click here for pdf
አሁን ባለንበት ዘመን ያለን የኢትዮጵያ
ትውልድ የሀገራችንን ታሪክ፣ የሕዝቦች የእርስ በርስ ግንኙነትና የመሪዎቻችንን ሁኔታ ስንነጋገርና ስንጽፍ በአብዛኛው አሉታዊውን
ነገር ይበልጥ ጎልቶ እንዲወጣ፣ ጥላቻ እንዲበቅል፣ ቂም እድሜ እንዲያገኝ፣ ልዩነት እንዲሰፋ፣ ጠብም ሥር እንዲሰድ በማድረግ ላይ
የተመሠረተ ሆኖ ይታያል፡፡ ርግጥ ነው በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የተፈጠሩ የመስተጋብር ችግሮች ሁሉ በኛም ሀገር ተፈጥረዋል፡፡ በኛ
ሀገር የተፈጠሩትም በሌሎች ይገኛሉ፡፡ በዓለም ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ የኩራትም የውርደትም፣ የፍቅርም የጠብም፣ የሰላምም የጦርነትም፣
የእኩልነትም የጭቆናም፣ የመረዳዳትም የመጠፋፋትም፣ የሥልጣኔም የስይጣኔም ታሪኮች አሉ፡፡ እንኳን በአንድ ሀገር የሚኖሩ የተለያየ
ዘውግ፣ ቋንቋ፣ እምነትና የኑሮ ደረጃ ያላቸው ቀርተው በተመሳሳይ ቋንቋ፣ ባሕልና የኑሮ ደረጃ የሚገኝ የአንዲት ሀገር አንድ ወጥ
ሕዝብ እንኳን በውስጡ ጽጌረዳም እሾህም አለው፡፡
የሚገርመው ነገር ኢትዮጵያን ከዓለም
የተለየች የሚያደርጋት ምን እንደሆነ አለመታወቁ ነው፡፡ ኢትዮጵያኮ ሲኦልም አልነበረችም መንግሥተ ሰማያትም አልነበረችም፡፡ ሀገር
ነበረች፣ አሁንም ሀገር ነች፡፡ ሀገር የሚገጥማት ፈተና ሁሉ ገጥሟታል፤ ሀገር የሚኖራት ጸጋ ሁሉ ታድሏታል፡፡ በአንዳንድ የታሪክ
ምእራፏ ለመንግሥተ ሰማያት ጠጋ፣ በሌላው ምእራፏ ደግሞ ለሲኦል ጠጋ ብላ ይሆናል እንጂ፣ ፈጽማ ሲኦልና መንግሥተ ሰማያት ሆና አታውቅም፡፡
እኛ ልጆቿ ግን ወደ መንግሥተ ሰማያት ጠጋ ማለት ብቻ ሳይሆን ምድራዊት መንግሥተ ሰማያት ብትሆንልን እንወዳለን፤ ለዚያም እንሠራለን፡፡
ወደዚያ በተጠጋችበት ታሪክም እንኮራለን፤ ወደ ሲኦል ለመውረድ አዘንብላ የነበረችበትንም ዘመን ስናስብ በልብ ስብራት እንመታለን፡፡
የታሪክ ሂደት ያመጣቸውን የትናንት
ነገሮች ዛሬ አንቀይራቸውም፡፡ ሆነዋልና፡፡ ነገር ግን እንማርባቸዋለን፤ ከትናንት ወስደንም ለዛሬ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ የዛሬ ማንነታችን
መገንቢያም እናደርጋቸዋለን፡፡ በተቃራኒውም ያለፉትን ዘመናት ጠባሳዎች እየነካካን ቂምን ማመርቀዝ፣ ጥላቻን ማጎንቆል፣ ልዩነትን
ማስፋት፣ ፍቅርንም ማደብዘዝ እንችላለን፡፡ ሁለቱም በእኛ ምርጫ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ ምርጫው ለእህሉ ወይስ ለአረሙ ትለፋለታለህ?
የሚለው ነው፡፡
ታሪካቸውን ለዕድገታቸውና ለሰላማዊ
መስተጋብራቸው የተጠቀሙት ግን ከአረሙ ይልቅ ለእህሉ ጊዜና ጉልበታቸውን ያፈሰሱት ናቸው፡፡ ገበሬ ዓመት በሙሉ የሚለፋው አረም ለማብቀል
አይደለም፡፡ አረም ለመብቀል ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ ጉልጓሎ፣ አያስፈልገውም፡፡ ወንፈልና ደቦ አይሰበስብም፡፡ ጉልበትና ጊዜውን
አያባክንም፣ ወዝና ላቡን አያንጠፈጥፍም፡፡ ለአረም አንድ ነገር በቂ ነው፡፡ ስንፍና ብቻ፡፡ ገበሬ ከሰነፈ ምንም ሳይደክም አረም
እርሻውን ከዳር ዳር ይወርስለታል፡፡ በሬ ሳይጠምድ፣ እርሻ ሳይውል፣ ሌሊት ሳይነሣ፣ ማታ ሳይገባ፣ ዝናብ ሳይመታው፣ ፀሐይ ሳይከካው፣
ብርድ ሳይገርፈው፣ ወላፈን ሳይጠብሰው አረም እንዲሁ ይበቅልለታል፡፡ ገበሬ ለአረም አይለፋም፡፡
የገበሬን ጥበብ፣ የገበሬን ድካም፣
የገበሬን ጉልበት፣ የገበሬን ማዳበሪያ፣ የገበሬን ትዕግሥት፣ የገበሬን ሐሞት፣ የገበሬን ልምድ፣ የገበሬን ጊዜ፣ የሚፈልገው እህሉ ነው፡፡ ወንፈልና ደቦ የሚሰበስበው ለእህሉ ሲል ነው፡፡
በሬ የሚጠምደው፣ ሞፈር የሚቆርጠው፣ ቀንበር የሚነድለው፣ ጎተራ የሚያዘጋጀው፣ አውድማ የሚለቅልቀው ለእህሉ ሲል ነው፡፡ አረም በስንፍና
የሚበቅለውን ያህል እህል የሚበቅለው በጉብዝና ነው፡፡ እህል ያለ ገበሬው ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ጉልበትና መሣሪያ ከምድር አይወለድም፡፡
አረም ግን አዋላጅ አይፈልግም፡፡ አረም በራሱ ተወልዶ በራሱ ያድጋል፡፡
በታሪክ መስክ ላይ የተሠማራ ትውልድም
ጊዜውን ማጥፋት፣ ጉልበቱን መሠዋት፣ ጥበቡን ማፍሰስ፣ ዕውቀቱን መከስከስ፣ ያለበት ለአረሙ አይደለም፡፡ ጥላቻው፣ ቂም በቀሉ፣ መቆራቆሱ፣
መናከሱ፣ መለያየቱ፣ መጠፋፋቱ፣ ይኼ የትውልድ አረም ነው፡፡ በስንፍና ብቻ ሊበቅል የሚችል፡፡ በታሪካችን ውስጥ በቅሎ የነበረው
እህል ፍቅራችን ነበረ፣ አንድነታችን ነበረ፣ መዋለዳችን ነበረ፤ መዋሐዳችን ነበረ፤ ሥልጣኔያችን ነበረ፤ ጀግንነታችን ነበረ፤ ነጻነታችን
ነበረ፡፡ ትኩረታችንን እህሉ ላይ ካደረግነው አረሙን እንቋቋመዋለን፡፡ መቋቋምም ብቻ ሳይሆን እናጠፋዋለን፡፡ አረሙን ማጥፋት ያለብን
አረም ስላልነበረ አይደለም፣ አረምን ለመሸፋፈን ሲባልም አይደለም፡፡ አረም ስለማይጠቅመን ነው፡፡ በሀገራችን እንክርዳድ የተሰኘው
አረም ሳይለቀም ቀርቶ ከስንዴ ጋር ገብቶ ጠላ የሆነ እንደሆነ ያሳብዳል፡፡ ለዚህም ነው፡-
እንክርዳድ እንክርዳድ የተንከረደደ
ስንዴ መስሎ ገብቶ ስንቱን አሳበደ
የተባለው፡፡
አሁን አሁን በሀገራችን ጉልበታችንን
እየጨረስን ያለነው አረሙን ለማብቀል ይመስላል፡፡ አንዲት ጽጌረዳን ከማብቀልና ፈንድታ አበባዋ ሠፈሩን እንዲያውድ ከማድረግ ይልቅ
አንድ ማሳ ሙሉ አረም ማብቀል በጣም ቀላል ነው፡፡ አረሙ ስንፍናን ብቻ ይጠይቃልና፡፡ ጽጌረዳዋን ለማብቀል ግን ከመሬቱ፣ ከሰማዩ፣
ከአየሩ፣ ከአራዊቱ፣ ከአላፊ አግዳሚው ጋር መጋደልን ይጠይቃል፡፡
በታሪካችን ውስጥ የነበረውን እህል
ዘሩን አምጥተን መዝራት፣ ዘርተን መከባከብ፣ ተከባክበንም ማሳደግ ይገባን ነበረ፡፡ ጥበባችንን፣ ዕውቀታችን፣ ገንዘባችንንና ጉልበታችንን
ለእርሱ ማፍሰስ ይገባን ነበረ፡፡ አሁን ግን ድርሰቶቻችንን፣ ሚዲያዎቻችንን፣ ሐውልቶቻችንን፣ ትርክቶቻችንን፣ ዲስኩሮቻችንን፣ ንግግሮቻችንን፣
የፖለቲካ ፕሮግራሞቻችንን የምናባክነው አረሙን ለማብቀል ሆኗል፡፡ አረምኮ ይህንን ሁሉ አይፈልግም ነበር፡፡ አረምን ለማብቀል ሥርዓተ ትምህርት መቅረጽ፣ ዩኒቨርሲቲ መገንባት፣ የፖለቲካ
ፓርቲ ማደራጀት፣ ሚዲያ መዘርጋት፣ ብዕርና ወረቀት ማባከን፣ ምስትርናና ዱክትርና መድረስ አያስፈልግም ነበረ፡፡ አረም እንዲሁ ይበቅላልኮ፡፡
የፖለቲከኞቻችን ብስለት፣ የምሁሮቻችን ብቃት፣ የትውልዱ ምጥቀት፣ የተቋሞቻችን
ሥልጠት፣ የሐሳቦቻችን ጥልቀት፣ የሚዲያዎቻችን ፍጽመት፣ የሥልጣኔያችን ርቀት፣ የጥበበኞቻችን ልህቀት የሚታወቀው ባበቀልነው እህል
እንጂ ባበቀልነው አረም ብዛት አይደለም፡፡ ለአረምማ እነዚህ ሁሉ አያስፈልጉትም፡፡ እነዚህ ያስፈለጉት ሲቻል አረሙን ቀድሞ ለመከላከል፣
ካልሆነም የበቀለውን አርሞ እህሉን አህል ለማድረግ ነበር፡፡ ለማስተማር እንጂ ለማደንቆር ምን ትምህርት ቤት ይሻል? ለማዳን እንጂ
ለማሳመም ምን ሆስፒታል ያስከፍታል? ለፍትሕ እንጂ ለወንጀል ምን ዳኝነት ያስፈልጋል? ለመግባባት እንጂ ላለመግባባት ምን ቋንቋ
ያስፈልጋል? ለልዕልና እንጂ ለውርደት ምን ኪነ ጥበብ ያሻል? ለዓለም ዓቀፋዊ እሴቶች እንጂ ለጎጠኝነት ምን ጥበብ መፍሰስ ያሻዋል?
ለማጥገብ እንጂ ለማስራብ ምን ፖሊሲ ያስፈልጋል? ለሥልጣኔ እንጂ ለስይጣኔ ምን ፓርቲ ማቋቋም ያስፈልጋል? ለጽድቅ እንጂ ለኃጢአት
ምን የእምነት ተቋም ያሻል?
የኛ ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉልበት አረም ላይ እየፈሰሰ ነው፡፡
የገበሬ ጉብዝና በአረም ብዛት እንደማይለካው ሁሉ የትውልድ ጉብዝናም በአረም አይለካም፡፡ ‹እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ›
እንዲሉ እንኳንና የእኛ ጥበብና ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ ተጨምሮበት አረም በራሱም ሀገር ያጠፋል፡፡
እንዲህ እርሻው ሁሉ አረም እስኪወርሰው
የለም ወይ፣ የለም ወይ፣ የለም ወይ ባገር ሰው
ተብሎ የለ፡፡
አረም አያዋለዱ ሀገርን ለማሠልጠን መመኘት፣ ተኩላን እያረቡ የበግ
ሥጋን እንደመመኘት ያለ ነው፡፡
በገበሬዎቻችን ታሪክ ውስጥ በ16ኛው መክዘ በሀገራችን ተከስቶ በነበረው
የሃይማኖት ጦርነት ጊዜ ከ20 ዓመታት በላይ ገበሬው ተረጋግቶ በእርሻ ላይ ስላልነበር አገሩን አረም ወርሶት ነበር ይባላል፡፡ በዚያ
ጊዜ ከሀገራችን ገጽ የጠፉ የእህል ዓይነቶች አሉ፡፡ ለዘር ተብሎ የተቀመጠው ወይ በቀጠና ምክንያት ተበልቶ፣ አለያም ቤቱ ሲቃጠል
ተቃጥሎ፣ ካልሆነም የተቀበረበት ቦታ በዘመን ብዛት ጠፍቶ ሳይተኩ የቀሩ የእህል ዘሮች አሉ፡፡ የካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔርን ኅብረ
ብዕር ያነበበ ሰው ከሚያያቸው የእህል ዘሮች መካከል ብዙዎቹ ስማቸውን ትተው ጠፍተው የቀሩት እንዲህ ባሉ ዘመናት ነው ይባላል፡፡
አረሙ ግን አልጠፋም፡፡ እንዲያውም ተመችቶት ነበር፡፡
በታሪካችንም ውስጥ እየጠፉና እየመነመኑ የመጡ በጎ እሴቶች፣ ባሕሎች፣
ልማዶችና ወጎች አሉ፡፡ አገር ችግር ላይ ስትወድቅ እህሉን የሚያመርተው ሲያጣ፣ ዘሩ ይጠፋል፡፡ ያንን ዕድልም አረሙ ይጠቀምበታል፡፡
ምድሩም እህል ተዘርቶበት የማያውቅ ይመስላል፡፡
አሁን ለዚህ ትውልድ ጥያቄው አንድ ነው፤ ለአረሙ እንድከም ወይስ ለእህሉ?
እህሉን በማምረት ብርታትህን ታሳያለህ ወይስ አረሙን በማብቀል ስንፍናህን? የኢትዮጵያ መልክ የሚቀየረው ለዚህ ጥያቄ በምንሰጠው
መልስ ነው፡፡
አሁን ለዚህ ትውልድ ጥያቄው አንድ ነው፤ ለአረሙ እንድከም ወይስ ለእህሉ? እህሉን በማምረት ብርታትህን ታሳያለህ ወይስ አረሙን በማብቀል ስንፍናህን?
ReplyDeleteለማስተማር እንጂ ለማደንቆር ምን ትምህርት ቤት ይሻል? ለማዳን እንጂ ለማሳመም ምን ሆስፒታል ያስከፍታል? ለፍትሕ እንጂ ለወንጀል ምን ዳኝነት ያስፈልጋል? ለመግባባት እንጂ ላለመግባባት ምን ቋንቋ ያስፈልጋል? ለልዕልና እንጂ ለውርደት ምን ኪነ ጥበብ ያሻል? ለዓለም ዓቀፋዊ እሴቶች እንጂ ለጎጠኝነት ምን ጥበብ መፍሰስ ያሻዋል? ለማጥገብ እንጂ ለማስራብ ምን ፖሊሲ ያስፈልጋል? ለሥልጣኔ እንጂ ለስይጣኔ ምን ፓርቲ ማቋቋም ያስፈልጋል? ለጽድቅ እንጂ ለኃጢአት ምን የእምነት ተቋም ያሻል?
ReplyDeleteእባክህ ይህን ጽሁፍ ለDhRTO ግልባጭ አድርግ:: ምክንያቱም የድሮውን ታሪክ እያነሳ ለጠብና ለቂም ማነሳሻ የሚሆኑ ፕሮግራሞችን እያስተላለፈ ስለሆነ፡፡
ReplyDeleteእህሌ ወይስ አረም ? ደጋግሜ አነበብኩት ይገርማል ትልቅ ትምህርት ነዉ ዳኒ ለለዉጥ የሚያበቃ እግዝያብሂር ይባርክህ አብዝቶ ይስጥህ……… የኛ ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉሌበት አረም ሊይ እየፈሰሰ ነው…….ይገርማል…..
ReplyDeleteእህሌ ወይስ አረም ? ደጋግሜ አነበብኩት ይገርማል ትልቅ ትምህርት ነዉ ዳኒ ለለዉጥ የሚያበቃ እግዝያብሂር ይባርክህ አብዝቶ ይስጥህ……… የኛ ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉሌበት አረም ሊይ እየፈሰሰ ነው…….ይገርማል…..
ReplyDeleteዲያቆን ዲኒ, ዕይታዎችህ ሁል ጊዜ ልብ የሚነኩ እውነተኛ ናቸው.ማስተዋሉን ይሰጠን.ምርጫዉ ለእህሉ ወይስ ለአረሙ ትለፋለታለህ?ምርጫችን ለእህሉ ለፍተን ፍሬ አፍርተን ኢትዮጵያችን ቀና ብላ እንድናያት የቅዱስን አምላክ ይርዳን .አሜን! አንተንም, መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!
ReplyDeleteሁላችንም ልንማርበት የሚገባዉ ታላቅ መልዕክት ነዉ:: ወደ ሠው ከመጠቆማችን በ ፊት እራሳችንን እንመልከት:: የተባሉትን ሁሉ ለመፈፀም እግዚአብሄር ይርዳን!!!
ReplyDeleteቴዲ_ቢኬ
ለሁላችንም የምጠቅም ታላቅ ወቅታዊ መልዕክት ነዉ:: ሁላችንም እራሳችንን እንመልከትበት:: እግዚአብሄር ለመተግበር ያብቃን!
ReplyDeleteGod bless you dani.no words at all to express you.but I always beg God to give you health .if there are 50 people in Ethiopia who are going to do like you ,for sure there will be dramatic change.Let God makes that of day
ReplyDeleteWow molla u r perfectly right , but 50 is too much only 10 is enough . .
DeleteI really thanks for your gorgeous idea
'እንዲህ እርሻው ሁሉ አረም እስኪወርሰው
ReplyDeleteየለም ወይ የለም ወይ የለም ወይ ባር ሰው'
Thanks God ! for giving great & unique Brother to Ethiopian.
ሃይ ዲያቖን ዳንኤል ፡ እግዚአብሄር ፀጋውን አብዝቶ ያድልልን
ReplyDelete- የሀገራችን ነገር አቅጣጫው ወደ የት እንደሆነ ለመገመት እያስቸገረ ይመስለኛል ፡፡ በዘመናችን እየሰራን ያለውን ስንፍና ከዘመናት በፊት በነበረው ክስተት ማላከክ ወግ መስሎን ተያይዘነዋል፡፡ በአንድ ወቅት ነፍሳቸውን ይማርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት (አለማይሁ አቶምሳ ) ይህንን ሲናገሩ በየትኛውም ሚዲያ ሣይሆን በአካል በጆሮዬ ሰማሁአቸው፡፡ የስብሰባው ተሳታፊዎች ያማረላቸው መስሎአቸው ባለፉት ዘመናት ስርአቶች እና መንግስታት ላይ የኩነኔ መአት ያዘንባሉ ፡፡ የወቅቱ ፕሬዝዳንት እንዲህ አሉ ‹ የተሰበሰብነው የራሳችንን ስራ ለመገምገም ሲሆን እኛ ግን የሌሎችን ጥፋት በመዘርዘር ተጠምደናል፤ እኛ እራሳችን ሀገሪቱን ከተረከብን 20 ዓመት ምልቶናል፤ እናም የራሳችንን ብንገመግም አይሻልም ? ‹‹ ይህንን በማለታቸውም ተሰብሳቢዎች ሲደነግጡና ሲገረሙ አይቻለሁ፡፡ እስኪ መልካም መልካሙን በመመኘት እና በማድረግ በጎ ነገር እንዲመጣልን አምላክ ይርዳን፡፡
- ባንተ በኩልም መስተካከል ያለባቸውን ነገሮች ነቅሶ በማውጣት ያለህን እይታ እንዲሁ መልካም ነገሮች እንዲጎለብቱ ለሁሉም ሞራል የሚሰጥ ፅሁፎችንም አጋራን (ልክ እንደ የዓመቱ በጎ ሰው አይነት ጅምርህ!!)
ዲ/ን ዳኒ እግዚአብሔር እድሜ እና ጤና ይስጥህ!!!
ReplyDeleteዲ/ን ዳኒ እግዚአብሔር እድሜ እና ጤና ይስጥህ!!!
ReplyDeleteGreat view!! Please write again and again and again and again. ..
ReplyDeleteግሩም ጽሁፍ ነው ዲያቆን እንዲያው ከርእሱ ጋርም ባይገናኝ ሰሞኑን ስለታዘብኩት ነገር እንድናገር ይፈቀድልኝ በሀገራችን ገጸ ድሮች የአቡነ ታዎድሮስ መምጣት የተዘገበበት መንገድ ገርሞኛል፡፡ በተለይ ፋና ብሮድካስቲክግ ኮርፖሬትና ኢዜአ የግብፅ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ እያሉ ሲጠሯቸው ነበር እና የግብፅ ኦርቶዶክስ ወይም ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ብለው እንዲያስተካክሉ እንደ አንተ አይነት ተሰሚነት ያለው ሰው ቢናገራቸው ጥሩ ነው
ReplyDeleteአስተዋይ ልቦና ቢገኝ ሀገርን ዛሬውኑ በቀየረ ነበር:: አስተዋዮችን ልዑል እግዚአሔር ያብዛልን!!!
ReplyDeleteአስተዋይ ልቦናን ያድለን!!!
ReplyDeleteGod bless you! Such a wonderful perspective!
ReplyDeleteቋንቋ በሃጥያት የመጣ በሽታ መሆኑን የዘነጋን።የባቢሎን ህንፃ እየገነባን ፍቅር የምናፈርስ ምስኪኖች። በሃጥያታችን ምክንያት የመጣን መለያየት የወደድን። ልናፍርበት ሲገባ ልንኮራበት "የምንተጋ" የመንፈስ ድሆች። እግዚአብሔር ይማረን። ዲያቆን ጥሩ ብለሃል። እግዚአብሔር ይጠብቅህ።
ReplyDeleteትኩረታችንን እህሉ ላይ ካደረግን አረሙን....እንቋቋመዋለን። መቋቋም ብቻ አይደለም እናሸንፈዋለን...እንረታዋለን...እናንበረክከዋለን....ድል እንነሳዋለን........እጅግ ግሩም መልእክት ነው......ወቅታዊም .....ግን ምን ዋጋ አለው ?ሰሚ ጆሮ አለን...እንክርዳዱ ሰውን እስነቅሎት የለ...ሰውን አስጨልሎታል ...........እንግዲ ምን እንላለን...ጌታ እግዚአብሔር ወደ እዚህ ሕዝብ በምሕረት ይመልከት።
ReplyDeleteGod bless you
ReplyDeleteGod bless you
ReplyDeleteውድ እይታህን አጋሪያችን ዲ/ን ዳንኤል እጅግ በጣም ግሩም የሆነ ምልከታና ትዝብት ነው። ይህንን ጉዳይ በየትኛውም የእድሜ ክልል፣ በየትኛውም የትምህርት ደረጃ፣ በየትኛውም የስራና የስልጣን ዕርከን ያለ ሁሉ ሊረዳው የሚችል ሃቅ ነው። ችግሩ እውነታውን የመቀበልና ያለመቀበሉ እንዲሁም ከአገር ይልቅ ለድርጅትና ለስልጣን ማሰቡ ላይ ነው። አገሩን የሚወድ ሁሉ እስከመቼ እንዲህ ከእውነታ እየሸሸንና እየራቅን እንደምንኖር እራሳችንን መጠየቅ ያለብን አሁን ነው።
ReplyDeleteዳኒ አንተ በጥሩ ሁኔታ በግልጽና በማያሻማ መንገድ እህሉን ከአርሙ መለየት እንደሚገባ አስቀምጠኸዋል። በዚህ ረገድ ከምሁር እስከ ለቂቅ ከላይ እስከ ታች ያለ የድርጅትና የመንግስት ባለስልጣናት በቀና መልኩ በመረዳት ሁሉም ቢረባረብ አረሙን ከስሩ መንግሎ ለመጣል ብዙ ጊዜና ጉልበት የሚጠይቅ አይመስለኝም።
ለዚህም ፈጣሪ ሁሉንም አንድ አድርጎ የአስራት አገር ኢትዮጵያን ጠብቆ ትንሳኤዋን ያሳየን አሜን!!!
ያቀበለህ ያሳሰበህ ያመራመረህ ይህን ሁሉ በሕሊናህ ውስጥ የቀረጸልህ እግዚአብሔር ለሃገራችን ለቤተ እምነትቶቻችን ሁሉ አረምን ሳይሆን እህል እንድናስብ ያድርገን የአንተንም ዓይነልቡና የበለጠ ያብራልህ ልጄ ።
ReplyDelete(እስከአሁን ድግሙ ነኝ) ከጀርመን
ኦ ዳኒ (ዲ/ን) ነፅሮትህ ድንቅ ነው፡፡ ስንቱን የመፍጠር አቅም አምላክ ሳይነፍገን ለምን ለምን አረም ለማብቀል እንደምንታትር... አንደኛውን የአረም ዓይነት ነቅለን ሌላ የአረም ዓይነት ለመትከል ለምን እንደምንሽቀዳደም ግራ የሚገባኝ ጉዳይ ነው# but you wrote well in details
ReplyDeleteኦ ዳኒ (ዲ/ን) ነፅሮትህ ድንቅ ነው፡፡ ስንቱን የመፍጠር አቅም አምላክ ሳይነፍገን ለምን ለምን አረም ለማብቀል እንደምንታትር... አንደኛውን የአረም ዓይነት ነቅለን ሌላ የአረም ዓይነት ለመትከል ለምን እንደምንሽቀዳደም ግራ የሚገባኝ ጉዳይ ነው# but you wrote well in details
ReplyDeleteአውነት ነው ተኝተናል ከእንቅልፋችን እንንቃ አረሙንም እናሰወግድ
ReplyDeleteBe ewnet hulachinim linimaribet yemigeba. Ltalak timihirt new.
ReplyDeleteዳኒ እናመሰግናለን!
ReplyDeleteእኔ እምለዉ አንድ ነገር አለኝ፤ አረም እንዲፈጠርና እንዲስፋፋ ያደረገዉ ማን ነዉ? በእኔ እምነት ችግሩ አረም መፈጠሩ አይደለም፣ለተፈጠረዉ አረም መድኃኒት መጥፋቱ ነዉ፡፡ ብልጥ ሰዉ ከታሪክ ይማራል፣ሞኝ ሰዉ በራሱ ሲደርስ ይማራል እንደ እሚባለዉ እንዳይሆን እፈራለሁ፡፡ሀገራችን የብዙ ዘመናት ታሪክ ባለቤት ብትሆንም፣በዲሞክራሲያዊ መንገድ በመነጋገርና በመግባባት ረገድ የመጨረሻዋ ድሀ ሀገር ናት፡፡ ለእኔ ከምንም ነገር በፊት መቀደም ያለበትን ነገር የረሳን ይመስለኛል፡፡
ዳኒ እናመሰግናለን!
ReplyDeleteGreat view
ReplyDeleteThank you!
አዲሷ ተሰታፊህ ነኝ፡፡ እስከዛሬ ድረስ የማውቅህ በወንጌል ትምህርትህ ብቻ ነው፡፡ ግን መቼ አግኝቼ ይህንን ጽሁፍህን አንብ ይሁን እያልኩኝ አስብና እመኝ ነበር፡፡ አንባቢ ስላልሆንኩኝና ፣ ከመረጃ የራቅሁ በመሆኔ ነው፡፡ ትናንት ግን ድንገት የከፈትኩት ዌብ ሳይት አንተን ስለአገኘሁኝ ደስ ብሎኛል፡፡ በእኔ ዘመንም እንደዚህ አይነት መምህራን መኖራችሁ ኩራት ይሰማኛል፡፡ ይህንን መንገድ የሚያስተምር በማጣት ስንቱ ወድቋል፣ እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክ፡፡ሙሉጌጥ/ወለተስላሴ ነኝ
ReplyDeleteእህል ወይስ አረም? ሁልጊዜ ያሚያመኝን ነገር በአንተ እይታ መገለጹ በእውነት ደስ አሰኝቶኛል፡፡ እግዚአብሔር ይባርክህ ጥሩ ገለጻ ነው፡፡ የሚገርመው የምናነበውም ሆንን ሌሎችም የተረዳነውን ያህል እንኳን ለመቀየር መጀመርም ሆነ ማሰብም አንፈልግም፡፡ በዚህም ምክንያት አድንቀን የምናልፍ ጥሩ ወሬኞች መሆናችን ደግሞ የበለጠ እኔን ይገርመኛል፡፡
ReplyDeleteልብ ላለው ልብ ይበል እንደ ቦይ ውሃ ወደተመራንበት ሁሉ እንሳብ !!!! ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እያየን ያላየነውን አትኩረን እንድናይ ላደረከን እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ እይታህን የበለጠ ያስፋው እናመሰግንሀለን
ReplyDeleteእናመሰግናለን ይበል ይቀጥል
ReplyDeletearemun man zeraw.....?
ReplyDeletegreat view
ReplyDeleteKale hiwot yasemaln !!!!
ReplyDeletegreat view!!!!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteእግዚአብሄር ጸጋውን ጥበቡን ያድልልን፡ መልካም እይታ ነው:: እህሉን በብርታትና በማስተዋል ማምረትን እመርጣለሁ::
ReplyDeleteYemisema norem alnorem lehlinah stl endih yalu negerochin kemechachar atbozn. Yeqen yelem Dani.
ReplyDeleteGod bless you brother.
ReplyDeleteEndihi erishaw Hulu arem eskiwerisew
ReplyDeleteYelemweyi yelemweyi yelemweyi bager sew
Egizabiger edime.ysitihi Daniel
ለአረም አብቃዮች እራሳቸውን እንድያዩ እድል ሰጠሃቸው።
ReplyDeleteብጠቀሙበት።
God bless you ,
ReplyDeleteAmlak lhulachenem mastwalen yadelen.kena lebuna eyetefa aremu becha eyetayen esun marabat hunual yemehuranu sera.
gerum teri new