Monday, June 1, 2015

ከመጸዳጃ ቤቱ ፊት ለፊት


አሜሪካ ዳላስ የሚኖር አንድ ወዳጄ ለትምህርት ከሠላሳ ዓመታት በፊት ፈረንሳይ እያለ የገጠመውን እንዲህ ነግሮኝ ነበር፡፡ ከዩኒቨርሲቲ ጓደኞቹ ጋር ምግብ ለመብላት ይወጣሉ፡፡ የገቡበት ምግብ ቤት ደረጃው ከፍ ያለ ነበር፡፡ የምግቡን ዝርዝር ያዩና ስሙ ደስ ያላቸውን ያዛሉ፡፡ ምን ዓይነት ነው? እንዴት ነው የሚሠራው? ምን ምን ያካትታል? የሚለውን የምግብ ማውጫ ዝርዝር ለማየት ዕድል የሰጠ ወይም አስተናጋጇን የጠየቀ ከመካከላቸው የለም፡፡ ሁሉም ያንኑ አዘዙ፡፡ አስተናጋጇም ጠረጲዛውን ካስተካከለቺ በኋላ በሰሐን ሙዳ ሙዳ ሥጋ በአራት መዓዝን ቆርጣ አመጣችና በየፊታቸው ከቢላዋና ከሹካ ጋር አስቀመጠች፡፡ 

 ፊታቸው ፈካ፣ ሀገራቸው የተውት ጥሬ ሥጋ ፈረንሳይ ድረስ ተከትሎ በመምጣቱ ተገረሙ፡፡ ምናልባት አበሻነታችንን ዐውቃ ይሆን ጥሬ ሥጋ ያመጣችልን? ብለውም አሰቡ፡፡ አዋዜ ባለመኖሩ ቢያዝኑም  በቢላዋ እየቆረጡ ጠረጲዛው ላይ በነበረው ቁንዶ በርበሬ እየጠቀሱ ያጣጥሙት ጀመር፡፡ ናፍቆት አሳስቷቸው ባንዴ ሰሐኑን ባዶ አደረጉት፡፡ የጥሬ ሥጋውን ነገር እያነሡ ሲደሳሰቱ አስተናጋጇ እሳቱ የፋመበት አራት መጥበሻ ይዛ መጣች፡፡ ፈገግ ብላ መጥበሻዎቹ ያሉበትን ትሪ መሰል ነገር ጠረጲዛው ላይ ስታስቀምጠው ግን ክው ብላ ነው የቀረቺው፡፡ ብርንዶ በመሰለው ፊቷ አፍጥጣ እያየቻቸው ‹‹ሥጋው የታለ›› ብላ በፈረንሳይኛ ጠየቀቻቸው፡፡ እነርሱ ሲፋጠጡ ሴትዮዋ በድንጋጤ እንደሄደች አልተመለሰቺም፡፡ 


  በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዝኩ ነው ይህን ታሪክ ያሰብኩት፡፡ የተቀመጥኩት የአደጋ ጊዜ መውጫው በር ያለበት ጋ ነበር፡፡ ፊት ለፊት በስተ ቀኝ በኩል የመጸዳጃ ክፍሉ አለ፡፡ እስካሁን ድረስ ወደ ሠላሳ የሚጠጉ ሰዎች ለመጠቀም መጥተዋል፡፡ ሰዎቹን እንድቆጥር ያደረገኝ የማየው ነገር ስላስገረመኝ ነው፡፡ የመጸዳጃው በር አንድ ሰው እንዲያስገባ ሆኖ የተሠራ፣ አካፋዩ ጋ የሚታጠፍ፣ መሐል ወገቡ ላይ ደግሞ ክፍሉ መያዝ አለመያዙን የሚያመለክት የሚበራ ምልክት ያለበት፣ ከምልክቱ ወረድ ብሎ የተንጠለጠለ የሲጋራ መተርኮሻ የተቀመጠበት፣ በሁለተኛው ተካፋይ ላይ በአማርኛ‹ ይጫኑ› በእንግሊዝኛ ደግሞ PUSH የሚል ቃል የተጻፈበት ነው፡፡ 

 ወደ መጸዳጃ ክፍሉ ወጣቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋውያንና ጎልማሶች መጥተዋል፡፡ በአብዛኛው የመጡት ወጣቶችና ጎልማሶች ናቸው፡፡ ወደ መጸዳጃ ቤቱ ከመጡት ሠላሳ ሰዎች መካከል አሥራ ሰባቱ የሲጋራ መተርኮሻውን የበሩ መክፈቻ መስሏቸው ሲስቡት ነቅለውታል፡፡ አጠገቤ የነበረው ሰው የተነቀለውን መልሶ መትከል ሥራው ሆኖ ነበር፡፡ ከመጡት መካከል አምስቱ መጸዳጃ ቤቱ መያዝ አለመያዙን በሚያሳየው ምልክት በኩል ለመክፈት ይታገሉ ነበር፡፡ ከእነዚህ ሃያ ሁለት ሰዎች ስድስቱ ብቻ አረጋውያን ናቸው፡፡ የቀሩት ደግሞ ወጣቶችና ጎልማሶች፡፡ ከጎኔ የነበረው ሰው ቢያንስ ለዘጠኝ ጊዜ ለመጸዳጃ ቤቱ ውኃ ለመልቀቅ ሄዷል፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን አረጋውያኑ ሁለቱ ብቻ ናቸው፡፡ 

 የምመለሰው ከአሜሪካ ነውና ተጓዦቹ ቢያንስ የተወሰኑ ቀናት ቢበዛ ደግሞ ዓመታትን በአሜሪካ ቆይተዋል ብዬ ገመትኩ፡፡ ያም ባይሆን እንኳን ወደ አሜሪካ የመጡት በአውሮፕላን ነው፡፡ በርግጥ በላቲን አሜሪካ በኩል አድርገው ወደ አሜሪካ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ እነርሱም ቢሆኑ ግን ወደ ላቲን አሜሪካ ሀገሮች በአውሮፕላን ገብተው ከዚያ በመኪናና በባቡር ወደ ሜክሲኮ የሚደርሱ ናቸው፡፡ 

 እነዚህ ወገኖቻችን የአውሮፕላኑ በር እንዴት እንደሚከፈት ለምን ጠፋቸው? ብዬ ጠየቅኩ፡፡ የመጀመሪያው በሁላችን ኅሊና ሊመጣ የሚችለው ምክንያት ‹የልምድ ማጣት ነው› የሚል ሳይሆን አይቀርም፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች በአውሮፕላን ተጉዘው ወደ አሜሪካ የመጡ ናቸውና ቢያንስ አንድ ጊዜ በዚህ በር መጠቀማቸው አይቀርም፡፡ በረራው ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ቢደረግ ወይም ከአንዳንድ የአውሮፓ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ ቢሆን ኖሮ ይኼ ምናልባት አንድ ምክንያት ሊሆን ይችል ነበር፡፡ ከኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወጣ አንዳንድ ሰው የአውሮፕላን ጉዞ ልምድ ሊያጥረው ይችላል የሚለውን እንይዝለታለን፡፡ በባሕር በኩል ወደ አውሮፓ የሚገቡ አንዳንድ ወገኖችም አውሮፕላን ላይ የሚሣፈሩት የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው ወደ ሀገር ሲመለሱ ነው፡፡ ይህም ሊያዝ የሚችል ነው፡፡ ግን አሁን እየተጓዝን ያለነው ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ ነው፡፡

 እኔ ግን የማናውቀውን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ስናውቅ በትምህርት መልክ ለማወቅ ያለመጣር ክፉ ልማድ አንዱ ምክንያት ይመስለኛል፡፡ አበው ‹ሞኝ ሺ ጊዜ ብልጥ አንድ ጊዜ ይሳሳታል› ይላሉ፡፡ ብልህ ሰው መጀመሪያ ባለማወቁ ቢሳሳትም አለማወቁን ወደ ዕውቀት ይቀይረዋል፡፡ አዲሱን ገጠመኝ በሚገባ አስተውሎ ዕውቀት ያደርገዋል፡፡ ሞኝ ግን ያኔውኑ ከችግር መውጣቱን ወይም ነገሩን መከወኑን እንጂ በድጋሚ በተስተካከለ መንገድ ነገሩን ለመፈጸም የሚያስችል ዕውቀትን አይሸምትበትም፡፡ ምናልባትም እንደ አጋጣሚ ሆኖ ትክክለኛውን ነገር ቢሠራው እንኳን፣ ዳግመኛ ለመሥራት የሚያስችል ልምድ ግን አይቀስምበትም፡፡ ገጠመኙን ወደ ዕውቀት አልቀየረውማ፡፡  

 በሩን መክፈት አቅቷቸው የሲጋራ መተርኮሻውን ካወለቁት ሰዎች መካከል ሦስቱ እንደገና ተመልሰው ያንኑ መተርኮሻ አውልቀውታል፡፡ እንዲያውም ሁለቱ ሰዎች አስተናጋጆቹ ጋሪ ይዘው እስከሚያልፉ ድረስ ከፊቴ ቆመው ነበርና የት ሀገር እንደሚኖሩ ለመጠየቅ ዕድል አግኝቼ ነበር፡፡ ሁለቱም አሜሪካ ነው የሚኖሩት፤ አንዱ ሰባት አንደኛው ደግሞ አምስት ዓመታቸው ነው፡፡     

 ብልህ ሰው አንድን ከዚህ በፊት አድርጎት የማያውቀውን ነገር ከማድረጉ በፊት ወይ ያነባል፣ ወይ ያጠይቃል፣ አለበለዚያ ደግሞ ሌሎችን አይቶ ይማራል፡፡ በሩ ላይ ‹ይጫኑ፣ PUSH› የሚል ምልክት አለው፡፡ ያንን አንብቦ የበሩን አከፋፈት መገመት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያውያን እናቶችና አባቶች ነገሩን ላያነቡት ይችላሉ፡፡ ወጣቶቹና ጎልማሶቹ ግን ለምን አላነበቡትም? በመመሪያ የመሥራት ልማድ አለመኖር ይመስለኛል፡፡ ስንቶቻችን ዕቃ ስንገዛ ከመጠቀማችን በፊት ማኑዋሉን እናየዋለን? ስንቶቻችንስ በካርቱኑ ላይ ለተጻፉት ነገሮች ትኩረት እንሰጣለን? ስንቶቻችንስ በዕቃዎች ላይ የሚጻፉ መግለጫዎች ጠቃሚዎች ናቸው ብለን እናምናለን? በሲጋራ መተርኮሻው ላይ የተለኮሰ ሲጋራ ሥዕል ይታያል፡፡ እርሱን የሚያይ ሰው ምን ይሆን? ብሎ ለማሰብ እንዴት ሰከንዶች ማጥፋት አቃተው? ወይም ከመንቀሉ በፊት ሥዕሉን ለምን አላየውም? ለዕውቀት ስሱ አለመሆን አይመስላችሁም፡፡  

 አንባቢ ሰው በአራት ይከፈላል፡፡ የመጀመሪያው ለጉዳዩ ሲል የሚያነብ ነው፡፡ የትምህርት ቤት መጻሕፍትን፣ የጥናት ደብተሩን፣ የምግብ መሥሪያ መመሪያውን የሚያነበው ዓይነት፤ እንዲህ ያለው ሰው ጉዳዩ ሲያልቅ አንባቢነቱም ያቆማል፡፡ አንዳንዶቻችን ከዩኒቨርሲቲ በኋላ ከመጽሐፍ ጋር የተቆራረጥነው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ለኑሮ የሚያነብ፡፡ ያለ ንባብ መኖር የማይችል፡፡ ምግበ ኅሊና የሚፈልግ፡፡ ካላነበበ የሚርበው ዓይነት፡፡ ሦስተኛው ዓይነት አንባቢ የሚባለው ደግሞ ከማንኛውም ነገር በፊት ስለዚያ ነገር የሚገልጠውን የሚያነብ ነው፡፡ ያለ ዕውቀት የማይመራ፡፡ መንገድ ሲሄድ፣ ዕቃ ሲጠቀም፣ መድኃኒት ሲወስድ፣ አዲስ ምግብ ሲመገብ፣ ወደማያውቀው ሀገር ሲሄድ፣ አዲስ ሞያ ውስጥ ሲገባ ስለዚያ ነገር የተጻፈውን አንብቦ ካልሆነ በቀር የማይወስን ዓይነት፡፡ አራተኛው ሰው ተገድዶ ብቻ የሚያነብ ነው፡፡ አንድን መግለጫ፣ ጽሑፍ ወይም ማስታወቂያ ለማንበብ ሁኔታዎች ሲያስገድዱት ብቻ የሚያነብ፡፡ 

 ሦስተኛው የንባብ ልምድ አለመኖር ሌሎቹን ዓይነት አንባቢዎችም ይጎዳል፡፡ ልብሶቻችን ላይ የተለጠፉትን መመሪያዎች አለማንበብ፣ የገዛነውን መድኃኒት መግለጫ አለማየት፣ የገዛነውን ዕቃ ማኑዋል አለማስተዋል የገንዘብም የጤናም ኪሣራ ያስከትላሉ፡፡ በእኛ ላይ ብቻም ሳይሆን በሌሎች ላይ ችግር ፈጣሪ ያደርገናል፡፡ 

 አንድን ነገር ስንሠራ መጀመሪያ ስለዚያ የተጻፈ ነገር የመፈለግ ልምድ ቢኖር ኖሮ በመጸዳጃ ቤቱ ላይ ‹ይጫኑ› የሚለውን ማንበብ ይቻል ነበር፡፡ ልምዱ ስለሌለ ግን ጽሑፉን የሚያየውም ሰው ደመ ነፍሱ የሚመራውን እንጂ ልቡናው የሚመራውን ለማድረግ ሲከጅል አላይም ነበር፡፡

 ሌላው ችግር ደግሞ ‹መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ› የሚለው አባባል መዘንጋቱ ያስከተለው ይመስላል፡፡ ስለ በሩ አከፋፈት  እዚያው የቆሙትን ወይም ፊት ለፊት የተቀመጡትን ሰዎች መጠየቅ ቀላል ነበር፡፡ ካልሆነም የበረራ አስተናጋጆቹን ጠርቶ ማማከር፡፡ መጠየቅ ነውር፣ ክብረ ነክ፣ አላዋቂነትን መግለጥ ይመስለናል መሰል የተለመደው እንዲሁ በመሰለኝ መሥራት ነው፡፡ አንደኛዋን ወጣት እንዲያውም ከጎኔ የነበረው ሰው ‹‹ብትጠይቂንኮ እንነግርሽ ነበር› ሲላት ‹‹በዚህ የሚከፈት መስሎኝ ነው›› ነበር ያለቺው፣ የነቀለቺውን የሲጋራ መተርኮሻ እያሳየቺው፡፡ እንዲህ ያለው መሰለኝ የሚመራው አስተሳሰብ በር ላይ ተከስቶ በሰላም ታለፈ እንጂ የሚፈነዱ ወይም የሚቃጠሉ ነገሮች ላይ ቢሆን ኖሮ ውጤቱ ይከፋ ነበር፡፡


 ‹አራዳ በፎቶ ኮፒ ይሠለጥናል› የሚል አባባል በፌስ ቡክ አይቻለሁ፡፡ ‹አድርገኸው የማታውቀውን ነገር ከማድረግህ በፊት የሚያውቀው ሰው ሲያደርግ አይተህ ተከተል› የሚል ነው የመዝገበ ቃላት ትርጉሙ፡፡ ወደ አውሮፓ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሻገሩ የሀገራችን ሰዎች የጻፏቸውን የጉዞ ማስተዋሻዎች ብንመለከት የአውሮፓውያንን አመጋገብ የለመዱት በዚህ ዘዴ መሆኑን ይነግሩናል፡፡ ሹካ ሲያነሡ ማንሣት፣ ፓስታ ሲጠቀልሉ መጠቅለል፣ ሲጎርሱ መጉረስ፡፡ 

 ይህንን ጽፌ ስጨርስ አንዲት ወጣት ልጅ መጣች፡፡ ‹ይጫኑ› የሚለው ምልክት ጋ የሚሳብ መክፈቻ ትፈልጋለች፡፡ ገርሞኝ ሳያት ከጎኔ የነበረው ተሳፋሪ ‹እሱ ምን ይላል?› አላት፡፡ ጠጋ ብላ አየቺውና ‹ኦ ሶሪ› ብላ ገፋ አደረገቺው፡፡ መጽሐፈ መነኮሳት ‹ከሰይጣን ይልቅ ልማድን ፍራ› ያለው ይኼን ነው አልኩ በልቤ፡፡ 
 
አሜሪካ ወደ አዲስ አበባ

40 comments:

 1. ‹ሞኝ ሺ ጊዜ ብልጥ አንድ ጊዜ ይሳሳታል›

  ReplyDelete
 2. ዳኒ ፡- መልካም እይታ ነው ቢሆንም ቢሆንም ...
  3 አቢይ ነገሮች እንደ ምክንያት ይታዩኛል፤

  1» በምትወጠርበት ደቂቃ መጸዳጃ ቤቱ በር ላይ በህሊና አጥርቶ ለማሰብ ፊኛ ጊዜ ስለማይሰጥ የደመ-ነፍስህን ያገኘኽውን መነካካትህ አይቀርም

  2» የ 'ሰው ምን ይለኛል' ልምምዳችን በጣም ስለ-ገነነብን አዲስ ነገርን በርብሮ ለማወቅ እንዳንችል ከባድ እክል ሆኖብናል።

  3» የምልክቶቹ እና የበሩ አሰራር የራሱ ችግሮች አሉት ፥ ፈረንጆች እንደሚሉት አይነት 'Idiot Proof' አሰራር የተሰራ አይመስለኝም፤ በፈረንጅ ሃገር ያሉ ፖስታዎች የቴምብር መለጠፊያው ቦታ ላይ የ አራት ማዕዘን ምልክት እና በላዩ ላይ"Please put the Stamp Here" የሚል ጽሁፍ አለበት። ቴምብር በእጄ ይዤ ከአራት ማዕዘኑ ቦታ ሌላ የት ላደርገው እችላለሁ??
  ለሚሉ- መልሱ ወይም ፖስታችን 'ካላዋቂ-ነጻ' ( Idiot proof ) መሆን ስላለበት ይሆናል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Daniel has written this article just to show how our reading habit is going on ?
   and to create awareness about the habit reading. it did not rese complain .

   Delete
 3. እስኩ ድግሙ ድግሙ ነኝ ዳኒ
  እንዲህ ጠብቄህ ነበር ያሰብኩት ተሳካ ነው ያለው ዘፋኙ
  እኔም አንድ ገጠመኝ ልንገርህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈርኩ ቀን መቼም ወዳጅ ዘመዶቼ ድግስ ደግሰው በደንብ በልቼ ጠጥቼ በተለይ አውሮፓ የአበሻ ምግብ ከዚህ በኋላ አይገኝም ብዬ ያልበላሁት ምግብ የለም ማለት ይቻላል ነገር ግን
  አውሮፕላኑ ውስጥ እንደ ገባሁ ሆዴ አንዴ ይጮሃል ይቆርጠኛል እንደ አጋጣሚ ሆኖ አጠገቤ ሰው የለም ሦስቱን መቀመጫ ብቻዬን ነው የያዝኩት ነገሩ አስጨነቀኝ ምን ብየ ልናገር አንድም አውሮፕላን ውስጥ ሽንት ቤት መኖሩን በቀልድም ሆነ በእውኑ የሰማሁት ነገር የለም ነገሩን ተሸክሜው እስከ ጀርመን ደረስኩ ማለትም እኔን አውሮፕላኑ ተሸክሞኝ እሱን እኔ ተሸክሜው ደረስኩ አስከሬን ሆኜ ልክ ዘመዶቼን እንዴት ሰላም እንዳልኳቸው አላውቅም ቶሎ ብየ ሽንት ቤቱን ነው የጠየቅኳቸው ተገላገልኩ ግን በማግስቱ መነሳት የለም መኝታ አቡላንስ ተጠርቶ ወደ ሆስፒታል ገና ስምንት ቀን ሆስፒታል ከረምኩልህ አሁን ሳወራ ቀላል ይመስላል ተወኝ በዘመኑ እንደ እኔ ያለ አራዳ የለምና እንዴት ሽንት ቤት የት ነው ብሎ ለመጠየቅ መጀመሪያውኑ አውሮፕላን ውስጥ ሽንት ቤትን ምን አመጣው ብዬ በኔ ሊቅነት ደምድሜ ነው ያልጠየቅኩትና ዘመዶቼንም ለአለስፈላጊ የሕክምና ወጪ ያዘጋጀኋቸው ጥሩ ብለሃል መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እናመሰግናለን ለገጠመኝህ - አስቂኝም አስተማሪም ነው፡፡ ከአርባ ምንጭ እ.ፈ

   Delete
 4. ከሰይጣን ይልቅ ልማድን ፍራ....

  ReplyDelete
 5. Impressive as always!

  ReplyDelete
 6. ሰላም ዲያቆን ዳኒ, ቶሎ መመለሥህን ባንወደውም በሰላም ግባ እንላለን.በአሁኑ ጉዞህ ለይ በጣም ተሰፈ አድርገን ነበር እግዚሃብሔር አብ ቤተክርሰቲያናችንን ታይልናለን ብለን አሁንም ተሰፈ አንቆርጥም አንድዬ ሲፈቅድ ትጎበኘናለህ.
  ግሩም የሆነ ዕይታ ነዉ ያቀረብክልን. በእውነተም በተለይ በአሁኑ ጊዜ በወጣቱ ላይ የሚታየውን ግዴለሽነትም ነው
  የማንበብ, ,የመጠየቅ እና የማዳመጥ ልምድ በየዕለት ኑሯችን እደጠፈ ሄዶዋል. ማስተዋሉን ይሰጠን !
  ዲያቆን ዲኒ መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 7. እንኳን በሰላም አገርህ ገባህ መምህር ! ጥሩ እይታ ነው፣ ምናልባትም በአለም ውስጥ ካሉ ህዝቦች ማንበብ የማይወድ አበሻ ብቻ ሳይሆን አይቀርም፣
  ከአመታት በፊት ነው ፣ አንድ ወዳጄ የላስ ቬጋስ ሀመረ ኖህ ወቅዱስ ሚካኤል
  ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምር ነበር፣ አንድ ቀን መምህር ሐይለ ማርያም ላቀው የተረጎሙትን የቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን መፅሀፈ ምስጢር እያነበብኩ እያለ ተገናኘን፣ እንዴት አይነት ድንቅ መጽሐፍ እንደሆነ ገልጨለት እንዲያነበው አስተያየት ከሰጠሁት በኋላ የመለሰልኝን አረሳውም፣ ምንም አይነት የማንበብ ፍላጎት እንደሌለው ሲነግረኝ በጣም ነው የገረመኝ፣ የፍልስፍና ፣ የታሪክ፣ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ መፃህፍት ይቅሩ ግዴልም፣ አንድ መንፈሳዊ ነኝ የሚል ሰው እንዴት የዘላለም የሕይወት ምግብ የሆኑ ቅዱሳት መፃህፍትን ለማንበብ ምንም አይነት ፍላጎት አይኖረውም? ይህ ሰው ለምን መድረክ ላይ ወጥቶ እንደሚዘምርም አላማው የገባው አይመስለኝ፣ ወገኖቸ እባካችሁን መፃህፍትን የማንበብ ልምድ እናዳብር፣ አለማንበብ ፣ ማንበብ አለመፈለግ እጅግ የኋላ ቀርነት ምልክት ይመስለኛል።

  ReplyDelete
 8. It is a very good example which can clearly shows personal and group way of thinking and daily repeated life style of ourselves . This is our main enemy which made us to repeat the same old mistakes again and again year after year decade after decade in our history as a nation It is obvious that most of us have not educated properly either traditionally or in the so called modern schools due to different local , national and international problems except following the feet steps of the generations before us like what we are doing now to the generation after us . As a nation we have number of problems , because of our literacy we have no solution even for a single issue let alone to give a comprehensive solutions to many complex ones . Fighting and migration were the only big means we learned from our fathers which might be good or bad during their time . We repeat the same means today instead of asking advise from others who passed similar problem or read their history to learn new way which is better than killing each other or being killed by wild animals and cave men while migrating to the unknown locations of the present world . ብልህ ሰው አንድን ከዚህ በፊት አድርጎት የማያውቀውን ነገር ከማድረጉ በፊት ወይ ያነባል፣ ወይ ያጠይቃል፣ አለበለዚያ ደግሞ ሌሎችን አይቶ ይማራል፡፡
  Dear Daniel thank you for sharing us this experience .

  ReplyDelete
 9. i love it Dani u do hv an eagle eye ! God bless u 10000000000 * !

  ReplyDelete
 10. I understood that U R back in Addis. Welcome Dn.

  ReplyDelete
 11. እሱ ምን ይላል?› አላት፡፡ ጠጋ ብላ አየቺውና ‹ኦ ሶሪ› ብላ ገፋ አደረገቺው፡፡ መጽሐፈ መነኮሳት ‹ከሰይጣን ይልቅ ልማድን ፍራ› ታዲያ ይሄንን ትውልድ ምን ትለዋለህ መጠየቅ ነውር የሆነበት እግዚአብሔር ይርዳው ትውልዱን

  ReplyDelete
 12. ዲ.ን ሁሉንም ነገር በዚህ አለም መነጽርነት እየተመለከትክ ሃይማኖታዊ ለዛህን እያጣህ መጥተሀል፡፡ እግዚአብሔር ወደ መስመርህ ይመልስህ፡፡ በየመሀሉ መንፈሳዊ ለማስመሰል የምትቀላቅላቸውን ጥቅሶች ትተህ በአንድ መስመር ሰዉን ብታስተምር ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ብዙ ተከታዮችና አድናቂዎች አሉህ ስለዚህ የምታስተምረውን ሰው ወዴት እየወሰድከው እንዳለ እራስህን ጠይቅ፡፡ መንፈሳዊ/መንፈሳይ

  ReplyDelete
 13. Dani EGZIABHER yibarkh! esti yihchin bante blog asifirat ,,ke yikrta gar! bizu sew biyanebew tiru silemeselgn new
  “የምክር ቃል”፦ የውጪ አገር ነገር
  http://www.adebabay.com/2011/02/blog-post_14.html

  ReplyDelete
 14. One thing you missed out is the fact that most of our people do not like to wear reading glasses even though they have sight problems. ... We see this at church and every where in the elderly as well as in the young. I agree that there is far less interest in reading these days amongst our people, but you cannot read what you cannot see clearly.

  ReplyDelete
 15. እንኮን በሰላም ተመለስክ። I see that the point is that diaspora is illiterate. wow Dani! great job and excellent excellent observation. But why is this kind of negative seed needed?

  ReplyDelete
 16. Dammam Saudi Arabia .

  ReplyDelete
 17. EXCELLENT VIEW DANI
  MAY GOD BLESS U .
  መጽሐፈ መነኮሳት ‹ከሰይጣን ይልቅ ልማድን ፍራ› ያለው ይኼን ነው አልኩ በልቤ፡፡ kELIBE NEWE YESAKUT EGZIABHERE YESTE

  ReplyDelete
 18. እንኳን ደህና መጣህ ዳኒ!!

  ReplyDelete
 19. A very good observation! But,the title should have better been your quote from the Book of Monks. Whenever I hear the socio-political opinions Ethiopians abroad air on media such as the VOA,I sense that I who live in my country and have never been to a foreign country may be better civilized than they are.Don't misunderstand me here.I am in no way implying that the reality under Ethiopian skies is different from what they say.I differ not in the what but in the how,in the manner of saying it.Who knows?maybe, even my English is also better than theirs.If they are at oods with the technology at their disposal,how'd they be OK in manipulating the language as the situation demands.they are just rich in their ugly mix of Amharic and English,showing their constraint in either tongue if it comes in its unadulterated,pure form.my people their are masters of bastardized language,maybe because they live with mulattoes.Come on!Let's make the most out of opportunities.

  ReplyDelete
 20. ውድ ዳኒ፣
  እንደምን አለህ!
  በአውሮፕላን ቢያንስ ከ20 ጊዜ በላይ በርሬያለሁ፤ ይሁን እንጅ ‹‹የሲጋራ መተርኮሻውን ካወለቁት ሰዎች…›› የሚለው ሀሳብ አልገባኝ አለ፡፡ ለመሆኑ አውሮፕን ውስጥ ማጨስ ይፈቀዳል እንዴ? ወይስ እኔ የበረርኩባቸው አውሮፕላኖች ይህ መተርኮሻ የላቸውም? በረራዬ ቢዝነስ ክላስና ኢኮኖሚ ክላስን ይጨምራል፤ ግን በሁለቱም ዓይነት በረራዎች ‹‹ሲጋራ ማጨስ ክልክል ነው›› የሚል መልዕክት ነው ያዬሁት፡፡ ለማነኛውም እይታህ እጅግ ድንቅ ነውና ቀጥልበት!!
  አብዮት፤ ከአዲስ አበባ

  ReplyDelete
 21. አራተኛው ሰው ተገድዶ ብቻ የሚያነብ ነው፡፡ አንድን መግለጫ፣ ጽሑፍ ወይም ማስታወቂያ ለማንበብ ሁኔታዎች ሲያስገድዱት ብቻ የሚያነብ፡፡

  ReplyDelete
 22. 'እነዚህ ወገኖቻችን የአውሮፕላኑ በር እንዴት እንደሚከፈት ለምን ጠፋቸው?' = አብዛኛው ተገልጋይ በሚረዳው መልክ በሩ እንዴት እንደሚከፈት ባለመገለጹ ይሆን?

  ReplyDelete
 23. yenja neger eko anedande.... dani astemari neger new

  ReplyDelete
 24. I have respect for you. I want to trust you as well. Even if you have the point, I couldn't think of the picture you tried to draw (the magnitude of the problem). Regarding your central issue, I would say " well done" wendime.

  ReplyDelete
 25. እኔ ደግሞ ምን ገጠመኝ መሰላችሁ፡፡ ሁሌም እኔ አራዳ ነኝ የሚል አመለካከት ነበረኝ፡፡ ነገር ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን ስጓዝ ቀበቶ እሰሩ በሚባልበት ሰዓት ልክ በመኪና ሰታይል ሳብ አደረኩና ቀዳዳው ላይ አስገባሁት፡፡ ከዛ ጉዞ አለቀና ውረዱ ሲባል እንዴት ልፍታው አቃተኝ መጠየቅ ሞት መስሎ ታየኝ ለመፍታት ስታገል ከኋላዬ የነበሩት ሁሉ ወረዱ እኔ ቀረሁ እንደታሰርኩ መጨረሻ የሞት ሞቴን ፋራ የሚመስል ሰው ሊያልፈኝ ሲል በእጄ ነካ አደረኩና አልፈታ አለኝ ስለው በሰከንድ ላጥ አድርጎ ፈታልኝና ዞር ብሎ መንገዱን ቀጠለ፡፡ እኔም ተመስገን አምላኬ ብዬ እንደሰው ወረድኩኝ፡፡ አራድነት በአፍንጫዬ ይውጣ፡፡ እልም ያልኩኝ ፋራ ነኝ መጠየቅን እንደውርደት የተመለከትኩኝ፡፡

  ReplyDelete
 26. Good observation. I have also similar experiences: Here are some of them-
  1-When we go for shopping to grocery or other stores, we don't read the list of items at each aisle. Rather we look in each shelve or aisle for the item we are looking for. We do the same next time we go to the same or other stores. We need to raise our head & look to the ceiling to read and "pray" what is in each aisle. "Atirut Angat" in Amharic. We need to make it our habit !!!

  2-Most Ethiopians don't read manuals! If we don't read and understand ,we do not utilize fully & effectively the material we bought, especially when we are new to the material, we need to read it thoroughly again and again at different occasions. This is very common when we buy new cars, electronics, house gadgets...We need to have patience to read the manuals before using them!!!

  3-When we get offers and discounts-We are afraid to try & get advantage of offers and benefits because we don't give attention to it or we do not understand it. Let us ask if we do not know. Native Americans are not afraid to ask foreigners even some simple things. Why would we? We are new to the system & have enough excuse even not to be intimidated. We should not be afraid to ask !!!

  4-There are much more similar examples : like about bus stops, related to boarding a train,driving directions, asking instructors in the class or during training, asking trainer, or co-worker, supervisor.....

  If I take my time and compile most of my observations and experiences, it can be book.
  Any way,Daniel, thanks for reminding me. God bless you, Ethiopia and America. It seems God visits every where, but lives in Ethiopia. TD

  ReplyDelete
 27. Deacon Dani, Ende ante yale mekarina ena astemari(memhir) Lehager,Lewegen Betam Asfelagi silehone, Egziabher Rejim Edme Ketena gar Yistih.

  ReplyDelete
 28. Ende ante Yale Mekarina Astemar (Memhir) Lehager, Lewegen Betam Asfelagi silehone, Egziabher Rejim Edme Ketena Gar Yistih

  ReplyDelete
 29. danit it is a good views thankes

  ReplyDelete
 30. በመመሪያ የመሥራት ልማድ አለመኖር ይመስለኛል፡

  ReplyDelete
 31. ዲያቆን ዲኒ መድሃሂያለም ይጠብቅህ አሜን!!!
  ከሰይጣን ይልቅ ልማድን ፍራ...

  ReplyDelete