Thursday, August 6, 2015

ዕውቀት ቦታ ሲያጣ

click here for pdf

ታላላቅ የሚባሉ ተቋማት አንድን ነገር ሲሠሩ ያንን የተመለከተ ሞያ ያላቸውን ሰዎች የማማከር ነገር እየቀረ፣ እንዴው በቦታው ላይ በተመደቡ፣ ካገኙበት ቦታ ብቻ ገልብጠው በሚያመጡ አካላት እየተዳደርን መሆኑን ከሚያሳዩን ነገሮች አንዱ የምናትማቸው ካላንደሮቻችን ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር የሺ ዓመታት ጉዞን የተጓዘ፣ ከሀገሪቱ ባሕል፣ እምነት፣ ፖለቲካ፣ ግብርና፣ የአየር ሁኔታና ታሪክ ጋር በብርቱ የተሣሠረ መሆኑን እንኳን እኛ ባለቤቶቹ ሀገሪቱን በተመለከተ የሚያጠኑና የሚጠይቁ ሁሉ ያውቁታል፤ ያደንቁታልም፡፡

ይህ የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት ራሱን የቻለ ሞያ ሆኖ በሀገር ቤት ትምህርት ቤቶች ሲሰጥ የኖረ፣ ለብዙ መቶ ዓመታት የሚያገለግሉ ቀመሮች ተዘጋጅተውለት ማንም ሰው በቀላሉ የዘመኑን ቁጥርና ሁኔታ እንዲያውቀው ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ አሁን አሁን ግን ‹ዋርካዎች ተቆርጠው እምቧጮ ሲበቅል፣ ጋኖቹ ጠፍተው ምንቸቶች ጋን ሲሆኑ› ታላላቆቹ ተቋማት ሳይቀሩ ይህንን ለዘመናት የዘለቀ የዘመን መቁጠሪያ እንደፈለጉ ያደርጉት ጀመር፡፡  

ይህ ዓመት 2007 ዓም ጳጉሜን 6 ቀን ናት፡፡ ስለዚህም አዲሱ ዓመት መስከረም አንድ ቅዳሜ እንጂ ዓርብ አይውልም፡፡ የዘመን መቁጠሪያ መጻሕፍቱ ሁሉ ይህንን ከመቶ ዓመታት በፊት ነግረውናል፡፡ ሌላው ቀርቶ በቅርቡ ልናገኘው የምንችለው የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ‹ባሕረ ሐሳብ› የተሰኘው መጽሐፍም ይህንኑ ይነግረናል፡፡ ሞያን በባለሞያው ያለ መሥራት፣ በዕውቀት ያለመመራት፣ ዕቅድን ከትክክለኛ ሥራ ይልቅ በክንዋኔ ሪፖርት የመገምገም ልማድ በሀገሪቱ ሥር አየሰደደ ስለመጣ ዓይናችን እያየ ኢትዮጵያን በሚያህል ሀገር አዲስ ዓመት መቼ እንደሚገባ ልንከራከር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፓርላማ ባሳተመው ‹‹የኢፌዴሪ የሕዝበ ተወካዮች ምክር ቤት ፳፻፯ House of peoples’ Representatives of The FDRE 2014/15›› አጀንዳ የዘንድሮውን 2007 .. ማብቂያ ጳጉሜን 5 ላይ አስቀምጦታል፡፡ ጳጉሜን ዘንድሮም ሠርዟታል፡፡ ዘንድሮ ያልኩት ያለምክንያት አይደለም፡፡ የዛሬ አራት ዓመትም ባሳተመው አጀንዳ ላይ ጳጉሜን ስድስትን ዘልሏት ስለነበር ነው፡፡  

በሕገ መንግሥቱ በዐንቀጽ 51 ቁጥር 20 ላይ ፓርላማው ‹‹አንድ ወጥ የመለኪያ ደረጃዎችና የጊዜ ቀመር ያወጣል›› ይላል፡፡ ይኼንን አውጥቶ ከሆነም የሕግ አወጣጥ ሥርዓትን ጠብቆ በዐዋጅ ማውጣት አለበት እንጂ በሚያሳትመው ካላንደር በኩል ሊነግረን አይችልም፡፡
በተለይም ፓርላማው የሀገሪቱ የሥልጣን የመጨረሻ አካል በመሆኑ የሚጽፋቸው ጽሑፎች፣ የሚናገራቸው ንግግሮች፣ የሚጠቀማቸው ፕሮቶኮሎች፣ የሚከተላቸው ሥርዓቶች፣ የሚያሳትማቸው ኅትመቶች አርአያነት ያላቸውና የሀገሪቱን ደረጃ የሚመጥኑ መሆን አለባቸው፡፡ ፓርላማው ስሕተቱን ከፈጸመ ‹አንደ ንጉሡ ..›› በሚለው ልማድ ሌሎቹም ተከትለውት ስሕተቱ ሀገራዊ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ የፓርላማው የሥራ ዘመን በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ነው ይላል(ዐንቀጽ 58 ቁጥር 2)፡፡ ይኼ ሰኞ ግን እንደ ፓርላማው ካሌንደርና እንደ ትክክለኛው ካሌንደር ይለያያል፡፡ ታድያ የትኛውን ሊከተል ነው፡፡ 

ከፓርላማው ቀጥሎ የገረመኝ ሸገር ሬዲዮ ነው፡፡ ለባሕላዊ ነገሮች ትኩረት በመስጠቱና በሀገርኛ አቀራረቡ የምናውቀው ሸገር እርሱም ጳጉሜን 6ን የዘለለው የሚጠይቀው ባለሞያ አጥቶ ነው ለማለት ይቸግረኛል፡፡ ‹በተለመደው መሠረት ይሠራ› ተብሎ ተመርቶለት ይሆናል እንጂ፡፡ ሌሎቹን ድርጅቶች አላነሣቸውም፡፡ ፓርላማውና ሚዲያው ከተሳሳተ እነርሱ ማንን ይከተሉ፡፡ የሂሳብ ሥራው ከዘመን አቆጣጠር ጋር በሚገባ የተቆራኘው ‹ሁሌም የምንተማመንበት ባንክ› ንግድ ባንክ ባሳተመው ካላንደር ላይ ጳጉሜን 6 ዘልሎ እንዳንተማመንበት ማድረጉ አሳዛኝ ነው፡፡ የዛሬ አራት ዓመትም በተመሳሳይ ይህንኑ ስሕተት ፈጽሞት ነበር፡፡ አሁን የባንኩ ሠራተኞች ቅዳሜ(እንደ ባንኩ መስከረም ሁለት፣ እንደ ካላንደሩ መስከረም አንድ) ሥራ ሲገቡ ልናይ አይደል?

የመስቀልን በዓል ለማክበር የሚመጡ ጎብኝዎችን የሚመዘግቡና ስለ በዓሉ ቀን መረጃ የሚሰጡ አካላት ጳጉሜ አምስት ስትሆንና ስድስት ስትሆን መስቀል በአውሮፓውያን ካላንደር የሚውልበት ቀን ስለሚለያይ በ2008 ዓም በጎብኝዎች ላይ ሊፈጠር የሚችለውን ችግር ካሁኑ መገመት ይቻላል፡፡በዚህ ረገድ የሚመሰገነው ጠንቃቃው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው፡፡

የባሕረ ሐሳብ ሊቁ ሄኖክ ያሬድ ‹‹ጊዜን ቀመርን በአግባቡ መጠቀም መሠረታዊ ነገር መሆኑ አይሳትም፡፡ አራት ነገሮችን የያዘ አንድ ቀዋሚ ጥንታዊ አገላለጽ አለ፡፡ ንግግር ለማድረግ ሐሳብን በጽሑፍ ለማስፈር ሰዋስው (ግራመር) የቋንቋ ሥርዓት አስፈላጊ ነው፡፡ ለአምልኮትም ይሁን ለክብረ በዓል ሙዚቃ ከነሥርዓቱ ያስፈልጋል፡፡ አገር ከነጓዙ ለመምራት ሕግና ቀኖና መሠረታዊው ነገር ነው፡፡ በዓላትና የዘመን መለወጫን በፀሐይም ሆነ በጨረቃ መንገድ ለማወቅ ካለንደር መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ ከእነዚህ አራት ምሰሶዎች በኢትዮጵያችን ክፍተት ያለው የዘመን አቈጣጠር፣ ባሕረ ሐሳብ ላይ ነው፡፡ መንጋደዱ ጳጉሜን 6 የመርሳቱ ነገርን ለማረቅ አራተኛው ምሰሶ ላይ አገሪቱ ትኩረት የምትሰጠውስ መቼ ነው?›› በማለት እንደጠየቀው ባለሞያዎቹ ሳይጠፉ አማክሮ መሥራት የተሳነን ለምንድን ነው?

ዕድገትና ብልጽና እንዲመጡ፣ መጥተውም እንዲዘልቁ ሀገር በዕውቀት መመራት ይገባታል፡፡ የሚሠሩ ሥራዎች በሙሉ በተገቢው ባለሞያ መከወንና በተገቢው የሞያ ደረጃ ሂደት ማለፍ ይገባቸዋል፡፡ ያለበለዚያ ግን እንኳን ወደፊት ከሚመጡት ግኝቶች ጋር ተጣጥመን ማደግ ቀርቶ አብረውን ከኖሩት ጥበቦችም ጋር መግባባት ያቅተናል፡፡

43 comments:

 1. - ኦባማን ለመቀበል በእንግሊዘኛ የተጻው ቢልቦርድስ ከነ ስህተቱ አደል እንዴ የተለጠፈው
  - የኢቢሲን ሰብ ታይትል በየቀኑ አስተውላች እዩት
  - በየግዜው የሚወጡ ጽሑፎችና ፖስተሮችን እዩዋቸው
  - ከመገናኛ ተርናሚል የሚል ታክሲ አለ ተርሚናል ይሆን?
  - ፓርላማው ብቻ ሳይሆን ሁሉም ዘርፍ ስህተትን ስራዬ ብሎ ይዞ ጥንቃቄን ረስቷል

  ReplyDelete
 2. የሃገር ፍቅር የሚንገበግበው፤ በሃይማኖቱ የፀና፤ ለባህሉ ተቆርቋሪ፤ የዘመናችን አቡነ ጴጥሮስ፤ ዲ/ን ዳንዔል ክብረት። እግዚአብሔር ጸጋ እና እድሜህን ያብዛልን።

  ReplyDelete
 3. ድሮስ ሀገራዊ የሆነ ጽኑ መሠረት ከሌለው ከዚህ ሥርዓት ምን ሊጠበቅ! ዉሻ በቀደደው ጅብ ይገባል…….ነገ ይህን ተከትለው ለኢትዮጵያ የማይተኙት……ታሪካችንን በሌላ ፈርጅ ጽፈው ያስነብቡናል….አኛም በሁለት ጽንፍ ተወጥረን እንፋጠጣለን!

  ReplyDelete
 4. ስንት ትልልቅ ስህተት እያለ ይህን እዚህ ግባ የማይባል ተራ ስህህተት ሰማይ አድርሰህ ማውራትህ ሌሎች ያላዩትን ጉዳይ እየሩሳሌም ባሰራህው መነፅር ያየህ ታሰመሰላለክ . . .ይህ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የስህተት ቅርስ ዘግይተህ በማየትህ አሁን አንተ ተገርመህ ሰውን ለማሰገረም መሞከር የለብህም. ከብዙ ሺህ አመታት በፊት ነበረች የሚትሎት ይችህ አገር አገር ሆነ እየኖረች ያለችውና አሁን የያዘችውን ቅርፅ ይዛ የተገኘችው በስህተት ላይ ተመሰርቶ የነበረ የህዝብ አሰተዳደር ስለነበረ ነው. ስለዚህ ስህተት ለአርተም ሆነ ለህዝቦቸ አዲስ ነገር(ብርቅ) አይደለም ይህ ስህተት እያደገ ሌላ አንተ ያለየሄውና ብታየውም በቀላሉ ልትረዳው በማትችለው የስህተት ደረጃ ላይ ደርሶል . . .ስለዚህ ሌላ ውሃ የሚያነሳ ጉዳይ ሰላጣክ ብቻ ፀሀይ የሞቀና በUNSCO እንደ ቅርስ ሊመዘገብ የሚገባ ጉዳይ አንስተክ አንተም አሰልችተህን በሌሎች ስህተት የራስህ ስህተት አታሳየን!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. I don't think this blog is your domain. What have you done for the "many errors" you have noticed?

   Did you at least pointed the errors for the owners to correct it? Start now, take part and be part of change. Don't be the typical . . .

   Delete
  2. ስማ እሱስ ዘግይቶም ቢሆን የታዘበውን እንዲታረም አሳውቋል፡፡ አንተ ግን ቀድመህ አውቀህ ምን አደረክ????? ለሀገርህ መጥፎ በመመኘት በስህተት እንድትታወቅ ታስባለህ፤ መጀመሪያ እራስህን አጥራ

   Delete
  3. እንደ ሐሳብህ ከኾነ ከዚህ በፊት በምድራችን ላይ ብዙ ስሕተቶች ተሠርተዋል በማለት ከስህተታቸው ባለመማር ሌላ ስሕተት በመሥራት ሕዝብን ወደ አልተፈለገ አግጣጫ ለመውሰድ የምትሻ ትመስላለህ፡፡ አልያም የትውልድን አሻራ በማጣመም ለኅትመት በሚወጡ ጽሑፎች ታሪክን ባሕልን ትውፊትን እና እውነትን በስሕተት ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ከሚተጉ ሰዎች አንዱ ሳትኾን አትቀርም፡፡ ለአንተ ስሕትት ብርቅህ አይደለም ወይም ደግሞ ከ አንድ ዓመት ላይ አንድነ ቀን መቀነስ ለአንተ ውኃ የሚያነሳ ስሕተት አይደለም ምክንያቱም ለአንተ ስሕትት ብርቅህ አይደለም ……… ሌላም ሌላም … ጸሐፊው የጠቀሰውን ዐይነት ስሕተት ለማየት የግድ የኢየሩሳሌም መነጽር ያስፈልገዋል ብየም አላምንም ምንም እንኳ የጠቀሰውን ስሕተት ፓርላማው በካሌንደር ላይ ለኅትመት ቢያበቃውም ይተገበራል ብየም አላስብም ኅትመቱ ግነ ኾን ተብሎ ሊደረግ ስለሚችል መጠራጠሩ ግን አይከፋም ፡፡ ምናልባት በየአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ ከምትመጣ ባለ ስድስት ቀን ጳጉሜን አንዱን ቀን መቀነስ እድሜ ያረዝም ይኾንን? … የሚያሳዝነው ግን የተለያዩ ስሕተቶች መፈጠራቸው ሳይኾን በዓለም ትልልቅ ቦታ ተቀባይነት አላቸው ያልናቸው የዓሳዎቻችን አናት መግማቱ ነው፡፡ በተረፈ ግን ወንድማችን ዳኒ የከተበልን ጦማር ወደፊት እንደ አንተ ዐይነቱ ሰሕተት ጠንሳሽ ለሚፈጥሩት ትንሽ መስለው ኋላ ለሚገዝፉት ስሕተቶች ለማስተዋያ መነሻ ሊኾን ይችላል

   Delete
  4. ምንድነዉ ወንድሜ? ካሌንደሩን ከነ ስህተቱ ያሳተምከዉ አንተ ነህ እንዴ?

   Delete
  5. Stay on topic

   Delete
  6. Zim Bel... yefugnit Lij... kalebotah Atgegn!!!

   Delete
  7. ውድ ወንድሜ ለአንተ ስህተት ምን ማለት እንደሆነ የጠፋህ ይመስለኛል ፡ ወይም ይኸንን ካዘጋጁት አንዱ ሳትሆን አትቀርም ፡፡ ለማንኛውም አንተነትህን በጣም ያሳንስሀል የሰጠኸው አስተያዬት በዚህ ከቀጠልክ በጣም ትንሽ ትሆናለህ፡፡ በማይመለከትህ ቦታ አስተያየት ከመስጠት ብትቆጠብ ጥሩ ነው፡፡

   Delete
  8. ስህተት ብርቅህ እንዳልሆነ ከፅሁፍህ ተረዳሁ። ይህ ጦማር የተፃፈው ግን ከነ እድፋችን ተዉን ለምትሉ ወገኖች ሳይሆን ስህተታችንን አርመን ትልቅ እንሁን ለሚሉት ነውና አንተ ውጣበት።ዲያቆን ዳንኤል፤ ያበርታልን ብለናል።

   Delete
  9. አንባቢ ተብዬ ገርመህኛል፡፡ ቆይ እንዴት ነው የምታስበውና የምታነበው ፊደል መደርደር ነው የያዝከው ወይስ አንብቦ ማስተዋል፤ አንዲት ጓደኛዬ ያለችይ ትዝ አለኝ ጠዋት ያደናቀፈህ ድንጋይ ማታ ከደገመህ ድንጋዩ አንተ ነህ፡፡ ያለችው፡፡ መንግስት ከተሳሳተና ስህተቱን ሳያስተውለው ቀርቶ ይሆናል ተብሎ ታለፈ በድጋሚ ተሳሳተ ስህተቱን ፀሐፊው አሳየ፡፡ እንደንተ አይነቱ ድንጋይ ደግሞ ደጋፊ ሲያገኝ ምን ይባላል፡፡ ሀገራችን እንደአንተ አይነቱ ስህተትን እንደአዋቂነት ይዘው የሚኖሩ በዝተውባት ነው ከስህተት ከመማር ይልቅ እየተሳሳተ ስህተትን እንደ እውነት እያየ የሚያልፈው፡፡ አንተ ስህተት ብርቅህ አይደለም መሰለኝ፡፡ ግን የተገለጸውን ስህተት የሚጎዳውን ነገር ማየት ግን አልቻልክም፡፡ አልፈርድም ሀገራችን ጠባብነትን የሚያጎለምሱ ጥበብን የሚያጠፉ ትውልዶችን በማፍራት ላይ ስለሆነች አይገርምም፡፡

   Delete
 5. I appreciate "Daniel Kibret's Views".

  Ewentu D.

  ReplyDelete
 6. ዕድገትና ብልጽና እንዲመጡ፣ መጥተውም እንዲዘልቁ ሀገር በዕውቀት መመራት ይገባታል፡፡ የሚሠሩ ሥራዎች በሙሉ በተገቢው ባለሞያ መከወንና በተገቢው የሞያ ደረጃ ሂደት ማለፍ ይገባቸዋል፡፡ ያለበለዚያ ግን እንኳን ወደፊት ከሚመጡት ግኝቶች ጋር ተጣጥመን ማደግ ቀርቶ አብረውን ከኖሩት ጥበቦችም ጋር መግባባት ያቅተናል፡፡

  ReplyDelete
 7. good bless you danie
  As we all know Eroupian calender has 1 extra day on Feburary 29 every 4 years so when Ethiopian calender will have an extra day in 4 years. is any one tell me what going happend if we scape pagume 6 what will hapened when the other calender has an extra day.

  ReplyDelete
 8. This shows how our institutions are led by people who are either negligent or have disregard to our values and heritages. On the other hand, it's a wake up call for all who care about it. They have to step in and show the right thing to the people.

  ReplyDelete
 9. Hi, Dani thank you so much for you comment, you may not know or didn’t read. This government doesn’t follow the three thousand years Ethiopian calendar. They prepare the one hundred year Ethiopian calendar. All civilization started from 1983
  so they won the election 100%.

  ReplyDelete
 10. አንባቢ ብለህ አስተያየት ለጻፍከው፣፣፣፣ላንተ ስህተቱ ምንም ሊሆን ይችላል ለ፹ ሚሊዮን ኢትዮጲያዊ ግን ችግር አለው፡፡ የታሪክ አተላ ማለት አንተ ነህ፡፡

  ReplyDelete
 11. Why do we worry about some body's mistake ? Let us take care our big burden off from our shoulders and then everything will be alright .

  ReplyDelete
 12. Dn. Yalayehutin silasayehegn amesegnalehu.

  ReplyDelete
 13. ከእነዚህ አራት ምሰሶዎች በኢትዮጵያችን ክፍተት ያለው የዘመን አቈጣጠር፣ ባሕረ ሐሳብ ላይ ነው፡፡ መንጋደዱ ጳጉሜን 6ን የመርሳቱ ነገርን ለማረቅ አራተኛው ምሰሶ ላይ አገሪቱ ትኩረት የምትሰጠውስ መቼ ነው?›› በማለት እንደጠየቀው ባለሞያዎቹ ሳይጠፉ አማክሮ መሥራት የተሳነን ለምንድን ነው?ከእኔ በላይ ፍጨት አፍ ማሞጥሞጥ ነው ብለው ይሆናላ

  ReplyDelete
 14. ይህ "አንባቢ" በሚል የብእር ስም ከAnonymous የተመለሰ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም አንድም ቀን ነገሮችን በሚዛናዊነት ላይ ተመስርቶ ሲያይ ስላላየሁት በጽሁፉ ሳየው ግምቴ ከፍ አለ፡፡

  ReplyDelete
 15. ዳንኤል የባህረ ሐሳብ ሊቁ ሄኖክ ያሬድ ሳይሆን አባትየዉ አለቃ ያሬድ ናቸዉ በ መዚህ ርዕስ መጽሐፍ አሳትመዋል እሱ የአባቱ ደቀመዝሙ ስለሆነ ከእሳቸዉ መጽሐፍ እየጠቃቀሰ በቴሌቪጅን ሲያስረዳ እኔም አይቼዋለሁ የአባት መልካም እሴቶች የሚወርሱ ብዙ ስልሆኑ አመሰግነዋለሁ

  ReplyDelete
 16. የኢትዮጵያ አዲስ አመት ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ከ 10-1 ቆጥረው ርችት የለኮሱ ቀን እኮ በቃኝ!!! ያልተማረ ልምራ ካለ ውጤቱ ከዚህም ይከፋል::መጽሐፋችንስ እውርን እውር ቢመራው አይደል ያለው:: ተጠያቂዋማ ነበረች!!!

  ReplyDelete
 17. It is my apology for writing in English. that is due the problem on software which I am going to fix next week, but I couldn't wait so long to reflect on your article!

  thanks Dani for this. the mistake is not only with the parliament. Many other institutions and especially private companies are doing the same. and , it becomes a norm. No one is paying attention to this. If you see banners, flyers, booklets, books, announcements on the notice boards, year books, sign boards...etc, you will find many other mistakes and careless handling. What I am thinking is that this is a result of general carelessness and laziness in the country. Lack of knowledge is not crime. But, we need to ask to fill the gap. If we are not ready to ask then we will be met by our pride of emptiness! It is true. Why managers and officials in charge of institutions ask professionals when they decide to public? Had the official at the Parliament who is in charge of such publications asked for editors/professional input s/he would have easily avoided such a silly but with huge implications mistakes. Dani I agree wityh your suggestions and thanks!

  ReplyDelete
 18. እባካችሁ አንባቢያን አእምሮ ይኑረን ዳንኤል ስሕተት የሆነውን ነገር ከማስረጃ ጋር ነው ያቀረበው ባያቀርብ ኖሮ ከየት አመጣህ የት አገኘህ እንለው ነበር ጥያቄውን ከነመልሱ ካስቀመጠልን አሁን የሚታየው ንትርክ የበለጠ ስሕተት ነውና ይታሰብበት
  ዳኒ ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ (እስከ ድግሙ ነኝ)

  ReplyDelete
 19. D/n Kal hiwot yasmalin erjim edime ktena gar yistilen.

  ReplyDelete
 20. ባለሞያዎቹ ሳይጠፉ አማክሮ መሥራት የተሳነን ለምንድን ነው?
  because you are asking for urgent reports for urgent programs. You don't have time to consult others (even if you want to ).

  ReplyDelete
 21. ተቃውሞው ምንድን ነው እንተራራም ነው እኮ ያለው መልካም የሆኑትን እየተቀበልክ ቀጥልበት ዳኒ.

  ReplyDelete
 22. ዳኒ በሀገራችን ዕውቀት ቦታ እያጣ ከመጣ የሰነባበተ ይመስለኛል ….. እንደውም ከርሟል፡፡ ቆሽትን እንዲያበግን ኾን ተብለው ቦታ የተነፈጋቸው ሀገራዊ ዕውቀቶች የዘርዘሩ ቢባል ፈርጁ ብዙ ነው፡፡ ግን ለምን??? ከማንም የተሻለ ነገር እያለን ስለምን የራሳችንን እንተዋለን? የራስ የኾነን ነገር መተውስ ጥቅሙ ምን ይኾን ? በዓለም ከምንታወቅባቸው አያሌ ነገሮች አንዱ የራሳችን ዘመን አቆጣጠር መኾኑ በደንብ ይታወቃል፡፡ ባህላዊ፤ ሃይማኖታዊ፤ ታሪካዊ እና ሳይንሳዊ ቅቡልነት ያለው ሺኽ ዘመናትን ያስቆጠረ የዘመን አቆጣጠር በፓርላማዊ የሕይወት ጉዞ ጨቅላ ዕድሜ ያለው (ዕድሜው ከዘመን አቆጣጠር ዕድሜ ጋር የተነጻጸረ ነው) የሀገራችን ፓርላማ እንዴት ያለምንም ምክንያትና ምርምር በዓመታዊ የቀን መቁጠሪያ ካሌንደር ላይ ዘመኑን ጠብቃ የምትመጣ ስድስተኛዋን የጳግሜን ቀን መቀነስ ተቻለው? ስሕተት ከኾነ ስሕተታቸውን ይቅር እንበላቸው ግን ስንት ጊዜ? ላለፈውስ ስሕተት ይቅርታ ጠይቀው ይኾንን? እንዲህ ዐይነቱ ስሕተት ወዲያው መፍትሔ ካላገኘ ነገ ደግሞ የባሰ ስሕተት መሠራቱ አሌ የማይባል ሐቅ ነው፡፡ ዳኒ ለዚህ ስሕተት ዐይነተኛ ምልከታ በማንሳትህ ምስጋና ይገባሀል፡፡ ምልከታውም መነሣት ይኖርበታል አለበለዚያ ‹‹ … ጠዋት የመታህ ድንጋይ ማታ ቢመታህ ድንጋዩ ሳይኾን ድንጋይ ድንጋዩ አንተ ነህ … ›› የሚለውን በሂል ልብ ይሏል፡፡
  የሀገራችንን ዕውቀት የራሳችንን ማንነት ኹላችን በኅብረት እንጠብቀው ዘንድ የገባል፡፡ ዕውቀት በተሳሳተ መንገድም ወደ አእምሮአችን መግባት ያለበት አይመስለኝም መግባትም የለበትም ፡፡ ሊጠየቁ የሚገባቸውን አካላት (ምሁራንን) በተለይም አንድን ዕውቀት ለዘመናት ጠብቆ ለትውልድ እንዲደርስ ከፍተኛ ኀላፊነት የተሸከመ አካልን መጠየቅ ከስሕተት ያድናል ፡፡ በተለይ በተለይ ደግሞ የመገናኛ ብዙኃን ለሕዝብ ቅርብ ስለኾኑ በጽሑፍም ኾነ በቃል ለሚያስተላልፉት ጦማር ቢጠነቀቁ መልካም ነው ምክንያቱም አሉታዊም ኾነ አዎንታዊ ተጽዕኖ በሕዝብ ላይ ለማሳደር እጅግ የቀረቡ ናቸውና፡፡ ለሀገራችን ኢትዮጵያም የሚበጃት ወደራሷ ሀገራዊ ዕውቀት መመልከቷ ይመስለኛል (እዚህ ላይ ግን የሌሎች ሀገሮች ጥበብ እና ተሞክሮ መመልከት የለብንም የሚል አስተያየት የለኝም ግን በአግባቡ ይኹን ማለቴ ነው፡፡ የሌሎች ሀገራትን ዕውቀት ስንመለከት ሀገራቱ ለራሳቸው ዕውቀት የሰጡትን ቦታ እግረ መንገዳችንን ብናስተውል መልካም ነው፡፡) ለምሳሌ ያኽል የሀገራችንን የመድኃኒት ቅመማ ሥርዐት በዘመናዊ መልኩ ብናቀናጀው በዕፀዋት ላይ የተደረገውን ጥንታዊ ምርምር በየብራናው የተከተቡትን ጥበብ ብንመለከት በተግባርም ብናውለው ዛሬ በዓለም ላይ በሕክምናው ዘርፍ በሚደረገው ውድድር በየ ሰዉ ሀገር ሕክምናን ፍለጋ ስንማስን አንኖርም …….. በሕንፃ ሥራውም ዘርፍ ብንቃኝ ዛሬ የምንኮፈስበት ግን ያላስተዋልነው ቦታም ያልሰጠነው የጥንቶቹ ኪነ ሕንፃ ጥበብ ምዕታት ዓመትን አልፎ ዛሬ ድረስ እንዴት እንደቆየ ብንመረምር የራሳችንን ዕውቀት ቦታ ብንሰጠው ዛሬ የምንሰራቸው የምናስገነባቸው ግንባታዎች ለአገልግሎት እንዲውሉ በተመረቁ ማግስት ከመናድ ይተርፉ ነበር፡፡ (ይህን እውነታ በየገጠሩ የሚሠሩ መንገዶችና ድልድዮች እንዲሁም በግንባታ ጥበብ ዐዋቂ እጥረት ምች የመታት ዋና ከተማችን ያለችበት ኹኔታ እማኝ ምስክር መኾን ይችላሉ፡፡)
  አሁን ያለውን ትምህርት አስተምህሮቱንም ኾነ ሂደቱን ብንመለከት ሕፃናት በሀገራቸው ቋንቋ ቢናገሩ የአሉታዊ ተጽእኖ ውርጅብኝ ከሚወርድባቸው ግቢ (መዋዕለ ሕፃናት) አንስቶ በጎሳ ተከፋፍለው እስከሚወጡበት ዩኒቨርሲቲ ያለውን የዕውቀት ሽግግር ብናይ ቦታ የተሠጠው የሀገራቸው ዕውቀት ለማግኘት መጣር በመርፌ ቀዳዳ ግመል እንደማሾለክ ነው ፡፡ (በዚህ ኹሉ ፈተኝ ኹኔታዎች ውስጥ ታግለው ይህ የሀገሬ ዕውቀት ነው ብለው ቦታ የሰጡትን ወንድምና እኅቶች ሳላመሰግን አላልፍም) በነገራችን ላይ ትምህርት ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ዐይነተኛ ድልድይ እንደመኾኑ መጠን በእጅጉ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል፡፡ ጣልያን ሀገራችን በወረረበት ወቅት የሠራው መንገድ እና ድልድይ እንዳልተመሰገነበት ልብ ይሏል እስከዛሬም ድረስ ጠላት የሰራው መንገድ እየተባለ በሕዝብ ዘንድ ይጠራል ፡፡ ታዲያ ዛሬም የምንሠራቸው ስራዎች የምንሳሳታቸው ስሕተቶች ነገ በጠላትነት እንደማያስፈርጁን በምን እናወቃለን? ጣልያንስ ወራሪ ስለነበር ጠላት የተባለው፡ የአንዲት ሀገር ተወላጅ ኾኖ ለተወለደባት ሀገር በጠላትነት መፈረጅ ግን ምንኛ ሕመም ይኾን? ትናንት የነበሩን ዛሬ ቦታ የነፈግናቸው የእኛ የኾኑ ዕውቀቶቻችን ለነገ ዋጋ ያስከፍሉናል፡፡ ለዛውም መክፈል የማንችለው ዋጋ፡፡ ሌላም ብዙ ስሕተቶች እና ተሳሳቾች መጥስ ይቻላል በተለይ ከሕዝብ ወጥተው ሕዝብን የሚያገለግሉ በአገልግሎታቸው መሰላል ከመሰላሉ ጫፍ ላይ ኾነው አንድ መንገድ ብቻ ላላቸው የኪነ ጥበብ ሰዎች ለሕዝቡ በሥነ ጽሑፍ፤ በዜማ፤ በሥነ ሥዕል ……. በመሳሰሉት የሚያስተላልፉት መልእክት በደንብ ከዐዋቂ ቢመክሩ መልካም ይመስለኛል ፡፡
  እጅግ በጣም ትኩረት ማድረግ የሚገባቸው ትውልድን በመቅረጽ የኀላፊነት ጫንቃ የተጣለባቸው የግልና የመንግሥት ተቋማት በሚሠሩት ሥራ ራሳቸውን ከስሕተት ቢጠብቁ ለሀገራችን ዕውቀት ቦታን ቢሰጡ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ድልድይን ይገነባሉ ‹‹..ሰማቸውንም በዚህች ሀገር በትልቅ ብዕር ይጽፋሉ …..›› ያ ካልኾነ ግን ውጤቱ የግርንቢጦሽ ኾኖ ለወገን ከአልጋነታቸው ይልቅ ቀጋነታቸው ሲታወስ ይኖራል ፡፡
  ዳኒ ለአብነት ያኽል የነሳኸው ስሕተት ሌላ ሌላ ብዙ ስሕተቶችን እንድናይ ይረዳል ኅሊና ላለው ከስሕተቱ እንዲታረም ያመላክታል ብሌ ዐስባለኍ፡፡ እውነት ወድቃ ምሣር በበዛባት በዚህ ዘመን እውነትን ይዞ መታገሉ የፈተናውን ትግል ያራዝመዋል፡፡ እውነት ግን ምንም ጊዜ ቢኾን ታሸንፋለች ፡፡ ዳኒ ትበረታ ዘንድ እግዚአብሔር ከአንተ ይኹን ፡፡ የሚያስተውሉትን እውነት ከፊታቸው አቁመው እውነትነቱን እያወቁ እያስተዋሉትም እውነት ምንድን ነው ብለው ከሚጠይቁ ጠቢባን አምላከ ቅዱሳን ይጠብቅህ፡፡ ዐውቆ የተኛን ይቀሰቀስ ዘንድ እንዴት ይቻላል???????

  ReplyDelete
 23. አንተ ባዳ የባዳ ልጂ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኖራለች ከባህሏዋ ከወጓ ከክብሯ ጋር አተ ትጠፋለህ።የባዳ ቅጥረኛ እናቴ አትጠፋም ።

  ReplyDelete
 24. ቃለ ህይወተት ያሰማልን፡፡ የአገልግሎት ጊዜህን ድንግል ማርያም ትባርክ!

  ReplyDelete
 25. ዳኒን ያየውን ስህተት እዲያርም የሚያደርገው የልጂነት ግዴታ ስላለበት ነው ።አንተ ግን ባዳ ከሀዲ አገር ፣ታሪክ ፣ባህል የምታዛባ ድልድይ አፍራሽ ባዳ የባዳልጂ መሆንህን እዲህ ባደባባይ እራስህን አጋለጥህ ።ኢትዮጵያን እንኳን ሊያጠፋት የሚሞክሩትን የሚያስቦትን በራሳቸው ሀሳብ እየተጋጩ ይጠፋሉ ከጠፊዎችም አድ አንተ ነህ ።እምዬ እናት ሀገር በባህሏ በወጓ እዳለች በማንነቷ ተከብራ ለዘለአለም ትኖራለች ።

  ReplyDelete
 26. በውስጣችን ያስቀመጥነው የጥላቻ መንፈስ ከሌለ በስተቀር ከአንድ አመት ላይ አንድ ቀን መቀነስ ትነሽ ስተት ሊባል አይችልም፡፡ ከቅርብ ያልመለሰ እርኛ ሲሮጥ ይውላል አንደሚባለው የዳንኤል እይታ አግባብ ነው፡፡

  ReplyDelete
 27. ስህተት ሆኖ በበቂ ማስረጃ ተረገጋግጠጦ ቀርቦ ለምን አንማርበትም ክርክር ለምን አስፈለገ

  ReplyDelete
 28. ዳኒ ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 29. ዲ.ዳንኤል እናመሰግናለን፤ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡

  ReplyDelete
 30. ዳኒ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ጠዋት ያደናቀፈህ ድንጋይ ማታ ከደገመህ ድንጋዩ አንተ ነህ በቃ ብዙ ድንጋይ ሀገራችን እያፈራች ነው፡፡

  ReplyDelete
 31. I hope you are not my generation! አስፈሪ: አሳፋሪ: ለቅጠል ብቻ የሚኖር!

  ReplyDelete