Monday, June 8, 2015

ጾምና የዩኒቨርሲቲዎቻችን አስተዳደር

የሰኔ ጾም መግባትን ተከትሎ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የምግብ ክርክሮች መፈጠራቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ‹የጾም ምግብ ምግብ ይሠራልን› ብለው በሚጠይቁ ተማሪዎችና ‹ያቀረብንላችሁን ብቻ ብሉ› በሚሉ የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች መካከል ነው ክርክሩ፡፡
የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች ይህንን የተማሪዎችን ጥያቄ ላለመቀበል የሚያቀርቧቸው መከራከሪያዎች ከሦስት የዘለሉ አይደሉም፡፡ የመጀመሪያው ሃይማኖታዊ አክራሪነትን ከመዋጋት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የአንድ ሰው መጾምና መጸለይ የአክራሪነት መመዘኛዎች መሆናቸውን የሚያሳይ ምንም ዓይነት መዝገበ ቃላት ሊቀርብ ባይችልም፡፡ መንግሥት መመሪያ ሰጠን እንዳይሉም መንግሥት በተለያዩ ቦታዎች አክራሪነትን ለመተርጎም የሚያዘጋጃቸው መዛግብት ጾምን የአክራሪነት መግለጫ አድርገው ያቀረቡበት ጊዜ የለም፡፡ አክራሪነት፣ ሽብርተኛነት፣ ጽንፈኛነት የሚሉት ጽንሰ ሐሳቦች በጥንቃቄና ገደብ ባለው ሁኔታ የማይተረጎሙ ከሆነ ለመለጠጥና የተፈለገውን ሁሉ ለማካተት ምቹዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሐሳቦች ለተቋማትና ባለ ሥልጣናት ግላዊ ትርጎማ የተመቹ በመሆናቸው በማሳያዎች፣ በመግለጫዎችና ገደብ ባለው ሁኔታ መተርጎምን የሚጠይቁ ናቸው፡፡

በወጣቶች በተለይም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የእምነት አክራሪነት እንዳይፈጠር ከተፈለገ የእምነት አክራሪነትን ከዩኒቨርሲቲዎች ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ሁሉንም ሊያግባባ በሚችል ሁኔታ መተርጎምንና ግልጽ የሆኑ ማሳያዎችን ማስቀመጥን ይጠይቃል፡፡ በተለይ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃይማኖት ከባሕል፣ ሥነ ልቡና፣ አመለካከትና አነዋወር ጋር በእጅጉ ድርና ማግ በሆነባቸው ሀገሮች የምዕራባውያንን ወይም የሩቅ ምሥራቆችን አስተሳሰብ ይዞ መጥቶ አክራሪነትን መበየን እንጀራን ምግብ ነው ለማለት በፓስታ መመዘኛ እንደመመዘን ያለ ነው፡፡
ለምሳሌ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ሂጃብ መልበስ ወይም ነጠላ ማድረግ የአክራሪነት መገለጫ ተደርጎ ሲወሰድ ይታያል፡፡ እነዚህ ሁለቱም መሠረታቸው እምነት ቢሆንም በሂደት ግን የሕዝቦች ባሕል ሆነዋል፡፡ አንድ ሰው በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ነጠላ ወይም ሂጃብ ሲለብስ እየገለጠ ያለው ሃይማኖቱን ነው ወይስ ባሕሉን? የሚለውን ለመወሰን እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ እንዲያውም በአንድ ኮሌጅ ውስጥ የኮሌጅ ጥበቃዎች ወደ ግቢው የሚገቡ ተማሪዎችን እያዩ ‹‹አንቺ መስቀለኛ አጣፍተሻልና አስተካክዪ›› እስከማለት የደረሱበትም ቦታ አለ፡፡ ለመሆኑ የአንድን ሰው አለባበስ ሃይማኖታዊ ነው ወይም ባሕላዊ ነው ብሎ የሚወስነው የግቢው ጥበቃ ነውን? በምን ሥልጣን? በየትኛውስ የዕውቀት መጠን? ለምሳሌ አንዲት ልጅ መስቀል የተጠለፈበት የሐበሻ ቀሚስ ለብሳ ወደ ኮሌጅ ግቢ ለመግባት አትችልም ማለት ነው? መስቀል የተነቀሰቺ ልጅስ?
‹የአበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም› እንዲሉ ሶርያና ኢራቅን፣ አፍጋኒስታንንና ሊቢያን ያየ ዩኒቨርሲቲ፣ ነጠላ መልበስንና ሂጃብ ማድረግን አክራሪነት ነው ብሎ ለመጨዋት መነሣት አልነበረበትም፡፡ የጾምም ጉዳይ እንዲሁ ነው፡፡ አንድ ሰው ሲጾም ይበልጥ ወደ አርምሞ፣ ይበልጥ ወደ ጽሙና ይገባል፡፡ ከብዙ ነገሮች ይቆጠብ ዘንድ ራሱን ይገዛል፤ አካላዊ ድካምን ተቀብሎ መንፈሳዊ ጥንካሬን ያገኛል፡፡ ጾም የልቡና ትንሣኤን የሚያመጣ ነው፡፡ እንዲያውም ጾም የአክራሪነት ተቃራኒ ነው፡፡ ራስን ለመቅጣት የሚጾም ሰው ዮሌሎችን ጥፋት ለማሰብ ዕድሉ አነስተኛ ነው፡፡ ይልቅስ አክራሪነትን ለመዋጋት ጾምን ማበረታታት አንዱ መፍትሔ ነው፡፡
ሌላው የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች የሚያነሡት ሐሳብ ሴኩላሪዝምን ነው፡፡ ትምህርት ቤቶች የእምነት ማስፋፊያዎች አይደሉም፡፡ ትምህርት ዓለማዊ(ሴኩላር) ነው፡፡ ስለዚህ ሃይማኖታዊ የሆነውን የጾም ጉዳይ አናስተናግድም ነው፡፡ ትክክል ነው ትምህርት ቤቶች መርሐቸው ዓለማዊነት(ሴኩላሪዝም) ነው፡፡ ትምህርት ቤቶች ሴኩላሪዝምን ይከተላሉ ማለት ግን ሃይማኖት በትምህርት ቤቶች ቦታ የለውም ማለት አይደለም፡፡ በአውሮፓና በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ሴኩላሪዝምን የተከተለ የትምህር መርሕ አላቸው፡፡ በግቢያቸው ውስጥ ግን ለተማሪዎቹ የማምለኪያ ቦታ ይፈቅዳሉ፡፡
በአሁኑ ዘመን የዓለም መንግሥታት ሴኩላሪዝምን በተመለከተ ሁለት ዓይነት አቅጣጫዎችን ይከተላሉ፡፡ የመጀመሪያው Assertive secularism ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ passive secularism ነው፡፡ አሰርቲቭ ሴኩላሪዝም ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችን፣ መገለጫዎችንና ምስሎችን በአደባባይ መጠቀምን፣ ማሳየትንና መግለጥን ይከለክላል፡፡ እምነት ከግላዊ ክበብ ውጭ በይፋ ሕዝባዊ መድረክ እንዳይተገበርም  በጥብቅ ይከታተላል፡፡ ለዚህ የሚጠቀሰው የፈረንሳይና የቱርክ ሴኩላሪዝም ነው፡፡ ፈረንሳይ እኤአ በ2003 ባወጣችው ሕግ በትምህርት ቦታዎች ሂጃብ፣ የአይሁድን ኪፓ፣ ትልልቅ መስቀሎችንና ሌሎች የእምነት ይፋዊ መገለጫዎችን ማድረግን ከልክላ ነበር[1]፡፡ ፓሲቭ ሴኩላሪዝም የሚባለው ደግሞ መንግሥት ምንም ዓይነት የክልከላም ሆነ የፈቃድ ሕግ ሳያወጣ ሰዎች በራሳቸው ፍላጎት ብቻ እምነታቸውን እንዲገልጡ ለራሳቸው ነገሩን መተው ነው፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ሴኩላሪዝም ይህንን የሚመስል ነው[2]፡፡
ምንም እንኳን በሴኩላሪዝም ሐሳባቸው ቢለያዩም ሦስቱም መንግሥታት ሴኩላር መንግሥታት ናቸው፡፡ ያም ማለት የሕግና የመንግሥት ሥርዓታቸው ከሃይማኖታዊ ተጽዕኖ ውጭ ነው፤ ከዚህም በተጨማሪ አንድን የተለየ ሃይማኖትን ወይም ደግሞ ፀረ እምነትነተን (Atheism) ኦፊሴላዊ አድርገው አልተቀበሉም፡፡ ብዙ ሊቃውንት ደግሞ ሴኩላር መንግሥትን በሁለት ነገሮች ይበይኑታል፡፡ የመጀመሪያው የመንግሥትና ሃይማኖት መለያየት ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ የእምነት ነጻነት ነው[3]፡፡ በብዙ ሴኩላር መንግሥታት የመንግሥትና እምነት መለያየት በሕገ መንግሥት የተገለጠ አይደለም፤ ትግበራውን በአጽንዖት የመከታተል ሁኔታም የለም(It is not a practical issue)፡፡ በተቃራኒው የእምነት ነጻነትን በተመለከተ ግን በሕገ መንግሥት ግልጽ በሆነ ሁኔታ የሚቀመጥ ተግባዊነቱንም በአጽዖት የሚከታተሉት ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው ከመንግሥትና እምነት መለያየት ይልቅ የእምነት ነጻነት መከበር ዋነኛው የሕዝቦች ጥያቄ መሆኑን ነው፡፡ የሦስቱም መንግሥታት ልዩነት የመጣው ይህንን የእምነት ነጻነት የመተርጎም ላይ ነው፡፡
 የኢትዮጵያ መንግሥት ብሎም የትምህርት ተቋማት የትኛውን ዓይነት የሴኩላሪዝም መንገድ እንደሚከተሉ ግልጽ አይደለም፡፡ አሰርቲቭ ሴኩላሪዝምን ነው እንዳንል መንግሥት ራሱ የእምነት በዓላትን በብሔራዊ ቴሌቭዥን ሲያስተላልፍ ይታያል፤ በፓርላማውም የእምነት መገለጫ ልብሶችን የለበሱ ተወካዮች ይታያሉ፡፡ ፓሲቭ ሴኩላሪዝምን ነው እንዳይባልም በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚፈጸሙ ክልከላዎች አሉ፡፡ የአሰርቲቭ ሴኩላሪዝም ዋናው ዓላማ እምነትን ከሕዝባዊ መድረክ(public sphere) ለማውጣት ይሁነኝ ብሎ መሥራት (comprehensive doctrine) ሲሆን የፓሲቭ ሴኩላሪዝም ሚና ግን መንግሥት በልዩ ልዩ እምነቶች ውስጥ ያለውን የገለልተኛነት ሚና አጽንቶ መጠበቅ ነው፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ብዙ እምነቶች፣ ባሕሎችና ልማዶች ባሉባት ሀገር፤ ሃይማኖት ትምህርት ብቻ ሳይሆን ባሕል፣ የቀን አቆጣጠር፣ አለባበስ፣ የአስተሳሰብ ቅኝትና የአነዋወር መንገድ በሆነባት ሀገር፤ በባሕልና እምነት መካከል የተቆረጠ መሥመር ለማስመር በሚያስቸግር ማኅበረሰብ ውስጥ፤ መንግሥትም ሆነ የትምህርት ተቋማት ቢከተሉት የሚመከረው ፓሲቭ ሴኩላሪዝምን ነው፡፡ አንደኛው በእምነቱ ምክንያት በሌላው ላይ ተጽዕኖ የማያደርግ ከሆነ፣ መንግሥታዊ ሥራን፣ ሕጋዊ ሂደትንና የመማር ማስተማር ሂደቱን ትርጉም ባለው መጠን እስካላወከ ድረስ፣ ተቋማቱም ይሁነኝ ተብሎ ለሚደረግ የእምነት ማስፋፋት ሥራ[4] መድረክ እስካልሆኑ ድረስ ፓሲቭ ሴኩላሪዝም ለኢትዮጵያ ተመራጭ ነው፡፡
ጾምን ከዚህ አንጻር የተመለከትነው እንደሆነ በምንም መልኩ ይሁነኝ ተብሎ በኮሌጅ ውስጥ የሚደረግ የሃይማኖት ማስፋፋት እንቅስቃሴ አይደለም፡፡ ሰዎች ተሰብስበው ሊማሩና ሊጸልዩ ይችሉ ይሆናል፡፡ ተሰብስቦ መጾም ግን አይቻልም፡፡ ጾም ግላዊ ስለሆነ፡፡ በተመሳሳይ የጾም ወቅት የሚሳተፉ ሰዎች ግን ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በሙስሊምና ክርስቲያን ተማሪዎች ዘንድ በኮሌጆች የሚታየውም ይኼው ነው፡፡ በአንድ ተመሳሳይ የጾም ወቅት የሚደረግ ሱታፌ፡፡ በርግጥ ይሄ የጾ ሐሳብ  እምነትን ግላዊ ብቻ ለማድረግ ከሚያስበው አመለካከት ይለያል፡፡ ምዕራባውያን ‹እምነት ግላዊ ብቻ ነው› ብለው የሚቀበሉት ሐሳብ በፕሮቴስታንት የእምነት አስተምህሮ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እምነት ግላዊ ምርጫ አለው፡፡ በግላዊ ወሳኔም የሚከተሉት ነው፡፡ ነገር ግን ይህንን ግላዊ ምርጫና ውሳኔ በኅብረት መግለጥና መሳተፍ የሚጠይቅበት ጊዜ ግን አለ፡፡ በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ፣ በእስልምናና በይሁዲ እምነቶች ዘንድ ግላዊ የሆኑ የእምነት ሕይወቶችና ሕዝባዊ(ማኅበራዊ) የሆኑ የእምነት ሕይወቶችም አሉ፡፡ የረመዳን ጾምና የሑዳዴ ጾም የዚህ ማኅበራዊ የእምነት ክበብ መገለጫዎች ናቸው፡፡
ትምህርት ቤቶች የጋራ ሱታፌን የሚጠይቁትን ማኅበራዊ የእምነት ክዋኔዎችን መከልከል የለባቸውም፡፡ ምናልባት የጋራ ክዋኔ(Public demonstration) የሚጠይቁ ማኅበራዊ ክዋኔዎች ላይ እንደየሁኔታው ተዐቅቦ ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል፡፡[5] ጾም ግን የጋራ ሱታፌን እንጅ ክዋኔን አይጠይቅም፡፡ የጋራ ሱታፌውም የሚመጣው በተመሳሳይ ወቅት በተመሳሳይ ሥርዓት ስለሚጾም ነው፡፡
ሃይማኖታዊ እሴቶችን በተመለከተ የክልከላን አሠራር ከመከተል የገለልተኛነትን አሠራር መከተሉ የሚጠቅመው ሃይማኖታዊ እሴቶች ዛሬ ዛሬ በኮሌጅ ተማሪዎች ዘንድ በአደገኛነት እየመጡ ያሉትን የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚነት፣ ሥርዓት አልበኝነት፣ የትምህርት ግዴለሽነት፣ በጊዜያዊ ጥቅሞችና ደስታዎች ዘላቂ መሥመርን መሳት፣ የጠባብነትና የጎጠኝነት አስተሳሰቦችንና ድርጊቶችን ለመከላከል የላቀ ሚና ስለሚኖራቸው ጭምር ነው፡፡ የትምህርት ተቋማት በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ውስጥ አፈጻጸሙ ውስብስብ ከሚሆነው አሰርቲቭ ሴኩላሪዝም ይልቅ ፓሲቭ ሴኩላሪዝምን ቢከተሉ ሃይማኖት በማኅበረሰቡ ውስጥ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት መንገዱን ያመቻቻሉ፡፡ የነገው ትውልድም ብዙኅነትን በአዎንታዊ መልክ ለምዶትና ገንዘብ አድርጎት ከዩኒቨርሲቲ እንዲወጣ ያደርጉታል፡፡ እንዲያውም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሌሎች የመንግሥት ተቋማት የሃይማኖትን ጉዳይ በ‹የለሁበትም› መንገድ ከማስተናገድ ይልቅ ምሁራዊ ውይይት እንዲደረግበት መንገድ ቢከፍቱ አንዱ ስለሌላው በጎውን የማወቅና ልዩነቱን ተቀብሎ በሰላም ለመኖር እንዲችል ያደርጉ ነበር፡፡ ሰው በጠባዩ የማያውቀውን ነገር ይፈራዋል፣ ይሠጋዋልም፡፡ የእምነት ጉዳዮችን በምሁራዊ መንገድ በማየት መተዋወቁ ቢፈጠር ፍርሃትና ሥጋቱን ለማስወገድ በተቻለ ነበር፡፤ የትምህርት ተቋማት ሴኩላር መሆንም ለዚህ ነበር ዋናው ጥቅሙ፡፡ ጾም ለመከልከል አልነበረም፡፡  
     ሌላው የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች የሚያነሡት መከራከሪያ ‹‹የተለያዩ ቡድኖችን ፍላጎት በአነስተኛ የኢኮኖሚ ዐቅም ውስጥ ማሟላት ስለማንችል በዩኒቨርሲቲው ዐቅም ላይ የተመሠረተ አንድ ወጥ መርሐ ግብር ብቻ ነው የምንከተለው›› የሚል ነው፡፡ በርግጥ ዩኒቨርሲቲዎች እንደ አውሮፓና አሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ለእምነቶቹ ሁሉ የማምለኪያ ቦታ ለመስጠት የሚያስችል ዐቅም ላይኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን የጾም ምግብ ለማዘጋጀት የሚያስችል አቅም አላቸው፡፡ በሁለት ምክንያት፡፡ የመጀመሪያው የኦርቶዶክስም ሆኑ የሙስሊም የጾም ወቅቶች ጊዜያቸው የታወቀ ነው፡፡ ለጋራ አስተዳደር አስቸጋሪ አይደሉም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የጾም ምግብን ማዘጋጀት ለአንድ ዩኒቨርሲቲ ከፍስክ ምግብ ይልቅ ርካሽ ነው፡፡ ይህም የዩኒቨርሲቲውን በጀት የሚያቃውስ ሳይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ የሚደጉም ነው፡፡ የተማሪዎቹ ጥያቄ ከምንበላው ምግብ የሥጋ፣ የቅቤ፣ የወተትና የዕንቁላል ነገር ተቀንሶ አትክልትና ሽሮ ይሰጠን ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲው ክርክር ደግሞ በጾም ሥጋ ካልበላችሁ የሚል ነው፡፡     
በዚህ ሰሞን ያለው ሁኔታ እንኳን ብንመለከት አንድ ኮሌጅ ሦስት የምግብ መርሐ ግብር ብቻ ይጠበቅበታል፡፡ ለሙስሊም ተማሪዎች የማፍጠሪያ ምግብ ማዘጋጀት(ያም ቢሆን ቀድሞ የሚሰጣቸውን የቁርስና የምሳ ነገር ትቶ እራት ላይ ማቅረብ እንጂ አዲስ ነገር አልጠየቁትም)፣ ለኦርቶዶክስ ተማሪዎች የጾም ምግብ ማዘጋጀት፣ ለሌሎች ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው መርሐ ግብር መሠረት ማዘጋጀት፡፡ ዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ ሠራተኞችንና ቁሳቁሶችን ለማቅረብ በጀት የለኝም ካለ እንኳን ተማሪዎች ሲጾሙ በተውት በጀት መጠቀም ይችላል፡፡ ቅንነቱ ካለ፡፡ ለዚያውስ ቢሆን ‹ለስሟ መጠሪያ ቁና ሰፋቺ› ሆኖ ነው እንጂ ኮሌጅ ውስጥ ስንት ቀን ሥጋ ተበልቶ ነው?
በአሁኑ ዘመን ሥጋን የማይመገቡ ማኅበረሰቦች በዓለም ላይ እየተፈጠሩ ነው፡፡ በብዙ ቦታዎችም ለእነርሱ የሚሆኑ ምግቦች ይዘጋጃሉ፡፡ ታላላቅ ሆቴሎች፣ የግብዣ ቦታዎች፣ መንግሥታዊ ሥነ ሥርዓቶች፣ በዓሎች፣ የአውሮፕላን ጉዞዎች፣ ወዘተ ሥጋ ለማይመገቡ ሰዎች የተለየ ምግብ ማዘጋጀታቸውን በይፋና በኩራት ይገልጡታል፡፡ ጉዳዩንም ከመብትና ለተጠቃሚ የተመቸ ከባቢ ከመፍጠር አንጻር ያዩታል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎቻችንም እነዚህ ሥጋ የማይበሉ ማኅበረሰቦች ቢፈጠሩባቸው ሥጋ የመብላት ግዴታ አለብህ ሊሉ ነው? ብዙዎቹ የዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ሹመኞች ለትምህርት ወይም ለሥልጠና አለበለዚያም ለልምድ ልውውጥ ወደ ውጭ ዩኒቨርሲቲዎች ሄደው ነበር፡፡ የተማሪዎችን ፍላጎቶች እንዴት ከትምህርት ቤት ፖሊሲ ጋር በተጣጣመና ማንንም በማይጎረብጥ መልኩ እንደሚያስተናግዱት አላዩምን? 
መካነ አእምሮ የሆነው ዩኒቨርሲቲ ጾምን የመሰሉ ሃይማኖታዊ እሴቶችን ከእምነት ነጻነትና ተገቢውን አገልግሎት ከማግኘት መብት አንጻር እጅግ በሠለጠነ መንገድ ተርጉሞ በቀላሉ ችግሩን መፍታት ካቃተው ‹መካነ አእምሮ› ከሚለው ቃል ውስጥ ‹ካ› እንዲጠብቅ ያደርገዋል፡፡ 

[1] Ahmet T. Kuru ,Passive and Assertive Secularism Historical Conditions, Ideological Struggles, and State Policies ,toward Religion, p.569
[2] Ahmet T. Kuru, Secularism and State Policies Toward Religion: The United States, France and Turkey , 2009
[3] D. E. Smith, “India as a Secular State,” in Rajeev Bhargava, ed., Secularism and Its Critics (Delhi: Oxford University Press, 1999), esp. 178–83
[4] ጉባኤ በመንግሥታዊና ሕዝባዊ ተቋማት ውስጥ ማከናወን፣ ሰዎችን በተቋማቱ ውስጥ መስበክ፣ ከግለሰባዊ ጥቅምነት ባለፈ በተቋማቱ አደባባይ ላይ የእምነት መግለጫዎችን መለጠፍ፣ ለእምት ማስፋፊያነት የተቋማቱን መዋቅሮች መጠቀም፣ ወዘተ፡፡
[5] ይህም ማለት ለሁሉም ሊያሳኩት ስለማይችሉ ወይም የጋራ ክዋኔዎች በሌላው ላይ ትርጉም ያለው ተጽዕኖ ስለሚያደርሱ (ለምሳሌ በግቢ ውስጥ የጋራ ዝማሬዎች፣ የጋራ ስግደቶች፣ የጋራ ትምህርቶች፣ ወዘተ)

36 comments:

 1. In Libiya IS killed only 28 Ethiopian but in Ethiopia when the govrment destrosy our fasting meaning that means killed all Orthodox Ethiopian followers. If we cann't stop it now after five year the goverment will say don't go church pray in your house only. As they told us " they are working day and night to destroy Ethiopian Orthodox and Amhara.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Tebab astesasebih fakew.
   1chigr betenesa kutir zeleh wede beher ena haymanot atzelel zelayu!!

   Delete
 2. እኒህ ሰዎች በአለም ላይ የሌለ አዲስ ነገር እየፈጠሩ ሕዝባችንን እያሰቃዩት ነው፣ እጅግ የሰለጠነ ነው በሚባለው እኔ በምማርበት አንድ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲ ማንኛውም ሰው የፈለገውን አይነት ልብስ ለብሶ ቢሄድ ማንም ዞር ብሎ አያየውም ፣ ነጠላየን መስቀልኛ አጣፍቼ ክፍል ብገባ እርግጠኛ ነኝ ማንም የዮኒቨርሲቲው ፖሊስም ሆነ ሌላው አካል ዞር ብሎ አያየኝም፣ የሙስሊም እምነት ተከታይ የሆኑ ሴቶች ሂጃብ ለብሰው ክፍል ውስጥ ሲማሩ የተለመደ ነው።
  የቀደሙት የዚህች ታላቅ አገር መሪዎች እግዚአብሄርን እጅግ አድረገው የሚፈሩ በቅዱስ ቁርባን የተወሰኑ እንዳልነበሩ የአሁኑ ዘመን መሪዎች በሰይጣን አምልኮ የተያዙና ለድንቁርናቸው አቻ የሌላቸው ፣ ከሌላ ፕላኔት የመጡ ይመስል
  ይህን ሐይማኖቱን የሚወድ፣ እግዚአብሔርን የሚፈራ ወጣት እጅግ እያስቆጡት ነው፣ ዋ! እግዚአብሔር ጅራፉን ሲያነሳ የዛኔ የማይጠቅም ለቅሶ ይሆናል! መሪዎች የድንቁርናችሁን መጋረጃ ብትገልጡት ይሻላል!!!

  ReplyDelete
 3. በአሁን ጊዜ የጾም ምግብ እንብላ ሲሉ ማበረታ ታት ይገባል ምክንያቱም ለነፍስ ቁስሎን ስለሚያድንላት ለስጋም ከ ኮልስትሮ ስለሚታደጋት ሲሆን ሌላው እውነት ደግሞ ከ1ጭልፋ ወጥ ውስጥ ከመረቅ በስተቀር 1 ፍሬ ስጋ ስለማይገኝበት ለነፍስም ለስጋም የሚበጃት ጾም ነው።

  ReplyDelete
 4. የሚገርም ነገር ነው የምንሰማውና የምናየው.እውን ይሔ ከዬኒቨሪሰቲዎቶች አሰተዳደር የሚጠበቅ ነው? እንዴት እንደተማረ ሰው ማሰብ አቃተቸው ?ከመሀከላቸውሰ እንዴት የተሻለ አሰተሳሰብ ያለው ሰው ጠፈ? እግዚኦ መሐርነ ክርሰቶሰ! ግልፅ የሆነ የሃይማኖት ጥላቻ ነው! መቼም ቢሆን ሃይማኖታችን እንደሆነ መሰቀል የበዛበት ነው. የሔ ለነሱ አይከብዳቸውም መድሃሂያለም በማያልቅብት በረከቱ ይመገባቸዋል !ይብላኝ ለነሱ እነደ ሰው ማሰብ ለተሳናቸው .ቢያሰተውሉማ የነገ የአገር ተረካቢዎች ናቸው ብለው አሰበው የጥያቄዎቻቸውን መልሰ በመለሱ ነበር! ይቺም ሰልጣን ሆና ፍርድ ማጓደል. አቤቱ ጌታ ሆይ ልቦና ሰጣቸው. ዲያቆን ዳኒ መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 5. እድሜና ጠና ይስጥህ ሀሳብህ ሁሌም ምሁራዊ ነው

  ReplyDelete
 6. በመጾም በመፀለይ ተጠቃሚው ራሱ መንግሥት መሆኑን ማወቅ አለበት ያልጾመ ያልጸለየ ትውልድ ምን እየሠራ እንደሆነ በዓለም እያየን ነው በጾም ራሱን የገዛ ሰው ለሥጋ ሳይሆን ለነፍሱ ነው የሚያደለው ስለዚህ ትውልዱ ወደ ነፍስ ሥራ ሊሠማራ ሲል አይሆንም ለሥጋ አድልዎ አድርግ ማለት የሚያመጣውን መዘዝ አለመገንዘብ ይመስለኛል ይታሰብበት ።

  ReplyDelete
 7. lega endet sanbetk mchem yorthodox fetanay bezew new lesom ymele watat sgaze mekelekelen lela tergom mestet egzaw mharen crhestose bekaceh balan!!swachacenn lebanachawen meleslachawe indsaw endyasbew amen!!

  ReplyDelete
 8. Perfect view , some times our universties did totally untagonesty things. In 2005 Ec AAU start distance education with two Australians universties which are Curtin and RMIT first degree level , most students complited the courses but no recognition from the government the main reason why they deny was students have no passport and visa .
  So for long time student faces a lot of chalanges . . .
  So D/n Daniel sometimes they don't know what and why they said NO . . .
  Anyways thanks for your perfect view . . .

  ReplyDelete
 9. ከችግሩ ገፈት ቀማሾች አንዱ እኔ ነኝ

  ReplyDelete
 10. Most of the administrators in the university did not know what they are doing, they are not knowledgeable, they are simply pupate for their party and they have also a mission against to the EOTC because they are protestant(followers of devils)!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 11. የእምነት ጉዳዮችን በምሁራዊ መንገድ በማየት መተዋወቁ ቢፈጠር ፍርሃትና ሥጋቱን ለማስወገድ በተቻለ ነበር፡

  ReplyDelete
 12. በዚህ አጋጣሚ አንድ ነገር ልበል የሰኔ ፆምን በተመለከተ በመስሪያቤት አካባቢ ያለውን ልበል ፆም የምንፆመው ለደህንነት እራስን ለመግዛት ከክፋት ለመጠበቅ ይመስለኛል ግን ፆምን እየለየን የምንፆምበት ምክንያቱ አልገባ ብሎኛል እንደሁልግዜው እንደምናደርገው አሁንም የሰኔን ፆም እንደው እንደእግዚብሔር ፍቃድ ቅዳሴው ተቀድሶ እንኳን እስኪያልቅ ድረስ ብንቆይ ብለን መቼም መፅሐፍ እንደሚለው ለአለቆቻችሁ ታዘዙ የሚለውን በመጠበብ የምሳው ሰአት ወደ ዘጠኝ ሠአስ ላይ እንድንጠቀም ብንጠይቅ የተሰጠን መልስ የሰኔ ፆም ደሞ ይፆማል እንዲ የሚል ምላሽ ሲሰጥ መከራከሩን በመጥላት ብቻ ዝም ብለን ስንቆም ከአሁን ቀደም ይፆም እንደነበርና አሁን አስፈላጊ እናዳልሆነ የራሱን ሃሳብ ብቻ ተናግሮ ጥሎን የሄደም አለቃ እንዳለ ልናገር ብዬ ነው እንደነዚህ አይነቶች ምቾት ባጋጣሚ ያጨናነቀውን ሰው ምን ትለዋለህ ከዚህ በፊት ምንም በሌለበት ጊዜ ይመስለኛል ሲፆም የነበረው በማግኘት ጊዜ እግዚአብሔር የሚከብርበትን ነገር ማድረጉ ነውር እየሆነ መጥቷል ወንድሚ ዳንኤል እኔ ግን ሁል ግዜ በምንተዳደረርበት መስሪያ ቤት ያሉ መሪዎችን ልባቸውን ለመልካም ነገር እንዲያደርጉት ዘወትር ፀሎት እያደረግሁ ነው የሰይጣን አሠራር በእንደነዚህ ያሉ ሰዎች ላይ ዝም ብለህ ታያለህ ስለዚህ ወደአማራጩ ለመሄድ ብዬ ፈተናዎችን በመታገስ እንደማንኛውም ሠራተኛ በምሣ ሰአት መጠቀሙን ተያይዤዋለው በፆምና ፀሎት ሠአት ያለው ''ፍላፃ '' ይህ ነው አልልህም ብቻ ለሁሉም ማስተዋልን ያድለው

  ReplyDelete
 13. According to The Federal Democratic Republic of Ethiopia Constitution Article 27:

  Freedom of Religion, Belief and Opinion
  1.
  Everyone has the right to freedom of thought, conscience and religion. This
  right shall include the freedom to hold or to adopt a religion or belief of his
  choice, and the freedom, either individually or in community with others, and
  in public or private, to manifest his religion or belief in worship, observance,
  practice and teaching.
  2.
  Without prejudice to the provisions of sub-Article 2 of Article 90, believers
  may establish institutions of religious education and administration in order to
  propagate and organize their religion.
  3.
  No one shall be subject to coercion or other means which would restrict or
  prevent his freedom to hold a belief of his choice.
  4.
  Parents and legal guardians have the right to bring up their children ensuring
  their religious and moral education in conformity with their own convictions.
  5.
  28/5 Freedom to express or manifest one’s religion or belief may be subject only to
  such limitations as are prescribed by law and are necessary to protect public
  safety, peace, health, education, public morality or the fundamental rights and
  freedoms of others, and to ensure the independence of the state from religion.

  ReplyDelete
 14. ስመኘው ሙንዬJune 9, 2015 at 10:46 AM

  ጥሩ ትንታኔ ነው፡፡እንደኔ የሚከተሉትን ብታክል ደግሞ የበለጠ ጥሩ ይሆናል፡፡
  1. ኢትዮጵያ እንደተጠቀሱት አውሮፓውያንና መካከለኛው ምስራቅ ሐገራት አንድ የበላይነት ያለው ባሕል፣ሃይማኖትና ትውፊት የቀረጻት ሀገር አይደለችም፡፡በሌላ አነጋገር ከነዋሪዎቿ 50 በመቶ የሆነውን ነዋሪ ማስከተል የቻለ ሃይማኖት የለም፤ብሔርም እንደዚያው፡፡ስለዚህ ቢያንስ በኦርቶዶክስና በእስልምና መካከል የቁጥር የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚካሄዱ ምሁር-ለበስ አተካሮዎች መኖራቸው ሀቅ ነው፡፡አተካሮዎቹ ወደ ትምህርት ተቋማትም እየዘለቁ በባለ አርማ ቲሸርቶች ግቢ ማጥለቅለቅን፣ፕሮቴስታንቶችም ‹‹ኢትዮጵያን ለኢሱስ›› አይነት መፈክሮችን መለጠፍን፣ተጋፊ መልእክት የተቀለሙ ነጠላዎችን ማጣፋትን፣ሁሉም ነቢያት ሙስሊሞች ናቸው አይነት ቲሸርቶችን ማስፋፋትን፣አዳዲስ ተማሪዎችን ሃይማኖታዊ ቲሸርት ለብሶ ገና ከመኪና ሲወርዱ በአቀባበል ሥም መቀራመትን፣የመሳሰሉ ፉክክሮች በዩኒቨርሲቲዎች መታዘብ ከጀመርን ቆየን፡፡
  2. ይህ ፉክክር የተጫነው ሂደት ለማንም የኢትዮጵያን መረጋጋትና ሃይማኖታዊ መቻቻል ለሚወድ ንቁ ዜጋ ምቾት የሚሰጥ አይመስለኝም--ያውም የነገይቱ ኢትዮጵያ መራህያን ይሆናሉ ተብለው በሚጠበቁ ተማሪዎች መካከል፡፡በመሆኑም መንግሥት ሂደቱን መስመር ለማስያዝና ለመግራት የጀመረው ጥረት በመሰረታዊነት ስህተት የለበትም፡፡
  3. ሆኖም በአካሄድ ረገድ መርሆዎችን እንደሚያስፈጽሙት ባለሥጣናት ዝንባሌ፣ፖለቲካዊ አተያይ፣ሃይማኖታዊ አስተሳሰብ፣ብሔር-ጠቀስ አመለካከት፣ወዘተ አፈጻጸሙ ከቦታ ቦታ መንሸዋረሩ ሊካድ አይችልም፡፡ለምሳሌ ይሄ አቤቱታ ከኦርቶዶክሳውያን ብዙ ጊዜ የሚቀርበው ከሀገሪቱ በስተደቡብ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይም በጅማ ዩኒቨርሲቲ ላይ ነው፡፡በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ያን ያህል ሲነገር አንሰማም፡፡በተቃራኒው በሀገሪቱ በስተሰሜን ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ሙስሊም ተማሪዎች የአምልኮ ቦታን በሚመለከት ተደጋጋሚ ስሞታ ያቀርባሉ፡፡እነዚህ ሁሉ ቅሬታዎች የሚመነጩት ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጫና፣ከዩኒቨርሲቲ አስተዳደሪዎች ግላዊ ድክመትና አስተሳሰብ፣በየሃይማኖቱ ካሉ አማንያን ተማሪዎች ያልተገቡ ተጋፊ ድርጊቶች ጭምር መሆኑ ነው፡፡
  4. ስለዚህ ወንድማችን ዳኒ ያነሳኻቸው አሳማኝና በበቤተክርስቲን በአዋጅ ከሚጾሙ 7 አጽዋማት አንዱ የሆነውን ጾመ-ሐዋርያት ለማሰናከል የሚደረደሩት ምክንያቶች አሳማኝ፣ምክንያታዊና ተገቢ እንዳልሆኑ ልስማማ፡፡እስማማለሁ!!በሌላ በኩል ግን ከየሃይማኖቱ አማንያን ተማሪዎች የሚታዩት ተጋፊነት ያላቸው የሃይማኖት አገላለጾች ፣የፉክክር መንፈሶች፣ለዓለምአቀፋዊና ፖለቲካዊ ሃይማኖት-ቀመስ ጫና ራስን አሳልፎ የመስጠት ዝንባሌ(ሙስሊሞች ላይ ይበረታል!)፣ነገሮችን ላልተገባ ፕሮፖጋንዳ የሚያውሉ ሃይማኖት ቀመስ ብሎጎችና ጋዜጦች አራጋቢነት(በኦርቶዶክሳውያን ይበረታል!) በመንግሥት የስልጣን ካባ ስር ተደብቀው ሕጉን ከታለመለት ዐላማ ውጭ ለጥጠው እየተረጎሙ የራሳቸውን ዐላማ ለማስፈጸሙ ከሚጣጣሩ ግለሰቦች እኩል ትኩረት ያስፈልገዋል፡፡
  5. መንግሥት ለሁሉም ነገር ብቻውን ኃላፊነት የሚወስድ አይመስለኝም፡፡ከእንደ አንተ አይነት ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ከሚዲያው፣ከማኅበረሰቡ፣ከየፖለቲካና የሃይማኖት አመራሮች ይቺን የብሔርና የሃይማኖት ዥንጉርጉርነት ያስጌጣት ሀገት ልዩነቷ ጌጡዋ ሆኖ እንዲቀጥል የሁላችንም ሚዛናዊና ከእለታዊ ስሜታዊነትና ሆታ የተሻገረ መንገድ አመላካችነት ይጠበቃል፡፡ሁሉን ነገር ከመንግሥት ፖሊሲና ስትቴጂ ጋር የተገናኘ በማስመሰል ችግሩን ላልተገባ የተቃውሞ ፖለቲካ ለማዋል ዳር ዳር ማለት ግን የዳር ዳር ባዮችን ፖለቲካዊ ዳር ዳርታ ከማመለከት ባለፈ የሚያስገኘው ሀገራዊ ጥቅም ያለ አይመስለኝም፡፡የሕገመንግስቱን አናቅጽ፣የፖሊሲና ስትራቴጅዎችን ይዘት፣የአዋጆችንና የዝርዝር ማስፈጸሚያ ሕጎችን መንፈስ፣ከሀገሪቱ በስተሰሜንና በስተደቡብ ያሉ ባለሥልጣናትን ሃይማኖታዊ አተያይና አፈጻጸም በቅጡ ሳይመረምሩ በአንድ ነጠላ ድርጊት ላይ ተመርኩዞ ኢትዮጵያ የምትከተለውን ሴኩራሊዝም ለመበየን መደርደር ችኮላና ለብ ለብ እንዳይሆን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ አይከፋም፡፡

  ሰላም ለኢትዮጵያ ከነዥንጉርጉርነቷ!!

  ReplyDelete
 15. እግዚኦ መሐርነ ክርሰቶሰ! ግልፅ የሆነ የሃይማኖት ጥላቻ ነው! በመጾም በመፀለይ ተጠቃሚው ራሱ መንግሥት መሆኑን ማወቅ አለበት ያልጾመ ያልጸለየ ትውልድ ምን እየሠራ እንደሆነ በዓለም እያየን ነው በጾም ራሱን የገዛ ሰው ለሥጋ ሳይሆን ለነፍሱ ነው የሚያደለው ስለዚህ ትውልዱ ወደ ነፍስ ሥራ ሊሠማራ ሲል አይሆንም ለሥጋ አድልዎ አድርግ ማለት የሚያመጣውን መዘዝ አለመገንዘብ ይመስለኛል ይታሰብበት ።

  ReplyDelete
 16. ይህ በደል ከሚፈፀምባቸው ተቋማት አንዱ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን መናገር ይቻላል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚማር ታናሽ ወንድሜ ግቢ ውስጥ ነጠላ ለብሶ መታየት መከልከሉንና ጾመኛ ተማሪዎች በፈቃደኝነት ለግቢ ጉባኤ የሚያበረክቱት ዳቦ መከልከሉን ሲነግረኝ በጣም ነበር የገረመኝ፡፡ እንደሚታወቀው ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ጊዜ የሚመራው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ በሆኑት ‘የጠቅላይ ሚኒስቴራችን’ ወንድም ሲሆን፣ ተማሪዎችን ሰብስበው ዩኒቨርሲቲው የሚያቀርበው ምግብ ተማሪው እምነት እንዲያስፋፋበት አሊያም ቤተ-ክርስቲያን እንዲታነጽበት አለመሆኑን፣ ስለዚህ ማንኛውም ተማሪ የቀረበለትን ምግብ ከመመገብ በስተቀር ምግቡን ይዞ መውጣትም ሆነ ለግቢ-ጉባኤ ማበርከት የተከለከለ መሆኑን ይፋዊ በሆነ ስብሰባ ላይ ነበር የተናገሩት፡፡ ይህን ጉዳይ የሰማሁት ካለፈው የትንሣዔ በዓል (ሚያዝያ 04፣ 2007 ዓ.ም.) ቀደም ብሎ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 17. GOD bless you d/n daniel kibret

  ReplyDelete
 18. በቀላሉ ችግሩን መፍታት ካቃተው ‹መካነ አእምሮ› ከሚለው ቃል ውስጥ ‹ካ› እንዲጠብቅ ያደርገዋል፡፡

  Excellent view MAy GOD BLESS U & all ur FAMILY

  ReplyDelete
 19. እግዚአብሔር ያክብርህ

  ReplyDelete
 20. we are always the wiener

  ReplyDelete
 21. geta hoy ethiopian ante tebkat endenssu hasabema behon........

  ReplyDelete
 22. "የተማሪዎችን ፍላጎቶች እንዴት ከትምህርት ቤት ፖሊሲ ጋር በተጣጣመና ማንንም በማይጎረብጥ መልኩ እንደሚያስተናግዱት አላዩምን?" Yemihedut lelemede lewuwut Sayehon Le Abel newu ! "

  ReplyDelete
 23. የጾም ምግብን ማዘጋጀት ለአንድ ዩኒቨርሲቲ ከፍስክ ምግብ ይልቅ ርካሽ ነው፡፡

  ReplyDelete
 24. በቅርብ ቀን የምሰራበት ድርጅት የእራት ግብዣ አንድ የታወቀ ሆቴል አደረገ ወቅቱ የጾምቅት መሆኑ ተረስቶ ምንም አይነት ጾም ምግብ ሳናይ ተመለስን ፡፡ በጣም አዘንኩ ብዙ ክርስቲያን ባለበት ሀገር ክርስቲያን የተረሳበት ሀገር ፡፡
  በዩኒቨርስቲ (በግቢ ጉባኤ ) በቆየሁነት አራት አመታት ጊዜያት ስራሆች ሁሉ የሚወሰኑት በተማሪሆች ዲን ግላዊነት ነው
  መመሪያው ቁራሽ ባዶ ከካፌ እንዳይወጣ ያዛል እንዳይወጣ ያዛል !! በኒ ቸርነት ነው ዳቦ ማውጣት የምትችሉት እየተባልን እየተዋሸን እየተበደልን እንገኛለን ፡፡
  በጣም የሚያናድደው ይህ ህግ ለ ኦርቶዶክስ ብቻ መሆኑ ነው ፡፡

  ReplyDelete
 25. ዳኒ በመጀመሪያ እግዚአብሄር ይባርክህ ፡፡በመቀጠል አንድ እውነተኛ ነገር ልንገርህ እኔ የተማርኩት መቀሌ ዩኒቨርስቲ ነው እናም አንተ ያነሳኸው የምግብ እና የፆም ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳው በዚሁ ዩኒቨርስቲ ነው፡፡ ይሄን ለማለት ያስደፈረኝ ነገር በወቅቱ እኔ የተማሪዎች መማክርት ውስጥ እሰራ ስለነበር በውሳኔው ላይ ትልቅ ተቃውሞ አንስተን የሚሰማን አጥተን ነበር፡፡ በእርግጥ በዚያን ጊዜ የነበረው ውሳኔ እንዳሁኑ የፆም ምግብ አይዘጋጅም አልነበረም ፤ምግብ ከካፌ አውጥቶ ወደ ዶርም መውሰድ አይቻልም፣ ነጠላ ለብሶ ግቢ ውስጥ መግባት አይቻልም ፣ ሂጃብ ማድረግ አይፈቀድም የሚል ነበር፡፡ ይሄ ከምን መጣ ብትሉኝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በፆም ወቅት 9፡00 ሰዓት ስለምንበላ ምግብ አውጥተን ዶርም እናስቀምጥ ነበር፣ሙስሊሞቹ ደግሞ የቅርጫት ኳስ ሜዳ ላይ ይሰግዱ ነበር፤ከዛ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የመማሪያ ክላስ ለፀሎት ማድረጊያ ይሰጠን የሚል ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው የማይሆነው ውሳኔ የሆነው፡፡በቃ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት የኃይማኖት እንቅስቃሴ አይደረግም ፤ ምክንያቱም ምግብ ከዶርም የማይወጣው food poison እንዳያስከትል ነው አለ መንግስት በታሪክ ግን እዛ ግቢ ውስጥ አንድም ቀን ይሄ ችግር ተከስቶ አያውቅም ፣ የጸሎት ቦታዎች የሚከለከሉት የትምህርት ተቋማት ከኃይማኖት፣ከፖለቲካና መሰል ጉዳዮች ነጻ ስለሆነ ነው አለ፡፡ ነገር ግን የነርሱ የፖለቲካ አባላት የተለያዩ የፖለቲካ ስብሰባዎችን፣ውይይቶችን በመማሪያ ክፍል ውስጥያካሂዱ ነበር፡፡ በአጭሩ ምን ለማለት ፈልጌ ነው ውሳኔው የመጣው አሁን አይደለም ከ1999ዓ.ም. ጀምሮ ነው፤ውሳኔዎቹ ግን ቀስ በቀስ ይዘታቸውን እየቀየሩ መጥተዋል፡፡ ትናንት ምግብ ይዞ መውጣት አይቻልም የተባለው ውሳኔ ዛሬ ጭራሽ የፆም ምግብ አይዘጋጅም ተብሎ መጣ ነገ ምን እንደሚወሰን ምን እናውቃለን????? እግዚአብሄር በጎውን ያምጣ እንጅ የእርሱ ነን መቼም አይተወንም፤ የጌታፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን፡፡
  ReplyDelete
 26. Very good analysis for policy makers "እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ብዙ እምነቶች፣ ባሕሎችና ልማዶች ባሉባት ሀገር፤ ሃይማኖት ትምህርት ብቻ ሳይሆን ባሕል፣ የቀን አቆጣጠር፣ አለባበስ፣ የአስተሳሰብ ቅኝትና የአነዋወር መንገድ በሆነባት ሀገር፤ በባሕልና እምነት መካከል የተቆረጠ መሥመር ለማስመር በሚያስቸግር ማኅበረሰብ ውስጥ፤ መንግሥትም ሆነ የትምህርት ተቋማት ቢከተሉት የሚመከረው ፓሲቭ ሴኩላሪዝምን ነው፡፡"

  ReplyDelete
 27. ዲ/ን ዳኒኤል ክብረት እግዚአብሔር ይባርክህ ፡፡

  ReplyDelete
 28. I graduated from Jimma tena science some 10 years ago and those Pente administrator Kora Toshine and JUMBO9 Cafeteria manager used to give all orthodox followers hard time.These two master mind of Pente leader should be kept in prison for what they did to all of us.God will punish them accordingly.

  ReplyDelete
 29. Guys do not mislead your self day after days and year after years by golden words usually told on the media of the present rulers . This was planned before 30 years ago while they were in the desert . It was a long term plan which can dissociate the generation from its root that means history, tradition and most importantly religious practices everyone . In short it was said by the leader of their party that they have easily " broke Orthodox and Amhara chauvinism " Stop the excitement on some reflection and understand the content of their detailed policy so that we can exist as a nation in the future before they destroy everything .

  ReplyDelete
 30. Dn Daniel, you have written what is in my mind!!!!!
  ዘወትር በአአእምሮዬ የሚመላለሰውን ጻፍክልኝ!!! እግዚአብሔር ልቦናቸውን ይመልሰው!!!!

  ReplyDelete
 31. ወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል ፅሁፉ አንድ ነገር አስታወሰኝ፡፡ አርሲ ውስጥ በቆጂ በሚባል ቦታ አንድ የግብርና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ነበር፡፡ የኮሌጁ ዲን ወደ አውሮፓና እሥራኤል ሄደው ተምረው የመጡ ሰው ናቸው፡፡ በዕድሜም በዚያን ወቅት ከ50ዎቹ ዘለል ያሉ ናቸው፡፡
  በኮሌጁ ውስጥ የሚማሩት ተማሪዎች በየእምነታቸው ፆም ሲመጣ ሁልጊዜ ሁከት ይነሳልና እኛ መፆም አለብን፤ ሥጋ ነክ ምግቦች ይቀነሱ የሚል ጥያቄ ሲቀርብ ጥያቄው ተገቢነት የለውም፤ የደሀ አገር ልጅ የሰጡትን ነው የሚበላው እያሉ ይመልሳሉ፤ ታዲያ ግቢ የሚማሩ ልጆች ለቤተክርስቲያን አስተዳደር አስታውቀው ቁጥራቸው ከ150 የሚዘሉት የግቢውን ምግብ ትተው ሕዝቡ ከውጭ የሚያቀብላቸውን በሶ በርበሬ ደረቅ እንጀራ ወዘተ መመገብ ቀጠሉ፤ ሰውየው ጉዳዩን የፖለቲካ አድርገው ተማሪዎቹን ማንገላታት ያዙ፤ ታላቁ አባት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ከሌሎች ብፁዓን ጳጳሳት ጋር ሆነው ዲኑን ሊያናግሯቸው መጡ፤ ሰውየው ማንን ፈርተው፤ ያንን የመሸበት ፍልስፍናቸውን ለማስተማር ሲቃጡ እኛም እንዳንተ የአውሮፓን ምድር ረግጠናል፤የምትጠቅሳቸው ሀገሮች የሰዎች ሰብዓዊ መብትና ፍላጎት የተከበረበት፣የሚበላውን አውቆ አንቦ ይዘቱን ተረድቶ የሚበላ ስለሆነ ይህን የጭቆና ቀንበርህን ከልጆቹ ላይ አውልቅ ብለው አሳምነው ተመልሰዋል፤
  ነገር ግን በወቅቱ በተማሪዎቹ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥረት ያደረጉትን ሁሉ የማይገባ ስም ሰጥተው ለብዙ ፈተና ዳርገዋቸዋልና አይረሳኝም፤
  በፅሁፍህ በጣም ረክቻለሁ፤ ከልብ አመሰግናለሁ!

  ReplyDelete
 32. G/medhin z tewahidoJuly 2, 2015 at 12:19 AM

  "if education goes wrong,nothing goes right"ያለውማን ነበር?

  ReplyDelete
 33. Dn,Daniel. Kale Hiwot Yasemalen.
  "እንዲያውም ጾም የአክራሪነት ተቃራኒ ነው." Alamawu Gin Amanawituan orthodox Tewahido emente Ke Hager Egziabeher Ethiopia Be Matefat Ena Hizibuan En Midiritun Matifate New. Neger Gine Ye Emebetachin Aserat Bekurat Yehone Hizibena Hager Ayitefafe. Yihime Yemihone Beya Hatiyat Bizate En Le Egziabeher Alemegezate Selehone Gulebetegna Gejie Yeseten. Amelake Hoyi Tareken !!!Endechernetih Newu Enji Endebedelachin Ayihu!!!..... Ebakchihu Kelebe Entselyi Hagerachine Ketifat Hizibachine Kegifegna geji Ye Kidusan Amelake. Yisewuren

  ReplyDelete