Tuesday, July 21, 2015

እህልና አረምየሀገሬ ገበሬ ዘር ያስቀምጣል፡፡ መርጦና መጥኖ፡፡ ሁሉም እህል ዘር አይሆንምና፡፡ በተቻለ መጠን ወፍ ያልቆረጠመው፣ ነቀዝ ያልቀመሰው፣ ሌላ ነገር ያልተቀላቀለበት፣ ያልተሸረፈና ያልተቦረቦረ፣ ሲያዩት የሚያምር፣ ሲበሉት የማያቅር ተመርጦ በልዩ ሁኔታ በልዩ ቦታ ይቀመጣል፡፡ አቀማመጡም የራሱ ሞያ አለው፡፡ ሞያውን ችሎ የሚያስቀምጠው ገበሬ ዘንድ ‹እገሌ ዘንድ ዘር አይጠፋም› እየተባለ አገር ይጠይቀዋል፤ ለሀገርም ዘር ያተርፋል፡፡
 
በዚህ ሁኔታ ጠብቆ ያኖረውን ዘር ሲዘራው ግን እንደ ገበሬው ቋንቋ የሚበቅለው ‹እህልና አረም ነው፡፡›› ፈልጎ ከዘራው እህል ጋር የማይፈልገው አረም አብሮ ይበቅልበታል፡፡ መጽሐፉስ ‹ዘሩ በበቀለ ጊዜ አረሙ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ› አይደል የሚለው፡፡ ገበሬው አረሙን ሁለት ጊዜ ነው የሚታገለው፡፡ መጀመሪያ እንዳይበቅል በመከላከል፡፡ ዘሩን የሚመርጠው፣ አበጥሮና አንጠርጥሮ፣ ለቅሞና ሸክፎ የሚይዘው ለዚህ ነው፡፡ ዘሩ የሚወድቅበትን መሬትም አስቀድሞ መንጥሮና አስተካክሎ፣ ጎልጉሎና ለቅሞ ያጸዳዋል፡፡ አረም እንዳይኖረው ሲል፡፡ ይህንን አልፎ ከዘሩ ጋር አብሮ አረሙ ሲበቅል ግን ቢችል ‹ሆ› ብሎ በደቦ ባይችል እርሱና ቤተሰቡ ወጥተው አረሙን ያርሙታል፡፡ ‹ለአረም ቦታ መስጠት ደግም አይደል›› ይላል ገበሬው፡፡ ቦታ ላለመስጠትም ከሥር ከሥሩ ያርማል፣ ሥር ከሰደደ ዋናውን እህል እስከመዋጥና እስከ ማጥፋት ይደርሳልና፡፡ ማሳውም የስንዴ፣ የጤፍ፣ የገብስ መባሉ ቀርቶ ‹የአረም እርሻ ይሆናል፡፡ 


በኢትዮጵያችን የታሪክ ግንዛቤ ብንከተለው የሚበጀን ይኼ የገበሬው መንገድ ይመስለኛል፡፡ መቼም ማንም ገበሬ ሆን ብሎ አረም አይዘራም፡፡ ከአረም የሚያገኘው ጥቅም የለምና፡፡ ትርፉ ድካምና ኪሳራ ስለሆነ፡፡ ነገር ግን ሳይወደው አረሙ ከእህሉ ጋር ይበቅላል፡፡ በታሪካችንም ማንም ሕዝብ ጦርነት፣ እልቂት፣ በደል፣ ግፍና መከራን ይሁነኝ ብሎ ወይም ፈልጎ የዘራ አይኖርም፡፡ እምነቶቻችን እነዚህን እንድንጠላና እንድንጸየፍ የሚያስተምሩ ናቸው፡፡ ብዙዎቹ ተረቶቻችንን ብናይ እነዚህን የሚኮንኑና የሚያወግዙ ናቸው፡፡ በአብዛኛው ባሕላዊ ዘፈኖቻችን ግፍን፣ መከራን፣ መገዳደልን፣ መተላለቅንና ጭቆናንን የሚያማርሩ ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ነገሮች ሳንወድ አብረውን በቅለዋል፡፡ ድልን፣ ስምን፣ ሥልጣኔን፣ ግዛት ማስፋፋትን፣ ሀብትን፣ ክብርን፣ ጀግንነትን፣ ሥልጣንን እንዘራለን ስንል ወይ ሳናውቀው አብረን ዘርተናቸዋል፣ ያለበለዚያም ሳንዘራቸው መሬቱ ተመችቷቸው በቅለዋል፡፡ ዘሩ ሲታይ አረሙም እንደዚያው አብሮ ታይቷል፡፡
 
ከአኩሪው ታሪካችን ጎን አሳፋሪው፣ ከአንድነት ታሪካችን ጎን የመለያየት፣ ከመዋደድ ታሪካችን ጎን የጠብና ጥላቻ፣ ከሥልጣኔ ታሪካችን ጎን የኋላ ቀርነት፣ ከድል ታሪካችን ጎን የሽንፈት፣ ከክብር ታሪካችን ጎን የውርደት ታሪኮች አብረውን በቅለዋል፡፡ አንፈልጋቸውም፤ ሆን ብለንም አልዘራናቸውም፤ ነገር ግን በቅለዋል፡፡ ታድያ ምን እናድርጋቸው? ነው ጥያቄው፡፡
 
እንደ ገበሬው ዕድል እንንፈጋቸው፡፡ ገበሬው ለአረም ዕድል አይሰጠውም፡፡ በአረሙና በእህሉ መካከል የሚፈጥረው ልዩነትም ይኼው ነው፡፡ እህሉ እንዲያድግ ይከባከበዋል፡፤ አረሙን ግን እንዳያድግ ዕድል ይነፍገዋል፡፡ አረሙ ይበቅላል፣ ብቅ ይላል፣ ከፍም ይል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እንዳያድግ፣ አድጎም እንዳያፈራ፣ አፍርቶም ዘር እንዳይተካ ዕድል ይነፍገዋል፡፡ እኛም እንደ አረም ለበቀሉብን የጥላቻ፣ የመገዳደል፣ የመጨቋቆን፣ የመለያየት፣ የመከፋፈል፣ ታሪኮች እንዳያድጉ ዕድሉን እንንፈጋቸው፡፡ ፍግና ማዳበሪያ አናድርግላቸው፡፡ መሬቱን አናመቻችላቸው፤ ዝናቡን እንዲጠቀሙ አንፍቀድላቸው፤ እነርሱ ሳይፈለጉ የበቀሉ አረሞቻችን ናቸው፡፡ ብንችል በደቦ ‹ሆ› ብለን ወጥተን እናርማቸው፡፡ ካልተቻለም በቤተሰብና በግል ለአረሞች ዕድል እንንፈጋቸው፡፡
 
ዘወትር ስለ እነርሱ እየተናገርን፣ ፊልምና ዶክመንተሪ እየሠራን፣ ሐውልት እያነጽና በዓል እያከበርን፤ ልጆቻችን አጥብቀው እርሱን ብቻ እንዲያውቁ እያደረግን፤ የንግግሮቻችን መክፈቻ የማንነታችን መመሥረቻ እያደረግን፤ ለአረሞቹ ዕድል አንስጣቸው፡፡ አዎ በቅለው ነበር፤ አዎ ዘሩ ሲታይ አብረው ታይተዋል፤ አዎ የታሪካችን አካል ናቸው፡፡ ነገር ግን የሚታረሙ እንጂ የሚበቅሉ አይደሉም፡፡ ሥር እንዳይሰዱ ዕድል የሚነፈጉ እንጂ አምመው ጠምጥመው እንዲወጡ ዕድል የሚሰጣቸው አይደሉም፡፡
ይልቅ ለእህሉ ዕድል እንስጠው፡፡ ካልሆነ የታሪክ እርሻችን ‹የአረም እርሻ› ይሆናል፡፡ አረምና እህል አብረን እያበቀልን ብዙ አንዘልቅም፡፡ ያለ ጥርጥር አረሙ እህሉን ይውጠዋል፡፡ መዋጥ ብቻም አይደለም ያጠፋዋል፡፡ ከዚያም እህል እንዳልተዘራበት ሁሉ የአረም እርሻ ያደርገዋል፡፡ ያኔ ማሳው ለከብት እንጂ ለሰው አይሆንም፡፡ ኢትዮጵያችን ለዜጎቿ እንድትሆን ከፈለግን ከአረሙ ይልቅ ለእህሉ ዕድል እንስጠው፡፡ አረሙን ዕድል እንንፈገው፡፡  
 
በጎ ነገር እንዳልነበረን፣ አብረን ዘምተን አብረን ድል እንዳላደረግን፣ እንዳልተዋለድንና እንዳልተጋባን፣ የሰሜኑ ደቡብ፣ የደቡቡም ሰሜን እንዳልሄድን፤ የምዕራቡ ምሥራቅ፣ የምሥራቁም ምዕራብ እንዳልተሰደድን፤ ባሕልና እምነት፣ ከብትና መሬት እንዳልተዋረስን፤ አብረን ተነሥተን አብረን እንዳልወደቅን፤ አብረን እንዳልሞትንና አብረን እንዳልተቀበርን፤ ሌላው ቀርቶ ከጦርነቶቻችንና ከወረራዎቻችን እንኳን ውሕደትንና ቅይጥነትን እንዳላተረፍን ሁሉ ክፉ ክፏችንን ብቻ እየተረክን፣ ጥላቻውን ብቻ ነቅሰን እያወጣን፣ ግፍና መከራውን ብቻ ከፍ አድርገን እየተናገርን፣ አረሙን ሆን ብለን በማሳደግ ላይ ነን፡፡ 
 
ምናለ ከገበሬው ብንማር፤ ለአረሙ ዕድል ባንሰጠው፡፡ አረም አረምን ይወልዳል፡፡ የትናንቱን አረም ዕድል እየሰጠነው ሥር ሰድዶ እንዲበቅልና ከፍ ብሎ እንዲታይ ባደረግነው ቁጥር ለተተኪውም ትውልድ አርሞ የማይጨርሰው ሌላ ገንጋና አረም እንዘራለታለን፡፡ ገበሬውኮ ለአረሙ ዕድል የሚነፍገው ወድዶ አይደለም፡፡ አረሙ እንደሆነ ገበሬው ሠራም አልሠራም፣ አረሰም አላረሰም፣ ዘራም አልዘራም ይበቅላል፡፡ ብቻ መሬት ያግኝ፡፡ የታረሰ ካገኘማ እሰየው፡፡ ግን ምንም ጥቅም የለውም፡፡ ጥቅም ለሌለው ነገር ለምን ይደክማል? የገበሬው ገበሬነት የሚለካውኮ ባጠፋው አረምና ባመረተው ምርት ልክ ነው፡፡ 
 
የአንዲት ሀገር ሥልጣኔ፣ ታላቅነትና ዕድገት የሚለካው በአረሟ ብዛት አይደለም፡፡ በምርቷ ብዛትና ጥራት እንጂ፡፡ አረሙን እያረመች፣ እህሉን እያበዛች ስትሄድ ብቻ ነው፡፡ ሀገር አደገች ተመነደገች የምትባለው፡፡ ፈረንሳይና ጀርመን እርስ በርስ ተዋግተዋል፣ ተጋድለዋል፣ ተጠፋፍተዋል፤ ያ ግን አረም ነው ብለው አረሙት እንጂ ይበልጥ እንዲያድግ ዕድል አልሰጡትም፡፡ ከጦርነቱና መተላለቁ አረም ይልቅ ለአንድነቱና ኅብረቱ እህል ዕድል ሰጡትና የአውሮፓ ኅብረት ዋና መሥራቾች ሆኑ፡፡ የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች ጎራ ፈጥረው እርስ በርስ ተዋግተዋል፣ ተጋድለዋል፣ ተጫርሰዋል፡፡ ያ አረማቸው ነው፡፡ አረሙን ግን ዕድል አልሰጡትም፡፡ አረሙን ትተው  ለእህሉ ዕድል እየሰጡ ይበልጥ አንድ፣ ይበልጥም ታላቅ ሆኑ፡፡ 
 
በአረም ማደግ እንደማይቻል ሶማልያና ኮንጎ እያስተማሩን ነው፡፡ እንግሊዝና ስኮትላንድ እየመከሩን ነው፡፡ ብልህ ከጎረቤቱ፣ ብልጥ ከስሕተቱ ይማራል እንዲሉ ብንችል ከጎረቤት ካልቻልንም አረም በራሳችን ላይ ካመጣው መዓት ብንማር መልካም ነበረ፡፡
አሁን እንኳን እንደገበሬው ምርጡን ዘር ለመዝራት እየሞከርን አይደለንም፡፡ በትምህርት ቤቶቻችን፣ በሚዲያዎቻችን፣ በሰብሰባዎቻችን፣ በንግግሮቻችን፣ በበዓሎቻችን፣ ስለየብሔረሰቡ በምንጽፈውም ታሪክና መግለጫ እየተጠነቀቅን አይደለንም፡፡ የተበላሸ ዘር እየዘራን ነው፡፡ እንደገበሬው አልተጠነቀቅንም፡፡ ዘሩን አልመረጥነውም፣ ክፉውን አልለቀምነውም፣ አረሙ እንዳይቀላቀል አላበጠርነውም፡፡ አረሙ ከዘሩ ጋር እየተዘራ፣ አረሙም ከዘሩ በላይ እየበቀለ፣ አረሙም እህሉን እየዋጠው ነው፡፡ እንደ ሀገር መቀጠል፣ እንደ ሀገር መቆም፣ እንደ ሀገር ማደግ፣ እንደ ሀገርም መሠልጠን ከፈለግን ለአረሙ ዕድል ልንነፍገው ይገባናል፡፡ ከአጥሩ ይልቅ ለድልድዩ፣ ከመለያያው ይልቅ ለመግባቢያው፣ ከመፋቻው ይልቅ ለመጋቢያው፣ ከርቀቱ ይልቅ ለግንኙነቱ ዕድል ልንሰጠው ይገባናል፡፡ 
 
አንዳንዱ ነገራችን እንዲያውም ከአረሙ ይልቅ ለእህሉ ዕድል የሚነፍግ ነው፡፡ ትውልዱ በሀገሪቱ ውስጥ አረም ብቻ ሲዘራ እንደኖረ አድርጎ እንዲያስብ የሚያደርግ ነው፡፡ ያ ደግሞ አገርን ‹‹የአረም እርሻ›› ያደርጋታል፡፡ በአረም ያደገና የሠለጠነ ሀገር ስለሌለ እስኪ እኛ እንሞክረውና ሪከርድ እንስበር ዓይነት ነው ጉዟችን፡፡  
አንዳንዴ ለአረም ዕውቅና መንፈግና ለአረም ዕድል መንፈግ የተምታታብን ይመስላል፡፡ አረም ነበረ፣ ይታወቃል፡፡ ሊካድም አይችልም፡፡ ታሪካችንም ምስክር ነው፡፡ ለአረሙ ዕውቅና መስጠት ማለት ለአረሙ የማደግ ዕድል መስጠት ማለት አይደለም፡፡ ‹አረም ነበረብን፣ ልናርመው ይገባል› ብሎ መወሰን ማለት እንጂ፡፡ አረሙን ማወቅ የሚጠቅመው አረሙን ለማጥፋት ዕድል ስለሚሰጥ ነው፡፡ ያላወቁትን ማጥፋት ስለማይቻል፡፡ በሌላም በኩል አረሙን ማወቅ የሚጠቅመን ‹አረሙን እንነቅላለን ስንል እህሉን አብረን እንዳንነቅለው› ሲባልም ነው፡፡ አረማችንን ዕንወቀው፤ ዐውቀንም እናርመው፡፡ ‹‹ዐውቀን እንታረም› ይሉ ነበር የቀድሞ ሊቃውንት፡፡ ለልጆቻችን ስለ አረሙ ስንነግራቸው ተጨማሪ አረም እንዲዘሩ፣ ወይም የበቀለውንም አረም ይበልጥ እንዲከባከቡና እንዲያሳድጉ አድርገን መሆን የለበትም፡፡ አረሙን ዐውቀው እንዲያርሙት፣ ሌላ አረም እንዳይበቅልም ዕድል እንዲነፍጉት መሆን አለበት እንጂ፡፡

46 comments:

 1. አንዳንዱ ነገራችን እንዲያውም ከአረሙ ይልቅ ለእህሉ ዕድል የሚነፍግ ነው፡፡ ትውልዱ በሀገሪቱ ውስጥ አረም ብቻ ሲዘራ እንደኖረ አድርጎ እንዲያስብ የሚያደርግ ነው፡፡ ያ ደግሞ አገርን ‹‹የአረም እርሻ›› ያደርጋታል፡፡ በአረም ያደገና የሠለጠነ ሀገር ስለሌለ እስኪ እኛ እንሞክረውና ሪከርድ እንስበር ዓይነት ነው ጉዟችን፡፡ ስለዚህ ለልጆቻችን ስለ አረሙ ስንነግራቸው ተጨማሪ አረም እንዲዘሩ፣ ወይም የበቀለውንም አረም ይበልጥ እንዲከባከቡና እንዲያሳድጉ አድርገን መሆን የለበትም፡፡ አረሙን ዐውቀው እንዲያርሙት፣ ሌላ አረም እንዳይበቅልም ዕድል እንዲነፍጉት መሆን አለበት እንጂ፡፡ እንደዚህ እያለ የሚኮተኩት ቤተሠብ ፣ ህብረተሰብ ከሌለ ዝም ብለን የዘመኑ ብንኮንን ምንምለውጥ አይመጣ ለሁውም ጌታ ይድረስ ያንተ ፅሁፍ ጥሩ ንባብ ነው የቱ ተመርጦ የቱ እንደሚተው አይታወቅም ጌታ ይባርክህ

  ReplyDelete
 2. Thank you Dani, I love your article. We are so confused about seed and weed. I read and discus with my family about some Ethiopian history book. All of them they have different message so we are confused which one is correct or incorrect. When I grow up ,and now our radio and TV tell as different history with the same topic. In addition that I work different Ethiopian region so each region have different knowledge about Ethiopia. I believe some Ethiopian have best seed but they don’t have space to spread to us. All radio station, TV station newspaper and hall captured by weed spreader. Two weeks ago Ethiopia government announced to open war with Eretria because the Ethiopian government doesn’t want change the weed with best seed. As you know that Gnbot 7 and Arbegnoch gnbar started war to change the weed but the current governments want war to protect the weed. They have planned to spend more than 20 billion birr instead of correcting themselves. What is the benefit of war? God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 3. When I write the comment its asked me to select all the food. could you change it please it is so confussing.

  ReplyDelete
 4. ዲያቆን ዳኒ , ቃለ ህይወት ያሰማልን !ለእኛም መሥማትና መማር በቻ አይሁንብን . ድንቅ የሆነ መልዕክት ነው ያሰተላለፎክልን .በሥራ ላይ ማዋል ነው የጉደለን እነግዲ ሁላችንም የሚጠበቅብንን እናድርግ ከቤታችን, ከትምህርት ቤታችን,ከአካባቢያችን, ከመሥራቤታችን, መለያየትን አሥወግደን እጅ ለእጅ ተያይዘን ኢትዬጽያችንን እናቅናት.ቅዱስ አምላክ ይርዳን አሜን!ዲያቆን ዳኒ, መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 5. ምን ዋጋ አለው አንዱ የበፊቱን ሲያርም፤ ሌላው ሲዘራ እየተገኘ አስቸገረን እንጂ።እኔን ምርር ያደረገኝ ግን የባለፈው አረም ሳይሆን አሁን እየተዘሩ ያሉት ናቸው።

  ReplyDelete
 6. Dear Dani
  I have always very good respect for your views, you are absolutely correct!! You are telling the blatant truth of our country . This is always in my mind, you telling us in very nice words and deep concept. Thank you so much!!! I wish if all Ethiopian read this and discuss about the issue, it is a wakeup call for all of us!!! Words are not enough to tell how your perspectives are deep, farsighted and your compassion for our country!!!! Let God bless Ethiopia, let God bless you!!!! Ethiopia le zealalem tenure !!!!!

  ReplyDelete
 7. God bless you Daniel.

  ReplyDelete
 8. Dn. dani, This is very hypothetical idea, Amhara philosophy. We had been with it for centuries. So Ethiopia goes down. This shows the weed in Ethiopian history was the Amhara philosophy. We weeded it from the root and never come again. Your article for me seems as to lobby not to weed the weed. But no way, it is already weeded and being weeded at ground. What remains is that in blogs and you can go on b/s it is non significant to poeples of Ethiopia ( oromo, Tigray, Wolaita, Sidama, Somali, Hadiya....................... and Amhara)

  ReplyDelete
  Replies
  1. You need to learn manner of governance. The amhara as a nation did not get any benefit different from other nations of the country during the previous administrations.

   The weakness of all previous administrations in the Ethiopian history undermined the social, economic and politics of the country, the nation of Amhara was not an exception here.

   You and your colleagues are planting a weed of hatred and division among nations, just like the Devil. This weed is what I assume Dn. Daniel is referring to as a weed.

   Keep this in your note; get used to putting the blame to individuals who deserve it, not the nationality they unintentionally belonged to by birth. This is a culture you need to develop in your governance theory.

   Delete
  2. Wondme, wode hilinah temels. Try to distance yourself from the pointless us and them discourse and see FACTS as they are. I am surprised to see your comment alleging what has been written in this piece as an Amhara philosophy. Don't ethnicize even lines of thinking like this one.

   Delete
  3. Is Amhara a philosophy or nation???

   Delete
 9. Dear Dani
  I have always very good respect for your views, you are absolutely correct!! You are telling the blatant truth of our country . This is always in my mind, you telling us in very nice words and deep concept. Thank you so much!!! I wish if all Ethiopian read this and discuss about the issue, it is a wakeup call for all of us!!! Words are not enough to tell how your perspectives are deep, farsighted and your compassion for our country!!!! Let God bless Ethiopia, let God bless you!!!! Ethiopia le zealalem tenure !!!!!

  ReplyDelete
 10. ዲያቆን ዳኒ , ቃለ ህይወት ያሰማልን !

  ReplyDelete
 11. Lib Yalew Lib Yibel ....Joro Yalew Yisma

  ReplyDelete
 12. Great advice form Dn. Daniel as usual, but no body will consider this very true and useful advice to save the sufferings and damages that can happen. It must be now, if it hasn't been already too late that we look in to the facts of our histories (not just selecting only black points for current interest) and the interests of Ethiopians (I don't agree with the concept of majority unless clear baseline is lined for minorities) to unify and develop our country. Traditional and religious values should be respected and used as an input for the leadership, development and modernization purposes. I believe in that we have lots of traditional and religious values and norms that we can even share with world let alone solving minor in side issues. But the problem is that these values are devaluing and depreciating because of unsupervised in take of others lifestyles. I am a kind of feeling that, if each one of us start thinking in a very constructive and positive way and express our feelings and practice to our best level, then we can contribute to the better shape of our country. Why we always fail to ask for the truth and for the right when something goes wrong? Why our life fortune determined by the good will of others rather than low, culture or religion? Why we silently watch when someone cross the line that has clearly lined by the constitution? When do we feel free to complain when we fail to get fair services from government and civil servants? There are so many questions that we should ask ourselves and seek answer for them.

  ReplyDelete
 13. ቃለ ሕይወትን ያሰማልን! ግሩም መልእክት ነው፡፡ እባካችሁ ሁላችንም ከዚህ ተምረን አረሙን ሥር ሳይድ በፍጥነት እናጥፋ፡፡

  ReplyDelete
 14. ብቸኛ አማራጭ ይህ ብቻ ነው!!!እግዚአብሔር ከነቤተስብህ ይጠብቅህ ዲያቆን ዳንኤል አንተን ጽሀፍ ቢያነቡ ምናለ ማስተዋልን ያድለን ተባረክ!!!

  ReplyDelete
 15. ምን ይደረግ ?? አልክ የዘገዩ ቢሆኑም በተከታታይ የወጡት ጽሁፎችህ ልብን ይነካሉ፥ዳ ዳኒ ትውልዱን ለማስተካከል አመታት ይወስዳል ለመበረዝ ግን ጥቂት ወራት ብቻ፥አውን በታሪክ ጃፓንን ያህል ትልቅ መቅሰፍት የደረሰበት አለ?ለዚያውም ለትውልድ እንዳይረሳ ሆኖ የተተከለ ጠባሳ አሜሪካዊያኑ ጣሉባት ኒውክልርን ግን ዛሬ ያ ሁሉ ቀርቶ ምርቱ በጃፓንና በ አሜሪካ ምን ይመስላል በይቅርታ የተዘጋ ፍሬ እንክርዳድ አልባ፥

  ReplyDelete
 16. ዲያቆን ዳኒ , ቃለ ህይወት ያሰማልን !ለእኛም መሥማትና መማር በቻ አይሁንብን . ድንቅ የሆነ መልዕክት ነው ያሰተላለፎክልን .በሥራ ላይ ማዋል ነው የጉደለን እነግዲ ሁላችንም የሚጠበቅብንን እናድርግ ከቤታችን, ከትምህርት ቤታችን,ከአካባቢያችን, ከመሥራቤታችን, መለያየትን አሥወግደን እጅ ለእጅ ተያይዘን ኢትዬጽያችንን እናቅናት.ቅዱስ አምላክ ይርዳን አሜን!ዲያቆን ዳኒ, መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 17. ግልባጭ ለመንግስት

  ReplyDelete
 18. በወቅቱ ያለው እውነታ ይህ ቢሆንም ይሄንን አረም እንደ ጥሩ ዘር አድርጎ እንዲታይ እና እንዲታዎቅ እንዲሁም እንዲሆን ያስቻለውን እንደ ሥርዓት የቀረበውን የአረም ማዕድ በግለሰብ ደረጃ ለመከላከል ቢቻልም ውጤቱ ከተከላካዮ አካልና መሰሎቹ ውጪ ወይም ዙሪያ አልፎ ጥሩ እምርታ አያመጣም ባይ ነኝ፡፡ ይህ ደግሞ ይደረግ ዘንድ ግድ ነውና አረምን እንደ መልካም ፍሬ እየታየበት በመጣበት ጊዜ እህሉ ወይንም ዘሩ በአረም ተዋጠ ተበላሸ ብለን ብንጮህ አበድክ እንዴ አረሙ እንዳይበቅል እህሉና ገበሬው ተባብረው ችግር ፈጠሩበት እንጂ የሚልህ አካል ከጎናችን ብቅ እያለ እየታየ መምጠቱ ደግሞ ተስፍ እንደሌለን አድርጎ የሚያስነግር ዜና ይሆንብናል፡፡ የሚያመራውም ወደዛ ነው እና በእግዚአብሔር እርዳታና በቅድስት ቦታው የማሳወቅና የማንቃት ሥራ መስራት ይጠብቀናል ብየ አስባለሁ አንደ ብቸኛ አማራጭም ነው ብየ አምናለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ግልባጭ ለመንግስት

   Delete
 19. "YE'ENAT HOD GZINGURGUR NEW" YIBALAL. YEHAGERIM ENDEZIAW NEW. ENEZIH SEWOCH GIN EZIH HAGER YEBEKELU YEMEHONACHEW NEGER AHUNIM GIRIM YILEGNAL. KEZIH BEFIT ENDENEZIH YALU ERGUM,AWIKEW YANKELAFU,GITIROCHIN YICHI HAGER ABIKILA ATAWIKIM(AYIMESILEGNIM). BICHA YEMINIMAREWN TEMIREN ENEZIHIN WODIYA MABARER NEW YEMIYAWATAW. HOHOHOHO.........Y!!!!

  ReplyDelete
 20. Outstanding View! In our current Ethiopia, body in one country with departed spirit. Many people are made to dig only the wrong doings of one over the other; expanding hatred . Why should we let that happen? In case we may gain some short term.... gain, but we cannot sustain in doing hatred in and b/n our children!

  ReplyDelete
 21. ዲያቆን ዳኒ , ቃለ ህይወት ያሰማልን !ለእኛም መሥማትና መማር በቻ አይሁንብን . ድንቅ የሆነ መልዕክት ነው ያሰተላለፎክልን .በሥራ ላይ ማዋል ነው

  ReplyDelete
 22. መምህር ዳኒ በጎ ህይታ ነው!! አስተዋይ እረኛ! ይስጠና ምን ይባላል!!!!

  ReplyDelete
 23. I always believe that what was happened in the former history of our country didn't happen in the way the so called illiterate politicians presented . If it was happened on the wrong analysis of the present rulers ,let alone to got victory over Italian aggregation as one nation at the Adwa battle ,the country itself couldn't survive before the war .I raised that battle as an example just to show the smooth relation of Emperor Minilek's leadership and the people of Ethiopia/nations ,nationalities.../ at that particular historic time which laid the foundation of today's strength . It is obvious that in the building history of every country there were many up and downs happened.As one of the ancient country , the same truth was happened and there were some minor damages on the indigenous people due to the newly coming settlers and new infrastructural lay outs . We have a very good example which we can see it today in our country . How is the land garb in Gambela,Northern Gonder etc have been done? How was the flower farm in the Eastern Showa started ? What was happened to the native people while all the Gilgel Gibe and Abby dams being constructed? Do we really have clear idea about the Midrock gold mining company and the people of Shakiso? What is happening now due to the expanding plan of the Addis Abeba city ? As a concerned matured adult most of the present so called politicians both in the country and abroad, don't like to talk based on tangible historic facts rather than aggravating baseless hear-says of extremists and power seekers of the present govt year after years .More than forty years we had killed each other in the name of certain nations for the freedom and now the silent killing is counting for the same cause with no end .This clearly shows that we have no solution for our own problems and can't stop blaming the past . So the solution is some where else and it is only found from the Almighty God who knows our weakness . Let us see ourselves and find out all our weaknesses and forgive ourselves and then stand up to forgive others for the sin which we think they might did on us. Then the impossible will be possible and the God of the universe will give us the leader,wisdom,know how,capital and etc so that we can live accordingly and use the fruit of our country with others .

  ReplyDelete
 24. አረሙ እንደሆነ ገበሬው ሠራም አልሠራም፣ አረሰም አላረሰም፣ ዘራም አልዘራም ይበቅላል፡፡ Dn.Daniel have you noticed many have already given up and encourage the weed growth by being the live evidence to those who harbor and reflect the past historic weed.

  ReplyDelete
  Replies
  1. True, this is what's making the problem worse!

   Delete
 25. ምናለ ከገበሬው ብንማር፤ ለአረሙ ዕድል ባንሰጠው፡፡ አረም አረምን ይወልዳል፡፡ የትናንቱን አረም ዕድል እየሰጠነው ሥር ሰድዶ እንዲበቅልና ከፍ ብሎ እንዲታይ ባደረግነው ቁጥር ለተተኪውም ትውልድ አርሞ የማይጨርሰው ሌላ ገንጋና አረም እንዘራለታለን፡፡

  ReplyDelete
 26. ግሩም ምልከታ ነው ዲያቆን ዳንኤል ። እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ ። እዚህ አሜሪካ ውስጥ አንድ የማዳበሪያና የምርጥ ዘር ድርጅት እንዳለ እሰማለሁ። ይሀ ድርጅት የሚሸጣቸው ምርጥ ዘሮች በመጀመሪያው ዙር እስከ አስር እጥፍ ምርት ያስገኛል ። ነገር ግን ይህ የምርት መጠን በየጊዜው እየቀነሰ ሔዶ መጨረሻ ላይ ምርት መስጠት ያቆማል። አረም ይሆናል ማለት ነው። ችግሩ የምርጥ ዘሩ ከእህል ዘርነት ወደ አረምነት የሚቀየረው ቀስ በቀስ የማምረት መጠኑን እየቀነሰ ስለሆነ ገበሬው በመጀመሪያዎቹ አመታት በሚያገኘው ምርት ተኩራርቶ እጁ ላይ የኖረውን ዘር ያጣል። ከዚያ በኋላ የዘር ፍላጎቱ በዚያ ድርጅት መዳፍ ውስጥ ይወድቃል። ነባሩን የእህል ዘር አጥቶ አረም እየገዛ ይኖራል ። ችግሩ በምርጥ ዘር ፍላጎት የዚህ ድርጅት ዘላላማዊ ሸማች መሆኑ ላይ ብቻ አይደለም። ይህ ድርጅት ገበሬው የራሱን ዘር አጥቶ በእርሱ እጅ መውደቁን ሲያረጋግጥ ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታዎች መቀመጥ መጀመራቸው ነው። ከማዳበሪያ እና ምርት ዘር ጋር ርዮተ ዓለም . . . ያኔ እራስን መሆን ያበቃለታል። በኛም ሀገር እየሆነ ያለው ተመሳሳይ ነው።
  ትናንት አረም የሆነውን የመገዳደል ፣ የመጠላላት ፣ የግፍ አገዛዝ ታሪክ ከፍ አድርገው ያራገቡ ግለሰቦችም ሆኑ የፓለቲካ ድርጅቶች ለጊዜው ያተፀረፉ ቢመስላቼውም እንኳ የዘሩት አረም ነውና መኸራቸውም አረም መሆኑ አይቀሬ ነው። ዛሬ ውጤታማ የሆኑ ቢመስላቼውም አብሮ ያኖረን የሚያግባባ እና የሚያስማማንን እጃችን ላይ ያለ ዘር
  ወይም የአብሮነታችንን እሴቶች አጥተን ስንጨርስ የሚቀረን ተንከባክበን ያሳደግነው አረም ብቻ ስለሚሆን አረም ማጨዳችን የግድ ነው ። በዚህ ደግሞ እንኳን ሠላምና አብሮነቱን እየወደደ በመሰሪ የመከፋፈል ፍልስፍአና እየተቀማ ያለው የኢትዬጵያ ህዝብ ከፋፋዮቹ እራሳቸውም አይጠቀሙም ። " ሰው የዘራውን እራሱን ያጭዳል " አይደል የሚለው መጽሐፉ ? ታዲያ አረም አጭዶ እንዴት ማትረፍ ይቻላል ? እግዚአብሔር ለአረም ናፋቂዎች ልብ ይስጥልን።

  ReplyDelete
 27. Egiziabher yebarkeh, Betam astamari yehon tsehu hulum enedianbew emekeralehu

  ReplyDelete
 28. I love your article Dani, as usual

  GOD Bless You and Ethiopia

  ReplyDelete
 29. አበባው አይመረAugust 2, 2015 at 5:40 PM

  በጣም አመሰግናለሁ።ይኸ ጉዳይ ሁሌም የማስበውና የሚያስጨንቀኝ ነገር ነው። በተገቢ ቋንቋ ገልፀኸዋል ልብ ያለው ልብ ይበል። አረም ምናልባት በመጠኑም ቢሆን ማንኛውንም መሬት የሚፈታተን ነገር ነው። ነገር ግን ከዚህ በፊት እኛ መሬት ላይ በቅለው የማያውቁትን አረሞች እንደበቀሉ መናገራችን በቀደሙት ትጉሀን ገበሬዎች ዘንድ ያስወቅሰናል።እንዲያውም እኛ ዛሬ አረምን ከመንቀል ይልቅ መጤ አረም ያውም በማዳበሪያ እያሳደግን እንገኛለን።ይኸን የሚንከባከብ ሰራተኛም የተቀጠረ ሁሉ ይመስለኛል።እባካችሁ አረሙ ይነቀል ለማንም አይጠቅምም።መንግስትም ሊያብበት የሚገባ ነገር ይመስለኛል ።አረሙ የሀገሪቷን ምርት ከመጉዳቱ በፊት የአረም ማጥፈያ መድሀኒቱን እና ርጭቱን ያስብበት።

  ReplyDelete
 30. Learning from others mistakes should be z thinking of his centuries nation than learning from own mistake which costs every thing

  ReplyDelete
 31. ያኔ ማሳው ለከብት እንጂ ለሰው አይሆንም
  እግዚአብሄር ከሚፈራው ይሰውረን
  ዳኒ እድሜና ጤና ጨምሮ ይስጥህ

  ReplyDelete
 32. What a blessing to be able to see from the heart. Our Ethiopia is in need of leaders, who can clearly see. I personally believe you are the true voice that is talking to this generation. May God give you strength, and more wisdom as you go on.

  ReplyDelete