click here for pdf
የምርጫ ሂደቱ ከታኅሣሥ ወር ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የበጎ ሰው ሽልማት ለሦስተኛ ጊዜ
ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓም በአኩስም ሆቴል ተከናወነ፡፡ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ተሸላሚዎች፣ የተሸላሚ ቤተሰቦች፣ ዕጩዎች፣ የክብር
እንግዶችና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት ተከናውኗል፡፡ በዕለቱ ለዕጩዎች የዕጩነት የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን ለአሸናፊዎች
ደግሞ የክብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡
በዚህ መሠረት

ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል በዳኞች የተመረጡት የዚህ ዓመት የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎች
የተመረጡባቸው ዋነኛ መሥፈርቶች ሦስት ሲሆኑ እነርሱም በዘመናቸው ካገኙት ዕድል በመነሣት በሞያቸው የተጓዙበት ርቀት፤ አርአያ በመሆን
ወይም ፈር በመቅደድ፣ ወይም ችግርን በመፍታት ወይም ደግሞ አዲስ መንገድ በመቀየስ፣ ወይም በጎ ተጽዕኖ በማሳረፍ ወይም ሌሎችን
በማፍራት ያበረከቱት አስተዋጽዖ፤ እና ማኅበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ ያላቸው አበርክቶ የሚሉት ናቸው፡፡ ከእነዚህም በተጨማሪ
ሌሎች ዝርዝር መመዘኛዎች ታይተዋል፡፡
1.
በሳይንስ ዘርፍ - ፕሮፌሰር
አበበ በጅጋ
2.
በማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ- አቶ
ደሳለኝ ራሕመቶ
3.
በበጎ አድራጎት ዘርፍ - ወ/ት
ትርሐስ መዝገበ
4.
በቢዝነስና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ
- ሰላም ባልትና
5.
በስፖርት ዘርፍ - ዶክተር
ወልደ መስቀል ኮስትሬ
6.
በሥነ ጥበብ ዘርፍ - ሰዓሊ
ታደሰ መስፍን
7.
በቅርስ፣ ባሕልና ቱሪዝም ዘርፍ
- አቶ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ
8.
መንግሥታዊ ኃላፊነትን በመወጣት
ዘርፍ - አቶ ሽመልስ አዱኛ
9.
በጋዜጠኝነትና ሚዲያ ዘርፍ-
አቶ ያዕቆብ ወልደ ማርያም
ተሸልመዋል፡፡
በመጀመሪያው ክፍል ዕጩዎች ታሪካቸው በአጭር ቀርቦ ክብር የተሰጣቸው ሲሆን በሁለተኛው
ክፍል ደግሞ ተሸላሚዎች ነጋሪት እየተጎሰመ፣ ጡሩንባ እየተነፋ፣ ካባ ለብሰውና ታጅበው በሕዝቡ መካከል ዑደት በማድረግ ከብረዋል፡፡
ሥራቸውም በታዋቂ ሰዎች ቀርቧል፡፡
·
የፕሮፌሰር አበበ በጅጋን -
አንዱ ዓለም ተስፋየ፤
·
የሰላም ባልትናን - ገጣሚ
ምሥራቅ ተረፈ፣
·
የአቶ ያዕቆብ ወልደ ማርያምን
- ጋዜጠኛ ብርቱካን ሐረገ ወይን፣
·
የአቶ ሺመልስ አዱኛን - ገጣሚ
ሜሮን ጌትነት፣
·
የወ/ት ትርሐስ መዝገበን -
ተዋናይ ሳምሶን ታደሰ(ቤቢ)፣
·
የዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬን-
ጋዜጠኛ ፍቅር ይልቃል፣
·
የአቶ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰን
- ጋዜጠኛ ማኅደረ ታሪኩ፣
·
የአቶ ደሳለኝ ራሕመቶን -
ደራሲ ዐሥራት ከበደ፣
የልዩ ተሸላሚውን የፊታውራሪ
ዐመዴ ለማን ታሪክም ሱራፌል ወንድሙ አቅርበዋል፡፡
ሽልማቱንም
·
አምባሳደር ዘውዴ ረታ - ለፕሮፌሰር
አበበ በጅጋ፣
·
ሰዓሊ ወርቁ ማሞ - ለሰዓሊ
ታደሰ መስፍን፣
·
ተዋናይ ሰሎሞን ቦጋለ - ለወ/ት
ትርሐስ መዝገበ፣
·
ዶክተር ወሮታው በዛብህ -
ለሰላም ባልትና፣
·
አቶ አብዲ ነጋሽ - ለአቶ
ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ፣
·
ደራሲ ሕይወት ተፈራ - ለአቶ
ደሳለኝ ራሕመቶ፣
·
አንጋፋው ጋዜጠኛ አጥናፍ ሰገድ
- ይልማ ለአቶ ያዕቆብ ወልደ ማርያም፣
·
አትሌት ደራርቱ ቱሉ - ለዶክተር
ወልደ መስቀል ኮስትሬ፣
·
ዶክተር በላይ አበጋዝ - ለአቶ
ሽመልስ አዱኛ፣
·
አባት አርበኛ ዳኛቸው ተመስገን
- ለፊታውራሪ ዐመዴ ለማ ሰጥተዋል፡፡
ከሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ቀደም ብሎ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ‹ለሀገር በጎ መሥራት ምንድን
ነው?›› በሚል ርእስ ንግግር አድርገው ነበር፡፡
የሽልማት አመራረጡና ሂደቱን የተመለከተ ሪፖርትም በኮሚቴው ጸሐፊ በአቶ ቀለመ
ወርቅ ሚደቅሳ ቀርቧል፡፡
መርሐ ግብሩን አበባው መላኩና ሐረገ ወይን አሰፋ ሲመሩት፣ ያምራል ሀገሬ ባንድ ሀገራዊ
ዜማዎችን አቅርቧል፡፡ ዝግጅቱ የተሳካ እንዲሆን ዳሽን ቢራ በክብር ስፖንሰርነት፣ ማርክ አድቨርት የግድግዳ ባነሩን ባማረ ሁኔታ
በማዘጋጀት፣ ወንድወሰን ዲጂታል ስቱዲዮ የምስክር ወረቀቶችን በዲጂታል ኅትመት በማዘጋጀት፣ ፍሊትዝ አድቨርታይዚንግ የምስክር ወረቀቶችን
ዲዛይን በመሥራት፣ አቦነሽ ዲዛይን ለዕለቱ የሚሆኑትን ካባዎች በልዩ ሁኔታ በማዘጋጀት፣ አቢሲንያ የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት ሞዴሎችን
ለዚህ አገልግሎት በመመደብ፣ ዐሥራት አስጎብኝ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ ለሥነ ሥርዓቱ መሳካት አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡
አራተኛው የሽልማት ሂደት በኅዳር 2008 የሚጀምር ይሆናል፡፡ ቸር ያሰንብተን፡፡
የበጎ ሰው የ2007 ዓምን መጽሔት እነሆ
እግዛአቢሄር ኢትዮዽያን የባርክ!!
ReplyDeleteእንኳን እግዚአብሔር በሰላም አስጨረሳችሁ!
ReplyDeleteNICELY DONE
ReplyDeleteNICELY DONE
ReplyDeletegemel yehedal wesha yechoal anete serahen sera werenaw em yawera berta egziabher yetbekehe
ReplyDeleteGood Job! I appreciate the institutionalization of the process. Keep up the good work M.T Daniel.
ReplyDeleteWell done
ReplyDeleteWELL DONE ALL THE TEAM, KEEP IT UP
ReplyDeleteIjig wub neber, ketilubet
ReplyDeleteBetam DES yilAL Bezihu yiqetil!
ReplyDeleteNice Job
ReplyDeleteእንዲህ ለሚገባቸው የሚገባቸውን ስንሰጥ ለሎች በጎዎች ን እናፈረራለን እግዚአሔር ለአዘጋዎቹ ረጅም ዕድሜን ይስጥልን
ReplyDeleteለእኛም በጎ የመሆን ዕድልን አምላክ ይስጠን አሜን
WTBMHG
አግዚያብሄር ያበርታህ
ReplyDeleteእጅግ ደስ የሚል የተቀደሰ ተግባር ዳኒ!!!
Deleteሌሎችም ተቋማት ይህንን አበረታች ተግባር እውነትን መሠረት አድረገው ቢሰሩበትና በተሻለ መልኩ ሰፍቶ እና አድጎ ማየት ምኞታቸን ነው!!!
Really it is very fantastic job. GOD blase you & the team...Need to be continue likewise this good job.
ReplyDeleteD/Daniel you are a great person, you always done a good job, GOD be with you forever,you also deserve praise. keep it up.thanks
ReplyDeleteI am so happy to see such better thing, which gives values for what they did.
ReplyDeleteThank you the creator of the idea,we Ethiopian have such a nice peoples that can have an influence on the people mind taxs a lot Danie.
WELL DONE
ReplyDelete