Monday, November 16, 2015

ፈረንጅ ሆይ ናና

ፈረንጅ ሆይ ናና ፈረንጅ ሆይ ናና
አንተ ስትናገር ይታመናልና
ፈረንጅ ሆይ ናና ፈረንጅ ሆይ ናና
አንተ ስትናገር ትሰማለህና
ፈረንጅ ሆይ፤
አንተ ገድላቱንና ድርሳናቱን፣ ዜና መዋዕሎችንና ታሪከ ነገሥቱን፣ የፍልስፍናውንና የጥበቡን፣ የመድኃኒቱንና የጠልሰሙን ነገር ከግእዝ ወደ እንግሊዝኛ ስትተረጉመው ሁሉም ያደንቅሃል፣ ያነብሃል፡፡ ይጠቅስሃል፡፡ ‹ከውጭ ድረስ መጥተው የኛን ታሪክ አጥንተው› እየተባለ ይነገርልሃል፡፡ እኛ ያደረግነው ቀን ግን ‹የደብተራ ጽሑፍ፣ የነፍጠኛ ድርሰት፣ ያበሻ ተረት ተረት ይባላል፡፡ እናም ፈረንጅ ሆይ ና፡፡ አባቶቻችን ለሺ ዘመናት ያቆዩትን የጽሑፍ ቅርስ ወሰድ፣ ስረቅ፣ አውጣ፣ ግእዝ ተማርና ተርጉም፤ ተርጉምና በዶላር ሺጥልን፡፡ ያን ጊዜ በእንግሊዝኛ ስታመጣው - ፓ- እያልን እናነብሃለን፡፡


ምን ማንበብ ብቻ ግእዙን ብንጠቅሰው የደብተራ ድርሰት፣ የቄሶች ግሳንግስ፣ የድሮ ናፋቂ፣ ምናምን ስለምንባል ምናለ በእንግሊዝኛ ብታመጣልንና ‹የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዜና መዋዕል› ብለን ጠቅሰን መከራ ከምናይ ‹The chronicle of king zare’a yae’qob> ብንል ማናለበት፡፡ እኛ ስለ ንግሥተ ሳባ ስንናገር ተረት ይሆናል፤ አንተ ሮምን የመሠረቷት ሮሙለስና ሙለስ የተባሉ ተኩላ ያሳደገቻቸው ልጆች ናቸው ስትል ግን ሁሉ ያምንሃል፡፡
ደግሞ ያንተ ጥሩነቱ ምንም ነገር ብትጽፍ፣ ምንም ነገር በትናገር - ኦሮሞ ስለሆንክ ነው፣ ጉራጌ ስለሆን ነው፣ አማራ ስለሆንክ ነው፣ ክርስቲያን ስለሆንክ ነው፣ ሙስሊም ስለሆንክ ነው፣ ደርግ ስለሆንክ ነው፣ ኢሕአዴግ ስለሆንክ ነው፣ ተቃዋሚ ስለሆንክ ነው፣ ካድሬ ስለሆንክ ነው- የሚልህ የለ፡፡ አገርህ አይጠየቅ፣ ወንዝህ አይጠና፣ ዘርህ አይፈለግ፣ ብቻ ፈረንጅ ሁን፡፡
ፈረንጅ ሆይ ና፤
ስለ ዳጉሳ፣ ስለ ቆጮ፣ ስለ ክትፎ፣ ስለ ቡላ፣ ስለ ገንፎ፣ ስለ ቃተኛ፣ ስለ ጨጨብሳ፣ ስለ ቆሎ፣ ስለ ንፍሮ፣ ስለ በቆሎ ጥብስ፣ ስለ ጠላና ጠጅ፣ ስለ አረቂና ቦርዴ፣ ስለ ቅቅልና ጥብስ በእንግሊዝኛ ተናገር፡፡ ይኼው ስንት ዓመት ስንመገበው ‹ከወኔ በቀር ሌላ የለውም› ሲባል የነበረው ጤፍ አንተ በእንግሊዝኛ ስትናገርለት አበሻ ሆዬ በኩራት ‹‹የጤፋችን ፓተንት ይመለስ›› ማለት ጀመረ አይደል? ትናንት እንኳን ስለ ፓተንቱ ስለመኖሩስ ማን ያስብ ነበር፡፡
አይ ፈረንጅ ቀን ይውጣልህ፤ ይኼው ለጥቁር ጤፍ እንኳን ቀን አወጣህለት፡፡ ማን ነበር ትናንት ቸግሮት ካልሆነ በቀር ጥቁር ጤፍ የሚሸምተው፡፡ ‹‹የሚበላው ነጭ፣ የሚጠጣው ጠጅ‹‹ አልነበር ፉከራው፡፡
ቢቸግረኝ እንጂ ጥቁር የምበላ
ያደግኩ ነበረ በማር በወለላ - ይባል ነበርኮ፡፡
ማን ነበር ትናንት ድግስ ላይ ጥቁር እንጀራ የሚያቀርበው? ሰፈር እንዲረግመው ካልፈለገ በቀር፡፡ ማን ነበረ ትናንት ጥቁር እንጀራ ምግብ ቤት ውስጥ የሚያቀርበው፤ የሚያስቀርበውስ፡፡ አእምሮው ተነክቶ ካልሆነ በቀር፡፡
ይኼው አንተ ‹‹ጥቁር ጤፍ ምናምን አለው፤ ከምናምን ነጻ ነው፤ ለምናምን መድኃኒት ነው›› ብለህ ተናግረህ አበሻ በኩራት ‹ነጭ ጤፍኮ ጥሩ አይደለም፤ ጥቁር ጤፍ ነው መብላት፤ እንትን እንዳለው ታውቃለህ አይደል›› እያለ የዕውቀት መለኪያ አደረገው፡፡ መቼም የወደቀን እንዳነሣህ የወደቁትን የሚያነሣ አምላክ ያንሣህ፡፡ አንተ አይደለህ እንዴ የገብስ ዳቦ፣ ጥቁር ዳቦ፣ የጥቁር ጤፍ ዳቦ፣ የሚባል ነገር ያመጣህብን፡፡ ደኅና ነጩን እንዳንበላበት፡፡ ድሮ እናቶቻችን ‹የጥቁር ገብስ ጠላ፣ የጥቁር ጤፍ እንጀራ፣ የጥቁር ስንዴ ዳቦ ጎን ይደግፋል› ሲሉ ማን ሰምቷቸው፡፡ እንኳን ለምግብነት ለኩስነት እንኳን ነጭ ነበርኮ የሚመረጠው፡፡
የፈሩ አህዮች ለጅብ በቀቁት ነጠላ ዜማ ላይ፡-
ምን ጥቁር ቢበሉ ነጭ ነው ኩስዎ
ምን ከሩቅ ቢጮኹ ይሰማል ድምጥዎ
አሁን የርስዎን ልጅ ምን አገኘብዎ፤
አይደል እንዴ ያሉት፡፡ ምናለ ጥቁሩን ጤፍ ከነጭ እንዳስተካከልከው እዚያው በነካ እጅህ፣ በሀገርህ ጥቁሩን ሰው ከነጭ ምናለ ብታስተካክለው፡፡
ፈረንጅ በሞቴ ና፤ አባቶቻችን፣ አያቶቻችን የቀመሩትን፣ በባሕላችን ውስጥ ያሳደጉትን፤ ሊቆቻችን ያጠኑትን፤ አሳቢዎቻችን የተናገሩትን ማን ከቁም ነገር ይወስደዋል፡፡ ያውምኮ ለራሳችን ወርድና ቁመት እንዲሆን ሆኖ በራሳችን የተሰፋውን፡፡ አንተ ግን ለራስህ አገር ያዘጋጀኸውን፣ የቀመርከውን ነገር፤ ከባህልህና ከልምድህ፣ ከሕዝብህ ፍላጎትና ዕድገት፣ ከሥነ ልቡናህና ጠባይህ ተነሥተህ ለራስህ የቀረጽከውን ሕግ፣ አሠራር፣ መሥሪያ ቤት፣ ዐዋጅና ፖሊሲ - ‹‹የውጭ ሀገር ልምድ ታክሎበት፣ የሌሎችን ሀገሮች ልምድ በመቀመር፣ ያደጉ ሀገሮችን ሕጎች በማገናዘብ›› እየተባለ ሕግና አሠራር ይወጣልናል፡፡ የኛ ሊቃውንት አንተ ሀገር መጥተው፣ ወይ በትምህርት፣ ወይ በዐውደ ጥናት፣ ወይ በሰባቲካል ሊቭ፣ ወይ በፌሎውሺፕ፣ ወይ በአማካሪነት ያጠኑትን ጥናት ትወስድና፣ በእንግሊዝኛ ትቀይርና፣ ‹‹የውጭ ሀገር ተሞክሮ›› የሚባል የክርስትና ስም ትሰጥና መልሰህ ለራሳችን ትሸጥልናለህ፡፡
አየህ - በኦሮምኛ፣ በትግርኛና በአፋርኛ፣ በወላይትኛና በአማርኛ፣ በሲዳምኛና በሶምልኛ ከምንሰማው በእንግሊዝኛ ብንሰማው የኛም ሊቅነታችን ይታመናል፡፡ ሙሽራ እንኳን ሲዳር
የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው
በእንግሊዝ አናግሪያቸው
አይደል የሚባለው፡፡ ተወው ሌላውን፤ የኛኑ ተረት፣ የኛኑ ምሳሌ፣ የኛኑ አባባል፣ የኛኑ አፈ ታሪክ - ከሰሜንና ከደቡብ፣ ከምሥራቅና ከምዕራብ ወስደህ፣ ብቻ የሆነ ርእስ ሰጥተህ - ወይ በፈረንሳይኛ፣ ወይ በጀርመንኛ ወይ በእንግሊዝኛ ስታሳትመው አቤት ያለን ደስታ፡፡ ከዚያ የኛ ሥራ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ‹‹የእንትን ብሔረሰብ ቃላዊ ቅርሶች ለዓለም ሥነ ጽሑፍ ያበረከቱት አስተዋጽዖ› የሚል ጥናት እናደርግና በገዛ ተረታችን አንተን እንጠቅስና፣ ተረታችን በሀገርኛ ቋንቋ ከሚጻፍ ይልቅ በውጭ ቋንቋ ቢጻፍ ለገጽታ ግንባታ ያለውን አስተዋጽዖ እንጨምርበትና፤ ቱሪስቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ያለውን አበረታችነት እናክልበትና በየወርክሾፑ በአበል ማቅረብ ነው፡፡
ኧረ ፈረንጅ እባክህ ና፡፡
መረጃ ፍለጋ በየገዳማቱ ብትዞር፣ በየመስጊዱ ብትኳትን፣ በየመሥሪያ ቤቱ ብትሄድ፣ መዛግብት ብታገላብጥ አንተን የሚጠረጥርህ የለ፡፡ የሚከለክልህም የለ፡፡ ፈረንጅ ነሃ፡፡ ፈረንጅኮ አይሰርቅም፡፡ የተዘጋ የገዳማት ዕቃ ቤት ላንተ ይከፈታል፤ ስብሰባ ላይ የሚውል ባለ ሥልጣን ላንተ ሲል ቢሮ ይገባል፤ የተከለከለ መረጃ ላንተ ይሰጣል፡፡ ባለ ሥልጣናቱ እንኳን ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኛ ከሚናገሩ በፈረንጅ አፍ ለፈረንጅ ቢያወሩ ይመቻቸው የለ፡፡ የዕውቀት መለኪያ እኮ ነው፡፡
ኢትዮጵያዊ ለሺ ዓመታት ሲወጣው የኖረውን ደብረ ዳሞ አንተ ስተወጣው በቴሌቭዥን ትቀርባለህ፡፡ በየንግሡ ስንሄድበት የኖርነውን ገርዓልታ አንተ ስትሆን ትደነቃለህ፡፡ ተወው ይኼማ ወግ ነው፡፡ ያልኖርክበትን፣ ያላደግክበትን መስቀልና ጥምቀት፣ አረፋና መውሊድ ጋዜጠኞቹ አንተን አይደል እንዴ የሚጠይቁት፡፡ ዜናውምኮ አንተ ነህ፡፡ ‹‹የመስቀልን በዓል ቱሪስቶች አደነቁ›› ነው ርእሰ ዜናው፡፡ እኛ ብናደንቅ ባናደንቅ ማን ከቁብ ይጥፈናል፡፡ በዓሉ የኛ - የምታብራራው አንተ፡፡
መስቀል አደባባይና ጃንሜዳ ውስጥ ገብቶ ፎቶ ለማንሣት እንኳን ፈረንጅ አንተ ትችላለህ፡፡ ፈረንጅ መሆንህ ከታየ ወይ የመግቢያ ካርድ ይሰጥሃል፤ ደግሞስ ማን ይከለክልሃል፡፡ ቱሪስት ነህና ፎቶ ታነሣለህ፡፡ አበሻን ማን ቱሪስት ያደርገዋል፡፡ ለመሆኑ አኩስምና ላሊበላ፣ ጎንደርና ጣና፣ አርባ ምንጭና ጀጎል የጎብኝ ቱሪስቶች ቁጥር በየዓመቱ ሲነገር ፈረንጅ ፈረንጁ ተመርጦ ነው ወይስ እኛንም ይጨምራል? እኛን ከጨመረ እንዴት ነው ቁጥሩ የሚያንሰው? ነው እኛ ከቁጥር የማንገባ ‹‹አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች›. ነን?
ካሜራው እንኳን ነፍስ ዐውቆ የመስቀሉን ደመራ፣ የጥምቀቱን ባሕር ትቶ አንተን አንተን ነው የሚያሳየን፡፡ እንኳን መስቀልና ጥምቀት ዘፈን ሲዘፈን እንኳን፣ ወይ የሚያጨበጭብ፣ ከተቻለም የሚወዛወዝ፣ ከተገኘም እስክስታ የሚመታ ፈረንጅ ከተገኘ ማን ይምረዋል፡፡ ስለ ሀገራችን ዘፈን ለማሳየት ፈረንጅ ሲዘፍን፣ ስለ ሀገራችን ምግብ ለማሳየት ፈረንጅ ሲበላ፤ ስለ ሀገራችን ሆቴሎች ለማስተዋወቅ ፈረንጅ ሲዝናና ማሳየት ሥልጣኔ ነው፡፡
እንኳንና አንተ ላንተ ቤት ያከራየው ሰውዬ እንኳን ኩራቱ፡፡ ‹‹እርሳቸውኮ ቤታቸውን ለፈረንጆች ነው ያከራዩት›› ይባልላቸዋል ዕድርና ልቅሶ ላይ፡፡ እርሳቸውም ሰው ሰላም ሲሉ በፈረንጅኛ ነው፡፡ ቤታቸውን ለፈረንጅ አከራይተዋላ፡፡ ድንኳን ውስጥም ቤትን ለፈረንጅ ማከራየት ያለውን ጥቅም በመዘርዘር ይታወቃሉ፡፡ ቤታቸውን ለፈረንጅ ስላከራዩም አንዳንድ እንግሊዝኛ ይሞክራሉ፡፡ ታዲያ ቤቱን ለአበሻ ካከራየው ሰው በምን ይለያሉ፡፡
አንተ ቁምጣ ብትለብስ፣ መሬት ብትቀመጥ፣ በነጠላ ጫማ ብትሄድ፣ መንገድ ላይ በቆሎ ገዝተህ ብትበላ፣ በአውቶቡስ ተሳፍረህ ብትሄድ፣ ልጆችህን ሽኮኮ አድርገህ ብትጓዝ፣ ተራ ሻሂ ቤት ገብትህ ዳቦ በሻሂ ብትገምጥ፣ አንተን ማን ገብጋባ ይልሃል፣ ማን ቋጣሪ ይልሃል፤ ማን ‹ምን ነካው› ይልሃል፡፡ ዕድር የለህ፣ ዕቁብ የለህ፣ ሰንበቴ የለህ፣ ማንንስ ትፈራለህ፡፡ እኛ የሆን እንደሁ ስንት ይጠብቀናል፡፡ አንተ ከሆንክ ግን ‹ፈረንጆችኮ ግድ የላቸውም፣ ቀለል ያለ ነገር ይወዳሉ፣ እነርሱ አይኮሩም፣ ጣጣም የላቸው፣ ይሉኝታ የላቸውም፣›› ይባልልሃል፤ ትደነቃለህ፡፡ ሀገርክን ያላየ ያመሰግንሃል፡፡
በምኒልክ አደባባይ አንጂ በፑሽኪን አደባባይ ማን ይከራከራል፡፡ በበላይ ዘለቀ መንገድ እንጂ በቼርችል ጎዳና ማን ይከራከራል፡፡
ፈረንጅ ሆይ ናና
ይኼው ቻይና እንኳን ፈረንጅ ሆና በየፊልሙ፣ በየክሊፑ እያየናት አይደል፡፡ ይኼው በመሬት ላይ መንገድ ልሥራ ብላ የመጣች ቻይና በሰማያችን ላይ ‹ሆስተስ› ሆነች አይደል፡፡ አይ ፈረንጅ መሆን ደጉ፡፡ እንኳን ‹ሆስተስነት› ‹ማናጅመንቱን ለውጭ ድርጅት መስጠት› በሚል ባለቤት አልባ ፍልስፍና በፈረንጅ መመራት የታላቅነት መለኪያ እየሆነ አይደል፡፡ ቀደምቶቻችን የኢትዮጵያ አየር መንገድን፣ ሲቪል አቪየሽንን፣ ፋብሪካና ኩባንያዎችን፣ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆችን፣ መከላከያና ሆቴሎችን ከፈረንጅ አመራር አውጥተው በሀገር ሊቆች እንዲመሩ ለማድረግ ስንት ነበር መከራ የተቀበሉት?
ሀገሪቱ ከልጅነት እስከ ዕውቀት፣ ከሽበት እስከ ኩተት ያሳደገቻቸው፤ ‹ይማርልኝ ብዬ በጌምድር ሰድጄ› እንደተባለው ውጭ ልካ ያስተማረቻቸው፣ በሥራ ልምድ ያበሰለቻቸው ልጆቿን፤ አስሳ፣ የማርያም መንገድ ሰጥታ፣ የጎደላቸውን ሞልታ ‹ያገሩን በሬ ባገሩ ሰርዶ‹ ማድረግ ትታ፣ በአድዋ በኩል ያሸነፍነው ፈረንጅ በአስተሳሰብ በኩል ገብቶ፣ ይኼው በዕውቀት አንሰው በንጣት ለሚበልጡ ሰዎች ‹‹ማናጅመንቱ ይሸጣል››፡፡ 
ፈረንጅ ሆይ ናና
ባንተ ያምራልና
ትሰማለህና
ትከብራለህና


67 comments:

 1. Thank you so much Mr. Daniel Kibret. I feel you are talking about me. Since I was six years old, I was eager to speak, write and read English then my dream come true. I never read a single Amharic book or newspaper. When people tell me about Ethiopian history I mention to them other countries writer. When I took ECLC, English A and Amharic D. I used to work for Ethiopian sport federation, whatever I said all the people agree with me because I speak English. I have only diploma but most of my coworker see me as “I am the smartest person and well educated” because of my English skill. I read English bible, listen English music and my entire dream was to become Fereng. I never try to learn other Ethiopian spoken languche. SHAME ON ME & THEANK YOU DANIEL.

  ReplyDelete
 2. Thank you so much Mr. Daniel Kibret. I feel you are talking about me. Since I was six years old, I was eager to speak, write and read English then my dream come true. I never read a single Amharic book or newspaper. When people tell me about Ethiopian history I mention to them other countries writer. When I took ECLC, English A and Amharic D. I used to work for Ethiopian sport federation, whatever I said all the people agree with me because I speak English. I have only diploma but most of my coworker see me as “I am the smartest person and well educated” because of my English skill. I read English bible, listen English music and my entire dream was to become Fereng. I never try to learn other Ethiopian spoken languche. SHAME ON ME & THEANK YOU DANIEL.

  ReplyDelete
  Replies
  1. still your English is not as good as you claiming.

   Delete
  2. Most peoples feel that you are very smart man, because you criticized other's English writing skill.

   Delete
 3. It is what it is and everything has time. As you know that we are in a big problem because of rain shortage. Our government and other political party tell the world to get emergency help but nobody answer for our question. When the BBC news maker reported about the drought most countries have been promised and start helping us. To promote our countries product and attract the visitor we have to rich to foreign writer. For example you have a blog but only Ethiopian follow your blog other people don’t know how to read Amharic and they don’t know you. In conclusion until we get attention or respect from other countries we have to go this way.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Mr Anonymous
   ዲን ጊዜውን ያልጠበቀ ጥሁፍ የጣፈ አይመስለኝም ምስጢር ያዘለ እንጂ
   ምክንያቱም ድርቅ ላይ ነን የሚለውን ጩሐታችን ፈረንጅ መቶ ካልተናገረልን ሰሚ አጥተናልና። መንግስታችን እንደሆን ሆዱ ተርቦ እሳት ይሞቃል እንዲል ዘፋኙ ህዝቡ ተርቦ ቤት ይገነባል።

   Delete
 4. ውብ ብለሃል ወንድም ዳኒ! ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ርሃብ ጉዳይ ግን የምትለው ነገር ቢኖር መልካም ነበር።ሁላችንም የድርሻችንን የምንወጣበት ለወገናችን የምንደርስበት እምነት የሚጣልበት አሰራር ቢኖር እጃችንን ለወገናችን ብንዘረጋ እና አንድም ብራብ አበላችሁኝ ተብለን ዋጋ እንድናገኝበት፤አንድም ደግሞ ወገናዊ ግዴታችንን መወጣት ስላለብን።

  ReplyDelete
 5. ጉዱ ካሳ በምናብ ይመጣል በገሀድ ይሉሀል ይሄ ነው፥ከዘመኑ የቀደመ ምርጥ ጥሁፍ ዳያቆን ፥ቀድመን ሮጠን አጨራረር ሳንችል ቀርተን የኛ መገለጫ ድህነትና እርዛት ቢሆን ግዜ ፈረንጅ ተከበረ ፥ተመለከ።እና በምን ስሌት በየትኛው ቀመር የእኛ የኛ ይሽተት፥ሚዲያው የሚያራግበው የሀገሩን ፍሬ ሳይሆን የተውሶ ፈርፋሪ ፈረንጁን ሰልባጁን ምን ቃላት ደግሞ አለው ለፈረንጁ ለዚህም ነው መሰል"ጥቁር ጥቁርን ሲያከብር አታይም" የሚለው ፈረንጁ ተጠግተህ ስትጠይቀው፥እርሱ ግን ቢናቆርም ይግባባል ፈረንጁ፥ለጥናትም ይሁን ለጽሁፍ ማድመቂያ ምስክር ብትጠራ ያው ፈረንጁን፥ አበው ነጻ ሀገር ሰጥተውን ባንድ ወቅት ግን በፈረንጅ ውስጥ የምንኖር ሰዎች ፥አበሾች።።።

  ReplyDelete
 6. ሰላም ዲያቆን ዳኒ, ቃለ ህይወት ያሰማህ. የሚገርም ነው ሰንት ጀግኖችን ,ሊቆችን ና ምሁሮች እንዳላፈራች ይህ ሁሉ ሲሆንባት ማየት በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው .ምን እንበል? ለማን እንጬህ? አቤቱ ሰለቀደሙት ብለህ ኢትዬጵያን አስባት አሜን!!!ዲያቆን ዳኒ, መድሃኒያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 7. "ውጭ ልካ ያስተማረቻቸው፣ በሥራ ልምድ ያበሰለቻቸው ልጆቿን፤ አስሳ፣ የማርያም መንገድ ሰጥታ፣ የጎደላቸውን ሞልታ ‹ያገሩን በሬ ባገሩ ሰርዶ‹ ማድረግ ትታ፣ በአድዋ በኩል ያሸነፍነው ፈረንጅ በአስተሳሰብ በኩል ገብቶ፣ ይኼው በዕውቀት አንሰው በንጣት ለሚበልጡ ሰዎች ‹‹ማናጅመንቱ ይሸጣል››፡፡ "

  በጣም ጥሩ እይታ እና የእኔ እና የጉዋደኞቻችን ህይዎት ጥርት አድርጎ የሚያሳይ ፅሁፍ ነው። እና ታዲያ ሃገሪቷ እንዲህ አድርጋ እንዲያ አድርጋ ክምንል፥ ከጻፍን አይቀር ፥ ክጫካ በመጣ ፍልስፍና ይህች ድሃ ሃገር የተማረ ስው ሳይሆን የፓርቲውን አላማ እስካስፈጸሙ ድረስ ባለ ሚኒስትሪዎችም፥ "ሚንስትሮች" መሆን ይችላሉ ተብለው ቦታው ላይ ጉብ ብለው ሰፍረው ታናናሾችን እያማረሩ ያባረሩትን ሆዳሞች ቢቻል በስም ባይሆን በያዙት ስልጣን ስም አጋልጦ ማሳየቱ ይሻላል እንጅ»»ያው እንደተለመደው የውስጣችንን ጩኽት በጡመራ ሸፈንፈን አርገን ተንፍስነው፣ ቀጥተኛ የሚመለከትው ሰው እርሱ ራሱ ቢያነበው "ምን ይደረግ! ...ይህች ሃገር አልታደለችም" ብሎ እንደሚያልፍው አልጠራጠርም።

  እኔ ልጀምር፥ የ"ዋልዋ" ልጅ እንዴ ሂልተን ሆቴል በተደረገ የ ''IT" ሲምፖዚየም ጠያቂዋ " Mr. Minster ...your country is loosing a huge number of highly educated manpower every year .....what is your reaction on that ?

  መልስ » መንገዱን ጨርቅ ያርግላቸው! - Literally

  After 10 years...

  The country's higher educational institution ,Gondar University,cordially awarded this same person an honorary doctorate stating "based on their contribution to our country in their line of work"

  ReplyDelete
 8. እጀግ ግሩም አስተያየት ነዉ፡፡ የ ሚያነብ እና የሚሰማ ቢኖር
  ለማንኛዉም እ/ር ይባረክህ፡፡ የ አገልግሎት ጊዚህን ያርዝምልን

  ReplyDelete
 9. ሰሚ ከተገኘ ዳኒ ሁሌ እይታህ በጣም ጥሩ ነው ፡፡

  ReplyDelete
 10. ‹ያገሩን በሬ ባገሩ ሰርዶ‹ ማድረግ ትታ፣ በአድዋ በኩል ያሸነፍነው ፈረንጅ በአስተሳሰብ በኩል ገብቶ፣ ይኼው በዕውቀት አንሰው በንጣት ለሚበልጡ ሰዎች ‹‹ማናጅመንቱ ይሸጣል››፡፡

  ReplyDelete
 11. ዲ/ን ዳንኤል እናመሰግናለን፡፡ እጅግ በጣም የሚገርም እይታ ነው፡፡ ፈረንጅን የመካብ ፈረንጅ የተናገረው ያደረገው ያየው ሁሉ በአጠቃላይ እውነተኛና የሚታመን ጥሩ እንደሆነ በሁሉም ህብረተሰብ ላይ ተቀባይነት ያገኘ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም እንኳን ፈረንጆቹ በኢኮኖሚና በስልጣኔ ከእኛ ቢበልጡም ፈረንጅን ማምለካችን ያሳዝናል…አስተሳሰባችንን ሰልበውናል… ፈጣሪ ይጠብቀን

  ReplyDelete
 12. በጣም ትክክል ነው፤ ከነጭ አምላኪነት ያውጣን

  ReplyDelete
 13. ዜጎች ማንኛውም ነገር በራሳቸው አቅም እና እውቀት ቢሰሩ ተመራጭ ነው። ነገር ግን አንዳንድ በራስ አቅም ለመስራት የሚያዳግቱ ወይም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ይኖራሉ። ዘመኑ ደግሞ የአለም ህዝቦች ትስስራቸውን በከፍተኛ ፍጥነት የሚያሳድጉበት ስለሆነ ከአለም ህዝቦች መማሩ ክፋቱ አልታየኝም። ነገር ግን የኛ ሀገር ሊቃውንትና ጠቢባን የሚያስተላልፉትን እውቀትም በተገቢው መንገድ መያዝ ግዴታችን ነው። ሊቃውንቶቻችንም አለም የደረሰበት የእውቀት ጫፍ ግምት ውስጥ በማስገባት በምክንያት የተደገፉ ሳይንሳዊ ውጤቶች ካቀረቡ አሁኑ ትውልድ ተቀባይነታቸው እየጨመረ እንደሚመጣ አልጠራጠርም። የአያት የቅድመ አያት...እውቀት አሁን ላለውና ለተተኪ ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ ግን የሁሉም ኢትዮፕያዊ ነው።

  ReplyDelete
 14. ጥሩ ብለሃል ወንድም ዳኒ
  ሰሚ የለም እንጅ አይዞህ
  በርታ ለኛም ሰሚ ልቦና
  ይስጠን አሜን

  ReplyDelete
 15. Dani I watched last week Dera Tube program, the program was question and answer. The questions were, what is the current Ethiopian president and Addis Ababa kentiba ? From fifty people only two people answered the question. If he asks about Manchester united and Arsenal coach the answer will be 50/50. This means we don’t care about our government or history.

  ReplyDelete
 16. no word dani thank u

  ReplyDelete
 17. Yes, Thank you. We lost our identity willfully. Shame on us.

  ReplyDelete
 18. Abet Tsega!!! Egiziber Abzeto yebarkih. Yitebkihi. Amen

  ReplyDelete
 19. እግዚአብሔር ይጠብቅህ የልቤን ነው ያደረስከው! ዻኒ

  ReplyDelete
 20. ሀገሪቱ ከልጅነት እስከ ዕውቀት፣ ከሽበት እስከ ኩተት ያሳደገቻቸው፤ ‹ይማርልኝ ብዬ በጌምድር ሰድጄ› እንደተባለው ውጭ ልካ ያስተማረቻቸው፣ በሥራ ልምድ ያበሰለቻቸው ልጆቿን፤ አስሳ፣ የማርያም መንገድ ሰጥታ፣ የጎደላቸውን ሞልታ ‹ያገሩን በሬ ባገሩ ሰርዶ‹ ማድረግ ትታ፣ በአድዋ በኩል ያሸነፍነው ፈረንጅ በአስተሳሰብ በኩል ገብቶ፣ ይኼው በዕውቀት አንሰው በንጣት ለሚበልጡ ሰዎች ‹‹ማናጅመንቱ ይሸጣል››፡፡
  ፈረንጅ ሆይ ናና
  ባንተ ያምራልና
  ትሰማለህና
  ትከብራለህና

  ReplyDelete
 21. 'የሳጥናኤል ጎል በኢትዮጵያ'

  ReplyDelete
 22. አንዱ የመክሽፍ ምልክት ይህ ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 23. ERE DANI MINU KITU!!!! SEW BETEWELEDEBET HAGER ENDEBARIYA......

  ReplyDelete
 24. ጥሩ ሀሳብ ነው፡፡ ያየሀውን/የተገነዘብከውን በመግለጥህ ትመሰገናለህ፡፡ በዚህም የሰዎችን ሀሳብ ትገዛለህ፡፡ ደጉን ታሳያለህ፡፡ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ቀጥልበት ወንድሜ፡፡

  ReplyDelete
 25. ውጭ ልካ ያስተማረቻቸው፣ በሥራ ልምድ ያበሰለቻቸው ልጆቿን፤ አስሳ፣ የማርያም መንገድ ሰጥታ፣ የጎደላቸውን ሞልታ ‹ያገሩን በሬ ባገሩ ሰርዶ‹ ማድረግ ትታ፣ በአድዋ በኩል ያሸነፍነው ፈረንጅ በአስተሳሰብ በኩል ገብቶ፣ ይኼው በዕውቀት አንሰው በንጣት ለሚበልጡ ሰዎች ‹‹ማናጅመንቱ ይሸጣል››፡፡

  ReplyDelete
 26. ውጭ ልካ ያስተማረቻቸው፣ በሥራ ልምድ ያበሰለቻቸው ልጆቿን፤ አስሳ፣ የማርያም መንገድ ሰጥታ፣ የጎደላቸውን ሞልታ ‹ያገሩን በሬ ባገሩ ሰርዶ‹ ማድረግ ትታ፣ በአድዋ በኩል ያሸነፍነው ፈረንጅ በአስተሳሰብ በኩል ገብቶ፣ ይኼው በዕውቀት አንሰው በንጣት ለሚበልጡ ሰዎች ‹‹ማናጅመንቱ ይሸጣል››፡፡

  ReplyDelete
 27. You point of view is interesting.

  ReplyDelete
 28. Dn Daniel, an interesting view.

  ReplyDelete
 29. አንዱ የመክሽፍ ምልክት ይህ ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 30. በምኒልክ አደባባይ አንጂ በፑሽኪን አደባባይ ማን ይከራከራል፡፡ በበላይ ዘለቀ መንገድ እንጂ በቼርችል ጎዳና ማን ይከራከራል፡፡

  ReplyDelete
 31. abo temechehenge ene yarada lej nenge gin maneneten saresa beethiopiawinet kiber kebede michael,tsegaye g/medhin,haddis alemayehu......................e.t.c kotekutew yasadegunge merte ETHIOPIAWI

  ReplyDelete
 32. እውነት ነው፤ የፃፍከው ነገር እጅግ ያማል! ያሳዝናል! አሁን እንኳ ፈረንጅ መጥቶ ተርባችኋል፤ ድርቅ ላይ ናችሁ ሲለን አደል ሆ ብለን የተነሳነው? ለምን የኛ ጋዜጠኞች አልነገሩንም መጀመሪያ ፈረንጅ መጥቶ እስኪነግረን ለምን ጠበቅን?? ብዙ ግዜ ሰዎች ለሚሰሩት ነገር ማረጋገጫቸው "ፈረንጅ እንኳን ያደርጋል" ሲሉ ይገርመኛል፤ ፈረንጅ የራሱ ጉዳይ! አንተ መሆን ወይም አለመሆን ያለብህ ማንም ስላደረገ ወይም ስለማያደርግ መሆን የለበትም… የራስህ እምነት እና አቀቋም ልትይዝ ይገባል!!

  ዳንኤል፣ አመሰግናለሁ ልክ ልካችንን ስለምትነግረን!!

  ReplyDelete
 33. አንተ ወደ ፈረንጅ ብትሄድ አይሻልም?

  ReplyDelete
 34. እዮቤል ደጀንNovember 19, 2015 at 7:59 PM

  አዬ ጉድ, በእጅ የያዙት ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል አለ ያገሬ ሰው. እ/ር ይስጥህ ዲ.ን ዳኒ.

  ReplyDelete
 35. ወንድም ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በቅድሚያ ላንተ ያለኝን ታላቅ አክብሮት ልገልጽልክ እወዳለሁ። በመቀጠል ሁሌም ያንተን ጽሑፍ ሳነብ እራሴን እንዳይ ይረዳኛል። በጣም አስተማሪና መካሪ ናቸው። እግዚአብሔር የልፋትህን ውጤት ያሳይህ። ከዚህ የበለጠ እንድትሰራ ይርዳህ። ፍጻሜህን ያሳምርልህ።

  ReplyDelete
 36. ግርማ ወንዳለNovember 20, 2015 at 9:04 AM

  ግሩም አቀራረብ ነው! እኔ ግን ፈረንጅነታቸው ብቻ አይቆጨኝም፡፡ ኢ-አማኒ ሆነው ቤተ-መቅደስ፣ ቤተ-መዘክር መንበረ-ጳጳስ ሢከፈትላቸው ይነደኛል፡፡ ግን ለምንድን ነው ቁዋንቁዋውን፣ መፅሐፍቱን፣ ቅዱሳት መካናትን፣ ወንዞችን የሚጎበኙት!!! ታቦተ ጽዮንን አሊያም መጽሐፈ-ሰሎሞንን ከመሻት (ከመመኘት) አይመስልህም ዳኒ፡፡
  ለምሳሌ ጀምስ ብሩስ፡ እውነት የዓባይን ምንጭ ለማጥናት ነበር የመጣው!!! ባይሳካለት እንጂ ሌላ እንደፈለገ ይሰማኛል፡፡

  ReplyDelete
 37. ግርማ ወንዳለNovember 20, 2015 at 9:08 AM

  ግሩም አቀራረብ ነው! እኔ ግን ፈረንጅነታቸው ብቻ አይቆጨኝም፡፡ ኢ-አማኒ ሆነው ቤተ-መቅደስ፣ ቤተ-መዘክር መንበረ-ጳጳስ ሢከፈትላቸው ይነደኛል፡፡ ግን ለምንድን ነው ቁዋንቁዋውን፣ መፅሐፍቱን፣ ቅዱሳት መካናትን፣ ወንዞችን የሚጎበኙት!!! ታቦተ ጽዮንን አሊያም መጽሐፈ-ሰሎሞንን ከመሻት (ከመመኘት) አይመስልህም ዳኒ፡፡
  ለምሳሌ ጀምስ ብሩስ፡ እውነት የዓባይን ምንጭ ለማጥናት ነበር የመጣው!!! ባይሳካለት እንጂ ሌላ እንደፈለገ ይሰማኛል፡፡

  ReplyDelete
 38. እጅግ የሚገርም ጽሁፍ 

  ReplyDelete
 39. As usual, insightful and educative. Libona yosten.

  Egze'abher Yistlin

  ReplyDelete
 40. ሰላም ዳኒ፡ ሀሳቡ ጥሩ ነው ግን በግልፅ አላማው አልገባኝም እነሱን ማስተዋወቅ ነው እንዴ! በግልጽ መልእክት ተናገረው የራሳችንን ነገር በራሳችን ቢሆን በለው፡፡ በግልጽ ከ ዘመናዊ ባርነት እንውጣ በለው ፡፡ ይብቃ በቀለም እና በተናጋሪው ማመኑ በለው፡፡
  በል ቻው

  ReplyDelete
 41. Betam dink melikt, Egziabhear yistlin

  ReplyDelete
 42. Betam dink melikt, Egziabhear yistlin

  ReplyDelete
 43. ግሩም አቀራረብ ነው! እኔ ግን ፈረንጅነታቸው ብቻ አይቆጨኝም፡፡ ኢ-አማኒ ሆነው ቤተ-መቅደስ፣ ቤተ-መዘክር መንበረ-ጳጳስ ሢከፈትላቸው ይነደኛል፡፡ ግን ለምንድን ነው ቁዋንቁዋውን፣ መፅሐፍቱን፣ ቅዱሳት መካናትን፣ ወንዞችን የሚጎበኙት!!! ታቦተ ጽዮንን አሊያም መጽሐፈ-ሰሎሞንን ከመሻት (ከመመኘት) አይመስልህም ዳኒ፡፡
  ለምሳሌ ጀምስ ብሩስ፡ እውነት የዓባይን ምንጭ ለማጥናት ነበር የመጣው!!! ባይሳካለት እንጂ ሌላ እንደፈለገ ይሰማኛል፡፡


  You are the comment above James bruse deliberately went to Ethiopia to look for the Ark of covenenant

  ReplyDelete
  Replies
  1. And he couldn't find it as it didn't exist

   Delete
 44. Thank you Daniyee as always. Our failer starts when we start giving Ye Ferenje Name for our own kids.Sheshit from Ethiopiawinet

  ReplyDelete
 45. Dani you remaind me back in a day when keble selling bread which was 10 breads 1 Birr 10cents each( they came 8 regular bread and two White bread used to call Michel Dabo) But the interesting thing was Those two Michel dabo were special and My mam used to keep to My Dad !! guess what I was telling to my friends as a joke so many times then here you are with this article. God bless your family Danni.

  ReplyDelete
 46. ቀይ ሰው መልክ አይፈጅም
  የቅዱስ ሚካኤል ምስል ፡መልአኩን ፈረንጅ ጥቁሩን ሴይጣን

  This is not only Ethiopian problem.It is an intrinsic psychic "problem"of all black/brown people.Africa,and to a lesser extent Indian subcontinent. ነጭ አምላኩ.
  I think it is in our DNA ,a curse of Ham or kush.
  አብዲሳ አጋ እና ባልቻ ነበሩ የሳር ቤቱ ሀውልት የሚገባቸው.
  BTW I do not have anything againt Carl H.He is a good man.My daughter and son tired of seeing ferengi hawelt in US..And I was ashamed when they see another ferengi hawelt....
  ReplyDelete
 47. Zekios Ze kuskuam GondarNovember 23, 2015 at 5:27 PM

  A well written article. It described the current situation well. It could be more than a rhetoric if you attach some references. This has to a national agenda and should be talked about in mainstream medias of the country(if any). Immense gratitude and appreciation to you brother Daniel.

  ReplyDelete
 48. ጥሩ እይታ አናመሰግናለን

  ReplyDelete
 49. I do not hate you but I hate your hypocrisy. You preach and write what you do not practice yourself. Do not write and preach for the sake of it or just because you can.

  You are such a pathetic person.

  ReplyDelete
 50. Dani,

  We have ten thousand preachers and writers who can point out what is wrong with us. The wrongs that we already know but none who can lead by example. There was one and he is behind prison bar.

  talk talk talk .....write write write..... blah blah blaha blah......

  ReplyDelete
 51. Selame Dani,

  Here is one excellent observer commented about scribbler like you:

  “እንግዲው ብዙ ጠሊው ቀጭን ነው” እንዱለ አንተም በሳምንት ሶስትና አራት ጽሁፍ ሇማምረት ስትሌ እውነታውን በሌቦሇዴ፤ ሪፖርቱን በትንቢት እያቀጣጠንክ በምትሇቀው ጽሁፍ ትዝብት ውስጥ አትውዯቅ። የየጁ ዯብተራ ቅኔው ሲጎሌበት ቀረቶ ሞሊበት እንዯተባሇው የሰሞኑ ጽሁፍህ ቀረርቶ በዝቶበታሌ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. How many days you took to write the aforementioned two sentence critics. Deacon Daniel is really smart.

   Delete
  2. this dead head guy appears to be just arrived from jungle

   Delete
 52. Can I get the English version of it dear Daniel Kiberet? Any one who can help me?

  ReplyDelete
 53. I found your view is qite nice however, you guys also need to learn how the critic should go along with.
  You were the one who was adversely condmened pro Getachew Hailes book Dekike estifanos that has been translated from Geez to Amharic and had been buried for long .

  ReplyDelete
 54. ጥሩ አድርገህ ገለጸኸዋል .... በቤታችን ካለው ለውጪው ጆሮአችንን የምንሰጥ ልባችንን የምንከፍት እንበዛለን .... ሀበሻ በአገሩ ደሙ መራር ነች... የሚጣፍጠበት ጊዜ ያምጣልን!! ..... አነተንም አብዝቶ ይባርክልን!!

  ReplyDelete
 55. It is so sad Ethiopians don't get any respect and acceptance both at their home country and being an immigrant. Where on earth that we are first citizens... not discriminated and being accepted as we are. Shame on each of us.

  ReplyDelete
 56. ምን አባቴ ላድርግህ ድንቅ አድርገህ ነው የገለጽከው። እንደሁልጊዜው ማለት ነው። እግዚአብሄር እድሜ እና ጤና ይስጥህ። ምርጥ ኢትዮጲያዊ ነህ የቀደምት አባት እና እናቶቻችን እውቀት እና ጥበብ የገባህ ያስተዋልክ።

  ReplyDelete
 57. It is true!we egnore our habesha personality.D/N daniel view is encouraged view. long live to you!

  ReplyDelete
 58. መምህር፡ እውነት ለመናገር ከሆነ ብታም ስደሰተኝ እይታ ነው ሊያውም ምንም እንከን የማይወጣለት እይታ፡፡ አንድ ጊዜ ጋሽ ሙላቱ የቀድሞው የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት በዓንድ መድረክ ላይ ሲናገሩት የሰማሁትን ነው ያስታወስከኝ “ …እኛ ፈረንጅ ያልባረከው አይመቸንም” ለማንኛውም ሁልመ የራሳችንን ልማውቅ እና ለመፈለግ ብንሞክር ጥሩ ነው እላለሁ…. አባቶቻችን ለእኛ ቀርቶ ለዓለም የሚበቃዉን ውብ ነገር አውርሰውናልና፡፡

  ReplyDelete