ ዝምታን መርጠው አጀንዳቸው ስለ ሌላ የመናፍቃን ምላሽ ምናምን እያሉ ጥቅም ተኮር ስብከት ቤ/ክርስትያን ውስጥ የስህተት አስተምሮን የስህተት ማጥመቅ የስህተት ክህነትን በዝምታ የሚያልፉ ሰባኪያን እዳ እንዳለባቸው ያውቁ ይሆን ?
  በክርስትና ልኑርበት ከሰው ምን አጣላኝ የምሰብከው አላጣው እያሉ ስብከትን ስራ ያረጉ ሰዋች ያንተ ለእውነት መቆም ለነሱ ደውል ነው ከእዳ አያመልጡም ክርስትና ለእውነት መቆም ሃሰትን መቃወም ነውና አምላክ ይጠብቅህ ።

  ReplyDelete
 3. kezih beqer mn malet yichalal?...
  ....ቀራንዮ ላይ ዮሐንስን መስሎ የመቆምን ያህል ከባድ ነገር የለም፡፡ ባልንጀሮቹ በሙሉ ሄደዋል፡፡ የሚወደው መምህሩ ራቁቱን ተሰቅሏል፡፡ ሽፍቶችና አልፎ ሂያጆች ይዘብቱበታል፡፡ ቀያፋና ሐና ድል አደረግን ብለዋል፡፡ ያንን ጌታ፣ ያንን ራቁቱን የተሰቀለ ጌታ፣ ተጠማሁ የሚለ ጌታ፣ ልብሶቹን ዕጣ የሚጣጣሉበትን ጌታ፣ በደም አበላ የተዋጠውን ጌታ - ጌታ ነው ብሎ እንደማመንና፣ ባመኑትም እንደመጽናት ያለ ምን ከባድ ነገር አለ? ጌታን ዓይን ሲያበራ፣ ጎባጣ ሲያቀና፣ ኅብስት ሲያበረክት፣ ሙት ሲያስነሣ፣ ማዕበል ጸጥ ሲያደርግ ማመን ቀላል ነው፡፡ ጌታን ተሰቅሎ ማመን ግን ከባድ ነው፡፡ ያ ቀን እውነት የተሰቀለችበት ቀን ነውና፡፡....

  ReplyDelete
 4. Kifu zena Kifu zemen Gifuan Yebezubet aweye betekristian endi mehoneshen enkuwanem alayu enza degage abatochesh meseweat yehonulesh kidusanochesh....abet egzio abes geberku....Abatochachen mengawen tebiku new aydel yetebalut???? gera geban eko bemenafikanuna kemibetenew yilek berasu bebetu sewoch yemibetenut eyebeza meta ....gedelem zemenu kerbowal talalkochem eskemisitu aydel yetebalew ...Ante gen betemarkebetena beteredahebet Tsenteh nur balen amanawi kale meseret Kebetu saneweta endintsena yeabatochachen amelak yirdane. Egna bekirstose kirestian bewold wulud yetebalenew lesew ayidelem le sinodos tebelo lekahinat tebilo ayidelem le erasu lebetekristian eras lehonelat le getachen le amelakachen le eyesus kirstose enji. abatochachen melak sehonu bemelekamenetachew enetekemalen enetazezalen melkam kalehonu demo betekristianen tilen teleyeten aninorem. Haimanotachenen yeseten erasu balebetu egziabher new sewoch degemo yihen lesewe hulu yidares zend telikewal telekowachewn beagebabu kalfetsemu enesu yiteyekubet gen egna betachen new sew alsetenem sew ayinetekenem.Ahun endebiret tenkiren And honene mekom yaleben seat new bezi keketele betekristianen lehulet likefeluwat new.

  ReplyDelete
 5. መጽናት ይኖርብናል፡፡

  ReplyDelete
 6. ዕለተ ዓርብ ያልፋል፡፡ የቀያፋ ድንፋታ፣ የሐናም ኩራት ያከትማል፡፡ የተቀበረው እውነት ይነሣል፡፡ የሄሮድስና የጲላጦስ ማኅተም ይፈታል፡፡ የሸሹ ሐዋርያት ይመለሳሉ፤ የካደው ጴጥሮስ ንስሐ ገብቶ ይመጣል፡፡ የሸጠው ይሁዳም ተቀስፎ ይሞታል፡፡ ያን ጊዜ በመስቀሉ ግርጌ እውነት ስትሰቀል ከእውነት ጋር የቆመው ዮሐንስ ‹ሞትን ከማይቀምሱት ወገን› ይሆናል፡፡ የዓርብን ግርግር፣ የቅዳሜን ጸጥታ በትእግሥትና በጽናት የሚያልፍ ዮሐንስ ከተገኘ - አላውቅም ካለው ከጴጥሮስ ጋር ሆኖ ትንሣኤውን ለማየት ወደ መቃብሩ ይጠራል፡፡

  ReplyDelete
 7. Kale hiwot yasemah.ye Fekure Egzine Bereket Yasatefeh.

  ReplyDelete
 8. ዳኒ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ እውነት ቢሰቀል በሶስተኛው ቀን ተነሳ፡፡ እውነትን የሰቀሉ ግን በልጆቻቸው ስጋ ሳሙና ተሰራባቸው፡፡
  ‘ዕለተ ዓርብ ያልፋል፡፡ የቀያፋ ድንፋታ፣ የሐናም ኩራት ያከትማል፡፡ የተቀበረው እውነት ይነሣል፡፡ የሄሮድስና የጲላጦስ ማኅተም ይፈታል፡፡ የሸሹ ሐዋርያት ይመለሳሉ፤ የካደው ጴጥሮስ ንስሐ ገብቶ ይመጣል፡፡ የሸጠው ይሁዳም ተቀስፎ ይሞታል፡፡ ያን ጊዜ በመስቀሉ ግርጌ እውነት ስትሰቀል ከእውነት ጋር የቆመው ዮሐንስ ‹ሞትን ከማይቀምሱት ወገን› ይሆናል፡፡ የዓርብን ግርግር፣ የቅዳሜን ጸጥታ በትእግሥትና በጽናት የሚያልፍ ዮሐንስ ከተገኘ - አላውቅም ካለው ከጴጥሮስ ጋር ሆኖ ትንሣኤውን ለማየት ወደ መቃብሩ ይጠራል፡፡ እስከዚያ ግን እውነት ትሰቀላለች፤ ልጆቿም ራሳቸው ለማዳንና መከራውን ላለመቀበል ሲሉ ትተዋት ይሄዳሉ፡፡ እውነት ያለብነ ትተው ገንዘብ ያለበትን ይመርጣሉ፤ ምቾት ያለበትን ይፈልጋሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እንደ ዮሐንስ የሚጸና ብጹዕ ነው፡፡’ የአገልግሎት ዘመንህ ይባረክ፡፡

  ReplyDelete
 9. "መንበሯ ከርእሰ መንበሯ በላይ ነው፡፡ ሲኖዶሷም ከአባላቷ በላይ ነው፡፡ ... እርሷ ‹መልዕልተ ኩሉ› ናትና፡፡
  ባለ ሥልጣኖቿ የሚሠሩት ስሕተትና ጥፋት ያሳዝነናል፤ ግን ተሥፋ አያስቆርጠንም፣ ያስለቅሰናል፣ ግን ከመንገድ አያስቀረንም፡፡ ከጥፋታቸው እንጂ ከአንድነቷ አያስወጣንም፣ እንደ ሸረሪት ቤታችን ሲቃጠል ትተን የምንጠፋ ሞኞች አይደለንም፡፡"

  ዲ/ን አንተን ያበርታልን።

  ReplyDelete
 10. lega tfthbg sasb nber enkan dhen mthe egezabher amlek ydengle Maryam leg ytabkh!! yga btkerestyn mtames mch kome ble new yrasy ylchacw legwechew ybglemedrlebsaw by btcrsestinew tsgsegaw eymswet new thdsw ymelwet kethiopa snkabachw amercen eymtew yhnen ywe hethem yzawet gadal eygabwe new egezabher amlak lenatwe bgabaw kalkedan mesart klasaben yamreca menme gaday assab new gatachen mdhantachen yeses crestos bmhertew ygabgan amen!!

  ReplyDelete
 11. ቃለ ህይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. eventualy Truth asserts itself!

   Delete
 12. It is one big step. God bless you.

  ReplyDelete
 13. This is a hymn to Integrity!

  ReplyDelete
 14. ቃለ ህይወት ያሰማልን !!!መጽናት ይኖርብናል!!!ዕለተ ዓርብ ያልፋል፡፡ የቀያፋ ድንፋታ፣ የሐናም ኩራት ያከትማል፡፡ የተቀበረው እውነት ይነሣል፡፡

  ReplyDelete
 15. ዲያቆን ዳንኤል ከአንተ የሚጠበቀው ችግሩን ብቻ ማውራት አይደለም፡፡የተወሰኑ አካላትና ግለሰቦች ላይ ብቻ ተጠያቂነቱን መደፍደፍም አይደለም፡፡መፍትሔውንና በጉዳዩ እንደ ግለሰብም እንደ ቡድንም ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦችን ከሁሉም ወገን አካትተህ ካላቀረብክ ጥቅም የለውም፡፡አንድ ጽንፍ ይዘህ በአንድ ረድፍ ጉዞህ ተደመደመ፡፡በቤተክርስቲያን ጉዳይ ያገባናል ስንል ለመብት ብቻ አይደለም፤በተጠያቂነቱም እንደየድርሻችን ተጠያቂ ነን፡፡ኃላፊነትን ሁሉ ለአንድ ወገን የመስጠት ያህል ተጠያቂነትንም ለአንድ ወገን መስጠት ጉዳት አለው፡፡
  ለችግሮች መወሳሰብ በሚዲያው ተሰሚነት ያላችሁ የቤተክርስቲያን ልጆች የምትከተሉት በአመራሩ አካባቢ ያሉ አባቶችንና ተቋሙን በፍቅርና በገንቢ ሂስ ከማገዝ ይልቅ ዘወትር ህጸጽ ብቻ ነቃሽ ሆኖ መቅረብም የራሱ አስተዋጽኦ አለው፡፡በዚህ አካሄዳችሁ የተነሳ በሂደት ያላችሁ ተሰሚነትና ሚና እየቀነሰ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡በእናንተ ረድፍ ያለው ተሰላፊ ወደ ትችት አዘንብሏል፡፡ስለቤተክሕነት ደግ ማውራት እርሙ ነው፡፡አንተ ራስህ ዝቋላ ላይ ኤሬቻ ሊከበር ነው ብለህ ጥሩ ጽሑፍ ጻፍክ፡፡ቤተክሕነቱ በጻፈው ደብዳቤ መነሻነት የበዓሉ አከባበር በዝቋላ ሳይሆን በተለዋጭ ቦታ እንዲደረግ ሲሆን የአንድ ዐረፍተ ነገር እውቅና እንኳ መስጠት ተሳነህ፡፡ፍጻሜው ገና ቢሆንም ቅዱስ ሲኖዶስ የ24 ሰዓት ቴሌቪዥን ለመጀመር ውሳኔ ሲያሳልፍ ምንም ማለት አልፈለክም፡፡ህጸጽ ለመንቀስ ሲሆን ግን ከፊት ትሰለፋለህ፡፡አየህ፡- በቤተክሕነት ያሉ መሪዎች ሰዎች ናቸው፡፡ለእርግማንና ለዘለፋ ብቻ ስማቸውን የሚያነሳ ሰው ለመስማት ኅሊናቸው ይተናነቃቸዋል፡፡ሲጀመር ላይሰሙህ ይችላሉ፤ቢሰሙህም በቸልታ ነው፤ልብ አይሰጡህም፡፡
  ቅኝትህ አንድ አይነት ሆኗል፡፡ምን ቢሳሳቱ የማትወቅሳቸው ወገኖች አሉ፤ምን ደግ ቢሰሩ እውቅና የማትሰጣቸው ሰዎች አሉ፡፡ጉዞአቸውን ሁሉ የጽድቅ፣ንግግራቸውን ሁሉ ክርስቶሳዊ፣የጻፉትን ሁሉ ቄርሎሳዊ የምታደርግላቸው ወገኖች አሉ፡፡ያለመግባባት ሲፈጠር አስታራቂ ሐሳብ እንደማቅረብ ቀድመህ የተወሰነውን አካል ሐና እና ቀያፋ ወይም ይሑዳ፤የደገፍከውን አካል ደግሞ ሐዋርያና ክርስቶስ አድርገህ ለሚዛናዊ አቀራረብ ቅንጣት ሳትጨነቅ ትጽፋለህ፡፡እንደዚህ ሲሆን በጽሑፍህ የብዙዎችን በቅኝትህ የታቀኙና ስለሌላው ስሕተት በማውራት ራሳቸውን ያጸደቁ ወገኖችን ታስደስት ይሆናል፤ልክ ልካቸውን ነገረልን የሚል ሙገሳ ታገኝ ይሆናል፡፡ለቤተክርስቲያን ግን አትጠቅማትም፡፡ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ችግር ምንጩ አንድ አካል ብቻ አይደለም፡፡መፍትሔውም እንደዛው፡፡ከዚህ አንጻር ቅንጣት መነሻ ስታገኝ የኖረ ቂምህን ሁሉ ከግብጽ የድሮ ጳጳሳት እስከ ቅርብ ዘመኑ አቡነ ጳውሎስ በመጥቀስ ማዥጎድጎድ ብቻ ጥቅሙ አይታየኝም፡፡
  በስክነት፣በሚዛናዊነት፣በመፍትሔ ተቋሚነት፣የራስንና ቡድናዊ ፍላጎትን ብቻ ተገን አድርጎ ባለመንቀሳቀስ፣በቤተክሕነቱ ውስጥ ከነቀዙ ግለሰቦች በተጓዳኝ አያሌ ቅን አባቶች ስላሉ ለእነሱ በመጨነቅ፣በንግግር ሊፈቱ የሚችሉና የመፈታት እድላቸው ተሟጡዋል ለማለት እጅግ ገና ብዙ የሚቀራቸውን ከላይ የጠቀስከውን ደብር አለመግባባት አይነት ገጠመኞች ባለማባባስ በኃላፊነት መንፈስ ብትጽፍ ደስ ይለኛል፡፡ችግር በማራገብና አንዱን አካል ብቻ ነጥሎ በመውቀስ ቤተክሕነቱ የሚቃና ቢሆን ኖሮ የአንተን ብሎግ ጨምሮ ፕሬሱና ማኅበራዊ ሚዲያው ለሁለት ዐሰርት ዓመታት የሰነዘሩት ወቀሳ ብቻ ለቤተክሕነት ክንፍ ያበቅልለት ነበር፡፡ስለዚህ ስንተች በስክነትና በሚዛናዊነት ቢሆን ደስ ይለኛል፤ያለበለዚያ አድማጩም ልማዱ ነው ብሎ በግራው ሰምቶ በቀኙ ያፈሰዋል፡፡እውነትን አንተም በኢ-ሚዛናዊነት ሰቅለኻታላ!የቤተክርስቲያንን ክፉ አያሰማን፤አሜን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. what is your difference as seen by your evaluation criteria!!!

   Delete
  2. የተላለፈው መልዕክት ይህ ነው፡-
   "ባለ ሥልጣኖቿ የሚሠሩት ስሕተትና ጥፋት ያሳዝነናል፤ ግን ተሥፋ አያስቆርጠንም፣ ያስለቅሰናል፣ ግን ከመንገድ አያስቀረንም፡፡ ከጥፋታቸው እንጂ ከአንድነቷ አያስወጣንም፣ እንደ ሸረሪት ቤታችን ሲቃጠል ትተን የምንጠፋ ሞኞች አይደለንም፡፡ ልጆቿ ነንና መከራዋን አብረን እንሳተፋለን፤ እንደ ባዕድ ባወጣ ያውጣሽ አንላትም፡፡ ድግስ እንደተጠራ ሰው ሲስተካከል ጥሩን ብለን ትተን አንሄድም፤ እንዲስተካከል በኣት አጽንተን እንጋደላለን እንጂ፡፡"
   ከዚህ ውጪ መፍትሄ አለ?
   "እውነትን አንተም በኢ-ሚዛናዊነት ሰቅለኻታላ!" እውነቱን እውነት ሀሰቱን ሀሰት ብሎ በማቅረቡ?
   እግዚሐብሄር ልቦና ይስጠን

   Delete
  3. "መንበሩን ከሰዎቹ፣ እምነቱን ከፖለቲከኞቹ፣ ሥርዓቱን ከዘረኞቹ መለየት ካልቻለ ፈተናውን አይቋቋመውም፡፡ ይሁዳን ብቻ የሚያይ ከሆነ ሐዋርያነትን ይጠላል፡፡"
   ይህ በእውነቱ 'ኢ-ሚዛናዊነት'ያስብላል?

   Delete
 16. ሙሐዘ ጥበባት፡-“ማን ይናገር የነበረ፥ማን ያርዳ የቀበረ፤” እንዲል፡-አንተ ብትናገር ያምራል።ምክንያቱም፡-የአንተ ምስክርነት፡-“በዘነአምር ንነግር፥ወበዘርኢነ ሰማዕተ ንከውን፤” ነውና።እንደሚታወቀው የቤተ ክርስቲያን ልጆች፡-“በስደተኞች ነን፤” ባዮች በተባረሩ ጊዜ፥አንተ ዴንቨር ነበርክ።ያን ጊዜ ያስተማርካቸው ትምህርት መጽናኛ ሆኖአቸው እስከ ዛሬ አሉ።አንተም ወደ ሰሜን አሜሪካ ብቅ ባልክ ቍጥር ዴንቨር ደብረ ሰላምን ሳትጐበኝ ተመልሰህ አታውቅም።በቀጥታ አነጋገር ያቀናኸው ቦታ ነው።ስለሆነም ምስክ ርነትህ የታመነ ነው።በነገራችን ላይ፡-ካህናቱ የምናገለግለውን ስለምናውቅ እና ዓላማችን ከእግዚአብሔር የተሰጠንን አደራ መጠበቅ ስለሆነ፥የሆነው ነገር ጥቂ ት ቢያሳዝነንም፡-በቀላሉ የምንናወጥ አይደለንም።በቤተክርስቲያን ውስጥ በማደጋችን፥የሆነው ነገር የተለመደ እንጂ አዲስ ክስተት አለመሆኑን እናስተው ላለን።የሆነውን ነገር ሁሉ እንዲሆን ያስደረጉት ሰዎች የኪዳነ ምሕረት ካህና ትና ሰባካ ጉባኤ አባላት ብቻም እንዳልሆኑ እናውቃለን።በየስቴቱ ያሉ ጽዋ አጣጪዎቻቸው ትብብርም እንዳለበት እናውቃለን።ይህ ነገር ገሀድ የወጣው ከሰባት ዓመት በፊት ነው።ከሚመስሏቸው ሰዎች ጋር፥ዴንቨር ባለ ሰው ሰብሳ ቢነት ሁለት ጊዜ ባደረጉት የስልክ ውይይት፥“ማኅበረ ቅዱሳንን ለማጥፋት” ተማምለው እንደነበረ በየድረ ገጹ አንብበናል።ቀጥሎም ለማስመሰል በማኅበረ ካህናት ስም ከሌሎችም በመቀላቀል፥ምን ሲወያዩ እንደነበረ በወቅቱ በደጀ ሰላም ላይ የወጣውን የድምፅ መረጃ ሁላችንም ሰምተናል።በማኅበረ ቅዱሳ ንም ላይ፡-“ይሙት በቃ፤” ፈረደው፥የተፈራረሙትን ደብዳቤም አንብበናል። ደብዳቤው በቀጥታ የተጻፈው በረከታቸው ይደርብንና ለብፁፅ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ነበር።በግልባጭም ለአሜሪካ መንግሥትና ለኢትዮጵያ መንግሥት አስ ታውቀዋል።ይህ ሁሉ ሲሆን አንድም ቀን “ለምን እንዲህ አደረጋችሁ?” ብለን አናውቅም፥እነርሱም እንድም ቀን ተጸጽተው ወይም ይሉኝታ ተሰምቶአ ቸው አያውቅም፥ወደፊትም ዓላማቸውን እስከሚያስፈጽሙ ድረስ እንቅልፍ እንደማይዛቸው እናውቃለን።ዛሬ ያየነው እንደ ተከታታይ የመጽሔት ጽሑፍ ካለፈው የቀጠለውን ነው።ለጊዜው “ይቆየን፤” ብለዋል፥ነገ እናቀጥለዋለን ማለ ታቸው ነው።እኛ ለእንደዚህ አይነቱ ነገር ጊዜ የለንም፥ነገራችን፡-ነገረ ክርስቶስ ፥ነገረ ማርያም፥ነገረ ቅዱሳን ነው።ዳኒ እናመሰግናለን።(ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው፤ )

  ReplyDelete
 17. እርግጥ ነው፡፡ ለተስፋችን ምክንያት፤ ለበዛውን ግፍ መታገሻ ዓለት፤ ለህመማችን ፈውስ በሆነችዉ እናት ቤተ ክርስቲያን ያጽናን፡፡ ስለእዉነት በእዉነት ለልጆቿ መረጋጋት ምክንያት የሚሆን ነዉና ዲ/ን በመጨረሻዉ ዘመን ነጩን ያልብስህ፡፡

  ReplyDelete
 18. It is really inspiring and well expressed article. May God Bless you Dn. Daniel. You are our eyes and ears!!

  ReplyDelete
 19. ይህ ሁሉ እንካ ሰላምታ ታሪክ ቁስቆሳ የኣባቶች ክብር ድምፅ እንዳይሰማ በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ቀጥሎ ቀስቱ ወደ እኔ እና መሰሎቼ ነው የሚል መልእክት ያዘለ ተራ ኣድርባይነት ነው:: ዳኒ ይህ ውሳኔውን ሰምቶ ከመታረም ይልቅ፣ አራግፎ ምዕመናንን የመሸወጃ ጽሁፍ ነው፥ ክርስቶስ የሾማቸውን ኣባቶቻችን ያከበርዋቸውን ናቁ እይልክ እስክዛሬ በፀሎት በሃይማኖት አንድነትዋ የተጠበቀችውን ቤተ ክርስቲያን በብሎግ እና በፌስቡክ በሃያ አመታት ውስጥ ለመቆጣጠር ካልሆነም ለመበታተን ብእርህን አንስተሃል:: እንጣጥ እንጣጥ በሉ ግን የትም አትደርሱም:: ለቤተ ክርስትያን የመሰረታት ሁሌ ይጠብቃታል::

  ReplyDelete
  Replies
  1. በፍፁም፤ አባት ልጁ ሲያጠፋ ሊመክረው ሊገስፀው ግድ ነው ነገር ግን እኔ አባት ነኝና ሁል ጊዜ ልክ ነኘ ማለት ግን ራስን ወደ ቅድስና ማድረስ እና ስህትን በትህትና እና መፍትሄ ለመፈለግ ከሚጠቁም ታማኝ ልጅ ይልቅ ውድቀትን እና የተሳሳተ አቓም ያለወ፤ የውሸት እየሳቀ የተቆረቆረ እየመሰለ ቤተ ክርስቲያንን ሊያጠፋ ለሚተጋ አካል ራሳችንን አጋልጠን እየስጠን ነው እና እባካችሁ ቆም ብለን እረሳቸንን እንይ፡፡ የምንፅፈውንም በማስተዋል ብንፅፍ ጥሩ ነው፡፡ ልዑል እግዚአብሄር ማስተዋሉን ያድለን፡፡

   Delete
  2. ወንድም ደባልቄ ምን እያልክ እነደሆነ ግልጽ አይደለም
   ነገር ተደባለቀብህ ይመስላል፡

   Delete
  3. የማንበብ ልምዱ አለህ ወይስ ታስንብባለህ ወይንስ ኮሜንት ብቻ አንብበህ ነው የምትጽፈው ወንድሜ አይከብድህም ደጋግመህ አንብብ

   Delete
 20. ውድ ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል፣ የቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጅ ነህ። ልዑል እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ። አባቶቻችን ይህንን ኃይለ ቃል ተገንዝብው ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ ኃያሉ እግዚአብሔር ይርዳቸው።
  "...ያን ጊዜ በመስቀሉ ግርጌ እውነት ስትሰቀል ከእውነት ጋር የቆመው ዮሐንስ ‹ሞትን ከማይቀምሱት ወገን› ይሆናል።

  ReplyDelete
 21. "አለቱ አርብ ነው"ዳ ዳንኤል ።

  ReplyDelete
 22. ባለ ሥልጣኖቿ የሚሠሩት ስሕተትና ጥፋት ያሳዝነናል፤ ግን ተሥፋ አያስቆርጠንም፣ ያስለቅሰናል፣ ግን ከመንገድ አያስቀረንም፡፡ ከጥፋታቸው እንጂ ከአንድነቷ አያስወጣንም፣ እንደ ሸረሪት ቤታችን ሲቃጠል ትተን የምንጠፋ ሞኞች አይደለንም፡፡ ልጆቿ ነንና መከራዋን አብረን እንሳተፋለን፤ እንደ ባዕድ ባወጣ ያውጣሽ አንላትም፡፡ ድግስ እንደተጠራ ሰው ሲስተካከል ጥሩን ብለን ትተን አንሄድም፤ እንዲስተካከል በኣት አጽንተን እንጋደላለን እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 23. ባለ ሥልጣኖቿ የሚሠሩት ስሕተትና ጥፋት ያሳዝነናል፤ ግን ተሥፋ አያስቆርጠንም፣ ያስለቅሰናል፣ ግን ከመንገድ አያስቀረንም፡፡ ከጥፋታቸው እንጂ ከአንድነቷ አያስወጣንም፣ እንደ ሸረሪት ቤታችን ሲቃጠል ትተን የምንጠፋ ሞኞች አይደለንም፡፡ ልጆቿ ነንና መከራዋን አብረን እንሳተፋለን፤ እንደ ባዕድ ባወጣ ያውጣሽ አንላትም፡፡ ድግስ እንደተጠራ ሰው ሲስተካከል ጥሩን ብለን ትተን አንሄድም፤ እንዲስተካከል በኣት አጽንተን እንጋደላለን እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 24. Dn Daniel kiberet GZEABHERE YEBARKEH.bewenet leben sersero yemgeba tsehufe new,ante ewenetegna ye Orthodox ye kurte ken lege nehe.ahunem yabatocachen amlake Ortodox ewenetegnawane haymanotachenen bete kiristianachenen yetebekelen. Ye Denver Medhanialem Abatoche ena Legoche ende Yohanse eske TINSSAW tsentew yemekomu endehonu amnalehu.Egzeabhere hulem yemaykeyer Amlake ethiopian yebarkat. endante yale hawarya ayasatane.kale hywot yasemahe Amen!

  ReplyDelete
 25. መንበሩን ከሰዎቹ፣ እምነቱን ከፖለቲከኞቹ፣ ሥርዓቱን ከዘረኞቹ መለየት ካልቻለ ፈተናውን አይቋቋመውም፡፡ ይሁዳን ብቻ የሚያይ ከሆነ ሐዋርያነትን ይጠላል፡፡

  God will not keep silence

  ReplyDelete
 26. መንበሩን ከሰዎቹ፣ እምነቱን ከፖለቲከኞቹ፣ ሥርዓቱን ከዘረኞቹ መለየት ካልቻለ ፈተናውን አይቋቋመውም፡፡ ይሁዳን ብቻ የሚያይ ከሆነ ሐዋርያነትን ይጠላል፡፡

  ReplyDelete
 27. ዲያቆን ዳንኤል ከአንተ የሚጠበቀው ችግሩን ብቻ ማውራት አይደለም፡፡የተወሰኑ አካላትና ግለሰቦች ላይ ብቻ ተጠያቂነቱን መደፍደፍም አይደለም፡፡መፍትሔውንና በጉዳዩ እንደ ግለሰብም እንደ ቡድንም ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦችን ከሁሉም ወገን አካትተህ ካላቀረብክ ጥቅም የለውም፡፡አንድ ጽንፍ ይዘህ በአንድ ረድፍ ጉዞህ ተደመደመ፡፡በቤተክርስቲያን ጉዳይ ያገባናል ስንል ለመብት ብቻ አይደለም፤በተጠያቂነቱም እንደየድርሻችን ተጠያቂ ነን፡፡ኃላፊነትን ሁሉ ለአንድ ወገን የመስጠት ያህል ተጠያቂነትንም ለአንድ ወገን መስጠት ጉዳት አለው፡፡
  ለችግሮች መወሳሰብ በሚዲያው ተሰሚነት ያላችሁ የቤተክርስቲያን ልጆች የምትከተሉት በአመራሩ አካባቢ ያሉ አባቶችንና ተቋሙን በፍቅርና በገንቢ ሂስ ከማገዝ ይልቅ ዘወትር ህጸጽ ብቻ ነቃሽ ሆኖ መቅረብም የራሱ አስተዋጽኦ አለው፡፡በዚህ አካሄዳችሁ የተነሳ በሂደት ያላችሁ ተሰሚነትና ሚና እየቀነሰ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡በእናንተ ረድፍ ያለው ተሰላፊ ወደ ትችት አዘንብሏል፡፡ስለቤተክሕነት ደግ ማውራት እርሙ ነው፡፡አንተ ራስህ ዝቋላ ላይ ኤሬቻ ሊከበር ነው ብለህ ጥሩ ጽሑፍ ጻፍክ፡፡ቤተክሕነቱ በጻፈው ደብዳቤ መነሻነት የበዓሉ አከባበር በዝቋላ ሳይሆን በተለዋጭ ቦታ እንዲደረግ ሲሆን የአንድ ዐረፍተ ነገር እውቅና እንኳ መስጠት ተሳነህ፡፡ፍጻሜው ገና ቢሆንም ቅዱስ ሲኖዶስ የ24 ሰዓት ቴሌቪዥን ለመጀመር ውሳኔ ሲያሳልፍ ምንም ማለት አልፈለክም፡፡ህጸጽ ለመንቀስ ሲሆን ግን ከፊት ትሰለፋለህ፡፡አየህ፡- በቤተክሕነት ያሉ መሪዎች ሰዎች ናቸው፡፡ለእርግማንና ለዘለፋ ብቻ ስማቸውን የሚያነሳ ሰው ለመስማት ኅሊናቸው ይተናነቃቸዋል፡፡ሲጀመር ላይሰሙህ ይችላሉ፤ቢሰሙህም በቸልታ ነው፤ልብ አይሰጡህም፡፡
  ቅኝትህ አንድ አይነት ሆኗል፡፡ምን ቢሳሳቱ የማትወቅሳቸው ወገኖች አሉ፤ምን ደግ ቢሰሩ እውቅና የማትሰጣቸው ሰዎች አሉ፡፡ጉዞአቸውን ሁሉ የጽድቅ፣ንግግራቸውን ሁሉ ክርስቶሳዊ፣የጻፉትን ሁሉ ቄርሎሳዊ የምታደርግላቸው ወገኖች አሉ፡፡ያለመግባባት ሲፈጠር አስታራቂ ሐሳብ እንደማቅረብ ቀድመህ የተወሰነውን አካል ሐና እና ቀያፋ ወይም ይሑዳ አድርገህ ታክፋፋዋለህ፤የደገፍከውን አካል ደግሞ ሐዋርያና ክርስቶስ አድርገህ ለሚዛናዊ አቀራረብ ቅንጣት ሳትጨነቅ ትጽፋለህ፡፡እንደዚህ ሲሆን በቅኝትህ የታቀኙና ስለሌላው ስሕተት በማውራት ራሳቸውን ያጸደቁ ወገኖችን ታስደስት ይሆናል፤ልክ ልካቸውን ነገረልን የሚል ሙገሳ ታገኝ ይሆናል፡፡ለቤተክርስቲያን ግን አትጠቅማትም፡፡ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ችግር ምንጩ አንድ አካል ብቻ አይደለም፡፡መፍትሔውም እንደዛው፡፡ከዚህ አንጻር ቅንጣት መነሻ ስታገኝ የኖረ ቂምህን ሁሉ ከግብጽ የድሮ ጳጳሳት እስከ ቅርብ ዘመኑ አቡነ ጳውሎስ በመጥቀስ ማዥጎድጎድ ብቻ ጥቅሙ አይታየኝም፡፡እንዲህ አለ ለመባል ካልሆነ በቀር!
  በስክነት፣በሚዛናዊነት፣በመፍትሔ ተቋሚነት፣የራስንና ቡድናዊ ፍላጎትን ብቻ ተገን አድርጎ ባለመንቀሳቀስ፣በቤተክሕነቱ ውስጥ ከነቀዙ ግለሰቦች በተጓዳኝ አያሌ ቅን አባቶች ስላሉ ለእነሱ በመጨነቅ፣በንግግር ሊፈቱ የሚችሉና የመፈታት እድላቸው ተሟጡዋል ለማለት እጅግ ገና ብዙ የሚቀራቸውን ከላይ የጠቀስከውን ደብር አለመግባባት አይነት ገጠመኞች ባለማባባስ በኃላፊነት መንፈስ ብትጽፍ ደስ ይለኛል፡፡ችግር በማራገብና አንዱን አካል ብቻ ነጥሎ በመውቀስ ቤተክሕነቱ የሚቃና ቢሆን ኖሮ የአንተን ብሎግ ጨምሮ ፕሬሱና ማኅበራዊ ሚዲያው ለሁለት ዐሰርት ዓመታት የሰነዘሩት ወቀሳ ብቻ ለቤተክሕነት ክንፍ ያበቅልለት ነበር፡፡ስለዚህ ስንተች በስክነትና በሚዛናዊነት ቢሆን ደስ ይለኛል፤ያለበለዚያ አድማጩም ልማዱ ነው ብሎ በግራው ሰምቶ በቀኙ ያፈሰዋል፡፡እውነትም በቤተክሕነት እንደተሰቀለች ዳግም በቨርጊኒያ ትሰቀላለች፤ምክንያቱም ግራቀኝ አይቶ ፍርድ የሚሰጥ የለም፤ሁሉም የፈረጀውን አካል ለመስቀል ሚስማርና መዶሻ ይዞ ነው የሚጓዝ፡፡መፍትሄ ሳይሆን መርዶ ነጋሪ በዛ፡፡ለተፈጠረው ችግር አረጋጊ ሳይሆን አረግራጊ በረከተ፡፡አፈ-ሊቃውንት በዙ፡፡የሁሉም ማጠንጠኛ እኛ ያልነው ካልሆነ ቤተ ክርስቲያን ትፈርሳለች፤ፈርሳለች ነው፡፡መፍትሄ ጥቆማ የተለየው እሮሮ ይሰለቻል፡፡እሹሩሩ በሉኝ፤እኔ ብቻ ጻድቅ ብሂል ይጎመዝዛል፡፡የሰላም ተስፋው ያልተሟጠጠ የአንድ አጥቢያ ችግርን ተጠቅሞ በዚህ መጠን ሀገራዊ ሟርት መጥራት ያሳዝናል፡፡ደብሩ በውግዘት አልተለየ፤የአገልጋዮቹ የቤተክርስቲያን ልጅነት አልተገፈፈ፤ክሕነታቸው አልተነካ፤ይሄ ሁሉ የተጋነነ ምላሽ ከየት መጣ!ወይስ የተወሰኑ ስብስቦች ያሉበት አጥቢያ ከሌላው አጥቢየ የተለየ ጥበቃ ይደረግለታል!ወይስ ዲያቆን ዳንኤል ለጉባኤ በየዓመቱ የሚጠራበት ደብር ስለሆነ ጉዳዩ በተለየ ዐይን መታየት አለበት!ተው እንጂ ጎበዝ፤ሚዲያውን ተቆጣጥራችሁ በአንድ አይነት ቅኝት እየቃኛችሁ እውነትን ዳግም በድምጽ ብልጫ አትስቀሏት፡፡ተሸቀዳድሞ ራስን ክርስቶስ ማድረግ ያስተዛዝባል፡፡ሊፈታ የሚችልን የአንድ የዲያስፖራ ቤተክርስቲያን አጥቢያ አለመግባባት በዚህ ልክ አስፋፍቶ ሀገራዊ መከራ መጥራት መሰለ፤የተቀናጀ አካሄዳችሁ፡፡ደስ አይልም፡፡ዝግ በሉ፤መፋጠን ሲበዛ መፍትሄ ትቀጥናለች፡፡የቤተክርስቲያንን ክፉ አያሰማን፤አሜን፡፡

  ReplyDelete
 28. Ybel! Kale hiwot yasemaln, mengste-semayat yawurslin!

  ReplyDelete
 29. ዴንበር መድሃኔዓለም መእመናን መለየት ኣልነበረባቸውም .... ግን ተለዩ ይህም እውነት ሲሰቀል... በመከራ ግዜ መካድን ያመለክታል....ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል ነገር ግን... ምክንያት ቤተክርስትያንን ለመክዳት ብቁ ኣይሆንም ምናልባት ደግሞ አዛ ያሉ መሪዎች ነን ባዮች ኣታልዋቸው እንጂ መእምናኑ ሁሉም እንደማይሄዱ እርግጠኛ ነን.... ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ሂወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 30. በእውነት የሚያረካ መልእክት።

  ReplyDelete
 31. Hiyente Abewuki Tewoldu Leki Dekik......yiluhal yehe new. Woadite amlak tatsinah.

  ReplyDelete
 32. Amen amen amen Qali hiwot yasemalin egizabihir yageligilot zemenikin abizito yichemirilihu

  ReplyDelete
 33. Whatever it is I am very disappointed by your comment. By my perspective you have accesses to meet, to call or email to Abune Matias so you shouldn’t give this kind of comment in public. He is our church leader so we have to give him respect. As you know that it is not easy to manage the all churches around the world. At this movement all of our leaders have big influence from current government so we have to pray for them instead of criticize on public. I know Abune Matias and Sereke Brhan, they work for government not for church or God but we have to pray for them again and again.

  ReplyDelete
 34. የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚያረጋጋና የሚያፀና አሥተማሪ መልእክት ነውና እግዚአብነብሔር ይባርክህ ፣ በእውነተኛው አገልግሎትህ ያጽናህ፤ ያቆይልን።
  የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም አባቶች አገልጋዮችና ምእመናን እናንተን እኔ ማሳሰብ ባይገባኝ የተሰጣችሁን ምክር ተቀብላችሁ በመንበሯ ሳትለቁ በእምነታችሁ ፀንታችሁ ቁሙ። እኔ እናንተን የማውቃችሁ የዛሬ ገ 8 ዓመትና ለዴንቨር አዲስ ሆኘ ነው። አገልግሎታችሁንና እምነታችሁን ከመፈፀማችሁ ሌላ የሰራችሁት የለምና የሆነው ልብን የሚሰብር ቢሆንም በመስቀልሞቶ ያዳነን ከዚህ በላይ ተቀብሎ ነውና ተጽናኑ።
  ለአባ ማትያስ፦ ለመሆኑ ምን ይሆን ጥፋታቸው አባ እረኛ
  ተብለው ከመንጋው ለይተው ለተኩላ ለመስጠት ያስጨከነዎት? ለአዳናቸው ጌታ ታምነው ስላገለገሉ? የህይወትን ቃል እውነተኛውን የቤተክርስቲያኗን እምነት ስላስተማሩ? እኛ ከክርስቶስ ነን እንጂ ከንትና ዘር ከሚባል አይደለንም ስላሉ? በባእዳን አገር እንቅልፍ እረፍት አጥተው ያገኟትን ለእምነታችን ፤
  ለቤተክርስቲያናችን ብለው በመስጠታቸው? የቤተክርስቲያኗ አባቶችና አገልጋዮች ወገናቸውን በሰው አገር በቃሉና በአገልግሎት እያረሰረሱ በማጽናናታቸው? ላጡ ለተቸገሩ ቤተክርስቲያ እንዳስተማረቻቸው ያቅማቸውን በሠርዳታቸው? የቤተክርስቲያኗን ህንፃ ከእዳ በማውጣታቸው? እረ ምን ይሆን ንገሩ አባ? የያዙት መስቀል የተመረኮዙት በትር ምን ይሆነ የተፈፀመበት ለእርስዎ?
  አባ፦ አሳምመውን ብቻ አይደለም የሔዱት አድምተውን እንጂ። የውሃ እንባ አይደለም ያስነቡን የደም እንባ ጭምር እንጂ። ያባረሩትና የገፉት ልጆችዎን ብቻ አይደለም የሞተለወትን መድኀኔዓለምን ጭምርእንጂ። እኔስ ለሥራ በመድኀኒዓለም ደጅ ባለፍ ቁጥ እንባየ ይቀድመኛል። የቤተክርስቲያንና የእውነተኞች መከራ እየታሰበኝ። እውነት ህሊናዎ እረፍት አግኝቶ ይሆን? የአገር ቤቱ ድጊትዎ ቁሥል ሳይሽር ሌላ ሁለተኛ የሚያቆስልና የቆሰለውን የሚመረቅዝ ሥራ ሰሩ። እውነት የተጠሩለት አላማ ምድራዊ ነው ወይስ ሰማያዊ። ገንዘብ በዶላር ቀይረው ላኩልን ብለው አላስጨነቁዎት ፤ ለምን ገፈተሯቸው?

  ReplyDelete
 35. ቃለ ህይወት ያስማልን.

  ReplyDelete
 36. SO VERY TRUE!!!Thank you for this insightful article.

  ReplyDelete
 37. "ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ብለው፣ ክብራቸውንም ትተው የአንበሳ ደቦል፣ የዝሆን ግልገል፣ የወርቅ እንከብል ይዘው እስክንድርያ ድረስ ጳጳስ ለማምጣት የደከሙትን ድካም እናስባለን፡፡"
  ቃለ ህይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 38. ዕለተ ዓርብ ያልፋል፡፡

  ReplyDelete
 39. ዕለተ ዓርብ ያልፋል፡፡ የቀያፋ ድንፋታ፣ የሐናም ኩራት ያከትማል፡፡ የተቀበረው እውነት ይነሣል፡፡ የሄሮድስና የጲላጦስ ማኅተም ይፈታል፡፡ የሸሹ ሐዋርያት ይመለሳሉ፤ የካደው ጴጥሮስ ንስሐ ገብቶ ይመጣል፡፡ የሸጠው ይሁዳም ተቀስፎ ይሞታል፡፡ ያን ጊዜ በመስቀሉ ግርጌ እውነት ስትሰቀል ከእውነት ጋር የቆመው ዮሐንስ ‹ሞትን ከማይቀምሱት ወገን› ይሆናል፡፡ የዓርብን ግርግር፣ የቅዳሜን ጸጥታ በትእግሥትና በጽናት የሚያልፍ ዮሐንስ ከተገኘ - አላውቅም ካለው ከጴጥሮስ ጋር ሆኖ ትንሣኤውን ለማየት ወደ መቃብሩ ይጠራል፡፡

  ReplyDelete
 40. What the patriarch did was disgusting and worldly assertion. He cannot disown any Christian from the Church. Nevertheless, all these things are happening because, we do not want to read the Bible and follow what Jesus is telling us. I beg all of you, my fellow Tewahido Christians including Dn Daniel himself to read Galatians chapter 1-6. If possible, please study the Gospel/book of John.The reason for all these animosity and ungodly fight is because we rejected Jesus and resorted to worshiping human beings who gave their precious lives for our Lord. I know that you would want to kill me because of this truth. That was what I used to say before starting reading the Bible. No sibket from Pente! believe me! Why should I want anybody to convince me, other than the Bile, that Jesus is the only way and we are saved by his precious blood and His Grace? Please, my dear souls do not hesistate, read the Bible! Some people do not want to read the Bible because they think that "enesasatalen". This is from the devil. You will get the Truth in the Bible and Peace too. May our Lord Jesus Christ lead to this TRUTH, Amen

  ReplyDelete
  Replies
  1. U stupid, daughter of Lucifer..shut ur mouth...anchin bilo astemari

   Delete
 41. God bless you Dani.....you are the one who has been teaching us without hesitation!!!

  ReplyDelete
 42. ክርስትና ለእውነት መቆም ሃሰትን መቃወም ነውና አምላክ ይጠብቅህ

  ReplyDelete
 43. It is really surprising to see why those priests who serve at the church didn't realize the importance of this. God bless you more!!!

  ReplyDelete
 44. Well Said D/n Daniel. "ይህ ዘመን እውነት የተሰቀለችበት ዘመን ነው፡፡ በእናት ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ አንዳንድ አባቶችና አገልጋዮች ራሳቸው አንዲቷን ቤተ ክርስቲያን ሊያፈርሱ ሲሠሩ፤ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ከሚጋደሉት ይልቅ አፍራሾቹ የቤት ልጆች ሲሆኑ፣ ከአማኞቹ ይልቅ ከሐዲዎቹ፣ ከጽኑዐኑ ይልቅ መናፍቃኑ በር ሲከፈትላቸው፣ ከልጆቿ ይልቅ ጠላቶቿ ሲሾሙ ‹እናት ቤተ ክርስቲያን› ብሎ መጋደል በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ እንደተገኘው እንደ ዮሐንስ መሆን ነው፡፡ እውነት ስትሰቀል ከእውነት ጋር መቆም፡፡"

  ReplyDelete
 45. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡፡
  ለልብ ሐሴት የሚሰጥ፤ መንፈስን የሚያድስ፤ የነብስ ምግብ መገብከን፡፡
  እግዚአብሔር ጸጋዉን እንደ አባቶቻችን አብዝቶልኃልና ደስ ይበልህ፡፡ የአባቶቻችን አምላክ እድሜው ና ጥበቃው ይስጥህ፡፡

  ReplyDelete
 46. የሰላም ተስፋው ያልተሟጠጠ የአንድ አጥቢያ ችግርን ተጠቅሞ በዚህ መጠን ሀገራዊ ሟርት መጥራት ያሳዝናል፡፡ደብሩ በውግዘት አልተለየ፤የአገልጋዮቹ የቤተክርስቲያን ልጅነት አልተገፈፈ፤ክሕነታቸው አልተነካ፤ይሄ ሁሉ የተጋነነ ምላሽ ከየት መጣ!ወይስ የተወሰኑ ስብስቦች ያሉበት አጥቢያ ከሌላው አጥቢየ የተለየ ጥበቃ ይደረግለታል!ወይስ ዲያቆን ዳንኤል ለጉባኤ በየዓመቱ የሚጠራበት ደብር ስለሆነ ጉዳዩ በተለየ ዐይን መታየት አለበት!ተው እንጂ ጎበዝ፤ሚዲያውን ተቆጣጥራችሁ በአንድ አይነት ቅኝት እየቃኛችሁ እውነትን ዳግም በድምጽ ብልጫ አትስቀሏት፡፡ተሸቀዳድሞ ራስን ክርስቶስ ማድረግ ያስተዛዝባል፡፡ሊፈታ የሚችልን የአንድ የዲያስፖራ ቤተክርስቲያን አጥቢያ አለመግባባት በዚህ ልክ አስፋፍቶ ሀገራዊ መከራ መጥራት መሰለ፤የተቀናጀ አካሄዳችሁ፡፡ደስ አይልም፡፡ዝግ በሉ፤መፋጠን ሲበዛ መፍትሄ ትቀጥናለች፡፡የቤተክርስቲያንን ክፉ አያሰማን፤አሜን፡፡

  ReplyDelete
 47. Sewuyewu yemichalu Aymeslum.Yeigziabiher iji yegebu gize gin Yemaytekim chuhet yihonibachewal.Tishalin sedije tibisin agebahu ale yehagere sewu

  ReplyDelete
 48. yih legna tilk timhirt new kale hiwot yasemalin

  ReplyDelete
 49. That's why I admire you Dani, always in time.

  ReplyDelete
 50. ባለ ሥልጣኖቿ የሚሠሩት ስሕተትና ጥፋት ያሳዝነናል፤ ግን ተሥፋ አያስቆርጠንም፣ ያስለቅሰናል፣ ግን ከመንገድ አያስቀረንም፡፡ ከጥፋታቸው እንጂ ከአንድነቷ አያስወጣንም፣ እንደ ሸረሪት ቤታችን ሲቃጠል ትተን የምንጠፋ ሞኞች አይደለንም፡፡ ልጆቿ ነንና መከራዋን አብረን እንሳተፋለን፤ እንደ ባዕድ ባወጣ ያውጣሽ አንላትም፡፡ ድግስ እንደተጠራ ሰው ሲስተካከል ጥሩን ብለን ትተን አንሄድም፤ እንዲስተካከል በኣት አጽንተን እንጋደላለን እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 51. There is no true father in our church who keeps his sheep(chrstian) from wolves.Orthodox church is administered by the TPLF man Abay Tsegaye.Whatever Aba Pawlos or Aba Matias are the servant of the racist TPLF.They are not trusted by the Orthodox believers rather they are elected by TPLF.They were TPLF fighters and we know that they are not religious leaders. Currently several hundreds of people are killed in Oromia and still it is happening; but they didn't say nothing about this mass killing of people by TPLF racist regime.Whatever the people belifs Chrstian,Muslim,phagan,..they are human beings.People killed in Gondar too,but what Aba Matias said about this? Nothing.If he is not stand for People why we are administered by him? Why His name is called in our Church during our praying(kidasie)? Even the Seinod in America are fulfilled by protestants and by renaissance activists.Therefore,we do not have "TRUE LEADERS" who stand for truth and to sacrify his life for his mission.Untill then we believe in one truth religion The Orthodox Tewahido Church and we pray to be given true fathers from Almighty God and we stay strongly in hope.

  ReplyDelete
 52. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲያቆን::

  ReplyDelete
 53. ያው ከማቅ የፈለቅህ ነህና ሁሉ ጊዜ ሚዛናዊ ነገር ትፅፋለህ ብየ አልጠብቅም መፃፍ ስለምትችል ብቻ ፃፍ እውነት ግን ይት እንዳለች ትታወቃለች ዳኒ

  ReplyDelete
 54. አባቶቻችን‹እስክንድርያ እናታችን፣ ማርቆስ አባታችን› ብለው ለ1600 ዓመታት ሲኖሩ በመንበረ ማርቆስ ሥር መቆየታቸው 'ይምጽኡ ተናብልት እምግብግብጽ ኢትዮጵያ ታበጽህ ዕደዊሃ ሃበ እግዚአብሔር' የተባለው የዳዊት ትንቢት ስላለ እንጂ በ1600 ዓመት ውስጥ በኢትዮጵያ የተነሡት ቅዱሳን ኢትዮጵያ የራስዋ ጳጳስ እንዲኖራትና ከግብጽ ጳጳስ እንዳይመጣ ማድረግ አቅ~ቸው አይደለም፡፡ያ እንደስህተት እየተወሰደ ያለው የ1600 ዓመት የግብጻውያን ጳጳሳት አሰተዳደር ዘመን ካሁኑ ዘመን እንደሚሻል መገንዘብ ይቻላል፡፡በዚያ ዘመን መናፍቅ አልነበረም አሁን እንደአሸን ነው፤ሌላም ብዙ ነጥብ ማንሳት ይቻላል፡፡ሌላው የአሁኑ ዘመን ችግር የቋንቋ ጉዳይ ነው፡፡ ቤ/ክ የራስዋ እድሜ ጠገብ ቋንቋ/ግእዝ/ አላት፡፡ልጆችዋን ይህን ቋንቋ አሰተምራ ቋንቋውን ከማሳደግ ይልቅ በአጼው ዘመን የተደረገው ሁሉንም የቤ/ክ መጻሕፍት ወደ አማርኛ መተርጎም/ቅዳሴው ሁሉ÷መልካ መልኩ ሁሉ/፤ይህም የግእዝን ቋንቋ ማዳከሙና በዚህ ዘመን የተነሳው የብሔረተኝነት በሽታና የአማርኛ ቋንቋ ጥላቻ ያደረባቸው በየብሔረሰቡ ያሉ ጽንፈኞች ተነስተው ቤ/ክ የአማራ ናት ወደሚለው ድምዳሜ መደረሱ፤ይህን ችግር ለመቅረፍ በሁሉም ቋንቋ የቤ/ክ መጻሕፍት እንዲተረጎሙ ወደ ማስገደድ እየተሄደ ነው፡፡ቤ/ክ የራስዋን ግእዝ ብታስፋፋ ኖሮ ልጆችዋ በብሔር ባልተከፋፈሉ፤የወንጌል ትምህርት በየቋንቋው መሠራጨቱ አስፈላጊና ከሐዋሪያት የወረደ ነው፡፡ ግን ቤ/ክ አንድ ማእከላዊ መግባቢያ ቋንቋ ሊኖራት ያስፈልጋል

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቋንቋ መግባቢያ ነዉ! ከመልእክቱ ወጥተህ ምን ያንኳኳሃል

   Delete
 55. ዳኒ ምን እንላለን እዳለው ነው ሐዋርያው እና እኔም የምለው የለም እ/ግ አምላክ ይባርክህ ቃል ኪዳንህን ሐይማኖትህን አጥብቀሃታልና በዚሁ ቀጥል ትጥቅህን አጥብቅ።አንተን እነርሱ የቀረጽ ህ አአባቶችህና ወንድም እህቶችህ እነሱን መስለው ሐይማኖትህን ለቤተክርስቲያንህ ጠበቃ እድትሆናት ሲያማት ልትታመም ስትደሰት እድትደሰት ነውና አሁን እዛ ላይ ነው ያለከው መከራዋ አልቆ የደስታዋን ቀን እድታይ እመኛለሁ።እኛማ እናዝናለን እናለቅስም አለን ህመሟን የምትገልጽበት የጦር አቃ የሆነው ቃላትህ እደጦር ይዋጋናል ሰርሰሮም ገብቶ ያደማናል እሄንን ጊዜ እድናይና እድንሰማ የትቢት መፈጸሚያ ልጆች ሁነናል እሄንን ሳያዩ ያለፍት ምንኛ የታደሉ ናቸው ።ሞት በልመና አይገኝም እጂ መሞት መልካም ነበር ቤተክርስቲያናችን እደ ዩሐንስ አይነቶች ሳ ይሆኑ ሌሎች ከበዋት ከማየት ።አንተን እ/ግ ያጽናህ።ቸር ይግጠመን ከበላይ ነኝ።

  ReplyDelete
 56. ዕለተ ዓርብ ያልፋል፡፡ የቀያፋ ድንፋታ፣ የሐናም ኩራት ያከትማል፡፡ የተቀበረው እውነት ይነሣል፡፡ የሄሮድስና የጲላጦስ ማኅተም ይፈታል፡፡ የሸሹ ሐዋርያት ይመለሳሉ፤ የካደው ጴጥሮስ ንስሐ ገብቶ ይመጣል፡፡ የሸጠው ይሁዳም ተቀስፎ ይሞታል፡፡ ያን ጊዜ በመስቀሉ ግርጌ እውነት ስትሰቀል ከእውነት ጋር የቆመው ዮሐንስ ‹ሞትን ከማይቀምሱት ወገን› ይሆናል፡፡

  ReplyDelete
 57. የጠመጠመ ሁሉ ቄስ አአይደለም።መስቀል የጨበጠ ሁሉ ካህን አይደለም።ሁሉ ከፍሬው ይታወቃል።ዘመኑን ዋጁ

  ReplyDelete
 58. የጠመጠመ ሁሉ ቄስ አአይደለም።መስቀል የጨበጠ ሁሉ ካህን አይደለም።ሁሉ ከፍሬው ይታወቃል።ዘመኑን ዋጁ

  ReplyDelete
 59. "መንበሯ ከርእሰ መንበሯ በላይ ነው፡፡ ሲኖዶሷም ከአባላቷ በላይ ነው፡፡ ... እርሷ ‹መልዕልተ ኩሉ› ናትና፡፡
  ባለ ሥልጣኖቿ የሚሠሩት ስሕተትና ጥፋት ያሳዝነናል፤ ግን ተሥፋ አያስቆርጠንም፣ ያስለቅሰናል፣ ግን ከመንገድ አያስቀረንም፡፡ ከጥፋታቸው እንጂ ከአንድነቷ አያስወጣንም፣ እንደ ሸረሪት ቤታችን ሲቃጠል ትተን የምንጠፋ ሞኞች አይደለንም፡፡"

  ReplyDelete
 60. ቃለ ህይወት ያሰማልን! አሜን!

  ReplyDelete
 61. Our Church for a time being is fallen under TPLF regime.The Church is ruled by " Abune Abay Tsegaye". Abune Mathias is better to have one of the ministry position of TPLF. I heard his speech as he will ban and disintegrate those who are serving the church voluntarily. That is not expected from him to do such kinds of evil words. By the way is he really the follower of Orthodox Tewahido Church? I don't think so.He is one of the wings of "TEHADSO". It is not sin to tell the truth. Anyways we will see his final destination. Till then may Almighty God with all of us.

  ReplyDelete
 62. ቃለ ሕይወት ያሰማልን
  +++ዕለተ ዓርብ ያልፋል፡፡ የቀያፋ ድንፋታ፣ የሐናም ኩራት ያከትማል፡፡ የተቀበረው እውነት ይነሣል፡፡ የሄሮድስና የጲላጦስ ማኅተም ይፈታል፡፡ የሸሹ ሐዋርያት ይመለሳሉ፤ የካደው ጴጥሮስ ንስሐ ገብቶ ይመጣል፡፡ የሸጠው ይሁዳም ተቀስፎ ይሞታል፡፡ ያን ጊዜ በመስቀሉ ግርጌ እውነት ስትሰቀል ከእውነት ጋር የቆመው ዮሐንስ ‹ሞትን ከማይቀምሱት ወገን› ይሆናል፡፡

  ReplyDelete
 63. God Bless You! No any evil power affects our church! It is only temporary and will pass like a shadow and cloud!

  ReplyDelete
 64. በዚህ ጊዜ እንደ ዮሐንስ የሚጸና ብጹዕ ነው፡፡

  ReplyDelete
 65. እግዚአብሔር ይባርክህ

  ReplyDelete
 66. Daniye You nailed it!! Thank you Brother you are a voice for this voiceless generation.

  ReplyDelete
 67. thanks a lot.
  May God be with all us!!

  ReplyDelete
 68. አቤቱ እኔና አባቴ ቤት በድለናለና ይቅር በለን!

  ReplyDelete
 69. መዳህኒዓለም እድሜህን ያርዝመው!!!

  ReplyDelete
 70. Tswaw memulatu ayikerm. Egziabher bezih zemen ewnetn kehaset yemnleyibetn mastewalun yadilen.

  ReplyDelete
 71. if our church were able to be destroyed, it would had been in the time of Italian invasion.But there will be many Christians who will be crucified for it.Otherwise no one can perished it. God look after it. And God is the King of kings.

  ReplyDelete
 72. ዘመንህን ጌታ ያርዝመው፡፡

  ReplyDelete
 73. MayGod bless you with all his blessings!!!!

  ReplyDelete
 74. ቃለ ህይወት ያሰማልን! አሜን!

  ReplyDelete