click here for pdf
ልጁ ሁልጊዜ እየመጣች ታማርራለች፡፡
ኑሮ አልተሳካልኝም፣ አልሞላልኝም፣ ባሌ ያስቸግረኛል፣ ሥራ ቦታ ሰላም የለኝም፣ ጎረቤቶቼ ረበሹኝ፣ ሕመሙ በረታብኝ፣ ገንዘቤ አልበረክት
አለ፤ ጓደኞቼ ያሙኛል፣ ልጆቼ ይበጠብጡኛል፡፡ ስለ ሸረኛ፣ ስለ መጋኛ፣
ስለ ምቀኛ፣ ስለ መተተኛ የማትለው ነገር የላትም፡፡ አባቷ የተለያዩ ታሪኮችን እየጠቀሰ ሊመክራት፣ ሊያጽናናትና ሊያበረታት ሞከረ፡፡
እርሷ ግን ማማረሯን፣ መማረሯንም አላቆመቺም፡፡ እንዲያውም ምሬቷ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ፤ ኑሮዋንም እየጠላቺው፣ ፈተናዋንም እየፈራቺው
መጣቺ፡፡
አንድ ቀን መኖር አስጠልቷት፣ ችግሩና
መከራም በርትቶባት፣ ምሬቷም ጫፍ ደርሶ መጣቺ፡፡ ‹‹በቃ ከዚህ በኋላ መኖር አልፈልግም፤ ይህንን ያህልስ እኔ ለምን እፈተናለሁ፤
ለምንስ ችግር ይበረታብኛል፤ ለምንስ ሁሉም ነገሮች ይጠሙብኛል፤ በቃ እኔ መኖር የለብኝም›› እያለች ታለቅስ ነበር፡፡
አባቷ ምክሩ ሁሉ እንዳልሠራ፣ የነገራትንም
ሁሉ እንደዘነጋቺው ተረዳ፡፡
‹‹ተከተይኝ›› አላትና ወደ ማዕድ
ቤት ገቡ፡፡