Tuesday, December 8, 2015

ኢዛናና የነገረ ክርስቶስ እምነቱ

በኢትዮጵያ ታሪክ ክርስትናውን በይፋ ያወጀው ንጉሥ ኢዛና ነው፡፡ ኢዛና ክርስትናውን በይፋ በማወጅ ብቻ ሳይሆን በድንጋይ ላይ የጦርነት ታሪኩን መዝግቦ በማቆየትም ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን የታሪክ ሊቃውንት በኢትዮጵያ ክርስትና የተሰበከበትን ጊዜ ከ4ኛው መክዘ ቢጀምሩትም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ግን ከጃንደረባው መጠመቅ አንሥተው ይቆጥሩታል፡፡
በኢትዮጵያ የክርስትና ትምህርት ቀደም ብሎ የተጀመረ ቢሆንም ኦፊሴላዊ እምነት የሆነውና መሠረት ባለው ጽኑ ዐለት ላይ የተተከለው ግን በ4ኛው መክዘ የፍሬምናጦስን ስብከትና ሹመት፣ የኢዛናንም ወደ ክርስትና መመለስ ተከትሎ ነው፡፡ ንጉሥ ኢዛና ከክርስትና ጋር የነበረውን ታሪክ በተመለከተ የሚነግሩን አራት ዓይነት የድንጋይ ላይ ጽሑፎች አሉ፡፡ ሁለቱ በግሪክና በግእዝ፣ ሦስተኛው በግእዝ ብቻ፣ አራተኛው ደግሞ በግሪክ ብቻ የተጻፉ ናቸው፡፡
የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ኢዛና በመንግሥቱ ላይ ያመጹ ሕዝቦችን(ቤጃዎችን) ለመውጋት ያደረገውን ዘመቻ የያዙ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ሲሆኑ ሁለቱ ጽሑፎች[1](ግሪኩና ግእዙ) ተመሳሳይ ሐሳብ ያላቸው ናቸው፡፡ ይሄ የኢዛና የድንጋይ ላይ ጽሑፍ በአንዱ ገጽ በግሪክ የተጻፈ ሲሆን በሌላው ገጽ ደግሞ በግእዝና በሳባውያን(ግእዝን በሳባውያን ፊደል) የተጻፈ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ላይ ኢዛና በአምልኮ ጣዖት ውስጥ እንደነበረ ያሳያል፡፡ ራሱንም የሚጠራው ‹ወልደ መሕረም ዘኢይትመዋዕ ለጸር - ለጠላቱ የማይደፈረው የመሕረም ልጅ› ብሎ ነው፡፡ ሦስተኛው የድንጋይ ላይ ጽሑፍ በኖባ ሕዝቦች ላይ ስለተደረገው ዘመቻ የሚገልጥ ሲሆን[2] በዚህ ጽሑፍ ላይ ኢዛና አምላኩን የሚጠራው ‹በኀይለ እግዚአ ሰማይ፣ ዘበሰማይ ወምድር መዋኢ - በሰማይና በምድር አሸናፊ በሆነው በሰማዩ ጌታ ኀይል› ብሎ ነው፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ‹በኀይለ እግዚአ ኩሉ - የሁሉ ጌታ በሆነው ኀይል› ይለዋል፡፡

ኢዛና ይህንን የድንጋይ ላይ ጽሑፍ ባስጻፈበት ጊዜ በአንድ አምላክ ወደማመን መጥቶ እንደነበር አምላኩን የጠራበት አጠራር አመላካች ነው፡፡ በዚህ የድንጋይ ላይ ጽሑፍ ‹እግዚአ ሰማይ› የሚለው ሰባት ጊዜ ተጠቅሷል[3]፡፡ ‹አረስ/ ማሕረም› የሚለው ስም እዚህኛው ጽሑፍ ላይ የለም፡፡ በሌላ በኩልም ደግሞ ‹እግዚአብሔር› የሚለው ስምም አልተገለጠም፡፡ በኋለኛው የድንጋይ ላይ ጽሑፍ የምናገኘው ስመ ሥላሴም አልተገለጠም፡፡ 
ሊቃውንቱ ይሄኛው የድንጋይ ላይ ጽሑፍ ሲጻፍ ኢዛና የነበረው አምልኮ ‹በአንድ አምላክ ማመን› መሆኑን ቢስማሙበትም ‹ማንን› የሚለውን በተመለከተ ግን ልዩ ልዩ ሐሳብ አላቸው፡፡ ኮንቲ ሮሲኒ፣ አንቶኒዮ ጉይዲ፣ ሥርግው ሐብለ ሥላሴና ባይሩ ታፍላ በዚህ ጊዜ ኢዛና ክርስትናን ተቀብሏል የሚለውን ሐሳብ ሲቀበሉ ሌሎቹ ግን ክርስትናን የሚያመለክት ነገር የለውም ብለው የተለያየ አመለካከት ሰንዝረዋል፡፡ ሩሲያዊው ዩሪ ኮቢችቻኖቭ በደቡብ ዓረቢያ ከነበሩት ‹በአንድ አምላክ ማመን›ን ከሚመስሉ እምነቶች ጋር ሲያያይዙት ኤ.ዜድ. አስኮሊ ደግሞ ኢዛና ይሁዲ ሆኗል ብለዋል፡፡ ኤፍሬም ይስሐቅ ‹እግዚአ ሰማይ› የሚለው አጠራርና በኋላ ዘመን ኢዛና በሳንቲሞቹ ላይ የተጠቀማቸው መስቀሎች በኢትዮጵያ ለሚታየው ብሉይ ኪዳን ጠቀስ ለሆነው ክርስትና ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ሥርግው ሀብለ ሥላሴ ስለ ጥንታዊና መካከለኛው የኢትዮጵያ ታሪክ በጻፉት መጽሐፍ ላይ ይሄ የኢዛና ገለጻ ክርስትናን ንጉሡ መቀበሉን የሚያመለክት ነው ይላሉ፡፡ ‹የአሬስ/መሕረም ልጅ› የሚለውን ትቶ ‹በኃይለ እግዚአ ሰማይ - በሰማዩ ጌታ ኀይል› ማለቱ በሀገሪቱ የመጣውን የሃይማኖት ለውጥ የሚያመለክት ነው ብለዋል[4]፡፡ ኢዛና ይህንን ባስጻፈበት ዘመን ክርስትና ቢሰበክም ነገር ግን ሃይማኖትን የሚገልጡ መግለጫ ቃላት ገና ያልዳበሩበት ጊዜ ይሆናል፡፡ ኢዛና በአንድ የድንጋይ ላይ ጽሑፍ ሰባት ጊዜ ‹የሰማይ ጌታ› እያለ መግለጡ በክርስትና ወሳኝ የሆነውን በአንድ አምላክ የማመን ነገር ማጽናቱ መሆኑን የሚገልጡ ሊቃውንት አሉ[5]፡፡
ከኢዛና የድንጋይ ላይ ጽሑፍ ክርስትናን በተመለከተ ወሳኝ የሚባለው አራተኛው የድንጋይ ላይ ጽሑፍ ነው፡፡ ይህ የድንጋይ ላይ ጽሑፍ የተገኘው በቅርቡ ሲሆን የተጻፈው በግሪክ ነው፡፡ የድንጋይ ላይ ጽሑፉን ያገኙት አለቃ ዘሩ ገብረ እግዚእ ሲሆኑ በአኩስም እንዳ ስምዖን በተባለ ቦታ ቤት ለመሥራት ሲቆፍሩ ነው፡፡ ነገሩ ከተሰማ ቤት እንዳልሠራ እከለከላለሁ ብለው ያሰቡት አለቃ ነገሩን በምሥጢር ይዘውት ቆይተው ነበር፡፡ በኋላ ሲያርፉ ግን ሐውልቱ ወደ አኩስም ጽዮን እንዲዛወር ሐሳብ ነበራቸው፡፡ እርሳቸው በ1961 ዓም ሲያርፉ በግንቦት 1962 ጉዳዩ ወደ አርኬዎሎጂስቶች ዘንድ ደርሶ ሊታወቅ ችሏል፡፡ ሐውልቱ በጀርባው በኩል በሰባውያን ፊደል የተጻፈ ጽሑፍ ሲኖረው በጽሑፉ መጨረሻ የመስቀል ምልክት ተቀርጾበታል፡፡
የድንጋይ ላይ ጽሑፉ ሲጀምር እንዲህ ይላል፡-
በእግዚአብሔር ባለ እምነት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ መንግሥቴን ባዳነልኝ በእርሱ፡፡ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለኝ እምነት፣ በረዳኝ፣ ዘወትርም በሚረዳኝ›
ጥቂት እልፍ ብሎ ደግሞ ‹የአልሜዳ ልጅ፣ የክርስቶስ አገልጋይ› ይላል፡፡
ቀጥሎም ….‹ለእኔ ያደረገልኝን ታላላቅ ነገሮችን አንደበቴና ልቡናዬ ለመናገር የማይቻላቸው ናቸው፡፡ እርሱ ጠናካራና ኃያል አድርጎኛል፤ በማምንበት በልጁም በኩል አዲስ ስም ሰጥቶኛል፡፡ የመንግሥቴም ሁሉ ገዥ አድርጎኛል፤ በክርስቶስ ባለኝ እምነት የተነሣ፣ በእርሱ ፈቃድ፣ በክርስቶስ ኃይል፤ ምክንያቱም የሚመራኝ እርሱ ራሱ ነውና፤ በእርሱ አምናለሁ፤ እርሱ ራሱም መሪዬ ነው› ይላል፡፡
አለፍ ብሎ ደግሞ ‹…በእግዚአብሔር ክርስቶስ ኃይል ተነሣሁ፤ በእርሱ አምናለሁ፣ እርሱም ይመራኛል›› ይላል፡፡
ነገረ ሥላሴ
በዚህ የኢዛና የድንጋይ ላይ ጽሐፍ አሚነ ሥላሴና ትምህርተ ሥላሴ ከቤተ ክርስቲያኒቱ መመሥረት ጋር አንድ ሆኖ የተሰበከ ትምህርት መሆኑን ያሳያል፡፡ ኢዛና ‹በእግዚአብሔር ባለ እምነት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል› ብሎ ነው ጽሑፉን የጀመረው፡፡ ይሄ በስመ ሥላሴ ነገርን መጀመር በኋላ ዘመን የታወቀና የተረዳ ትውፊት ሆኖ የጸሎትም፣ የመጽሐፍም፣ የሥራም፣ የደብዳቤም መጀመሪያ ሆኗል፡፡ ነገሥታተ ኢትዮጵያ በጻፏቸው ደብዳቤዎች ሁሉ ይህንን ስመ ሥላሴ እናገኘዋለን፡፡  
ነገረ ክርስቶስ
ኢዛና በዚህ ጽሑፉ በክርስቶስ ላይ ያለውን እምነት በግልጽ አሳይቷል፡፡
1.      ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ‹በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለኝ እምነት፣ በረዳኝ፣ ዘወትርም በሚረዳኝ›
2.     ክርስትና የክርስቶስ አገልጋይነት ነው ‹የአልዓሜዳ ልጅ፣ የክርስቶስ አገልጋይ›
3.     ክርስቲያን የሆነው በልጁ በክርስቶስ በማመን ነው ‹በክርስቶስ ባለኝ እምነት የተነሣ፣ በእርሱ ፈቃድ፣ በክርስቶስ ኃይል፤ ምክንያቱም የሚመራኝ እርሱ ራሱ ነውና፤ በእርሱ አምናለሁ፤ እርሱ ራሱም መሪዬ ነው›
4.     ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው ‹በእግዚአብሔር ክርስቶስ ኃይል ተነሣሁ›
ኢዛና ክርስትናን የመንግሥቱ ሃይማኖት ያደረገው በአውሮፓና በእስያ በነገረ ክርስቶስ የተነሣ ከባድ ክርክር በነበረ ጊዜ ነው፡፡ በ325 ዓም የተወገዘው የአርዮስ ትምህርት ምንም እንኳን በጉባኤ ኒቂያ ቦታ ቢያጣም ቤተ መንግሥቱን እየቦረቦረ በመኳንንቱና በነገሥታቱ ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ ነበር፡፡ አርዮስ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር አይደለም፤ ከአብም ጋር በህልውናም ሆነ በአሪና አይተካከልም የሚል ትምህርት ነበረው፡፡ ከ332 ዓም ጀምሮም አርዮሳዊነት በባዛንታይን ቤተ መንግሥት በኦፊሴል ተቀባይነት አግኝቶ እስከ 378 ድረስ ዘልቆ ነበር፡፡ በኋላ ይሄው የኒቂያ ትምህርተ ሃይማት በ381 በጉባኤ ቁስጥንጥንያ እንዲጸና ተደረገ፡፡
በዚህ አርዮሳውያን የባዛንታይንን ቤተ መንግሥት በተቆጣጠሩበት ዘመን የኒቂያን ትምህርተ ክርስቶስ አቋም በማስጠበቅ ተጠቃሹ ሐዋርያ ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ (328- 373 ዓም) ነበር፡፡ በልጅነቱ እለስክንድሮስን ተከትሎ ወደ ኒቂያ በመሄድ በጉባኤው ተገኝቶ አርዮስን ተከራክሮታል፡፡ የጉባኤ ኒቂያ ጸሎተ ሃይማኖት የአትናቴዎስ ሥራ መሆኑን የሚገልጡም አሉ፡፡ ከኒቂያ መልስ በ3ኛው ዓመት የእስክንድርያን መንበር የተረከበው ቅዱስ አትናቴዎስ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው፣ ከአብና ከወልድ ጋር በእሪና የተካከለ ነው፤ በህልውናም አንድ ነው የሚለውን ትምህርት አጽንቶ ያስተምራል፡፡
ፍሬምናጦስ ጵጵስናን የተቀበለው ከአትናቴዎስ በመሆኑ የኒቂያን ትምህርተ ሃይማኖትና የአትናቴዎስን የምሥጢረ ሥጋዌ አቋም አጽንቶ ይዟል፡፡ ፍሬምናጦስ በትምህርተ ሃይማኖት በርትቶ ማስተማሩንና ለነገረ ክርስቶስ ትምህርት ከመጀመሪያው ትኩረት መስጠቱን በኢዛና ጽሑፍ እናየዋለን፡፡ ኢዛና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አጽንቶና ደጋግሞ ይናገራል፡፡ በተለይም ‹ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው› የሚለውን የአትናቴዎስን የነገረ ክርስቶስ እምነት በተረዳ ነገር መስክሯል፡፡
ኢዛና ሲጀምር ኃይልን ለአብ፣ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ነው የሰጠው፡፡ ይህም ወልድን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል አድርጎ የገለጠበት ነው፡፡ ክርስቶስንም ‹እግዚአብሔር ክርስቶስ› ብሎ ነው የገለጠው፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ እግዚአብሔር ወልድ እንጂ አርዮስ እንዳስተማረው ከእግዚአብሔር ያነሰ(ፍጡር) አለመሆኑን ሲመሰክር ነው፡፡ ስለ ኃይል በገለጠባቸው ሦስት አንቀጾች፡-
·         ‹በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል›
·         ‹በክርስቶስ ባለኝ እምነት የተነሣ፣ በእርሱ ፈቃድ፣ በክርስቶስ ኃይል›
·         ‹በእግዚአብሔር ክርስቶስ ኃይል ተነሣሁ›
መጀመሪያ ‹ኃይል› የሚለውን ለሥላሴ ሰጥቶ ተናግሯል፤ ቀጥሎ ለክርስቶስ ሰጥቶ ተናግሯል፣ በመጨረሻም ለእግዚአብሔር ክርስቶስ› ሰጥቶ ተናግሯል፡፡ በዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥላሴ አንዱ፣ በሥልጣን የተካከለ፣ የሚያመልኩት አምላክ መሆኑን የሚገልጥ ነው፡፡
በተለይም ኢየሱስ ክርስቶስን ‹እግዚአብሔር ወልድ፣ እግዚአብሔር ቃል፣ ጌታ እግዚአብሔር› ማለት እንጂ ‹እግዚአብሔር ክርስቶስ› ብሎ መጥራት የተለመደ አይደለም፡፡ እስካሁን በተገኙት በቅዱስ አትናቴዎስ ድርሰቶች ውስጥም ይሄ አገላለጥ የለም፡፡ የኢዛና ክርስቶስን ‹እግዚአብሔር ክርስቶስ› ብሎ መጥራቱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ከመጀመሪያውም ‹ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው› የሚለውን በትምህርት ይዘትነቱ ብቻ ሳይሆን በስም አጠራርም አጽንተው እንዳስተማሩት የሚያሳይ ነው፡፡
ይህንን የኢዛና የሃይማኖት መግለጫ አስደናቂ የሚያደርገው ሌላው ነጥብ ደግሞ በሮም ግዛት ውስጥ የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን የአርዮስን ትምህርት እንድትቀበል ከቤተ መንግሥቱ ግፊት እየተደረገባትና የኒቂያ ትምህርተ ሃይማኖት ጠበቃው አትናቴዎስ ከመንበሩ በተደጋገሚ እየተሰደደ እያለ ኢዛና ግን በመንግሥቱ ላይ የሚመጣውን ነገር ሁሉ ተቀብሎ በእምነቱ መጽናቱ ነው፡፡ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ከሮም ግዛት ውጭ ብትሆንም ዙሪያዋ ግን በሮም ተጽዕኖ ሥር ነበር፡፡ የንግድ መሥመሮቹንና ዋና ዋና የሀብት ምንጮችን ሮማውያን ነበሩ የሚቆጣጠሩት፡፡ ኢትዮጵያም አንደኛዋ የንግድ አጋሯ ሮም ነበረች፡፡ ይህ ሁሉ ግን ኢዛናን እምነቱን በይፋ ከመመስከር አላገደውም፡፡
ሌላው አስደናቂ ነገር ኢዛና ይህንን እምነት ሲያንጸባርቅ ቆስጠንጢኖስ 2ኛ ለኢዛናና ሳይዛና አትናቴዎስን የሚቃወምና አርዮስን የሚደግፍ ደብዳቤ ሁለት ጊዜ ልኮለት ነበር፡፡ በዚህ ደብዳቤ ላይ ፍሬምናጦስ ወደ እስክንድርያ ተመልሶ ከአርዮሳዊው ጳጳስ ከጊዮርጊስ እንደገና ጵጵስና እንዲቀበል የሚገልጥ ነው፡፡ አትናቴዎስንም ይከሳል[6]፡፡ ኢዛናና ሳይዛና ለዚህ የሰጡት መልስ አልታወቀም፡፡ በተዘዋዋሪ መንገድ ግን ኢዛና ባስጻፈው የድንጋይ ላይ ጽሑፍ የአርዮስ ትምህርት እንዳልተቀበለውና ለኒቂያ ጉባኤ ውሳኔና ለቅዱስ አትናቴዎስ ትምህርት ያለውን ጥብቅና ገልጧል፡፡  
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዚህ የኢዛና አቋም ባትጸና ኑሮ ይሄ አርዮስን የሚቃወመው የኢዛና አገላለጥ በኋላ ዘመን እንዲጠፋ በተደረገ ነበር፡፡ እንዲያውም ‹አርዮስ› ትምህርቱ ብቻ ሳይሆን ስሙ ሳይቀር የክፉ ነገር መግለጫ ሆኖ ነው የቀረው፡፡ ይህም ከ1400 ዓመታት በላይ ሥር የሰደደ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ሀገሪቱም እንኳን ፍሬምናጦስን መልሳ ወደ አርዮሳውያን ልትልከው ቀርቶ ‹ከሣቴ ብርሃን› ብላ ክብሩን ከፍ አድርጋ ገልጣዋለች፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላትን የጠራና የነጠረ ትምህርትና እምነት ይዛ እስከዛሬ እንድትዘልቅ አድርጓታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለስብከት ሲባል የምትጠራው ስም ሳይሆን ዋጋ የከፈለችበት አዳኟ ነውና፡፡ ይህንን ታሪኳንና ጠባይዋን የማያውቁ ብቻ ናቸው ‹ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አታውቀውም› የሚለውን የማይም ድፍረት የሚደፍሩት፡፡

የበለጠ ለማንበብ የዚህ ጽሑፍ ዋና ምንጭ የሆኑትን Stephen L. Black, In the Power of God Christ; Greek inscriptional evidence for anti- Arian of Ethiopia’s first Chrstian king. Bulletin of the School of Oriental and African Studies, University of London.Vl. 71.No.1(2008),pp. 93-110
Stephen Kaplan, ‘’ Ezana conversion reconsidered’’, Journal of Religion in Africa. Vol. 13, 1982

ያንብቡ

[1] Deutsche Aksum – Expedition 4 and 4 bis
[2] Deutsche Aksum – Expedition 11
[3] Stephen Kaplan, Journal of Religion in Africa, , 13, 1982, 103
[4] Ancient and Medieval Ethiopian History, 102
[5] Stephanie L. Black, “In The Power of God Christ”: Greek inscriptional Evidence for the Anti-Arian Theology of Ethiopia’s First Christian King, p.107
[6] Defense before Constantius.

46 comments:

 1. Thank you so much, God bless you and your family.

  ReplyDelete
 2. የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዚህ የኢዛና አቋም ባትጸና ኑሮ ይሄ አርዮስን የሚቃወመው የኢዛና አገላለጥ በኋላ ዘመን እንዲጠፋ በተደረገ ነበር፡፡ እንዲያውም ‹አርዮስ› ትምህርቱ ብቻ ሳይሆን ስሙ ሳይቀር የክፉ ነገር መግለጫ ሆኖ ነው የቀረው፡፡ ይህም ከ1400 ዓመታት በላይ ሥር የሰደደ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ሀገሪቱም እንኳን ፍሬምናጦስን መልሳ ወደ አርዮሳውያን ልትልከው ቀርቶ ‹ከሣቴ ብርሃን› ብላ "ኢየሱስ ክርስቶስ ለስብከት ሲባል የምትጠራው ስም ሳይሆን ዋጋ የከፈለችበት አዳኟ ነውና፡፡ ይህንን ታሪኳንና ጠባይዋን የማያውቁ ብቻ ናቸው ‹ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አታውቀውም› የሚለውን የማይም ድፍረት የሚደፍሩት፡፡"

  ReplyDelete
  Replies
  1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቶስን በሚገባ አታዉቅም ማለት ስሙን አትጠራም ማለት ሳይሆን መጽሃፍ ቅዱስ ባስተማረዉ መንገድ አታስተምርም ማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ መጽሃፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ፣እዉነት ሕይወት ስለሆነ ያለ እርሱ ኣብን ማየት እንደማይቻል ያስተምራል (ዮሀ 14፡6)፡፡ ኦርቶዶክስ ግን ማሪያምም፣ መላዕክትም፣ ፃድቃንም ወደ ኣብ ያዳርሳሉ ትላለች፡፡

   Delete
  2. Dear Anonymous, you have the wrong understanding of the bible. Please do not try to understand the bible your way

   Delete
  3. ተው ወንድም ይሄን የጨቅላ ትምህርት ልታስተምረን አትሞክር

   Delete
  4. Do you think the place of the son and the father different? I think you are very infant for the bible and Ethiopian orthodox church. Ethiopian orthodox church never say saints are ways, but she say they well lead towards the way (it is based on the bible). And you better ask and learn what does the way mean when the bible says Jesus is the way...

   Delete
  5. Endew Afer Betbela Yishaleh neber... Yefetari enatu wode fetari betaders men yidenkal...wodefetari kemadres ena fetarin kemewuled man yikebdal? beferenj tergum yedenezezezk... Felg Rasehn.

   Delete
  6. ቀጣይ…
   መጽሀፉን ከምንጩ የተረጎሙትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሰዎችን ጠይቅ፤ እዚህ ላይ ምን ለማለት ፈልጋችሁ ነው አልገባኝም በል፤ ምን ያሳፍራል አዋቂን መጠየቅ፡፡ አይ እኔ የግሪክ ወይ የእብራይስጥ፣ ወይ የእንግሊዝ መጽሀፍ ካልሆነ የኢትዮጵያን ቋንቋ ትርጉም አልፈልግም ልትል ታስብ ሆናል፤ ሆኖም ያገርህን ቋንቋ በቅጡ ሳይገባህ ሌላ ቋንቋ ይገባሃል ብየ እንዴት ልጠርጠር? በእርግጥ በመንፈስ ቅዱስ ረዳትነት የተጻፉ የኢትዮጵያ መጻኅፍት ላንተ ጭንቅላት አይስማሙም፡፡ ኢትዮጵያውያን ብቃት የላቸውም ብለህ ስለምታምን ጎበዝ የሆንክ ይመስልሃል፤ ራስህን ነው ምትሰድበው፡፡ ወደድክም ጠላህም ግን ኢትዮጵያዊ ነህ፤ እንዳንተ ያለ ሰው ኢትዮጵያዊ ባይሆን ግን ደስ ይለኝ ነበር፤ አንተም ኢትዮጵያዊ፣ ኢጥዮጵያዊው ጃንደረባም ኢትዮጵያዊ ትባላላችሁ፡፡ ኢትዮጵያውያን ማቴሪያሊስቶች ስላልሆኑ ከሀብት ይልቅ እውነትን መርጠው እስካሁን አቆይተውታል፡፡ እውነትን በገንዘብ ብዛት አትለካ፡፡ ለመደመጥ ወሳኙ ነገር ገንዘብ አይደለም፡፡ ለመደመጥ ወሳኙ ነገር እውነት ነው፡፡ እንደዛ ባይሆን ጌታችን ክርስቶስ በልጅነቱ ስደት አይወጣም ነበር፤ በስደት ክርስቶስ ከእናቱ ጋር ሲለምን ብታገኘው ምን ይሰማሃል፤ ደሃን የምትጸየፍ ከንቱ ሰው እርሱን ተጸይፈኃልና እውነት ካንተ በብዙ የራቀ ነው፡፡ እርሱ ግን ሁሉን ቻይ ስለሆነ እንደሰው ቀስ እያለ አደገ፤ እውነትን አስተማረ፤ ፍቅርን ሰበከ፤ ከድሆችና ከሀጥያተኞች ጋር ዋለ፣ ለሀብታሞችና ለባለስልጣኖች የሚጠቅማቸውን ነገራቸው፤ በስጋ የታመሙትን ፈወሳቸው፡፡ እምነትን በተግባር አስተማረ፤ በባህር ላይ እየተራመደ፡፡ ህዝብ ሁሉ ወደደው፣ ደሃም ሀብታምም፤ እርሱም ሁሉንም ይወዳቸዋል፤ የወደዱት ግን ሀብታምም ባለስልጣንም ስለሆነ አይደለም፤ እውነት ስለሆነ ነው፣ ፍቅር ስለሆነ ነው፡፡ ስለርሱ ብዙ ቢባልም አይገልጹትም፡፡ እውነትን የትም ፈልጋት፤ ስትፈልጋት ግን የተናቁ የተባሉ ቦታዎችን፣ የተናቁ የተባሉ ሰዎችን አትለፋቸው፤ ምናልባት እውነትን ተራምደህ አልፈህ እየሄድክ ነው፡፡ በየዋህ ልብ ከፈለካት ታገኛታለህ፤ በትእቢት ከሆንክ ግን በእርሷና በአንተ መካከል ያለው ለዘላለም እየሰፋ እየሰፋ እንተ ደሞ እየጠፋህ እየጠፋህ ትሄዳለህ፡፡ እኔ ክፉ አልመኝልህም፤ ከእውነት ያገናኝህ፡፡
   ቀጣይ…

  7. ያንተ አይነቱን አውቆም ሳያውቅም የተኛ ማንቃት እንዴት ይቸግራል… እምነት ቢጎልህ ሎጅክ እንኳን ቢገባህ እንዴት ጥሩ ነበር፡፡ ከፈጠሪ ጋር አብረው የሚዉሉ መላእክት፣ ከፈጣሪያቸው ጋር ለመነጋገር የበቁ ጻድቃን ወደ ፈጣሪ ቢያደርሱህ ምን ይደንቃል፤ እነሱ እኮ Already ደርሰዋል (ይህም አይገባህ ይሆን)፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ… የፈጣሪ እናቱ ወደ ፈጣሪ ብታደርስህ ምን ያስደንቃል? ለመሆኑ “ሰውን” ወደ ፈጣሪ ከማድረስ እና “ፈጣሪ”ን ከመውለድ የትኛው ይከብዳል? ጭንቅላትህ በፈረንጅ ትርጉም የተሞላ ስለሆነ ይህች ቀላሏ ነገር እንደግዙፍ ተራራ ከበደችህ፡፡
   ሲጀመር ፕሮቴስታንቶች ፕሮቴስት ያደረጉት ካቶሊክን እንጅ ንጽኅት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አይደለም፤ አባትህ ሉተር ካቶሊኮች በገንዘብ ፍቅር ናውዘው የመንግስተ ሰማይ መግቢያ ካርድ እንሸጣለን ብለው ህዝቡን ሲበዘብዙ ቢያይ እሱ በበኩሉ ምንግስተ ሰማይ በነጻ እናስገባለን ብሎ የራሱን የመጽሀፍ ትርጉም ይዞ ተቃዎማቸው፤ እርሱ ካንተ በብዙ እርቀት የተሻለ ነው፤ የሚቃዎመውን ስለሚያውቅ፡፡ የኛ ኢትዮጵያውያን ፕሮቴስተሮች ፕሮቴስት የምታረጉትን አታውቁምና ይቅር ይበላችሁ፡፡ አንዳንድ ደህና እውነትን ፈላጊ ፕሮቴስታንቶች ስላጋጠማችሁኝ ተቃውሞየ እናንተን አይጨምርም፡፡
   በሰፊው አሜሪካ፣ በአውሮፓ ወዘተ የሚኖሩ “እውነትን ፈላጊ” ፕሮቴስታንቶች ግን ወደ ኢትዮጵያ በአጋጣሚም ሆነ በእቅድ ሲመጡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ትሩፋቶች እጅግ ተደስተው፣ ዜማውን አድምጠው፣ ህንጻውን አድንቀው፣ ጸበሉን ተረጭተው፣ ያደላቸው ደግሞ ስለእምነቲቱ ድንቅነት (የእውነት ማህደርነት) በቃላቸው፣በጽሁፋቸው፣ ወዘተ መስክረዋል፡፡ ያለፉትን ብዙ ጥበብን ፈላጊ ፈረንጆች ትተን በዘመናችን ታቦተ ፅዮንን ፍለጋን (The sign and the seal) የፃፈው ግራሃም ሃንኮክ ሀይማኖቱ ምን እንደሆነ አጣራ እስኪ? ለመሆኑ ከመጽሀፍ ቅዱስ ውጭ ሌላ መጽሀፍ ታነባለህ? መጽኃፍ ቅዱስን ስታነብ ደሞ እንደፈለክ አትተርጉም፣
   መጽሀፉን ከምንጩ የተረጎሙትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሰዎችን ጠይቅ፤ እዚህ ላይ ምን ለማለት ፈልጋችሁ ነው አልገባኝም በል፤ ምን ያሳፍራል አዋቂን መጠየቅ፡፡ አይ እኔ የግሪክ ወይ የእብራይስጥ፣ ወይ የእንግሊዝ መጽሀፍ ካልሆነ የኢትዮጵያን ቋንቋ ትርጉም አልፈልግም ልትል ታስብ ሆናል፤ ሆኖም ያገርህን ቋንቋ በቅጡ ሳይገባህ ሌላ ቋንቋ ይገባሃል ብየ እንዴት ልጠርጠር? በእርግጥ በመንፈስ ቅዱስ ረዳትነት የተጻፉ የኢትዮጵያ መጻኅፍት ላንተ ጭንቅላት አይስማሙም፡፡ ኢትዮጵያውያን ብቃት የላቸውም ብለህ ስለምታምን ጎበዝ የሆንክ ይመስልሃል፤ ራስህን ነው ምትሰድበው፡፡ ወደድክም ጠላህም ግን ኢትዮጵያዊ ነህ፤ እንዳንተ ያለ ሰው ኢትዮጵያዊ ባይሆን ግን ደስ ይለኝ ነበር፤ አንተም ኢትዮጵያዊ፣ ኢጥዮጵያዊው ጃንደረባም ኢትዮጵያዊ ትባላላችሁ፡፡ ኢትዮጵያውያን ማቴሪያሊስቶች ስላልሆኑ ከሀብት ይልቅ እውነትን መርጠው እስካሁን አቆይተውታል፡፡ እውነትን በገንዘብ ብዛት አትለካ፡፡ ለመደመጥ ወሳኙ ነገር ገንዘብ አይደለም፡፡ ለመደመጥ ወሳኙ ነገር እውነት ነው፡፡ እንደዛ ባይሆን ጌታችን ክርስቶስ በልጅነቱ ስደት አይወጣም ነበር፤ በስደት ክርስቶስ ከእናቱ ጋር ሲለምን ብታገኘው ምን ይሰማሃል፤ ደሃን የምትጸየፍ ከንቱ ሰው እርሱን ተጸይፈኃልና እውነት ካንተ በብዙ የራቀ ነው፡፡ እርሱ ግን ሁሉን ቻይ ስለሆነ እንደሰው ቀስ እያለ አደገ፤ እውነትን አስተማረ፤ ፍቅርን ሰበከ፤ ከድሆችና ከሀጥያተኞች ጋር ዋለ፣ ለሀብታሞችና ለባለስልጣኖች የሚጠቅማቸውን ነገራቸው፤ በስጋ የታመሙትን ፈወሳቸው፡፡ እምነትን በተግባር አስተማረ፤ በባህር ላይ እየተራመደ፡፡ ህዝብ ሁሉ ወደደው፣ ደሃም ሀብታምም፤ እርሱም ሁሉንም ይወዳቸዋል፤ የወደዱት ግን ሀብታምም ባለስልጣንም ስለሆነ አይደለም፤ እውነት ስለሆነ ነው፣ ፍቅር ስለሆነ ነው፡፡ ስለርሱ ብዙ ቢባልም አይገልጹትም፡፡ እውነትን የትም ፈልጋት፤ ስትፈልጋት ግን የተናቁ የተባሉ ቦታዎችን፣ የተናቁ የተባሉ ሰዎችን አትለፋቸው፤ ምናልባት እውነትን ተራምደህ አልፈህ እየሄድክ ነው፡፡ በየዋህ ልብ ከፈለካት ታገኛታለህ፤ በትእቢት ከሆንክ ግን በእርሷና በአንተ መካከል ያለው ለዘላለም እየሰፋ እየሰፋ እንተ ደሞ እየጠፋህ እየጠፋህ ትሄዳለህ፡፡ እኔ ክፉ አልመኝልህም፤ ከእውነት ያገናኝህ፡፡

   Delete
 3. EGZABIHER TSEGA YABZALIH , qale hiwet yasemalinge . eritrea silemigengu haweltoch adulis , qohayto and belewkelew yemibalu yalut tsifoch meche beman sewna qanqa endtesafe yemitaqew kezi gar yemitayaz tarik kale bitnegren.

  ReplyDelete
 4. ይህንን ታሪኳንና ጠባይዋን የማያውቁ ብቻ ናቸው ‹ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አታውቀውም› የሚለውን የማይም ድፍረት የሚደፍሩት፡፡

  ReplyDelete
 5. ኢየሱስ ክርስቶስ ለስብከት ሲባል የምትጠራው ስም ሳይሆን ዋጋ የከፈለችበት አዳኟ ነውና፡፡ ይህንን ታሪኳንና ጠባይዋን የማያውቁ ብቻ ናቸው ‹ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አታውቀውም› የሚለውን የማይም ድፍረት የሚደፍሩት፡፡ ወንድሜ ዳኒ ተባርክ መቼ ይገባቸዋል ብለህ ነው ማስተዋሉን ይስጣቸው፡፡ ለአንተ ቃለ ሕይወት ያሰማልን የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልን፡፡

  ReplyDelete
 6. Eski ebakihin sile nigus Nejashim be zirzir asinebiben.

  ReplyDelete
 7. ኢየሱስ
  ክርስቶስ
  ለስብከት
  ሲባል
  የምትጠራው
  ስም
  ሳይሆን
  ዋጋ
  የከፈለችበት
  አዳኟ
  ነውና

  ReplyDelete
 8. ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ አሸናፊ እግዚአብሄር ነው። እናቱም እመ እግዚአብሄር፣ ወላዲተ አምላክ ትባላለች። የሉተራውያን የራስ ምታት የሆነባቸው ይህ ነው። ፕሮቴስታንቲዝም ክርስቶስን እግዚአብሄር ነው ብሎ ለመናገር ድፍረት የለውም። ኦርቶዶክሳዊው መምህር ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ፕሮቴስታንቲዝምን/ ሀራጥቃ ተሀድሶን Latent Arianism ይለዋል። ይህም ማለት የፕሮቴስታንቱ አለም ምንም እንኳን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ግልፅ በሆነ አነጋገር ፍጡር ነው ባይለውም ከእግዚአብሔር አብ የሚያንስ፣ ትንሽ አምላክ፣ የሚለምን፣ ልመና የሚያቀርብ መሆኑን ሁሉም ሉተራዊ የሚያምነው በመሆኑ ፕሮቴስታንቲዝም ኦርቶዶክሳውያን እንደምናምነው ኢየሱስ ቅዱስ አሸናፊ እግዚአብሄር ነው ብሎ አያምንም። ለዚህም ተጨማሪ ጥሩ ማሳያ የሚሆነው ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ እመ እግዚአብሄር ናት ስንል እነሱ ወላዲተ አምላክ ልትባል አይገባም ብለው አብዝተው ይከራከራሉ። ይህም የክርስቶስን አምላክነት ፈፅሞ የካደ ከአርዮሳዊ እምነት ጋር ተመሳሳይ የሆነ Latent Arianism ቢባል በጣም ትክክል ነው። የዲያቆን ያረጋልን አዲሱን መጽሐፍ ያንብቡ።

  ReplyDelete
 9. lega Daqan danale kale Hewitt yasmalen !! mch tftochow msaleh ymlewt menenewn sywnabdyt new eng egezabhear lebwen ystachw gzaw ahen new nsh ygbu orthodox twedo gatachen mdhentachen eysess crestosen knsew bfet endsbkech ywkalew tmelesew hare tkawech aywtachem mkadew!! amen!!

  ReplyDelete
 10. Pls,Tell us about the so called negash/negashi,Bdar.

  ReplyDelete
 11. የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ።

  ReplyDelete
 12. ያገልግሎት ጊዜህን ይባርክልህ

  ReplyDelete
 13. የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ።

  ReplyDelete
 14. የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ።

  ReplyDelete
 15. በእግዚአብሔር ክርስቶስ ኃይል ተነሣሁ፤ በእርሱ አምናለሁ፣ እርሱም ይመራኛል›› ይላል፡

  ReplyDelete
 16. እጅግ ደስ አለኝ ቆንጆ አቀራረብ።መጽሀፍትን አገላብጦ ላላወቁት ማሳወቅ።ግን ነፍሳቸው ከፈጣሪ ጋር ያለ ሳይሞቱ ምን እይታ አላቸው?

  ReplyDelete
 17. ከላይ Fikere Bahirdar Desta ለጠቀሰው ሃሳብ እንዲህ ብለህ አስተያየትክን ለሰጠህ አኖኒመስ፡
  “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቶስን በሚገባ አታዉቅም ማለት ስሙን አትጠራም ማለት ሳይሆን መጽሃፍ ቅዱስ ባስተማረዉ መንገድ አታስተምርም ማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ መጽሃፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ፣እዉነት ሕይወት ስለሆነ ያለ እርሱ ኣብን ማየት እንደማይቻል ያስተምራል (ዮሀ 14፡6)፡፡ ኦርቶዶክስ ግን ማሪያምም፣ መላዕክትም፣ ፃድቃንም ወደ ኣብ ያዳርሳሉ ትላለች፡፡” ብለሃል፡፡
  ያንተ አይነቱን አውቆም ሳያውቅም የተኛ ማንቃት እንዴት ይቸግራል… እምነት ቢጎልህ ሎጅክ እንኳን ቢገባህ እንዴት ጥሩ ነበር፡፡ ከፈጠሪ ጋር አብረው የሚዉሉ መላእክት፣ ከፈጣሪያቸው ጋር ለመነጋገር የበቁ ጻድቃን ወደ ፈጣሪ ቢያደርሱህ ምን ይደንቃል፤ እነሱ እኮ Already ደርሰዋል (ይህም አይገባህ ይሆን)፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ… የፈጣሪ እናቱ ወደ ፈጣሪ ብታደርስህ ምን ያስደንቃል? ለመሆኑ “ሰውን” ወደ ፈጣሪ ከማድረስ እና “ፈጣሪ”ን ከመውለድ የትኛው ይከብዳል? ጭንቅላትህ በፈረንጅ ትርጉም የተሞላ ስለሆነ ይህች ቀላሏ ነገር እንደግዙፍ ተራራ ከበደችህ፡፡
  ሲጀመር ፕሮቴስታንቶች ፕሮቴስት ያደረጉት ካቶሊክን እንጅ ንጽኅት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አይደለም፤ አባትህ ሉተር ካቶሊኮች በገንዘብ ፍቅር ናውዘው የመንግስተ ሰማይ መግቢያ ካርድ እንሸጣለን ብለው ህዝቡን ሲበዘብዙ ቢያይ እሱ በበኩሉ ምንግስተ ሰማይ በነጻ እናስገባለን ብሎ የራሱን የመጽሀፍ ትርጉም ይዞ ተቃዎማቸው፤ እርሱ ካንተ በብዙ እርቀት የተሻለ ነው፤ የሚቃዎመውን ስለሚያውቅ፡፡ የኛ ኢትዮጵያውያን ፕሮቴስተሮች ፕሮቴስት የምታረጉትን አታውቁምና ይቅር ይበላችሁ፡፡ አንዳንድ ደህና እውነትን ፈላጊ ፕሮቴስታንቶች ስላጋጠማችሁኝ ተቃውሞየ እናንተን አይጨምርም፡፡
  በሰፊው አሜሪካ፣ በአውሮፓ ወዘተ የሚኖሩ “እውነትን ፈላጊ” ፕሮቴስታንቶች ግን ወደ ኢትዮጵያ በአጋጣሚም ሆነ በእቅድ ሲመጡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ትሩፋቶች እጅግ ተደስተው፣ ዜማውን አድምጠው፣ ህንጻውን አድንቀው፣ ጸበሉን ተረጭተው፣ ያደላቸው ደግሞ ስለእምነቲቱ ድንቅነት (የእውነት ማህደርነት) በቃላቸው፣በጽሁፋቸው፣ ወዘተ መስክረዋል፡፡ ያለፉትን ብዙ ጥበብን ፈላጊ ፈረንጆች ትተን በዘመናችን ታቦተ ፅዮንን ፍለጋን (The sign and the seal) የፃፈው ግራሃም ሃንኮክ ሀይማኖቱ ምን እንደሆነ አጣራ እስኪ? ለመሆኑ ከመጽሀፍ ቅዱስ ውጭ ሌላ መጽሀፍ ታነባለህ? መጽኃፍ ቅዱስን ስታነብ ደሞ እንደፈለክ አትተርጉም፣
  መጽሀፉን ከምንጩ የተረጎሙትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሰዎችን ጠይቅ፤ እዚህ ላይ ምን ለማለት ፈልጋችሁ ነው አልገባኝም በል፤ ምን ያሳፍራል አዋቂን መጠየቅ፡፡ አይ እኔ የግሪክ ወይ የእብራይስጥ፣ ወይ የእንግሊዝ መጽሀፍ ካልሆነ የኢትዮጵያን ቋንቋ ትርጉም አልፈልግም ልትል ታስብ ሆናል፤ ሆኖም ያገርህን ቋንቋ በቅጡ ሳይገባህ ሌላ ቋንቋ ይገባሃል ብየ እንዴት ልጠርጠር? በእርግጥ በመንፈስ ቅዱስ ረዳትነት የተጻፉ የኢትዮጵያ መጻኅፍት ላንተ ጭንቅላት አይስማሙም፡፡ ኢትዮጵያውያን ብቃት የላቸውም ብለህ ስለምታምን ጎበዝ የሆንክ ይመስልሃል፤ ራስህን ነው ምትሰድበው፡፡ ወደድክም ጠላህም ግን ኢትዮጵያዊ ነህ፤ እንዳንተ ያለ ሰው ኢትዮጵያዊ ባይሆን ግን ደስ ይለኝ ነበር፤ አንተም ኢትዮጵያዊ፣ ኢጥዮጵያዊው ጃንደረባም ኢትዮጵያዊ ትባላላችሁ፡፡ ኢትዮጵያውያን ማቴሪያሊስቶች ስላልሆኑ ከሀብት ይልቅ እውነትን መርጠው እስካሁን አቆይተውታል፡፡ እውነትን በገንዘብ ብዛት አትለካ፡፡ ለመደመጥ ወሳኙ ነገር ገንዘብ አይደለም፡፡ ለመደመጥ ወሳኙ ነገር እውነት ነው፡፡ እንደዛ ባይሆን ጌታችን ክርስቶስ በልጅነቱ ስደት አይወጣም ነበር፤ በስደት ክርስቶስ ከእናቱ ጋር ሲለምን ብታገኘው ምን ይሰማሃል፤ ደሃን የምትጸየፍ ከንቱ ሰው እርሱን ተጸይፈኃልና እውነት ካንተ በብዙ የራቀ ነው፡፡ እርሱ ግን ሁሉን ቻይ ስለሆነ እንደሰው ቀስ እያለ አደገ፤ እውነትን አስተማረ፤ ፍቅርን ሰበከ፤ ከድሆችና ከሀጥያተኞች ጋር ዋለ፣ ለሀብታሞችና ለባለስልጣኖች የሚጠቅማቸውን ነገራቸው፤ በስጋ የታመሙትን ፈወሳቸው፡፡ እምነትን በተግባር አስተማረ፤ በባህር ላይ እየተራመደ፡፡ ህዝብ ሁሉ ወደደው፣ ደሃም ሀብታምም፤ እርሱም ሁሉንም ይወዳቸዋል፤ የወደዱት ግን ሀብታምም ባለስልጣንም ስለሆነ አይደለም፤ እውነት ስለሆነ ነው፣ ፍቅር ስለሆነ ነው፡፡ ስለርሱ ብዙ ቢባልም አይገልጹትም፡፡ እውነትን የትም ፈልጋት፤ ስትፈልጋት ግን የተናቁ የተባሉ ቦታዎችን፣ የተናቁ የተባሉ ሰዎችን አትለፋቸው፤ ምናልባት እውነትን ተራምደህ አልፈህ እየሄድክ ነው፡፡ በየዋህ ልብ ከፈለካት ታገኛታለህ፤ በትእቢት ከሆንክ ግን በእርሷና በአንተ መካከል ያለው ለዘላለም እየሰፋ እየሰፋ እንተ ደሞ እየጠፋህ እየጠፋህ ትሄዳለህ፡፡ እኔ ክፉ አልመኝልህም፤ ከእውነት ያገናኝህ፡፡

  ReplyDelete
 18. ልጅ ዳንኤል ሰው ሁሉ ይባርካል።መባረክ የካህን አይደለም እንዴ? ምርቃት እራሱን የቻለ ዘርፍ አለው።
  ይህ ቢተነተን?

  ReplyDelete
 19. ከላይ Fikere Bahirdar Desta ለጠቀሰው ሃሳብ እንዲህ ብለህ አስተያየትክን ለሰጠህ አኖኒመስ፡

 20. ከላይ Fikere Bahirdar Desta ለጠቀሰው ሃሳብ እንዲህ ብለህ አስተያየትክን ለሰጠህ አኖኒመስ፡

  ከላይ Fikere Bahirdar Desta ለጠቀሰው ሃሳብ እንዲህ ብለህ አስተያየትክን ለሰጠህ አኖኒመስ፡
  “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቶስን በሚገባ አታዉቅም ማለት ስሙን አትጠራም ማለት ሳይሆን መጽሃፍ ቅዱስ ባስተማረዉ መንገድ አታስተምርም ማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ መጽሃፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ፣እዉነት ሕይወት ስለሆነ ያለ እርሱ ኣብን ማየት እንደማይቻል ያስተምራል (ዮሀ 14፡6)፡፡ ኦርቶዶክስ ግን ማሪያምም፣ መላዕክትም፣ ፃድቃንም ወደ ኣብ ያዳርሳሉ ትላለች፡፡” ብለሃል፡፡

  ReplyDelete
 21. Go look the picture of Memher Girma crying on Memher Girma facebook.
  Congradulation!!!!

  ReplyDelete
 22. D/n Dani Betam tefahe eyekoyeh new mitsefew ahun enkuwan ketsafk wer limolak new beselam new?????

  ReplyDelete
 23. "የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላትን የጠራና የነጠረ ትምህርትና እምነት ይዛ እስከዛሬ እንድትዘልቅ አድርጓታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለስብከት ሲባል የምትጠራው ስም ሳይሆን ዋጋ የከፈለችበት አዳኟ ነውና፡፡ ይህንን ታሪኳንና ጠባይዋን የማያውቁ ብቻ ናቸው ‹ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አታውቀውም› የሚለውን የማይም ድፍረት የሚደፍሩት፡፡"

  ReplyDelete
 24. " የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላትን የጠራና የነጠረ ትምህርትና እምነት ይዛ እስከዛሬ እንድትዘልቅ አድርጓታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለስብከት ሲባል የምትጠራው ስም ሳይሆን ዋጋ የከፈለችበት አዳኟ ነውና፡፡ ይህንን ታሪኳንና ጠባይዋን የማያውቁ ብቻ ናቸው ‹ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አታውቀውም› የሚለውን የማይም ድፍረት የሚደፍሩት፡፡"
  ቃለ ህይወት ያሰማልን!

  ReplyDelete
 25. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡፡
  ለልብ ሐሴት የሚሰጥ፤ መንፈስን የሚያድስ፤ የነብስ ምግብ መገብከን፡፡
  እግዚአብሔር ጸጋዉን እንደ አባቶቻችን አብዝቶልኃል ና ደስ ይበልህ፡፡ የአባቶቻችን አምላክ እድሜው ና ጥበቃው ይስጥህ፡፡

  ReplyDelete
 26. ቃለ ህይወት ያሰማልን! አሜን!

  ReplyDelete
 27. Dear Dn Daniel,

  If Ezan was a pagan (believer of idol), then one can claim that the history of Solomonic route dynasty will be in question? b/c if so one can expect him to be the believer of old testament.

  The other thing is the 'janderebaw" history in the bible suggests that Ethiopians were believer of old testament.
  Then I may ask 'Was that only EZANA who was pagan or all his officials? or some were the followers of Old Testament and some were pagan which may not give sense.

  Please the Gap between these conflicts if you can.
  Please respond to this request or write it officially.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Lineage is not subject to beliefs, book of Samuel, kings and chronicles all show within a few generations after King David, pagan kings like Ahab arose.

   Delete
 28. kale hiwot yasemalin Dn Daniel Kibret

  ReplyDelete
 29. ቃለህይወት ያሰማልን!!

  ReplyDelete
 30. ኢየሱስ ክርስቶስ ለስብከት ሲባል የምትጠራው ስም ሳይሆን ዋጋ የከፈለችበት አዳኟ ነውና፡፡ ይህንን ታሪኳንና ጠባይዋን የማያውቁ ብቻ ናቸው ‹ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አታውቀውም› የሚለውን የማይም ድፍረት የሚደፍሩት፡፡

  ReplyDelete
 31. በእግዚአብሔር ባለ እምነት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ መንግሥቴን ባዳነልኝ በእርሱ፡፡ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለኝ እምነት፣ በረዳኝ፣ ዘወትርም በሚረዳኝ›
  ጥቂት እልፍ ብሎ ደግሞ ‹የአልሜዳ ልጅ፣ የክርስቶስ አገልጋይ› ይላል፡፡
  ቀጥሎም ….‹ለእኔ ያደረገልኝን ታላላቅ ነገሮችን አንደበቴና ልቡናዬ ለመናገር የማይቻላቸው ናቸው፡፡ እርሱ ጠናካራና ኃያል አድርጎኛል፤ በማምንበት በልጁም በኩል አዲስ ስም ሰጥቶኛል፡፡ የመንግሥቴም ሁሉ ገዥ አድርጎኛል፤ በክርስቶስ ባለኝ እምነት የተነሣ፣ በእርሱ ፈቃድ፣ በክርስቶስ ኃይል፤ ምክንያቱም የሚመራኝ እርሱ ራሱ ነውና፤ በእርሱ አምናለሁ፤ እርሱ ራሱም መሪዬ ነው› ይላል፡፡
  አለፍ ብሎ ደግሞ ‹…በእግዚአብሔር ክርስቶስ ኃይል ተነሣሁ፤ በእርሱ አምናለሁ፣ እርሱም ይመራኛል›› ይላል፡፡

  ReplyDelete
 32. በእግዚአብሔር ባለ እምነት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ መንግሥቴን ባዳነልኝ በእርሱ፡፡ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለኝ እምነት፣ በረዳኝ፣ ዘወትርም በሚረዳኝ›