በግፈኛው አይሲስ ከተሠዉት ወንድሞች መካከል ብርሃኑ ጌታነህ የተባለው በአዲስ አበባ አቧሬ
አካባቢ ይኖር የነበረው ወንድም ይገኝበታል፡፡ ብርሃኑ ከሀገሩ የወጣው ከአራት ወራት በፊት ሲሆን ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት
ነበረ፡፡ ቤተሰቦቹ እንደሚናገሩት ወደ ሱዳን ሲሄድ ለባለቤቱ የ3 ወር የቤት ኪራይ ከፍሎ ነበር የሄደው፡፡ ሁለቱ ልጆቹ የስምንትና
የአራት ዓመት እድሜ ያላቸው ሲሆኑ ቤተሰቡ በችግር ላይ እንደሚገኝ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው መሐመድ ካሣ ማክሰኞ ምሸት ወደ
አሜሪካ ልበር ስል ነግሮኝ ነበር፡፡ እስካሁን መርዶ የተረዱት የሰማዕታቱ ቤተሰቦች ወላጆች፣ እኅቶች ወይም ወንድሞች ሲሆኑ ብርሃኑ
ግን ባለቤቱና ገና ክፉና ደግ ያልለዩት ሁለቱ ልጆቹ ናቸው የተረዱት፡፡
![]() |
ፎቶ፡- ያሬድ ሹመቴ
|
ከሰማዕታቱ ቤተሰቦች መካከል ይበልጥ ትኩረት የሚፈልጉት እነዚህ ምንም የማያውቁ ሕጻናትና
እናታቸው ናቸው፡፡ መማር፣ ተምሮም ማደግ አለባቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ መኖሪያ ቤትና የትምህርት ቤት ክፍያ ይፈልጋሉ፡፡ እናታቸውንም
በሥራ ማሠማራት ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም የክፉዎቹ ሥራ ውጤት እንዳይኖረው እነዚህን ሁለት ሕጻናትና እናታቸው እንርዳ፡፡ ቤታቸው አቧሬ
አድዋ ድልድይ አካባቢ ነው፡፡
ጉዳዩን በሚገባ ለመረዳትና ርዳታውን ለማስተባበር መሐመድ ካሣን ብታነጋግሩት ያግዛችኋል፡፡
ስልኩ 0911602795 ነው፡፡
ዳላስ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ዋሽንግተን ዲሲ
በሚገባ እንረዳለን ! ይህንን ማድረግ የሁላችንም
ReplyDeleteሀላፊነት ነው.እግዚሃብሔር ይመሰገን! ኢትዬጵያውያን በዚህሰ ጥሩ ሰም አለን. የእነሱ አባት ለኛ ብርሃን ,መሰቀል, ሆኖ አልፎ አይደል እነዴ የሄደው. እኛም የእነሱን ቤተሰቦች አጎንብሰው እንዳይቀሩ መጣር አለብን!ዲያቆን ዳኒ እንኳን ደህና መጣህ.መድሃሂያለም ቢፈቅድ መንፈሰቅዱሰ ያቀበለህን ታሰተምረናለህ ብዬ ተሰፈ አደርጋለሁ! እመብርሐን ትጠብቅህ አሜን!!!!
አካውንት ተከፍቶላቸው ከያለንበት ብናስገባና ስልክ ካላቸው ደውለን ብናሳውቃቸው በጣም ቀላል ይመስለኛል እንደኔ
ReplyDeleteኀይለገብርኤል ነኝ
ወገን ለወገን እንረዳዳ እና በረከቱን እንፈስ
ስለ አሳወከን እግዚአብሔር ይስጥህ ። እባክህ እዚህ ዲሲ ከሆንክ የት ትምህርት እንደምትሰጥ ንገረኝ ከነቀኑ።
ReplyDeleteewnt blhal leg ezh kmetah ebakhen kalhebet bota lalewet orthodox twhedow legawech abrrth negerachow smataten masb btlyme ysmat legwech ymydgubeten wlegwech ymetrebeten mengadwe tkklgaw gleslachow ezam bakemachen endenreda egezabher ytabkh lega amen!!
ReplyDeleteDany well come !!! i hope you came teach us please inform the date place and time
ReplyDeleteThanks
Great idea
ReplyDeleteWendime endalew acc number binagegn tiru new
ReplyDelete