Tuesday, September 15, 2015

‹አርቲስቶቹ›ን ወይስ ጠቅላይ ሚኒስትሩንአንድ ጆሮና ጊዜ የገጠሙለት ሰው ነበር አሉ፡፡ ሰውዬው የተማረው ትምህርት የለውም፡፡ ሁለት ችሎታ ግን ነበረው፡፡ ሲባል የሰማው እውነትም ይሁን ስሕተት ልቅም አድርጎ ይይዝና ሌላ ቦታ ሄዶ የተማረው ያህል ያንደቀድቀዋል፡፡ ሁለተኛው ችሎታው ደግሞ አፈ ጮሌ ስለሆነ ነገር በምላሱ ይቆላል፡፡ ያንንም ይኼንንም እያቆላመጠ ከተማሩትና ከተመራመሩት በላይ ከብሮና ታፍሮ ይኖራል፡፡ አንድ ቀን የማያውቀውን ቀለም ሲያዜም የሰሙት ሊቅ አፍረው አቀረቀሩ፡፡ እርሱ ግን ከዕውቀት የደነገለ ነበርና አልገባውም፡፡ በኋላ ቀረብ ብሎ ‹ደኅና ነዎት የኔታ› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹ደኅና ነህ›› ብለው ዝም አሉት፡፡ እርሱም ያላወቁት ስለመሰለው ‹አላወቁኝም መሰል መሪጌታ እኮ ነኝ› አላቸው፡፡ሊቁም ‹ዐዉቄሃለሁ› አሉት፡፡ እንዳቀረቀሩ፡፡ ‹ታድያ ምነው ካወቁኝ ከነ ማዕረጌ ሳይጠሩኝ ቀሩሳ› አላቸው፡፡ ‹አንተን አከብራለሁ ብዬ ሞያውን እንዳልሰድበው ፈርቼ ነው›› አሉት ይባላል፡፡
እኔም ‹እርቲስቶቻችን› የሚለው ቃል በትእምርተ ጥቅስ ያደረግኩት ሊቁ የፈሩትን ፈርቼ ነው፡፡ እንዳልተውባቸው ደግሞ ምን ብዬ እንደምጠራቸው ግራ ገብቶኝ፡፡ የአዲስ ዓመት ዋዜማውን መርሐ ግብር በዕለቱ ለማየት ስላልቻልኩ ቪዲዮውን ነው የተመለከትኩት፡፡ ሊነግሩን የፈለጉት ስለ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ፣ ስለ ሀገራችን ዕድገት፣ ስላለፈው ስኬታችን ቢሆንም እንኳን የቀረበው ዝግጅት ግን አደገች የምትባለውን ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ጥበብ ዞር ብላ ያላየቺው፣ ከንግግር ከፍ፣ ከፉከራ ዝቅ ያለ፤ ከፕሮፓጋንዳ ወረድ፣ ከዲስኩር ራቅ፣ ከድንፋታ ጠጋ ያለ ወለፈንዲ ሆኖ ነው የታየኝ፡፡ 

በሀገራችንኮ የልቅሶ ሥነ ሥርዓት እንኳን ወግ አለው፤ ጥበብ አለው፤ ትርዒት አለው፤ ፍሰት አለው፤ ድባብ አለው፤ ፈጠራ አለው፤ ርቀት አለው፣ ምጥቀት አለው፤ ደረጃ አለው፡፡ ይኼኮ ወግ የለው፣ ጥበብ የለው፣ ትርዒት የለው፣ ፍሰት የለው፣ ፈጠራ የለው፣ ደረጃ የለው፡፡ ድፍረት ብቻ፡፡ መሪዎቻችን ግን ለምንድን ነው የጥበብ አማካሪ የማይኖራቸው? ለምንድን ነው ጥበብን ከሚሰድቡ ሰዎች ጋር አብረው የሚቆሙት? ለምን ‹አርቲስቶቹን› እናከብራለን ብለው ሞያውን ይሰድቡታል? ይህቺ ሀገርኮ ሰማየ ሰማያት ደርሰው የመጡ፣ ድንጋዩን አቅልጠው ጥበብ የሚያፈልቁ፣ አራት ጸሐፊ አስቀምጠው አንድ አንድ ምዕራፍ እየነገሩ መጽሐፍ የሚያስጽፉ፤ መሰንቆ እንደ ሰው፣ ክራር እንደ ወፍ፣ በገና እንደ መልአክ የሚያናግሩ፤ ስንትና ስንት ጠቢባን ነበሩባት፡፡ ከሐይቅ ዳር የሸንበቆ ውዝዋዜ ተነሥተው ኅሊና የሚመስጥ አቋቋም የቀመሩ፣ እያዜሙ ሲሄዱ እንኳን ገበሬውን በሬዎቹን የሚያስደምሙ ጠቢባን ነበሩባት፡፡ እንዴት በጥበብ ሀገር በኢትዮጵያ ጠቢብ ነኝ የሚል ሰው ‹ከዕውቀት ርቆ፣ ንጽሕ ጠብቆ› በድፍረት ይኖራል? ይኼኮ ሀገርን መድፈር ነው?  

አገሪቱ አድግበታልሁ፣ እመነደግበታለሁ፣ እለወጥበታለሁ፣ አሰላለፌን አስተካክልበታለሁ ብላ የደከመችበት የአምስት ዓመት ዕቅድ እንዴት በስሕተትና በድፍረት በተሞላ መድረክ እንዲታወጅ ይፈቀዳል? ይህንን ዕቅድ ባስታወስን ቁጥር ያንን ትልቅ ስሕተት እንድናስታውስ ለምን ተፈረደብን? ጥበብ ሳይሆን ድፍረት ትዝ እንዲለን ለምን ተገደድን? 
ጥበብ ምንም ዓይነት ይዘት ይኑረው የጥበብን ደረጃ ማሟላት ግን አለበት፡፡ ልማታዊም ሆነ አብዮታዊ፣ ዲሞክራሲያዊም ሆነ አምባገነናዊ፣ ይዘቱ ይለያይ እንጂ የጥበብ ደረጃው ግን አንድ ነው፡፡ ጥበብም የሚያሰኘው የጥበቡ ደረጃ እንጂ የያዘው ይዘት አይደለም፡፡ እንዴት ምግብ ቤቶቻችን ለምግብ አሠራርና አቀራረብ የሚጨነቁትን ያህል ለሀገራዊ መድረክ የሚጨነቅ ይጥፋ? እንዴት የበያይነቱ ምግብ ያህል ጥበብ በሀገራዊ መድረክ ላይ እንጣ?
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹ሀገራችን የራስዋ የሆነ ልዩ የዘመን አቆጣጠር አላት› ብለው ነገሩን፡፡ እውነት ነው ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሀገር ባህል ልብስ ለብሰው በነገሩን የሀገራችን ልዩ የዘመን ቆጠራ እንስማማለን፡፡ ‹አርቲስቶቹ›› ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሳስተዋል፤ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር የላትም›› አሉን፡፡ ‹‹አዲስ ዘመንም የሚብተው እንደ አውሮፓውያን በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የዘመን አቆጣጠራችን የተለየ ነው ያሉት ተሳስተው ነው›› አሉን፡፡ ኧረ እባክዎን ይጠይቁልን? ለምን ‹‹አርቲስቶቹ›› ጠቅላይ ሚኒስትሩን መቃወም ከፈለጉ የፖለቲካ ድርጅት መሥርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ተቃዋሚ ፓርቲ አያቋቁሙም? ደግሞስ ለሌሎች ያልተፈቀደ እንዴት ለእነርሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የቀጥታ የዓመት በዓል ሥርጭት እንዲቃወሙ ተፈቀደላቸው? እንደ አሜሪካ የምርጫ ክርክር በቀጥታ ሥርጭት ተቃዋሚና መንግሥት በአንድ መድረክ የሚቀርቡ ከሆነማ እውነትም ሀገሬ ተለውጣለች?
የዛሬ ዓምስት ዓመት እንዲሁ ያለ ስሕተት ‹አርቲስቶቹ› ሲሠሩ ዐውቀው በድፍረት ሳይሆን ሳያውቁ በስሕተት ነው ተብሎ ታለፈ፡፡ ዘንድሮ እንዳይደገምም ብዙዎች በሚችሉት ሁሉ አስቀድመው አሳሰቡ፡፡ ሰሚም መስሚያም ጠፋና ስሕተቱ በባሰ ሁኔታ ተደገመ፡፡ ሰውና ሰይጣን የተለያዩትኮ ከስሕተት በመታረምና ባለመታረም ነው፡፡ ወደ ሥልጣኔው መሄድ ሲገባን ወደ ስ…   
ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ፤ አሁን ማንን እንመን? እርስዎን እንመን ወይስ ‹አርቲስቶቻችንን››?
  

33 comments:

 1. Both of them are not our reference we have tangible & substantial evidence and real history so any body how wants to know his/her dignity ask our fathers
  Grateful for Dani !

  ReplyDelete
 2. ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ፤ አሁን ማንን እንመን? እርስዎን እንመን ወይስ ‹አርቲስቶቻችንን››? እስኪ ይንገሩን

  ReplyDelete
 3. << በሀገራችንኮ የልቅሶ ሥነ ሥርዓት እንኳን ወግ አለው፤ ጥበብ አለው፤ ትርዒት አለው፤ ፍሰት አለው፤ ድባብ አለው፤ ፈጠራ አለው፤ ርቀት አለው፣ ምጥቀት አለው፤ ደረጃ አለው፡፡ ይኼኮ ወግ የለው፣ ጥበብ የለው፣ ትርዒት የለው፣ ፍሰት የለው፣ ፈጠራ የለው፣ ደረጃ የለው፡፡ ድፍረት ብቻ፡፡ መሪዎቻችን ግን ለምንድን ነው የጥበብ አማካሪ የማይኖራቸው? ለምንድን ነው ጥበብን ከሚሰድቡ ሰዎች ጋር አብረው የሚቆሙት? ለምን ‹አርቲስቶቹን› እናከብራለን ብለው ሞያውን ይሰድቡታል? >>

  ReplyDelete
 4. ሰላም ዲያቆን ዳኒ, ጥበብን የሚከተላት ከጠፋ እኮ ቆየ. ይህ ስህተት እኮ በየዐመቱ ይደጋገማል.የሃይማኖት አባቶቻችንም ስህተቱን ማረም አልቻሎም. የሚያሳዝን ነገር ነው."አንተን አከብራለው ብዬ ሞያውን እንዳልሰድበው ፈርቼ ነው አሉት"እንደሱ ብለን እንለፈው. ስንት ሊቆችን ያፈራች አገር እንዲህ ሰው ትጣ?እግዜር ይሁናት.ዲያቆን ዳኒ ,መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 5. Algebagnim. 'Artistochu' min bilew naw?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Degmeh anbew begilts tekemtoal

   Delete
  2. ''...‹አርቲስቶቹ›› ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሳስተዋል፤ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር የላትም›› አሉን፡፡''
   I think Dani had some inferences to say this. But I couldn't get the exact word said by 'አርቲስቶቹ'...

   Delete
  3. እሩሳሌም ሰማያዊትNovember 6, 2015 at 11:33 AM

   ጥበብ የምትባለው ነገር አልገባችህም ማለት ነው
   ይሄንን ነው ትውልዱ ያጣው ሁሉንም ነገር ፈትፍቶ በማንኪያ Spoon feeding ዓይነት፡
   በግልጽማ አልተናገሩም በእኛ ኢትዮያውያን አቆጣጣጠር ምሽቱ የሚብተው ከምሽቱ 12 ሠዓት ነው
   ስለዚህ መስከረም 1 የሆነው ከለሊቱ 6 ሰዓት ሳይሆን ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ነው፤ ይህ የለሊት 6 ሰዓት ድለቃ
   የአውሮፓውያን ነው ማለቱ ነው‹፣ ይህ የአውሮፓውያን ከሆነ የአርቲስቶቹም እወጃ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር
   ለሊት 6 ሰዓት ከሆነና ጠቅላይ ሚንስተሩ ደግሞ የራሳችን አቆጣጣር አለን ካሉ ሁለቱ አልተጋጩም ትላለህ/
   ትያለሽ ወንድሜ/እህቴ ፡፡
   አስቀይሜ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ ተሳስቼም ከሆነ እታረማለሁ

   Delete
 6. Thank you Dn. Daniel.
  That night was disappointing! All the advertisements and everything mentioned were just "UNREALISTIC" or applies to few groups. Majorities of our people are suffering from unaffordable life expenses. I was watching on their advertisement the foods that I have never tested in the last 10 years because of high price. Look at the clips of and all the shows on the so called "cultural musics". They are all offensive to our people. The price of chicken goes up to 500 birr!!!!!!!!!I can't believe this is happening and we hear their development carton show on the television screen! Very sad!!!

  ReplyDelete
 7. ይህቺ ሀገርኮ ሰማየ ሰማያት ደርሰው የመጡ፣ ድንጋዩን አቅልጠው ጥበብ የሚያፈልቁ፣ አራት ጸሐፊ አስቀምጠው አንድ አንድ ምዕራፍ እየነገሩ መጽሐፍ የሚያስጽፉ፤ መሰንቆ እንደ ሰው፣ ክራር እንደ ወፍ፣ በገና እንደ መልአክ የሚያናግሩ፤ ስንትና ስንት ጠቢባን ነበሩባት፡፡ ከሐይቅ ዳር የሸንበቆ ውዝዋዜ ተነሥተው ኅሊና የሚመስጥ አቋቋም የቀመሩ፣ እያዜሙ ሲሄዱ እንኳን ገበሬውን በሬዎቹን የሚያስደምሙ ጠቢባን ነበሩባት፡፡ እንዴት በጥበብ ሀገር በኢትዮጵያ ጠቢብ ነኝ የሚል ሰው ‹ከዕውቀት ርቆ፣ ንጽሕ ጠብቆ› በድፍረት ይኖራል? ይኼኮ ሀገርን መድፈር ነው?

  ReplyDelete
 8. Dn Dani, please ሼር አድርግልን!!!! ምን እንደተባለ!!! መቅለል እንደሆነ አገራዊ አመል ሆኖ አርፎታል!!!
  Pls share the video on fb, atleast!!

  ReplyDelete
 9. Mastwalin yistachew

  ReplyDelete
 10. ፤ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር የላትም›› አሉን፡፡ ‹‹አዲስ ዘመንም የሚብተው እንደ አውሮፓውያን በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የዘመን አቆጣጠራችን የተለየ ነው ያሉት ተሳስተው ነው›› አሉን፡፡ ኧረ እባክዎን ይጠይቁልን? ለምን ‹‹አርቲስቶቹ›› ጠቅላይ ሚኒስትሩን መቃወም ከፈለጉ የፖለቲካ ድርጅት መሥርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ተቃዋሚ ፓርቲ አያቋቁሙም? ደግሞስ ለሌሎች ያልተፈቀደ እንዴት ለእነርሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዲቃወሙ ተፈቀደላቸው? it is pity to hear such national plan in way of irresponsible.

  ReplyDelete
 11. " . . .ዘንድሮ እንዳይደገምም ብዙዎች በሚችሉት ሁሉ አስቀድመው አሳሰቡ፤. . ." ታድያ ለምን ሰሚ ጠፋ ? ለእኔ እንደሚገባኝ አንድም ከእኔ በላይ ማን አዋቂ በሚል ታጅረዋል፤ አልያም የውስጥ ጠላት ሆነው በታሪካችን ላይ የሚድያ ጦርነት አውጀዋል። ሳያቃጥል በወቅጠል ይኼኔ ነው።

  ReplyDelete
 12. Ohhh... going pwerful!

  I agree, this should have been the rational; linear relationship between Artists and quality of Art. We're witnessing the vice versa in ETHIOPIA! This is historical! :( !

  ReplyDelete
 13. ኢትዮጵያ የተማረ አርቲስት የላትም የልምድ እንጂ፡፡ ለሙያው ሳይሆን ለሆዱ የሚያድር፡፡ መንግስትም እምነት የሌለውን እየሰበሰበ ነገሮችን ለመበረዝ ይሮጣል፡፡ ለህሊናው የሚገዛውንማ መች ያቀርቡታል፡፡

  ReplyDelete
 14. yenem tizbt neber kedem silm endezihu neber neger gin betelemdo denb eyehone meta. man min madreg endalebte enkuan yemiyawuk teftual

  endene letazebachu .................................

  ReplyDelete
 15. ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ፤ አሁን ማንን እንመን? እርስዎን እንመን ወይስ ‹አርቲስቶቻችንን››? እስኪ ይንገሩን!!!

  ReplyDelete
 16. dani sima kelematawe gazetegna ena kelematawe mere man yebeletal yehen teyake melsilign?

  ReplyDelete
 17. kelimatawe gazetefna ena kelematawe mengist man yebeltal?

  ReplyDelete
 18. ለምን ‹‹አርቲስቶቹ›› ጠቅላይ ሚኒስትሩን መቃወም ከፈለጉ የፖለቲካ ድርጅት መሥርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ተቃዋሚ ፓርቲ አያቋቁሙም?

  ReplyDelete
 19. በኢትዮጵያ ታሪክ ጉዳይ ላይ ኢሕአዴግን እንዴት ማመን ይቻላል?!
  በዲ/ን ኒቆዲሞስ
  ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል የኢትዮጵያችን ልዩ ቅርስ በኾነው የዘመን አቆጣጠራችንን በተመለከተ አንድ ጥያቄ አንስቶአል፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር በተመለከተ ‹‹ጠቅላይ ሚ/ሩን እንመን ወይስ አርቲስቶቻችንን?!›› የሚል ጥያቄ አንስቶ አንድ ትዝብትና ማሳሰቢያ አከል ጽሑፍ አስነብቦናል፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላለሁ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠርም ሆነ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ጉዳይ ላይ ኢሕዴግን/ክቡር ጠቅላይ ሚ/ሩን እንዳናምናቸው የሚያደርጉን አንዳንድ የታሪክ ሐቆች እንዳሉ ላንሣ፡፡
  እስቲ እነዚህን ሐቆች በጥቂቱ ብቻ ለማየት እንሞከር፡፡ በመሠረቱ የአገሪቱን ታሪክ ወደ መቶ ዓመት አውርዶ ለሚተነትነው፣ ጥንታዊው የሆነው ፊደላችን፣ ሦስት ሺሕ ዘመንን ያስቆጠረውን የሥነ-መንግሥት ታሪክ ‹‹የአቢሲኒያውያን/የነፍጠኞች ቅኝ ገዢዎች ታሪክ›› አድርጎ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ታሪክ በብሔር ብሔረሰቦች ማዕቀፍ ቀንብቦ ዳግም ለመፍጠር ለሚውተረተረው፤ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመሩት የኢሕአዴግ መንግሥት በምን ሞራልና ተጠየቅ፡- ‹‹ከአፍሪካ አገራት ሺሕ ዘመናትን ያስቆጠረ የራሳችን ፊደልና የዘመን አቆጣጠር ያለን ኩሩ ሕዝቦች …፡፡›› ተብሎ በአደባባይ ሊነግሩን እንደደፈሩ አይገባኝም፡፡ የታሪክ እውነት/ሐቅ ሲያሻን የምንደርበው እንዲያ ሲል ደግሞ አውልቀንና አሽቀንጥረን የምንጥለው የበረሃ ሽርጥ ኾነ እንዴ ጎበዝ …?! ይሄ በእውነት ያስተዛዝባል፡፡ ወይስ ደግሞ እንደው ሳንሰማ ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያለውን አቋም አስተካክሎ ይሆን እንዴ … እ…እ…እ… አይመስለኝም፡፡
  በዚህ ረገድ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትራችን የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊም፣ ‹‹… የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ ዓመት ታሪክ ነው፣ የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው …?! እንዳላሉን ኹሉ የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ሲከበር ባደረጉት ንግግራቸው፣ ‹‹… እኛ ኢትዮጵያውያን የሦስት ሺሕ ዘመን ታሪክና መንግሥት ያለን ነጻና ኩሩ ሕዝቦች …›› ሲሉ ሰምተናቸው መገረማችንን አስታውሳለኹ፡፡ እዚህ ጋራ የኢትዮጵያን ታሪክ ‹‹በአቢሲኒያውያን/በነፍጠኞች ቅኝ ግዛት ወረራ›› የታሪክ መነጽር የሚመለከተው ኢሕአዴግ ሙሉ ድጋፉንና ፈቃዱን በቸረበትና የኤርትራውያን ጥያቄ ‹‹የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው›› በሚል የኤርትራውያን ነጻ እንዲወጡ ባደረገበት ወቅት የኾነውን የታሪክ ቀውስም በጥቂቱ ማየት እንችላለን፡፡
  ትናንትና የኢትዮጵያ አካል የነበሩት ኤርትራውያን ወገኖቻችን ነጻነታቸውን ባወጁ ማግሥት የዘመን አቆጣጠራቸውን ወደ ጎርጎርሳውያን የቀየሩት የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ቅኝ ገዢዎቹ አቢሲኒያውያን/ነፍጠኞች እንደ ብርድ ልብስ የደረቡብን የእኛ ያልሆነ- ታሪካችንን፣ ቅርሳችንንና ማንነታችንን የሚያራክስ፣ የሚያጣጥል ነው በሚል አመክንዮ እንደሆነ የምንስተው አይመስለኝም፡፡ የኋላ ኋላ የኾነውን ነገር ኹሉ እናስታውሳለን፤ ባልነበረ የፈጠራ ታሪክ ሺሕዎች ጭዳ የኾኑበትን የጦርነት፣ እልቂት መዘዝ በኀዘን እናስታውሳለን፡፡ አሁንም ድረስ የኹለቱ አገራት ጉዳይ የተዳፈነ እሳት ሆኖ አለ፡፡
  በዚሁ የፈጠራ ታሪክ ጦስ የሆነውን ሌላኛው ትዝብቴን ላክል፡፡ ኤርትራዊ ብሔርተኝነትን በአዲስ የታሪክ ሂደትና ትንታኔ ለመፍጠር ሲውተረተር የነበረው የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂና ደጋፊዎቹ/ብሔርተኛ ኤርትራውያን ባለፈው ዓመት ደግሞ፣ ‹‹… ለመሆኑ እንደው የሆነስ ሆነና ኢትዮጵያ ከማን ተሸላ ነው እኛን ሥልጡን፣ የራሳችን የዘመናት ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባህልና ሥልጣኔና ያለንን ሕዝቦች ቅኝ ለመግዛት የቻለችው?!›› በሚል ለዓመታት ሲያቀነቅኑ የነበረውን ‹‹ኢትዮጵያ ቅኝ ገዘታናለች›› የሚለውን የታሪክ ምጸት በውስጣቸው የፈጠረውን የበታችነት ስሜትና የማንነት ቀውስ በሌላ ተረት ተረት ላማከምና ኤርትራዊ ብሔርተኝነትን በሁለት እግሩ ለማቆም ደፋ ቀና ሲሉ ታዝበናቸዋል፡፡
  በተጨማሪም ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብንም ለዘመናት ሲጠቀምበት የነበረውን ፊደሉን ከግእዝ ፊደል ወደ ላቲን ፊደል እንዲቀይር ያስገደደው ይኸው ኢሕአዴግ በሚያቀነቅነው ‹‹የአቢሲኒያውያን/የነፍጠኞች የቅኝ ገዢዎች ታሪክ›› ትንታኔ መነሻነት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ታዲያ ባለ ሥልጣኖቻችን እንዲህ የሚያጣጥሉትንና የሌሎችና ታሪክና ቅርስ፣ ማንንት ያመከነና የዘረፈ ነው ብለው የሚከራከሩበትን የኢትዮጵያን ታሪክና ቅርስ እንዴት በአደባባይ ሺሕ ዘመናትን ያስቆጠር የፊደል፣ የዘመን አቆጣጠር ያለን የሦስት ሺሕ ዘመናት ታሪክ ባለቤት ሕዝቦች ሊሉን የቻሉበትን ድፍረት የት እንዳገኙት ለመጠየቅ፣ ለመሞገት እንገደዳለን፡፡ እንዲህ እንደ እስስት በመለዋወጥስ የታሪክ ሐቅን መለወጥ ይቻላል እንዴ?!
  ከኢትዮጵያን ታሪክ አንስቶ እስከ ፊደላችን ድረስ በርካታ ጥያቄዎች አሉብን፡፡ ለአንዳንዶች የኢትዮጵያ የሺሕ ዘመናት ታሪክ የአቢሲኒያውያን/የነፍጠኞች ቅኝ ግዛት ታሪክ እንደሆነ ነው የሚሰማቸው፡፡ ለአንዳንዶች ደግሞ ፊደላቱ ያለ ቅጥ በዝተዋልና ይቀነሡ በሚል ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ፡፡ ይህን ጥያቄ መዳኘትና መልስ መስጠት የሚገባቸው ከእውነት ጋር የወገኑ የእውቀት ሰዎች-ጠቢባኑ ደግሞ ከመድረክ ተገፍተው ታሪክን እንዳሻቸው የሚተነትኑ አድር ባዮች፣ በአገሪቱ ታሪክ ማኅፀን ሌላ ለከፋፋይ ፖለቲካቸው የሚመቻቸውን ጽንስ እያበጁ እያየንና እየሰማን ይኸው በፍርሃት ተሸብበን አለን፡፡ እነርሱም ያለ ምንም እፍረት ታሪካችንን ለጊዜያዊ ፖለቲካቸው ጥቅም ሲሉ እንዳሻቸው ሲለዋውጡት በአግርሞት እያየናቸውና እየሰማናቸው ነው፡፡
  በመጨረሻም ወደ ዘመን አቆጣጠራችን ጉዳይ ስመለስ ዛሬ ዓለም ኹሉ እየተደመመበት ያለውንና ይህ የዘመን አቆጣጠርም ከሥነ ፍጥረት ሕግና ሂደት ጋራ የተስማማ እንደሆነ የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት የካቶሊኩ ፖፕ የነበሩት ጀርመናዊው ፖፕ ቤኔዲክት የአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር ስህትት እንደሆነና ከአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር ይልቅ ይኸው የእኛው የኢትዮጵያ ዘመን አቆጠጠር ትክክል እንደሆነ Jesus of Nazareth: The Infancy Narratives በሚል መጽሐፋቸው ለመላው ዓለም አሳውቀዋል፡፡
  የኢትዮጵያን ዘመን አቆጣጠርና ደማቅ ክብረ በዓሉን በተመለከተ ደግሞ ዘንድሮ በተለየ ሁኔታ እንደ ለንደኑ ቢ.ቢ.ሲ፣ የአሜሪካው ሲ.ኤን.ኤን፣ የዶሃው አልጀዚራና የኢራኑ ፕሬስ ቴሌቪዥኖች ሽፋን በመስጠት ዘግበውት ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ የኩባ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በስፓኒሽ ቋንቋ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኩባውያን ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ልዩ ዘገባ እንዳቀረቡ ተከታትለናል፡፡ ተወደድም ተጠላ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅርስ የኾነው ይህ የዘመን አቆጣጠራችን ከአፍሪካ አልፎ የዓለም ኹሉ ቅርስ ወደመሆን እየተሸጋገረ እንዳለ እየታዘብን ነው፡፡ ይህን ዓለም ሁሉ አምኖ የተቀበለውንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አሻራ ያለበትን የአገሪቱን የታሪክ ሐቅ መካድ፣ ማፋለስ፣ መበረዝ፣ … ከራስ ጋራ፣ በፍቅርና በአንድነት የጥበብ ልዩ ሸማ ከተዋበው፣ ዘመናት ካልሻሩት ኢትዮጵያዊ ማንነት፣ ታሪክና ቅርስ ጋራ መጣላት መሆኑን በመግለጽ ልሰናበት፡፡
  ሰላም!  ReplyDelete
  Replies
  1. ድንቅ እይታ፣ ሆድ አደር እና የታሪክ አተላዎች በበዙበት ዘመን እደናንተ ለወገን እና ሀገር ተቆርሪዎችን ያላሳጣን እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን፡፡

   Delete
  2. ድንቅ ነው !!!
   መቼ ይህ ብቻ የሚያደርጉትስ የታሪክ ሽሚያ ቀላል ነው እንዴ?
   ለምሳሌ አሸንዳዬ /አሸንድዬ የማናት፣የትግራይ ወይስ የሰቆጣ
   አሁን አሁንማ የቡሄን/ደብረታቦር በዓልን ለማስረሳትና በአሸንዳዬ
   ለመተካት ትግል ላይ ናቸው፡፡የኢትዮጵያን ታሪክ የእምቧይ ካብ እንዲሆን
   የሚጥሩ ብዙዎች ናቸው፡ አይሳካላቸውም
   እግዚአብሄር የሚሠራው ከማንም ይበልጣልና፡፡

   Delete
 20. Truth cast to earth shall raise again! nobody has the power to divert the bold fact! unless we ourselves are in position to be changed the fact is remains as it is! there are a great deal of living symbol of evidences that testify about the the very ancient history of the country. As one is simply tries to deal with many of the country's ancient profile, some of them are beyond the knowledge of human imagination, for me it remains secret and forced to simply to admire it and get into spiritual satisfaction. therefore some times it is good to be in this state of mind rather than we tried to investigate things in the way we commonly would like to do it b/se it is the works of the Holy Spirit. that is why many of our colleagues often get confused with the history of Ethiopia and made mistakes. May God open our mind to recognize the truth and feel comfort with our ancient history .

  ReplyDelete
 21. ጥበብ እውነት የሆነውን ግንዛቤን ወስዶ መልሶ ያንኑ እውነት ማንፀባረቅ ነው። ላለፉት አመታት ግለሰቦች ሳይሆኑ ህዝባችን በልጽጎ ቢሆን ኖሮ፣ ይህንን እውነት በመድረክ ለመተወን አጣፍጦ ለማቅረብ ምን ያሸግር ነበር። በውሸት ግን ልንጠበብ አንችልም፣ የግለሰቦችን ብልጽግና የሰፊው ህዝብ እድገት ልናረገው አንችልም። ስለዚህ እጣ ፋንታችን እጅ እጅ ያለ፣ ወጥ መገጉረስ ነው!!!

  ReplyDelete
 22. ዲ.ን ዳንኤል እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቅህ።

  ReplyDelete
 23. Anonymous, September 18, at 11:11 am , I proud of you! And thank you!

  ReplyDelete
 24. ዳኒ.....ይብራብህ በቃ...ማንም ሚሰማህ የለም...ሁሉም መስሚያው ጥጥ ነው።

  ReplyDelete
 25. both of them are not trusted by all.we have not grace leader and grace artists.

  ReplyDelete