Tuesday, June 16, 2015

ይህም ያልፋል


አንድ ንጉሥ አማካሪዎቹን ሰበሰበና እንዲህ ሲል አዘዛቸው፡፡ ‹‹ስከብርም ሆነ ስዋረድ፣ ሳገኝም ሆነ ሳጣ፣ የሁሉም የበላይ ስሆንም ሆነ የበታች፣ እጅግ ስደሰትም ሆነ ስከፋ፣ ድል ሳደርግም ሆነ ድል ስሆን፣ ዝናዬ ሲናኝም ሆነ ሲከስም፣ ያንን ነገር በሰላምና በጥበብ እንዳልፈው የሚያደርግ አንድ ዐረፍተ ነገር ስጡኝ፡፡ ላስታውሰው የምችል፣ መንገዱንም የሚመራኝ፣ ከልክ አልፌ እንዳልሄድ፣ ከልክ ወርጄም እንዳልወድቅ፣ የሚያደርግ አንድ ዐረፍተ ነገር አምጡልኝ፡፡ የተወሳሰብ ፍልስፍና አልፈልግም፣ ቀላልና ግልጽ የሆነውን እሻለሁ፡፡ ይህንን ሳትይዙ እንዳትመለሱ››

አማካሪዎቹ ከቤተ መንግሥቱ ወጥተው ለአራት ወራት ያህል መከሩ፡፡ አነሡ ጣሉ፤ በመጨረሻም የደረሱበትን ሐሳብ በብራና ጽፈው ወደ ንጉሡ ዘንድ መጡ፡፡ የተጠቀለለውንም ብራና ሰጡት፡፡ ንጉሡም ገለጠና አነበበው፡፡ እንዲህ ይል ነበር ‹‹ይህም ያልፋል››፡፡
ለምን? አላቸው ንጉሡ፡፡


በየትኛውም የሥልጣንና የሀብት ከፍታ ላይ ብትሆን፣ በየትኛውም የዝናና የክብር ሠገነት ላይ ብትደላደል፣ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ ካሰብክ ግፍ አትሠራም፣ ፍትሕ አታዛባም፣ ድኻ አትበድልም፣ ከልክህም አታልፍም፡፡ ራስህን ዘላለማዊ አድርገህ ካሰብክ፣ ጊዜ የማይቀየር ዓለምም የማትዞር ከመሰለህ ግን ራስህን ለማስተካከል እንኳን ጊዜ ሳታገኝ ነገሮች ይቀየሩና በሠራኸው ወኅኒ ትወረወራለህ፣ ባወጣኸው ሕግ ትቀጣለህ፣ በቆረጥከው ዱላ ትመታለህ፣ ባሳደግከው ውሻ ትነከሳለህ፡፡ ስለዚህ አሁን የተቀመጥክበትን ዙፋን፣ የምታንቀጠቅጥበትንም ሥልጣን፣ ‹ይህም እንኳን ያልፋል› ብለህ አስበው፡፡

ተቀናቃኞችህን ድል እንዳደረግክ፣ አገሩን ጠቅልለህ እንደያዝክ፣ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ እንደሆነ፣ በለስ እንደቀናህ፣አንደኛ እንደወጣህ፣ እንደ ተጨበጨበልህ፣ እንደታፈርክና እንደተከበርክ፣ አትቀርም፡፡ ይህም በጊዜው ያልፋል፡፡ እነዚህ ዛሬ በዙሪያህ ሆነው የሚያፍሱልህ የሚያጎነብሱልህ፣ ሳታስነጥስ ይማርህ፣ ሳትወድቅ እኔን የሚሉህ፤ ሳይበርድህ ካልደረብንልህ ሳታዝን ካላለቀስንልህ የሚሉህ፤ ሳትጠራቸው አቤት፣ ሳትልካቸው ወዴት የሚሉህ፣ ይኼ ሁሉ ሲያልፍ ያልፋሉ፡፡

ካንተም በፊት ሌሎች ነበሩ፣ ካንተም በኋላ ሌሎች ይመጣሉ፡፡ ከፊትህ ሌላ ባይኖር ኖሮ ከኋላህ ሌላ ባልመጣም ነበር፡፡ በጊዜ ውስጥ ትናንት ዛሬና ነገ አሉ፡፡ ዛሬ ትናንት፣ ነገ ዛሬ እየሆኑ ያልፋሉ፡፡ አንተ ሌሎችን እንደተካህ ሁሉ የሚተካህም የግድ ይመጣል፡፡ አንተ ሌሎችን እንደረታህ ሁሉ የሚረታህም ነገ ይመጣል፡፡ አንተ ሌሎችን እንዳሠርክ ሁሉ የሚያሥርህም ነገ ይመጣል፡፡ አንተ እንደቀበርክ ሁሉ ቀባሪህም ነገ ይመጣል፡፡ እስኪ ለቀስተኞችን እይ፤ የዛሬ ቀባሪ ሁሉ ነገ በተራው ተቀባሪ ነው፡፡ ማንም ራን የሚቀብር የለም፡፡ ሌላውን እንደቀበረ ሁሉ እርሱን ሌላ ይቀብረዋል እንጂ፡፡ ‹ይህም ሁሉ ያልፋል› ብለህ ካሰብክ ሁሉን በልኩ፣ ሁሉን በደንቡ ታደርገዋለህ፡፡

የሌሎችን ታሪክ አጥፍተህ፣ የሌሎችን ሐውልት ሰብረህ፣ የሌሎችን ዋጋ አርክሰህ፣ የሌሎችን ስም ገድለህ መኖር ትችላለህ፤ ዐቅሙና ሥልጣኑ እስካለህ ድረስ፡፡ ነገር ግን ይህም ያልፋል፡፡ ያንተንም ታሪክ የሚያጠፋ፣ ያንተንም ሐውልት የሚሰብር፣ ያንተንም ስም የሚያጎድፍ፣ ያንተንም ዋጋ የሚያረክስ በተራው ይመጣል፡፡ የሚተካህን የምትፈጥረው ዛሬ በምታደርገው ተግባር ነው፡፡ ክፉ ከሆንክ ክፉ ይተካሃል፣ ርቱዕ ከሆንክ ርቱዕ ይተካሃል፡፡    

ይኼ ሁሉ ዓለም አልፎ ብትወድቅ፣ ብትሰበር፣ ብትታሠር፣ ብትረሳ፣ ብትሰደድ፣ ብታጣ፣ ብትነጣ፣ ከላይ ወደታች እንዳየኸው ሁሉ ከታች ወደ ላይ የምታይበት ዘመን ቢመጣ፣ ያሰብከው ቀርቶ ያላሰብከው ቢሆን፣ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ አስብ፡፡ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ ካሰብክ ተሥፋ አትቆርጥም፣ ነፍስህ ሳትወጣ አትሞትም፣ ራስህን ለብስጭትና ንዴት፣ ለቁጣና ትካዜ አሳልፈህ አትሰጥም፡፡ ከሞት በኋላ ትንሣኤ፣ ከእሥር በኋላ መፈታት መኖሩን ታያለህ፡፡ የድል ጫፉ ሽንፈት እንደሆነው ሁሉ የሽንፈት ጫፉ ድል ነው፡፡ የሥልጣን ጫፉ መውረድ እንደሆነው ሁሉ የውርደት ጫፉ ሥልጣን ነው፡፡ የብርሃን ጫፉ ጨለማ፣ የጨለማም ድንበሩ ብርሃን ነው፡፡ የበሽታ ጫፉ ጤና፣ የጤናም ጫፍ በሽታ ነው፡፡

ዓለም ቋሚ አይደለቺም፡፡ ጊዜ ወደ ፊት ብቻ ነው የሚሄደው፡፡ እሥር ቤቱ ሲተከል የነበሩት አሁን የሉም፤ ስለዚህም አንተም እዚያ እሥር ቤት አትኖርም፡፡ ችግር ሲጀመር የነበሩት አሁን የሉም፤ አንተም ችግር ውስጥ የግድ አትሰምጥም፡፡ እንደሚያልፍ ካመንክ፡፡ እንደሚያልፍ ካመንክ ለማሳለፍ ትጥራለህ፡፡ እንደሚያልፍ ካላመንክ ግን ያለህበትን ትቀበለዋለህ፡፡ የተቀበልከውን ነገር ደግሞ አትለውጠውም፡፡ ችግርን ያልፋል ብለህ ከተቀበልክ ወደ ውጭ ታያለህ፣ ወደ ውጭ ታስባለህ፣ ወደ ውጭም ትመኛለህ፡፡ ከአጥሩና ከድንበሩ አልፈህ ታልማለህ፡፡ ሰው የሚኖረው ከሥጋው በላይ በኅሊናው ነው፡፡ ውድቀት በሥጋ መኖር ሲጀመር ይመጣል፡፡ ክብርና ድል ደግሞ በኅሊና መኖር ሲጀመር ይመጣሉ፡፡

እባብ ሲደበደብ ራሱን ይከላከላል፡፡ ለምን? ራሱ ካለ የተቆረጠ አካል ቢኖረው እንኳን ይቀጠላል፣ የተጎዳ አካል ቢኖረው እንኳን  ይፈወሳል፡፡ ራሱን ከተመታ ግን አለቀለት፡፡ ሰውም ኅሊናውን ከተመታ ሞተ ማለት ያን ቀን ነው፡፡ ኅሊናህ እንዳይመታ ከፈለግክ ‹‹ይህም ያልፋል› ብለህ አስብ፡፡ የቆምክበት ቦታና ጊዜ አስመራሪ፣ አታካች፣ አንገሽጋሽ፣ ከባድና ጽኑ ቢሆን እንኳን ግን ያልፋል፡፡ አንተ ያንን መከራ እየቀመስክ ባለህበት ጊዜ እንኳን እያለፈ ነው፡፡

ለዚህ ነው ይህንን የሰጠንህ፡፡ በጥጋብም ሆነ በረሃብ፣ በሀብትም ሆነ በድህነት፣ በሥልጣንም ሆነ በውርደት፣ በድልም ሆነ በሽንፈት፣ በጤናም ሆነ በሕመም፣ በዝናም ሆነ በክስረት፣ የሚመጣ መከራ አለ፡፡ ከዚያ መከራ መውጣት ከፈለግክ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ አስብ፡፡ ይኼ መንገዱን መመልከቻ መነጽርህ ነው፡፡ ከሠገነቱ እንዳትወድቅ መውረጃህ፣ ከጉድጓዱም እንድዘቅጥ መውጫህ መሰላል ነው፡፡

ንጉሡ ምክራቸውን ሰምቶ በቤተ መንግሥቱ፣ በፍርድ ቤቱ፣ በግብዣ ቤቶቹ፣ በባለሥልጣናቱ እልፍኞች፣ በጦር አዛዦች ሠረገሎች፣ በባዕለ ጸጎች አዳራሾች፣ በወኅኒ ቤት ግድግዳዎች፣ ‹‹ይህም ያልፋል› የሚለው ምክር እንዲለጠፍ አዘዘ፡፡ እርሱም ሲነጋ ሲጠባ፣ ሲወጣና ሲገባ፣ ሲፈርድና ሲወስን ሁሌ ያየው ጀመር፡፡ ‹ይህም ያልፋል› እያለ፡፡

64 comments:

 1. ድንቅ መልዕክት
  ቃለ ህይወት ያሰማልን
  ግዜክስ

  ReplyDelete
 2. astewy kale telek tmhert new, Emebete dengel mariam bemeljawa atlyh. Amen

  ReplyDelete
 3. ዲያቆን ዳኒ, ቃለ ህይወት ያሰማህ! ልብ የሚነካ ዕይታ ነው.ቢነበብ ቢነበብ የማይሰለች ግሩም የሆነ አመለካከት ነው. እውነትም "ይህም ያልፉል" አቤቱ አምላካችን ሆይ ለሁለችንም የሰማነውን በልቦናችን አሳድርብን. ለሀገር መሪዎች ለሃይማኖት አባቶች ይህም ያልፉል እያሉ ህዝቡን ሳይበድሉ ፍርድ ሳያጓድሉ የሚመሩበትን ልቦና ሰጣቸው.ዲያቆን ዳኒ ,መድሃሂያለም ይጠብቅህ.አሜን!!!

  ReplyDelete
 4. Ewnetm yihem yalfal.

  ReplyDelete
 5. ይህም ያልፋል፣ ያም ያልፋል፣ ሁሉም ያልፋል።የሰው ልጅ ሕሊናውን ሸጦ አንድ ቀን ለዘለዓለሙ ላይመለስ የሚያልፍ መሆኑን ዘንግቶ በሌላው ወገኑ ላይ ግፍ ይፈፅማል፣ ይገላል፣ ያሰቃያል፣እጅግ ዘግናኝ የሆነ ኢሰባዊ ድርጊት ይፈፅማል፣ አንድ ቀን ግን ለዘለዓለሙ ይጠፋል፣ ይረሳል፣ የፈጸመው ክፉ ስራው ግን በቀጣዩ ትውልድ በክፉ ይነሳል።
  እነ ዲዮቅልጥያኖስ በዘመኑ በነበሩ ክርስቲያኖች እንደዚያ በሰው ልጅ ታሪክ ተሰምቶ የማይታወቅ ዘግናኝ ነገር ሲፈፀሙ፣ በአገራችን በመካከለኛው ዘመን የነበሩ ነገሥታት በገዳማውያኑ በቅዱሳኑ ላይ ያን ሁሉ ግፍ ሲፈፅሙ የማያልፉ ለዘለዓለሙ የሚኖሩ መስሏቸው ይሆን? እነ ሂትለር በዘመናዊ የሰው መግደያ ማሽን ያን ሁሉ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሲደመድስሱ ነገ ለዘለዓለም ላይመለሱ እንደሚጠፉ የሚያስብ አእምሯቸውን የት አስቀምተውት ይሆን?

  የእምነት መሪዎችስ እናስተዳድረዋለን የሚሉትን እምነት ረስተው የፖለቲካ መሳሪያ ሲሆኑ አንድ ቀን ከተደላደለ ስጋዊ ኑሯቸው እንደሚለዩ እንዴት ሊረሱ ቻሉ? ሮማዊው ፖፕ የጣሊያንን ታንክ ባርከው የኢትዮጵያ ክርስቲያኖችን እንዲገድል፣ ገዳማቶቻንንና ታሪካችንን እንዲያጠፉ ወታደሮችን ሲልኩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ለዘለዓለም እንደሚያሸልቡ እንዴት ሊረሱ ቻሉ? ፓትርያርክ ጳውሎስ በሥልጣን ልይ በነበሩባቸው በርካታ አመታት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምንኩስና ቆብ ባጠለቁና መስቀል በያዙ ግን ምንም አይነት እምነት በሌላቸው ኢአማንያን ሰዎች እንደዚያ ስትመዘበር፣ የሌላ ቤተ እምነት ሰዎች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአመራር ቦታ ተቀምተው በእናታችን ላይ እንደዚያ ሲያላግጡ አቡኑ ግን ምንም ዴንታ ያልሰጣቸው፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በባእዳን እና ኢአማነያን የምትመራ እስክትመስል ድረስ ያለ ሁሉ ግፍና ሰቆቃ ሲፈፀም እያዩ ምንም ትንፍሽ የማይሉ እንዲያውም መከራው እንዲፋፋም ግፊት ያደርጉ የነበሩ የሚመስሉ፣ ለዘለዓለሙ ላይመለሱ ሲጠሩ ሁሉም እንደሚያልፍ በመጨረሻ ሰአት ትዝ ብሏቸው ይሆን? አባ ማትያስ በየቀኑ በዘመኑ የመረጃ መረብ እንደምንሰማው ከሆነ በሚሰሩት ግፍ እና ሰቆቃ ከቀዳሚያቸውም ፓትርያርክ አባ ጳውሎስ በክፉ ሥራቸው የባሱ እንደሆነ ነው ትውልዱ እየሰማ እያየ ያለው፣ በፌስቡኩ አለም ኦርቶዶክሳዊው ወጣት አንድም ቀን አባ ጳውሎስን በመልካም ነገር ሲያነሳቸው አይቼ አላውቅም፣ የክፉ ነገር ተምሳሌት ሆነው እንጂ። በሌላ መልኩ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ ትውልድ እድሜያቸውን እና ሕይወታቸውን ሁሉ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰጥተው እውነተኛ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባት ሆነው ያለፉትን ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳን
  ለእሳቸው ካለው ፍቅር የተነሳ ምስላቸውን ፕሮፋይል ምስል በማድረግ፣ ጊዜ የማይሽራቸውን የጹሑፍ፣ የድምፅና የቪዲዮ ትምህርቶቻቸውን በመማማር ፣ በተለያየ መልኩ አሁን ካረፉ ከሦስት አመት በኋላም ቢሆን ህያው የሆነ ቅዱስ ሥራቸውን ልክ እንደ አዲስ ይዘክራል፣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አሁን እንደመናየው የአባ ጳውሎስ ስም ለዘለዓለም በትውልድ ዘንድ ይረሳል ብዬ አስባለሁ። ይህንን ጉዳይ አባ ማትያስ ያስተውሉታል ብዬ እገምታለሁ። አባ አሁን ያሉበት የሥልጣን ቦታ፣ አሁን የሚያዙበት ከድሀ ልጆቿ የተሰበሰበው ገንዘብ፣ አሁን በዙሪያዎ የከበቡዎት የተሐድሶ መናፍቃን፣በዙሪያዎ ሆነውየሚያጨበጭቡለዎት የማያምኑ ሰዎች ያልፋሉ። አባ ጳውሎስ በሚችሉት መጠን ሁሉ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሊያጠፏት ሞከሩ ግን ግን እሳቸው ጠፉ! ለዘላለም ላይመለሱ ሄዱ፣ እናታችን ግን አለች፣ ለዘላለም ትኖራለች። አባ ማትያስ እባክዎን ልለምንዎት፣ ሁሉም ያልፋል የሚለውን ጹሑፍ በትልቁ አስፅፈው በቢሮዎ፣ መኪናዎ ውስጥ፣ መኝታ ክፍልዎ ውስጥ፣ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ከምንም በላይ አእምሮዎ ውስጥ ያስቀምጡት፣ እዚህ ሥልጣን ላይ የሚቆዩበት ጊዜ ከነፍስ ዘላለማዊነት ጋር ሲነፃፀር ዜሮ አመት ነው ማለት ይቻላል፣ እባክዎን የታላቁን ሰው የሰለሞንን መጽሐፈ መክብብን እንዲያነቡት ልለምንዎ። ከፀሐይ በታች ያለው ነገር ሁሉ ከንቱ ነው፣ ሁሉም ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው ... ሁሉም ያልፋል!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኢያረምም ህየንተ ጳውሎስ ፓትርያርክJune 17, 2015 at 10:03 AM

   ወንድም ማሩ-አማተሩ፡- ያንተ በፌስቡክና በኢሚዛናዊ ብሎግ ላይ የተመሰረተ ሐሜትና ሥም ማጥፋትም ያልፋል!!!የአባቶቻችን ሚዛን ፌስቡክና ብሎግ የሆነ ቀን ነው ነገሩ የተበላሸው፡፡የባከነ ትውልድ!!!ቀናኢነትና ቅናት፣ብሎግና ብልግና፣ቅሬታና ነቀፌታ፣ተቆርቋሪነትና ቆርቋሪነት፣ሊቅነትና ልቅነት፣ማነጽና ማመጽ፣መስበክና መስበቅ፣ወንጌልና ወንጀል…ያልለየ አማተር የእውቀት ጣራ ላይ መድረሱን ማረጋገጫው አንጋጦ መዝለፍ ነው፡፡እንደ አንድ ምዕመን፣እንደ አንድ ሰ/ተማሪ፣እንደ አንድ የማኅበር አባል፣እንደ አንድ ካሕን፣እንደ አንድ ሊቀጳጳስ የሰራነውን ያልሰራነውን እንፈትሽ፡፡ከዚያ በመቀጠል የፈረደበትን ፓትርያርክ እንቦጭቃለን፡፡ስለሌላው ግዴታ ብቻ ምላሱ እስኪዝል የሚደሰኩር ትውልድ እንዴት ይሰለቻል!!!የሃይማትም ሆነ የሐገር መሪ የሚፈጠረው ከእኛ ማሕል ነው፡፡ምናለበት ጊዜያችንን በሐሜታና በአመጻ ብቻ ለማዋል ከዳረገን የፌስቡክና የብሎግ ጫጫታ ይልቅ ቆም ብለን እያንዳንዳችን ወደ ውስጣችን ብናይ!!
   እውነቱን ለመናገር አቡነ ጎርገርዮስና አቡነ ተ/ሃይማኖት በዚህ ዘመን ባለመኖራቸው እድለኛ ናቸው፡፡ምክንያቱም በግፍ ስለተገደሉት ቴዎፍሎስ ሞት ምንም አልተናገሩም፣የኃይለሥላሴን ሥም በጸሎት አላነሱም፣ቅ/ሥላሴ ካቴድራል እና የታዕካ ነገሥት በዓታ ገዳም በሮች በደርግ ሲዘጉ አልተናገሩም፣ቀይሽብር እና ነጭ ሽብር ሲፋፋም አላወገዙም፣ራጉኤል ከመርካቶ ተነስቶ እንጦጦ እንዲዳበል በደርግ ሲወሰን አልተቃወሙም፣በእርስ በርስ ጦርነት ያን ያህል ደም ሲፈስ አልሸመገሉም፣የተወረሰውን የኢኦተቤክ ለማስመለስ ምንም አልሰሩም…እየተባለ ዛሬ በየፌስቡክ መወቀሳቸው አይቀርም ነበር፡፡እግዚአብሔር ቸር ነው!!እንኳንም በዚህ ‹‹የምን ላውራ›› ዘመን አልፈጠራቸው፡፡ያ ባለመሆኑ ነው እነሱም ‹‹ይህም ያልፋል›› ብለው በዚያ አረመኒያዊ ዘመን ስማቸውን በልበ-ምዕመናን ወ ካሕናት የቀረጸ ሥራ ሰርተው ያለፉት፡፡
   እንደ አቡነ ጳውሎስ ያለ እድለ ቢስማ ባሁን ዘመን ቢተመን ቢሊዮናትን የሚቆጠር ንብረት ከመንግሥት እጅ ፈልቅቆ አስመልሶም፣በሺህ ሚቆጠሩ ሰባክያንን ከየኮሌጁ አስመርቆም፣የተዳከመውን የቤ/ክ የውጭ ግንኙነት አነሳስቶ እነ አቡነ ሺኖዳን ሳይቀር ለሐገራዊ ቡራኬ ጠርቶም፣መሬት ወርቅ በሆነባት አዲስ አበባ ቁጥራቸው ከ60 ያላለፉ አብያተ ክርስቲያናት ወደ 160 እንዲያሻቅቡና የሰፋፊ ይዞታዎች ባለቤት እንዲሆኑ የተቻለውን አድርጎም፣በዘመኑ ከቀደምት ፓትርያርኮች ጋር ሲነጻጸር ቁጥራቸው የላቀ ቀሳጥያን በውግዘት እንዲለዩ አድርጎም፣በቤተክሕነቱ የስልጣንና የክሕነት መዋቅር ከተረሱ ወገኖችም በመቀላቀል ‹‹ኦርቶዶክስ የነፍጠኛ ሃይማኖት›› የሚል መርዘኛና እጅግ ጸያፍ ቅስቀሳ ለመቋቋም ጥረት አድርጎ፣ጨቅላ የነበረው ማኅበረቅዱሳን የራሱ ሕንጻና አደረጃጀት እንዲኖረው ስሕተቶቹን ብዙ ጊዜ እንዳላየ በማለፍና ከመንግሥት ይሰነዘር የነበረውን ጫና ‹‹የእነሱን ነገር ለእኔ ተውት›› እያለ ስልታዊ ከለላ ሲሰጥ የነበረው አባት፣ከእነ ባሕታዊ ገብረመስቀልና አባ ፈቃደሥላሴ ሰልፋና ሰይፍ የተረፈው ሰማዕት ዘእንበለ ደም፣ወጣንያኑ እነበጋሻው የመስቀል ሥር ቁማርተኛ ሲሉ የዘለፉት አባት፣ጋዜጣና ብሎግ ጭራቅ አድርጎ እየሳለ በሀዘን ወደ መቃብር እንዲወርድ ያደረገው አባት….በሰበብ አስባቡ፣በኤቢሲዲ ሽፍታዎች በየብሎጉና ፌስቡኩ ሥሙ ሲዘነጠልና አጽሙ እረፍት ሲያጣ ማየት ያማል፡፡ሰብአዊ ስሕተቶቹን ብቻ እያጎሉ ውብና ያማሩ ግንባታዎቹን ‹‹የድንጋይ ቁልል ብቻ›› እያሉ በቅርብ ያለው አባታቸውን ተግባር ላለማየት ሲሉ ዘወትር የትናንቷን የደርግ ዘመን ቤ/ክ እና የባሕር ማዶዋን ግብፅ የሚናፍቁ ጥራዝ ነጠቆች መድረኩን ተቆጣጥረው ቅኝት ሲያበላሹ ማየት ያማል፡፡ደግነቱ ይሄም ያልፋል!!
   በአቡነ ጳውሎስ የተመለሱ ሕንጻዎች፣ያስገነቧቸው ውብ ግንባዎች፣ያስገኙዋቸው አያሌ የቤ/ክ ይዞታዎች፣ከምንም እያነሱ አስተምረው ለመዐርግ ያበቁን እኛ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ግን እስከ ምጽአተ-ክርስቶስ በጎ አስተዋጽኦዋቸውን እንመስክራለን!!!የአልፎ ሂያጆች ፌስቡክና ብሎግ አይሸረሽረንም!!በኩራት እንዘክራቸዋለን!!ምክንያቱም፡-ሕንጻ ወውሉድ የዐብዩ ሥመ!!አትሳሳቱ የጳውሎስ ሐውልት ፀሐይና ዝናም የሚያወይባቸው የቦሌ መድኃኔዓለምና እነ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ያሰሩት የቅ/ሥላሴ ካቴድራል ሐውልት አይደለም!!የእሳቸው ሐውልት እዚህ ነው--በእኛ ውስጥ--ከምንም ያነሱን ሰዎች ልብ ውስጥ!!!ያንማ ብትፈልጉ አንድ ጊዜ ሳይሆን 7 ጊዜ አፍርሱት!!!አይገደንም!!!
   አንድ ነገር ግን ላረጋግጥላችሁ!! በአቡነ ጳውሎስ የሆነው ዳግም በአቡነ ማትያስም ሆነ በሌላ ተተኪ ፓትርያርክ ላይ ሲሆን ዳግም ማየት አንፈልግም፡፡፡፡ሁሉንም እንደ አመጣጡ ለመመለስ አቅማችን እስከቻለ ድረስ እንሄዳለን፡፡፡‹‹ይሄም ያልፋል›› የምንለው ከዚያ በኋላ ነው---ልክ እናንተ በብሎግም፣በጋዜጣም፣በፌስቡክም፣በሰይፍም፣በሰልፍም ብላችሁ-ብላችሁ አልሆን ሲል በቀቢጸ ተስፋ--ይሄም ያልፋል--ኃይል የእግዚአብሔር ነው-- እያላችሁ ማዕምረ ኅቡዐቱን የድንግል ልጅ እንደምትሸነግሉት!!!!

   Delete
  2. What type of argument is this for this specific article please learn for yourself from the above article and change yourself both of You then come back to argue about the others.

   Delete
  3. what is your difference from maru...

   Delete
  4. Maru kebede medhanialem yibarkih ! Dn.Danel eregim edmena tena yistih

   Delete
  5. ወንድሜ መልካም ብለሃል፣ አዎ አማተር ነኝ፣አማተር እኮ ለመማር በእውቀቱ ለማደግ ለመመንደግ የሚጥር የሚደክም ነው፣ ከድክመቴ ለመማር ጥፋቴን ለማስተካከል፣ ያልታየኝን ነገር በሰዎች መነጽርነት ለማየት እጥራለሁ።
   ብዙ መልካም ነገሮችን ብለሃል። አባ ጳውሎስ መልካም ነገሮችን ሰርተው አልፈዋል፣ ግን ምንም እንከን እንደሌለባቸው አድርጎ መሳል መልካም አይደለም። ሌላው ቢቀር የሚታየውን ነገር ልበል።አንተ ስለ ድንጋይ ህንፃ መመለስ ጠቁመሀል። በእሳቸው የአመራር ዘመን ነው የእግዚአብሔር ህንፃ የሆኑት የቤተ ክርስቲያን ልጆቿ ቁጥር በ10 ሚሊዮን የቀነሰው። ይህ እጅግ ብዙ ቁጥር ነው፣ ለዚህ ቁጥር መቀነስ እንደ የበላይ ሃላፊነታቸው የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ። የጥንታዊውንና ታላቁን ገዳማችን የዋልድባ ገዳም መንግሥት ለስኳር ማምረቻነት ሲወስደው ክርስቲያኑ ህዝብ አፉን እንዲይዝ በሚችሉት መንገድ ሁሉ ሞክረዋል፣ ከማስታውሰው የአገር ቤቱን ተወውና ጀርመን የሚኖሩ የቤተ ክርስቲያኑቱ ልጆች ገዳሙን በተመለከተ ሰላማዊ ሰልፍ ሊወጡ ሲዘጋጁ አባ ጳውሎስ አርፈው እንዲቀመጡ የፃፉትን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ማየቴን አስታውሳለሁ።ማለት ያ የቅዱሳን መናኸሪያ እንዲጠፋ የአባ ጳውሎስ ፈቃድ ነበር!!! ነገር ግን የቅዱሳን ጌታ በተአምራት እየጠበቀው ለሰዎቹም የንስሀ እድሜ እየሰጠ ስኳር ፋብሪካው ከተጀመረ አራት አመት ቢሆንም አንድ ነገር ሳይሰራ እስካሁን እንደተጀመረ አለ። ይህ መረጃው ከሌለህ savewaldiba.org ተመልከት። ዋልድባ እንዲጠፋ የሚፈልግ የቤተ ክርስቲያን መሪ" የቤተ ክርስቲያን አባት" ሊባል ይችላል??? እኔ በፍፁም አይገባኝም። ለነገሩ ከወደቅህበት እንዳነሱህ ነግረኸናል። የአባ ጳውሎስን ፍርፋሪ የቀመሰ ሰው እንዲህ አይኑ ይታወርበታል። የስጋዊ ጥቅም ትስስር እንደዚህ ያበሳጫል። ምናልባትም የቤተ ክርስቲያን ሐብት የዝርፊያ ኤክስፐርት ትሆናለህ።ለዚህም ሣይሆን አይቀርም ሰውን አማተር ብለህ ለመሳደብ የቃታህ። ለነገሩ ብዙ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐብት ሌቦች ዘራፊዎች፣ ወሮ በሎች በአባ ጳውሎስ ሞት በጣም አዝነዋል። ልክ እንዳንተ አባ ጳውሎስ ከወደቁበት አንስተው ከድሀ ልጆቿ በሚሰበሰብ ገንዘብ የቪላ ና የማርቸዲስ መኪና ባለቤት የሆኑ ሰዎች የሚያዘርፋቸው ሰው ሲሞት ያለቅሳሉ፣ አሁንም ድረስ ያነባሉ። የቤተ ክርስቲያንን ሐብት የሚሰርቅ ሰው በእግዚአብሔር ያምናል ብዬ አላስብም።
   እኔ ግን የዘላለም ቤቴ የሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያኔን እንደዚያ እቃ እቃ ሲጫወቱባት ማየት ያመኛል። ስለዚህ መጮሄን አላቆምም።እጮሀለሁ።

   አንድ ሰው መልካም ከሆነ እኮ ሌላ ነገር ሳይሆን በሕይወት ዘመኑ እያለ የሰራው መልካም ነገር ነው ምስክሩ የሚሆነው። እስኪ ነገረኝ ከታሪክ የምታውቀው ካለ፣ መልካም ሰርቶ ያለፈ ሰው መልካምነቱ በክፉ የተቀየረበት፣ ከታወቁ የታሪክ ክስተቶች አንጻር እስኪ አስረዳኝ? ቅዱሳን ሺህ ዘመናትን ተሻግረው ዛሬም እንደ አጥቢያ ኮከብ የሚያበሩት እኮ ያ ቅዱስ የሆነ ሥራቸው እስከዘላለም ስለ ሚያበራ ነው። ስለዚህ ያንድን ክርስቲያን መልካምነት የሚገልፀው ማንም ተራ ወሬኛ አይደለም፣ ህያው የሆነው ስራው እንጂ። አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊ ከ70 አመት በኋላ ዛሬም እንደ አዲስ ዜና ሁሌም በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ አሉ፣ ወደ ፊትም ይኖራሉ፣ ራሳቸውን ለዚህች ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ና ታላቅ አገር መስዋዕት አድረገው ስለ ሰጡ።

   ሌላም እጅግ ብዙ ነገር አለ ... ህዝቡ የሚያውቀው ስለሆነ እዚህ መዘርዘር ለቀባሪው ማርዳት ነው የሚሆነው።
   እኔ እጅግ ተራ ሰው ነኝ፣ ነገር ግን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ የዚህች ታላቅ አገር ታሪክ ነገ በወጉ በስርአቱ ይፃፋል። የቤተ ክርስቲያን መሪ የነበሩት ሰዎች የታሪኩ ዋና ተዋናይ ይሆናሉ። የአባ ጳውሎስ ታሪክ የሚፃፈው አንተ እንዲሆን የፈለግኸው ሳይሆን እውነተኛው፣ የሆነው፣ የተደረገው፣ የነበረው ትክክለኛው ነገር ነው። ያ ትክክለኛ መረጃ እውነቱ ደግሞ ከሌላ ፕላኔት የሚመጣ ሳይሆን ህዝቡ የሚያውቀው፣ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው መረጃ፣ በታሪክ መረጃዎች የተመዘገበው ነገር ነው እስከ አለም ፍፃሜ ለሚመጣው ትውልድ በታሪክ መጻሕፍት ተፅፎ የሚተላለፈው። ስለ ተበሳጨህ ምንም የምትቀንሰው የምትጨምረው ነገር የለም። እውነት እውነት ነው። ምናልባት በሕይወት እያለህ ተፅፎ ታየዋለህ።

   Delete
  6. ኢያረምም ህየንተ ምን እያልክ እንደሆነ አልገባኝም፡፡ አሁን ፓትሪያርኩን አቡነ ጳውሎስን እንደዚህ አድርገህ ያስቀመጥካቸው በእውነት ማሩ ከበደ እንዳለው ብዙ ስለቤተክርስቲያን ታሪክ የማያውቁ ሰዎች አድናቂ እንዳላቸው የነገረንን እውነቱን ነው አንተ አንድ ምሳሌ ነህ፡፡ አንድ ፓትሪያርክ ምን ማድረግ እንዳለበት በናትህ ስርዓተ ክህነት መጽሐፍ ፈልገህ አንብብና ከዚያ እሷቸውን ማወደስም ሆነ መንቀፍ የምትችለው እውቀት ይኖርሀል፡፡ አለበለዚያ ዘመኑ የአህዛብ እውቀት የበዛበት ዘመን ስለሆነ ስለማቴሪያል ፣ ህንፃ ምናምን ብታወራን አይገባንም፡፡ ዘመኑ ሀዲስ ኪዳን ነው የማቴሪያሊስት ዘመን ሳይሆን የሰው ልጅን የማትረፍ ዘመን ነው፡፡ አስተውል፣ የምትደግፈውንና የምትናገረውን አስተውል፣ በእውቀት ማነስ ነው ይህ እየሆነ ስለሆነ ወደኋላችን ተመልክተን አባቶቻችንን ቅዱሳንን እንመልከት፡፡

   Delete
 6. lega malkamm tnagerk !! hulem yLfal!! kale gen aylfm kalew kgetache medhanetachen yeses crestos kale basteker hlem alfena feture mhnacenn eyresan snmat ymmataw tmket mtherasation aymerm !! egezabher ytabke lega!!ydengle Maryam ysrat leg berta!!

  ReplyDelete
 7. ይህም ያልፋል !

  ReplyDelete
 8. የኛ ህዝብ እኮ አብዛኛዉን ‹‹ ይህም ያልፋል›› ብሎ ካለፈለትና ከተለወጠ በኋላ ስጋዊ ፍላጎቱ ከመናሩ የተነሳ ይህን ፍላጎት ለማስታገስ ሲል በቀልና ሃጢያት መስራትን ከሰማይ እንደወረደለት አድርጎ የሚቆጥር ነዉ፡፡ ብዙዎቻችን በገንዘብ፣ በበቀልና በጠባብነት አዙሪቶች ተወጥረን ‹‹ ይህም ያልፋል›› ብለን ለእግዚአብሄር መተዉን እንደ ሞኝነትና ቂልነት ቆጥረን ያለንን ቀሪ እድሜ እንኳ ሳናሰላስል የእድሜ ድሪቶ ይዘን በንሰሃና በበጎ ምግባር ሳናጥበዉና ሳናስለቅቀዉ እየተሳለቅንና እየተሳቀቅን እየኖርን እንገኛለን፡፡ ስለሆነም ‹‹ ይህም ያልፋል›› ብለን ወደ ህሊናዊ ጓዳችንና አስተዉሎታችን እንመለስ እላለሁ፡፡ ትክክለኛ በሰዎች አዕምሮ ዉስጥ መታተም ያለበት የህሊና ጽሁፍ ነዉ!!!

  ReplyDelete
 9. እባብ ሲደበደብ ራሱን ይከላከላል፡፡ ለምን? ራሱ ካለ የተቆረጠ አካል ቢኖረው እንኳን ይቀጠላል፣ የተጎዳ አካል ቢኖረው እንኳን ይፈወሳል፡፡ ራሱን ከተመታ ግን አለቀለት፡፡ ሰውም ኅሊናውን ከተመታ ሞተ ማለት ያን ቀን ነው፡፡ ኅሊናህ እንዳይመታ ከፈለግክ ‹‹ይህም ያልፋል› ብለህ አስብ፡፡ የቆምክበት ቦታና ጊዜ አስመራሪ፣ አታካች፣ አንገሽጋሽ፣ ከባድና ጽኑ ቢሆን እንኳን ግን ያልፋል፡፡ አንተ ያንን መከራ እየቀመስክ ባለህበት ጊዜ እንኳን እያለፈ ነው፡፡ ጥሩ መልእክት ይህም ያልፋን እውነት ነው ፡፡

  ReplyDelete
 10. ብዙ ነገር አልፏል፤ ይህም ያልፋል፤
  ዳኒ ቃለ-ህይወት ያሰማልን፡፡ ለእኛም ማስተዋሉን ስጠን!!!

  ReplyDelete
 11. ....ሁሉም ያልፋል....
  በጣም ብዙ ተማርኩኝ!
  አ/ር ይስጥልኝ... ዳኒየ

  ReplyDelete
 12. የዛሬ ቀባሪ ሁሉ ነገ በተራው ተቀባሪ ነው፡፡

  ReplyDelete
 13. እዉነት ነው ነገሩ፡ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ይህንን የሚረዱት አይመስለኝም፡ አይናቸው እያያ እንዳላየ የመንሆን ፍጡሮች ነን። ጥሩ ታሪክ ነው፡ ለህሉም ልቦናችንን ያብራልን። ላንተም እድሜና ጤና ይስጥህ።

  ReplyDelete
 14. eskahun saygbagie sentu neger alefe meseleh yalfal salelew berasu giza seyalf ahun gin temarku HULUM NEGER YALFAL BEYA ASBALEW KEZI WEDI AMSEGNALE DIAKON DANIEL

  ReplyDelete
 15. "ይህም ያልፈል" ዲ/ን ዳኒ በርታልን

  ReplyDelete
 16. There are so many excellent sayings of such type which can guide human brain and heart to the good . They were said generation after generation in different parts of our country but are not collected and compiled in a written form .It is easy to say the phrase ይህም ያልፋል but very hard to live in it in this greedy and temporary world . Dear Daniel thank you for raising the point so that we can learn from it and do our part by collecting and sharing such golden phrases and sayings to the next generation .

  ReplyDelete
 17. ቃለ እይወት ያሰማልን ዲያቆን ዳንኤል ሰሚ ከተገኘ

  ReplyDelete
 18. ሰው የሚኖረው ከሥጋው በላይ በኅሊናው ነው፡፡ ውድቀት በሥጋ መኖር ሲጀመር ይመጣል፡፡ ክብርና ድል ደግሞ በኅሊና መኖር ሲጀመር ይመጣሉ፡፡ .......... ሰውም ኅሊናውን ከተመታ ሞተ ማለት ያን ቀን ነው፡፡ ኅሊናህ እንዳይመታ ከፈለግክ ‹‹ይህም ያልፋል› ብለህ አስብ፡፡ የቆምክበት ቦታና ጊዜ አስመራሪ፣ አታካች፣ አንገሽጋሽ፣ ከባድና ጽኑ ቢሆን እንኳን ግን ያልፋል፡፡ አንተ ያንን መከራ እየቀመስክ ባለህበት ጊዜ እንኳን እያለፈ ነው፡፡

  ReplyDelete
 19. Egziabher Yisteh Wud Daniel! Gerum Yehelena Megeb Beltenal... Besega sayihon behelina Menor..

  "...ሰው የሚኖረው ከሥጋው በላይ በኅሊናው ነው፡፡ ውድቀት በሥጋ መኖር ሲጀመር ይመጣል፡፡ ክብርና ድል ደግሞ በኅሊና መኖር ሲጀመር ይመጣሉ፡፡ ..."

  ReplyDelete
 20. ክብርና ድል በኅሊና መኖር ሲጀመር ይመጣሉ፡፡ሰው ኅሊናውን ከተመታ ሞተ ማለት ያን ቀን ነው፡፡ ኅሊናህ እንዳይመታ ከፈለግክ ‹‹ይህም ያልፋል› ብለህ አስብ፡፡

  ReplyDelete
 21. በየትኛውም የሥልጣንና የሀብት ከፍታ ላይ ብትሆን፣ በየትኛውም የዝናና የክብር ሠገነት ላይ ብትደላደል፣ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ ካሰብክ ግፍ አትሠራም፣ ፍትሕ አታዛባም፣ ድኻ አትበድልም፣ ከልክህም አታልፍም፡፡ ራስህን ዘላለማዊ አድርገህ ካሰብክ፣ ጊዜ የማይቀየር ዓለምም የማትዞር ከመሰለህ ግን ራስህን ለማስተካከል እንኳን ጊዜ ሳታገኝ ነገሮች ይቀየሩና በሠራኸው ወኅኒ ትወረወራለህ፣ ባወጣኸው ሕግ ትቀጣለህ፣ በቆረጥከው ዱላ ትመታለህ፣ ባሳደግከው ውሻ ትነከሳለህ፡፡ ስለዚህ አሁን የተቀመጥክበትን ዙፋን፣ የምታንቀጠቅጥበትንም ሥልጣን፣ ‹ይህም እንኳን ያልፋል› ብለህ አስበው፡፡
  thanks for your precious words,and God bless u and you family

  ReplyDelete
 22. ልክ ብለሀል።

  ማስተዋል ያድለን

  ReplyDelete
 23. በሐይመኖት በከል ያለው ፣ በአሰተዳደር ያለው፤ በማሕበራዌ በኩል ፤ ከዜያም ታልፎ በአለማችን የሜሆነው ያለ ሀሉ ቆም ብለን ካስተዋል ነው ፤ ምንም ደሕና ነገር የሜሰማም፤ የሜታይም ጠፍቶአል። ስለዜሕ በሕብረት ሁነን "ይሕም ያልፉል" በማለት እጃችን ወደፈጠረን ጌታ ብናነሳ መልከም ይሆናል።መፍትሔው ይሔው ነው።

  ReplyDelete
 24. ዲ. ዳንኤል መልካም ስብዕና፣ ምሉዕ እውቀት፣ድንቅ ምልከታና ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ በመመርመር እና በሁሉም የህይወት ጥምረታዊ ሚዛን በመመዘን ዓለም ግራ ያጋባችውን ምእመን ሊያረጋጋና በተመስጦ ሆኖ ሊረዳው እና ሊያስበው በሚችለው መልኩ ሃሳቦችን እንድታቀርብ የፈቀደልህን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ ሁልጊዜ የሚገርመኝና የአንተን መጣጥፎች ባለመሰልቸትና እንዴውም በጉጉት እንዳነባቸው የሚገፋፋኝ ነገር ፣ ብዙ ሰዎችን እንደሚያደርጋቸው ሁሉ፣ ቢኖር የምትመርጠው ርዕስና በርዕሱ ዙሪ የሚኖርህ እይታ፣ የቃላት አመራረጥ ፣ የሃሳብ ቅደምተከተልና የጭብጥ ዳሰሳ እጀግ ግሩምና ጆሮ ገብ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን ከህሌና የማይጠፋ እና በዓይምሮ ውስጥ የራሱን ቦታ ይዞ የትውስታና የተግሳጽ ደወል በመደወል የማንቃትና ለበጎ ስራ በማነሳሳት ለመንፈሳዊ ሆነ ለስጋዊ ህይወት እንቅስቃሴ እና የተስተካከለ ስብዕና እንዲኖር ትልቅ ግብዓት የሚሆን ልዩ የህይወት ምግብ ከመሆኑም በላይ ሀሳቡ የሚያነበውን ሰው ሕይወት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የመዳሰስ ሃይል ስላለው ነው፡፡ ከዚህም በላይ የምታነሳቸው ሀሳቦች ከየትኛውም አካል ያልወገኑ ነገር ግን እምነቱን፣ ፖለቲካውን፣ ኢኮኖሚውን፣ ባህሉን፣ ስነ-ምግባሩን፣ ቋንቋውን፣ ታሪኩንና ሌላውንም የማህበራዊ ህይወት መስተጋብር በእኩል ሚዛናዊ እይታ በመዳሰስ ሁሉም ሊረዳውና ሊጠቀምበት በሚችል መልኩ ድንቅ እይታን እና ከብዙ የጥበብ ማዕድ የተቀዳን ሀሳብ በተመረጡ ቃላት እና እውነተኛ የኢትዮጵያዊነት አቀራረብ ዘይቤ ቀምመህና አታፍጠህ ማቅረብህ ከሌሎች ጸሐፍት በተለየ መልኩ እንድትታይ አድርጎሀል፡፡ - በእኔ እምነት፡፡
  ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስና ፣ ዛሬ ይህንችን መጠነኛ አስተያየት ለመስጠት ያነሳሳኝ ትልቁ ጉዳይ ‹‹ይህም ያልፋል ›› በሚል ርዕስ ያስነበብከን ድንቅ እና እጅግ ብዙ የህይወት ዘርፎችን በመዳሰስ በአጭር አገላለጽ ያቀረብክበት መጣጥፍ ነው ፡፡ ከምንም በላይ ምን ባደርግ ይሻላል ብሎ የሚጠይቅ ገዥ ማግኘት ራሱ ትልቅ መታደልን ይጠይቃል ፡፡ አንድ ሰው ምን ብሰራ ይሻላል፣ የትኛውን መንገድ ብከተል ከምፈልገው ቦታ በደህና ያለ ችግር የደርሰኛል ብሎ ማሰብ ከቻለ እና እሱ የማያውቀው ነገር እንዳለ እና የሌሎች ሀሳብ ይጠቅማል በሚል እሳቤ ከተገነዘበ የሰውየው አዋቂነት ከዚህ ይጀምራል ፡፡ አባቶቻችን እኮ እኔ አውቃለሁ ብለው ሳይሆን የሚያውቁትን ጉዳይ እንኳን ሳይቀር ከሌላ ሰው ጠይቀው ሌላው ሰው በምን መልኩ እንዳየውና እንደተረዳው ከመረመሩ በኋላ የተመከረበትና የተጨመቀ ሀሳብን ብቻ ወደ ተግባር በመቀየር የጋራና በስምምነት ላይ የተመሠረተ ሀሳብን አንግበው ሃይማኖታቸውን፣ ሀገራቸውን ፣ ባህላቸውን እና ማንነታቸውን ያለምንም እንከን ጠብቀው ለዚህ ትውልድ አስረክበው አልፈዋል ፡፡ ካለእኔ አዋቂ የለም በሚል መጥፎ እና ሴጣናዊ አስተሳሰብ ተለክፈው እኔ ብቻ አውቅልሀለሁ በማለት ተከታዮቻቸውን በምሬትና በሰቆቃ የህይወት መንገድ እንዲጓዙ የሚያደርጉ ገዥዎች መጨረሻቸው እንደባቢሎን ግንብ መፈራረስ ብቻ ሳይሆን በወጡበት መሠላል መውረድ ተስኗቸው ከረጅም ርቀት ሲወድቁ መመልከት የተለመደ ድርጊት ከሆነ ሰነባብቷል ፡፡ ነገሮች ሁሉ እያለፉና እየተለወጡ ከመሄዳቸው ጋር ተያይዞ አሁን የያዝነውና ያለን ነገር ሁሉ ነገ ከነገወዲያ እንደማይኖር በመረዳት ለምናደርገው ነገር ሁሉ ቅንነትና መልካምነት ቢታከልበት ውጤቱ የነገን ጸጸት ከመቀነሱም በላይ የህሊና እረፍትን እንደሚሰጥ ከቀረበው ጽሁፍ በሚገባ መረዳት ይቻላል፡፡ ስልጣን፤ ውበት፣ ሀብት፣ ጉልበት፣ ትቢትና ሌሎችም ነገርች ማለፋቸው የግድ ነው ፡፡ ህይወት ያለው እየከሰመ የልለው እንደአዲስ እተከሰተ በጊዜ ቅብብሎሽ የሚኖሩባት የጉዞ ሂደት ነች፡፡ ሌላው ቀርቶ መልካም ስራ እንኳን ያልፋል፡፡ - ምንም እንኳን ውጤቱ ዘላለማው ዝና፣ክብርና ሞገስን የሚያጎናጽፍ ቢሆንም፡፡ የአብርሃም እንግዳ ተቀባይነት (ደግነት) ፣ የዳዊት ንግስና፣ የጠቢቡ ሶሎሞን ጥበበኛነት፣ የኢዮብ ታጋሽነት ፣ ሁሉም በዘመኑ የነበረው ነገር ሁሉ አልፏል ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ደጋግ አባቶች በነበሩበት ዘመን ሁሉ ሁሉም ያልፋል በሚል ትልቅ የህይወት መርህ ይመሩ ስለነበር እነሱ ቢያልፉም መልካም ስራቸው ዘመናትን ተሻግሮ እየበራ ከዚህ ዓለም ድቅድቅ ጨለማ ሲወጣንና ያ መልካም ድርጊታቸው እና ምግባራቸው መርሃ ህይወት እንዲሁም ጥበባቸው የህይወት ጊጥ ሆኖን ዛሬ እኛ አርዐያ እንድናደርጋቸው ሆነዋል ፡፡ በመሆኑም ሁሉም ያልፋል ብለን መልካም ሀሳብ በማሰብና ስለምንሰራው ስራ ከሌሎች በመማከር የተጣጣመና ከብዙ አዋቂዎችና ጠበብት እንቅላት ከወጣ እሳቤ የተጨመቀ ሀሳብ በመያዝ ሰውን እና ፈጣን የሚያስደስት ተግባር በመፈጸም ከነገ ጸጸትና የታሪክ ተወቃሽነት እንዳን ፡፡ ቸር ይግጠመን ፡፡

  ReplyDelete
 25. በጥጋብም ሆነ በረሃብ፣ በሀብትም ሆነ በድህነት፣ በሥልጣንም ሆነ በውርደት፣ በድልም ሆነ በሽንፈት፣ በጤናም ሆነ በሕመም፣ በዝናም ሆነ በክስረት፣ የሚመጣ መከራ አለ፡፡ ከዚያ መከራ መውጣት ከፈለግክ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ አስብ፡፡ ይኼ መንገዱን መመልከቻ መነጽርህ ነው፡፡ ከሠገነቱ እንዳትወድቅ መውረጃህ፣ ከጉድጓዱም እንድዘቅጥ መውጫህ መሰላል ነው፡፡

  ReplyDelete
 26. ሰው የሚኖረው ከሥጋው በላይ በኅሊናው ነው፡፡ ውድቀት በሥጋ መኖር ሲጀመር ይመጣል፡፡ ክብርና ድል ደግሞ በኅሊና መኖር ሲጀመር ይመጣሉ፡፡

  እባብ ሲደበደብ ራሱን ይከላከላል፡፡ ለምን? ራሱ ካለ የተቆረጠ አካል ቢኖረው እንኳን ይቀጠላል፣ የተጎዳ አካል ቢኖረው እንኳን ይፈወሳል፡፡ ራሱን ከተመታ ግን አለቀለት፡፡ ሰውም ኅሊናውን ከተመታ ሞተ ማለት ያን ቀን ነው፡፡ ኅሊናህ እንዳይመታ ከፈለግክ ‹‹ይህም ያልፋል› ብለህ አስብ፡፡ የቆምክበት ቦታና ጊዜ አስመራሪ፣ አታካች፣ አንገሽጋሽ፣ ከባድና ጽኑ ቢሆን እንኳን ግን ያልፋል፡፡ አንተ ያንን መከራ እየቀመስክ ባለህበት ጊዜ እንኳን እያለፈ ነው፡፡

  ReplyDelete
 27. ምን ዋጋ አለው ለኛ ሰዎች አይሰራም

  ReplyDelete
 28. እናመሰግናለን ዳኒ

  ReplyDelete
 29. ዎዉ ትልቅ ምክር እግዚያብሄር ለሁሉ ማሰተዋልን ይሰጥ በተለይ....

  ReplyDelete
 30. ዎዉ ትልቅ ምክር እግዚያብሄር ለሁሉ ማሰተዋልን ይሰጥ በተለይ....

  ReplyDelete
 31. ትክክል የሰዉ ልጅ "ይህም ያልፋልን" መመርያዉ ቢያደርግ ኖሮ ዓለም ባልተበጠበጠች ነበር::

  ReplyDelete
 32. Betam dis yemile new gata yebarikeki

  ReplyDelete
 33. ዳኒ እ/ግ የረስጥልኝ ቃለ ህይወት ያሰማልኝ ጀሮ ያለወረ ይስማ አእምሮ ያለው ካለ ያስተውል ከዚህ በላይ ምንም አያስፈልግም የሚሰማ ጀሮና ልብ ያለው ሰው ።እ/ግ ይባርክህ።

  ReplyDelete
 34. እናመሰግናለን::

  ReplyDelete
 35. ሁሉም ያልፋል፡፡

  ReplyDelete
 36. ሉምያልፋል ነገ ላ ቀን ነና

  ReplyDelete
 37. Dear, D. Daniel
  You have amazing wisdom. You pass your message in a very educational mood and you have abundant of wisdom to do so. God bless you and keep on teaching us.

  Thank you so much

  ReplyDelete
 38. እረጅም እድሜና ጤና ከነመላዉ ቤተሰብህ ያድልህ!!! መፃፍ የታደላትሁ መጠላላት ሰይጣናዊ ነዉ ፍቅር ስበኩ «ይህም ያልፋል»

  ReplyDelete
 39. ዲ/ን ዳንኤል ረጅም እድሜ ከነመላዉ ቤተሰብህ!!!
  መፃፍ ፍቅርን ነዉ «ሁሉም ያልፋል»
  «ከሁሉም ግን ፍቅር ይበልጣል»

  ReplyDelete
 40. eskialf...Yalefal -! new negeru enji,, esuma yalfal. bayhon gizewn lemasater "Melafatu" saybej aykerim?

  ReplyDelete
 41. ይህም ያልፋል!! በትክክል በተለይ ከወንበር አንወርድም ላሉት ቆሞ ማንበብ ነበረ

  ReplyDelete
 42. ወይ ጉድ ሊያልፍ ያለፋል አይደል

  ReplyDelete
 43. በውነትም ያልፋል! ዳንዔል አድናቂህ ነኝ::ጌታ ይባርክህ!

  ReplyDelete
 44. ዲ/ን ዳንኤል በጣም ነው ማከብርህ ረጅም ዕድሜ እና ጤና ፍቅሩን ይስጥህ "ሁሉም ያልፋል........እስኪያልፍ ያለፋል"

  ReplyDelete
 45. ፍፁም በሆነ መልካምነት
  ፍፁም በሆነ ደግነት
  ነገሮችን ካየናቸው የዲ ዳን መልክቶች የህይወት መንገድ ናቸው ።
  እግዝያብሄር እድሜ ና ጤና ይስጥልን
  ሁሉ ያልፋል ✝

  ReplyDelete
 46. Egziabher Yistilin ...... betsihufih ereft Agegnalew

  ReplyDelete