Thursday, September 10, 2015

የዕብድ ኀሙስ


የታደለ አገልጋይ የበላዩን ከስሕተት ይጠብቃል፡፡ ‹አማካሪ የሌለው ንጉሥ ያለ አንድ ዓመት አይነግሥ› እንዲሉ፡፡ አክዓብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት(871-852 ቅልክ) የነበረ ንጉሥ ነው፡፡ የሚስቱን የኤልዛቤልን ቃል ሰምቶ ነቢያተ እሥራኤልን ሊያጠፋ ተነሣ፡፡ ብዙዎች በሰይፉ ጠፉ፣ ብዙዎችም አገር ጥለው ተሰደዱ፡፡ በአክአብ ቤተ መንግሥት ውስጥ ግን አብድዩ የተባለ ልብ ያለው ባለሟል ነበር፡፡ ንጉሡን ከጥፋቱ ማዳን ቢያቅተው በንጉሡ ስሕተት ባለመስማማቱ 100 ነቢያትን በሁለት ዋሻ ውስጥ ደብቆ የቤተ መንግሥቱን ምግብ እየመገበ ከአክዓብ ጥፋት አድኗቸው ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ነቢያት የእሥራኤል የዕውቀትና የእምነት መሪዎች ናቸው፡፡ የእሥራኤል ባህል፣ ታሪክ፣ ትውፊትና ዕውቀት የሚተላለፈው በነቢያት ትውፊት ነበርና፡፡ ነቢያቱን ማጥፋትም ሀገሪቱን ያለ ታሪክ፣ ዕውቀት፣ ባህል፣ ሥርዓትና ቅርስ ማስቀረት ነበር፡፡ ለዚህ ነው አብድዩ የንጉሡን ዐዋጅ ማስቀየር ቢያቅተው ነቢያቱን ደብቆ እየመገበ ሀገሪቱን ከከባድ ጥፋት የታደጋት፡፡ 

ይህንን ሥራውን ማንም እንዲያውቅለትም፣ እንዲያውቅበት አላደረገም፡፡ ዓላማው ዕውቅና ጥቅም ማግኘት ሳይሆን ሀገር ማትረፍ ነውና፡፡ የንጉሡን የጥፋት ዐዋጅ ማስቀረት አልችልም ብሎ ዝም አላለም፤ ነገር ግን በዐቅሙ የሚችለውን በማድረጉ በእውነትም እሥራኤል የዕውቀት፣ የታሪክና የባህል ጥፋት እንዳይገጥማት አደረገ፡፡ ያን ክፉ ዘመንም አሻገራት፡፡  
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የበላዮቻቸውን ጥፋት ከማስቀጠል ይልቅ በራሳቸው ዐቅም የሚችሉትን መልካምነት የፈጸሙትን ብቻ ሳይሆን፣ ‹ትእዛዝ ከበላይ እግር ወደ ላይ› ከማለት አልፈው አለቆቻቸውን ከጥፋት የታደጉ የበታች አገልጋዮችንም ታሪክ እናገኛለን፡፡ የሶርያው ንጉሥ የቤን ሐዳድ 2ኛ የጦር አዛዥ ንዕማን ወደ ሰማርያ መጥቶ ነቢዩ ኤልሳዕን ባገኘው ጊዜ ከለምጽ ሕመሙ ይድን ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ እንዲጠመቅ መክሮት ነበር፡፡ ንዕማን በዚህ ደስተኛ አልሆነም፡፡ ተቆጥቶም ወደ ሀገሩ ሊጓዝ ተነሣ፡፡ አንደኛው ባለሟሉ ግን ለጦር አዛዥ የሚገባ ምክርን መከረው ‹‹ጌታዬ ምን ቸገረህ፣ ውረድና ተጠመቅ፤ ከተፈወስክ እሰዬው፤ ክልሆነ ግን ከሰማርያ ጋር የምንዋጋበት ምክንያት እናገኛለን››፡፡ የጦር አዛዡ ንዕማን በዚህ የወታደሩ ሐሳብ ተስማማ፡፡ ዮርዳኖስ ወርዶም ተጠመቀ፡፡ ዳነም፡፡ አገልጋዩም አዛዡን ከጥፋት አዳነው፡፡ ንዕማንም ሊፈጽመው በነበረው ስሕተት ተጸጸተ፡፡
 
በታሪክ ውስጥ ግን እንደ አብድዩና የንዕማን ወታደር የበላዮቻቸውን ስሕተት የማይደግሙ ወይም አለቆቻቸውን ከስሕተት የሚታደጉ የበታቾች ብቻ አይደሉም የነበሩት፡፡ ያሉትም፡፡ አለቆቻቸው ያላሰቡትን ጥፋት በመሥራት አለቆቻቸውን ያስደሰቱ መስሏቸው ሀገር ያጠፉም አሉ፡፡ ‹ከለማበት የተጋባበት› እንዲሉ፡፡ ‹ጌታዬ እንዲህ ባደርግለት ይደሰታል› ብለው በማሰብ ከልክ እያለፉ፣ የሌለ እየጻፉ፣ ያልታዘዘ እየፈጸሙ ግፍ ሲሠሩ የኖሩ፡፡ ያዘው ሲባሉ ጣለው፤ እሠረው ሲባሉ ግደለው፤ አምጣው ሲባሉ ስቀለው፤ ተቀበለው ሲባሉ ቀማው የተባሉ እየመሰላቸው ሕግ ሲያልፉ፣ ገደብ ሲጥሱ የኖሩ አሽከሮችም ነበሩ፡፡ አሉም፡፡   
 
በሀገራችን ከነነዌ ጾም በኋላ የሚመጣው ኀሙስ ‹የዕብድ ኀሙስ› ይባላል፡፡ ቀኑ አለቆቻቸውን ለማስደሰት ሲሉ በግፍ ላይ ግፍ፣ በክፋት ላይ ክፋት፣ በመከራ ላይ መከራ፣ በቅጣት ላይ ቅጣት፣ በእንግልት ላይ እንግልት በሕዝብ ላይ ለሚጨምሩ አሽከሮች መታሰቢያ ነው፡፡ እንደ አብድዩና የንዕማን ወታደር ‹እስኪ ነገሩን እንየው› ከማለት ይልቅ ጭካኔ፣ ግፍ፣ ቅጣትና በደል አለቆቻችንን ይበልጥ ያስደስትልናል ብለው ለሚያስቡ አሽከሮች መታሰቢያ፡፡
 
በሸዋው ንጉሥ አስፋ ወሰን ዘመን ንጉሡ ለዘመቻ እየተጓዙ በደብረ ብርሃን አልፈው አንጎለላ ደረሱ፡፡ ይህን ጊዜ ጎሜ ጎሹ የተባለ አሽከር አስፋ ወሰንን በምን ላስደስታቸው ይልና በራሱ ጊዜ ዐዋጅ ያውጃል (‹መቼም ንጉሡ ሥራ በዝቶባቸው ረስተውት ነው እንጂ ይህን ሳያውጁ አይቀሩም‹ ብሎም ይሆናል)፡፡ ‹‹በዚህ ሀገር ያለውን ሰው ሁሉ አንድ ሳታስተርፍ በለው ብለውሃል› የሚል ዐዋጅ፡፡ ሠራዊቱም የንጉሥ ዐዋጅ መሰለውና አእምሮው ትቶ ጉልበቱን በማሠራት ፈረሱን እየጋለበ ከበሬሳ እስከ አያብር፣ ካንድ ዐርብ እስከ መገዘዝ የነበረውን ሀገር ሁሉ በነነዌ ፋሲካ ዕለት ኀሙስ ዘምቶበት ዋለ፡፡ ሕዝብ አለቀ፣ ተሰደደ፣ በሀገርም ላይ መከራ ወረደ፡፡ ንጉሡም የሆነውን ሲሰሙ አዝነው ጎሜ ጎሹን ‹‹ማን አዞህ ዐወጅክ?› ቢሉት ‹‹ጌታዬ መቼም የዘመትነው ለዚህ ነው ብዬ ነው›› አለ ይባላል፡፡ ቃላዊ መረጃዎች እንደሚነግሩን አስፋ ወሰን ጎሜ ጎሹን ቀጥተውና አሥረው ከዘመቻ ወደ አንኮበር ላኩት፡፡
ሕዝቡም ‹‹ወይ ጎሜ ጎሹ ወይ ጎሜ ጎሹ
በድፍን ሀገር ዕዳ ነስናሹ› ብሎ ገጠመበት፡፡ ቀኑም ‹የዕብድ ኀሙስ ተባለ›› ይላሉ ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ በጻፉት የዳግማዊ ምኒሊክ ታሪክ ላይ፡፡
 
የቻለ እንደ ንዕማን ወታደር አለቃውን ከስሕተት ይታደጋል፣ ከጥፋት ያድናል፤ ያልቻለም እንደ አብድዩ የበላዩን ስሕተት ማረም ቢያቅተው እርሱን ስሕተቱ ይዞት እንዳይጠፋ ራሱን ከስሕተቱ ያድናል፣ ከጥፋቱም ይጠብቃል፡፡ ለሌሎችም የመዳኛ ምክንያት ይሆናል፡፡ እንደ ጎሜ ጎሹ ‹አለቃየ ይህን ባጠፋለት ደስ ይለዋል› ብሎ የሚያስብ አሽከር ግን ‹በድፍን ሀገር ዕዳ ይነሰንሳል›፡፡ ጎሜ ጎሹዎች ትንሽ ቀዳዳ ካገኙ አስፍተው ስለሚጓዙባት አለቆቻችን ምንም አይሉንም ብለው ያስባሉ፤ እንዲያውም አብልጠው በማሰባቸው እንደሚሸለሙ ያምናሉ፡፡ ጎሜ ጎሹዎች የአለቆቻቸውን በር በመዝጋት፣ እንደ አለቆቻቸው ሆነው በመወሰን፣ ቁጣውን ወደ ጥፊ፣ ጥፊውን ወደ ግርፊያ፣ ግርፊያውን ወደ ግድያ በማሳደግ የተሻለ አፈጻጸም ለማሳየት ይተጋሉ፡፡ 
 
አብድዩና የንዕማን ወታደር የበዙላት ሀገር ዶፍ ዝናብን በጣራ፣ ካፊያን በጥላ እንደሚከለል ሰው፣ ከላይ የሚመጣውን ጥመት አቃንተው፣ የሚወርደውን ጥፋት አርመው፣ ቁጣውን በትዕግሥት፣ መዓቱን በምሕረት ስለሚለውጡት ድፍን ሀገር ዕዳ ሳይሆን ፋታ ያገኛል፡፡ ጎሜ ጎሹዎች ሲበዙ ግን በበሆር ላይ ቆረቆር፣ በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፣ በዕዝል ላይ እንጥልጥል፣ በራቁት ላይ ብርድ፣ በጥማት ላይ ንቃቃት ይሆናል፡፡ ሕዝቡ እንዳለው ጎሜ ጎሹዎች ‹በድፍን ሀገር ዕዳ ይነሰንሳሉ›፡፡ እነርሱ ለዕለቱ የሚያገኙትን ሹመት ሽልማት፣ ጉርሻና ድርሻ እንጂ አለፍ ዘለቅ አድርገው የችግሩን ውጤት አያስቡትምና ጎሜ ጎሹዎች የሚያመጡትን ዕዳ ሀገር ስትከፍለው ትኖራለች፡፡    
 
በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያችን ጎሜ ጎሹዎች ሳይሆን አብድዩዎችና የንዕማን ወታደሮች የሚበዙባት ሀገር ትሁን፡፡

29 comments:

 1. Amen! This is helping in prayer! For those who believe in prayers, The O.T.Church pray for everybody.

  ReplyDelete
 2. Dear Daneil,
  I know what you try to say, but you should SAY it in open. You should have been oppose the TPLF with out hiding in the story of bible.

  ReplyDelete
  Replies
  1. This year TPLF and EPRDF have declared, that there were bad trends of governance which will be averted in the GTP 2. I hope all members get it well and do as declared. So Solomon, please donot politicize things...although sometimes critics strikes hard...do we have to wait 5 years till the parties themselves see it/them...it will be to late next time to make corrective measures. Any ways

   Delete
  2. Dear solomon
   first understood the history and then as if you can learn from history that is good unless don't smash together with politics. No one know others idea but you said ' I know you ' it is trash comment

   Delete
 3. አሜን ዘመኑን የማስተወያ የህሌና ስራ መስሪያ ያድርገልን አሜን
  WTBMHG

  ReplyDelete
 4. ውድ ዲ.ን ዳንኤል ፣
  ሁሌም ያለስስት በዚህ ብሎግ ለምታቀርባቸው ታላቅ ቁምነገሮች እጅግ አድርጌ አመሰግንሀለሁ፡፡ በእኔ እምነት ክርስትና ከእውነትና ቅን ነገር ጋር መቆም ነው ፡፡ እነሆ አንተ ለብዙዎች ምሳሌ ሁነህ እውነቱን በመተንተን በተለያየ መንገድ ሰዎች ከክፉ ተግባራቸው እንዲታቀቡ የምታደርገው ጥረት የሚስመሰግን ነው፡፡ ሁላችንም በቅን መንፈስ ሰዎችን ከጥፋት መንገድ እንዲመለሱ በምክርም፣በፀሎትም እንድንተጋ እግዚአብሄር ይርዳን፡፡

  ReplyDelete
 5. በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያችን ጎሜ ጎሹዎች ሳይሆን አብድዩዎችና የንዕማን ወታደሮች የሚበዙባት ሀገር ትሁን፡፡

  ReplyDelete
 6. ዲያቆን ዳኒ ቃለ ህይወት ያሰማልን!አሜን የኢትዬጵያን ትንሤሔዋን እንድናይ አምላከ ቅዱሳን ይርዳን.ሁላችንም በፀሎት እናስባት .ዲያቆን ዳኒ, መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 7. ጌታየ እሽ በልና ተጠመቅ ከዳንህም እሰዬው ካልዳንህም ምክንያት አገኘን ከሰማርያ ጋር ለመዋጋት ?ግሩምና ድቅ አገላለጽ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥፍት እያስተማረ ሊያድን ከመሞከር አልፎ እዬታመመ፣እየቆሰለ፣ እተተደበደበ፣እየተሰደደ፣እየተዋረደ፣እየታሰረ፣እየሞተ፣ሀገሩን፣እያስረከበ፣ምፃተኛ፣እየሆነ አረ ስንቱ ስንቱ ምኑ ተነግሮ ምኑ ይቀራል ጽዋው ሞልቶ ፈሶ ሊያስተምር ቢሞክር አከቆችም አሽከሮችም አልሰማ ስላሉ።በቀጣዩ አመት ኢትዮ አብዲዎችን ብትሆን ተጠያቂው ማነው በማንስ ይፈረዳል መልሱን ላንባቢያንና ኢትዮጵያውያን እተዋለሁ? ለማንኛውም አምላኮ አይተዋትምና ኢትዮጵያን በፀሎት እንበርታ መልካም አዲስ አመት።ቸር እንሰንብት።ከበላይ ነኝ።

  ReplyDelete
 8. የወገብ ቀማል የሆኑባትን ለማረፍ የግድ ያስፈልጋል ።ከወገቦ ላይነቅሎ የሚጥል የሚገልላት የንዓም ወታደሮች ትፈልጋለች እማማ።

  ReplyDelete
 9. የትኛውን እንመን?
  "...የዘንበሪም ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ በሰማርያ ሀያ ሁለት ዓመት ነገሠ።" ይለናል መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ ነገሥት16:29 ላይ
  እንዲሁም አንድ በእንግሊዝ አፍ የተጻፈ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ እንዲህ ይነበባል:-
  Ahab, son of Omri; seventh king of the northern kingdom of Israel, second of his dynasty; reigned 22 years, from 919 to 897 B.C.
  ታዲያ ዲያቆን ዳንኤል በጽሁፍህ መግቢያ ላይ ያስቀመጥከው:- "አክዓብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት(871-852 ቅልክ) የነበረ ንጉሥ ነው፡፡" ከመጽሐፍ ቅዱስም (22 ዓመት/ካንተ 20/19 ዓመት ጋር) ከማብራሪይውም(22/20) ጋር ይጣረሳል::
  የትኛውን እንመን? አንተን: ማብራሪያውን ወይስ መጽሐፍ ቅዱስን:: እኔ በበኩሌ የመጽሐፍ ቅዱስንና ማብራሪያውን 22 ዓመት መርጫለሁ

  ReplyDelete
 10. በቤተመንግስቱ እና በቤተክህነቱ ያሉት ጎሹዎች መልካም ልቡና አምላከ ቅዱሳን በአዲሱ ዘመን ያድልላቸው አለበለዚያ በሀገራችንና በሃይማኖት ቦታዎች ከዚህ የከፋ እንዳይመጣብን ስጋታችን የሰፋ ሆኖአል።
  እስኩ ድግሙ ነኝ ከጀርመን ዳኒ በጣም አመሰግናለሁ ።

  ReplyDelete
 11. አሜን። በዚሁ አጋጣሚ እንኳን አደረሰህ ዳኒ።
  "በሀገራችን ከነነዌ ጾም በኋላ የሚመጣው ኀሙስ ‹የዕብድ ኀሙስ› ይባላል፡፡" ባልከው ላይ እኔ ባደኩበት አካባቢ ግን ዕብድ ኀሙስ ከነነዌ ቀጥሎ የምትመጣው ሳትሆን በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ያለችው ኀሙስ ነች።
  መልካም ዘመን።

  ReplyDelete
 12. አማካሪ የሌለው ንጉሥ ያለ አንድ ዓመት አይነግሥ

  ReplyDelete
 13. ውድ የሀገር ልጅ፥የምታቀርባቸው ጽሁፎች ታሪክንና መፅሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረጉ በመሆናቸው ያስተምራሉ ይሰብካሉ ብሎም ያንጻሉ፥ የማይገባኝ ግን ጠማማ ጠማማ ነው ብሎ መንገርን ብታውቅበት ደግ ነው ምክንያቱም ለዚህ ትውልድ ውስጠ ወይራ ንግግር ትርፉ ድካም ይሆናል ፍቺውም ከስው ሰው ይለይና ግቡን ይስታል ብዬ ነው፥ ያም ቢሆን ለጫማ ቁጥር ጥያቄ ከበሬው ብንጀምር ምን እንደሚሆን ገምት ፥ቢሆንም ብዙ ብልህ ተምሮ ብዙ ደግሞ ተማሮ ንባቡን ስለሚያቆም please to the point!!

  ReplyDelete
 14. It is the end of the world so we don’t expect from them to have miracle. HAPPY NEW YEAR AND PLEASE READ MATTHEW 24. ምዕራፍ 24
  1 ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።

  2 እርሱ ግን መልሶ። ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው።

  3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

  4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።

  5 ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።

  6 ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።

  7 ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤

  8 እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።

  9 በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

  10 በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤

  11 ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤

  12 ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።

  13 እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

  14 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።

  15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥

  16 በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥

  17 በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፥

  18 በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።

  19 በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።

  20 ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤

  21 በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።

  22 እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።

  23 በዚያን ጊዜ ማንም። እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም። ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤

  24 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።

  25 እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።

  26 እንግዲህ። እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤

  27 መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና፤

  28 በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ።

  29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥

  30 የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤

  31 መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።

  32 ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤

  33 እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ።

  34 እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።

  35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።

  36 ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።

  37 የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።

  38 በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥

  39 የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

  40 በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤

  41 ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች።

  42 ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።

  43 ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር።

  44 ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።

  45 እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?

  46 ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤

  47 እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።

  48 ያ ክፉ ባሪያ ግን። ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ፥

  49 ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥

  50 የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥

  51 ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፥ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

  ReplyDelete
 15. እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።

  7 ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤
  በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

  10 በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤

  ReplyDelete
 16. ‹‹ወይ ጎሜ ጎሹ ወይ ጎሜ ጎሹ

  በድፍን ሀገር ዕዳ ነስናሹ›

  ReplyDelete
 17. ‹‹ወይ ጎሜ ጎሹ ወይ ጎሜ ጎሹ

  በድፍን ሀገር ዕዳ ነስናሹ›

  ReplyDelete
 18. እንኳን አደረሰህ ዲ/ን ዳንኤል!
  ኢትዮጵያችን ጎሜ ጎሹዎች ሳይሆን አብድዩዎችና የንዕማን ወታደሮች የሚበዙባት ሀገር ትሁን፡፡

  ReplyDelete
 19. አማካሪ የሌለው ንጉሥ ያለ አንድ ዓመት አይነግሥ

  ReplyDelete
 20. አማካሪ የሌለው ንጉሥ ያለ አንድ ዓመት አይነግሥ....
  http://www.easyflight365.com/

  ReplyDelete