Tuesday, October 27, 2015

የወታደሮቻችን ነገር


አፕሪል 12፣ 1868 የተጻፈ
click here for pdf
የመቅደላው ጀግና ዐፄ ቴዎድሮስ በመጨረሻዋ ሰዓት ለጄኔራል ናፒየሪ በጻፉት ደብዳቤ አበክረው የጠየቁት ነገር ከሁለት ቀናት በፊት በተደረገው ውጊያ የወደቀውን የወዳጃቸውንና የጦር መሪያቸውን የፊታውራሪ ገብርዬን አስከሬን ለመቅበር እንዲፈቀድላቸው ነበር፡፡ ‹‹ፊታውራ ገብርዬን የኔን ወዳጅ ሳላነሣው ያደርኩ ከሞትኩኝ ሁሉንም አብረው ይቅበሩኝ ብየ ነበር፡፡ ቁሜ ከዋልኩ ግን ልቅበረው ይፍቀዱልኝ›› ይላል ደብዳቤው፡፡ ለሀገሩና ለወገኑ በክብር የተሠዋ አስከሬኑም የክብር ዕረፍት ይሻዋልና፡፡
አሜሪካኖችና አውሮፓውያን የተሰጣቸውን ግዳጅ ለመወጣት የዘመቱ ወታደሮቻቸው ሲሠው በክብር አስከሬናቸውን ወደ ሀገር በማምጣት በብሔራዊ ሥነ ሥርዓት የመቅበር ያልጠፋ ልማድ እንዳላቸው በየጊዜው ሚዲያው ያሳየናል፡፡ እነዚህ ወታደሮች ሀገራዊ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የዘመቱ በመሆኑ መሥዋዕትነታቸውም ሀገራዊ ሆኖ መታሰብ አለበት፡፡
በኢትዮጵያ የቅርብ ዘመን ታሪክ የተሠዉ ወታደሮችን በክብር የመዘከር፣ በክብር የመቀበልና በክብር የመቅበር ሥነ ሥርዓት አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ በኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት የተሠዉ ስንት ወታደሮች ናቸው? የተሠዉትስ ወታደሮች መርዶ እንዴት ተነገረ? የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውስ እንዴት ተከናወነ? ሚዲያውስ ለዚያ ምን ዓይነት ሽፋን ሰጠው? የሁል ጊዜ ጥያቄዬ ነው፡፡ እኔ ሳልሰማና ሳላውቅ ተከናውኖ ካልሆነ በቀር፡፡ ለምንስ አስከሬናቸው በወታደራዊ ሥነ ሥርዓት ታጅቦ፣ ሰንደቅ ዓላማ ለብሶ፣ ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ፣ ሕዝቡ ወደ አደባባይ በነቂስ ወጥቶ አላከበርናቸውም? እያልኩ እጠይቃለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር በአፍሪካ ልዩ ልዩ ሥፍራዎች ዘምቷል፡፡ ሲዘምትም በክብር እንደተሸኘ በሚዲያዎቻችን አይተናል፡፡ እነዚህ ዘማቾች ሁሉም በሰላም ነው የተመለሱት? የተሠዋ ካለ ለምን ይፋዊ በሆነ ሀገራዊ ሥነ ሥርዓት አስከሬኑን ተቀብለን አልቀበርነውም? ፖለቲካው ተፈርቶ ከሆነ ለግዳጅ የተሠማራ ወታደር ወይ በድል መመለስ፣ ወይ መማረክ፣ ወይ መቁሰል አለያም መሠዋት እንደሚያጋጥመው እንኳን እኛ ታሪካችን በጦርነት የተሞላው ቀርቶ ሌሎችም ያውቁታል፡፡  

የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሶማልያ ሲዘምቱ ፓርላማው ወስኖ ነው የዘመቱት፡፡ የሄዱት በእር በርስ ጦርነት ሲታመስ ወደኖረውና እጅግ አስቸጋሪ ወደሆነው የጦርነት ሥፍራ ነው፡፡ ከሶማልያ መንግሥት ወታደሮችና ከአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር ጋር በጋራ በመሆን በሶማልያ ከአልሸባብና ከሌሎችም ኃይሎች ጋር በመዋጋት ያገኙትን ድል ሚዲያዎቻችን ይዘግባሉ፡፡ መቼም የሄዱት ለጦርነት ነውና፣ በጦርነት ውስጥ መግደል፣ ድል ማድረግና መማረክ እንዳለ ሁሉ መሞት፣ መቁሰልና መማረክም አለ፡፡
ታድያ የሀገሬ ወታደሮች አልተሠዉም፣ አልቆሰሉም፣ አልተማረኩም? የሄዱት ሁሉ ሰላም ናቸው? ከሆኑ መልካም፡፡ ግን ቦታውም የነ አልሸባብ ቦታ፣ ሁኔታውም ጦርነት፣ ሰዎቹም ወታደሮች ናቸውና ቢያንስ መሞትና መቁሰል አይቀርም፡፡ የአሜሪካና የአውሮፓ ሚዲያዎች በአፍጋኒስታን፣ በኢራቅና በሶርያ ጦርነት የተሠዉትንና የቆሰሉትን ማንነት እንደሚናገሩት፣ በክብርም ሲቀበሩ እንደሚያሳዩት፣ የኛዎቹ የተሠዉት በክብር ሲቀበሩ፣ የቆሰሉት በክብር ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ለምን እንደ ሕዝብ አናያቸውም? ለመሆኑስ በክብር የተሠዉ የኢትዮጵያ ወታደሮች መቃብር የት ነው?

ወደኋላም ተመልሰን ከአድዋ ጦርነት በኋላ የሆነውን ስናስታውስ በእንዳ ኢየሱስ ያለው የአባቶቻችንን መቃብርና ከዚያ እልፍ ብሎ የሚገኘውን የጣልያኖች መቃብር መመልከቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በእንዳ ኢየሱስ የሚገኘው የአድዋ ዘማቾች አባቶቻችን መቃብር ለመሥዋዕትነታቸው የማይመጥን ነው፡፡ አልፎ አልፎም ፈርሶ እናየዋለን፡፡ የጣልያኖቹ መቃብር ግን በክብር ታጥሯል፡፡ ጠባቂም ተመድቦለታል፡፡ መቃብሩንም ለማየት የጣልያን ኢምባሲ ፈቃድ ይጠይቃል፡፡ 

በአሥራ ሰባቱ የደርግ ዓመታት የዘመቱት ወታደሮች ኢትዮጵያ የመለመለቻቸው፣ ያሠለጠነቻቸውና ያዘመተቻቸው ነበሩ፡፡ ምንም ጦርነቱ የእርስ በርስ ጦርነት ቢሆንም፡፡ የተሠዉት አብዛኞቹ ወታደሮች ለቤተሰብ መርዶ አልተነገረም፡፡ በተለይ ኤርትራ በረሃ የቀሩት መጨረሻቸው ምን እንደሆነ አልታወቀም፡፡ ጦሩ ሲበተን ወደ ቤተሰባቸው መምጣት የቻሉት ቁርጣቸው ታወቀ፤ ከዚያ ውጭ ያሉት ግን አሁንም ለቤተሰብና ለሀገር ጥያቄ እንደሆኑ ናቸው፡፡
የአንድ ወታደር ክብር የሀገራዊ ዓላማና የሀገራዊ ግዳጅ ክብር ማሳያ ነው፡፡ አሜሪካ ውስጥ በአውሮፕላን በተጓዝኩ ቁጥር ለአሜሪካ ወታደሮች የሚሰጠውን ክብር አደንቃለሁ፡፡ አውሮፕላኑ ምድር ደርሶ ተሣፋሪዎቹ እንደተቀመጥን ለወታደሮቹ ቅድሚያ ተሰጥቶ እያጨበጨብን ወደ በሩ እንሸኛቸዋለን፡፡ ወደ አውሮፕላን ውስጥ ስንገባም አስተናጋጆቹ ‹ዩኒፎርም የለበሱ ጀግኖቻችን አሉና እናክብራቸው›› ብለው ያውጃሉ፡፡ ሁላችንም እንጨበጭባለን፡፡ እኔ የሀገሬ ወታደር በአውሮፕላን እንኳን ባይሆን በታክሲና በአውቶቡስ፣ በመዝናኛ ቦታዎችና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዲህ ሲከብር ማየት እናፍቃለሁ፡፡
ወታደሮቻችንን ጉሮ ወሸባየ ብለን እንደሸኘናቸው ሁሉ የጀግና አቀባበል እንድናደርግላቸው፣ ሲሠዉ በክብር አደባባይ ወጥተንና የሞቱለትን ሰንደቅ ዓላማ አልብሰን እንድንሸኛቸው፣ የቆሰሉትን በክብር እንድንቀበላቸው፣ ያስገኙት ድል ብቻ ሳይሆን የገጠማቸው ፈተናና የከፈሉት መሥዋዕትነትም እንዲነገርላቸው እመኛለሁ፡፡ የክብር አቀባበልን ላሸነፈ ሯጭና እግር ኳስ ተጨዋች፤ የክብር አቀባበርንም ለአርቲስት ብቻ ማን ሰጠ?

75 comments:

 1. A very good perspective. It's also annoying to see that many priests ignore the prayer for soldiers at Melka Kurban and replace 'woserawita' with 'wohaymanota'. the latter doesn't make sense in the context.

  ReplyDelete
 2. የክብር አቀባበልን ላሸነፈ ሯጭና እግር ኳስ ተጨዋች፤ የክብር አቀባበርንም ለአርቲስት ብቻ ማን ሰጠ?

  ReplyDelete
 3. የክብር አቀባበልን ላሸነፈ ሯጭና እግር ኳስ ተጨዋች፤ የክብር አቀባበርንም ለአርቲስት ብቻ ማን ሰጠ? እውነት አልክ ወንድሜ፡፡ አቤት እይታህ………፣ እግዚአብሔር ይባርክህ ደስ የሚል እይታ ነው፡፡ እኔም ይህንን ቀን እናፍቃለሁኝ፡፡ ስንት እናቶች የልጆቻቸውን ደም ወይም በሕይወት መኖርና አለመኖር ባለማወቅ እንደናፈቁ የቀሩና አሁንም ደጅ፣ ደጅ የሚሉ እናቶች አሉ፡፡ ጌታ እግዚአብሔር በቃችሁ ይበለን፡፡

  ReplyDelete
 4. የክብር አቀባበልን ላሸነፈ ሯጭና እግር ኳስ ተጨዋች፤ የክብር አቀባበርንም ለአርቲስት ብቻ ማን ሰጠ?

  ReplyDelete
 5. Ere tew tew tew ante sew ehe neger aymeleketihm, aygebahim atkelakil, atiwred!!! yebetekristianun neger wedet geshesh aderekew?

  ReplyDelete
 6. lega malkam blhale mach keber lwtader mstat tlemed ymototme yalewetm ekule new nwrachaw yza wetaderwech ensw lagerachew keber landentachw slew ytwagweten en ymatweten ykosalewten yethiopia weteder yderg wetader tblew sem endwetalechaw atwekem enzhzwechewn metchem gegne new bza gethe yall weteder lmalet yoneal tawez yebkaz kweslen nekthawe new ytnfaskut!!" tdekew kertobez bketw bkonnz" blew ytaretwet ykadmow abtochcen!!

  ReplyDelete
 7. ክብርና ሞገስ ለሁሉም ሰዉ የተገባ ቢሆንም፣እንዲያዉ የለም ደረጃ ይዉጣለት ብለን ብንስማማ፣ለእኔ ዉድ የሆነዉን ህይወት አሳልፎ የሚሰጥ ወታደር ለእኔ አንደኛ ነዉ፡፡ ታዲያ እንዲህ ከሆነ እንደተባለዉ ብዙ ወገኖቻችን ዉድ ቤተሰቦቻቸዉንና ያደጉበትን ቀዪ ትተዉ እንዲሁ እንደወጡ የቀሩ ብዙ ናቸዉ፡፡ አይደለም ስለአሟሟታቸዉ ይቅርና በእርግጥ ስለሞሞታቸዉ ሳንሰማ የቀረን ቀላል አንሆንም፡፡ በምን ምክንያት እንደማይነገር ለጊዜዉ ባይታወቅም፣እንዲህ በመሆኑ ግን ያሳዝናል፡፡ ለወደፊቱ ይህ ነገር ታስቦበት የሚገባቸዉን ክብርና ሞገስ እንዲያገኙ ቢደረግ ምኞቴ ነዉ፡፡ መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ…………!!!!

  ReplyDelete
 8. Dany it is nice the responsible body should give attention.

  ReplyDelete
 9. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 10. Daniel goes far. “She doesn’t have food but she want to dress expensive scrub” First of all there is no comparative between USA and Ethiopia. I don’t blame you even if you compare it because the government said “our economy growth is double digit and only 8.2million people need urgent support.” During World War II and before all American buried outside the country after that they start bring into their country. To berried one solider it costs more than 3million dollar. American can afford it but it is not possible Ethiopia. In current situation everyday three Ethiopians died in Somalia so it is difficult to cover this cost for our country. As you know that if the current government start bring this solider our tax increase more than this. How we can afford?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ድንቁርናን እና አለማስተዋልን የእውቀት እና የጥበብ ሠራዊት ይዝመትባቸው!!! መጋጠሚያው የእርስዎ ልቡና ይሁን !!!

   " afford" .... ምንድን ነው እሱ?

   ምን ዋጋ አለው ከድል በኋላ ዘማቾቹን ይረሷቸዋል ወይም afford afford ይሉ ይሆናል!

   ለመሆኑ ተመኑን ከየት አገኙት? ይህ ጉዳይ =ክፍያው- ለርስዎ የቀረጥ ነው... ለጀግናው ግን የሕይወት ነው !!!

   Delete
  2. አንድ የተሰዋየአሜሪካ ወታደርን ለመቅበር 3 ሚሊዬን የአሜሪካን ገንዘብ (dollar) ያስፈልጋል?
   "ሥጥ እንግዲህ!" ይላል መንዜ እንዲህ አይነት መሰረተቢስ ወሬ ሲሰማ። ለመሆኑ በማርስ (Mars) ወይም በህዋ (space) ላይ ከተደረገ ውጊያ ነው የአሜሪካ ወታደሮች የሚመለሱት እንዴ? 3 million dollar for one soldier entombment (burial)? Hope nobody believe your absurd story!
   አስተያየት ለመስጠት እኮ ውሸት መፈበረክ አይደለም የሚያስፈልገው መረዳት እንጂ!
   አዲስ ነኝ።

   Delete
  3. I advice you to consult an economist! Are you telling as that it cost 3 million US dollar per soldiers? You know what you are underestimating our Ethiopian people. If it costs the government this much per soldiers compute how much it will costs your family to bring your body, because you are already dead.

   Delete
 11. Thank you so much Daniel for your comment because there is no opposition party so you have to give them different view.

  ReplyDelete
 12. ሰላም ዲያቆን ዳኒ, ዛሬ ደግሞ የፃፍክልን በጣም የሚያሳዝን የሚያሰቆጭ ፁሁፍ ነው. ለመሪዎቻችን ልቦና ይሰጥልን .የአገራችን ወታደሮችማ እንደ ከፋቸው ዘመቱ ብዙዎቹ ሳይመለሱ ቀ ሩ. ጥሩ ማረፊያ ሳይኖራቸው, የረባ ምግብ ሳይበሉ , ጤንነታቸው ሳይጠበቅ አንድ ቀን ጥሩ እንቅልፍ ሳይተኙ , ቤተሰባቸውን ትተው ትንሣሔዋን ለማየት ለጓጓላት ለእናት አገር እራሳቸውን ሰጡ. አርቲሥቶቹም ,እሯጮቹም ,ዶክተሮቹም ,ባለሥልጣኖቹም አስተማሪዎቹም ,ተማሪዎቹም....እነሱ በጠበቁት ድንበር ለይ ሆነው ነው ሥራቸውን የሰሩት . ከማንም በላይ ክብር ልንሰጣቸው ልንዘክራቸው ይገባል.በእውነትም ክብር ይገባቸዋል የማዕረግ ማረፊያ ቦታ ሊኖራቸው ይገባል .ያንን ቀን እንዲያመጣው እግዚሃብሔር የመሪዎቻችንን ዐይነ ልቦና ይክፈትልን .ዲያቆን ዳኒ,መድሃኒያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 13. ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል፥
  ይህንን ፅሁፍህ ከበፊቶቹ በተለየ የመረጃ እጥረት እንዳለበት ለመጠቆም እወዳለሁኝ፤
  ኣስፈላጊ ከሆነ ሌላ ግዜ በሰፊው እፅፋለሁኝ፤ለግዜው ግን የተወሰኑትን ልጠቀስ፥
  ፩። በኢትዮ፡ኤርትራ በተካሄደ ጦርነት የሞቱትና የቆሰሉት
  በዚህ ጦርነት የሞቱትና የቆሰሉት ለማንሳትና በክብር ለማሳረፍ በጣም ከፍተኛ ስራ ተሰረተዋል፤፤ በጦረነቱ ጊዜ ኣግላይ የሚባሉ የሰለጠኑ ግን ወግያ ያልጀመሩ ጀማሪ ወታዶሮች እግር በእግር እየተከታተሉ የሞተና የቆሰለ ኣንስተዋል፥፥
  ፪፥ በዚህ ጦረነት የኣከባቢው ወጣቶች፤ሚሊሺዎችንና (በኣጠቃላይ የሚች ሁሉ) በመከላከያ ከተወከሉ እየተመራ ከመከላከያ ሰራዊታችን እግር በእግር እየተከታተሉ የሞተና የቆሰለ ኣንስተዋል፤፤
  ፫፥ጦርነቱ ካለቀ በኋላከመከላከያ ሰራዊታችን ጦረንት የተካሄደባቸውን ኣከባቢዎች በሙሉ ለ ፮ ወራት ሙሉ እስከ ኤርትራ መሬት ዘልቆ ምሽጎችንና የውጊኣያ ቀጠናዎች ኣሰሳ በማድረግ በጦረነት ጊዜ ሳይነሱ የቀረቱ ካሉ ኣሰሳ ኣድርጓል

  ከዚህ በኋላም የያንዳንዱ የተሰዋ ኣባል ስም ዝርዝር በክብር ጦርነቱ በተካሄደበት ግንባ ኣቅራቢያ በተሰራ በተ መዘክር ወስጥ ኣኑረዋል፤ ብዙ ትምህርት ቤቶችም የነሱን ቡድን (ሻለቃ ክፍለ ጦር)በሚዘክር መልኩ ተሰይመዋል፥፥ ይህንን በቂ ነው ማለት ግን ኣላዋቂነት ነው። ለጀግኖቻችን የሚያንሳቸው ቢሆንም የተደረገው ነገር ሽምጥጥ ኣድርጎ መካድና እና ሁሉም ድሮ ቀረ የሚለውን ኣባዜ ግን በእርስዎ ኣያምርም። በሶማሊያ የተሰዉ ወጎኖቻችንም የሚሰጥ ክብርም በኢትዮ፡ኤርትራ በተካሄደ ጦርነት ከተደረገው በላይ እንጂ በታች ይሆናል የሚል እምነት ኣይኖረኝም፥፥

  ReplyDelete
  Replies
  1. Your are liar! we have seen the body of our soldiers scattered in the desert here and there and being eaten by the scavengers. The ruling party don't give a shit to our dignity even before our passage/death. All they need is to sacrifice ourselves to protect and safeguard their power. All of the are greedy, selfish and heartless.This government is a snatcher who snatch the dollar paid to the Ethiopian peace keeping soldiers to UNITED NATIONS.

   Delete
 14. Dn Daniel betam Yemewedhena yemakebrhe yemenfese kiduse ehethe negne gen menew gera atagabagna band bekule yet neberke asegehegne yahulu wetader ena betesebu bemeteleya weste sitagore ena lehageru baderegew messwat ena bekefelew meswatenet endemenamente betekoterebet weket esatem belayu laye eyeteleke sesekaye ende wegen endezga saykotere menew wedage bettewen Menew kuslachenen batnekka zem endalen bennorbet menew ene ye wetadere lege negna

  ReplyDelete
  Replies
  1. Anchis yane yet nebershi? yihin asteyayet yane atsechim naber? zimbilesh atawuri saw bederesbet bechalebet akimu befekede gize naw yeminagerew. bewoktu tilik derejana lemidiyaw kirbet yalachew tawaki gileseboch ena yemidiya dirijitoch naberu yihin tiyakeshin enesun tayiki. diakon daniel gin gizena botana teseminat siyagegn asteyayetun ena melkam eyitawun akafilonal Amlak yibarkew!

   Delete
 15. "tsideku keretobegne beketu bekonnenge"ale yagere sew twe enge Dn daniel wedet wedet.

  ReplyDelete
 16. መቼም አንተ የማትገባበት የለም። እውነት ተናገር ካልከኝ የኢትዮጵያን ህዝብ ከምረግምበት ነገሮች አንዱ ይህ ነው።ለሰራዊቱ ያለዉን ክብር ተወው ንቀቱን ቢተወው እንዴት መልካም ነበር።ወታደሩን መሪው እንደ እቃ ነው የሚያየው፤ወታደር ያለው ወታደራዊ መመሪያም ይጫነዋል፤ለአገሩ ፣ለህዝቡ የህይወት መስዋእትነት ለመክፈል የተዘጋጀ የህብረተሰቡ አካል ነው።ግን የህብረተሰቡ ንቀት ልክ የለዉም፤ጦርነት ላይ ብቻ ነው ጀግናው አንበሳው እያለ የሚሸኝህ። በአንድ ወቅት ከደብረዘይት ወደ አዲስአበባ ቤተሰብ ለመጠየቅ በዛውም ለመዝናናት ጎራ አልኩ።ታዲያ ከዘመዶቼ ቤት ማታ ማታ ብቅ እያለች ቡና የምታጣጣ ዉብ አካዉንታንት ነበረች፤ለመግባባት ግዜ አልወሰደብኝም በጣም ተግባቢ እና ጨዋታ አዋቂ ቢጤ ስለሆንኩ፤ከዚህም ሲዘል ጥሩ ቁመና እና ዉበት ነበረኝ፤ ታዲያ ልጅቱ በጣም የሚወደድ ብሃሪ ነው ያለህ ስትለኝ ከረመች እና አንድ ቀን 'ቆንጆ እንደሆንክ ታዉቃለህ?' አለችኝ ቡና ስታፈላ የነበረች የአጎቴ ልጅ 'ወይኔ መታወቂያው ላይ ያለውን ፎቶውን ብታይው እንዴት ያምራል አለቻት፤እዉነቷን ነበር የሚሊተሪ ልብስ ስለብስ ያምርብኝ ነበር። ታዲያ ይህች አካዉንታንት መታወቂያህን ካላየሁ ታንቄ እሞታለሁ አለች።እኔም እኔው ልሙትልሽ ወድጄ ወታደር የሆንኩት አልኩና መታወቂያየን አዉጥቼ ሰጠኋት።እጅግ ደነገጠች እና 'ወይኔ ወታደር ነህ፤ሲያስጠላ' ብላኝ እርፍ።እኔም ልጅቱ ላይ ቀልቤ አርፎባት ስለነበር ያለጠበኩትን ነገር ስሰማ ከአዲስአበባ የተተኮስኩ ደብረዘይት ደረስኩ።ከዚያ በኋላ ቀድሜ ወታደር መሆኔን እገልጻለሁ ግን ሰው መልካም ነገር አያሳይህም። ሰው ልብ የማይለውን መልካም ነገር ነው ያነሳሃው።የተሰዉትን አባቶቻችን ማሰብ ለሃገር አንድነት ፣ፍቅር እና ሰላም ወይም መተሳሰብ ያለው ፋይዳ ቀላል አይደለም።እግዚአብሄር ያስፋህ።

  ReplyDelete
 17. I have nothing to say for what I haven't done. I want to say this is another good observation that needs attention.

  I just want to ask a question, what's the value of a human being in Ethiopia? It doesn't necessarily have to be a soldiers' life or a King's.

  ReplyDelete
 18. የክብር አቀባበልን ላሸነፈ ሯጭና እግር ኳስ ተጨዋች፤ የክብር አቀባበርንም ለአርቲስት ብቻ ማን ሰጠ?

  ReplyDelete
 19. ዳኒ አፌ ቁርጥ ይበልልህ!

  ReplyDelete
 20. ክብርና ሞገስ ለሁሉም ሰዉ የተገባ ቢሆንም፣እንዲያዉ የለም ደረጃ ይዉጣለት ብለን ብንስማማ፣ለእኔ ዉድ የሆነዉን ህይወት አሳልፎ የሚሰጥ ወታደር አንደኛ ነዉ፡፡ ታዲያ እንዲህ ከሆነ እንደተባለዉ ብዙ ወገኖቻችን ዉድ ቤተሰቦቻቸዉንና ያደጉበትን ቀዪ ትተዉ እንዲሁ እንደወጡ የቀሩ ቤት ይቁጠራቸዉ፡፡ አይደለም ስለአሟሟታቸዉ ይቅርና በእርግጥ ስለሞሞታቸዉ ሳንሰማ የቀረን ቀላል አንሆንም፡፡ በምን ምክንያት እንደማይነገር ለጊዜዉ ባይታወቅም፣እንዲህ በመሆኑ ግን ያሳዝናል፡፡ ለወደፊቱ ይህ ነገር ታስቦበት የሚገባቸዉን ክብርና ሞገስ እንዲያገኙ ቢደረግ ምኞቴ ነዉ፡፡ መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ…………!!!!

  ReplyDelete
 21. ዲ/ን ዳኒ
  እግዚአብሄር እድሜና ጤና ይስጥልን።

  ReplyDelete
 22. ዲ/ን ዳኒ
  እግዚአብሄር እድሜና ጤና ይስጥልን።

  ReplyDelete
 23. Brilliant!!... u have eagle eyes!...God bless u & ur pen, Dan:)!

  ReplyDelete
 24. In early 2001, a concerned Ethiopian woman asked Meles as to the whereabouts of her son who did not return from his war with Eritrea. Irritated by the tone of her question, he responded with:


  "Lady, if your son does not return in six months time, then you'll have your answer!"

  source Durame

  ReplyDelete
 25. በህይወት ያሉትስ ቢሆኑ መጨረሻቸው የሌባ ሀብታም ቤት ጥበቃ ሆኖ መቀጠር አይደል እንዴ የሚሆነው
  ኧረ ይህች ሀገር መቼ ይሆን ያከበሯትን ማክበር የምትችለው

  ReplyDelete
 26. የመቀበሪያቸው ቦታ ወይብላ ማርያም ሲሆን ስነስርአቱም እንዲህ እንደውጪው በደመቀ ሁኔታ ሳይሆን በሹልክታ ነው የሚያደርጉት ለምን እንደሆነ አይገባኝም ሁሌም ጥያቄ ነው የሚሆንብኝ ልንሰማም የምንችለው ትንሽ ወደ ስልጣን ጠጋ ብለው የሞቱ ካሎ አጋጣሚ ሆኖ ቀብራቸው አዲስ አበባ ከሆነ አለበለዚያ ያው እንደምታውቀው እህሉም ፣ በርበሬውም ፣ አስከሬኑም ወደ ትግራይ ስለሆነ ነው ብዙም የማትሰማው ዘረኝነት በሰፈነበት አገር ወሬ ለማግኘት በጣም ይቸግራል ቆመውም በህይወት አያሉ አታውቃቸውም ሞተውም አታውቀቸውም

  ReplyDelete
 27. If you want to get this benefit please change your citizen. Please don’t bring other country culture to us. If you compare Ethiopia to Kenia or Uganda ok but you compare us with the world leader country. Do you know American annual income? One year American annual income equal to 300 years Ethiopian income.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Nice try! You are a good game changer! You are barking for those who pet you!

   Delete
  2. OMG, Anonymous, where did you get this data? beside giving some respect to our solider doesn't mean bringing other culture to our country. if you really worry about our culture you better watch other people not D. Daniel.

   Delete
 28. እንደዚህ እውነት ስትናገር ያምርብሀል

  ReplyDelete
 29. Very touchy. I myself and my family are the victim among the many Ethiopians. I lost my elder brother during the derg regime. We have no idea where our dear brother is since 1990.

  ReplyDelete
 30. Very touchy. I myself and my family are one of the victim among the many Ethiopians. We lost our beloved brother, son and many things for us during the derg regime. We have no idea where our beloved brother is since 1990. Uffffffffff......traumatic

  ReplyDelete
 31. Very touchy. I myself and my family are one of the victim among the many Ethiopians. We lost our beloved brother, son and many things for us during the derg regime. We have no idea where our beloved brother is since 1990. Uffffffffff......traumatic

  ReplyDelete
 32. ክብርና ሞገስ ለሁሉም ሰዉ የተገባ ቢሆንም፣እንዲያዉ የለም ደረጃ ይዉጣለት ብለን ብንስማማ፣ለእኔ ዉድ የሆነዉን ህይወት አሳልፎ የሚሰጥ ወታደር አንደኛ ነዉ፡፡ ታዲያ እንዲህ ከሆነ እንደተባለዉ ብዙ ወገኖቻችን ዉድ ቤተሰቦቻቸዉንና ያደጉበትን ቀዪ ትተዉ እንዲሁ እንደወጡ የቀሩ ቤት ይቁጠራቸዉ፡፡ አይደለም ስለአሟሟታቸዉ ይቅርና በእርግጥ ስለሞሞታቸዉ ሳንሰማ የቀረን ቀላል አንሆንም፡፡ በምን ምክንያት እንደማይነገር ለጊዜዉ ባይታወቅም፣እንዲህ በመሆኑ ግን ያሳዝናል፡፡ ለወደፊቱ ይህ ነገር ታስቦበት የሚገባቸዉን ክብርና ሞገስ እንዲያገኙ ቢደረግ ምኞቴ ነዉ፡፡ መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ…………!!!!

  ReplyDelete
 33. እዮቤል ደጀንOctober 29, 2015 at 7:31 PM

  እግዚአብሔር ይባርክህ ሌላ ምን ይባላል. እኔም አንድ የማውቀው እውነት አለ እሱን አስታወስክኝ.

  ReplyDelete
 34. The U.S. military didn't always bring home its dead. In the Seminole Indian Wars in the early 1800s, most of the troops were buried near where they fell. The remains of some dead officers were collected and sent back to their families, but only if the men's relatives paid all of the costs. Families had to buy and ship a leaded coffin to a designated military quartermaster, and after the body had been disinterred, they had to cover the costs of bringing the coffin home.

  Today, air crews have flown the remains of more than 5,000 dead troops back to the U.S. since the conflicts in Iraq and Afghanistan began.

  For those charged with bringing out the dead, it is one of the military's most emotionally taxing missions. The men and women of the Air Force's Air Mobility Command function as the nation's pallbearers, ferrying flag-draped remains to Dover Air Force Base in Delaware from battlefields half a world away.

  A Navy carry team carries a transfer case containing the remains of Petty Officer Zarian Wood at Dover Air Force Base in Dover, Del. Stephen Voss for The Wall Street Journal
  .
  The missions take a heavy toll on the air crews, but many of the pilots and loadmasters say their work is part of a sacred military obligation to fallen troops and their families. Air Force Capt. Tenaya Humphrey was a young girl when her father, Maj. Zenon Goc, died in a military plane crash in Texas in 1992. She remembers his body being flown to Dover before his burial in Colorado.

  Capt. Humphrey and her husband, Matthew, are now C-17 pilots who regularly fly dead troops back to the U.S. and then on to their home states for final burial. "It's emotional for everyone who's involved," she says. "But it's important for the family to know that at every step along the way their loved one is watched over and cared for."  Advertisement
  ReplyDelete
 35. Bringing fallen troops home is a relatively modern idea. Until the late 19th century, military authorities did little to differentiate and identify dead troops. Roughly 14,000 soldiers died from combat and disease during the Mexican-American War of 1846, but only 750 sets of remains were recovered and brought back, by covered wagon, to the U.S. for burial. None of the fallen soldiers were ever personally identified.

  The modern system for cataloguing and burying military dead effectively began during the Civil War, when the enormity of the carnage triggered a wholesale revolution in how the U.S. treated fallen troops. Congress decided that the defenders of the Union were worthy of special burial sites for their sacrifices, and set up a program of national cemeteries.

  During the war, more than 300,000 dead Union soldiers were buried in small cemeteries scattered across broad swaths of the U.S. When the fighting stopped, military authorities launched an ambitious effort to collect the remains and rebury them in the handful of national cemeteries.  Remembering Adam »  ENLARGE
  Lucas Family

  Lance Cpl. Kevin Adam Lucas had volunteered to relieve a fellow Marine, who had a pregnant wife, from taking the lead during a foot patrol. The 20-year-old was killed a half hour later. Read story>>>
  .
  The move "established the precedent that would be followed in future wars, even when American casualties lay in foreign soil," Michael Sledge writes in "Soldier Dead," a history of how the U.S. has handled its battlefield fatalities.

  The first time the U.S. made a serious effort to repatriate the remains of soldiers killed overseas came during the Spanish American War of 1898, when the military brought back the remains of thousands of troops who were killed in places like the Philippines and Cuba.

  The relatives of fallen troops in both world wars were given the choice of having their loved ones permanently interred in large overseas cemeteries or brought back to the U.S. for reburial.

  ReplyDelete
 36. Those who wanted their sons or husbands returned to them were in for a long wait. Fallen troops had been buried in hundreds of temporary cemeteries near the sites of major battles throughout Europe. When World War I ended, the families of 43,909 dead troops asked for their remains to be brought back to the U.S. by boat, while roughly 20,000 chose to have the bodies remain in Europe. The war ended in 1918, but the first bodies of troops killed in the conflict weren't sent back to the U.S. until 1921.  The burial site of an unknown Marine or solider on Guadalcanal in 1943. ENLARGE
  The burial site of an unknown Marine or solider on Guadalcanal in 1943. Associated Press
  .
  World War II posed a bigger logistical challenge, since American war dead were scattered around the globe. Nearly 80,000 U.S. troops died in the Pacific, for example, and 65,000 of their bodies were first buried in almost 200 battlefield cemeteries there.

  Once the fighting ended, the bodies were dug up and consolidated into larger regional graveyards. The first returns of World War II dead took place in the fall of 1947, six years after the attack at Pearl Harbor. Eventually, 171,000 of the roughly 280,000 identified remains were brought back to the U.S.

  Today, the remains of 124,909 fallen American troops from conflicts dating back to the Mexican-American war are buried at a network of 24 permanent cemeteries in Europe, Panama, Tunisia, the Philippines and Mexico.

  The military reshaped its procedures for handling war dead during the Korean War, when territory changed hands so many times that temporary U.S. battlefield cemeteries were at constant risk of falling into enemy hands. In the winter of 1950, the U.S. launched a policy of "concurrent return," which called for flying the bodies of fallen troops back to the U.S. as quickly as possible.

  ReplyDelete
 37. The military now goes to tremendous lengths to recover the remains of fallen troops. In March 2002, a Navy Seal named Neil Roberts fell out of the back of a Chinook helicopter in Afghanistan and was cornered and killed by militants on the ground. The U.S. sent in a second helicopter to attempt a rescue, but six members of its crew were killed in the ensuing firefight.

  Then-Brig. Gen. John Rosa, the deputy director of operations for the Joint Staff, told reporters that U.S. commanders ordered the high-risk recovery mission to ensure that Petty Officer Roberts' body didn't fall into enemy hands.  A chaplain reads last rites over a grave during the Korean War. ENLARGE
  A chaplain reads last rites over a grave during the Korean War. Keystone/Getty Images
  .
  "There was an American, for whatever reason, [who] was left behind," Gen. Rosa said at the time. "And we don't leave Americans behind."

  The military's system of concurrent return is basically still in use today, with modern technology cutting the lag time between when troops die in the field and when they are returned to their families down to as little as one day.

  ReplyDelete
 38. On May 16, Navy Petty Officer Zarian Wood, a 29-year-old medic who had deployed overseas less than a month earlier, died from wounds suffered in a bomb blast in southern Afghanistan's Helmand Province. Marine Cpl. Nicolas Parada-Rodriguez, the son of immigrants who moved to the U.S. two decades ago, was killed in Helmand that same day.

  The following evening, the remains of both men were slowly lowered from the cargo deck of a civilian 747 that the military had chartered to fly their bodies back to Dover. Cpl. Parada-Rodriguez's relatives could be heard weeping as the transfer case carrying his body was taken off the plane.

  The plane that brought the two men back to their families was operated by Evergreen International Airlines Inc., a military contractor. The Pentagon employs four other companies, including UPS and Federal Express, to help bring bodies back to Dover. Officials at the base say that 70% of the dead are flown back on the civilian planes, with the remainder coming home aboard military aircraft.

  ReplyDelete
 39. Zway yenafeqechih timeslaleh. Dani?

  ReplyDelete
 40. I personally support your idea . However we as a nation, have had a very long long time problem which diminishes the scarification of our own heroes and admiring others . This deep rooted problem of ours may continue in the future for unlimited time until the next generations will change our backward attitude and start to honor those who scarified their lives for the nation . So don't except some thing good to see today which is the extension of yesterday .Any how history will make clear the good did's of yesterday and today's armed forces of our country and the coming generations will give them honor which they deserved yesterday and today . Thank you for your concern as usual .

  ReplyDelete
 41. ጥሩ ተመልክተሀል
  እድሜና ጤና ይስጥልን፡፡
  ሁሌም አደንቅሀለሁ፡፡

  ReplyDelete
 42. ሃሳብህ መልካም ዲያቆን ይህ እኮ በአፍሪካ ሁሉ ይመስለኛል ግን እንኳን ለሞተው በህይወት ላለው መቼ ክብር ሰጠነውና ነው ስለሞተው የምትተርከው ወንድሜ ሃሳብህን ባደንቀውም እስቲ መጀመሪያ ቅድሚያ ያለውን በቁም ያለውንእኮ ነው ስለሞተው የምናስበው እስቲ እንግዲህ ቢያንስ እነዚህ ጎበኘኋቸው ባልከው ሀገር እንኳን ለሰው ልጅእኮ ክብር የሚሰጥበት ሀገር ነው።ታዲያ ለሰው ክብር በቁም የሚሄደን ሰው እያዋረድን እያንቋሸሽን በእግዚአብሔር የተፈጠረውን ሰው እንዳልሆነ እያሳየን እንዴት ስለአስከሬኖች እናወራለን ቢቻል መልካም ነው ብለው ጠየቁ ይባላል።ሰው ተረፈ ወይ በህይወት ስላለ ሰው ሳይሆን የተጨነቁት ለአስከሬን ነውና ይህን ባህል እስቲ በታሪክም በትምህርትም ማሻሻል ቢቻል!ለማንኛውም ሃሳብህን አደንቀዋለሁ!!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 43. Semi kale tiru new but thank u sir

  ReplyDelete
 44. Anbabi kale tiru new but thank u sir

  ReplyDelete
 45. Anbabi kale tiru new but thank u sir

  ReplyDelete
 46. Semi kale tiru new but thank u sir

  ReplyDelete
 47. ለወታደሮቹ ቅድሚያ ተሰጥቶ እያጨበጨብን ወደ በሩ እንሸኛቸዋለን

  ReplyDelete
 48. ዩኒፎርም የለበሱ ጀግኖቻችን አሉና እናክብራቸው

  ReplyDelete
 49. lenegeru ahun yalew wetaderis kibir yigebawal ? minm inkwan hulunm bayateqalil. Indyawm hizbu wetader simeleket demu yifelal aynu yiqelal indemimeslegn yahun gize wetader be siltena bizat wenewn atenkiro le hager yemikomina meswat lemehon qortxo yetenesa sayhon xuncha lemaferxem ina sew/hizb lemedebdeb yetenesu new yemimeslew yih hulu gin yene ina yene bixew hasab new KIBIR LE IWNETEGNA JEGNOCH WETADEROCHACHIN

  ReplyDelete
 50. ወታደሮቻችንን ጉሮ ወሸባየ ብለን እንደሸኘናቸው ሁሉ የጀግና አቀባበል እንድናደርግላቸው፣ ሲሠዉ በክብር አደባባይ ወጥተንና የሞቱለትን ሰንደቅ ዓላማ አልብሰን እንድንሸኛቸው፣ የቆሰሉትን በክብር እንድንቀበላቸው፣ ያስገኙት ድል ብቻ ሳይሆን የገጠማቸው ፈተናና የከፈሉት መሥዋዕትነትም እንዲነገርላቸው እመኛለሁ፡፡

  ReplyDelete
 51. Ene hul ken sasibew yenebere guday new Abate Asmera new yemotew wotader neber, hul gize gin asmera new yemotew le hulum masetawosha yasfelegal beta betam.

  ReplyDelete
 52. Bezih comment ayagebahim yale sew yemelkam neger tilat selehone hospital hido yimetemer
  Kizh yeteshale konjo asteyayet mentebko endehone gilit new
  Ayagebahim yemilew meles tekikil ayidelem
  Yegna yalageban man liyagebaw new enazinalen kendezih yalu sewoch gar abren menorachin

  ReplyDelete
 53. ዳኒ ብቻህን የምትፅፈውን ና የምታስተምረውን ያክል ሁሉም የኤፍኤም ጣቢያዎች አይሞክሩትም፡፡

  ReplyDelete
 54. በባለፈው ምርጫ በነበረው የፓርቲዎች የምረጡኝ ክርክር ላይ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ እንዲህ ብለው ነበር " አሜሪካ በአፍጋኒስታን፣በኢራቅ በሌሎች ጦሩዋን ባሰማራችባቸው ሀገሮች ስንት ወታደሮች እደሞቱባት አውቃለሁ አትዮጵያ ግን በሶማሊያ ስንት ሰው እደሞተባት አናውቅም " በለው ነበር በውጭ ጉዳይ ላይ በተደረገ ክርክር ፣በሌላ ዜና ስሰማ አሜሪካ በመንገደኛ አውሮፕላኖቹዋ አንድ ወታደራዊ ሰው ከተሳፈር ለክብሩ ሲባል ወታደሩ ቀድሞ ካልወረደ ሌሎች መንገደኙች አይወርዱም... እና በጎ ከሚመስልን ነገሮች ሁሉ መማርና መሻሻል አይከፋም ነገር ግን ሁሉ ነገራችን ባለቀበት ላይ ደርሰ እና ተቸገርን እግዚአብሔር አምላክ!!! የሰማዩን ያስተካክልልን እናንተ የተጎዳችሁ በሚለው ቃሉ….

  ReplyDelete
 55. Some say soldiers live for nothing and die for something. Unlike us (civilians) soldiers fight along side death with out any privileges, they choose to keep us safe ignoring theirs. .....soldies deserve a better respect and dignity from all.........I wish a long live for my brothers and sisters who chose to protect me and my country

  ReplyDelete
 56. ቃለ ህይወት ያሰማልን! አሜን!

  ReplyDelete