Thursday, July 16, 2015

የኛ ሠፈር ፍርድእኛ ሠፈር ነው፡፡ አንዲት ሴትዮ በእኩለ ሌሊት እሪታዋን አቀለጠቺው፡፡ እኛም እየተንጋጋን ከቤታችን ወጣን፡፡ ሠፈርተኛው፣ የአካባቢ ጸጥታ አስከባሪዎች፣ መንገደኛው፣ የቀበሌ ሹሙ፣ ውሾቹ እንኳን ሳይቀሩ የተጮኸበት ቤት ጋ ተሰበሰቡ፡፡ ጎረምሶቹ የቤቱን በር ሰብረው ሲገቡ ባሏ ሚስቱን ውኃ ውኃ በሚያሰኝ ዱላ ይደበድባል፡፡ ጎረምሶቹ ዱላውን ነጥቀው እርሷን ከቤት አወጧት፡፡ ልብሷ ተቀዳዷል፤ የተረፈውም በደም አበላ ተጠምቋል፡፡  
ከጸጥታ አስከባሪዎች አንዱ ‹‹ለምን ይህንን ያህል በመጮኽ ሠፈሩን ጸጥታ ትነሻለሺ›› አላት ደም በደም የሆቺውን ሴትዮ፡፡ አልመለሰቺም፡፡ እርሷ ደሟን በልብሷ እየጠረገቺ ታለቅሳለቺ፡፡ እንኳን መልስ የምትሰጥበት በሕይወት የምትቆዪበት ዐቅም ያላት አትመስልም፡፡
‹‹ሁልጊዜ ኮ ነው የምትጮኸው፤ እኛ ሠፈሩን ሰላማዊና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ ቀን ከሌት እንለፋለን፡፡ የኮብል ስቶን መንገድ አሠራን፣ የጥበቃ ቤት አሠራን፣ ዛፍ ተከልን፤ ትልልቅ ቢል ቦርዶችን ሰቀልን፣ ምን ዋጋ አለው፡፡ ይቺ ሴትዮ ሌሊት ሌሊት የሠፈሩን ሰላም ትበጠብጠዋለቺ›› አለ የአካባቢው ሹም በምሬት፡፡
‹‹ለምንድን ነው ሠፈሩን እንዲህ የምታሸብሪው?›› አላት ጸጥታ አስከባሪው፡፡
‹‹ ይልቅ እርሱን ‹ለምን ትደበድባታለህ›? ብላቺሁ አትጠይቁትም›› አለቺ ደሟን እየጠረገቺ፡፡
‹‹የችግሩን ምንጭ ትታችሁ የችግሩ ውጤት ላይ ለምን ታተኩራላችሁ፡፡ የጮኸቺው ስለተደበደበቺ ነው፡፡ መጠየቅ ያለበት ደብዳቢው እንጂ ስትደበደብ የጮኸቺው አይደለቺም› አለ አንድ ወጣት፡፡ ተሰብሳቢዎቹ ‹ዝም በል - ቀዥቀዣ › ብለው ተረባረቡበት፡፡

 
‹‹እኛን የረበሸን፣ ፀረ ሰላም የሆነብን፣ ሽብር የለቀቀብን እርሱ አንቺን መደብደቡ አይደለም፡፡ ያንቺ በሌሊት መጮኸ ነው፡፡ ‹አንተ ዐውቃለሁ ባዩ› አለው ወጣቱን ‹‹ለኛ ምን? የሚለው እንጂ ለምን? የሚለው ብዙም አያሳስበንም‹‹ አለ የጸጥታ አስከባሪው፡፡
‹‹ታድያ ስደበደብ መሳቅ ነው እንዴ ያለብኝ›› አለቺ ጥያቄው የደሟን መፍሰስ ሊያስረሳት ደርሶ፡፡
‹‹ብትደበደቢስ፤ ሠፈሩ እስኪሸበር መጮህን ምን አመጣው?›› አሉ አንድ ተረኛ ጥበቃ፡፡ ‹‹መደብደብ ባንቺ ነው እንዴ የተጀመረው፡፡ በየቤቱ ስንቱ ይደበደባል፡፡ እንዳንቺ የሠፈሩን ሰላምና ጸጥታ የሚነሣ ሰው ግን የለም፡፡ ሁሉም ዕንባውን እያፈሰሰ ውጦ ዝም ይላል እንጂ እንዳንቺ አገር ይያዝልኝ ብሎ እሪ አይልም፡፡ እኛኮ በአንቺ ጩኸት ምክንያት ችግር ውስጥ እየገባን ነው፡፡ ሰማሽ! አሸባሪነት ትልቅና ትንሽ የለውም፡፡ እንዲህ ሠፈር ከማሸበር ተጀምሮ ነው በኋላ ሀገር ማሸበር የሚመጣው፡፡ ሠፈራቺንማ የአሸባሪዎች መናኸሪያ ሲሆን ዝም ብለን አናይም፡፡ ልጆቻችንስ ከዚህ አይደል እንዴ አሸባሪነትን ተምረው የሚያድጉት፡፡›› አሉ ጥበቃው፡፡
‹‹ጋሽ እርገጤ ልክ ናቸው፡፡›› አለ አቶ ለጥ ይበሉ፡፡ ‹‹አንደኛ የርሷ ጩኸት ሠፈሩን ሰላም አሳጥቶታል፡፡ ሰላም ደግሞ ለሠፈራችን ዕድገት ወሳኝ ነው፡፡ በሠፈራችን ይኼንን ሁሉ ዕድገት ያስመዘገብነው በአንጻራዊ መልክ ሠፈራችን ሰላም ስለነበረው ነው፡፡ አሁን ግን እንደ እርሷ ዓይነት ፀረ ሰላም ኃይሎች እየበጠበጡን ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ዕድገታችንን እያደናቀፈቺ ነው፡፡ ተመልከቱ ይኼ ሁሉ የመንደሩ ነዋሪ በእኩለ ሌሊት ዕንቅልፉን አጥቶ እዚህ ተሰብስቧል፡፡ የጸጥታ ሠራተኞች እዚህ ናቸው፡፤ ጥበቃዎች እዚህ ናቸው፤ የሀገር ሽማግሌዎች እዚህ ናቸው፡፡ እንደምታውቁት ነገ የውኃ መፍሰሻ ቦይ ለመሥራት ሠፈሩ ተቀጥሯል፡፡ እንደዚህ ዕንቅልፍ አጥተን እያደርን ነገ በጠዋት መነሣት አንቺልም፤ ብንነሣም ድካም ስለማይለቀን ቦዩን መሥራት አንችልም፡፡ ታድያ ዕድገታችን ተደናቀፈ ማለት አይደለም?›› እዚያ የተሰበሰቡት ሁሉ ‹ልክ ነው› ‹ልክ ነው› አሉ፡፡
‹‹ሦስተኛው›› አለና ቀጠለ ለጥ ይበሉ፡፡ ‹‹የዚህች ሴትዮ ጩኸት የሠፈራችንን የገጽታ ግንባታ እያበላሸው ነው›› ሲል ወሮ እንዳሉሽ ወገባቸውን ያዙና ‹‹ልክ ነው የገጥታ ግንባታው ነገር ሊታሰበብበት ይገባል፡፡ እኛ ወሸቅ ወሸቅ አድርገን ሰርቪስ ቤት የሠራነውኮ ተርፎን አይደለም፤ ከሌላ ሠፈር ተከራይ ለመሳብ ነው፡፡ አሁን የሠፈሩ የገጥታ ግንባታ ከተበላሸ ተከራይ አናገኝም፡፡ ብናገኝም በርካሽ ነው የሚከራዩን፡፡ ይኼው የገጥታ ግንባታቸው ያማረ ሠፈሮች አንድ ክፍል በሁለት ሺ ብር ያከራያሉ፡፡ የዚህ ሁሉ መነሻ ይቺ ሴትዮ ናት፡፡ ገጥታችን ተበላሽቷል፡፡››
‹‹ልክ ነው›› አለ ወጣት ዘለሌ ‹‹ባለፈው ጊዜ ስንት ዘፈን አዘጋጅተን፤ መፈክር ሰቅለን፣ ቢል ቦርድ አሠርተን፣ ቀለም ቀብተን የገነባነውን የሰፈራችንን ገጽታ ይቺ መናጢ ሴትዮ አበላሸቺው››  
‹‹እዚህ ላይ ልጨምርበት›› አሉ አንድ የትምህርት ባለሞያ፡፡ ‹‹ባለፈው ዓመት በያዝነው ዕቅድ ዘንድሮ የትምህርቱን ውጤታማነት ለማሻሻል ብዙ ጥረት ማድረጋችንን ታውቃላችሁ፡፡ ምንም እንኳን የወንበርና ጠረጲዛ፣ የላቦራቶሪ ዕቃዎችና የመብራት ችግር በትምህርት ቤቶች ላይ ቢገጥመንም ትምህርት ቤቶችን ግን ገንብተናል፡፡ ምንም መስተዳድሩ ይህንን ሁሉ ጥረት ቢያደርግ ልጆቻችን ግን የትምህርት ውጤታቸው ሊሻሻል አልቻለም፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነው፡፡ ልጆቹ ማታ ማታ ማጥናት አልቻሉም፡፡ ይቺ ሴትዮ በጮኸች ቁጥር ይረበሻሉ፡፡ የሠፈሩ መምህራን የትምህርት ዕቅድ ለማዘጋጀት አልቻሉም፡፡ ሥራቸው የእርሷን ጩኸት ማዳመጥና እየመጡ መገላገል ሆኗል፡፡›› የከበቡት ሁሉ ራሳቸውን በስምምነት ነቀነቁ፡፡
አንድ የቀበሌ ሹም ጠጋ አለና ‹‹ስትደበደቢ ሠፈር እስኪበጠበጥ ከምትጮኺ ለምንድን ነው ወደ ቀበሌው ፍርድ ሸንጎ በጠዋት የማትሄጂው›› አላት በቁጣ፡፡ ደሟን ከጉንጯ ላይ ጠረገቺና የንዴት ፈገግታ ፈገግ ብላ ‹‹የቀበሌው ፍርድ ሸንጎ ሰብሳቢ ባሌ አይደለም እንዴ፡፡ እንዴት ነው ለደብዳቢየ አቤት የምለው›› አለቺው፡፡
ይህንን ሁሉ ሲያዳምጥ የነበረው ባሏ በደስታ ቀና አለ፡፡ መግረፊያውን ቀምተውት የነበሩት ጎረምሶችም ይቅርታ ጠይቀው ሌላ አንድ መግረፊያ ጨምረው መለሱለት፡፡ ያ ሁሉ ሕዝብ ሲሰበሰብና በሩን ሰብሮ ሲገባ ‹ሚስትህን ለምን ደበደብክ? የሚስትህን ሰብአዊ መብት ነክተሃል፤ በአካል ላይ ጉዳት አድርሰሃል፤ ወደ ሕግ መውሰድ ሲገባህ ራስህ ከሳሽ ራስህ ዳኛ ሆነህ ወንጀል ሠርተሃል› ብለው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይወስዱኛል ብሎ ገምቶ ነበር፡፡ የሆነው ግን ተገላበጠለት፡፡ እርሱም ፍርሃቱን ገለበጠው፡፡
መግረፊያውን እያወዛወዘ ‹ተቸገርንኮ ጎበዝ፡፡ አሁን በዚህ ተመታሁ ብላ ይህንን ያህል መጮህ ነበረባት፡፡ ሠፈሩንስ ሰላም መንሣት ነበረባት፡፡ አሁን እኔ ስማታ ሠፈሩን እረብሻለሁ?››
‹‹ኧረ ፈጽሞ፤ እርስዎ ሲደባደቡ በጭራሽ ድምጽ አልተሰማም፤ በሰላማዊ መንገድ ነው የሚደባደቡት›› አሉት የከበቡት ሰዎች
‹እኔ ስጋረፍ ገጽታችንን አበላሽቻለሁ? ሥራ አስፈትቻለሁ?›› ሁሉም አለማድረጉን መሰከሩለት፡፡
‹‹እርሷምኮ ጸጥታ ሳትነሣ፣ ሽብር ሳትፈጥር፣ ዕድገት ሳታደናቅፍ፣ ገጽታ ሳታበላሽ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ልቅሶዋን ማልቀስ ትችል ነበር፡፡ ለማልቀስ ይህንን ያህል መጮህ ምንድን ነው?››
ሁለት ጎረቤቶች ቀረብ ብለው ትከሻውን እየነኩ አጽናኑት፡፡   
በዚህ መካከል የከበበውን ሰው ገፋ ገፋ እያደረጉ አንዲት እናት ወደ መሐል ገቡ፡፡ ‹የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ፤ የሟች ልጅ እያለ የገዳይን ልጅ ልቅሶ ደረሱት› አለ ያገሬ ሰው፡፡ የተጎዳቺዉ እያለቺ ምን እርሱን አይዞህ ትሉታላችሁ፡፡ ይልቅ እርሱን ወደ ሕግ፣ እርሷንም ወደ ሐኪም ቤት እንውሰዳት›› አሉ፡፡
የተሰበሰቡት ሰዎች ገላመጧቸው፡፡
‹‹ካልሆነ እኔ ወደ ሐኪም ቤት እወስዳታለሁ›› ብለው ሊወጡ ሲሉ ቀበሌው ሹም ያዝ አደረጋቸው፡፡
‹‹እማማ አሁን አይወስዷትም›› አላቸው፡፡
‹‹ለምን?›› አሉ እኒያ እናት
‹‹የቀበሌው ጋዜጠኞች እየመጡ ነው››
‹‹ለምን?›› አሉ ሴትዮዋ
‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ በቀበሌያችን ቴሌቭዥን የሚቀርብ ዶክመንተሪ እንሠራለን››

38 comments:

 1. እንዴት ነው ለደብዳቢየ አቤት የምለው!!!

  ReplyDelete
 2. Thanks Dani,you really show us our society judgment about the right thing, that is offended,most of the people are give their support for those who have power,money,and etc.nobody give the right judgment for the right things.

  ReplyDelete
 3. የኔ ስጋ እንደ ሰጋ
  ስንት መዐልት አልፎ ስንት ሌሊት ነጋ

  ReplyDelete
 4. ዳኝነት እንዲህ ነዉ በኛም ሠፈር በእማማ ኢትዮጵያ

  ReplyDelete
 5. Thank you Dani, you always teach us to improve our self.

  ReplyDelete
 6. እማማ አሁን አይወስዷትም›› አላቸው፡፡

  ‹‹ለምን?›› አሉ እኒያ እናት

  ‹‹የቀበሌው ጋዜጠኞች እየመጡ ነው››

  ‹‹ለምን?›› አሉ ሴትዮዋ

  ‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ በቀበሌያችን ቴሌቭዥን የሚቀርብ ዶክመንተሪ እንሠራለን››


  ReplyDelete
 7. ‹‹እዚህ ላይ ልጨምርበት›› አሉ አንድ የትምህርት ባለሞያ፡፡ ‹‹ባለፈው ዓመት በያዝነው ዕቅድ ዘንድሮ የትምህርቱን ውጤታማነት ለማሻሻል ብዙ ጥረት ማድረጋችንን ታውቃላችሁ፡፡ ምንም እንኳን የወንበርና የጠረጲዛ፣ የላቦራቶሪ ዕቃዎችና የመብራት ችግር በትምህርት ቤቶች ላይ ቢገጥመንም ትምህርት ቤቶችን ግን ገንብተናል፡፡ ምንም መስተዳድሩ ይህንን ሁሉ ጥረት ቢያደርግ ልጆቻችን ግን የትምህርት ውጤታቸው ሊሻሻል አልቻለም፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነው፡፡ ልጆቹ ማታ ማታ ማጥናት አልቻሉም

  ReplyDelete
 8. I live in out side the country so it is difficult to understand your message. Is there any one help me what he want to say?

  ReplyDelete
  Replies
  1. if U can read Amharic, then it should be bread and butter.....
   "Tedirew Bimelesu Ye-Wuha Menged Resu" ...

   Delete
  2. Behavior is difficult if no change. Yes it is true"it should be bread and butter.....".

   Delete
 9. My suggestion will be we have to pray to have the right goverment that he/she belive in the truth instead of politics. God bless Ethiopia

  ReplyDelete
 10. I don't blame the neighbour hood because they scare the policy.

  ReplyDelete
 11. le nigussu yagonbisu new

  ReplyDelete
 12. Thank you Dani
  bizuwechachine senfered firdegemdle nen lalew ena ledelaw bicha new yeminferdew, lelaw yelelasew hasab teketlen new yeminiguze yerasachine yehone hasab anamenchime, so yehe yemengist bich sehitet aydelem yehizeb chimer engi, hizebu lerasu ena lelaw sew mebit kekome one day goverment will learn his mistake, so we have to learn how we respect others wishes, Identity and back ground.

  ReplyDelete
 13. Thank you Dane you always publish very heart touching
  first sorry for my grammer and spelling
  I have a suggesion for all of as ( Ehiopian people) as my understanding most of as needs to change our attitude
  1= we follow some body's idea specially that person reach or well known or the community forced as to follow, if we have defferent idea than them we will be isolate
  2= most of as we don't know our righ or responsible, we dont respect some body wishs, back ground, idea
  3= we blame the government or some body elses, let start from our home, husband or wives not respect each others, parents does't respect for there kids, friends doens't respect or be honest each other neighbours not repect each others. work colleague not respect each other, every where coraption, every one helping the system back home or diaspors sorry to say this Ethiopins grown up from out of the truth and being honest, but we are the one talk rights and responsibe, How can Ehtiopian goverment give democracy to his people, we are supported him for his decision.

  ReplyDelete
 14. የናንተ ሰፈር ሰው እሪታውን ሰምተው ተንጋግተው መውጣታቸው ራሱ ያስመሰግናቸዋል፡፡
  የራሴ ቤት ስላም ከሆነ ምን ቸገረኝ ብለው በቤታቸው ክትት ብለው ቢሆን ኑሮ ይሄንን ሁሉ ጉድ መች እንሰማ ነበር?

  ReplyDelete
 15. ኢትዬጵያ, ጀግኖችን እነዳላፈራሸ ዛሬ ላይ ግን የወላድ መካን ሆነሸ ቀረሸ. ጌታ ሆይ እውነተኞ ዳኛ አንተ ብቻ ነህ እውነትም አንተ ነህ .አሁን ላይ እየሆነባባት ያለውን ግፍ እሰከ መቼ ነው የምትታገሰው? ቃል ኪዳን የገባህላትን አገር አሰባት!ዲያቆን ዳኒ ,የመድሃሂያለም ጥበቃ አይለይህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 16. Some times your point is trash I don't understand !

  ReplyDelete
  Replies
  1. I don't think Daniel's point is some times trash, but your mind may be always trash. Try to clean it, then you w

   Delete
  2. I think there is a virus in u'r mind , if u want i will send u antivirus to u to cleanup trash from ur mind then u know how much Daniel wrote important thing for us .

   Delete
 17. Lib yalew lib yibel! This is the true picture of Every Ethiopians Living/experiencing.

  ReplyDelete
 18. "ተረኛው ጥበቃ ጋሽ እርገጤ" - የምእራብውያን እርዳታ ድርጅቶች (የስለላ ተቅዋሞች) አሻንጉሊት የሆነው የዘመኑ ፀረ-ኢትዮጵያ ርኩስ መንጎች ስብስብን ይወክላል። "ለጥ ይበሉ" ደግሞ የአጨብጫዊንና ተኮላሽቶ እና ደንዝዞ ሌላውንም የሚያኮላሸውን የማህበረሰቡን አካል ይወክላል። "የቀዥቃዣ ወጣቱስ" ስም ማን ይሆን ? እንዴት ስም ሳይሰጠው ቀረ ? ደፋሯ "እናትስ" ምን አይነት ስያሜ ይስማማቸው ይሆን ? ወይስ "እናት" የሚለው ስያሜ በቂ ይሆን ?

  ReplyDelete
 19. የሚያስሮጠዉ እያለ የሚሮጠዉን ቁም እንደማለት ሆነኮ !

  ReplyDelete
 20. Dani please publish articles that maintain your status. don't write such idiot articles

  ReplyDelete
  Replies
  1. I think you must be ye KEBELE SHUM. If you are, of course this article is idiot for you. But for most Ethiopians this is the reality.

   Delete
 21. This is will be continued unless we pray to God,God bless Ethiopia

  ReplyDelete
 22. እንዴዬ ኧረ ለክራችን ክር የሌለን ለህሊናችን እንኑር
  ወደ ነፈሰበት አንሁን

  ReplyDelete
 23. አዎን ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል ይባል የለም የሁሉ ጩኸት ከውስጥ ከሆነ ጊዜና ሰዓት የለውም በዓለም ውስጥ ያለው ሁኔታ የፍርድ አሰጣጡ (ልጁ ቀማኛ አባቱ ዳኛ) ከሆነ ሰነባብቷል ።ብቻ ዓይነ ልቡናህን የበለጠ ያብራልህ ።
  ( እስኩ ድግሙ )

  ReplyDelete
  Replies
  1. ታዲያ መቼ ነው የውስጥ ጩኸታችን ወደ ውጭ ወጥቶ የሚሰማው ዳኒ የአንተ ሠፈር ሰዎች ደጋጎች ናቸው የኛ ሰፈሮችማ ለመስማት መጀመሪያ ጆሮ ሲኖራቸው አይደል ።

   Delete
 24. 1st Lol and e'thing will pass! Thanks Dn

  ReplyDelete
 25. ‹‹ካልሆነ እኔ ወደ ሐኪም ቤት እወስዳታለሁ›› ብለው ሊወጡ ሲሉ ቀበሌው ሹም ያዝ አደረጋቸው፡፡
  ‹‹እማማ አሁን አይወስዷትም›› አላቸው፡፡
  ‹‹ለምን?›› አሉ እኒያ እናት
  ‹‹የቀበሌው ጋዜጠኞች እየመጡ ነው››
  ‹‹ለምን?›› አሉ ሴትዮዋ
  ‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ በቀበሌያችን ቴሌቭዥን የሚቀርብ ዶክመንተሪ እንሠራለን›› በጣም የሚገርመ ነው

  ReplyDelete
 26. Thanks for those people who gave their ears for the scrumming poor lady though they have no power and unity to take her well before she dies .Ones the dark night passes, she may has a better possibility to decide for a better life in the broad day light .

  ReplyDelete
 27. First, thank you and may GOD bless you Dn. Daniel.
  This article shows the ambiguity of her husband role and
  the lost confident b/n people to stand for their right.
  IF HE DOESN'T GET IT RIGHT AT HOME HOW WILL HE GET IT RIGHT AS POBLIC SERVANT!!
  MY GOD BLESS YOUR CHILDREN ETHIOPIA!!!

  ReplyDelete
 28. ‹‹ካልሆነ እኔ ወደ ሐኪም ቤት እወስዳታለሁ›› ብለው ሊወጡ ሲሉ ቀበሌው ሹም ያዝ አደረጋቸው፡፡
  ‹‹እማማ አሁን አይወስዷትም›› አላቸው፡፡
  ‹‹ለምን?›› አሉ እኒያ እናት
  ‹‹የቀበሌው ጋዜጠኞች እየመጡ ነው››
  ‹‹ለምን?›› አሉ ሴትዮዋ
  ‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ በቀበሌያችን ቴሌቭዥን የሚቀርብ ዶክመንተሪ እንሠራለን››

  ReplyDelete
 29. አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ

  ReplyDelete
 30. ‹‹የችግሩን ምንጭ ትታችሁ የችግሩ ውጤት ላይ ለምን ታተኩራላችሁ፡፡ ችግሮቻችን ለመፍታት ከመሞከር በሚያስከትላቸው ውጤቶች የፍላጎታችን ማስፈፀሚያ ቅልፍተደረጎ በአብዛኞቻቻን በመወሰዱ አድርባይነታችን አግንኖታል፡፡ በተለይም መስሪያቤቶቻችን፡፡አምላክ ማስተዋልህን ይጨምርልህ፡፡

  ReplyDelete