click here for pdf
ልጁ ሁልጊዜ እየመጣች ታማርራለች፡፡
ኑሮ አልተሳካልኝም፣ አልሞላልኝም፣ ባሌ ያስቸግረኛል፣ ሥራ ቦታ ሰላም የለኝም፣ ጎረቤቶቼ ረበሹኝ፣ ሕመሙ በረታብኝ፣ ገንዘቤ አልበረክት
አለ፤ ጓደኞቼ ያሙኛል፣ ልጆቼ ይበጠብጡኛል፡፡ ስለ ሸረኛ፣ ስለ መጋኛ፣
ስለ ምቀኛ፣ ስለ መተተኛ የማትለው ነገር የላትም፡፡ አባቷ የተለያዩ ታሪኮችን እየጠቀሰ ሊመክራት፣ ሊያጽናናትና ሊያበረታት ሞከረ፡፡
እርሷ ግን ማማረሯን፣ መማረሯንም አላቆመቺም፡፡ እንዲያውም ምሬቷ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ፤ ኑሮዋንም እየጠላቺው፣ ፈተናዋንም እየፈራቺው
መጣቺ፡፡
አንድ ቀን መኖር አስጠልቷት፣ ችግሩና
መከራም በርትቶባት፣ ምሬቷም ጫፍ ደርሶ መጣቺ፡፡ ‹‹በቃ ከዚህ በኋላ መኖር አልፈልግም፤ ይህንን ያህልስ እኔ ለምን እፈተናለሁ፤
ለምንስ ችግር ይበረታብኛል፤ ለምንስ ሁሉም ነገሮች ይጠሙብኛል፤ በቃ እኔ መኖር የለብኝም›› እያለች ታለቅስ ነበር፡፡
አባቷ ምክሩ ሁሉ እንዳልሠራ፣ የነገራትንም
ሁሉ እንደዘነጋቺው ተረዳ፡፡
‹‹ተከተይኝ›› አላትና ወደ ማዕድ
ቤት ገቡ፡፡
ወንበር ሰጣትና እርሱ ወደ ምግብ
ማብሰያው ሄደ፡፡ ኮመዲኖውን ከፈተና ዕንቁላል፣ ድንችና የተፈጨ ቡና ይዞ መጣ፡፡ እርሷ ግን ትዕግሥቷ አልቆ ነበር፡፡ በልቧም
‹‹እኔ ኑሮ መርሮኝ እርሱ ምግብ ሊጋብዘኝ ይፈልጋል›› ትል ነበር፡፡ ‹‹አባቴ ችግሬን አልተረዳውም ማት ነው፤ ርቦኝ የተነጫነጭኩ
መሰለው›› አለቺ፡፡ ‹‹እኔ ምግብ አልፈልግም፣ ቡናም አልጠጣም፤ በቃ እንዲያውም እሄዳለሁ›› አለቺው፡፡ ዝም አላት፡፡
ሦስቱ ምድጃዎች ላይ የሻሂ ማፍያዎችን
ጣደ፡፡ በአንደኛው ላይ ዕንቁላሉን፣ በሌላው ላይ ድንቹን፣ በሦስተኛውም ላይ የተፈጨውን ቡና ጨመረው፡፡ ከዚያም ወደ ልጁ መጣና
ከጎኗ ተቀመጠ፡፡ ‹‹ምን እየሠራህ ነው፤ የኔ ችግርና ምግብ ምን አገናኛቸው፤ ቤቴ ውስጥ ሞልቷልኮ፤ ሕጻን አደረግከኝ እንዴ፤ ዕድሌ
ነው፣ አንተ ምን ታደርግ›› ትነጫነጫለች፣ ትቆጣለች፣ ታማርራለች፡፡ አባቷ ግን ዝም ብሎ ያዳምጣታል፡፡ ማልቀስ ጀመረች፡፡ ትከሻዋን
እየደባበሰ ዝም አላት፡፡ ቃል ከአፉ አልወጣም፡፡
ውኃው መንፈቅፈቅ ጀመረ፡፡ አልፎ
አልፎም ውኃው ከመክደኛው ወጥቶ እሳቱ ላይ ሲንጠባጠብ ‹ትሽ› የሚለው ድምጽ ይሰማ ነበር፡፡ አባቷ ድንገት ቆመ፡፡ ደንግጣ እንደተቀመጠች
አቅንታ አየቺው፡፡ ‹‹በይ ተነሺ› አላት፡፡ ዘገም ብላ ተነሣቺ፡፡
‹‹ሦስቱንም የሻሂ ማፍያዎች ክፈቻቸው››
አላት፡፡
‹‹ለምን?›› አለቺ ግራ ተጋብታ፡፡
‹‹ግዴለም እሺ በይኚ››
መንቀር መንቀር እያለቺ ወደ ማንደጃው
ሄደቺ፡፡
‹‹ሦስቱም ማፍያዎች ውስጥ ያሉትን
ነገሮች አውጫቸው›› አላት፡፡ ዕንቁላሉንና ድንቹን በጭልፋ አወጣቺና ሰሐኖቻቸው ላይ አደረገቻቸው፡፡ ቡናውን ስኒ ላይ ቀዳቺው፡፡
‹‹እና ምን ይሁን?›› አለቺው
ልጁ፡፡
‹‹ድንቹን ተጫኚው፣ ዕንቁላሉን
ላጭው፣ ቡናውንም ቅመሺው››
‹‹ተመልከቺ፤ ድንቹ ውኃ ውስጥ
ከመግባቱ በፊት ጠንካራ ነበረ፡፡ የፈላው ውኃ ግን ጠንካራውን ድንች ፈረካከሰው፡፡ ዕንቁላሉ የፈላው ውኃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት
ውጩ ጠንካራ ውስጡ ግን ፈሳሽና ስስ ነበረ፡፡ ውኃው ሲፈላ ግን ውስጡ ፈሳሽና ስስ የነበረው አስኳሉ ጠንካራ ሆነ፡፡ ቡናው ሲፈላ
ቤቱን በመዓዛው ዐወደው፣ የአካባቢውንም ጠረን ቀየረው፤ ጣዕሙም ልዩ ሆነ፡፡
‹‹ሦስቱም በተመሳሳይ ማፍያ በተመሳሳይ
ዓይነት እሳት ነበር የተጣዱት፡፡ ችሀግራቸው አንድ ነው፤ ለአንድ ዓይነት ችግር የሰጡት ምላሽ ግን የተለያየ ነው፡፡ ድንቹ ጥንካሬውን
አጣ፣ ዕንቁላሉ አስኳሉ ጠነከረ፣ ቡናው መዓዛውና ጣዕሙን ይበልጥ እንዲያወጣው አደረገው፡፡ ልጄ ያንቺም ችግር ያለው ከገጠመሽ ችግርና
ፈተና አይደለም፡፡ ለገጠመሽ ችግርና ፈተና ከምትሰጪው ምላሽ እንጂ፡፡ የተለያዩ ሰዎች አንድ ዓይነት ፈተና ሊገጥማቸው ይችላል፤
እንዲያውም በኑሮው ውስጥ የማይፈተን ሰው የለም፡፡ ነገር ግን ሰዎች ለችግርና ለፈተና የሚሰጡት ምላሽ የተለያየ ነው፡፡
‹‹ፈተና አንዳንዱን እንደ ድንች
ጥንካሬውን አጥቶ እንዲፈረካከስ ያደርገዋል፡፡ አንዳንዱን ሰው ደግሞ እንደ ዕንቁላሉ ውስጡን ያጠነክርለታል፤ ሞራሉን ገንብቶ፣ መንፈሱን
ያበረታዋል፡፡ እሳት የብረትን ዝገት እንዲያስወግድ ፈተናም የአንዳንዱን የስንፍና ዝገት ያስወግድለታል፣ ውስጡን ጠንካራ ያደርግለታል፡፡
አንዳንዱ ደግሞ ችግርና መከራው፣ ፈተናና ስቃዩ ውስጣዊ መዓዛውንና ጣዕሙን እንደ ቡናው እንዲያወጣ ያደርገዋል፡፡ ውስጣዊ ችሎታውን፣
ዕምቅ ዐቅሙን፣ የተዳፈነ ተሰጥዖውን፣ ለሌሎች ሊተርፍ የሚችል ጸጋውን ያወጣለታል፡፡
‹‹ውሳኔው በእጅሽ ላይ ነው ልጄ፤
ችግር እንዳይመጣ፣ ፈተናም እንዳይኖር፣ መከራም እንዳይገጥም ተግዳሮትም እንዳይደርስ ማድረግ አይቻልም፡፡ ራስን ወይ ድንች፣ ወይ ቡና ወይም ደግሞ ዕንቁላል ማድረግ ግን ይቻላል፡፡››
ልጁ ጉንጩን ስማው አንገቷን እየነቀነቀች
ወጣች፡፡ ውስጧም ‹ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና› ይል ነበር፡፡
source; philosophical short stories
source; philosophical short stories
girum eyta new dani
ReplyDeleteልጁ ጉንጩን ስማው አንገቷን እየነቀነቀች ወጣች፡፡ ውስጧም ‹ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና› ይል ነበር፡፡
ReplyDeleteይገርማል ብልህ መካሪ አያሳጣን።
Thank you dani betam amesegenalehu.endeterdahutem bemangnawm fetna dench alemehon enj mtenkerem lelelaw araya mehonem(ende buna meshtet) yechalale denech kemehon yadenen.
ReplyDeletewow wow wow very nice history....
ReplyDeleteamazing
ReplyDeleteThanks God. I have learned a lot from this article as my work place is so bad that I presumed, I can't bear it. But now on i will tolerate with God. Thank you again.
ReplyDelete‹‹ፈተና አንዳንዱን እንደ ድንች ጥንካሬውን አጥቶ እንዲፈረካከስ ያደርገዋል፡፡ አንዳንዱን ሰው ደግሞ እንደ ዕንቁላሉ ውስጡን ያጠነክርለታል፤ ሞራሉን ገንብቶ፣ መንፈሱን ያበረታዋል፡፡ እሳት የብረትን ዝገት እንዲያስወግድ ፈተናም የአንዳንዱን የስንፍና ዝገት ያስወግድለታል፣ ውስጡን ጠንካራ ያደርግለታል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ችግርና መከራው፣ ፈተናና ስቃዩ ውስጣዊ መዓዛውንና ጣዕሙን እንደ ቡናው እንዲያወጣ ያደርገዋል፡፡ ውስጣዊ ችሎታውን፣ ዕምቅ ዐቅሙን፣ የተዳፈነ ተሰጥዖውን፣ ለሌሎች ሊተርፍ የሚችል ጸጋውን ያወጣለታል፡፡
ReplyDeleteአቤት የዛሪው መልእክትህ ደግሞ በጣም የሚገርም ነው ስለፈተናው አበዛዝ ብዙም አይገርመኝም ማንቀላፋት ሲመጣ እንድንነቃ የሚያደርጉ ደውሎች ከየአቅጣጫው ይመጣሉ በሚለው ስለምረዳ ግን ትርጓሚው ፣ አባትየው የፈጠሩት መላ ፣ የልጃቸውን የውስጥ ጫጫታ እንዲት አድርገው ቢያዳምጡት ነው ይህንን መላ የፈጠሩት አቤት ከእንደዚህ አይነት ቤተሰብ መፈጠር በራሱ አድሜ ይቀጥላል በጣም ደስ የሚል መልእክት ነው እግዚአብሔር ይባርክህ እኔም ዛሪ እኔ በሌለሁበት ያማኝ አለቃዬ ነገር ቢያበሳጨም መልእክትህ እኔንም ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና እንዲል አድርጐታል ተባረክ
ReplyDelete‹‹ሦስቱም በተመሳሳይ ማፍያ በተመሳሳይ ዓይነት እሳት ነበር የተጣዱት፡፡ ችሀግራቸው አንድ ነው፤ ለአንድ ዓይነት ችግር የሰጡት ምላሽ ግን የተለያየ ነው፡፡ ድንቹ ጥንካሬውን አጣ፣ ዕንቁላሉ አስኳሉ ጠነከረ፣ ቡናው መዓዛውና ጣዕሙን ይበልጥ እንዲያወጣው አደረገው፡፡ ልጄ ያንቺም ችግር ያለው ከገጠመሽ ችግርና ፈተና አይደለም፡፡ ለገጠመሽ ችግርና ፈተና ከምትሰጪው ምላሽ እንጂ፡፡
ReplyDeletewow great!!!
ReplyDeleteEgziabehere yebarkehe Decon Daniel.ene gene endedenech eyehonku techegrealehu ena kene yeberetachu asebugne beselotachu!
ReplyDeleteselam deyakoni dear Daniel kibret kale hiwot yasemalini
DeleteYou customized well and very interesting.
ReplyDeleteበጣም በከፋኝ ሠዓት ስለሆነ ይህን ፅሁፍ ያነበብኩት እግዚአብሐር ይስጥህ ተስፋ ከመቁረጥ አድኖኛል፡፡ ቃለ ህይወት ያሰማልኝ!!!
ReplyDeleteGood way of teaching.
ReplyDeleteWritten for me!!!
ReplyDeleteright article on the right time for me
ReplyDeleteThanks. Keep it up!
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን። ዲ/ን ዳኒ እድሜና ጤና እመኝልሃለዉ። Just as before (1988/89 E.C) at AAU, you are still teaching us. Keep up the good work.
ReplyDeleteMy site is provides the best villas to rent for you.Villas to rent
ReplyDeletethank u
ReplyDeleteEdge
ReplyDeleteዲ ዳንኤል ረጅም እድሜ መልካም ጤንነት እግዚአብሔር ያድልህ በመድረክ ቆመህ የምታስተምረው በፅሑፍህ የምታስተላልፈው ጥብቅና ግልፅ መልእክት ሰውን ያንፃል እውቀት ይጨምራል ያረጋጋል ያስታርቃል ያፅናናል ማስተዋልን ይሰጣል ሀገራችን እንደአንተ ያሉ ቢበዙላት መታደል ነበረ ከላይ በምሳሌ ያስተላለፍከው መልእክት ሁሉንም የሚመለከት ይመስለኛል የማይፈተን የማያማርር የለም እናቱ ውሀ ልትቀዳ የሔደችበትም እናቱ የሞተችበትም ( ዘዘገኑ ወርቀ ወዘኢዘገኑ ክልኤሆሙ ህቡረ ኃዘኑ ) እንደተባለው ሆነናልና ሁሉ እያማረረ የሚያረጋጋ በሚቸግርበት ጊዜ የምታስተላልፈው በሳል መልእክት ብዙዎችን ይጠቅማልና በርታልን አክባሪህ ከሴንትሊውስ
ReplyDeleteዲ ዳንኤል ረጅም እድሜ መልካም ጤንነት እግዚአብሔር ያድልህ በመድረክ ቆመህ የምታስተምረው በፅሑፍህ የምታስተላልፈው ጥብቅና ግልፅ መልእክት ሰውን ያንፃል እውቀት ይጨምራል ያረጋጋል ያስታርቃል ያፅናናል ማስተዋልን ይሰጣል ሀገራችን እንደአንተ ያሉ ቢበዙላት መታደል ነበረ ከላይ በምሳሌ ያስተላለፍከው መልእክት ሁሉንም የሚመለከት ይመስለኛል የማይፈተን የማያማርር የለም እናቱ ውሀ ልትቀዳ የሔደችበትም እናቱ የሞተችበትም ( ዘዘገኑ ወርቀ ወዘኢዘገኑ ክልኤሆሙ ህቡረ ኃዘኑ ) እንደተባለው ሆነናልና ሁሉ እያማረረ የሚያረጋጋ በሚቸግርበት ጊዜ የምታስተላልፈው በሳል መልእክት ብዙዎችን ይጠቅማልና በርታልን አክባሪህ ከሴንትሊውስ
ReplyDeleteሰላም ዲያቆን ዳኒ, ቃለ ህይወት ያሰማህ! ችግራቸው ለዘላለም እንደሚኖሩ አድርገው ማሰባቸውና ምንም አይነት ፈሪሃ እግዚሃብሔር ሰሌላቸው ነው.ብዙ ሊያደርጉላት የሚችሉትን አገር ቀብረዋት የቀሩት. አንድ ቀን የህዝቧን ጩኀት የሚሰማ መሪ ይኖረናል ተሰፋ አንቆርጥም. ይብላኝ ለነሱ የሰላም እንቅልፍ ሳይተኙ ለሚኖሩ . ዲያቆን ዳኒ, መድሃሂያለም ባለህበት ይጠብቅህ አሜን!
ReplyDeleteአት ስረቅ ይላል ቃሉ ምንጭ ሳትጠቅስ መጻፍ ነውር ነው!!!
ReplyDeletehttp://ecumenicalwomen.org/2010/01/09/are-you-an-egg-a-potatoe-or-a-coffee-bean/
ወዳጄ እኔኮ በጽሑፉ መጨረሻ ዋናውን ምንጭ ጠቅሼልህ ነበር፡፡ አንተ የጠቀስከው ሁለተኛ ምንጩን ነው፡፡ ለወደፊቱ እስከ መጨረሻው ሳታነብ አትፍረድ፡፡
DeleteFirst of all, dani god bless u and give peace for better work , really life changing advice amazing
DeleteEyob, did you want to tell us you read it from the source? Unfortunately, you quoted a second source.
DeleteIt's like me quoting Dn Daniel's blog as a source for this specific story.
እዮብ ብርሀን ‘የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል!!!!!!!!!!!!’ አደራ ምንጭ እንዳትለኝ ሲሉ ሰምቼ ነው፡፡ለማውራትና ለመክሰስ የፈጠነ ትውልድ ቢኖር ይሄኛውን ትውልድ የሚያክለው የለም፡፡
Deleteእዮብን ለወደፊቱ እስከ መጨረሻው ሳታነብ አትፍረድ ብለሃል፡፡ ንግግርህ ጉንተላ አለው ፡፡ እስከ መጨረሻ አንብቦ ነገር ግን ልብ ሳይል ቀርቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም እንደ እኔ በፒዲኤፍ አውርዶ አንብቦ ከሆነ ደግሞ የወጉ ምንጭ እዚያ ላይ የለም/አልወጣም/አልተጠቀሰም፡፡ እሱም ሁሉን አማራጭ ሳይመለከት ፈረደ አንተም እስከ መጨረሻው አላነበብኩትም እስካላለ ድረስ በግምትህ እርግጠኛ ሆነህ ሳታነብ አትፍረድ ብለህ ፈረድክበት፡፡
Delete‹‹ፈተና አንዳንዱን እንደ ድንች ጥንካሬውን አጥቶ እንዲፈረካከስ ያደርገዋል፡፡ አንዳንዱን ሰው ደግሞ እንደ ዕንቁላሉ ውስጡን ያጠነክርለታል፤ ሞራሉን ገንብቶ፣ መንፈሱን ያበረታዋል፡፡ እሳት የብረትን ዝገት እንዲያስወግድ ፈተናም የአንዳንዱን የስንፍና ዝገት ያስወግድለታል፣ ውስጡን ጠንካራ ያደርግለታል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ችግርና መከራው፣ ፈተናና ስቃዩ ውስጣዊ መዓዛውንና ጣዕሙን እንደ ቡናው እንዲያወጣ ያደርገዋል፡፡ ውስጣዊ ችሎታውን፣ ዕምቅ ዐቅሙን፣ የተዳፈነ ተሰጥዖውን፣ ለሌሎች ሊተርፍ የሚችል ጸጋውን ያወጣለታል፡፡
ReplyDeleteThis was just what I needed sitting where I work and thinking about my life. Much Thanks to Diaqon Daniel from USA.
ReplyDeleteመልካም ምክር ዲያቆን
Deleteመልካም ምክር ነው እግዜር ይስጥልን
ReplyDeleteመልካም ምክር ነው እግዜር ይስጥልን
ReplyDeleteበጣም እናመሰግናለን @ዳንኤል ክብረት። የሁልግዜ ተከታታይህ ነኝ እና ቀጥልበት እኛ እንድንበረታ እና ኣካባቢያችን እንድንገነዘብ የምታደርገው ጥረት እጅግ በጣም እናመሰግናለን እግዚኣብሄር ካንተ ጋ ይሁን
ReplyDeleteልጄ፤ ችግር እንዳይመጣ፣ ፈተናም እንዳይኖር፣ መከራም እንዳይገጥም ተግዳሮትም እንዳይደርስ ማድረግ አይቻልም
ReplyDeleteዳን እግዚአብሔር ጥበቡን አብዝቶ ይጨምርልህ፤ ራስን ወይ ድንች፣ ወይ ቡና ወይም ደግሞ ዕንቁላል ማድረግ ግን ይቻላል፡፡›› የሚገርመው እንደዚህ አይነት መፍትሄና ሀሳብ የሚሰጥ ፣ የሚናገርና የሚያሳይ አባት ማግኘት በራሱ እድለኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡ የዛሬ አባቶች ልጅን ይዞ በየመጠጥ ቤት ነው የሚገኙት፡፡ አዝናናሁ ብሎ ሰካራም፣ አጫሽና፣ ቃሚ ትውልድ የሚያፈሩ አባቶችን ማየት ልማድ ሆኗልና ማስተዋል ይስጥልን እላለሁኝ፡፡
ReplyDeletebetam asdesach timhirt.
ReplyDeleteጥሩ ትምህርት ነው የውሰድኩበት። እግዛብሄር ይባርክህ
ReplyDeleteበጣም የሚገርም ምክር ነው፡፡ Thank you Dani. God bless you.
ReplyDeleteበስራ ሰአት ከስራ ውጪ ምንም ነገር አላይም ፣፣ስራዬን ስለማከብር ..እግዚአብሄር ይክበር ስራም አክብሮኛል፣ሆኖም በዚች ቅጽበት በጣም ያዘንኩባት ቅጽብ ነበረች ..በቃ የዳንኤል እይታን ከፈትኩ …እንቁላልና ድንች .ቡና…ቀደም ሲል በአንድ ስልጠና የሰማሁት ቢሆንም ዛሬ በለየ መልኩ ለኔ ተጽፎ አገኘሁት..
ReplyDeleteእናም ተጽናናሁ ..
..ሁሌም ማስተዋልን ነው የምለምነው..ከጤና ቀጥሎ ..ሌላው በጊዜው ይመጣል…
እግዚያብሄር ማስተዋልህን ያብዛልህ !!!!!!!!!!
Z
that is nice really.add like this.just like me they may get a solution.
ReplyDeleteDn,Daniel. Kale Hiwot Yasemalen. Endetelmedwu Yemigerm Eyita, Behiwot zemen hulu fetenawochi seagetimugne end denech ehonena. Be egziabehr cherenet bekidusanu amalagnenet wode enkulalu emelesalehu. Neger gin end bunawu meaza lemhone alechalkum lelelawu mesale lemehon alchalekum ena. kene yeberetachu asebugne beselotachu.
ReplyDeletesenay timhrt
ReplyDeleteBemekera yalteftne hiwot bebiet wist yadege tekil malet new wubet enji tinkarie yelewum
ReplyDeleteamazing
ReplyDeletewow dani your are gift for this generation. i wish long life for you.
ReplyDeleteDiakon Daniel Edmena Tena Yestehe Eneme Endesuwa Bizu techgere nebre ahune tenesh tekrefolegne
ReplyDeleteEyob minch ateqaqeseh yeteshale new. Ato Daniel ke Eyob misgana bayqerbleh guntelaw lemin asfelege? kegnehin lemeta girahin sitew new qalu?
ReplyDeleteየተጠቀሰው ወግ አንድ ተመሳሳይ ችግር በተለያዩ ሰዎች የሚሰጠውን ምላሽ የሚያሳይ ጥሩ ምክርና መንፈስን የሚያፀና ነው፡፡
ReplyDeleteየተለያየ ችግር የተለያዩ ሰዎች ላይ ሲደርስ ለምሳሌ ድንችን በቢላዋ ቢከተፍ፣ ዕንቁላል በማንኪያ ቢመታ እና ቡና በዘነዘና ቢወቀጥ የሚሰጡት ምላሽና ውጤት ከተጠቀሰው ወግ በተለየ መልኩ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ እንደ ችግር ለምን እንደደረሰብን በጥሞና ብንመለከት የተሸለ ይመስለኛል፡፡ ከባዱ መንገድ ቢሆንም የተሻለ ይመስለኛል፡፡
What an amazing topologic thought!!!
ReplyDeleteThanks You Very Much
ReplyDelete